Kembata Tembaro updates

Kembata Tembaro updates This page is created to update fast and creditable informations about Kembata Tembaro zone.

 #ማስታወቂያ
08/04/2024

#ማስታወቂያ

07/04/2024



አዲስ የአመራር ለውጥ መምጣቱ የከምባታን የልማትና፣የደህንነት ጥያቄ ይመልሰዋል? አዎም አይደለምም ስትሉ ከበቂ ምክኒያት ጋር🙏🙏

ከምባታ ጠምባሮ አፕዴትስ(ኬ.ቲ.ዩ) ጷጉሜን 03/2014ዓ.ምከከምባታ ጠምባሮ ዞን የክልልነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ በ12/12/14 ተጠርቶ ከነበረው ሰልፍ ጋር በተገናኘ ታስረው የነበሩ ሦሥቱም...
08/09/2022

ከምባታ ጠምባሮ አፕዴትስ(ኬ.ቲ.ዩ) ጷጉሜን 03/2014ዓ.ም

ከከምባታ ጠምባሮ ዞን የክልልነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ በ12/12/14 ተጠርቶ ከነበረው ሰልፍ ጋር በተገናኘ ታስረው የነበሩ ሦሥቱም ተጠርጣሪዎች በዋስትና መፈታታቸውን ሰምተናል።ጷጉሜን 1 ቀን 2014 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተጠርጣሪዎቹ ወንድምአለም ደሳለኝ እና አሸናፊ ኤልያስን እያንዳንዳቸውን በአሥር ሺህ ብር ዋስትና እንዲፈቱ የከምባታ ጠምባሮ ዞን ከፍተኛው ፍርድ ቤት ባሳለፈው ውሳኔ መሠረት ከእስር መፈታታቸው ይታወሳል።የዛሬው ችሎት ደግሞ ሌላኛውን ተጠርጣሪ ሔኖክ ታደሰን በተመሳሳይ የዋስትና መብት በመስጠት ከእስር ነፃ አድርጎታል።


ከምባታ ጠምባሮ አፕዴትስ(ኬ.ቲ.ዩ) ነሐሴ 26/12/14የከምባታ ጠምባሮ ዞን ከፍተኛው ፍርድ ቤት በሔኖክ ታደሰ ላይ ፖሊስ የጠየቀውን የ10 ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ውድቅ በማድረግ የ 7...
01/09/2022

ከምባታ ጠምባሮ አፕዴትስ(ኬ.ቲ.ዩ) ነሐሴ 26/12/14

የከምባታ ጠምባሮ ዞን ከፍተኛው ፍርድ ቤት በሔኖክ ታደሰ ላይ ፖሊስ የጠየቀውን የ10 ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ውድቅ በማድረግ የ 7 ቀናት የምርመራ ግዜን ፈቅዷል።ፖሊስ በተሰጠው የ10 ቀናት የምርመራ ግዜ ምን ማስረጃ እንዳገኘ ሲጠየቅ ተጠርጣሪው ወጣቶችን በማደራጀት የፖሊስን ሥራ ሲረብሽ ነበር ብሏል።የዚህን ድርጊት የሰውና የሰነድ ማስረጃ ለማሰባሰብም የ10 ቀናት ተጨማሪ ቀን ጠይቋል።ተጠርጣሪው በበኩሉ የተጠረጠርኩበት ጉዳይ በወንጀል የሚያስጠይቀኝ ሳይሆን ህገመንግሥታዊ መብቴ ነው በማለት ጉዳዩን ውጭ ሆኖ ለመከራከር የዋስትና መብቱ እንዲከበርለት ጠይቋል።ፍርድ ቤቱ የዋስትና ጥያቄውን ውድቅ በማድረግ ለቀጣዩ ጷጉሜን 3 ጉዳዩ በወንጀል ያስጠይቃል አያስጠይቅም የሚለውን ብይን ለመስጠት ቀጠሮ ሰጥቷል።በነዚህ ቀናት ፖሊስ በቂ ማስረጃ ይዞ እንዲመጣ፣የተሰጠውን ግዜ በአግባቡ እንዲጠቀምና ተጠርጣሪዎችን ለማጉላላት እንዳይጠቀምበት ፍርድ ቤቱ አሳስቧል።


