Ethiomereja ኢትዮመረጃ

Ethiomereja ኢትዮመረጃ We provide information to people that make their lives easier.
(3)

Ethiomereja provides you with up-to-date and comprehensive information for your current and future needs.

ለ 2023 አዲስ ተመራቂዎች (Fresh Graduates) ብቻ የወጣ አሪፍ የስራ እድል!!! Share አድርጉት!!!
20/12/2023

ለ 2023 አዲስ ተመራቂዎች (Fresh Graduates) ብቻ የወጣ አሪፍ የስራ እድል!!! Share አድርጉት!!!

ለ 2023 አዲስ ተመራቂዎች (Fresh Graduates) ብቻ የወጣ አሪፍ የስራ እድል!!! Share አድርጉት!!!👩‍💼👩‍💼👩‍💼👩‍💼
19/12/2023

ለ 2023 አዲስ ተመራቂዎች (Fresh Graduates) ብቻ የወጣ አሪፍ የስራ እድል!!! Share አድርጉት!!!👩‍💼👩‍💼👩‍💼👩‍💼

25/11/2023

እጅግ በጣም ያማል !!!😭😭😭
!!!

17/11/2023

ተወዳጁ ኮሜዲያን ናፒ ኢትዮጵያ ገብቷል።
"I don't want peace...i want problems" በሚለው ትዕይንት የሚታወቅና በቲክቶክ 2 ሚሊዮን የሚጠጋ ተከታይ ያለው ኮሜዲያን የመጀመሪያውን የኮሜዲ ስራውን ከቦሌ አለምአቀፍ አየር ማረፍያ እንዲህ ጀምሮታል።
comedian in Ethiopia Click, follow, like, share this link For more videos https://www.tiktok.com//video/7302347150061669638

THE SECOND VULTURE:In the 1990's there was a widely circulated photo of a vulture waiting for a starving little girl to ...
17/06/2023

THE SECOND VULTURE:
In the 1990's there was a widely circulated photo of a vulture waiting for a starving little girl to die and feast on her corp. That photo was taken during the 1993/94 famine in Sudan, by Kevin Carter, a South African photojournalist, who later won the Pulitzer Prize for this 'amazing shot'.*

*However, as Kevin Carter was savouring his feat and being celebrated on major news channels and networks worldwide for such an 'exceptional photographic skill', he lived just for a few months to enjoy his supposed achievement and fame, as he later got depressed and took his own life!*

*Kevin Carter's depression started, when during one of such interviews (a phone-in programme), someone called in and asked him what happened to the little girl. He simply replied, "I didn't wait to find out after this shot, as I had a flight to catch..." Then the caller said, "I put it to you that there were two vultures on that day, one had a camera".*

*Thus, his constant thought of that statement, later led to depression and he ultimately committed su***de. Kevin Carter could have still been alive today and even much more famous, if he had just picked that little girl up and taken her to the United Nations Feeding Center, where she was attempting to reach or at least take her to somewhere safe.*

*Today, regrettably this is what is happening all around the world. The world celebrates stupidity and inhumane act, at the detriment of other. Kevin Carter should have taken the girl away from that place, which will cost him nothing, yet he didn't. Here is the inhuman posture, "he had all time to take his shot, but he had no time to save the girl's life".*

*Thus, we must all understand that, the purpose of life, is to also touch lives. So are you too a Vulture. In whatever we do, let humanity come first, before what we stand to gain out of the situation. In all we do let's always think of others and how we can be of benefit to humanity, how we can lend a helping hand and wipe away tears. Hence, when we seek knowledge, wealth, fame, skills or even positions, let's think of how we can use it to benefit the people and society at large.*

*Today, there is a lot of poverty in the land, so if our God Almighty has blessed you, be a blessing to others, extend a helping hand to those in need. Remember, you giving, is also a way of appreciating divine blessings, bounties, and favour of God Almighty upon you. Therefore, it is very important that we all should help the poor and needy, the orphans and widows amongst us, so that they can meet their needs. Please don't be a Kevin Carter, be human and think humanity.*

*Beware, we humans are not humans, if we lack humaneness in all we do.*

የጥቆማና የጥንቃቄ መልእክት!!! እባካችሁ ለምታቋቸው ሼር አርጉት!!!ይህ ፎቶውን የምትመለከቱት ግለሰብ አደገኛ በመተት የታገዘ የማጭበርበር ልምድ ያለው ሲሆን በአሁኑ ሰአት በገንዘብ ማጭበር...
27/05/2023

