19/05/2023
የዛይራይድ ተጠቃሚዎች ክፍያን በዲጂታል መንገድ በVISA ካርድ መፈፀም ይችላሉ ተባለ!
ዛይ ራይድ ከአለም አቀፉ የፋይናንስ ድርጅት VISA ጋር እና አቢሲኒያ ባንክ ጋር በመተባበር ወደ ኢትዮጵያ ለሚመጡ ቱሪስቶች ጥሬ ገንዘቦችን በማስቀረት በኤሌክትሮኒክ ክፍያ መፈፀም የሚያስችል ቪዛ ካርድ ይፋ አደረገ።
ኢትዮጵያ በአፍሪካ ከፍተኛውን የዲፕሎማቲክ ፍስት የምታስተናግድ ቢሆንም ብዙዎቹ ግብይቶች በጥሬ ገንዘብ ተወስነው የቆዩ ሲሆን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየታዩ ያሉ ለውጦች አበረታች ናቸው ያሉት የዛይ ራይድ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሀብታሙ ታደሰ ዛይ ራይድም የአግልግሎት ድርሻውን ለማድግ፣ አግልግሎቱን ለማሻሻል እንዲሁም አለም በቴክኖሎጂ እየተራመደ ያለበትን የኤሌክትሮኒክ የክፍያ ስርዓትን በሀገራችን ለማስፋፋት የተለያዩ ጥረቶችን ሲያድርግ ቆይቷል ብለዋል።
በአለም አቀፍ ደረጃ እጅግ የተለመደውን በካርድ የአግልግሎት ክፍያን የመፈጸም ዘዴ ከአቢሲንያ ባንክ እና በአለም አቀፍ ደረጃ የካርድ ክፍያ አግልግሎት ቴክኖሎጂ አቅራቢ ከሆነው ቪዛ ጋር በመተባበር ወደ አገር ውስጥ የሚገቡ የቪዛ ተጠቃሚዎች የትራንስፖርት አግልግሎቱን ዋጋ በካርዳቸው መክፈል የሚያስችልበትን አግልግሎቱን ለማግኘት ዘመናዊ፣ ቀላል፣ ቀልጣፋ እና ፍፁም አስተማማኝ መንገድ መዘርጋቱን ነው ዛይ ራይድ ዛሬ ያስተዋወቀው።
ደንበኞች የዛይ ራይድን በአዲስ መልክ የተሻሻለውን አፕልኬሽን ከፕሌይ ስቶር ወይም ከአፕ ስቶር በማወረድ እና የሚያስፈልግውን የደንበኛ መረጃ በማስገባት መጠቀም የሚችሉ መሆኑ ተገልጿል።