ከምባታ ጠምባሮ አፕዴትስ(ኬቲዩ) ሐምሌ 25/12/14ወንድማለም ደሳለኝ ለከምባታ ጠምባሮ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የግዜ አቆያየት መዝገቡ ተገልብጦ እንዲሰጠው የሁለተኛ ዙር ማመልከቻ አስገብቷል...
31/08/2022

ከምባታ ጠምባሮ አፕዴትስ(ኬቲዩ) ሐምሌ 25/12/14

ወንድማለም ደሳለኝ ለከምባታ ጠምባሮ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የግዜ አቆያየት መዝገቡ ተገልብጦ እንዲሰጠው የሁለተኛ ዙር ማመልከቻ አስገብቷል።ተጠርጣሪው ከክልልነት ጥያቄ ጋር ተያይዞ በዱራሜ ከተማ ለ12/12/14 ዓ.ም ተጠርቶ የነበረውን ሰልፍ በማስተባበር ተጠርጥሮ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሉ ይታወሳል።ወንድማለም ተጠርጥሮ ከታሰረበት ግዜ አንስቶ የሰጠው ቃል በትክክል ይመዝገብ አይመዝገብ ለማወቅና ችግር ካለም ለፍርድ ቤቱ አቤቱታ ለማሰማት ይችል ዘንድ የግዜ አቆያየት መዝገቡ ኮፒ ተደርጎ እንዲሰጠው ነው የጠየቀው።በ24/12/2014 ዓ.ም በጽሑፍ ያስገባው ማመልከቻ የፍርድ ቤቱ ምላሽ በፖሊስ በኩል በቃል እንደተነገረው ዛሬ በድጋሚ ባስገባው ማመልከቻ ገልጿል።የግዜ አቆያየት መዝገቡ ኮፒ ተደርጎ እንደማይሰጠው መስማቱን በመጥቀስ ይህ የፍርድ ቤት ድርጊት እና ውሳኔ ከህገመንግስቱ አንቀጽ 292 እንደሚቃረን ገልጾ ፍርድ ቤቱ የመዝገቡን ኮፒ የማይሰጠው ከሆነ የዛሬው አቤቱታ ግልባጭ የደረሳቸው የኢፌዴሪ የህዝብ ዕምባ ጠባቂ ተቋም፣ኢሰመኮ፣የኢፌዴሪ ፍትህ ሚኒስቴር እና የደቡብ ክልል ፍትህ ቢሮ በጉዳዩ ጣልቃ እንዲገቡ ጠይቋል።የከምባታ ጠምባሮ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ሆነ የዞኑ ፖሊስ በጉዳዩ ላይ ማረጋገጫም ይሁን ማስተባበያ አልሰጡም።


