Amlaku Gebeyehu

Amlaku Gebeyehu ዘላለማዊ ክብርና ነፃነት ለኢትዮጵያ

06/04/2022

ም/ኮማንደር በቀለ አብየ የምዕራብ ጎጃም ዞን ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ሆነው ተመድበዋል ።
መልካም የስራ ዘመን !

06/04/2022
04/04/2022
03/04/2022

" መንግሥት የዋጋ ንረቱን ለመፍታት የአጭር የመካከለኛና የረጅም ጊዜ ዕቅድ ነድፎ እየስራ ነው"
-የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልገሎት
*******************
(ኢ ፕ ድ)

መንግሥት የዋጋ ንረቱን ለመፍታት የአጭር የመካከለኛና የረጅም ጊዜ ዕቅድ ነድፎ እየተሰራ ነው ሲሉ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልገሎት ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉ አሰታወቁ።

በኢኮኖሚ ውስጥ ያለ አሻጥር የሚቆጣጠር ግብረ ሀይል ተቋቁሞ የማያዳግም እርምጃ እየተወሰደ መሆኑንም ተናግረዋል።

ሚኒስትሩ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ መንግሥት የዋጋ ንረቱን ለመፍታት የአጭር የመካከለኛና የረጅም ጊዜ ዕቅድ ነድፎ እየተንቀሳቀሰ ነው ብሏል።

የዋጋ ንረትና ግሽበት ሦስት መሠረታዊ ምክንያቶች መከሰቱን ጠቅሰው፣ የዩክሬይንና የራሽያ ጦርነት በዓለም አቀፍ ደረጃ የዋጋ ንረትና ግሽበቱን አባብሶታል።

በሸማቾችና በአምራቾቾ መካከል ቀጥተኛ ግንኙነት አለመኖር ለዋጋ ንረት አስተዋፅኦ አድርጓል ተብሏል።

የመሠረታዊ ፍጆታዎች የምርትና ምርታማነት አለመመጣጠን ለዋጋ ንረትና ግሽበት ሌላው ምክንያት ነው ያሉት ሚኒስትሩ መንግስት ችግሩን ለመፍታት የአጭር ፣ የመካከለኛና የረጅም ጊዜ እቅድ ቀርፆ እየሠራ መሆኑን ተናግረዋል።

በዚህም በኢኮኖሚ ውስጥ ያለ አሻጥር የሚቆጣጠር ግብረ ሀይል ተቋቁሞ የማያዳግም እርምጃ እየተወሰደ ተብሏል።

እንደ ሚኒስትሩ ገለጻ ከዚህ በፊት የተፈፀሙ ግዢዎች በአጭር ጊዜ እንዲገቡና ሌሎች ግዢዎችን መፈፀም ሥራዎች እየተሠሩ ነው። ምርትና ምርታማነት ን ለማሳደግ መሥራትም በመካከለኛና በረጅም ጊዜ ችግሩን ለመፍታት ይሠራል ተብሏል።

በውብሸት ሰንደቁ

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼
ተጨማሪ የመረጃ አማራጮቻችን ‼
ዩቲዩብ 👇
https://youtube.com/channel/UCoH2CVwWn9suWP7q0u2L7MA
ቴሌግራም 👇
https://t.me/ethpress
ትዊተር 👇
https://twitter.com/PressEthio
ድረ ገጽ 👇
https://www.press.et/

01/04/2022
25/03/2022

"ትምህርት ሚኒስቴር ውጤቶቹን ተንትኖ ፍትሐዊ የሆነ የመቁረጫ ነጥብ መወሰንና ግልጸኝነት የመፍጠር ኃላፊነት አለበት።"

የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ

በርካታ ቅሬታዎች በተነሱበት የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን አስመልክቶ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ማተብ ታፈረ (ዶ/ር) ዛሬ ለክልሉ ምክር ቤት አባላት ማብራሪያ ሰጥተዋል።

የ12ተኛ ክፍል ተማሪዎች በጦርነት ስነ ልቦና ውስጥ ሆነው ፈተና መውሰዳቸው እንደጎዳቸው ኃላፊው ገልጸዋል፡፡

ተማሪዎች፣ ወላጆች፣ መምህራን፣ የትምህርት ሥራ ኃላፊዎች፣ በትምህርት ሥርዓቱ ላይ አመኔታ የሚያጡ ከሆነ ተሻጋሪ የሆነ ችግርን ሊያስከትል እንደሚችል ተናግረዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር እየተፈጠረ ያለውን የእምነት ማጣት ጉዳይ ግልጽ አሠራር በመዘርጋት መተማመን መፍጠር እንዳለበት ክልሉ ያምናል ብለዋል፡፡

