Yegna Media Network YMN

  • Home
  • Yegna Media Network YMN

Yegna Media Network YMN Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Yegna Media Network YMN, Media/News Company, .

መንግሥት ' ሸኔ ' እያለ ከሚጠራው (እራሱን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት የሚለው ታጣቂ ቡድን) ጋር ሁለተኛው ዙር የሰላም ድርድር እየተካሄደ መሆኑን ለመጀመሪያ ጊዜ ይፋዊ ማረጋገጫ ሰጥቷል‼️የሰ...
17/11/2023

መንግሥት ' ሸኔ ' እያለ ከሚጠራው (እራሱን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት የሚለው ታጣቂ ቡድን) ጋር ሁለተኛው ዙር የሰላም ድርድር እየተካሄደ መሆኑን ለመጀመሪያ ጊዜ ይፋዊ ማረጋገጫ ሰጥቷል‼️

የሰላም ድርድሩ እየተካሄደ መሆኑን ማረጋገጫ የሰጠው ትናንት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል በሰጠው መግለጫ ነው።

ባለፉት ቀናት የዲፕሎማቲክ ምንጮች በታንዛኒያ ዳሬሰላም የኢትዮጵያ መንግሥት እና የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት የሰላም ድርድር ላይ እንደተቀመጡ ፣ በዚሁ የሰላም ድርድር ላይ የታጣቂው ቡድን አመራሮች ጃል መሮ ድሪባ እና ጃል ገመቹ አቦዬ ወደ ዳሬሰላም እንዲሄዱ ተደርገው ድርድሩን እየተካፈሉ እንደሆነ መነገሩ አይዘነጋም።

በትናንትናው ዕለት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም ምንም እንኴን የተብራራ ነገር ባይገልጹም በታንዛኒያ ሁለተኛው ዙር ድርድር ከ "ሸኔ" ጋር እየተካሄደ መሆኑን አረጋግጠዋል።

አምባሳደር መለስ ፤ " የመጀመሪያው ዙር ከሸኔ ጋር የተደረገ ውይይት ነበር ሁለተኛ ዙር አሁንም ቀጥሏል። እየተካሄደ ነው የሚገኘው " ብለዋል።

" በእኛ በኩል ድርድሩ በመገናኛ ብዙሃን በኩል እንዲደረግ/እንዲሆን ፍቃደኛ አይደለንም። ስለዚህ ጊዜው ሲደርስና ሁኔታዎች ሲፈቅዱ ይፋ የሚሆን ይሆናል " ሲሉ ተናግረዋል። አምባሳደር መለስ ፤ " የዲፕሎማሲ አንደኛው ባህሪ በግልፅም በይፋም የሚደረጉ ነገሮች እንዳሉ ሆነው ሌሎች ነገሮች ግን ጊዜያቸውን የሚጠብቁ እንደሆኑ መረዳት ያስፈልጋል። ግን እየተከናወነ እንደሆነ እገልፃለሁ።" ብለዋል።

YMN

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Yegna Media Network YMN posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share