Gezehagn melese

Gezehagn melese Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Gezehagn melese, Film/Television studio, Durame.

15/08/2022

የአካላችን ጤንነት ለአእምሮአችን ጤንነት አንዱ መሠረት ነው
አንብባችሁ ለወዳጆቻችሁ ሼር አርጉት
☞ የጀርባ ህመም መነሻ 10 ምክንያቶች፦
1. በሆድ በኩል መተኛት:
በሆድ በኩል ተደፍተዉ ሲተኙ በጀርባዎና በአከርካሪ አጥንትዎ ላይ ተጨማሪ ሸክም ይጨምራል። በአከርካሪ አጥንትዎ ላይ ተጨማሪ ሸክም ጨመሩ ማለት ደግሞ የሙሉ ሰውነትዎን ቅርጽ ያዛባዋል ጭንቅላትዎን ወደ ጎን ሲያዞሩት ደግሞ ጭንቅላትዎንና አከርካሪዎት ከመደበኛ አቅጣጫዎ ውጪ አደረጉት ማለት ነው።
2. የሚያደርጉት ጫማ:
ጫማ ለጀርባዎ ጤንነት ከፍተኛ ሚና ይጫዎታል የማይገባ/ትክክል ያልሆነ ጫማ አቋምዎን በማዛባት ማዕከላዊ የግራቪቲ ቦታን ያዛባል ይህም በታችኛው የጀርባ ክፍልዎ ላይ ህመም ይፈጥራል።
3. እግርን አጣምሮ መቀመጥ:
እግርዎን አጣምረው በሚቀመጡበት ጊዜ የአከርካሪ አጥንትዎ ቀጥ ማለት ይሳነዋል። ይህም በዳሌ አካባቢ የሚገኙ ጡንቻዎች ከመጠን በላይ እንዲለጠጡ ያደርጋቸዋል። በተጨማሪም የደም ዝውውር በመስተጓጐሉ ምክንያት ቫሪኮስ ቬይን (Varicose vein) ለተባለ በሽታ ያጋልጣል።
4. የቢሮ ወንበር :
የቢሮ ወንበርዎ ለጀርባ ህመም ከፍተኛ አስተዋጽዎ ያደርጋል። በተለይ ሲቀመጡ ጎበጥ የሚሉ ከሆነ ጀርባዎ ላይ ጫና ያደርጉበታል፤ አከርካሪ ሊጋመንታችን ከአቅም በላይ ይለጠጥና ዲስካችን የጀርባ አጥንታችን እንዲወጠር ያደርጋል ከጊዜ ብዛት የጀርባ አጥንታችንን በመጉዳት ለጀርባ ህመም ይዳርገናል።
5. የሚተኙበት ፍራሽ:
የሳሳ (ስስ) ፍራሽ መጠቀም የታችኛዉን የጀርባ ክፍል እንዲሰምጥ ያደርጋል። በተጨማሪም የአከርካሪ አጥንቶችን እንዲዛቡ በማድረግ በጡንቻዎች እና የአከርካሪ መገጣጠሚያዎች ላይ ውጥረት ይፈጥራል።
6. የጀርባ ቦርሳ:
የሚይዙት የጀርባ ቦርሳ ትልቅ ከሆነ ብዙ እቃዎችን የመያዝ እድል ይኖርዎታል፤ ተጨማሪ ሸክም በጀርባዎ ላይ መጫን ትልቁ የጀርና ህመም ምክንያት ነው። በአንድ በኩል ያለው የሰውነት ክፍልዎ ላይ ሸክም መጨመር የአከርካሪ አጥንቶች እንዲጎብጡ በማድረግ የጀርና ህመም እንዲከሰት ያደርጋል።
7. ትከሻ ወይም አንገት:
ለረጂም ሰዓት አንገት አዘንብሎ (ደፍቶ) መቆየት ወይም መጓዝ በትከሻዎቻችን መሀል ያሉትን ጡንቻዎች እንዲዝሉ በማድረግ የላይኛው ጀርባ ክፍል እና የአንገት ህመም ያስከትላል።
8. ላኘቶኘና ስማርት ስልኮች:
በአለም ላይ ያሉ ሰዎች ሁሉ በኤሌክትሮኒክስ መገልገያዎቻቸው ፍቅር ስለወደቁ በነዚህ ሰዎች ላይ የጀርባ ህመም የተለመደ ነው። በስራ በተጠመድበት ወቅት ስልክዎትን በትከሻዎና በጆሮዎ መሀል በመያዝ ለረጂም ጊዜ ማውራት የአንገት ህመም ያስከትላል።
9. ከመጠን ያለፈ ውፍረት:
ከሌሎች በሽታዎች በተጨማሪ ከመጠን ያለፈ ውፍረት ለጀርባ፣ መገጣጠሚያ እና ጡንቻዎች ህመም ያጋልጠናል። አብዛኛዎቹ በሚኖራቸው ውፍረት በዳሌና በታችኛው የጀርባ ክፍል ህመም ያጋጥማቸዋል።
10. ሲጋራ ማጨስ :
በሲጋራ ውስጥ ያለው ኒኮቲን ወደ ዲስክ (Disc) የሚሄደውን የደም ዝውውር በመቀነስ የአከርካሪና ጎን አጥንት ችግር ያስከትላል። በተጨማሪም ካልሲየም በአግባቡ ከሰውነታችን ጋር እንዳይዋሀድ በማድረግ የአጥንት እድገትን ይገታል በመሆኑም ሲጋራ የሚያጨሱ ሰዎች ከማያጨሱ ሰዎች በአንድ እጥፍ የጀርባ ህመም ችግር ያጋጥማቸዋል። ....
@ ምንጭ: ዶክተር አለለሌሎችም ሰዎች ሼር አርጉት
🖍 Telegram channel:
https://t.me/Psychoet

08/05/2022

የካርቡራተር ክፍሎች ! ቶፕ ኢትዮ - አውቶሞቲቭ
🔷 ቦውል ቻምበር = ነዳጅ የሚጠራቀምበት
🔷 ቦውል ቬንት = ቦውል ቻምበር ውስጥ ነዳጅ በሚቀንስበት ሰአት አየር እንዳይፈጠር ወይም ቫኩየም እዳይኖር ትጠቅማለች ።

24/03/2022

የካይዘን ስራ አመራር ፍልስፍና ምንነት
✅ ካይዘን የሚለው ቃል የጃፓን ቃል ሆኖ ካይ ማለት ለውጥ ሲሆን ዘን ማለት ደግሞ የተሻለ ማለት ነው፣

✅ ቀጣይነት ያለው የተሻለ ለውጥ ማለት እንደሆነ ትርጓሜው ያመላክታል፣

✅ የካይዘን ስራ አመራር ፍልስፍና ትኩረት የሚሰጠው ነባራዊ ሁኔታን በመረዳትና የስራ አካባቢን በማሻሻል ላይ ነው፣

✅ ዋና የለውጥ ተዋናይ አድርጎ የሚወስደውም የሰው ኃይሉን በተለይም ፈጻሚውን ነው፣

✅ የካይዘን የለውጥ መርሆ አንድም ቀን ቢሆን ያለ ለውጥ ማለፍ የለበትም የሚል ነው፣

✅ የካይዘን የለውጥ ቡድን የማያቋርጥ የጥራት መሻሻልን ማዕከል ያደረገና ከታች ጀምሮ ያለውን ሰራተኛ የሚያቅፍ ቡድን ነው፣

✅ የየካይዘን የለውጥ ቡድን ፍልስፍና የሚመነጨው ከአሳታፊነት እና ሰብዓዊ ተኮር ከሆነ አመራር /Participative and Human Oriented Management/ ሲሆን የዚህ አመራር ፍልስፍና ለሰዎችና ለፍላጐታቸው ትኩረት የሚሰጥ ነው፣

ለዚህም ምክንያቱ ሰዎች የአንድ ተቋም ከፍተኛው ሀብት ናቸው ተብሎ ስለሚታመን ነው፣
ሰዎች ለተቋማቸው ትርጉም ያለው አስተዋጽኦ ሊያበረክቱ የሚችሉት በተለመደው ድርጅታዊ መዋቅር የሰው ኃይል አሰላለፍ የተዋረድ አሠራር ላይ በተመሠረተ የሥራ ትዕዛዝ በመስጠትና በመቀበል አመራር ብቻ ሳይሆን በሥራ ቦታ ላይ እንደ አንድ የሥራ ክፍል ቡድን እና ግለሰብ ስለሚሰጡት አገልግሎት እና ስለአሠራራቸው የተሻለ ሀሣብ እንዲያመነጩ፣ እንዲመክሩ፣ እንዲተገብሩ፣ ለውጣቸውን እንዲያዩ፣ ከለውጡም እንዲቋደሱ የሚያስችል የሥራ አካባቢ ሲፈጠርላቸው ነው፣

የካይዘን ልማት ቡድኖች ለውጥ እንዲያመጡ ከሚያስችሏቸው ዘዴዎች መካከል የሚከተሉት በመሠረታዊነት ይጠቀሳሉ፤

🔷 የሠራተኞችን የችግሮች/ማነቆዎች የማቃለልና የመፍታት አቅማቸውን ማሳደግ፣

🔷 የጋራ ብልጽግና ወይንም ዕድገት መርህን መከተል፣

🔷 ቀና አስተሳሰብን መፍጠርና ማስረጽ፣

🔷 የሥራ ላይ ሥነ ምግባርን መገንባት፣

🔷 የደንበኞችን ፍላጐት ማዕከል ያደረገ አሠራርን በመከተል፣ የሥራ ፍላጐትን ማነሳሳት፣

✅ ለሥራ ከፍተኛ መበረታታትን መፍጠር፣

✅ የግል ኃላፊነትን በአግባቡ የመገንዘብና የመወጣት ስሜትን መፍጠር፣

✅ እያንዳንዱ ሠራተኛ ከሥራ ክፍልና ከተቋም ባሻገር የህብረተሰብ ዕድገትን ማምጣት አስተዋጽኦ እንዳለው ማስገንዘብ ናቸው፡፡

⏺⏺⏺ጠቀሜታ⏺⏺⏺
✅ ሠራተኛውንና የሥራ አመራሩን ያቀራርባል፣
✅በሠራተኞች መካከል የሥራ ትብብርን ይፈጥራል፣
✅ የሥራ ዕርካታን ያስገኛል፣
✅ ለሥራ ያነቃቃል፣
✅ በራስ መተማመንን ይፈጥራል፣
✅ መሪዎችን ለማፍራት ይረዳል፣
✅ ተተኪዎችን ለማፍራት ይረዳል፣
✅ የሥራ ፈጠራን ያበረታታል፣

እንዲሁም ከዚህ በፊት የለቀቅኳቸውን ቪዲዮዎችን ብትከታተሉ ምርጥ እውቀትን ልታገኙ ትችላላችሁ
አሁንም የቴሌግራምና የYouTube ቻናሌን Subscribe በማድረግ ድጋፋችሁን አሳዩኝ።
✅✅✅ #ያወቁትን ማሳወቅ ብልህነት ነው!✅✅✅

የ YouTube ቻናል ሊንክ 👇👇👇
https://www.youtube.com/channel/UCZBIP6PqUdmmagdTjbyp_AQ

ቴሌግራም ቻናል
👇👇👇👇👇👇 https://t.me/MuhammedComputerTechnology

28/01/2022

ፍቅር ስራን ይጠይቃል!
ለፍቅረኛሞች፣ ለእጮኛሞችና ለባለትዳሮች . . .