ውጤቱ ከተገለጸ በኋላ ቢሯቸው ባደረገው ግምገማ የክልሉ ተማሪዎች ውጤት እንደ ሀገርም ሆነ እንደ ክልሉ ዝቅ ያለ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ውጤቱ እንዲስተካከል፣ ዩኒቨርሲቲ የሚገባበት ጊዜ እንዲራዘም እና ጉዳዩ እንዲጣራ ለትምህርት ሚኒስቴር በጽሑፍ ጥያቄ መቅረቡን አስታውሰዋል፡፡ ሂደቱን የሚያጣራ ቡድን ወደ ሚኒስቴሩ መላኩንም ተናግረዋል፡፡

"ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ውጤቶችን ተንትኖ የውሳኔ ሀሳብ ካቀረበ በኋላ፤ ትምህርት ሚኒስቴር ውጤቶቹን ተንትኖ ፍትሐዊ የሆነ የመቁረጫ ነጥብ መወሰንና ግልጸኝነት የመፍጠር ኃላፊነት አለበት" ብለዋል። አሚኮ

25/03/2022
21/03/2022

የጀግኖች አቀባበል

21/03/2022
ለምርት ጭማሬ እና እድገት የተ/ሃብ ተግባር ጥራቱን ጠብቆ ዕቅዳችንን ለመፈፀም በጥልቀት ችግራችን አይተን የቀጣይ የመፍቻ ቁልፍ ለይተን መክረናል::  ለዚህ ተግባር ተፈፃሚነት ጎናችን ትቆሙ ...
20/03/2022

ለምርት ጭማሬ እና እድገት የተ/ሃብ ተግባር ጥራቱን ጠብቆ ዕቅዳችንን ለመፈፀም በጥልቀት ችግራችን አይተን የቀጣይ የመፍቻ ቁልፍ ለይተን መክረናል::
ለዚህ ተግባር ተፈፃሚነት ጎናችን ትቆሙ ዘንድ ጥሪአችንን እናስተላልፋለን

ሠ/ሜጫ ላይ በታታሪ ልጆቷ እና ህዝቦቷ ተዳምረዉ አየተከወኑ ያሉ የልማት ተግባራት
18/03/2022

ሠ/ሜጫ ላይ በታታሪ ልጆቷ እና ህዝቦቷ ተዳምረዉ አየተከወኑ ያሉ የልማት ተግባራት

ከህዝብ ዉይይት--- በቁጭት የጀመረዉ የብራቃት የወንዝ ዳር ማስተካከል ስራ
10/03/2022

ከህዝብ ዉይይት--- በቁጭት የጀመረዉ የብራቃት የወንዝ ዳር ማስተካከል ስራ

ከተሞች ያላቸዉን ኃብት በተገቢዉ መንገድ በመሠብሠብ የተጣለባቸዉን ህዝባዊ አደራ እንዲወጡ መክረናል:: ለነዋሪዎች ምቹ: ዉብ:ለወጣቶች የስራ እድል መፍጠሪያ እንዲሆኑ ህዝቦች ባለቤት ሁነዉ እ...
08/03/2022

ከተሞች ያላቸዉን ኃብት በተገቢዉ መንገድ በመሠብሠብ የተጣለባቸዉን ህዝባዊ አደራ እንዲወጡ መክረናል::

ለነዋሪዎች ምቹ: ዉብ:ለወጣቶች የስራ እድል መፍጠሪያ እንዲሆኑ ህዝቦች ባለቤት ሁነዉ እንዲደግፋ ጥሪ በጋራ አስተላልፈናል::

ትናንትን አስከብራችሁዛሬን እዚህ ያደረሳችሁነገን ምታስቀጥሉ ምሽግ ሠባሪ ጀግኖቻችን
08/03/2022

ትናንትን አስከብራችሁ
ዛሬን እዚህ ያደረሳችሁ
ነገን ምታስቀጥሉ ምሽግ ሠባሪ ጀግኖቻችን

የሠሜኑ አማፂ ኃይል ቆፍሮ ከገባበት የጋሽና ምሽግ የቀበረዉ የሠ/ሜጫ ሚሊሻ እና ፋኖ  እዉቅና ሠጠናል::       ዘላለማዊ ክብር በዚህ የዉጊያ አዉድ ለተሳተፋችሁ ጀግኖቻችን
08/03/2022

የሠሜኑ አማፂ ኃይል ቆፍሮ ከገባበት የጋሽና ምሽግ የቀበረዉ የሠ/ሜጫ ሚሊሻ እና ፋኖ እዉቅና ሠጠናል::

