Wolaita Herald

  • Home
  • Wolaita Herald

Wolaita Herald Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Wolaita Herald, Media/News Company, .

20/03/2023
20/03/2023

👉 አራተኛው ፈተና ፦ የኑሮ ውድነት

በዓለም አቀፍና በሀገር ውስጥ ባጋጠሙ ችግሮች የተነሣ በተፈጠረው የማክሮ ኢኮኖሚ መዛባት የኑሮ ውድነቱ እየጨመረ መምጣቱን ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ገምግሟል፡፡ ከኑሮ ውድነቱ ጋርም የሥራ አጥ መጠኑ ጨምሯል፡፡ ችግሩን በጊዜያዊነትና በዘላቂነት ለመፍታት ርምጃዎች እየተወሰዱ መሆኑንም ተመልክቷል፡፡ ፈተናውን በብቃት ለመሻገር መንግሥት መራር ውሳኔ ሊወስንባቸው የሚገቡ ጉዳዮች መኖራቸውንም አረጋግጧል፡፡

ችግሩ በዘላቂነት እስከሚፈታ ድረስ መንግሥት የኑሮ ውድነቱን የሚያቃልሉ ጊዜያዊ ርምጃዎችን መውሰድ አለበት፡፡ በተለይም በችግሩ ላይ ቤንዚን የሚጨምሩ አካሄዶችን ማረም የሚገባ ነው፡፡ ምርትን በተገቢ መጠን ለማምረትና ወደ ገበያ ለማድረስ የሚታዩ የአመራርና የአሠራር ችግሮች መፈታት አለባቸው፡፡ በየአካባቢው የሚዘረጉ ኬላዎች ከሕግ አግባብ ውጭ የሚያካሂዱት እገዳና ዘረፋ በአመራር ቁርጠኝነትና ሕግን በማስከበር ሊፈታ ይገባዋል፡፡

የሕዝቡን ችግር በማባባስ ኪሳቸውን መሙላት በሚፈልጉ ስግብግቦች ላይ አስተማሪ ርምጃ መወሰድ አለበት፡፡ በአምራቾችና በሸማቾች መካከል ያለው ሠንሠለት እንዲራዘም በሚያደርጉ ደላሎችና ስግብግብ ነጋዴዎች ላይ የሕግ የበላይነት ሊከበር ይገባዋል፡፡ ኢንቨስትመንትን፣ ንግድንና የሥራ ፈጠራን የሚያቀላጥፍ አሠራር መዘርጋት አለብን፡፡ ንግድና ኢንቨስትመንት እንዲደናቀፍ በሚያደርጉ አመለካከቶች፣ ኃላፊዎችና ሠራተኞች ላይ ተገቢውን የእርምት ሥራ መሥራት ይገባናል፡፡ ለዚህም መላው የፓርቲያችን አመራርና አባላት፣ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የንግዱ ማኅበረሰብ፣ የፍትሕና የጸጥታ አካላት የሚጠበቅባቸውን በቁርጠኝነት እንዲወጡ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ጥሪ ያቀርባል፡፡ የሥራ አጥነትን ለመቀነስ የተጀመሩ ተነሣሽነቶች በተፋጠነና ትርጉም በሚያመጣ መንገድ እንዲከናወኑ፤ በሥራ ዕድል ፈጠራ ለተሠማሩ አካላትም አስፈላጊው ሁሉ ድጋፍ እንዲደረግላቸው፣ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው አቅጣጫ ሰጥቷል፡፡

20/03/2023

ሶስቱ የሰላማችን ማረጋገጫ መንገዶች ፦

ፍቅር ፦
ከጥል ይልቅ ሰላምን የሚሻ ለመዋደድ እና ለአብሮነት ታላቅ ዋጋ የሚሰጥ በፍቅር የተገነባ ማህበረሰብ መፍጠር ስንችል ሰላምን በሙሉ ቁመና በህብረተሰባችን ዘንድ ማስረፅ እንችላለን።

