Food science and Technology

Food science and Technology Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Food science and Technology, Digital creator, Wolaita, Sodo.

11/08/2022
15/06/2022

👍The 7 principles of HACCP
HACCP is a logical process that needs to be followed step by step in order for it to work properly. The HACCP system is made up of seven principles as described by Codex; they can be summarised as:
1. Hazard analysis
2. Determine Critical Control Points (CCPs)
3. Establish critical limits at CCPs
4. Monitor critical limits
5. Establish corrective actions when control
at CCPs is lost

27/10/2021
18/08/2021
08/08/2021

ጠቃሚ ጤና መረጃ

7 ሰባቱ የቅመም ዓይነቶች ለጨጓራ መፍትሔ ሲውሉ!!!

የጨጓራ ባክቴሪያ ወይም ሄሊኮባክተር ፓይሎሪ

የጨጓራ ባክቴርያ የባክቴሪያ አባል ሲሆን ወደ ሰውነታችን በመግባት በምግብ ጉዞ መንገድና ጨጓራ ውስጥ መኖር የሚችል ነው፡፡

የጨጓራ ባክቴርያ የሚከተሉት ምልክቶች ሊታዩ ይችላሉ፡-
📌 የሆድ መነፋት፣
📌ግሳት፣
📌የረሃብ ስሜት አለመሰማት፣
📌ማቅለሽለሽ፣
📌ማስመለስ፣
📌ያለምክንያት ክብደት መቀነስ ሊታዩ ይችላሉ፡፡

✔️በጨጓራ ውስጥ የሚያጋጥም ቁስለት ደም ወደ ከርሳችንና አንጀታችን እንዲፈስ ሊያደርግ ይችላል፤ ከባድ የሚባል የጤና ችግርም ሊፈጥርብን ይችላል፡፡ በመሆኑም የሚከተሉት ምልክቶች ከታዩን ወደ ሕክምና በመሆድ የምንገኝበትን ሁኔታ መመርመር አለብን፡፡
📌የሰገራ መጥቆርና ደም መቀላቀል ካለ፣
📌ለመተንፈስ መቸገር ካጋጠመን፣
📌ያለስራ የመልፈስፈስና የድካም ስሜት ከተጫነን፣
📌የቆዳ መገርጣትና ራስን የመሳት ሁኔታ ከታየብን፣
📌የተፈጨ ቡና የመሰለ ነገር የሚያስመልሰን ከሆነ፣
📌 ከባድ የሆድ ህመም ካለን የጨጓራ ባክቴሪያ ሊሆን ስለሚችል መታየት አለብን፡፡

✔️አልፎ አልፎ ደግሞ የጨጓራ ባክቴሪያ የጨጓራ ካንሰር ሊያስከትል ይችላል፤ እንዲያ ሲሆን በመጀመሪያ አንዳንድ ምልክቶች ሊያሳይ ይችላል፤ ለምሳሌ ማቃር ሊበዛን ይችላል፡፡ በመቀጠል ግን የሆድ ሕመምና ማበጥ፣ ማቅለሽለሽ፣ ያለመራብ ስሜት፣ ትንሽ ከተመገብን በኋላ በጣም የጠገብን የሚመስለን ስሜት መሰማት፣ ማስመለስና ምክንያቱ ያልታወቀ የክብደት መቀነስ ሊታይብን ይችላል፡፡

ምክር
የጨጓራ ባክቴሪያን ለመከላከል የምንወስደው እርምጃ ሌሎች ጀርሞችን ለመከላከል ከምንወስደው የጥንቃቄ እርምጃ ጋር ተመሳሳይ ነው፤ ይኸውም እጅን በሳሙና ከምግብ በፊትና ከመፀዳጃ ቤት መልስ በደንብ መታጠብ፣ በፅዱ ሁኔታ ያልተዘጋጀ ወይም የቀረበ ምግብና መጠጥ አለመጠቀም፣ ያልበሰሉ ምግቦችን አለመጠቀም ናቸው፡፡ እንዲሁም ጭንቀትና ውጥረት፣
ቅመም የበዛባቸው ምግቦችና
ሲጋራ ማጨስ ለጨጓራ ቁስለት የማይዳርጉን ቢሆንም ሁኔታውን ግን ሊያባብሱ ስለሚችሉ ቢያንስ ከቁስለት እስከምንድን ድረስ መጠቀም ወይም ማድረግ የለብንም፡፡