30/08/2022



የከምባታ ጠምባሮ ዞን ከፍተኛው ፍርድ ቤት በወንድምአለም ደሳለኝ እና አሸናፊ ኤሊያስ(ቾምቤ) ላይ በ23/12/14 ከሰዓት በኋላ ባዋለው ችሎት ፖሊስ የጠየቀውን የ14 ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ውድቅ በማድረግ የ 7 ቀናት የምርመራ ግዜን ፈቅዷል።ፖሊስ ተከሳሾቹ ከሀዋሳ እስከ አዲስ አበባ የተዘረጋ ሰፊ መረብ አላቸው፤ጉዳዩም ከአጠቃላይ ሀገራዊ ሁኔታ ጋር የሚገናኝ ነው ብሏል።በተጨማሪም ተከሳሾች ከወጡ መረጃ ያጠፋሉ፣እነርሱም ይሸሻሉ ሲል ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል።ምርመራውን ለማጠናቀር የ14 ቀናት ተጨማሪ ግዜንም ጠይቋል።ተከሳሾች በበኩላቸው ከሀገር የሚወጡ ሰዎች እንዳልሆኑ፣መረጃም እንደማያሸሹ በመግለጽ የ14 ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ግዜን ፍርድ ቤቱ ውድቅ እንዲያደርግላቸው ጠይቀዋል።ከዚህም በተጨማሪ ባለፉት 10 ቀናት ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹን ለክስ የሚያበቃ ማስረጃ አለማቅረቡን በመጥቀስ ተጨማሪ ግዜ መፍቀዱ የግዜ ብክነት ካልሆነ ፋይዳ ስለሌለው ፍርድ ቤቱ በነፃ እንዲያሰናብታቸው ጠይቀዋል።ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክር ተመልክቶ ፖሊስ የጠየቀውን የ14 ቀናት የምርመራ ግዜ ውድቅ በማድረግ በ7 ቀናት ውስጥ ምርመራውን አጠናቆ እንዲያቀርብ ውሳኔ አስተላልፏል።
ከከምባታ ጠምባሮ ዞን የክልልነት ጥያቄና በ12/12/14 ተጠርቶ ከነበረው ሰልፍ ጋር በተያያዘ በእስር ላይ ያለው ሔኖክ ታደሰ ሐሙስ ማለትም በ26/12/14 ፍርድ ቤት እንደሚቀርብ ኬ.ቲ.ዩ የመረጃ ምንጭ አጋርቶናል።

18/08/2022

ከምባታ ጠምባሮ አፕዴት(ኬ.ቲ.ዩ) ነሐሴ 12/2014

1.የኢፌዲሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 6ኛ የፓርላማ ዘመን፣1ኛ አመት፣ 1ኛ አስቸኳይ ጉባኤው ከምባታ ጠምባሮ፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የስልጤ፣ጉራጌ ዞኖችና የም ልዩ ወረዳ በነባሩ ክልል እንዲቀጥሉ ተወስኗል።ቀደም ሲል በቀረበው የክላስተር አደረጃጀት ምክረ ሃሳብ መሠረት እነዚህ ዞኖችና ልዩ ወረዳው ከጉራጌ ዞን በስተቀር በአብላጫ ድምፅ ማጽደቃቸው ይታወሳል።ከእነዚህ በተጨማሪ በቀድሞው ክልል የሚቀጥሉ ይኑሩ አይኑሩ የምክር ቤቱ ጉዳዩን የዘገቡት የመንግሥት ሚድያዎች ያሉት ነገር የለም።

2.የኢፌዲሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 6ኛ የፓርላማ ዘመን፣1ኛ አመት፣ 1ኛ አስቸኳይ ጉባኤው ወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ጌዲዖ እና ኮንሶ ዞኖች እንዲሁም ደራሼ፣ አማሮ፣ ቡርጂ፣ አሌና ባስኬቶ ልዩ ወረዳዎች በቅርቡ በየምክር ቤቶቻቸው ያፀደቁትንና ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ያስገቡትን አዲሱን "የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል" የማደራጀት ምክረ ሃሳብ በሕዝብ እንዲያስወስኑ በአብላጫ ድምፅ አፅድቋል።ሕዝበ ውሳኔውን በ3 ወራት ውስጥ ምርጫ ቦርድ ከ6ቱ ዞኖችና ከ5ቱ ልዩ ወረዳዎች ጋር በገለልተኝነት እንዲያዘጋጅም ተብሏል። የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በሕዝበ ውሳኔው የሚጸድቅ ከሆነ ባለበት እንዲቀጥል የተወሰነው የቀድሞው የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል መንግሥት በስያሜ መቀራረብ ምክንያት የስም ለውጥ ይደረግለት አልያም ባለበት ይቀጥል አልታወቀም።