አንድ ሰው እንዲህ ሲል ተናገረ፣ “የዘመኑ አሳዛኝ ሁኔታ፣ አንዳንድ ሰዎች እየተፋቀሩ አብረው ግን መሆን አለመቻላቸው፣ አንዳንድ ሰዎች ደግሞ አብረው ሆነው አለመፋቀራቸው ነው”፡፡ የብዙ ሰዎችን ወቅታዊ ሁኔታ የሚገልጽ አባባል!

እየውላችሁ፣ በፍቅር፣ በእጮኝነትም ሆነ በትዳር አብራችሁ ከሆናችሁ አይቀር ተፋቀሩ፡፡ ፍቅር ደግሞ በምትሃት የሚመጣና በተአምራት የሚቀጥል ጉዳይ አይደለም፡፡ በፍቅር የተጀመረው ግንኙነት በፍቅር እንዲቀጥል ስራን ይጠይቃል፡፡ ፍቅርን የሚያሳዩ ተግባሮችን መስራት፣ የፍቅር ንግግሮችን መናገር፣ ለአጋር መጠንቀቅ፣ ችግርን መፍታት፣ መወያየት፣ ማቀድ . . . ምናምን የሚባሉ ስራዎች አሉ፡፡

ምናልባት “እንፋቀራለን ነገር ግን አብረን አይደለመንም” የምትሉ ከሆነ፣ ይህም ሁኔታ ስራን እንደሚጠይቅ አትርሱ፡፡ ይህ ሁኔታ የተከሰተው ከጋብቻ በኋላ በመጣ መለያየትም ሆነ የተጀመረን የፍቅር ግንኙነት ወደፊት ለማራመድ ከማቃት ይሁን ስሌቱ ያው ነው፡፡ በሚገባ መተዋወቅ፣ ወደፊት አብሮ የመሆንን እቅድ አብሮ መንደፍ፣ በየጊዜው ወደ አብሮነት ለመምጣት አንድ ተግባራዊ እርምጃን መራመድ . . . ምናምን የሚባሉ ስራዎች አሉ፡፡

https://t.me/Dreyob
https://m.youtube.com/user/naeleyob623
https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

24/01/2022

🌀የእኔ ለምትለው ሠው የምትሠጠው ትልቁ ስጦታህ ጊዜህን፣ አትኩሮትህን ነው፡፡›🌀

✅እንደራስህ ለምትወደው ወዳጅህ ልትሠጠው የምትችለው ትልቁ ስጦታህ ጊዜህን፣ ፍቅርህንና አትኩሮትህን ከሆነ ለዚህ ሠው ያለህ አመለካከት መልካምና ቅንነት የተሞላው እንደሆነ ማወቅ ይቻላል፡፡ ምክንያቱም በዚህ ዘመን ጊዜ ወርቅ ነው፡፡
ለማትወደው ወይም ጥሩ አመለካከት ለሌለህ ሠው ውዱን ጊዜህን አታካፍለውም፡፡

ፍቅር ወረት በሆነበት ዘመን ፍቅርህን የምትቸረው ሠው በአንተ ልብ ውስጥ ትልቅ ቦታ ላለው ሠው ነው፡፡
ፍቅር በዚህ ዘመን ውድ ከመሆኑ የተነሳ እንደከበሩ ማዕድናት ብርቅ ሆኗል፡፡
✅አትኩሮትህንም ቢሆን እንደው ለማንም ዝም ብለህ የምትለግሠው አይደለም፡፡

አትኩሮት ማለት የምታውጠነጥነው ሃሳብህ ነው፡፡ ስንት የሚያሳስብህና የምታሠላስልበት የኑሮ ጉዳይ እያለህ ሃሳብህን ሁሉ ሰብስበህ የምትሠጠው በልብህ ፅላት ውስጥ ላሠፈርከው ሠው ነው፡፡

🌀አትኩሮት ለወዳጅነት፣ ለባለትዳርነት፣ ለተማሪ አስተማሪ ግንኙነት፣ ለአለቃና ለምንዝር እንዲሁም ለሌሎችም ነገሮች ወሳኝ ነገር ነውና፡፡ አትኩሮት አጥተው የተለያዩ ባልና ሚስቶች ቤት ይቁጠራቸው፡፡
እሷ ለእኔ ግድ የላትም፡፡ እሱ ለእኔ ግድ የለውም እየተባባሉ ለዘመናት የገነቡትን ጓደኝነታቸውን፣ ጉርብትናቸውን ወይም ዝምድናቸውን የተዉ እልፍ ሠዎች ናቸው፡፡

🌀አትኩሮት አጥቶ ትምህርቱ ላይ ስኬታማ ያልሆነ ተማሪ እንደአሸን ነው፡፡ አትኩሮት ለራስ፣ ለወዳጅ፣ ለቤተሠብ ወሳኝ ነገር ነውና፡፡
አትኩሮት መስጠት ማለት ለወዳጃችን ወይም ለቤተሠባችን ሃሳባችን ከሃሳቡ አስማምቶ፤ መንፈሳችንን ከመንፈሱ አዋህዶ፣ ልብ ለልብ ተገናኝቶ መኖር ማለት ነው፡፡

ምርጥ መጣጥፎች
ሼርርርር

24/01/2022

የካሮት የጤና ጥቅሞች
******************
🥕 ለምግብ መፈጨት ይረዳናል
🥕ለጥርስ ጤንነት
🥕 የልብን ጤንነት ይጠብቃል
🥕ለቆዳ ጤንነት
🥕 ለእስትሮክ ታጋላጭነትን ይቀንሳል
🥕የኩላሊት ስራን ይደግፋል
🥕 ባክቴሪያን ይከላከልልናል
🥕የአይናችንን ጤንነት ይጠብቃል
🥕የጉበትን የመስራት አቅም ያጎለብታል!

24/01/2022

የዝምታ ጨዋታ! (Silent treatment)

ለፍቅረኛሞች፣ ለእጮኛሞችና ለባለትዳሮች . . .

በፍቅር ግንኙነትም ሆነ በትዳር አጋርነት ውስጥ አንዱ ሌላውን ጊዜ እየጠበቀ ባለማናገር፣ በመዝጋትና የቀድሞውን ትኩረት በመንፈግ የሚያሳልፍበትን የዝምታ ወይም የመዝጋት ልምምድ ፈረንጆቹ Silent treatment በማለት ይጠሩታል፡፡ ይህ ባህሪይ አብዛኛውን ጊዜ በወንዶች ላይ የሚንጻበረቅ እንደሆነ ቢናገሩም፣ ቁጥራቸው ቀላል ያልሆኑ ሴቶችም ፍቅረኛቸውን ወይም የትዳር አጋራቸውን የመዝጋት አባዜ አለባቸው፡፡

በድንገትና ባልታወቀ መንገድ አጋራቸውን የሚዘጉ ሰዎች ለአያያዝ እጅግ አስቸጋሪ ሰዎች ናቸው፡፡ እነዚህ ሰዎቸ በድንገት አጋራቸውን በመዝጋትና ቀድሞ ይሰጡት የነበረውን ትኩረት በመንፈግ ለቀናት፣ ለሳምንታት፣ አንዳንዴም ለወራት ይቆዩና በፈለጉበት ቀን ልክ እንደቀድሞው በመሆን ይመለሳሉ፡፡

መንስኤው የአኩራፊነት፣ የቂመኝነት፣ በቀላሉ የመጎዳት ስስነት ወይም ደግሞ አጋርን በዚህ መልኩ የመቅጣትና ልክ የማስገባት ሊሆን ይችላል፡፡ ምክንያቱ ያም ሆነ ይህ ይሀ ባህሪይ ከፍቅር ግንኙነት አንቅፋት ከመሆኑም ባሻገር እጅግ በጣም ያለመብሰል ምልክት ነው፡

አጋራችሁ በየጊዜው እናንተን የመዝጋት ልማድ ካለበት …
1. በየጊዜው ለምን ያንን ባህሪይ እንደሚያሳዩ በግልጽ ማነጋገርና መሞገት፡፡
2. መንስኤው እናንተ ከሆናችሁ በግልጽ መናገር እንዳባቸው እንጂ መዝጋት እንሌለባቸው መሳሰብ፡፡
3. ከገቡበት የዝምታ ዋሻ ምንም እንዳልተፈጠረ ሲወጡና እንደቀድሞው መሆን ሲፈልጉ የቻላችሁትን ያህል መታገስ፡፡
4. ሁኔታው ከልክ ካለፈ በፈለጉበት ጊዜ እንደቀድሞው ሊሆኑ ከዝምታቸው ሲመለሱ በዚያው ፍጥነት እናንትም እንደዚያ መሆን እንደማትችሉና መለስ ለማለት ጊዜ እንደሚፈልግባች በመንገር የራሳችሁን ጊዜ መውሰድ፡፡
5. አሁንም ካልታረመ ከእንዳንዷ ዝምታ በኋላ ሲመለሱ ለምን ዘግተዋችሁ እንደከረሙ በሚገባ ሳያብራሩ፣ ስህተት ከሆነ ይቅርታ ሳይጠይቁና ይህባህሪይ ወደፊት እንደማይቀጥል ቃል ሳይገቡ መቀጠል እንደማይችሉ ማሳሰብ፡፡
6. ከዚህ ሁሉ እርምጃ በኋላ ነገሩ አሁንም ከባሰ፣ የፍቅር ግንኙነት ከሆነ የመቀጠሉን ጉዳይ በሚገባ ማሰብ፣ ግንኙነቱ የትዳር ከሆነ ግን አማካሪ መፈለግ አስፈላጊ ነው፡፡

https://t.me/Dreyob
https://m.youtube.com/user/naeleyob623
https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

24/01/2022

ራስን መቀበል - ክፍል አንድ

ራስን መሆን

ራስን መሆን ማለት፣ ማንነትን ተቀብሎ፣ ሳይደባብቁና ሌላውን ሰው ለመሆን ሳይሞክሩ በነጻነት መኖር ማለት ነው፡፡ ራስን የመሆን ጉልበት የሚመነጨው ማንነቴን የሰጠኝ ፈጣሪ እንደሆነ ከማመን ነው፡፡

አንዳንድ ሰዎች ራሳቸውን ስለማይቀበሉ ራሳቸውን ሆነው መኖር አይችሉም፡፡ ራሱን መቀበል ያስቸገረው ሰው ላይ የሚታየው የመጀመሪያው ምልክት ራስን አለመሆን ነው፤ የማይቀበሉትን ማንነታቸውን ለውጠው ለመታየት ሲሞክሩ ራሳቸውን ያገኙታል፡፡
ፈጣሪ በሰጠን ማንነት ስንደላደልና ስንቀበለው ቀና ብለን መኖር እንጀምራለን፡፡