❓ልብ በሉ ቅመም የጨጓራ ህመም እንደሚያባብስ ሁላ ቅመማቅመም የጨጓራ መዳኛ ሲሆኑም እናያለን።

✅የጨጓራ ባክቴርያ፣አሲድ የመርጨት ችግር፣መፍትሔዎቻቸው✅

🌿የጥቁር አዝሙድ ፍሬ
🌿የኮረሪማ ፍሬ
🌿የጤና አዳም ፍሬ
🌿የሰሊጥ ፍሬ
🌿የእንስላል ፍሬ
🌿የፌጦ ፍሬ
🌿የቁንዶ በርበሬ ፍሬ

✅እነዚህ የቅመም ዝርያዎች ከምግብነት ማጣፈጫ አልፈው ለየቅልም ቢሆኑ እጅግ ፍቱን እና ውስብስብ ያሉ ችግሮችን የመፍታት ዓቅም ያላቸው አሁን ደግሞ በሕብረት ሁነው የጨጓራ በሽታን ለማከም በሰፊው የጥበብ ድህረገጻችን በኔ ጋባዥነት ብቅ ብለዋል።

✅የቅመሞቹ አዘገጃጀት እና አጠቃቀም!
በቅድምያ በንጽሕና ለየብቻ እንዲደርቁ ማድረግ የደረቀ ከገዛንም ለየብቻ በንጽህና መፍጨት።

✅ከዛ በመቀጠል ንፁህ ሩብ ኪሎ ማር ማዘጋጀት ለስኳር ታማሚዋችም ይሆናል።የስኳሩ መጠኑ ቅመሞቹ ስለሚያቀዘቅዙት አትስጉ!

ከላይ ያስቀመጥናቸው የቅመም ዓይነቶች ግማሽ ግማሽ የስኳር ማንኪያ ከ ሰባቱም ቅመማቶች በመለካት ወደ ተዘጋጀው ሩብ ኪሎ ማር ማቀላቀል።

በመቀጠል አንድ ላይ በንጽህና በደንብ አድርገው ማዋሃድ!
ይህ የቅመሞች ውህድ ጧት ጧት አንድ አንድ የስኳር ማንኪያ በመለካት በባዶ ሆድ መብላት።

መድኃኒቱ ከወሰዱ ከ አንድ ሰዓት በኃላ የሚስማማዎት ምግብ መመገብ ይችላሉ።

ይህ መፍትሔ ልዩ ከመሆኑ የተነሳ በጨጓራ ምክንያት ለዓስርት ዓመታት የሚያቃጥሉ ነገር፤ስጋ፣ዶሮ ወጥ፤ስንዴ ነክ፣ መብላት የማይችሉትን ማከም የቻለ ልዩ ውህድ ነው።

ፍቱን ነው።
📌መፍትሔውን ተጠቅመው ምስክር ይሁኑ፡፡

ውድ የዚህ ድህረገጽ ቤተሰቦች ስለ ሰባቱ ቅመማት ሌላ እና ልዩ ምስጢራቸው በሌላ ጊዜ የማጋራችሁ ይሆናል።
ለበለጠ ጤና መረጃ የፌስቡክ ሊንካችንን ተጭነው ቤተሰብ ይሁኑhttps://www.facebook.com/Drbeza/

07/08/2021

ምግባችን ያክመን

“ታሞ ከመማቀቅ አስቀድሞ መጠንቀቅ” ይላሉ አስተዋዮች ሲተርቱ፡፡ እውነት ነው ! ለመድሀኒትና ለህክምና የምናወጣው ገንዘብና ግዜ የህይወታችንን ሰፊ ድረሻ ይዛል፡፡ ምግባችንን እንደመድሀኒት ካልወሰድን መድሀኒትን እንደ ምግብ የምንወስድበት ግዜ ይመጣል የሀሎ ዶክተር ፌስቡክ ገጽ፡፡ ይህንን ለማስተካከል ደግሞ ግዜው አሁን ነው ፡፡ ከምግቦች የምናገኘውን ጥቅም ለማወቅ ይረዳችኁ ዘንድ ይህን ከየሀሎ ዶክተር ፌስቡክ ገጽ የተገኘ ጽሁፍ እንሆ ብለናል፡፡

1. ፓፓያ

1) የሞቱ የቆዳ ሴሎችን ለማስወገድ ይረዳል፡፡
2) የቆዳ ድርቀትን ይከላከላል፡፡
3) ፓፓያን በቀጥታ ቆዳዎን በመቀባት ወይም በመመገብ የሚያምር ለስላሳ ቆዳን መጎናፀፍ ይቻላሉ፡፡
4) የተፈጨ ፓፓያ የተሰነጣጠቀ ተረከዝን ለማከም ይጠቅማል፡፡
5) ተፈጥሮአዊ የሞቱ ሴሎችን ከቆዳ ላይ ማስወገጃ መንገድ ነው፡፡
6) የቆዳን ተፈጥሮአዊ ቀለም ለመመለስ ይረዳል፡፡
7) ለሆድ ትላትል ህክምናነት ይጠቅማል፡፡