ይቅርታ ፦
ትላንት ከተጓዝንባቸው መንገዶች በላይ ነገ የምንጓዝባቸው ብዙ ናቸው፤ በትላንቱ ጉዟችን የገጠሙን መሰናክሎች ለነገው እንቅፋት እንዳይሆኑ ከክፉ ታሪኮቻችን ትምህርት ቀስመን በይቅርታ የበለፀገ ማህበረሰብ መገንባት ይኖርብናል።

እርቅ ፦
የይቅርታችን መቋጫ እርቅን ማረጋገጥ ነው፤ ነባር የሆኑ ቂም እና የጥላቻ ትርክቶች በህብረተሰባችን ዘንድ ጥቁር አሻራ ጥለው እንዳያልፉ እና ለሰላማችን መታወክ መንስኤ እንዳይሆኑ በይቅርታ የተዘጉ መዝገቦች ሁሉ በእርቅ ሊቋጩ ይገባል።

መልካም ሳምንት ይሁንልዎ !!

ምርጫ ቦርድ የወላይታ ህዝብን ድምጽ ባላከበረ ሁኔታ የወሰነውን ውሳኔን ተከትሎ በከፍተኛ ፍርድቤት ቢከሰስ ህዝቡ እንደሚያሸንፍ ተገለጸየወላይታ ህዝብ ምርጫ ቦርድ የመራጮች ምዝገባ፣ የድምጽ አ...
07/03/2023

ምርጫ ቦርድ የወላይታ ህዝብን ድምጽ ባላከበረ ሁኔታ የወሰነውን ውሳኔን ተከትሎ በከፍተኛ ፍርድቤት ቢከሰስ ህዝቡ እንደሚያሸንፍ ተገለጸ

የወላይታ ህዝብ ምርጫ ቦርድ የመራጮች ምዝገባ፣ የድምጽ አሰጣጥና ውጤት በተመለከተ የወሰነው ውሳኔን ተከትሎ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድቤት ሰበር ችሎት ቢከሰስ እንደሚያሸንፍ የህግ ምሁራኖች ገለጹ።

ህዝበ ውሳኔው ጋር ተያይዞ ምርጫ ቦርድ የወጣው መግለጫ መራጩን መላው የወላይታ ህዝብንና የዞኑን መንግስትን እንደማይወክልና እንደማይመለከትም ጭምር አስታውቋል። ምክንያቱም የመራጮች ምዝገባና የድምጽ አሰጣጥና ውጤት በተመለከተ ተዘርዝረው የተቀመጡ ነጥቦች በአጠቃላይ የምርጫ አስፈጻሚዎች ጉድለትና ጥሰት መሆኑ ያሳያልም ብሏል።

ከእነዚህም መካከል ለአብነቱ #የውጤት መግለጫ ቅጾችና የመራጮች መዝገብ ላይ ምርጫ አስፈጻሚዎች ፊርማቸውን በሠነዶቹ ላይ አለማሥፈራቸው" የሚለውን ብቻ ካየን በቂ ነው።

ይህ የወላይታ ህዝብን ለማሸማቀቅ የተቀናጀና የተቀነባበረ ሴራ መሆኑን ገልጿል። ለዚህም መላው የወላይታ ህዝብ ተስፋ ሳይቆርጥ የአይበገሬነት ወኔን በመላበስ ዳግሚ የሚካሄደው ምርጫ ታርክ መስራት ያስፈልጋል።

በቁጫ ህዝብ በ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ፥ ምርጫ ቦርድ ሆን ብሎ የምርጫ ውጤት እንዲሰረዝና እንዲካሄድ ህገወጥ ውሳኔን ተከትሎ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድቤት ሰበር ችሎት ተከስሶ የቁጫ ህዝብ ሰሞኑ ማሸነፉን በመጠቀስ ይህም የምርጫ ቦርዱ ገለልተኝነት አደጋ ላይ መውደቁን ተናግረዋል።

የወላይታ ህዝብ ከወንድም ህዝቦች ጋር በአንድ ክልል ለመደራጀት የወሰነውን ውሳኔን ለመቀልበስና የፖለቲካ ትርፍ ለመግኘት እየሰሩ ያሉ አጭበርባሪዎች መኖራቸውን ጠቅሷል።