ራስህን ለመሆን መውሰድ የምትችላቸው እርምጃዎች፡-

1. መለወጥ ወይም ማሻሻል የምችለውን መለወጥና ማሻሻል፡፡
በማንነቴ ላይ የማልቀበለውን ነገር ለማሻሻል ጤናማ መንገዶችን መሞከሩ ክፋት አይኖረውም፤ ከተሳካልኝ፡፡ ቁም ነገሩ፣ አሻሻልኩትም አላሻሻልኩት ራሴን ወደ መቀበል መምጣቴና ጤናማ የሕብረተሰቡ አካል ሆኜ መኖሬ ነው፡፡

2. መለወጥ ወይም ማሻሻል የማልችለውን መቀበል፡፡
ዘሬን፣ መልኬን፣ አወላለዴንና የመሳሰሉትን ከፈጣሪ የተቀበልኩትን አሁን የሆንኩትን ማንነት ለመቀየር አስቸጋሪ ወይም የማይቻል እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡ ምርጫዬ አንድ ነው፣ ራሴን ተቀብዬ፣ በተደላደለ አመለካከት ዓላማዬ ላይ በማተኮር በሰላም መኖር፡፡

3. አዎንታዊነትን ማዳበር፡፡
በራሳችን ላይም ሆነ በኑሯችን ላይ ያለንን አመለካከት ከጨለምተኝነት አውጥተን ወደ አዎንታዊነት የማሸጋገር ስራ ካለማቋረጥ መስራት ይጠበቅብናል፡፡ ይህ ነገሬ ጎዶሎ ነው እያልን ስንጨናነቅ ከመኖር፣ ከላይ የተጠቀሱትን ሁለት መመሪያዎች እየተከተልን አዎንታዊነትን ማዳበር ተመራጭ ነው፡፡

ይቀጥላል . . .

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

23/01/2022

Throttle Position Sensor

The throttle position sensor monitors how far open the throttle valve (or blade) is open, which is determined by how far down the accelerator pedal has been pushed.

The throttle position controls the amount of air that flows into an engine’s intake manifold; when it’s opened wide more air flows in; when it’s nearly closed, little air flows in.

The position of the throttle and how quickly it’s opening or closing is transmitted to the engine control module, and that information is among the factors the computer uses to decide how much fuel is injected into the engine and the spark timing.

The TPS is usually mounted on the throttle body (the housing that contains the throttle valve).

When a TPS malfunctions it can trigger a “check engine” warning light or cause the engine to idle roughly, surge, hesitate or stall because the engine control module doesn’t know what the throttle position is and can’t correctly set the fuel mixture or ignition timing.
...................................................................................................

Subscribe - https://www.youtube.com/InnovationDiscoveries
...................................................................................................

Read More:

THROTTLE BODY FUEL INJECTION - https://bit.ly/3aVVlJO

VEHICLE SENSORS: FUNCTIONS AND TYPES - https://bit.ly/3ruzKil

6 Most Common Crankshaft Position Sensor Symptoms - https://bit.ly/2N2QM8m

How To Reset Tire Pressure Sensor: A Step-By-Step Guide - https://bit.ly/3rqWYGf

ECU Chip Tune | Ignition Timing | Increase Horsepower - https://bit.ly/3oWCsf4

Throttle Body Fuel Injection - https://innovationdiscoveries.space/throttle-body-fuel-injection/

22/01/2022


አንድ ቀን ልጅ ወዳባቱ ይሄድና፦ አባቴ አባቴ "የሕይወቴ ዋጋ ምንድነው?" ብሎ ይጠይቀዋል። አባትም ድንጋይ አንስቶ ይሰጠውና፦
"ልጄ የሕይወትህን ዋጋ ማወቅ ከፈለክ ይህን ድንጋይ ወደ ገበያ ይዘህ ሂድ ማንም ሰው ዋጋውን ቢጠይቅህ ምንም አትመልስ 2 ጣቶችህን ብቻ ከፍ አድርገህ አሳያቸው።"
ልጅም አባቱ እንዳለው ያደርጋል። ወደ ገበያም ይሄድና ድንጋዩን ይዞ ገበያ ዉስጥ ዞር ዞር ይላል ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላም፤ አንዲት ሴትዮ ከአጠገቡ ትደርስና " ልጄ የድንጋዩ ዋጋ ስንት ነው?" ብላ ትጠይቀዋለች።
ልጁ በአፉ ቃል ሳያወጣ አባቱ እንዳለው 2 ጣቱን ከፍ አድርጎ ያሳያታል።
ሴትዮዋም " 2 ብር ከሸጥከው እወስደዋለሁ"
ትለዋለች ልጅ ይደነቃል፤ ወደ አባቱም እየሮጠ ሊነግረው ይመለሳል።
አባቴ አባቴ፦
"አንዲት ሴትዮ በገበያ ውስጥ ድንጋዩን ካየችው በኋላ (2ብር) ልውሰደው አለችኝ።"
አባትም እንዲህ ይለዋል፦
ልጄ " በቀጣይ ደግሞ እንድትሄድ የምፈልግበት ቦታ ወደ ሙዚየም ነው። ማንም ሰው ዋጋውን ቢጠይቅህ ምንም አትመልስ 2 ጣቶችህን ብቻ ከፍ አድርገህ አሳያቸው።"
ልጅም አባቱ እንዳለው ያደርጋል።ድንጋዩን ይዞ ወደ ሙዚየም ይሄዳል። በሙዚየሙም ውስጥ 20 ደቂቃ ከቆየ በኋላ አንድ በመካከለኛው እድሜ የሚገኝ ሰው ይቀርበውና
አለቃ "የድንጋዩ ዋጋ ስንት ነው?" ብሎ ይጠይቀዋል። እሱም በአፉ ቃል ሳያወጣ አባቱ እንዳለው 2 ጣቱን ከፍ አድርጎ ያሳየዋል።ሰውዬውም " 200 ብር ከሸጥከው እወስደዋለሁ" ይለዋል። ልጅ ይደነቃል፤ ወደ አባቱም እየሮጠ ሊነግረው ይመለሳል።
አባቴ አባቴ፦
"በሙዚየም ውስጥ አንድ ሰው ድንጋዩን 200ብር እወስደዋለሁ አለኝ" በመደነቅ።
አባትም " እሺ ልጄ የመጨረሻው ቦታ እንድትሄድበት የምፈልገው ቦታ ደግሞ የከበሩ ድንጋዮች ወደ ሚሸጥበት መደብር ነው። ድንጋዩን እንደያዝክ ወደ መደብሩ ግባ ማንም ሰው ዋጋውን ቢጠይቅህ ምንም አትመልስ 2 ጣቶችህን ብቻ ከፍ አድርገህ አሳያቸው።"
ልጅም አባቱ እንዳለው ያደርጋል ፤ ድንጋዩን ይዞ የተከበሩ ድንጋዮች ወደ ሚሸጡበት መደብር ይዘልቃል። አንድ ሽማግሌ ሰውዬም ባንኮኒው ውስጥ ቆሞ ነበር። ከልጁም እጅ ድንጋዩን ባየ ጊዜ፤ እየዘለለ በመጮኽ " በእግዚአብሔር ስም እድሜዬን በሙሉ ስፈልገው የነበረውን ድንጋይ በእጅህ ይዘኸዋል! ምን ያህል ነው ለሱ የምትፈልገው? ዋጋው ስንት ነው?
"እሱም በአፉ ቃል ሳያወጣ አባቱ እንዳለው 2 ጣቱን ከፍ አድርጎ ያሳየዋል።"
ሽማግሌውም ድንጋዩን እያየ " 200ሺህ ብር! እወስደዋለሁ"
ልጁ ማመን ያቅተዋል እጁን በአፉ ይጭናል። ድንጋዩን እንደያዘ ለአባቱ ሊነግረው እየከነፈ ይሄዳል።
አባቴ አባቴ ፦
የከበሩ ድንጋዮች መደብር ውስጥ አንድ ሽማግሌ ሰው የሰጠኸኝን ድንጋይ 200ሺህ ብር ልግዛህ አለኝ።
አየህ ልጄ ፦
" አሁን የሕይወትህን ዋጋ ምን ያህል እንደሆነ ተረዳህ? የሕይወትህን ዋጋ የሚወስነው ራስህን ያስቀመጥክበት ቦታ ነው።
የምትፈልግ ከሆነ የ 2ብሩን ድንጋይ ለመሆን መወሰን ትችላለህ ወይም ደግሞ የ 200ሺህ ብሩን ድንጋይ መሆን ትችላለህ።"
በማንነትህ ብቻ የሚወዱህ ጥቂት ሰዎች ይኖራሉ ፤ ጥቂቶቹ ደግሞ ልክ እንደ እቃ ይጠቀሙብሃል ለነርሱ ምንም ጥቅም የለህም። ስለዚህ ልጄ ያንተ ድርሻ ነው፤ የሕይወትህን ዋጋ መወሰን።

21/01/2022

የነጭ ሽንኩርት የጤና ጥቅሞች
o በነጭ ሽንኩርት ውስጥ የሚገኝ ንጥረ ነገር በፈንገስ ምክንያት ለሚከሰቱ የቆዳ ሕመሞች መድኃኒትነት አለው፡፡
• በከፍተኛን ደረጃ ባክቴሪያንና ቫይረሶችን የማጥፋት ብቃት ያለው የምግብ ዓይነት ነው፡፡
o ነጭ ሽንኩርት በውስጡ የደም መርጋትን የሚከላከል ንጥረ ነገርን ይይዛል፡፡ የደም ግፊት መጨመርን ይከላከላል፡፡
o ከዕድሜ መጨመር የተነሳ የሚከሰት የደም ቧንቧ ጥበትን የመከላከል ጥቅም ያለው ነጭ ሽንኩርት ይህንን በማድረግ በደም ቧንቧ ጥበት ምክንያት የሚከሰት የልብ ሕመምን ይከላከላል፡፡
o በሰውነታችን ውስጥ ያለውን የኮሌስትሮል መጠን በመቀነስ በደም ቧንቧ ላይ የሚገኘውን የስብ መጠን እንዲቀንስ ያድርጋል፡፡
o ሰውነታችን በአለርጂ እንዳይጠቃ የማድረግ አቅምም አለው፡፡ በሰውነት ላይ ለሚወጣ ሽፍታና በአንዳንድ ነፍሳት ምክንያት የሚወጣንን ሽፍታም ይከላከላል፡፡
o ነጭ ሽንኩርት በጉንፋን የመያዝ ሁኔታን በከፍተኛ ደረጃም ይቀንሳል፡፡ከተያዝንም በኋላ እንዳይበረታብንና ቶሎም እንድንድን ይረዳል፡፡
o ነጭ ሽንኩርት በሰውነታችን የሚመነጨውን የኢንሱሊን መጠን መጨመርና በደም ውስጥ የሚገኙትን የስኳር መጠን በመቆጣጠር ለስኳር ሕመም ጠቀሜታነት ይሰጣል፡፡
• የተፈጨ ነጭ ሽንኩርት ጥርሳችንን በሚያመን ቦታ ላይ በማድረግ ባክቴሪያዎችን ማጥፋትና ሕመምን የመቀነስ ጥቀም አለው፡፡