ጥቁር ነጠብጣቦችን ለማስወገድ በቆዳ ላይ የሚታዩ የእርጅና ምልክቶችን ለመቀነስና ለማከም ይረዳል፡፡
9) ራሰ በራነትን ይከላከላል፣ የፀጉር እድገትንና ጥንካሬን ይጨምራል፡፡

2. ሎሚ

1. ጸረ¬ባክቴሪያ ባህሪ አለው፡፡
2. በቫይታሚን ሲ የበለጸገ ነው፡፡
3. የሎሚ ጭማቂ በውሃ ቀላቅሎ መጠጣት ሰውነታችን የአሲድ አልካላይን ሚዛኑን ለመጠበቅ ይረዳዋል፡፡
4. የጉበትን ስራ በማነቃቃት ዩሪክ አሲድና ሌሎችንም ጎጂ ንጥረነገሮች ከሰውነታችን ውስጥ ለማስወገድና የሀሞት ፈሳሽንም የፈሳሽነት ባህሪውን እንዳያጣ ያደርጋል፡፡
5. የሎሚ ጭማቂ በቫይታሚን ፒ የበለጸገ እንደመሆኑ ከህዋሳት መጎዳትና በእድሜ መጨመር ሳቢያ የሚከሰቱትን ʻፍሪ ራዲካሎችʼን ለማስወገድ ይረዳል፡፡
6. የሎሚ ጭማቂ ጸረ¬ካንሰር ባህሪያት አሉት፡፡
7. ከእድሜ መጨመር ጋር ተያይዞ የሚመጣውን የመገጣጠሚያ አካላት በሽታን ይከላከላል፡፡
8. በሎሚ ውስጥ ያለው ፔክቲን ፋይበር የመጥፎውን ኮልስትሮል መጠን ከመቀነሱም በላይ የመጥገብ ስሜትን ስለሚፈጥር በብዛት ከመመገብ ያግዳል፡

3. ሃባብ

1) ለሰውነት እጅግ አስፈላጊ የሆኑ ቪታሚኖችን፣ ማዕድንና ሳይበዛ ለሰውነት በሚያስፈልግ መጠን ካሎሪንም የያዘ ተወዳጅ ፍራፍሬ ነው።
2) ውፍረት ለመቀነስ ይረዳል፡፡
3) ከስኳር በሽታ
4) ከልብ ህመም ችግር
5) ለሰውነት ተጨማሪ ሃይል መስጠት
6) ለጤናማ የጸጉር እድገት
7) ለጤናማ የምግብ መፈጨት ስርአት እና የሰውነት ድርቀትን ለመከላከል ይረዳል፡፡

4. ሃባብን መመገብ

ሃባብን መመገብ ደም ግፊትን መከላከል፣ሌላው ጠቀሜታው ከጉልበት በታች የሚከሰትን ከፍተኛ የሆነ የደም ዝውውር ወይም ግፊትን ማስወገድ መቻሉ ነው። ለካንሰር፣ ሰውነት ላይ የሚፈጠሩ አላስፈላጊ ነገሮችን ለማስወገድ በሚረዱ የቪታሚን ሲ አይነቶች የበለጸገው ሃባብ ሌላኛው ጠቀሜታ የካንሰር ተጋላጭነትን መቀነስ መቻሉ መሆኑን ይኼው ጥናት ያሳያል።

5. ቃርያ

1. ቫይታሚን ኤ ዋነኛ ከሚባሉ ቃርያ ውስጥ ከሚገኙ ንጥረ ነገሮች ስለሆነ እና ለአይን ጥራት እና ጤናማነት ከፍተኛ ሚናን ስለሚጫወት ቃርያን መመገብ ጠቀሜታን ይሰጣል።
2. ቃርያ በቫይታሚን ሲ እጅግ የበለጸገ በመሆኑ ቆዳችንን ጤናማና የሚያበራ እንዲሆን ያደርጋል።
3. በሽታን የመከላከል አቅምን ማዳበር።
4. የምግብ መፈጨት ሂደትን ያፋጥናል።
5. ጉንፋን፣ሳል፣እንዲሁም የሳንባ ካንሰርን የመከላከል አቅም አለው።
6. ለአጥንት ጤናማነት እና ጥንካሬ እጅግ ጠቃሚም ነው።
7. ለሰውነታችን ጠቃሚ ያልሆኑ ንጥረነገሮችን በማስወገድ እና የፋይበር ምንጭ በመሆን የሆድ ድ