ዘላለማዊ ክብር በዚህ የዉጊያ አዉድ ለተሳተፋችሁ ጀግኖቻችን

04/03/2022
በረከትዎ በእኛ ላይ ይደር
04/03/2022

በረከትዎ በእኛ ላይ ይደር

አድዋየዛን ዘመን የጀብጆ ስነ ግጥምምኒሊክ ተወልዶ ባያነሣ ጋሻግብሩ እንቀላል ነበር ይሄን ጊዜ አበሻ፤***ገበየሁ ቢሞት ተተካ ባልቻመድፍ አገላባጭ ብቻለብቻ፤***የአድዋ ሥላሴን ጠላት አረከሰ...
03/03/2022

አድዋ
የዛን ዘመን የጀብጆ ስነ ግጥም

ምኒሊክ ተወልዶ ባያነሣ ጋሻ

ግብሩ እንቀላል ነበር ይሄን ጊዜ አበሻ፤

***

ገበየሁ ቢሞት ተተካ ባልቻ

መድፍ አገላባጭ ብቻለብቻ፤

***

የአድዋ ሥላሴን ጠላት አረከሰው

ገበየሁ በሞቴ ግባና ቀድሰው፤

ሜጫ------ዳጊ----ድንብክ መስክ----አ/ልደት  ስኬታማዉ የማልማት ትልም በበጋዉ አረንጓዴ ለብሶ ግርማ ሞጎሱን ተላብሶ ለህዝቦች ተስፉ ሊሆን እንዲህ በፍሬ ዘሞል ሜጫ /ምዕ/ጎጃም/አማራ ...
02/03/2022

ሜጫ------ዳጊ----ድንብክ መስክ----አ/ልደት

ስኬታማዉ የማልማት ትልም በበጋዉ አረንጓዴ ለብሶ
ግርማ ሞጎሱን ተላብሶ ለህዝቦች ተስፉ ሊሆን እንዲህ በፍሬ ዘሞል ሜጫ /ምዕ/ጎጃም/አማራ ላይ
ክብ ለዚህ ክብር ላበቁን አመራሮች ባለሙያዎች እና ህዝቦች

"ከቸር ወሬ በስከጀርባ ደማቅ ድል"
"እውን ብልጽግና"

🇪🇹 መሠረት እየጣለ የመጣዉን የአማራ ብሔርተኝነት ዘየውን ሳይለቅ ፋፍቶ እንዲቀጥል የሁላችንም እጂ ከደም ንክኪ ማንፃትይገባል 🇪🇹     የህዝባችንን የተመረዘ እሴት : የተዘረፈውን ርስት እ...
10/02/2022

🇪🇹 መሠረት እየጣለ የመጣዉን የአማራ ብሔርተኝነት ዘየውን ሳይለቅ ፋፍቶ እንዲቀጥል የሁላችንም እጂ ከደም ንክኪ ማንፃትይገባል 🇪🇹

የህዝባችንን የተመረዘ እሴት : የተዘረፈውን ርስት እና የማንነት ጥያቄ ከቅርቃ ለማውጣት የተጓዝንበት የሞግዚት ፓለቲካ አውድ ያስከፈለን የሠው እና የሃብት ውድመት ምንም እንኳ አሁን ያለው ፓለቲካ ኢኮኖሚ በይዘቱም በቅርፁም የማይመጥን ቢሆንም ሁነቱ ግን እርስ በእርስ ተጠራጣሪ እንድንሆን ጋብዞናል።

ይህን አዙሪት ደግሞ መጠኑ እየቀነሠ መግባባቱ እድገት እያሳየ መጓዝ ካልቻለ እና ከግዜ ወደ ግዜ እየጨመረ ፈሩን እየለቀቀ የጥቅመኞች ሠለባ እየሆነ ከሄደ የክልላችን ዳግም ኢኮኖሚያዊ : ፓለቲካዊ: ማኀበራዊ እሴትን ንዶ መቀመቅ ውስጥ እንዳይከተን እሠጋለሁ።

በመሆኑ ከምንፀፈው እስከ ምንነጋገረው አንድነትን ምናጠነክርበት ወንድማማችን ምናጎለብትበት ሊሆን ይገባል።

31/01/2022
29/01/2022

ሀገሪቱ ካለችበት አንጻራዊ ሰላም ጋር ተያይዞ የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁን ከተቀመጠለት የስድስት ወር ገደብ ቀድሞ ማንሳት አስፈላጊ ኾኖ መገኘቱን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ።

አዲስ አበባ፡ ጥር 19/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትሩ ዶክተር ለገሰ ቱሉ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ መግለጫ ሰጥተዋል።