የጥቆማና የጥንቃቄ መልእክት!!! እባካችሁ ለምታቋቸው ሼር አርጉት!!!
ይህ ፎቶውን የምትመለከቱት ግለሰብ አደገኛ በመተት የታገዘ የማጭበርበር ልምድ ያለው ሲሆን በአሁኑ ሰአት በገንዘብ ማጭበርበር ወንጀል የሚፈልግ ስለሆነ ያያችሁት ወይም ያለበትን የምታውቁ በአቅራቢያችሁ ወዳለ ፖሊስ ጣብያ ወይም በ 0911674653 እንድታሳውቁን በትህትና እንጠይቃለን።

Really sad!!!
24/02/2023

Really sad!!!

" በዛሬው እለት በነዳጅ ፍለጋ ላይ ተሰማርቶ ከቆየው ፖሊ—ጂሲ.ኤል ጋር የነበረን ውል አቋርጠናል።  ከፖሊ—ጂሲ.ኤል ጋር የነበረው ውል የተቋረጠው ከረጅም ጊዜ ትእግስትና ማስጠንቀቂያዎች በኋ...
21/09/2022

" በዛሬው እለት በነዳጅ ፍለጋ ላይ ተሰማርቶ ከቆየው ፖሊ—ጂሲ.ኤል ጋር የነበረን ውል አቋርጠናል። ከፖሊ—ጂሲ.ኤል ጋር የነበረው ውል የተቋረጠው ከረጅም ጊዜ ትእግስትና ማስጠንቀቂያዎች በኋላ ነው። በቀጣይም የነዳጅ ሀብቱን ወደ ስራ የሚያስገቡ አፋጣኝ ስራዎችን እንሰራለን። " ኢ/ር ታከለ ኡማ (የማዕድን ሚኒስትር)

18/09/2022

For Clarity: We are saying No More to the exploitation of the Horn of Africa! No more disinformation, division and war used to promote and maintain that exploitation! No more TPLF! No more to its child soldiers! No more terror on Amharas and Afars! No more scapegoating Eritrea! No more puppet clannist governments in Somalia! No more tribalism and clannism! No more divide and conquer! No more terrorism! No more sanctions! No more gunboat diplomacy! No more interfering in the affairs of sovereign African nations! No more neocolonialism in Africa! No more insulting the intelligence of African peoples! No more gaslighting us! No more censorship of African voices!

18/09/2022
18/09/2022

New Profile Pic! In Solidarity.🇪🇹🇪🇷🇸🇴🌍 See you at the White House at 2:00PM. Division

18/09/2022

A PROTEST AGAINST US FOREIGN POLICY IN THE HORN OF AFRICA

18/09/2022

New Profile Pic in Solidarity with those rallying in DC today against destructive US foreign policy in the Horn of Africa.

አቶ ሬድዋን ሁሴን አቶ ገዱ አንዳርጋቸውን ተክተው የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ፡፡ሹመቱ የተሰጠው በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ነው፡፡ጠቅላይ ሚኒስት...
03/06/2022

አቶ ሬድዋን ሁሴን አቶ ገዱ አንዳርጋቸውን ተክተው የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ፡፡

ሹመቱ የተሰጠው በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ነው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተጨማሪም፡- አቶ ሄኖስ ወርቁን የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ፣ አቶ ወንድሙ ሴታ የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ፣ አቶ ካሊድ አብዱራሂማን በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ የፕሮጀክቶች ክትትል ሃላፊ አድርገው ሾመዋል፡፡

በሌላ በኩል ወ/ሮ መሰረት ዳምጤ የፌዴራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ዋና ኦዲተር እንዲሁም አቶ አበራ ታደሰ ደግሞ ምክትል ዋና ኦዲተር ሆነው በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት እንዲሾሙ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠይቀዋል፡፡