አንድ ሚሊዮን ገደማ የሚጠጋ ህዝቡ ከለሊቱ 9:00 ጀምሮ ተሰልፎ እንዲሁም ብርድና ፀሐይ ሳይበግረው የሰጠው ድምጽ ምርጫ ቦርድ የወሰነው ውሳኔ እጅግ የሚቃረን ነው ብሏል።

የህዝበ ውሳኔ ድምጽ አሰጣጥ ጋር ተያይዞ አንዳንድ ጥቃቅን ችግሮች ከዚህ በፍትም፣ ወደፊትም የሚካሄዱ ምርጫዎች የህግ ጥስት ሊኖሩ እንደሚችል አንስቷል።

በአጠቃላይ አንድ ምርጫ ልሰራዝ የሚቻለው ሠላማዊ፣ ነጻ፣ ገለልተኛ እና ፍታሃዊ ሆኖ ሳይጠናቀቅ ስቀር እንደሆነም ጠቁመዋል።

በመጨረሻም አንዳንድ ጽንፈኞችና የፀረ-ሠላም ኃይሎች አጀንዳ ለማስፈጸምና የወላይታን ገጽታ ለማበላሸት በማህበራዊ ሚዲያ ሀሰተኛና የተዛቡ መረጃዎችን የሚሰራጩ አካላት ላይ መንግስት የማይዳገም እርምጃ መወሰድ እንዳለበት ጠይቀዋል።

28/01/2023

በወላይታ ዞን ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ ባለሀብቶች ወደ ሥራ ገብተዋል

ወላይታ ሶዶ፤ ጥር 19/2015 በተያዘው በጀት ዓመት ስድስት ወራት ውስጥ ከ1 ቢሊዮን 349 ሚሊዮን በላይ ብር ካፒታል ያስመዘገቡ ባለሀብቶች ወደ ሥራ መግባታቸውን የወላይታ ዞን አስተዳደር አስታወቀ፡፡

የወላይታ ዞን አስተዳዳሪ አቶ አክሊሉ ለማ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለፁት፤ በተያዘው ዓመት ስድስት ወራት በኢንዱስትሪው ዘርፍ 49 ኢንቨስትመንቶችን ወደ ሥራ ለማስገባት ታቅዶ 34 ኢንቨስትመንቶችን መሳብ ተችሏል።

በዚህም በዞኑ አንድ ቢሊዮን 349 ሚሊዮን በላይ ብር ያስመዘገቡ ኢንቨስተሮች ወደ ሥራ ገብተዋል፡፡

አቶ አክሊሉ እንደገለፁት፣ በመጀመሪያው ግማሽ ዓመት ሁለት ቢሊዮን የሚጠጋ ካፒታል ያላቸውን ባለሀብቶች ወደ ዞኑ ለመሳብ ሲሠራ የቆየ ሲሆን፤ ከ1 ቢሊዮን 349 ሚሊዮን ብር በላይ ኮፒታል ያስመዘገቡ ኢንቨስተሮች ወደ ሥራ መግባት ችለዋል።

ወደ ሥራ ገብተዋል ከተባሉት 34 ኢንቨስትመንቶች 18 ያህሉ በግብርና ዘርፍ የተሰማሩ መሆናቸውን ያብራሩት አቶ አክሊሉ፤ ሌሎች 11 የአገልግሎት እና 5 የሚሆኑ ደግሞ በማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ዘርፎች ወደ ሥራ ገብተዋል ሲሉ አስረድተዋል።

በገጠሩ አካባቢ 500 ሄክታር መሬት ለኢንቨስተሮች ለማቅረብ ታቅዶ ከአንድ ሺህ 500 በላይ ሄክታር መሬት ማቅረብ መቻሉንና በከተማው አካባቢ በካሬ የነበረውን ወደ ሄክታር በመቀየር አምስት ሄክታር መሬት ለማቅረብ ዕቅድ ተይዞ ከስምንት ሄክታር በላይ መሬት ለኢንቨስተሮች አቅርቦት መዋሉንም አክለው አብራርተዋል፡፡