20/01/2022

በጣም ጠቃሚ የሆነ 20 የኮምፒውተር አቋራጮች
------------------------------
CTRL + A - Select all
CTRL + Z – Undo
CTRL + Y - Redo
CTRL + S – Save
CTRL + C - Copy
CTRL + V - Paste
CTRL + U - Underline
CTRL + X - Cut
CTRL + B - Bold
CTRL + D - Fill down cell
CTRL + E - Center Alignment
CTRL + F - Find
CTRL + G - Go to current
CTRL + H - Replace
CTRL + I - Italic
CTRL + J - Full justification
CTRL + K - Create hyper link
CTRL + L - Left Alignment
CTRL + M - Tab
CTRL + N - New page
CTRL + O - Open
CTRL + P - Print
CTRL + R - Fill right cell
CTRL + S - Save
CTRL + U - Underline
CTRL + V - Paste
CTRL + X - Cut
CTRL + Y - Redo
CTRL + Z - Undo
እንዲሁም ከዚህ በፊት የለቀቅኳቸውን ቪዲዮዎችን ብትከታተሉ ምርጥ እውቀትን ልታገኙ ትችላላችሁ
አሁንም የቴሌግራምና የYouTube ቻናሌን Subscribe በማድረግ ድጋፋችሁን አሳዩኝ።
✅✅✅ #ያወቁትን ማሳወቅ ብልህነት ነው!✅✅✅

የ YouTube ቻናል ሊንክ 👇👇👇
https://www.youtube.com/channel/UCZBIP6PqUdmmagdTjbyp_AQ

ቴሌግራም ቻናል
👇👇👇👇👇👇 https://t.me/MuhammedComputerTechnology

19/01/2022

ጉልበትን መቆጠብ!

ሶስቱ ሊቆጠቡ የሚገባቸው ነገሮች (ክፍል ሶስት)

ስኬታማ ሕይወት ለመኖር መቆጠብ ስለሚገቡን ነገሮች በጀመርነው ሃሳብ መሰረት ባለፉት ፖስቶች ስለ ጊዜ እና ስለ ስሜት ቁጠባ አስፈላጊነት ተመልክተናል፡፡ ዛሬ የምንመለከተው ጉልበትን ስለመቆጠብ ነው፡፡

በሕይወታችን ውስን ከሆኑ ነገሮች አንዱ ጉልበታችን ነው፡፡ በቀን ውስጥ ማከናወን የሚገቡን ነገሮች ሳናከናውን ድካምና አቅም ማጣት ከተሰማን ጉልበት እየባከነ ነው፡፡

ጉልበትን ለመቆጠብ . . .

1. ትኩስ ጉበታችንን ለአስፈላጊው ነገር ማዋል፡፡
ጠዋት አርፈን ትኩስ ጉለበት ይዘን ስንነሳ ያንን ትኩስና ውጤታማ ጉልበት ለአስፈላጊ ነገሮች ማዋል አስፈላጊ ነው፡፡ የመጀመሪያ ጉልበታችንን አስፈላጊ ላልሆኑት ካዋልንና ከደከምን አስፈላጊውን የግድ ለማሟላት ተጨማሪ ጉልበት ስለምናጠፋ ድካም የማይቀር ነው፡፡

2. በቂ እንቅልፍ ማግኘት፡፡
የቱንም ያህል ጉልበታም ብንሆን በቀን ውስጥ ማግኘት የሚገባንን በቂ እንቅልፍ ካላገኘት ጉልበትን በመቆጠብ መጠቀም አንችልም፡፡ በቂ እረፍትና እንቅልፍ አቅማችንን እንድናጠራቅ ይረዳናል፡፡ አጉል ማምሸትና በጠዋት መነሳት ቀንደኛው ጉልበት አባካኝ ነው፡፡

3. ስፖርት መስራት
ስፓርት ስንሰራ በወቅቱ ጉልበት ብናወጣም እያባከንን ግን አይደለም፡፡ የዛሬ ድካም ለነገ ጡንቻና መነቃቃት ይሆንልናል፡፡ ስፖርት የሚሰሩ ሰዎች አካላቸው ብርቱ ከመሆኑም በላይ አእምሯቸው ንቁ ስለሚሆን ጉልበትን ይቆጥባሉ፡፡
ከላይ የተጠቀሱትን ነጥቦች በመለማመድ ስሜታችሁን ስትቆጥቡ ይህ ልምምድ ከሌላቸው ሰዎች የላቀ ነገርን ማከናወን ትጀምራላችሁ፡፡

ጉልበት ይቆጠብ!

ነገ በሌላ ፖስት እሰከማገኛችሁ ሰላም ሁኑልኝ፡፡

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

16/01/2022

የቀይ ሽንኩርት ጥቅም !
******************
ሽንኩርትን ሲከትፉ ያስለቅስዎታል ጥሬውን ሲመገቡት ደግሞ የሚረብሽ የአፍ ሽታ እንዲኖረን ያደርጋል። ከእነዚህ ሁለት ችግሮች ውጪ ቀይ ሽንኩርት አስገራሚ የጤና እና የውበት ጥቅሞች ያበረክትልናል።

ቀይ ሽንኩርት ፀረ-ኢንፍላሜሽን፣ ፀረ-አለርጂክ፣ ፀረ-ኦክሲዳንትና ፀረ-ካንሰር ባህሪ አሉት። በተጨማሪም በቫይታሚን ኤ፣ ቢ6፣ ቢ ኮምፕሌክስ እና ሲ፣ ብረት (አይረን)፣ ፎሌት እና ፖታሲየም የበለፀገ ነው። የሰልፈር፣ ግላቮኖይድ እና ፋይቶኬሚካል ምርጥ መገና ነው።

1. የፀጉር እድገትን ያሻሽላል!

ቀይ ሽንኩርት የፀጉር መሳሳትን በከፍተኛ ሁኔታ ከመቀነሱ ባሻገር የፀጉር እድገትን ይጨምራል። በሽንኩርት ውስጥ የሚገኘው ሰልፈር (Sulfur) በራስ ቅል ውስጥ የደም ዝውውር እንዲጨምር ያደርጋል፣ ለፀጉር እድገት አስፈላጊ የሆነውን ኮላጅን (Collagen) ምርት እንዲጨምር ያደርጋል።

2. የደም ስኳርን ያመጣጥናል!

ቀይ ሽንኩርት የስኳር በሽታ ላለባቸው ሰዎች በጣም ጠቃሚ ነው። በሽንኩርት ውስጥ የሚገኝው የሰልፈር ውህድ አላይል ፕሮፓይል ዳይሰልፋይድ የኢንሱሊን መመረትን በመጨመር የደም ስኳር መጠንን በስኳር አይነት 1 እና 2 ይቀንሳል። በተጨማሪም የቀይ ሽንኩርት ጭማቂ ክሮሚየም በጥቂቱ የያዘ ሲሆን ሰውነታችን ግሉኮስን እንዲያመጣጥን ይረዳዋል።

3. ካንሰርን ይከላከላል!

ቀይ ሽንኩርት የተለያዩ ዓይነት ካንሰሮችን እንደሚከላከል ተረጋግጧል ከነዚህም መካከል የሳንባ፣ ሆድ፣ ጡት፣ ጉነትና ጭንቅላት ካንሰር ተጠቃሽ ናቸው። የቀይ ሽንኩርት ፌኖሊክና ፍላቮኖይድ ይዘቶች ከፀረ-ኦክሲዳንት ባህሪው ጋር በመተባበር የካንሰር ሴሎችን ይዋጋሉ።

4. በልብ ህመም መጠቃትን ይቀንሳል!

ቀይ ሽንኩርትን በመደበኛ ሁኔታ መመገብ በደም ግፊት፣ የልብ ችግርና ስትሮክ የመያዝ እድላችንን ይቀንሳል፡፡ በቀይ ሽንኩርት ውስጥ የሚገኝው ኪዊርሲቲን ፀረ-ኢክሲዳንትና ፀረ-ኢንፍላማቶሪ ባህሪ ስላለው ለልብ ጤንነት በጣም አስፈላጊ ነው፡፡

5. ጠንካራ የበሽታ መከላከል አቅም ይገነባል!

ሽንኩርት በፖሊፌኖል ይዘቱ ምክንያት ሰውነትዎን ከፍሪራዲካሎች በመከላከል በሽታ የመከላከል አቅምዎን ይጨምራል፡፡ በተጨማሪም ሽንኩርት ጥቂት የሰሊኒየም ሜኔራል ይዟል ይህም በሽታን የመከላከል ግብረ መልስን በማነሳሳት በሽታ የመከላከል አቅምን ይጨምራል፡፡

24/10/2021

ሞሪንጋ ( ሺፈራሁ) ባለ ዘረፍ ብዙ መድኃኒተ እፅ
ከሰሜን ሕንድ ለዓለም የተበረከተው የሞሪንጋ ተክል ከብዙ ሺህ ዓመታት በፊት ጀምሮ ለጤና ጠቃሜታ ሲውል የነበረ ምስጉን
ተክል ነው፡፡

የሞሪንጋ ተክል በአልሚ ምግቦች፣ በቫይታሚኖችና
በአሚኖ አሲዶች የበለጸገ በመሆኑ ለሰውነታችን የሚፈለገውን ሁሉ በሟሟላት ተመልሶ እንዲታደስና አስፈላጊውን ኃይል
እንዲያገኝ የሚያደርግ ችሎታ ያለው ተክል ነው፡፡ ይህን
የተገነዘቡት ምዕራብአዊያን በተጨመሪ ምግብነት
(supplementary food) አድርገው በመውሰድ በዱቄትና
በኪንኒን መልክ አዘጋጅተው ለገበያ እስከማቅረብ ደርሰዋል፡፡
የሞሪንጋን ቅጠል ዱቄት በማንኛውም የእለት ተዕለት ምግባችን ውስጥ በመጨመር ልንመገበው እንችላለን፡፡ በተለያዩ የሾርባ ምግቦች ውስጥ በመጨመር፣በሻይ መልክ በፈላ ውሃ በጥብጦ
በመጠጣት እና በጁስ ዓይነት በንፁህ ውሀ በጥብጦ አቀዝቅዞ
በማንኛውም ሰዓትና ጊዜ መጠጣት ይቻላል፡፡

በሳይንስ የተረጋገጡ የሞሪንጋ የጤና ጥቅሞች
1. የተፈጥሮ የሰውነት ኃይል ያጎለብታል፡፡
2. የሰውነት በሽታ የመቋቋም ችሎታን ያጠናክራል፡፡
3. የሰውነት ቆዳን ጤንነት ይጠብቃል፡፡
4. የደም ግፊትን ይቆጣጠራል፡፡
5. በደም ውስጥ ያለውን የስኳር መጠን ያስተካክላል፡፡
6. ራስ ምታትንና ማይግሬይንን ያስወግዳል፡፡
7. በእሪህና በመሳሰሉት የሚከሰት የህመም ስቃይን
ያስታግሳል፡፡
8. የሰውነት እጢዎችን ሁኔታ ይቆጣጠራል፡፡
9. የጨጓራ አልሰርና የመሳሰሉትን ይፈውሳል፡፡
10. የሰውነት ጡንቻዎችን በማዝናናት የተስተካከለና ጤናማ የለሊት እንቅልፍ እንዲኖረን ይረዳል፡፡

በሳይንስ የተረጋገጡ የሞሪንጋ የምግብ ይዘት ጥቅሞች
1. ከብርቱካን ከሚገኘው ቫይታሚን ሲ ሰባት እጅ የበለጠ
2. ከካሮት ከሚገኘው ቫታሚን ኤ አራት እጅ የበለጠ
3. ከስፒናች ከሚገኘው ብረት ሦስት እጅ የበለጠ
4. ከወተት ከሚገኘው ካልስየም አራት እጅ የበለጠ
5. ከሙዝ ከሚገኘው ፖታስየም ሦስት እጅ የበለጠንጥረ ነገር ይዟል፡፡

ከሀሎ ዶክተር ዶከተር መሠረት ቤዘ
የደቡብ ክልል ጤና ቢሮ

20/10/2021

በአሁኑ ጊዜ አሳሳቢ የሆነው የኩላሊት ህመም ቀድሞ መከላከያ መንገዶችን ያውቃሉ ?