31/07/2021

የኦቾሎኒ የጤና ጥቅሞች፦
በእጽዋት ላይ የተመሠረተ የፕሮቲን ምንጭ ከሆኑት ምንጮች መካከል ኦቾሎኒ አንዱ ነው።
28 ግራም ኦቾሎኒ አገልግሎት 7 ግራም የእፅዋት ፕሮቲን አለው ፡፡ ኦቾሎኒ በንጥረ-ነገር የበለፀገ የኃይል ምንጭ ነው ፡፡ በእውነቱ ኦቾሎኒ ልዕለ-ምግብ ማዕረግ ይገባዋል ፡፡ ከፕሮቲን በተጨማሪ ኦቾሎኒ አገልግሎት 19 ቫይታሚኖችን እና ማዕድናትን ይዟል ፣ ከእነዚህም ውስጥ ብዙዎቹ የልብ በሽታን ይዋጋሉ (እንደዚህ ያለ ቫይታሚን ኢ ፣ ፎሊክ አሲድ ፣ ኒያሲን ፣ ማግኒዥየም ፣ ቫይታሚን ቢ 6 ፣ ዚንክ ፣ መዳብ እና ፖታሲየም) ፣ ፀረ-ኦክሳይድቶች ፣ ሞኖአንሳቹረቲድ እና ፖሊአንሳቹሬቲድ የያዘ እና “መጥፎ” ኤል.ዲ.ኤል ኮሌስትሮልን ለመቀነስ እና “ጥሩ” ኤች.ዲ.ኤል ኮሌስትሮልን እና የልብ-ጤናማ ፋይበርን ለመጨመር የሚረዱ ቅባቶች አሉት ፡፡
በጥናት የተረጋገጡ የኦቾሎኒ ጥቅሞች ፦
1. የካንሰር ተጋላጭነትን ይቀንሳል ። እ.ኤ.አ. በ 2018 የታተመው የኔዘርላንድስ የቡድን ጥናት የጥናት ውጤቶች እንደሚያመለክቱት በየቀኑ ኦቾሎኒን መመገብ በድህረ ማረጥ ሴቶች ላይ ለማከም አስቸጋሪ የሆነ የጡት ካንሰር የመያዝ አደጋ ይቀንሳል ፡፡ ሌላ የኔዘርላንድስ የቡድን ጥናት በቀን አንድ የሻይ ማንኪያ ወይም ከዚያ በላይ የኦቾሎኒ ቅቤን የሚወስዱ ወንዶች ለቆሽት ካንሰር የመጋለጥ እድላቸው አነስተኛ ነው ፡፡
2. የልብ ጤናን ለማሳደግ ይረዳሉ። በወቅታዊው አተሮስክለሮሲስ ሪፖርቶች በ 2018 የታተመ አንድ ጥናት ኦቾሎኒን አዘውትረው የሚመገቡ ሰዎች በልብና የደም ሥር (cardiovascular) በሽታ የመሞት እድላቸው ቀንሷል ፡፡ ከ 200,000 በላይ ተሳታፊዎችን የመረመረ በ 2017 በተደረገው ሌላ ጥናት መደበኛ የኦቾሎኒ ፍጆታ የደም ቧንቧ ህመም ተጋላጭነትን በ 15 በመቶ እንደሚቀንስ ያመለክታል ፡፡
3. የኦቾሎኒ እና የኦቾሎኒ ቅቤ ዓይነት 2 የስኳር በሽታ መጀመሩን ለመከላከል ይረዳሉ።
ከሀርቫርድ ዩኒቨርሲቲ በተደረገ አንድ የ 2016 ጥናት እንደሚያመለክተው እንደ ኦቾሎኒ እና የኦቾሎኒ ቅቤን በመሳሰሉ የእፅዋት ፕሮቲኖች አገልግሎት ላይ የእንሰሳት ፕሮቲን አገልግሎት መስጠቱ ለ 2 ኛ ዓይነት የስኳር በሽታ ተጋላጭነትን በእጅጉ ቀንሷል ፡፡ በአሜሪካን ሜዲካል አሶሲዬሽን ጆርናል ላይ የወጣ ሌላ ትኩረት የሚስብ ጥናት ቀደም ሲል እንዳመለከተው የኦቾሎኒ ቅቤ አጠቃቀም በሴቶች ላይ የታይፕ 2 የስኳር በሽታ ተጋላጭነትን በ 21 በመቶ ቀንሷል ፡፡
4. በጊዜ ሂደት የእውቀት እና የአእምሮ ግልፅነትን ለመጠበቅ ይረዳሉ። ኦቾሎኒ ከፍተኛ መጠን ያለው የኒያሲን መጠን ያለው ሲሆን የአልዛይመር በሽታን እና ከእድሜ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን የግንዛቤ ማሽቆለቆልን ለመከላከል ለረጅም ጊዜ የታወቁ ሁለት ንጥረ ነገሮች የቫይታሚን ኢ ጥሩ ምንጭ ናቸው ፡፡ አንድ ጥናት እንዳመለከተው ዕድሜያቸው 65 ዓመትና ከዚያ በላይ ለሆኑት ወደ 4,000 የሚጠጉ ሰዎች ናያሲን ከምግብ ውስጥ የእውቀት (ኮግኒቲቭ) የመቀነስ ፍጥነትን ቀንሷል ፡፡ሌላ ጥናት ደግሞ የአልዛይመር በሽታ ላለባቸው ታካሚዎች የቫይታሚን ኢ መመገብ የአሠራር ማሽቆልቆልን ሊያዘገይ እንደሚችል አጉልቷል ፡፡