ሚኒስትሩ ዶክተር ለገሰ ቱሉ በሰጡት መግለጫ ኢትዮጵያ በልዩ ልዩ ኹነቶች የምታጌጥበት የጥር ወር ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በዓለም ደምቃ እንድትታይ በሚያደርግ መልኩ በዓላትን አክብራለች ብለዋል። በዓላቱ ከመንፈሳዊ ፋይዳቸው ባለፈ የኢትዮጵያን ሰላማዊ ሁኔታ ለዓለም ያሳየ ነው ሲሉ ጠቅሰዋል። በወይብላ ማሪያም የተፈጠረውን ችግር መንግሥት እያጣራ እንደሚገኝም ገልጸዋል።

የአፍሪካ ሕብረት ጉባኤን በተመለከተ ዶክተር ለገሰ እንደገለጹት 35ኛው የአፍሪካ ሕብረት ጉባኤ ከኮሮናቫይረስ ጋር ተያይዞ ከሁለት ዓመታት በኋላ የሚካሄድ በመሆኑ ለጉባኤው ተገቢዉ ዝግጅት ተደርጓልም ብለዋል።

በጉባኤዉም ኢትዮጵያ የራሷን ችግሮች በራሷ እንደፈታች የምታሳይበት ይሆናልም ነው ያሉት፡፡ የጉባኤዉ ተሳታፊዎችም በአዲስ አበባ እንዲካሄድ መወሰናቸዉ አጋርነታቸዉን እንደሚያሳይም ጠቅስዋል።

በአዲስ አበባ እና ከአዲስ አበባ ዉጭ የቱሪዝም መዳረሻ የሆኑ ከተሞች ላይ የሚኖሩ ሕዝቦች በኢትዮጵያዊ እንግዳ አቀባበል ባህል እንግዶችን እንዲያስተናግዱ ጥሪ ቀርቧል።

በተጨማሪም ከአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ወረራ ነጻ በወጡ አካባቢዎች ማኅበረሰቡ ወደ ተሟላ እንቅስቃሴ መግባታቸዉን በመግለጫቸዉ አንስተዋል። በአማራ ክልል የነበሩ የፀጥታ ችግሮችን ከማኅበረሰቡ ጋር በመሆን እንደተፈታም ሚኒስትሩ ተናግረዋል። የመልሶ ግንባታዉም በተጠናከረ መልኩ መቀጠሉን የገለጹት ሚኒስትሩ በዘላቂነት የተፈናቀሉ ወገኖችን በማቋቋም በኩል በጋራ ልንቆም ይገባል ብለዋል።

ዶክተር ለገሰ በኦሮምያ፣ በደቡብ እና በሶማሌ ክልሎች አንዳንድ አካባቢዎች ባጋጠመዉ የድርቅ አደጋ ዜጎች እንዳይሞቱ የዕለት ደራሽ ድጋፎች እየተደረጉ ነዉ ሲሉም ጠቅሰዋል።

በትግራይ ክልል ስላለዉ አሁናዊ ሁኔታ የተናገሩት ዶክተር ለገሰ ቱሉ ወደ ክልሉ ድጋፍ እንዲገባ እየተደረገ ነዉ ብለዋል፡፡ በአባላ የሚደረገዉ ጉዞ ግን የሽብር ቡድኑ በዚህ አካባቢ በከፈተዉ ትንኮሳ ምክንያት ተቋርጧልም ብለዋል፡፡

አሸባሪዉ ትግራይ ወራሪ ቡድን በአማራ እና በአፋር ክልሎች እያደረገ ያለዉ ትንኮሳ ወደ ትግራይ ሰብዓዊ እርዳታ አልደረሰም የሚለውን የሐሰት ፕሮፖጋንዳ ለመንዛት መሆኑን ገልጸዋል። በበራህሌ በኩልም ለማጥቃት የሞከሩ የሽብር ቡድኑ አባላት በአየር ኃይል ተደምስሷልም ሲሉ ጠቅሰዋል።

ሀገሪቱ ካለችበት አንጻራዊ ሰላም ጋር ተያይዞ የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁን ከተቀመጠለት የስድስት ወር ገደብ ቀድሞ ማንሳት አስፈላጊ ኾኖ መገኘቱንም ገልጸዋል፡፡
የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁ እንዲነሳ የሚኒስትሮች ምክርቤት ዉሳኔ አስተላልፎ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መርቷልም ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ዘጋቢ፡-ኤልሳ ጉዑሽ-ከአዲስ አበባ

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ። https://ameco.bankofabyssinia.com/

መልካም ቅዳሜ
28/01/2022

መልካም ቅዳሜ

Address

W/gojam
Durame

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Amlaku Gebeyehu posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Share

Category