ኩላሊታችንን የሚጎዱ 10 ልማዶች

////////////////////////////////////////////

ኩላሊቶቻችን በታቸኛው ጀርባችን ከጎድን አጥንታችን በታች የሚገኙ ሁለት ባቄላ መሰል አካሎች ናቸው። ኩላሊቶቻችን ደማችንን የማጣራት ስራ ሰርተው ቆሻሻውን በሽንት መልክ እንዲወገድ ያደርጋሉ።

የኩላሊት ሌላኛው ጥቅም ሰውነታችን ውስጥ የሚገኝ የማያስፈልግ ውሃ ማስወገድ ነው። ሰውነታችን ውሃ ሲያስፈልገው በማጠራቀም ይታወቃሉ። በተጨማሪም ሰውነታችን ውስጥ ያለውን የካልሲየም እና ፎስፌት መጠን ይቆጣጠራሉ። የደም ግፊት የሚቆጣጠሩ ሆርሞኖችንም በማመንጨት ይታወቃሉ።

በጤንነት ለመቆየት የኩላሊቶቻችንን ጤንነት መጠበቅ አለብን። የኩላሊት ህመም ከሚያመላክቱ ስሜቶች መሃከል የሽንት ቀለም መቀየር፣ የሽንት ብዛት መቀየር፣ የማዞር ስሜት፣ ማስመለስ፣ የደም ማነስ፣ የመተንፈስ ችግር፣ የመቀዝቀዝ ስሜት፣ የድካም ስሜት፣ ቆዳን ማሳከክ እና የተለያዩ የህመም ስሜቶች ይገኙበታል።

እነኚህ ስሜቶች ከተሰሙዎት ዶክተር ማማከር አለብዎት። የኩላሊት ህመም ብዙ መንስኤዎች አሉት። ብዙ ልማዶች ለኩላሊት ህመም ተጠያቂ ይሆናሉ።

👉👉1) ሽንትን መቋጠር
ሽንት ስይሸኑ ረጅም ግዜ መቆየት ኩላሊት ከሚጎዳባቸው ዋነኛ ምክንያቶች ውስጥ ይጠቀሳል።

ሽንት በፊኛ ውስጥ ረጅም ሰአት ሲቆይ በውስጡ የሚያድጉት ባክቴሪያዎች ይበራከታሉ። እንዚህ ባክቴሪያዎች የሽንት ቧንቧ ወይም የኩላሊት ኢንፌክሽን ሊያመጡ ይችላሉ። ሽንትን መያዝ ኩላሊት ላይ በሚያደርሰው ጫናም ኩላሊት ተጎድቶ ሽንትን የመቆጣጠር ችሎታችንን ሊያጠፋ ይችላል።

በየግዜው ሽንትዎን የሚይዙ ከሆነ በፍጥነት ልማዱን ማቆም አለብዎት። በስራ ምንም ያህል ቢጠመዱም የተፈጥሮ ጥሪን ሰምቶ ማስተናገድ ተገቢ ነው።

👉👉2) በቂ ውሃ አለመጠጣት

በቂ ውሃ አለመጠጣት ኩላሊት ላይ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል። የኩላሊት ዋና ስራ የሰውነታችንን ቆሻሻ ማስወጣት አና ኢሪትሮሳይት ማምረት ነው።

ሰውነታችን ውሃ ሲያንሰው ወደ ኩላሊታችን የሚሄደው የደም መጠን ይቀንሳል። ደማችን ይበልጥ ይረጋል። በዚህም ሁኔታ ኩላሊታችን ደማችን ውስጥ ያለውን ቆሻሻ ማጣራት ይቸገራል። ቆሻሻው በጨመረ ቁጥር ለጤናችን አደጋ ይሆናል።

እንደ ናሽናል ኩላሊት ፋውንዴሽን አንድ ሰው በቀን ቢያንስ ከ10 እስከ 12 ብርጭቆ ውሃ መጠጣት አለበት። ነገር ግን ውሃ ማብዛትም ለኩላሊት ህመም ሊፈጥር ይችላል። ስለዚህ ማብዛት የለብንም።
ይህ ቆንጆ ኢትዮጵያ የቁምነገሮች ፔጅ ነው ። ንባብዎን ሲጨርሱ ፔጃችንን ላይክ ቢያደርጉ በየእለቱ አዳዲስ ቁምነገሮችን እናደርሶታለን ። አሁን ንባብዎን ይቀጥሉ እናመሰግናለን ።

👉👉3) ጨው ማብዛት

ብዙ ጨው መመገብ ኩላሊታችን ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሊያመጣ ይችላል። በምንመገበው ጨው የሚገኘውን ሶዲየም 95% ያህሉ በኩላሊታችን ነው የሚቀየረው። ጨው ስናበዛ ኩላሊታችን ጨውን ለማጣራት ይበልጥ መስራት ይኖርበታል። ኩላሊቶቻችን ከአቅማቸው በላይ ሲሰሩ ሰውነታችን ውስጥ ከፍተኛ ውሃ ጥርቅም ይፈጠራል። ይህ ጥርቅም የደም ግፊታችንን ይጨምራል ለኩላሊት ህመምም ተጋላጭነታችንን ይጨምራል።

👉👉4) ፔይን ኪለር(ህመም የሚቀንሱ) መድሃኒቶችን መጠቀም ማዘውተር

ብዙዎቻችን በየግዜው የሚሰማንን እራስ ምታት እና የህመም ስሜቶች ለማስታገስ ፔይን ኪለርን አዘውትረን እንጠቀማለን። እንደዚህ ስናደርግ ግን ሳናውቀው እኩላሊታችንን ጨምሮ የተለያዩ የሰውነት አክሎችን እየጎዳን ነው።

የህመም ማስታገሻ መድሃኒቶች ወደ ኩላሊት የሚሄደውን የደም ዝውውር መጠን ይቀንሳሉ። የኩላሊትን ስራ ይረብሻሉ። አልፎም በከፍተኛ ደረጃ መድሃኒቶቹን መጠቀም የሰገራ መቆጣጠር ብቃታችንን ያጠፋል። ክሮኒክ ኢተርስቲሻል ኔፍራይቲስ የሚባል ዘላቂ የኩላሊት ህመም ያስከትላል።

የኩላሊት ህመም ካለብዎ ዶክተርዎን ሳያማክሩ የህመም ማደንዘዣ መድሃኒቶችን አይጠቀሙ። እኩላሊታችን ያለችግር እየሰራም ቢሆን መድሃኒቶቹን በትንሹ ነው መጠቀም ያለብን።

👉👉5) ፕሮቲን ያላቸው ምግቦች ማብዛት

ፕሮቲን ለሰውነታችን እና ለጤናችን አስፈላጊ የሆነ ንጥረ ነገር ነው። ግን ስጋ ወይም ሌላ ፕሮቲን ጠገብ ምግቦችን ከልክ በላይ የምንበላ ከሆነ እራሳችንን ለኩላሊት ህመም እያጋለጥን ነው።

የኩላሊት አንዱ ጥቅም ፕሮቲንን በመፍጨት ወደ ናይትሮጅን ቀይሮ ማስወገድ ነው። ከፍተኛ የፕሮቲን ተጠቃሚ ከሆንን እኩላሊታችን ላይ ከፍተኛ ጫና እያደረግንበት ይሆናል። የኩላሊት ህመም ያለባቸው ሰዎች ቀይ ስጋ ከመብላት መቆጠብ ይኖርባቸዋል።

👉👉6) መጠጥ ማብዛት

በመጠን መጠጣን ችግር የለውም። መጠጥ ሲበዛ ግን እኩላሊታችንን አደጋ ላይ ይጥላል። መጠጥ እኩላሊታችን እና ጉበታችን ላይ ከፍተኛ ጫና ያሳድራል። በከፍተኛ ደረጃ መጠጣት ሪናል ቲዩቡልስ የሚባለው አካላችን ላይ የዩሪክ አሲድ ክምችት እንዲፈጠር ያደርጋል። ይህም የኩላሊት ስራ ማቆም ሊያስከትል ይችላል። አልኮል ሰውነታችን ላይ ውሃ ማነስ ስለሚፈጥር በዛ ረገድም ለእኩላሊታችን ጥሩ አይደለም።

መጠጥ የሚጠጡ ከሆን በመጠኑ ያድርጉት። ለወንድ በቀን ሁለት ግዜ ለሴት ደግሞ በቀን 1 ግዜ መጠጣት ተገቢ ነው ተብሎ ይታመናል።

👉👉7) ሲጋራ ማጨስ

እንደ ሴንተር ፎር ዲዚዝ ኮንትሮል(ሲዲሲ) ማጨስ ኩላሊትን ጨምሮ ለእያንዳንዱ የሰውነት አካል መጥፎ ነው። ብዙ ጥናቶች በማጨስ እና ኩላሊት በሽታ መሃከል ከፍተኛ ግንኙነት እንዳለ ይናገራሉ።

ኤንድ ስቴጅ ሪናል ዲዚዝ(ኢኤስአርዲ) ለሚባለው በሽታ ማጨስ እንደ አንደኛ መንስኤ ተጠቃሽ ነው። ማጨስ የደም ግፊትን እና የልብ ትርታን ይጨምራል። በሰውነታችን ውስጥ የደም ዝውውር ይቀንሳል። የኩላሊት በሽታ ካለብን ይበልጥ ያባብሰዋል።

👉👉8) ከመጠን በላይ ቡና መጠጣት
ቡናን ማብዛት የደም ግፊትን ይጨምራል። እሱ ደግሞ በተራው እኩላሊታችን ላይ ጫና ይፈጥራል። ከግዜ በኋላ እኩላሊታችን እየተጎዳ ይመጣል።