03/06/2022

ግንቦት 26 ቀን 2014 ዓ.ም
አዲስ አበባ
9ኛ መደበኛ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ ውሳኔ
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 9ኛ መደበኛ ስብሰባ በ2015 የፌዴራል መንግስት በጀት ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ፡፡
የፌዴራል መንግስት የ2015 በጀት ዓመት የበጀት ዝግጅት በአስር ዓመቱ መሪ የልማት ዕቅድ የተቀመጡ ግቦችን ከማስፈጸም አኳያ፣ የሀገር ደህንነትን ከማስጠበቅ፣ የተፈናቀሉ ዜጎችን ከመርዳትና የወደሙ መሰረተ ልማቶችን እና አገልግሎቶችን መልሶ ከማቋቋም፣ ቀጣይ የማህበራዊና የኢኮኖሚ ትራንስፎርሜሽን አቅጣጫዎችና ዓላማዎችን ማሳካት ማእከል በማድረጋ እንዲሁም የ2015-2019 የመካከለኛ ዘመን የማክሮ ኢኮኖሚና የፊስካል ማዕቀፉን መሰረት በማድረግ ተዘጋጅቶ የቀረበ ነው፡፡
በዚህም መሰረት ለ2015 በጀት ዓመት ለመደበኛ ወጪ ብር 347.12 ቢሊዮን፣ ለካፒታል ወጪ ብር 218.11 ቢሊዮን እንዲሁም ለክልል መንግሥታት ድጋፍ ብር 209.38 ቢሊዮን እና ለዘላቂ የልማት ግቦች ማስፈጸሚያ ብር 12.0 ቢሊዮን የተያዘ ሲሆን አጠቃላይ የፌዴራል መንግሥት የ2015 በጀት ብር 786.61 ቢሊዮን ሆኖ ቀርቧል፡፡ ከ2014 በጀት ዓመት በጀት ጋር ሲነጻጸር የብር 111.94 ቢሊዮን ወይም የ16.59 በመቶ እድገት አሳይቷል፡፡
ምክር ቤቱም በቀረበለት የፌዴራል መንግሥት የ2015 በጀት ላይ በስፋት ከተወያየ በኋላ ግብዓቶችን በማከል ይጸድቅ ዘንድ ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ መካሄዱን የቀጠለ ሲሆን ዛሬ በተካሄደ ምርጫ ጉባኤው ፤ ብፁዕ አቡነ አብርሃምን የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ እንዲሁም ብፁዕ አቡነ ጴጦሮስን የቅዱስ ሲ...
01/06/2022

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ መካሄዱን የቀጠለ ሲሆን ዛሬ በተካሄደ ምርጫ ጉባኤው ፤ ብፁዕ አቡነ አብርሃምን የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ እንዲሁም ብፁዕ አቡነ ጴጦሮስን የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ በማድረግ መሾሙን ከኢኦተቤ ህዝብ ግንኙነት ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

የቀድሞ የሜቴክ ዋና ዳይሬክተር ሜ/ጀ ክንፈ ዳኘው ከእስር ተፈቱ እየተባለ በማህበራዊ  ድረ ገጽ የሚሰራጨው መረጃ ሀሰት ነው።ሜ/ጀ ክንፈ ዳኘው ከተከሰሱባቸው የሙስና ክሶች መካከል የመርከብ ...
05/03/2022

የቀድሞ የሜቴክ ዋና ዳይሬክተር ሜ/ጀ ክንፈ ዳኘው ከእስር ተፈቱ እየተባለ በማህበራዊ ድረ ገጽ የሚሰራጨው መረጃ ሀሰት ነው።

ሜ/ጀ ክንፈ ዳኘው ከተከሰሱባቸው የሙስና ክሶች መካከል የመርከብ ግዢ እና የእርሻ መሳሪያ ግዥ ጋር ተያይዞ የቀድሞ ጠ/ሚ አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ እና የኢጋድ ዋና ጸሀፊ ዶ/ ር ወርቅነህ ገበየሁን ጨምሮ ሌሎችም የመከላከያ ምስክሮች እንዲቀርቡ በታዘዘው ትዕዛዝ መሰረት የመከላከያ ማስረጃ ለመስማት ፍርድ ቤቱ በቀጠሮ ላይ መሆኑ ይታወቃል።

በሌላ በኩል ሜ/ጀ ክንፈ ዳኘው ከህዳሴው ግድብ ምንጣሮ ጋር ተያይዞ በቀረበባቸው ሌላኛው የሙስና ክስ ነጻ የተባሉ ቢሆንም በቀሪ ክሶች ግን በቀጠሮ ላይ ይገኛሉ።

ከእስር ተፈተዋል እየተባለ የሚናፈሰው መረጃ ሀሰት ነው።

ሩስያ ፌስቡክን አገደች።ሩስያ በሀገሯ ውስጥ ፌስቡክ የተሰኘው የማህበራዊ ሚዲያ አገልግሎት እንዳይሰጥ ሙሉ በሙሉ ዘግታዋለች።ሩስያ ከጥቅምት 2020 ጀምሮ ቢያንስ 26 በሚሆኑ የሩሲያ ሚዲያዎች...
05/03/2022