ከዶክተር አዱኛው ብርሀን
የደቡብ ክልል ጤና ቢሮ

30/07/2021

የስኳር ድንች የሚከተሉትን 8 ጥቅሞች ያስገኛል!
***********************************
1. የልብ ድካም ተጋላጭነትን ይቀንሳል
ስኳር ድንችን መመገብ ቫይታሚን 6 የሚያስገኝ ሲሆን ይህ የቫይታሚን አይነት ደግሞ በሰውነታችን ውስጥ ያለውን ለልብ ድካም የሚያጋልጥ የሆሞሳይስታይን ኬሚካል ያስወግዳል፡፡

2. የቆዳን ውበት እና ጤንነት ለመጠበቅ
ይረዳል። ቫይታሚን ሲ እንደ ጉንፋን ያሉ በሽታዎችን
ለማከም እና ለመከላከል የሚረዳ ሲሆን ስኳር
ድንች ውስጥም ይገኛል፡፡
ቫይታሚን ሲ ለአጥንት እና ለጥርስ ጤንነት፣
ለምግብ መፈጨት እንዲሁም ለደም ህዋስ መመጣጠን የራሱ ጥቅም አለው፡፡
ከዚህም ባሻገር የቆዳን ውበት እና ጤንነት የሚጠብቅ ሲሆን ሰውነታችን ከካንሰር ጋር
ለተያያዘ የበሽታ ስጋት እንዳይጋለጥ ያደርጋል።
በመሆኑም በውስጡ ቫይታሚን ሲ የያዘውን
ስኳር ድንችን መመገብ ፋይዳው የጎላ ነው፡፡

3. የአጥንት ጤንነትን ይጠብቃል
በስኳር ድንች ውስጥ የምናገኘው ቫይታሚን
ዲ ለሰውነታችን የበሽታ መከላከል አቅም እና
ለአጠቃላይ ጤንነታችን ያለው ፋይዳ ከፍተኛ
ነው፡፡
ከቫይታሚን ዲ የሚገኙት ንጥረ ነገሮች
በዋናነት ምንጫቸው የፀሐይ ብርሃን ነው፡፡
ቫይታሚን ዲ ሃይልን፣ መነቃቃትን፣ የአጥንት፣
የቆዳ እና የጥርስ ጥንካሬን ያመጣል፡፡
በመሆኑም ከፀሐይ ብርሃን በተጨማሪ ከስኳር
ድንች የሚገኘው ቫይታሚን ለሰውነታችን ጤና
ወሳኝነት አለው።

4. በሽታ የመከላከል አቅምን ያሳድጋል
ስኳር ድንች በውስጡ የአይረን ንጥረ ነገርን
የያዘ መሆኑ ለሰውነታችን የበሽታ መከላከል
አቅም ከፍ ማለት ጥቅም እንዲኖረው
አድርጎታል።
አይረን ሰውነታችን በቂ ሃይል እንዲኖረው የሚያግዝ ንጥረ ነገር ሲሆን የነጭ እና የቀይ የደም ህዋሶችን በማጠናከር የበሽታ መከላከል አቅም እንዲጨምር ያደርጋል፡፡

5. ጭንቀትን ለማስወገድ ይረዳል
ስኳር ድንች በውስጡ የማግኒዥየም ንጥረ ነገር ክምችት ያለው በመሆኑ አዕምሮን በማነቃቃት ድብርትን ለመቀነስ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ይኖረዋል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ ማግኒዥየም ለደም ቅዳ፣
ለደም፣ ለልብ፣ ለጡንቻ እና ለነርቭ ተግባራት
መፋጠን ቀላል የማይባል ጠቀሜታ አለው።

6. የልብ ምትን ለመቆጣጠር ይረዳል
ፖታሺየም የተሰኘው ንጥረ ነገር የልብ ምትን እና የነርቭ መልዕክቶችን ለመቆጣጠር ይረዳል፡፡
የጡንቻ መሸማቀቅ እንዳያጋጥም፣ የኩላሊትን
እንቅስቃሴ የተስተካከለ እንዲሆንና የሰውነት
እብጠትን በመቀነስ ረገድ ጉልህ ፋይዳ አለው፡፡