በ2002 በኩላሊት ኢንተርናሽናል እንደታተመው ጥናት ቡና መጠጣት ከኩላሊት ጠጠር ጋር ግንኙነት አለው።

ቡናን በመጠኑ መጠጣት ለአብዛኛው ሰው ችግር አያመጣም። በቀን ከ 1 እስክ ሁለት ስኒ ቡና እና 3 ስኒ ሻይ መጠጣት ችግር አያመጣም።

👉👉9) ቀላል ኢንፌክሽኖችን በግዜው አለመከታተል

ጉንፋን፣ ቶንሲል እና ለመሳሰሉት ቀላል ኢንፌክሽኖች ተገቢውን ክትትል አለማግኘት ኩላሊትን አደጋ ላይ ሊጥል ይችላል።

ብዙ የኩላሊት ህመም ያላቸው ሰዎች ሌላ ህመም ሲያማቸው ባለማረፍ ይታወቃሉ። በተጨማሪም የኩላሊት ህመም ያለባቸው ሰዎች በአየር ጸባይ ለውጥ በቀላሉ ይታመማሉ። ቀላል ህመም የሚፈጥሩ ባክቴሪያዎች እና ቫይርሶች ኩላሊት ላይ ጉዳት ይፈጥራሉ። እነዚህን ቀላል ህመሞች ተከታትሎ መፍትሄ መፍጠት ያስፈልጋል።

👉👉10) የእንቅልፍ እጦት

በስራ መጠመድ ምክንያት ብዙ ሰዎች የእንቅልፍን አስፈላጊነት ይረሳሉ። ከ6-8 ሰአት መተኛት ለጤናችን አስፈላጊ ነገር ነው።

በእንቅልፍ ግዜ የተጎዱ የሰውነት አካላችን ይታደሳሉ።

በቂ እንቅልፍ አለማግኘት ይህ እድሳት በተገቢው ሁኔት እንዳይካሄድ እንቅፋት ይሆናል።
ኩላሊት እና ሌሎች የሰውነታችን አካሎች ይጎዳሉ።

ሌሎች ጥናቶች እንደሚጠቁሙት እንቅልፍ እጦት የደም ግፊትን ይጨምራል።
ይህም ለኩላሊት መጥፎ ነገር ነው። እንዲህ እንቅልፋችንን በተገቢው በጊዜ እና ስዓት ሰጥተን በቂ እንቅልፍ ማግኘትን ኩላሊት አስይዞ መቆመር እንዳይሆን ለገጻችን ተከታታዮች እና ተወዳጃጆች ዶክተር ሀያት በፌስቡክ ገጻቸው ያሰፈሩትን የደቡብ ክልል ጤና ቢሮ አስነብቧል ።

15/10/2021

«የምትሰማውን ነገር ሁሉ ለማመን ፈጽሞ አትቸኩል፣ ምክንያቱም ውሸት ከእውነት ፈጥኖ ይሰራጫልና!»
የሙሌ ቤስት ፌስቡክ ገጽ~Mule Best✍
❀︵♡┈┈┈••✦✿✦••┈┈┈♡︵❀

☞በአንድ ወቅት አንዲት በግ እና አንዲት ፍየል አብረው ሲኖሩ ባለቤቶቻቸው በጣም ይጨቁኗቸው ስለነበረ በጣም ገርጥተው፣ ከስተውና ተጎሳቁለው በጣም፣ በጣም አሳዛኝ መልክ ይዘው ነበር፡፡ ባለቤቶቻቸውም በበጓና በፍየሏ እጅግ መጎሳቆል ተስፋ ቆርጠው ስለነበረ አይንከባከቧቸውም ነበር፡፡ ሌሎቹን እንስሳት ሩቅ ቦታ ወደሚገኝ ፍል ውሃ ሲወስዷቸው በጓንና ፍየሏን ግን ከቤት አስረው ያቆዩዋቸው ነበር፡፡ ይህ ለበጓና ለፍየሏ እጅግ በጣም የሚያበሳጭ ነበር፡፡ ምክንያቱም እነርሱም ከሌሎቹ እንስሳት ጋር ሄደው ከለምለሙ መስክ ሳር መጋጥና ውሃውንም መጠጣት ይፈልጉ ነበር፡፡ ነገር ግን ጉዞው ወደ ሁለት ቀናት ገደማ ስለሚፈጅና ባለቤቶቹም ብዙ እንስሳትን ወደ ስፍራው መንዳት ስለማይችሉ በጓንና ፍየሏን ሁልጊዜ ትተዋቸው ይሄዱ ነበር፡፡ ብዙ ወተት የምትታለበውን ላም፣ ወፍራሞቹን በጎችና ፍየሎች እንጂ ምስኪኖቹን በግና ፍየል ይዘዋቸው አይሄዱም ነበር፡፡ እነዚህ ሁለት ጎስቋላ እንስሳት ሁልጊዜ በግቢው ውስጥ ታስረው የሚበሉት ሳይኖራቸው ይውሉ ነበር፡፡

