23/07/2024
የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ አለም አቀፍና ቀጣናዊ ትስስር ሃላፊ ፋኖ ዳዊት ቀፀላ መልዕክት
**********************************
ጋሽ አሰግድ ዛሬ ላይ በጠላት እጅ ቢወድቅም ሺሺሺሺዎች አሰግድ አለንና ልባችሁ አይታወክ ሁላችንም በያለንበት ጸንተን እንቁም!!
የትግሉ ባለቤት አማራ የተባለ ህዝብ ነው የምናደርገው የነፃነት ጉዞ ውጣ ውረድ ያለበት ብርሃንና ጨለማም የሚፈራረቅበት ብዙ ሥቃይና መንገላታት የማይታጠበት ነው እንደሁኔታው የራስ ጥላም ሳይቀር ይሸሻል በየትኛውም አጋጣሚ ቢሆን ሞገድ በማይሰብረው ጽኑ ዓላማ ከጫፍ መድረስን ግብ ያደረገ እልፍ ሰራዊት አለን እናም ልባችሁ አይታወክ። መጣ ሄደ በሚል ጉዳይ ላይ የሚባክን ጊዜ የለንም አንበሳው መሬት ላይ ታሪክ መስራቱን እንደቀጠለ ነው ይልቅስ በደራሽ አጀንዳ አትራኮቱ እያለፋችሁ ሂዱ ድላችንን አጣጥሙ ትግላችንን በልኩ ደግፉ በዚህ ግርግር ውስጥም የቆመ ስራ የለም በርካታ ድሎች ተመዝግበዋል።
ይህ ጉዞ መራራ ነው ነብስ የሚገበርበት ነው እንጂ የቅንጦት አይደለም በውስጥ ባንዳ አሳልፎ መስጠትም መማረክም የትግል አጋጣሚዎች ናቸው። ይህ ነውረኛ የሆነ የአገዛዝ ስርዐት ከእስከዛሬው ትግላችን በላይ ዛሬ አንድ ነገር አብራርቶልናል። በተለያዩ የዜና አውታሮቹና በዲጅታል ሰራዊቱ በኩል ካለበት የድል ናፍቆት የተነሳ በሰበር ያራገበው እጅ የመስጠት ዘገባ ለረጅም ጊዜ ያጣውን ደስታ እየካሰበት ቢሆንም ለእኛ ግን ክንዳችን በርግጥም ኃያል እንደሆነ አቅማችንም ጠንካራ ጉልበታችንም የተፈራ ስማችንም የሚያስጨንቅ እንደሆነ የተረዳንበት በጎ አጋጣሚ ነው።
የአማራ ትግል ከዚህም ከፍ ሲል ብዙ ጀግኖችን የሰዋ ነው ይሄው የአማራ ትግል በጀግኖች የደም መስዋዕትነት እልፎች እየተወለዱ ዛሬ መላው የአማራ ምድር በጀግኖች ተሞልቷል እናም አትሸበሩ አይዟችሁ እጅ በአፍ የሚያስጭን ተጋድሎ ውስጥ ያለው ብዙ ነው። ከፊት ካለው ኃያል ስም በላይ እጆቻቸው ኢላማ የማይስቱ ጽኑ ተፋላሚዎች አሉ መሬት ላይ ባሉት ተአምር አድራጊዎች ትገረማላችሁ የሰነፎች ወሬ አይጥለፋችሁ ዝም ብላችሁ እለፉ። ተስፋ የሚያስቆርጥ የትግል ጉዞ የለንም መራራ ዋጋ የሚጠይቅ የድል ጉዞ ላይ ነን ፍፃሜያችን የሚሆነው የፍትህ አደባባይ ላይ ነው። የመላእክት ዓለም በሁከት ተሞልቶ ነበር ነገር ግን በያለንበት ፀንተን እንቁም የሚል የሚያረጋጋ ድምጽ ነበር እኛም እንላለን ሁላችን በያለንበት ፀንተን እንቁም።