7. በደም ውስጥ የሚገኘው የስኳር መጠን እንዲጨምር አያደርግም
ስኳር ድንች ጣፋጭ ምግብ ቢሆንም ወደ
ደማችን የሚቀላቀለው ተፈጥሯዊ የስኳር መጠናቸው እጅግ ዝቅተኛ ነው፡፡ ይህም ለውፍረትም ሆነ ላልተፈለግ ክብደት የሚዳርግ የስኳር መጠን በደማችን ውስጥ ጭማሪ ሳይከሰት የሰውነት ሃይላችን እንዲስተካከል ያደርጋል፡፡

8. እርጅናን እና የካንሰር ህመምን
ለመቋቋም ይጠቅማል የስኳር ድንች ውስጣቸው በብርቱካናማ ቀለም የበለጸገ መሆኑ ከፍተኛ የካርቶኖይዶች መገኘት ማሳያ ነው፡፡
እነዚህ ካርቶኖይዶች ደግሞ ሰውነታችን ቫይታሚን ኤ እንዲያገኝ የሚያደርጉ ናቸው፡፡ ካርቶኖይዶች እይታችን የተስተካከለ እንዲሆን የበሽታ መከላከል አቅማችን ከፍ እንዲል እንዲሁም የካንሰር ህመም ተጋላጭነትን እና እርጅናን ለመቀነስ ጠቃሚ ናቸው።

The use of lemon
25/06/2021

The use of lemon

23/10/2020

የስኳር ድንች ዘጠኝ ጥቅሞች ያስገኛል፡፡
***************************
(ሼር በማድረግ ለለሎች ያጋሩ)
1. የልብ ድካም ተጋላጭነትን ይቀንሳል
ስኳር ድንችን መመገብ ቫይታን 6 የሚያስገኝ
ሲሆን ይህ የቫይታሚን አይነት ደግሞ
በሰውነታችን ውስጥ ያለውን ለልብ ድካም
የሚያጋልጥ የሆሞሳይስታይን ኬሚካል
ያስወግዳል፡፡
2. የቆዳን ውበት እና ጤንነት ለመጠበቅ
ይረዳል
ቫይታሚን ሲ እንደ ጉንፋን ያሉ በሽታዎችን
ለማከም እና ለመከላከል የሚረዳ ሲሆን ስኳር
ድንች ውስጥም ይገኛል፡፡
ቫይታሚን ሲ ለአጥንት እና ለጥርስ ጤንነት፣
ለምግብ መፈጨት እንዲሁም ለደም ህዋስ
መመጣጠን የራሱ ጥቅም አለው፡፡
ከዚህም ባሻገር የቆዳን ውበት እና ጤንነት
የሚጠብቅ ሲሆን ሰውነታችን ከካንሰር ጋር
ለተያያዘ የበሽታ ስጋት እንዳይጋለጥ ያደርጋል።
በመሆኑም በውስጡ ቫይታሚን ሲ የያዘውን
ስኳር ድንችን መመገብ ፋይዳው የጎላ ነው፡፡
3. የአጥንት ጤንነትን ይጠብቃል
በስኳር ድንች ውስጥ የምናገኘው ቫይታሚን
ዲ ለሰውነታችን የበሽታ መከላከል አቅም እና
ለአጠቃላይ ጤንነታችን ያለው ፋይዳ ከፍተኛ
ነው፡፡
ከቫይታሚን ዲ የሚገኙት ንጥረ ነገሮች
በዋናነት ምንጫቸው የፀሐይ ብርሃን ነው፡፡
ቫይታሚን ዲ ሃይልን፣ መነቃቃትን፣ የአጥንት፣
የቆዳ እና የጥርስ ጥንካሬን ያመጣል፡፡
በመሆኑም ከፀሐይ ብርሃን በተጨማሪ ከስኳር
ድንች የሚገኘው ቫይታሚን ለሰውነታችን ጤና
ወሳኝነት አለው።
4. በሽታ የመከላከል አቅምን ያሳድጋል
ስኳር ድንች በውስጡ የአይረን ንጥረ ነገርን
የያዘ መሆኑ ለሰውነታችን የበሽታ መከላከል
አቅም ከፍ ማለት ጥቅም እንዲኖረው
አድርጎታል።
አይረን ሰውነታችን በቂ ሃይል እንዲኖረው
የሚያግዝ ንጥረ ነገር ሲሆን የነጭ እና የቀይ
የደም ህዋሶችን በማጠናከር የበሽታ
መከላከል አቅም እንዲጨምር ያደርጋል፡፡
5. ጭንቀትን ለማስወገድ ይረዳል
ስኳር ድንች በውስጡ የማግኒዥየም ንጥረ
ነገር ክምችት ያለው በመሆኑ አዕምሮን
በማነቃቃት ድብርትን ለመቀነስ ከፍተኛ
አስተዋፅኦ ይኖረዋል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ ማግኒዥየም ለደም ቅዳ፣
ለደም፣ ለልብ፣ ለጡንቻ እና ለነርቭ ተግባራት
መፋጠን ቀላል የማይባል ጠቀሜታ አለው።
6. የልብ ምትን ለመቆጣጠር ይረዳል
ፖታሺየም የተሰኘው ንጥረ ነገር የልብ ምትን
እና የነርቭ መልዕክቶችን ለመቆጣጠር
ይረዳል፡፡
የጡንቻ መሸማቀቅ እንዳያጋጥም፣ የኩላሊትን
እንቅስቃሴ የተስተካከለ እንዲሆንና የሰውነት
እብጠትን በመቀነስ ረገድ ጉልህ ፋይዳ
አለው፡፡
7. በደም ውስጥ የሚገኘው የስኳር
መጠን እንዲጨምር አያደርግም
ስኳር ድንች ጣፋጭ ምግብ ቢሆንም ወደ
ደማችን የሚቀላቀለው ተፈጥሯዊ የስኳር
መጠናቸው እጅግ ዝቅተኛ ነው፡፡
ይህም ለውፍረትም ሆነ ላልተፈለግ ክብደት
የሚዳርግ የስኳር መጠን በደማችን ውስጥ
ጭማሪ ሳይከሰት የሰውነት ሃይላችን
እንዲስተካከል ያደርጋል፡፡
8. እርጅናን እና የካንሰር ህመምን
ለመቋቋም ይጠቅማል
የስኳር ድንች ውስጣቸው በብርቱካናማ
ቀለም የበለጸገ መሆኑ ከፍተኛ የካርቶኖይዶች
መገኘት ማሳያ ነው፡፡
እነዚህ ካርቶኖይዶች ደግሞ ሰውነታችን
ቫይታሚን ኤ እንዲያገኝ የሚያደርጉ ናቸው፡፡
ካርቶኖይዶች እይታችን የተስተካከለ እንዲሆን
የበሽታ መከላከል አቅማችን ከፍ እንዲል
እንዲሁም የካንሰር ህመም ተጋላጭነትን እና
እርጅናን ለመቀነስ ጠቃሚ ናቸው፡፡
▬▬ Share ▬▬▬▬
ለተጨማሪ እውቀት እና ጠቃሚ የቴክኖሎጂ መረጃ ለማግኘት በዚ የቴሌግራም ቻናላችንን ከታች ባለዉን ሊንክ በመጫን ማግኘት ይችላሉ።
here it is
https://t.me/Information_Science_Technology
በተጨማሪም የዩቲዩብ ቻናላችንን Subscribe በማድርጉ ሌሎች መረጃዎች ይሸምቱ
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/channel/UCpKx7Pd_viT9nnmheRu6o8Q