↪በዚህ ምክንያት በጣም የተበሳጩትና ግቢው ውስጥ ታስሮ በቤቱ አካባቢ ያለውን ነገር ከመለቃቀም ባለፈ ምንም የማያገኙት ሁለቱ እንስሳት ከእለታት አንድ ቀን ጠፍተው ወደ ፍል ውሃው ስፍራ በመሄድ የሚፈልጉትን ያህል መብላትና መጠጣት ፈለጉ፡፡ ስለዚህ በማለዳ ተነስተው ጉዟቸውን በመጀመር መንገዱ በጣም ረጅም ነበርና ሲሄዱ፣ ሲሄዱ ውለው በድንገት ከአንድ ትልቅ አንበሳ ዘንድ ደረሱ፡፡ አንበሳውም “ጎሽ! ፍየልና በግ አገኘሁ! እበላቸዋለሁ!” ብሎ በደስታ አገሣ፡፡በጓና ፍየሏም ፈጠን ብለው “ምን እንደተፈጠረ አልሰማህም እንዴ?” ሲሉት እርሱም “አልሰማሁም፡፡ ምን ተፈጠረ?” አላቸው፡፡ “ኧረ ምድር እየተሰነጠቀች ነውና ሰማዩ ሊወድቅ ስለሆነ ነው እኛ እየሸሸን ያለነው፡፡ ሁሉም ከዚህ የተፈጥሮ አደጋ እየሸሸ ነው፡፡” በጓና ፍየሏ ይህንን ብለው መሮጥ ሲጀምሩ አንበሳውም እውነት መስሎት ወደ ጫካው መሮጥ ጀመረ፡፡
:
↪በጓና ፍየሏም ሮጠው፣ ሮጠው፣ሮጠው ከአንድ ነብር ዘንድ ደረሱ፡፡ ነብሩም “ጎሽ! ምግቤን አገኘሁ!” ብሎ ዘሎ ጉሮሮአቸውን ሊዘነጥለው ሲል ሁለቱም “ኧረ ቆይ አያ ነብር! ክፉውን ዜና አልሰማህም እንዴ? መሬት ተሰንጥቃ ሰማዩ ሊወድቅ እኮ ነው! ስለዚህ አንተ እኛን የምትበላ ከሆነ የተፈጠረው አደጋ ይደርስብህና ይገድልሃል፡፡ ስለዚህ ሮጠህ ህይወትህን ብታተርፍ ይሻላል፡፡” አሉት፡፡ ነብሩም እነርሱን ትቷቸው ህይወቱን ለማዳን ሩጫውን ቀጠለ፡፡
:
↪አሁንም ሁለቱ እንስሳት ሲሮጡ፣ ሲሮጡ አንድ ጅብ ዘንድ ደረሱ፡፡ ጅቡም “ጎሽ! በጣም ተርቤአለሁና የምበላው ያስፈልገኛል፡፡” አለ፡፡ እነርሱም “ኧረ ቆይ አያ ጅቦ! እኛን ለመብላት ጊዜ የለህም፡፡ የተፈጠረውን ነገር አልሰማህም እንዴ? ሰማዩ ሊወድቅ ነው፡፡ ምድሪቱም እየተሰነጠቀች ነውና ይልቅ ሸሽተህ ህይወትህን አትርፍ፡፡” አሉት፡፡ ጅቡም “እሺ” ብሎ ሩጫውን ተያያዘው፡፡
:
↪ከዚያም በጓና ፍየሏ ሩጫቸውን ቀጥለው ብዙ ከተጓዙ በኋላ ፍል ውሃው ይህን ያህል የሚርቅና ከለምለሙ የሳር ምድርም ለመድረስ ይህን ያህል ጊዜ የሚወስድባቸው አልመሰላቸውም ነበር፡፡ ከተወሰነ ጊዜም በኋላ አንድ ቀበሮ አጋጠማቸው፡፡ ቀበሮውም “ጎሽ! ሁለታችሁንም እበላችኋለሁ፡፡” ሲል እነርሱም “ኧረ አይሆንም! ይህን ለማድረግ ጊዜ የለህም፡፡ የተፈጥሮ አደጋ ተነስቶ ምድሪቱ በመሬት መንቀጥቀጥ እየተሰነጠቀች ስለሆነ ሰማዩ እየወደቀ ነውና አንተም እንደሌሎቹ ሮጠህ ህይወትህን ብታተርፍ ይሻልሃል፡፡” አሉት፡፡ ቀበሮውም ሽሽቱን ተያያዘው፡፡
:
↪ከዚያም ለረጅም ጊዜ ሮጠው፣ ሮጠው ሲያበቁ ፍል ውሃው ካለበት ከአንድ ጥልቅ ሸለቆ አጠገብ ደረሱ፡፡ በዚህ ጊዜ አቀበታማውን ገደል በሩጫ በመውረድ ከውሃው ከደረሱ በኋላ የሚችሉትን ያህል ጠጥተው እስኪጠግቡም ድረስ ሳሩን ጋጡ፡፡ ጣፋጩን ፍል ውሃ ጠጥተው፣ ጠጥተው እንዲሁም አጠገቡ ያለውን ለምለም ሳር ግጠው፣ ግጠው፣ ሲያበቁ በዚያ ስፍራ ለረጅም ጊዜ ቆዩ፡፡ በመጨረሻም ወደቤታቸው መመለስ እንዳለባቸው ወስነው መንገዱን ተያያዙት፡፡ ነገር ግን የገደሉን አቀበት ሽቅብ መውጣት እንደመውረዱ ቀላል አልነበረም፡፡ ሙሉ ቀን ሲሮጡ ስለዋሉ ከመድከማቸውም በላይ ሆዳቸው በበሉት ሳርና በጠጡት ውሃ ተወጥሮ ነበረ፡፡ ሆኖም ቀስ በቀስ፣ ደረጃ በደረጃ ወደ ላይ ከፍ እያሉ በመውጣት ሆዳቸው በጥጋብ እንደተወጠረ ከረጅም ጊዜ በኋላ አቀበቱን ወጥተው ጨረሱ፡፡ ከተደላደለው መስክ ላይ በደረሱ ጊዜም በጣም ደክሟቸውና ቀኑም መሽቶ ነበር፡፡
:
↪በመጨረሻም ቀኑ በመሸ ጊዜ ሌሊቱን ከቤት ውጪ ሜዳ ላይ አድረው ስለማያውቁና በአውሬዎች እንበላለን ብለው ስለሰጉ ምን ማድረግ እንዳለባቸው ግራ ገባቸው፡፡ ከዚያም ወደ አንድ ግዙፍ ዛፍ አጠገብ ሄደው ጥቂት ከተነጋገሩ በኋላ “እንግዲህ እዚህ ዛፍ ስር ካደርን አውሬ ሊበላን ስለሚችል ቅርንጫፎቹ ላይ ብንወጣ ይሻላል፡፡” አሉ፡፡ ታዲያ በተፈጥሮአቸው ፍየሎች አንደዳንድ ነገሮች ላይ መውጣት ቢችሉም በጎች ግን አይችሉም፡፡ ስለዚህ ፍየሏ ዛፍ ላይ በቀላሉመውጣት ስትችል ምስኪኗ በግ ግን ሸሆናዋ ስለማይቆነጥጥላት ዛፉ ላይ ለመውጣት ብዙ ትግል ገጠማት፡፡ በመጨረሻም ቀስ በቀስ እየቧጠጠች ከዛፉ ላይ ወጣች፡፡
:
↪ከዚያም ሁለቱም ለትንሽ ጊዜ ዛፉ ላይ ከተኙ በኋላ ከበታቻቸው አንዳች ድምፅ ሰምተው ቁልቁል ሲመለከቱ የእንስሳት ስብሰባ መሆኑን አዩ፡፡ ሁሉም እንስሳት፤ አንበሳ፣ጅብ፣ነብር፣ ተኩላ፣ ቀበሮንም ጨምሮ በታላቅ ስብሰባ ላይ ሆነው ሲወያዩ ተመለከቱ፡፡ በዚህ ጊዜ በጓና ፍየሏ በጣም ደንግጠውና ፈርተው ቀስ ብለው በቅርንጫፎቹ ላይ በመለጠፍ ከስራቸው የሚካሄደውን ስብሰባ መከታተል ጀመሩ፡፡ ከተሰብሳቢዎቹም አንዱ “እና ምን ብናደርግ ይሻላል?” ሲል ሌላኛው “እባክህ ዝም ብለህ አዳምጥ፡፡” አለው በለሆሳስ፡፡ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ እንስሳቱ መናገር ጀመሩ፡፡ በመጀመሪያ አንበሳው “ያምላክ ያለ! ዛሬ እንዲህ ልታለል?!” አለ፡፡ ሌሎቹም “እውነት? ምን ሆንከ?” ሲሉት “አንዲት በግና ፍየል መንገዴ ላይ አጋጥመውኝ ልበላቸው ስል ምድር እየተሰነጠቀች መሆኗንና ሰማይም ሊወድቅ እንደሆነ አስጠነቀቁኝ፡፡ እኔም የሚናገሩት ነገር እውነት መስሎኝ ህይወቴን ለማትረፍ ሮጥኩ፡፡ ለካስ እነርሱ ህይወታቸውን ለማዳን የፈጠሩት ውሸት ነበር፡፡” አለ፡፡ ነብሩም ወዲያው ቀበል አድርጎ “የፈጣሪ ያለህ! እኔም ላይ ይኸው ነገር ደርሶብኛል፡፡ እኔም ሳዳምጣቸው በተመሳሳይ ሁኔታ አታለውኛል፡፡ በእነዚያ ደደብ በግና ፍየል መታለሌ ሞኝነት ኖሯል፡፡”አለ፡፡ ጅቡና ቀበሮውም ይኸው ታሪክ በእነርሱም ላይ እንደተፈፀመ ተናገሩ፡፡ በመጨረሻም እንስሳቱ በሙሉ “ይህ በጣም አሳፋሪ ነውና በሌላ ጊዜ እነዚያን ሁለት ወሽካቶች ይዘን እንበላቸዋለን፡፡” ብለው ተስማሙ፡፡
:
↪በዚህ ጊዜ የበጓ ፊኛ በጠጣችው ውሃ ምክንያት በሽንት ስለተሞላ መሽናት ፈለገች፡፡ ነገር ግን ከዛፉ ላይ ሆና ቁልቁል ብትሽና ሽንቷ ከታች ያለው አንበሳ ላይ ስለሚያርፍ ሁሉም ዛፉ ላይ ወጥተው በአንድ ደቂቃ ይሰለቅጧቸዋል፡፡ ስለዚህ በጣም ተጨነቀች፡፡ ሽንቷን ችላ ልትይዘው ብትሞክርም ፊኛዋ ሊፈነዳ ሆነ፡፡ ስለዚህ ፍየሏን “ፍየሊት ሆይ! ፊኛዬ ስለሞላ ወደ ሽንት ቤት መሄድ አለብኝ፡፡” ብላ በሹከሹክታ ነገረቻት፡፡ ፍየሏም “የማትረቢ! አንዳች ነገር አደርጋለሁ ብለሽ ታስጨርሺናለሽ፡፡ ትንሽ ታገሽ፡፡” አለቻት፡፡ “በፍፁም፣ በፍፁም፣ በፍፁም ከዚህ በላይ መታገስ አልችልም፡፡ መሽናት አለብኝ፡፡” አለች፡፡ “አንቺ ደደብ በግ፣” አለች ፍየሏ፣ “ቢያንስ ራሳችንን ማዳን ስላለብን ልታደርጊ የምትችይው አንድ ነገር ብቻ ነው፡፡ ይኼውም ጭንቅላትሽን ቀስ ብለሽ ወደታች ዘቅዝቀሽ በቀስታ በመሽናት ሽንትሽ በሙሉ ያለ አንዳች ጠብታ የሰውነትሽ ፀጉር ውስጥ እንዲቀር ማድረግ ነው፡፡ ሽንትሽን ከዚህ በላይ መቋጠር ካልቻልሽ ያለን ብቸኛው አማራጭ ይህ ነው፡፡” በጓ ግን “አይሆንም! አይሆንም! አልችልምና መሄድ አለብኝ፡፡” ብላ ቀስ ብላ በመዘቅዘቅ እላዩዋ ላይ ለመሽናት ልትሞክር ስትገላበጥ ሸሆናዎቿ ቅርንጫፎቹን ቆንጥጠው መያዝ ባለመቻላቸው ተንሸራታ ዱብ በማለት ከዛፉ ስር ካሉት እንስሳት መሃከል ወደቀች፡፡ ታዲያ በጓ ወድቃ ከመሬቱ ጋር በከፍተኛ ድምፅ ስትላተም እንስሳቱ እውነትም ሰማይ የወደቀ መስሏቸው ህይወታቸውን ለማትረፍ በየአቅጣጫው መሸሽ ጀመሩ፡፡ በዚህ ዓይነት በጓና ፍየሏ ከመሞት ተርፈው ሌሊቱ ሲነጋ በሰላም ወደ ቤታቸው ተመለሱ ይባላል።

