26/06/2024
የ2016 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር የዓመቱ ኮከብ ተጫዋች እጩዎች ይፋ ሆኑ
*****************
የ2016 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር የዓመቱ ኮከብ ተጫዋች፤ ግብ ጠባቂ እና የዓመቱ ወጣት ተስፈኛ ተጫዋች እጩዎች ይፋ ሆነዋል።
የዓመቱ ኮከብ ተጫዋች እጩዎች ባሲሩ ኡመር፣ ሽመልስ በቀለ፣ ፈቱዲን ጀማል፣ ቸርነት ጉግሳ፣ አሊ ሱሌይማን፣ ከነዓን ማርክነ እና ቢንያም ፍቅሬ ሆነዋል።
የዓመቱ ኮከብ ግብ ጠባቂ እጩዎች አቡበክር ኑራ፣ ሰዒድ ሀብታሙ እና ፍሬው ጌታሁን ሆነው ተመርጠዋል።
የዓመቱ ወጣት ተስፈኛ ተጫዋች እጩዎች ወገኔ ገዛኸኝ፣ ተመስገን ብርሃኑ፣ ዮሐንስ መንግሥቱ፣ በፍቃዱ አለማየሁ እና መድን ተክሉ ሆነዋል።
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አ.ማ ተመልካቾች እስከ ሰኔ 28/2016 ዓ.ም ብቻ በተቋሙ የቴሌግራም ቻናል በመግባት ድምፅ መስጠት እንደሚችሉ አስታውቋል።