3.ክልልን በክላስተር ለማደራጀት ተጠርቶ በነበረው ሰላማዊ ሰልፍ ጋር ተያይዞ በትናንትናው ዕለት በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉት የሰልፉ አስተባባሪዎች ወንድማለም ደሳለኝ እና ቾምቤ በሐምሌ 12 ቀን 2014 ዓ.ም ፍርድ ቤት መቅረባቸው ታውቋል።የፍርድ ሂደቱንና በተጨማሪ የታሰሩ ሰዎችን ጉዳይ ተከታትለን የምናደርሳችሁ ይሆናል።

17/08/2022



መንግሥት ያቀረበውን ዞኖችን በክላስተር አደራጅቶ ክልል የመመስረት ምክረ-ሃሳብ የከምባታ ጠምባሮ ዞን ምክር ቤት ማጽደቁን ተከትሎ ለ12/12/14 በዞኑ ዋና ከተማ ዱራሜ የተጠራውን ሰላማዊ ሰልፍ የከተማ አስተዳደሩ እንዳልፈቀደው ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።አሁን ሀገራችን ካለችበት የፀጥታ ሁኔታ አንጻር የድጋፍም ሆነ የተቃውሞ ሰልፎችን ማድረግ እንደማይቻል የፀጥታው ምክር ቤት ኮማንድ ፖስት ማስታወቁንም የዱራሜ ከተማ አስተዳደር ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት በፌስቡክ ገጹ ይፋ አድርጓል።የከተማ አስተዳደሩ የትኛውን የሀገሪቱን የፀጥታ ሁኔታ እንደገለጸና ከተማዋም በኮማንድ ፖስት ስር ስለመሆኗ ያለው ነገር ባይኖርም ሰላማዊ ሰልፉን ግን እንዳልፈቀደ ገልጿል።በሌላ በኩል ሰላማዊ ሰልፉን ያስተባበሩት "ዞባ" የተሰኘው የዞኑ ወጣቶች ኢ-መደበኛ አደረጃጀት ሲሆን ከአስተባባሪዎች መካከል በእስር ላይ ያሉ እንዳሉ፣ሌሎችም የዞባ አባላት የእስር ማዘዣ እንደወጣባቸው ሰምተናል።ስለታሰሩት ሰዎችም ሆነ በድርጊቱ ተጠርጥረው ስለሚፈለጉ ሰዎችም የከተማ አስተዳደሩ መግለጫ ምንም አላለም።

KTU  በደቡብ ክልል ከምባታ ጠምባሮ ዞን፣ጠምባሮ ወረዳ በአጠቃላይ 105,000(ከአንድ መቶ አምስት ሺ) በላይ ነዋሪዎች ለድርቅ አደጋ እንደተጋለጡ ሰምተናል።ወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ በመጀመሪ...
11/07/2022

KTU

በደቡብ ክልል ከምባታ ጠምባሮ ዞን፣ጠምባሮ ወረዳ በአጠቃላይ 105,000(ከአንድ መቶ አምስት ሺ) በላይ ነዋሪዎች ለድርቅ አደጋ እንደተጋለጡ ሰምተናል።ወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ በመጀመሪያው ዙር እርዳታ ከ15,000 ሰዎች በላይ የእለት ደራሽ እርዳታ ያከፋፈለ ሲሆን የደቡብ ክልል አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮምሽንም 54,000 ለሚጠጉ የድርቅ ተጎጂዎች የዕርዳታ እህል አቅርቧል።በአሁኑ ወቅት በብሔራዊ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮምሽን በመቅረብ ላይ ካለው 8000 ኩንታል እህል 3000 ኩንታሉ ለተጎጂዎቹ እየተከፋፈለ ሲሆን የተቀረው በመመጓጓዝ ላይ እንደሆነ አቶ አበራ ኤርፊጦ የወረዳው አስተዳዳሪ አሳውቀውናል።

በከምባታ ጠምባሮ ዞን ጠምባሮ ወረዳ ድርቅ መከሰቱን ተከትሎ የአደጋ ስጋት አመራር ኮምሽን ኮምሽነር አቶ ምትኩ ካሳ ክልሉ በሚያቀርበው ጥያቄ መሠረት የእርዳታ እህል ወደ አካባቢው እንደሚላክ ...
22/06/2022