ሩስያ ፌስቡክን አገደች።

ሩስያ በሀገሯ ውስጥ ፌስቡክ የተሰኘው የማህበራዊ ሚዲያ አገልግሎት እንዳይሰጥ ሙሉ በሙሉ ዘግታዋለች።

ሩስያ ከጥቅምት 2020 ጀምሮ ቢያንስ 26 በሚሆኑ የሩሲያ ሚዲያዎች እና የመረጃ ምንጮ ላይ መድልዎ መፈፀሙን ገልፃለች።

በተጨማሪም በቅርብ ጊዜ ከክሬምሊን ጋር የተቆራኙ የሚዲያ ምንጮች RT Newsና Sputnik News በመላው አውሮፓ እንዲገደቡ መደረጉን አመልክታለች።

ይህንንም ተከትሎ ሩስያ ፌስቡክ ሙሉ በሙሉ በምድሯ ላይ አገልግሎት እንዳይሰጥ ዘግታዋለች።

የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ።በ2013 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ሊሰጥ የነበረው የ12ኛ ክፍል ፈተና በተለያዩ ሀገራዊ ምክንያቶች ወደ 2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ተሸጋግሮ በሁለት ዙ...
23/02/2022

የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ።

በ2013 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ሊሰጥ የነበረው የ12ኛ ክፍል ፈተና በተለያዩ ሀገራዊ ምክንያቶች ወደ 2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ተሸጋግሮ በሁለት ዙር መሰጠቱ ይታወቃል።

የመጀመሪያው ዙር የሲቪክስ ፈተና በሁሉም ትምህርት ቤቶች በሚባል ደረጃ የውጤት መመሳሰልና ግሽበት ታይቶበታል። ስለሆነም የሲቪክስ የፈተና ውጤት ለዩኒቨርስቲ መግቢያ መወዳደሪያነት #እንዳያገለግል ተወስኗል።

በሌሎቹ የትምህርት ዓይነቶች የተገኘው የውጤት ትንተና ሲታይ ምንም ዓይነት ችግር የሌለበት በመሆኑ እንዲመዘገብ ተደርጓል።

ለከፍተኛ ትምህርት ገብተው ለመማር ብቁ የሚሆኑ ሁሉም ተማሪዎች ለመግቢያነት የሚያገለግሉ የትምህርት ዓይነቶችን አጠቃላይ አማካይ ነጥብ 50% እና በላይ ያመጡ ተማሪዎች ይሆናሉ።

ለምሳሌ በሰባት የትምህርት ዓይነት ተፈትነው ከ600 ለሚያዝላቸው ተማሪዎች አማካይ ውጤት 300 እና በላይ ማምጣት ይጠበቅባቸዋል።

በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ገብተው ለሚማሩ ተማሪዎች የዩኒቨርስቲዎችን የመቀበል አቅም በማገናዘብ ዝርዝር የመግቢያ ነጥብ ወደፊት ይገለፃል።

ተማሪዎች የሚከተሉትን አማራጮች በመጠቀም ውጤታቸውን ማወቅ ይችላሉ።

1) በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዌብሳይት፡- www.result.neaea.gov.et

2) በትምህርት ሚኒስቴር ዌብሳይት፡- www.result.ethernet.edu.et
ውጤታቸውን ማየት ይችላሉ።

(የአገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ)

የወልቂጤ ከተማ እና የሲዳማ ቡናን የመሩት ረዳት ዳኛ ዳንኤል ጥበቡ ከውድድሩ መሰናበታቸው ተገልጿል፡፡ በተጠናቀቀው የ13ኛ ሳምንት የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ወልቂጤ ከተማ እና ሲዳማ...
23/02/2022

የወልቂጤ ከተማ እና የሲዳማ ቡናን የመሩት ረዳት ዳኛ ዳንኤል ጥበቡ ከውድድሩ መሰናበታቸው ተገልጿል፡፡
በተጠናቀቀው የ13ኛ ሳምንት የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ወልቂጤ ከተማ እና ሲዳማ ቡና ባደረጉት ጨዋታ ላይ ረዳት ዳኛው ባሳዩት የዳኝነት ስህተት ነው ቅጣቱ የተላለፈባቸው፡፡
በዕለቱ ወልቂጤ ከተማ በመጀመሪያው አጋማሽ በአማካዩ በሀይሉ ተሻገር አማካኝነት ግብ ያስቆጠረ ቢሆንም÷ ረዳት ዳኛ ኳሱ ከጫዋታ ውጭ ነዉ ማለታቸውን ተከትሎ ጎሉ ሳይፀድቅ ቀርቷል፡፡
ይሁን እንጂ ጎሉ ከጨዋታ ውጭ አለመሆኑ በዳኞች ኮሚቴ ከተረጋገጠ በኋላ ኮሚቴዉ የዕለቱ ረዳት ዳኛ ዳንኤል ጥበቡ በፈፀሙት የዳኝነት ስህትት ከውድድሩ በማገድ ከድሬዳዋ አሰናብቷቸዋል፡፡