11/06/2020

በፔሩ ወረርሽኙን ተከትሎ የዝንጅብል የውጭ ገበያዋ 150 በመቶ ጭማሪ አሳየ
--------------------------------------------------------------------------
የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ተከትሎ በበርካቶች ዘንድ ለመከላከያነት ሲመከር የነበረው ዝንጅብል በዓለም ተፈላጊነቱ ጨምሯል።
ወረርሽኙንም ተከትሎ ፔሩ ወደ ውጭ የምትልከው የዝንጅብል መጠን በሦስት እጥፍ አድጓል።
ወረርሽኙ ከተከሰተ ጀምሮ ያለው አሃዝ ከባለፈው ዓመት ጋር ሲወዳደር በ150 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል።
የዝንጅብል ምርቱን ከፔሩ በገፍ እያስገቡት ያሉት ስፔን፣ ሆላንድና አሜሪካ ናቸው።
የሰውነት በሽታን የመከላከል አቅም ያሳድጋል የሚባልለት ዝንጅብል ከኮሮናቫይረስ ከመያዝ ሊታደገን ይችላልም በሚል ብዙዎች እየወሰዱት ይገኛል።
ዝንጅብል ለጤና ጠቃሚ ከሚባሉ ስራስሮች አንዱ መሆኑ ሳይታለም የተፈታ ቢሆንም በቫይረሱ ከመጠቃት እንደማይከላከል ግን ልብ ሊባል እንደሚገባ ባለሙያዎች ይመክራሉ።
BBC

Food Safety is ze first, foregat ze rest !!
07/06/2020

Food Safety is ze first, foregat ze rest !!

30/05/2020

YOU ARE WHAT YOU EAT !!!!