♡┈┈┈••✦✿✦••┈┈┈♡
:
☞አዎን ወዳጆቼ ውሸት ማለት በዕለት ተዕለት የህይወት መስተጋብር ውስጥ ያልተገባ መረጃን መልቀቅ ማለት ነው፡፡ የእለት ተዕለት ማህበራዊ መስተጋብር የሚከወነው በጓደኛሞች፣ በስራ ባልደረቦች፣ በቤተሰብ አባላት፣ በጎረቤታሞች መካከል ነው፡፡ በነዚህ መካከል የሚካሄድ ትክክል ያልሆነ የመረጃ ዝውውር ነው ውሸት የሚባለው፡፡
:
↪ውሸት በማህበራዊ መስተጋብር ስሜታዊ በሆኑ ጉዳዮች ውስጥ የሚደረግ ስሜትን ያዘለና በአንደበት የሚነገር ነው፡፡ ውሸት ቢደጋገም ያው ውሸት ነው። ሲደጋገም ተጽእኖ አያሳድርም ማለት አይደለም። መንግሥታት ሕዝባቸውን፣ ነጋዴ ገበያተኛውን፣ ወዘተ፣ በመደጋገም ብዛት ለማሳመን ይጥራሉ። እውነቱን ለይቶ ማወቅ ትጋትና ንቃት የሚጠይቀው ለዚህ ነው። መደጋገም እንደሚንጠባጠብ ውኃ ነው። የሚንጠባጠብ ውኃ አለት ያፈርሳል። አለቱ የሚፈርሰው በመጀመሪያው ጠብታ ላይሆን ይችላል፤ በሁለተኛው ላይሆን ይችላል። ሲደጋገም ግን ድንጋይ ለውኃ መንገድ ይለቅለታል። ውኃም በተከፈተለት ቀዳዳ ገብቶ አለቱን ከመሠረቱ ያናጋዋል።
:
☞ውሸት ስንሰማ ምን እናደርጋለን? ውሸት መሆኑን እንዴት እንለያለን? እውነትን ለማወቅ ለሚሻ ይህ የማያቋርጥ ጥያቄ ነው። ውሸት ኃይሉ የሚበረታው እውነቱን በማያውቁ ወይም ለማወቅ በማይጥሩ ላይ ነው፤ ደግሞ እውነቱን እያወቁ ችላ በሚሉና ውሸትን በሚለማመዱ ላይ እና ምን አገባኝ በሚሉ ላይ ነው። እነዚህም ከእውነት ጋር ስላልቆሙ ውሸትን ለመቋቋም ኃይል አይኖራቸውም። የውሸት ማዕበል ያንሳፍፋቸዋል፤ ጠርጎ ይዞአቸው ይሄዳል። የስነምግባር ወገብ በላላ መጠን እውነትን ከውሸት ለመለየት እያዳገተ ይመጣል። ኑሮም እያደር የውሸት ኑሮ ይሆናል።
:
☞ውሸታሞች በሁለት ይከፈላሉ፡፡ የመጀመሪያዎቹ በማንኛውም ቦታ፣ ጊዜና ሁኔታ የሚዋሹ ሲሆን ሁለተኛዎቹ በተወሰነ ጊዜና ቦታ ብቻ የሚዋሹ ናቸው፡፡ እነዚህ ውሸቶች ቀደም ብሎ እንደተጠቀሰው የተለያዩ ናቸው፡፡ በዚህ ላይ ነጭና ጥቁር ውሸት አለ። ጥቁር ውሸት ዐይን ያወጣ ዓይነቱ ነው፤ ነጩ ከእውነቱ የሚያስቀረው ነው። ቢያጋንኗቸው ቢያሰማምሩአቸው ነጩም ጥቁሩም ያው ውሸት ናቸው።
:
☞በእርግጥም ውሸትን ማንኛውም ሰው ይዋሻል፡፡ የማይዋሽ ማንም የለም፡፡ በየትኛውም የእውቀትና እድሜ ደረጃ እንዲሁም አኗኗርና ባህል ውስጥ ያለ ሰው ይዋሻል፡፡ ማንኛውም ሰው ትክክለኛነትን ማረጋገጥ ስለማይችል ህይወቱን ለማስተካከል፣ ስጋቶቹን ለመቅረፍ የሚዋሽበት ሁኔታ ይፈጠራል።
:
➡ውሸት ራሱን የቻለ የስብዕና መለያ ሊሆን ይችላል፡፡ የተለያየ እድሜ ላይ ሊከሰትም ይችላል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ከጨቅላነት እድሜ የሚጀምር ሲሆን አንዳንድ ጊዜ ደግሞ በጉርምስና ጊዜ ይጀምራል፡፡ ውሸትን ከልጅነት እድሜ ጀምሮ እየተሸለመ የመጣ (ሲዋሽ በቤተሰቡ ትኩረት እየተሰጠው ያደገ) ህፃን እድሜ ልኩን ውሸትን በልማድና በስብዕና መለያነት ይዞት ይኖራል፡፡
:
➡ሌላው የውሸት አይነት በስብዕና ቀውስ መዛባት የሚመጣ ነው፡፡ እንዲህ ዓይነቱ ውሸት ለማህበረሰብ ጠንቅ የሆነ የስብዕና አይነትን ይፈጥራል፡፡ ሰዎችን ማታለል፣ ወዳልሆነ አቅጣጫ መምራት የመሳሰለው ተግባር እንደ አንድ መጥፎ የስብዕና መለያ ምልክት ይወስዳል፡፡ ስለሆነም እነዚህ የስብዕና መዛባት ችግር ያለባቸው ሰዎች ውሸት አንደኛው መለያቸው ይሆናል፡፡
:
➡በሌላ በኩል የአዕምሮ ጭንቀት ህመም ለውሸት መነሻ ምክንያት ይሆናል፡፡ የጭንቀት ህመም በጉዳት ወቅትና ከጉዳት በኋላ የሚፈጠር ሲሆን ይህ ጭንቀት ሰዎችን ከእውነተኛው ስብዕናቸው እንዲያፈነግጡ ያደርጋቸዋል፡፡ ሰዎች በአንድ ምክንያት ከተጎዱ በኋላ ሚደርስባቸው የጭንቀት ህመም፣ ያንን ጉዳታቸውን እያስታወሱ ላለመሰቃየት ሲሉ ሌላ ያልሆነ ነገር በመፍጠር መዋሸት ይቀጥላሉ፡፡ እንዲህ አይነቱ ሰዎች ሆን ብለው በመዋሸት ሌላውን ለመጉዳት የሚታትሩ አይደሉም፡፡ ያንን ጉዳታቸውን ላለማስታወስና ወደ ጉዳታቸው ላለመመለስ የሚዋሹ ናቸው፡፡
:
☞ውሸት ራሱን የቻለ በሽታ ሳይሆን የበሽታ ምልክት ነው። ውሸት ወደ ስብዕና ደረጃ ከተሸጋገረ፣ ግለሰቦቹ ችግር እንዳለባቸው አይቀበሉትም። ከላይ ለመግለፅ እንደተሞከረው ውሸት የስብዕና መዛባት ችግር፣ የጭንቀትና ከፍተኛ የአእምሮ ጉዳት ምልክት ነው፡፡ ለምሳሌ የስብዕና መዛባት ችግር ያለበት ሰው ውሸት አንዱ ምልክቱ እንጂ ከዚያ በላይ በርካታ መለያዎች ይኖራሉ፡፡
:
↪በሌላ በኩል “Boarder light” የሚባል የስብዕና ችግር አለ፡፡ ሲሆን ይህ ችግር ስሜታቸው የሚቀያየርና ከሰዎች ጋር ያላቸው መስተጋብርና ከማህበረሰቡ ጋር ያላቸው ግንኙነት የሚለዋወጥ ግለሰቦች ላይ የሚታይ ነው፡፡ እነዚህ ሰዎች ስሜታቸውን መቆጣጠር የማይችሉ፣ ግልፍተኝነት የሚያጠቃቸውና፣ በማህበራዊ ግንኙነታቸው ችግር ያለባቸው ሰዎች የሚያንፀባርቁት የስብዕና አይነት ነው - “ቦርደር ላይ የሚባለው፡፡ እነዚህ ሰዎች ስሜታቸው ለመቆጣጠር ጥረት የሚያደርጉ ሲሆን በዚህ በሚያደርጉት ጥረት ውስጥ ስለሚዋሹ አንዱ የስብዕናቸው መለያ ይሆናል እንጂ ውሸት ራሱን የቻለ በሽታ አይደለም፡፡
:
፩.ሰዎች እንዲዋሹ የሚያደርጉ ምክንያቶች ምንድናቸው?
:
➊.ሰዎች ውሸትን እንዲዋሹ ከሚያተጓቸው ነገሮች አንዱና ዋናው የፍርሀት ስሜት ነው፡፡ ፍርሀት የሚከሰትባቸው በርከት ያሉ መሰረታዊ ምክንያቶች ያሉ ሲሆን አንደኛው ትችትን ነቀፌታን ውርደትንና ሸንፈን ያለመቀበል ነው፡፡
:
➋.ሌላኛው ምክንያት ደግሞ አንድ ግለሰብ በአንድ በቡድን ወይም ማህበረሰብ ውስጥ ራሱን የቻለ ማንነት ይኖረዋል፡፡ ይህን ማንነቱን የሚያጎድልበት ነገር ካለ ያንን ለመሙላት ሲል ሊዋሽ ይችላል፡፡
:
➌.በሌላ በኩል ህልውናን ለማስጠበቅ፣ በስነ ልቦና ችግርና የተፈላጊነትን ስሜት ለመጨመር የሚዋሽበት ጊዜ አለ፡፡ ለምሳሌ እድሜን ቀንሶ መናገርን ማንሳት ይቻላል፡፡ እድሜያችን እየጨመረ ሲሄድ ተፈላጊነት እያጣን እንደምንመጣ ስለምናስብ ፍርሃት ይለቅብናል፡፡ ከዚህ ከፍርሀት ለመላቀቅ እንዋሻለን። በእነዚህና መሰል ምክንያቶች የማይዋሽ ሰው አለ ማለት ይቸግራል፡፡
:
☞አንዳንድ ጊዜ ውሸት “reaction formation” ይባላል፡፡ ይህም ማለት እራሳችንን ከእውነተኛው ነገር በተቃራኒው የማሰብ ሂደት ላይ ማድረግ ማለት ነው፡፡ ባሉብን ጉድለቶች የተነሳ አዕምሯችን ጭንቀት ላይ እንዳይወድቅ የማድረግ ሂደት ነው… ሪአክሽን ፎርሜሽን፡፡ ለምሳሌ፦ አንዲት ሴት አንድን ወንድ አፍቅራው በሰው ፊት እንዳላፈቀረችው ትናገራለች፡፡ ይህ ምንድነው? ውሸት ነው፡፡ የምትዋሸው ደግሞ በምትኖርበት ማህበረሰብ ውስጥ ያላትን ዋጋ ላለማጣት ስትል ነው፡፡ የበታችነት ስሜት እንዳይሰማት ያደረገችው ትግል ነው፡፡ ማለት ይቻላል፡፡ ይህቺ ሴት በዋሸችው ውሸት ታማሚ ናት ወይም ትክክል አይደለችም ብሎ ለመደምደም ይቸግራል፡፡ ይህቺ ሴት ሌላውን ለመጉዳት፣ በሌላው ላይ ችግር ለመፍጠር አልተጋችም፡፡
:
♡┈┈┈••✦✿✦••┈┈┈♡
:
☞ወዳጆቼ እውነት ነው ብለን የያዝነው ስንት ውሸት ይኖር ይሆን? እያንዳንዱ ሰው ራሱን ይመርምር። እውነት፤ ነገርን ማጣራትና ማመዛዘንን፣ ለእውነትና በእውነት መኖርን ይጠይቃል። ውሸትን ተግቶ መቋቋምና መግለጥን ይጠይቃል። ውሸትን መደጋገም ከእውነት እንደሚያዘናጋ ሁሉ፤ እውነትን መደጋገም እውነት እንዳይረሳና እንዳይበረዝ ይረዳል።
:
↪ውሸት ሲሰሙት ደስ የሚል ፣ ቀላል የሆነ፣ እጅግ የሚያምርና የሚያታልል ነው። እውነት ደግሞ በተቃራኒው ብዙውን ጊዜ ለስሜት የማይመች፣ የሚከብድ፣ ዋጋ የሚያስከፍልና የሚያሳምም ነው። ለዚህ ይመስለኛል መዋሸት ከእውነተኝነት ይልቅ ብዙ ሰዎች የሚከተሉት የህይወት መርህ የሆነው። ውሸትና እውነት ሁሌም በውድድር ሜዳ ላይ ናቸው። እውነት ባለበት ውሸት፣ ውሸት ባለበትም እውነት ስፍራ የላቸውም።
:
↪ማንም ሰው በአንድ ጊዜ እውነተኛም ውሸታምም መሆን አይችልም። ወይ እውነትን ይመርጣል ወይ ደግሞ ለውሸት ይሸነፋል። ታዲያ የእውነትና የውሸት ልዩነትና መሸናነፍ ውጤቱ የሚታየው በፍሬው ነው። ውሸት መንታ መንታ ውሸትን እየወለደ እውነትን ለማሸነፍ ይታትራል፣ በጥረቱ ግን ራሱን በራሱ ጠልፎ ይጥልና እውነት እጅ ላይ ይወድቃል።
:
↪እውነት የተገለጠ እለት ታዲያ ያ ሁሉ ክምር ውሸት ውርደትን ይለብሳል። ዋጋ ያስከፈለው እውነት በአደባባይ እውነተኞችን ያከብር ዘንድ ደምቆ በብርሃን ይገለጣል። በውጤቱ ታዲያ ሁል ጊዜም እውነት እውነተኞችን ያኮራል። በፍፃሜው እውነት ሁልጊዜ ያሸንፋል። ይህ የተፈጥሮም የፈጣሪም አሰራር ነው።

➊.በውሸት ከሚገኝ ከጊዜያዊ እፎይታ ይልቅ ዘለቄታዊ ድልን ለመላበስ እውነትን መርጠን ዋጋ እንክፈል።
:
➋.ወሬ አቀባዩ ማነው? ለምን ይህን አለ? ለምን አሁን? ሌላ ምን መረጃ አለ? አቋሜ ምን ሊሆን ይገባል? ብሎ መጠየቅ ግድ ነው። መስዋእት መክፈል ግድ ነው።
:
➌.የምንሰማውን ነገር ሁሉ ለማመን ፈጽሞ አንቸኩል፣ ምክንያቱም ውሸት ከእውነት እጅግ ፈጥኖ ይሰራጫልና!....አበቃሁ✍
:
♡ስለ ሁሉም አምላክ ማስተዋሉን ለሁላችንም አብዝቶ ያድለን! (አሜን)
:
«ሼር በማድረግ ለወዳጆ ያካፍሉ»
:
"በቸር ያቆየን"
:
(ሙሌ ቤስት ➐/➒/➊➊ ዓ/ም አርባምንጭ~ኢትዮጵያ)
❀︵♡┈┈┈••✦✿✦••┈┈┈♡︵❀

Address

Durame

Telephone

+251916680131

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gezehagn melese posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share