 የቀድሞ የብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት ቢሮ 22 ሰራተኞች  የስር ፍርድ ቤት የፈቀደውን የዋስትና መብታቸው  በጠቅላይ ፍርድ ቤት ተሻረ።ውሳኔውን የሻረው የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት 1ኛ ይግ...
23/02/2022



የቀድሞ የብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት ቢሮ 22 ሰራተኞች የስር ፍርድ ቤት የፈቀደውን የዋስትና መብታቸው በጠቅላይ ፍርድ ቤት ተሻረ።

ውሳኔውን የሻረው የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት 1ኛ ይግባኝ ሰሚ ችሎት ነው።

የቀድሞ የብሔራዊ መረጃና ደህንንነት ቢሮ ምክትልዳሬክተር አቶ ያሬድ ዘሪሁን እና የተቋሙ የፀረሽብር ጉዳዮች መምሪያ ሀላፊ አቶ ተስፋዬ ኡርጌን ጨምሮ 22 ተከሳሾች የዋስትና መብታቸው እንዲከበር ፍርድ ቤቱን ጠይቀው የነበረ ሲሆን ከሳሽ ዓቃቤ ህግም ዋስትናው ሊፈቀድ እንደማይገባ እና ተደራራቢ ክስ እንዳለባቸው በማመላከት ተከሳሾቹ ቢወጡ ላይመለሱ እንደሚችሉ እና ከህወሓት የሽብር ቡድን ጋር ሊቀላቀሉ ይችላሉ ሲል በመቃወም ዘጠኝ ነጥቦችን ጠቅሶ መቃወሚያ አስገብቶ ነበር።

መዝገቡን የመረመረው ይግባኝ ሰሚ ችሎቱ በዛሬው ቀጠሮ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔን በመሻር በሁለት አብላጫ ድምጽ በአንድ ዳኛ ልዪነት ተከሳሾቹ ከነበራቸው ስልጣን አንጻር በወንጀለኛ መቅጭያ ስነስርአት ህግ አንቀጽ 67/ሀ መሰረት የሀገሪቱን ነባራዊ ሁኔታን ፣ በዋስ ቢወጡ ግዴታቸውን አክብረው ላይቀርቡ ይችላሉ የሚለውን ግምት በመያዝ እና ተደራራቢ ክስ የቀረበባቸው እና ቅጣቱን በመስጋት ቢወጡ ተመልሰው ላይመጡ ይችላሉ የሚል ግምት በመያዝ ጭምር ዋስትናውን መሻሩን ችሎቱ በጽ/ቤት አብራርቷል።

ባሉበት ማረሚያ ቤት ሆነው ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ ውሳኔ ተሰጥቷል።

 አሜሪካ የትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር (TPLF) ተዋጊዎች በአማራ ክልል በነሀሴ ወር መጨረሻ እና በመስከረም መጀመሪያ 2021 የጾታዊ ጥቃትን ጨምሮ አሰቃቂ ድርጊቶች መፈፀማቸውን የሚገልፁ ሪ...
23/02/2022



አሜሪካ የትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር (TPLF) ተዋጊዎች በአማራ ክልል በነሀሴ ወር መጨረሻ እና በመስከረም መጀመሪያ 2021 የጾታዊ ጥቃትን ጨምሮ አሰቃቂ ድርጊቶች መፈፀማቸውን የሚገልፁ ሪፖርቶች በጣም እንዳሳሰባት ገልጻለች።

ሀገሪቱ ይህን ያለችው በቅርቡ የወጣውን የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ሪፖርትን ተከትሎት ትላንት በውጭ ጉዳይ ሚኒስትቴር መስሪያ ቤቷ በኩል ባወጣችው መግለጫ ነው።

ሁሉም የታጠቁ ተዋናዮች በሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚደርሱትን የሰብአዊ መብት ረገጣ እና ጥቃት እንዲያቆሙ አሜሪካ ጥሪ አቅርባለች።