በከምባታ ጠምባሮ ዞን ጠምባሮ ወረዳ ድርቅ መከሰቱን ተከትሎ የአደጋ ስጋት አመራር ኮምሽን ኮምሽነር አቶ ምትኩ ካሳ ክልሉ በሚያቀርበው ጥያቄ መሠረት የእርዳታ እህል ወደ አካባቢው እንደሚላክ ተናግረዋል።የክልል ቢሮም በስፍራው ተገኝቶ ጉብኝት ማድረጉን ሰምተናል።

03/09/2021

ውድ የከምባታ ጠምባሮ አፕዴት ተከታዮች፣አብራችሁን ስላላችሁና እየተከታተላችሁን ስለሆነ ከልብ እናመሰግናለን።ስለጠፋንባችሁ ይቅርታ እንጠይቃለን።ስራችንን በሰፊው ለመስራት በጎ ፈቃደኛ ጋዜጠኞችን እንፈልጋለን። ለ Kembata Tembaro updates ጋዜጠኞች በቅርቡ በአለምአቀፍ ጋዜጠኞች ስልጠና ለመስጠት እያሰብን ስለሆነ በበጎ ፈቃድ ህዝባችሁንና ገጻችንን ማገልገል የምትፈልጉ በውስጥ መስመር አናግሩን።ሌሎቻችሁ ከምባታ ጠምባሮ ዞንን በሚመለከት እንድናጣራላችሁ የምትፈልጉትን ማንኛውንም ነገር በውስጥ መስመራችን አልያም ደግሞ [email protected] ላይ ላኩልን።

14/07/2021

በደቡብ አፍሪካ በተጠቀሰው ግጭት የ30 ሰዎች ህይወት ማለፉን ቪኦኤ እንግሊዝኛ ዘግቧል።የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚደንት ጃኮብ ዙማን መታሰር ተከትሎ ደጋፊዎቻቸው አመጽ የተቀላቀለበት ግጭት ማስነሳታቸው ይታወሳል።የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስተርም ጉዳዩን ደቡብ አፍሪካ ባለው ኤምባሲ በኩል እየተከታተልኩት ነው ብሏል።በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲም በጉዳዩ ላይ የፅሑፍ መግለጫ ማውጣቱን እኛም ዘግበን ነበር።ግጭቱ ትልቋ ከተማ ጆሃንስበርግን ጨምሮ በቀድሞው ፕሬዚደንት ጃኮብ ዙማ ትውልድ መንደርም ቀጥሏል።የደቡብ አፍሪካ መንግስትም ጦሩ ግጭቱን እንዲያረጋጋ ትዕዛዝ ሰጥቷል።ከግጭቱ ጋር በተያያዘም በርካቶች ታስረዋል ተብሏል።
KTU
https://www.facebook.com/36235438073/posts/10158820594703074/
https://www.facebook.com/100380642254839/posts/125172899775613/
https://www.facebook.com/484414308376589/posts/2035901559894515/

ከሰሞኑ በደቡብ አፍሪካ የተከሰተውና በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መልዕክት።ወገኖቻችን ጥንቃቄ አድርጉ! ምን ሁኔታ ላይ እንዳላችሁም አጋሩን።            KTU
13/07/2021

ከሰሞኑ በደቡብ አፍሪካ የተከሰተውና በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መልዕክት።
ወገኖቻችን ጥንቃቄ አድርጉ! ምን ሁኔታ ላይ እንዳላችሁም አጋሩን።
KTU

የአንጋጫ አንደኛ ደረጃ ሆስፒታል ግዜው ያለፈባቸው መድኃኒቶችን ሊያቀርብ ነው? *****************************ከሰሞኑ የአንጋጫ አንደኛ ደረጃ ሆስፒታል ጊዜአቸው  ያለፈባቸውን ...
13/07/2021