የኢንቨስትመንት ሌላኛው ዓላማ የሥራ ዕድል መፍጠር ነው ያሉት አቶ አክሊሉ፤ ለ10 ሺህ 51 ወጣቶች የሥራ ዕድል ለመፍጠር የታቀደ ሲሆን፤ ከስድስት ሺህ በላይ የሚሆኑ ወጣቶች የሥራ ዕድል አግኝተዋል ሲሉ አስረድተዋል።

መሬት ከተሰጣቸው በኋላ የተለያዩ ምክንያቶችን በማንሳት በሚፈለገው ፍጥነት ወደ ሥራ የማይገቡ ኢንቨስተሮች እንዳሉ በመግለጽም፤ ወደ ሥራ ገብተው ማልማት ከጀመሩ በኋላ የሚያቋርጡ መኖራቸውን ጠቅሰዋል።

ይህን ድርጊት በሚፈጽሙ ባለሀብቶች ላይ የማስጠንቀቂያና የተቀበሉትን መሬት በመንጠቅ በተገቢ ሁኔታ ለሚያለሙ ባለሀብቶች እየተሰጠ መሆኑን አስረድተዋል ሲል ኢፕድ ዘግቧል።

28/01/2023

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ህዝበ ዉሳኔ ልዩ ምልክት ነጭ እርግብ ነዉ።

11/11/2021

በወላይታ ዞን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በተጠናከረ ሁኔታ ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑ ተገለጸ፡፡

ወላይታ ሶዶ፤ ህዳር 02/2014 የወላይታ ዞን ፖሊስ መምሪያ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን በተመለከተ የጸጥታ መዋቅሩ ከሕዝቡ ጋር ተቀናጅቶ እየሠራ መሆኑን ገልጿል፡፡

የወላይታ ዞን ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ኢንስፔክተር ጎኣ ኩሳ እንደተናገሩት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በተመለከተ በሁሉም የዞኑ መዋቅሮች የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ ተሠርቷል፡፡

ፈቃድ ያላቸው መሣሪያ የታጠቁ ግለሰቦችን በሚመለከት የያዙትን መሣሪያ አስመዝግበው መጠቀም እንደሚችሉ ገልጸው ይወረሳል የሚል ስጋት ሊኖርባቸው እንደማይገባ ተናግረዋል፡፡

አዛዡ አክለውም ፈቃድ ያለውን የጦር መሣሪያ የያዙ ግለሰቦች ከዚህ በፊት በሀገራችን ብሎም በክልላችን ከተገለጸው ጊዜ ገደብ ላይ ቅዳሜና እሁድን ሳይጨምር አንድ ሳምንት ተጨማሪ ጊዜ መሰጠቱን ጠቁመው በተገለጸው ጊዜ ገደብ ውስጥ ሁሉም የጦር መሣሪያ የያዘ አካል በማስመዝገብ ህጋዊ እንዲሆን አሳስበዋል፡፡

በሌላ በኩል የግልም ሆነ የመንግስት ባለሁለት እግር ሞቴር ተሸከርካሪዎችን በአቅራቢያቸው በሚገኘው ፖሊስ ጣቢያ በሁለት ቀናት ዉስጥ ማስመዝገብ እንዳለባቸው አሳስበው ማንኛውም አካል ከተፈቀደለት ጊዜ ዉጪ ሳያስመዘግብ ሲያሽከረክር ቢገኝ በአዋጁ በተቀመጠው መሠረት እርምጃ የሚወሰድ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

አዛዡ ለዞኑ ኅብረተሰብ ባስተላለፉት መልዕክት እያንዳንዱ ግለሰብ ከሰፈሩ ጀምሮ አካባቢውን እንዲጠብቅ፣ ከጸጥታ አካላት ጋር እንዲተባበር እንዲሁም ፀጉረ-ልዉጦች ሲገኙ ለሚመለከተው የጸጥታ አካል ጥቆማ በማድረግ ለጸጥታ ዘብ እንዲቆም ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

18/10/2021

Address


Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Wolaita Herald posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share