Use of Ginger
30/05/2020

Use of Ginger

15 የዝንጅብል የጤና ጥቅሞች 🍵🍵

ዝንጅብል ከስኬታማ የቤት ውስጥ ተፈጥሯዊ ፈዋሾች ዋናውን ስፍራ የሚይዝ ነው:: በመላው አለም ታሪክ በተለያየ ባህል ውስጥ ሲጠቀሙት የኖረ ነው፣ ዝንጅብል ለጥገኛ ተዋስያን ህመሞች አስደናቂ የፈውስ ሀይል መሆኑ የተረጋገጠ ሀቅ ነው:: ይህ ቅመም እጅግ ጠቃሚ በሆኑ ንጥረነገሮች (በቫይታሚን ሲ፣ ማግኒዢየም እና በሌሎችም ማዕድናት) እና የማደስ አቅም ባላቸው ውህዶች የታጨቀ ነው:: ምንም እንኳ ዝንጅብል ለብዙ ትንሽ ለሚባሉ የጤና ችግሮች ልክ እንደ ሆድ ቁርጠት ፈውስ መሆኑ ቢታወቅም፣ አስደናቂነቱ ግን ካንሰርን ከፋርማሲ መድሀኒቶች የበለጠ መከላከል የሚችል መሆኑ ነው::

👉 ከዝንጅብል ዘርፈ ብዙ ጠቅሞች መካከል;-

1. የምግብ መፈጨት ስርዓትን ያቀላጥፋል

2. ከጉዞ ጋር ተያይዞ የሚመጣ እንዲሁም በእርግዝና ጊዜ የሚመጣን
የማቅለሽለሽ ስሜት ያስወግዳል

3. የጡንቻ ህመምን ይከንሳል

4. የመገጣጠሚያ አካላት ሕመም እና እብጠትን ይቀንሳል

5. ለጉንፋንና ለመተንፈሻ አካላት ሕመሞች ይረዳል

6. በካንሰር የመያዝ እድልን በከፍተኛ መጠን ይቀንሳል

7. የደም ዝውውርን ያሻሽላል

8. የልብና ተዛማጅ ሕመሞችን ለመከላከል ይረዳል

9. የመጥፎ ኮሌስትሮል መጠንን ይቀንሳል

10. የወር አበባን ተከትሎ የሚመጣን የሕመም ስሜት ያስወግዳል
• የዝንጅብል ሻይን በጨርቅ ነክሮ ሆድ ላይ ማድረግ እንዲሁም
የዝንጅብል ሻይ መጠጣት የወር አበባን ሕመም ያስወግዳል

11. የሰውነት የበሽታ መከላከል ብቃትን ይጨምራል

12. የውጥረት ስሜትን ይቀንሳል

13. ለአእምሮ ጤንነት እና የመርሳት በሽታን ይከላከላል

14. የማይግሬን ህመም ስሜትን ይቀንሳል

15. በደም ውስጥ የስኳር መጠንን ያረጋጋል

✔ከነዚህ ጥቅሞች ተቋዳሽ ለመሆን ዘወትር የዝንጅብል ሻይ ፣ የዝንጅብል
ዱቄት ፣ እንዲሁም የዝንጅብል ውሃ መጠቀም ይመከራል

29/05/2020

YOU ARE WHAT YOU EAT !!!!!

WHO RECOMMENDATION🙏🙏🙏
20/05/2020

WHO RECOMMENDATION🙏🙏🙏

Ha qummaa sunttaa eriyay oonee.. anne xufiyan qonccisitte!!🙏🙏🙏🙏🙏🙏
19/05/2020

Ha qummaa sunttaa eriyay oonee.. anne xufiyan qonccisitte!!
🙏🙏🙏🙏🙏🙏

19/05/2020

Healthy food makes healthy life🙏🙏🙏🙏

19/05/2020
18/05/2020

በቅድምያ ሰላማችሁ ይብዛ እያለን የዝህ ፔጅ ሃሳብ ለመግለጽ እንወዳለን፡፡ምግብ ለሳዉ ልጅ መሠረታዊ ነገር ነዉ፡፡ የበለጸገች ወላይታ እንድሁም ኢትዮጵያ ለማየት የምግብ ደንነት መሬጋገጥ አለበት፡፡ይህ ሃሳብ እዉን ሆኖ ማየት የዝህ ፔጅ ዋና ዓላማ ነዉ፡፡
ከሚነሱ ሃሳቦች ፡-
-በወላይታ እና አካባብ ያለዉን የግብርን ምርቶችን በመጠቀም አግሮ ኢንዳሰተር ለማሳደግ የምያግዙ ሀሳቦችን ማምጣት፤
-በምግብ ሳያንስ እና በጠና ዙርያ መወያየት::
THANK YOU!

Address

Wolaita
S**o

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Food science and Technology posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Nearby media companies