የአንጋጫ አንደኛ ደረጃ ሆስፒታል ግዜው ያለፈባቸው መድኃኒቶችን ሊያቀርብ ነው?
*****************************
ከሰሞኑ የአንጋጫ አንደኛ ደረጃ ሆስፒታል ጊዜአቸው ያለፈባቸውን መድኃኒቶች ሊያቀርብ ነው በሚል በማህበራዊ ድሮች በተለይም በፌስቡክ ወሬው ሲናፈስ ነበር።
ጉዳዩን ለማጣራት የሆስፒታሉ የአሁኑ ስራ አስኪያጅ አቶ ግርማ አማዶ ጋር ደውለን ነበር።እርሳቸውም አዲሱ የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተርም ለሆስፒታሉ ከመሾማቸው በፊት የመድኃኒት ግዥ እንደተፈጸመና ከእነዚህም መካከል በህገወጥ መንገድ የተገዙ ናቸው ተብለው የተጠረጠሩ አስራሶስት(13) የመድኃኒት አይነቶች ተለይተው የመድኃኒቶቹ ፈዋሽነት በምግብ መድሃኒትና ጤና ነክ ክብካቤ ደቡብ ኢትዮጵያ ቅርንጫፍ እንዲጣራለት ሆስፒታሉ በጠየቀው መሰረት ተቋሙ ለሆስፒታሉ ምላሽ ሰጥቷል።በምላሹም ሆስፒታሉ መድኃኒቶቹን መጠቀም ይችላል፣ፈዋሽነታቸውም የተረጋገጠ ነው ብሏል።
ከዚህ ጋር በተያያዘ የተከሰቱ ነገሮችንና የግዥ ሂደቱ ላይ የሚነሱ ጉዳዮች በፍርድ ቤት የተያዙ ስለሆነ በዘገባችን አልተካተተም።
ከህክምና፣ከምግብና መድኃኒት ጋር የተያያዙ ጉዳዮች ከሰዎች ህይወት ጋር ቀጥታ ግንኙነት ስላላቸው ስንዘግብ የማስረጃና የሃላፊነት ጥንቃቄ መውሰድ ያስፈልጋል።
KTU

08/07/2021

በእዚህ ገጽ ላይ የከምባታ ጠምባሮ ዞን ጉዳዮችን ከተዓማኒ ምንጮች እያጣራን፣የጉዳዩን ባለቤቶች አካተን መረጃ እናደርሳችኋለን።
1.አብራችሁን መስራት የምትፈልጉ ካላችሁ
2.ከምባታ ጠምባሮ ዞንን የተመለከቱ ማንኛውንም አይነት ጥያቄዎች፣እንድናጣራላችሁ የምትፈልጉትን ነገር እንዲሁም በአካባቢያችሁ የታዘባችሁትን በውስጥ መልዕክት(inbox) ልታደርሱን ትችላላችሁ
3.የተረጋገጡ ማስረጃዎችንም(የተጻፉ ደብዳቤዎች፣የስብሰባ ቃለ-ጉባኤዎች፤የድምፅ፣የተንቀሳቃሽ ምስል(video) እና የፎቶግራፍ ማስረጃዎችን) በማንኛውም ሰዓት በውስጥ መልዕክት ልታደርሱን ትችላላችሁ
፨የዚህ ገጽ ዋና ዓላማ ስለ ከምባታ ጠምባሮ ዞን ተዓማኒና ትክክለኛውን መረጃ ከምንጩ የጋዜጠኝነት መርህን ተከትሎ ሀላፊነት በተሞላው አዘጋገብ ለእናንተ ማቅረብ ነው።አብራችሁን ላላችሁ ጋዜጠኞች ምስጋናችን የላቀ ነው።
በቅርብ ቀን እንጀምራለን!

21/05/2021

KTU
Coming Soon!

21/05/2021

KTU
በቅርብ ቀን!

Address

Durame

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Kembata Tembaro updates posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Kembata Tembaro updates:

Share