ለችግሩ ዘላቂ እልባት መስጠት እንዲቻል ለተፈጸመው ግፍ ተዓማኒነት ያለው ምርመራ ተደርጎ ተጠያቂነት ሊኖር ይገባል የሚለው ጽኑ አቋሟ መሆኑንም ሀገሪቱ ገልፃለች።

አሜሪካ የጭካኔ ድርጊቶችን የሚገልጹት ሪፖርቶች ቀጣይነት ያለውን ወታደራዊ ግጭት በእስቸኳይ ማስቆም አስፈላጊ መሆኑን አጉልቶ ያሳያል ብላለች።

ግጭቶች እና የጭካኔ ድርጊቶች እንዲቆሙ፣ ሰብዓዊ እርዳታዎች በተሟላ ሁኔታ እንዲዳረስ እና ሰላማዊ የመፍትሔ መንግዶችን ለማፈላለግ ከግጭቱ ተዋናዮች ጋር ተቀራርባ መስራቷን እንደንትቀጥል አሳውቃለች።

 የኢፌዴሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽንን የሚመሩ 11 ኮሚሽነሮችን ሹመት በ5 ድምፀ ታአቅቦ በአብላጫ ድምጽ አፅድቋል።በዚህ መሰረት ፦1ኛ. ፕሮፌሰር መስፍን...
21/02/2022



የኢፌዴሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽንን የሚመሩ 11 ኮሚሽነሮችን ሹመት በ5 ድምፀ ታአቅቦ በአብላጫ ድምጽ አፅድቋል።

በዚህ መሰረት ፦

1ኛ. ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ (ሰብሳቢ)
2ኛ. ወ/ሮ ሂሩት ገብረስላሴ (ምክትል ሰብሳቢ)
3ኛ. ዶ/ር አይሮሪት መሐመድ
4ኛ. ዶ/ር ተገኝወርቅ ጌቱ
5ኛ. ዶ/ር ዮናስ አዳዬ
6ኛ. ዶ/ር አምባዬ ኦጋቶ
7ኛ. አምባሳደር መሐመድ ድሪር
8ኛ. ወ/ሮ ብሌን ገብረመድህን
9ኛ. አቶ ዘገየ አስፋው
10ኛ. አቶ መላኩ ወልደማርያም
11ኛ. አቶ ሙልጌታ አጎ የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክርን በኮሚሽነርነት እንዲመሩ ተሹመዋል።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ተነሳ።የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ በሃገሪቱ ተጥሎ የቆየውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አንስቷል።ምክር ቤቱ በ63 ተቃውሞ በ21 ተአቅቦ በአብ...
15/02/2022

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ተነሳ።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ በሃገሪቱ ተጥሎ የቆየውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አንስቷል።

ምክር ቤቱ በ63 ተቃውሞ በ21 ተአቅቦ በአብላጫ ድምጽ ነው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲነሳ የወሰነው።

ይህን ውሳኔ ተከትሎ÷ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርድ ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም ጋር ተያይዞ ያላጠናቀቃቸው ጅምር ስራዎች ካሉ ይህ ውሳኔ ከተላለፈበት ከዛሬ ጀምሮ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ አጠናቆ ለሚመለከተው አካል ሪፖርት እንዲያደርግ ተወስኗል፡፡

በተመሳሳይ የፍትህ አካላት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም ጋር ተያይዞ የጀመሯቸውን ጉዳዮች በመደበኛው የፍትህ አሰጣጥ ስርአት እንዲያጠናቅቁም መወሰኑን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

 #ተፈርዶበታልበጣልያን ሀገር ገጠራማ ስፍራ በሆነችው ፍራሲሎንጎ ከተማ ፍየሎችን እያረባች በአይብና በፍየል ምርቶቿና በጠንካራ ሰራተኝነቷ የታወቀችውን ኢትጵያዊቷን አጊቱ ጉደታን ቤቷ ውስጥ እ...
15/02/2022

#ተፈርዶበታል

በጣልያን ሀገር ገጠራማ ስፍራ በሆነችው ፍራሲሎንጎ ከተማ ፍየሎችን እያረባች በአይብና በፍየል ምርቶቿና በጠንካራ ሰራተኝነቷ የታወቀችውን ኢትጵያዊቷን አጊቱ ጉደታን ቤቷ ውስጥ እያለች በአሰቃቂ ሁኔታ የገደለው የ33 ዓመቱ ጋናዊ ስደተኛ ሱሌይማን አዳምስ 20 ዓመት እስር ተፈርዶበታል።

የትