HIV AIDS club

  • Home
  • HIV AIDS club

HIV AIDS club Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from HIV AIDS club, Publisher, .

03/02/2023

የ2015 ዓ.ም ባሕረ ሐሳብ
የአጽዋማትና የበዓላት ማውጫ ስሌት
▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰
ዓመተ ዓለም = ዓመተ ምሕረት + ዓመተ ኩነኔ (ፍዳ) = 2015 + 5500 =7515
ወንጌላዊ ፦ በዓመቱ የሚሾም ወንጌላዊ ማለት ነው፡፡
ዓመተ ዓለም፥4
7515 ÷ 4 = 1878
1878 ፦ መጠነ ራብዒት ይባላል፡፡
1878×4=7512
7515-7512=1341 ደርሶ ቀሪ 3
ቀሪው ' 1 ' ከሆነ ዘመኑ ዘመነ ማቴዎስ
ቀሪው ' 2 ' ከሆነ ዘመኑ ዘመነ ማርቆስ
ቀሪው ' 3 ' ከሆነ ዘመኑ ዘመነ ሉቃስ
ቀሪው ' 0 ' ከሆነ (ያለ ቀሪ ከተካፈለ)ዘመኑ ዘመነ ዮሐንስ ይሆናል።
ስለዚህ ቀሪው '3' ስለሆነ የዘንድሮው ወንጌላዊ ሉቃስ ሲሆን ዘመኑ ዘመነ ሉቃስ ይባላል።
•••
ዕለተ ቀመር፦ መስከረም አንድ የሚውልበት ቀን ነው፡፡
ዕለተ ቀመር= ዓመተ ዓለም + መጠነ ራብዒት÷7
= 7515 + 1878 =9393
= 9393 ÷ 7 = 1341 ደርሶ ቀሪ 6 ይሆናል
ቀሪው '0 'ከሆነ ሰኞ
ቀሪው '1' ከሆነ ማክሰኞ
ቀሪው '2 'ከሆነ ረቡዕ
ቀሪው '3 'ከሆነ ሐሙስ
ቀሪው '4 'ከሆነ ዓርብ
ቀሪው '5 'ከሆነ ቅዳሜ
ቀሪው '6 'ከሆነ እሁድ መባቻ ይሆናል። በመሆኑም ዘንድሮ ቀሪው '6' ስለሆነ ዕለተ ቀመር
እሑድ ይሆናል።
•••
መደብ = ዓመተ ዓለምን በዐቢይ ቀመር(532) በማዕከላዊ ቀመር(76) እና በንዑስ ቀመር(19) በማካፈል ማግኘት እንችላለን
1.7515፥532=14 ደርሶ ቀሪ 67
2.67 ለ ማዕከላዊ ቀመር ወይም ለ 76 መካፈል ስለማይችል ቀጥታ ለንዑስ ቀመር (19) ይካፈላል።
67 ፥19=3 ደርሶ 10 ይቀራል።
ስለዚህ መደብ 10 ይሆናል፡፡
•••
• ወንበር =መደብ ሲቀነስ አንድ ነው(አሐደ አእትት ለዘመን የሚል አዋጅ አለና ላለፈው መሸኛ ለሚመጣው መቀበያ) ።
መደብ - 1=ወንበር (10 - 1= 9) ይሆናል።
በዚህም መሠረት ወንበር 9 ነው እንላለን
• አበቅቴ ፦ጥንተ አበቅቴን በዘመኑ ወንበር አባዝተን ከ 30 በላይ ከሆነ በ30 ገድፈን ቀሪውን ከ30 በታች ከሆነ ደግሞ የመጣውን ቁጥር በመጠቀም እናገኛለን።
አበቅቴ =11×9=99
99፥30= 3 ደርሶ ቀሪው 9 ይሆናል ስለዚህ የዘንድሮው አበቅቴ 9 ነው እንላለን።
አበቅቴን ለማግኘት ሌላው አማራጭ ያለፈው ዘመን አበቅቴ ላይ ጥንተ አበቅቴን (11) በመጨመር የሚገኘው ቁጥር ከ30 በላይ ከሆነ ለ 30 በማካፈል ቀሪውን ከ30 በታች ከሆነ ደግሞ የመጣውን ቁጥር በመጠቀም ማግኘት እንችላለን ። ይህም ማለት
የ2014 ዓ.ም አበቅቴ 28 ነበር፤ ስለዚህ የ2015 ዓ.ም አበቅቴን ለማግኘት 28+11=39
ይህን በ30 ገድፈን ቀሪው 9 ስለሆነ አበቅቴ '9' ይሆናል ማለት ነው።
• መጥቅዕ፦ ጥንተ መጥቅዕን በዘመኑ ወንበር አባዝተን በ 30 በመግደፍ(በማካፈል) እናገኛለን።
መጥቅዕ = 19×9 = 171
171 ÷ 30= 5 ደርሶ ቀሪው '21 'ስለሆነ መጥቅዕ ዘንድሮ '21 'ይሆናል።
መጥቅዕን ለማግኘት ሌላው አማራጭ ያለፈውን ዘመን መጥቅዕ ከጥንተ መጥቅዕ ላይ( 19 ) በመጨመር የሚገኘው ቁጥር ከ30 በታች ከሆነ ራሱ ከ30 በላይ ከሆነ ለ 30 ተካፍሎ ቀሪው የዘመኑ መጥቅዕ ይሆናል። ይህም ማለት የ2014 ዓ.ም መጥቅዕ 2 ነበር፤ ስለዚህ የ2015 ዓ.ም መጥቅዕን ለማግኘት
2+19=21 ስለዚህ የ2015 መጥቅዕ '21' ይሆናል ማለት ነው።
“አበቅቴ ወመጥቅዕ ክልዔሆሙ ኢይበዝኁ እም ሠላሳ ወኢይውኅዱ እም ሠላሳ ወትረ ይከዉኑ ሠላሳ ፤
አበቅቴ ቢበዛ መጥቅዕ ቢያንስ መጥቅዕ ቢበዛ አበቅቴ ቢያንስ ከሠላሳ አይበዙም ከሠላሳ አያንሱም”
ይህም ማለት በሌላ አገላለጽ መጥቅዕና አበቅቴ ተደምረዉ ውጤቱ ከሠላሳ መብለጥና ማነስ
የለበትም፤ ሁልጊዜ ሠላሳ ይሆናል፡፡ የዘንድሮዉ የ2015 ዓ.ም = 9+21= 30
መጥቅዕ ከ14 በላይ ከሆነ በመስከረም ይዉላል፤
መጥቅዕ ከ14 በታች ከሆነ በጥቅምት ይዉላል፤
መጥቅዕ በመስከረም ቢዉል ጾመ ነነዌ በጥር፣ መጥቅዕ በጥቅምት ቢዉል ጾመ ነነዌ
በየካቲት ይውላል።
ስለዚህ በዚህ ዓመት መጥቅዕ 21 ስለሆነ ከ14 ይበልጣል፤ ስለዚህም መጥቅዕ በመስከረም ይዉላል፤
•••
ስለዚህ የ2015 መጥቅዕ መስከረም 21 ሲሆን መጥቅዕ የሚወድቅበት ዕለት (ዕለተ መጥቅዕ) ቅዳሜ ይሆናል፡፡
•••
መባጃ ሐመር= የዘመኑ መጥቅዕ + መጥቅዕ የወደቀበት የዕለት ተውሳክ በመጠቀም የሚገኘው ቁጥር ከ 30 በላይ ከሆነ ለ 30 በማካፈል ቀሪውን መባጃ ሐመር እንላለን፡፡

ልብ ይበሉ የዕለታት
ተውሳክ ከቅዳሜ ይጀምራል፡፡
የቅዳሜ---8
የእሑድ---7
የሰኞ------6
የማክሰኞ--5
የረቡዕ------4
የሐሙስ----3
የዓርብ ------2 ነው
የዕለታት ተውሳክ የአመጣጥ ስሌቱም የሚከተለውን ይመስላል።
ከዕለተ መጥቅዕ ጀምረን እስከ ነነዌ ጾም መግቢያ ስንቆጥር 128 ቀን ይሆናል፡፡
በ30 ብንገድፈዉ 4 ደርሶ ቀሪ 8 ይሆናል፡፡ ይህም የቅዳሜ ተውሳክ ነው። በዚህ ዓይነት ስሌት ስንሄድ መጥቅዕ የሚወድቅበት ዕለት
• ቅዳሜ ከሆነ ፡- 128፥30= 4 ቀሪ 8
• እሁድ ከሆነ፡127፥30= 4 ቀሪ 7
• ሰኞ ከሆነ፡ 126፥30=4 ቀሪ 6
• ማግሰኞ ከሆነ፡ 125 ፥30= 3 ቀሪ 5
• ረቡዕ ከሆነ ፡124 ፥30= 2 ቀሪ 4
• ሐሙስ ከሆነ ፡ 123፥ 30= 2 ቀሪ 3
• ዓርብ ከሆነ ፡122፥ 30= 2 ቀሪ 2
ስለዚህ የዕለታት ተውሳክ ቀሪዎቹን በመያዝ ይታወቃል።
መባጃ ሐመርን ለማግኘት መጥቅዕንና በዓለ መጥቅዕ የዋለበትን የዕለት ተውሳክ በመደመር ነው።
መባጃ ሐመር= 21+8=29
መባጃ ሐመር ከ30 ስለሚያንስ ራሱ 29 ይያዝና መጥቅዕ መስከረም ላይ ስለወደቀና መጥቅዕ የወደቀበት ዕለት ቅዳሜ ስለሆነ የዘመኑ መጥቅዕ 21 የቅዳሜ ተውሳክ 8 ድምር 29 ስለሆነ ጾመ ነነዌ ጥር 29 ቀን በዕለተ ሰኞ ይውላል ማለት ነው።
• ጾመ ነነዌ፦ መጥቅዕና የዕለቱን ተውሳክ በመደመር በ30 ገድፈን እናገኛለን፡፡ይህ ጾም ተውሳክ የለውም የሚወጣውም በደረቅ መባጃ ሐመር ነው፡፡ ሌሎችን አጽዋማትና በዓላት
ተውሳካቸውን ጾመ ነነዌ የዋለበትን የቀን ቁጥር (መባጃ ሐመር)ደምረን ከ30 ከበለጠ ለ30 እያካፈልን ከ30 በታች ከሆነ ደግም ራሱን በመጠቀም እናገኛለን።
•••
፩፦ ከነነዌ ጾም እስከ ዐቢይ ጾም 14 ቀናት አሉ።
ስለዚህ የዐቢይ ጾም ተውሳክ 14 ይሆናል፡፡
፪፦ ከነነዌ እስከ ደብረዘይት 41 ቀኖች አሉ፡፡
41 ÷ 30 = 1 ደርሶ ቀሪው 11 የደብረዘይት ተውሳክ ይሆናል፡፡
፫፦ ከነነዌ እስከ ሆሣዕና 62 ቀኖች አሉ፡፡
62 ÷ 30 = 2 ደርሶ ቀሪው 2 የሆሣዕና ተውሳክ ይሆናል፡፡
፬፦ ከነነዌ እስከ እስከ ስቅለት 67 ቀኖች አሉ፡፡
67 ÷ 30 = 2 ደርሶ ቀሪው 7 የስቅለት ተውሳክ ይሆናል፡፡
፭፦ ከነነዌ እስከ ትንሣኤ 69 ቀኖች አሉ፡፡
69 ÷ 30 = 2 ደርሶ ቀሪው 9 የትንሣኤ ተውሳክ ይሆናል፡፡
፮፦ ከነነዌ እስከ ርክበ ካህናት 93 ቀኖች አሉ፡፡
93 ÷ 30=3 ደርሶ ቀሪው 3 የርክበ ካህናት ተውሳክ ይሆናል፡፡
፯፦ ከነነዌ እስከ ዕርገት 108 ቀኖች አሉ፡፡
108 ÷ 30 = 3 ደርሶ ቀሪው 18 የዕርገት ተውሳክ ይሆናል፡፡
፰፦ ከነነዌ እስከ ጰራቅሊጦስ 118 ቀኖች አሉ፡፡ 118 ÷ 30 = 3 ደርሶ ቀርው 28
የጰራቅሊጦስ ተውሳክ ይሆናል፡፡
፱፦ ከነነዌ እስከ ጾመ ሐዋርያት 119 ቀኖች አሉ፡፡ 119 ÷ 30 =3 ደርሶ ቀሪው 29 የጾመ
ሐዋርያት ተውሳክ ነው፡፡
፲፦ ከነነዌ እስከ ጾመ ድኅነት 121 ቀኖች አሉ፡፡ 121 ÷ 30 = 4 ደርሶ ቀሪው 1 ሲሆን የጾመ ድኅነት ተውሳክ 1 ይሆናል፡፡
•••
ከዚህ ተነስተን አጽዋማትንና በዓላትን ተውሳኮቻቸውን ከነነዌ ጋር (ከዘመኑ መባጃ ሐመር) ጋር እየደመርን እናገኛለን፡፡
ስለዚህ የ2015 የነነዌ ጾም መግቢያ ጥር 29 ቀን ይሆናል፡፡
21+8= 29 ስለሆነ ነው፡፡
★ ዐቢይ ጾም ተውሳኩ 14 ነው
= 14 +29= 43 ይህን በ30 ገድፈን ቀሪው 13 ሲሆን ስለዚህ ዘንድሮ በዘመነ ሉቃስ ዐቢይ ጾም የካቲት 13 ይገባል ማለት ነው፡፡
* ደብረ ዘይት፡ ተውሳኩ 11 ነው፡፡
11+29 = 40 ይህን በ30 ገድፈን ቀሪው 10 ይሆናል፡፡ የካቲትን ስላለፍን በመጋቢት 1ዐ
እሁድ ደብረዘይት ይሆናል።
★ ሆሣዕና ተውሳኩ 2 ነው፡፡
= 2+29 =31 ይህን በ30 ገድፈን ቀሪው 1 ስለሆነና መጋቢትን ስላለፍን ሆሳዕና ሚያዚያ
1 ቀን በዕለተ እሁድ ይሆናል፡፡
★ ስቅለት ተውሳኩ 7 ነው፡፡
7+29= 36 ይህን በ30 ገድፈን ቀሪው 6 ሲሆን ዘንድሮ በሚያዝያ 6 ዓርብ ስቅለት
ይሆናል፡፡
★ ትንሣኤ ተውሳኩ 9 ነው፡፡
9 +29 = 38 ይህን በ30 ገድፈን ቀሪው 8 ሲሆን ሚያዝያ 8 በዓለ ትንሣኤ ይውላል።
★ ርክበ ካህናት ተውሳኩ 3 ነው፡፡
3 +29 = 32 ይህን በ30 ገድፈን ቀሪው 2 ስለሚሆንና በሚያዝያ ስላለፍን በግንቦት 2
ረቡዕ ርክበ ካህናት ይሆናል።
★ ዕርገት ተውሳኩ 18 ነው፡፡
18 +29 = 47 ይህን በ30 ገድፈን ቀሪው 17 ሲሆን ዘንድሮ ግንቦት 17 ሐሙስ በዓለ
ዕርገት ይሆናል።
★ ጰራቅሊጦስ ተውሳኩ 28 ነው፡፡
28 +29= 57 በ30 ገድፈን ቀሪው 27 ስለሆነ በግንቦት 27 እሁድ በዓለ ጰራቅሊጦስ
ይውላል።
★ ጾመ ሐዋርያት ተውሳኩ 29 ነው፡፡
29 +29=58 ይህን በ30 ገድፍን ቀሪው 28 ሲሆን በግንቦት 28 ሰኞ የሐዋርያት ጾም
ይገባል።
★ጾመ ድኅነት ተውሳኩ 1 ነው፡፡
= 1 + 29 =30 በመሆኑም ጾመ ድኅነት(የረቡዕና ዓርብ ጾም) ግንቦት 30 ይገባል።
አምላካችን እግዚአብሔር በዲሱ ዓመት አዲስ ልብና ቀና መንፈስ ያድለን የስደት፣የርኃብ፣የጦርነትና የጭንቅ ጊዜያትን ያሣጥርልን።

ዐውደ ዓመት ለባርኮ ባርኮ ዐውደ ዓመት
ንዒ ማርያም ለምሕረት ወሣኅል

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when HIV AIDS club posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share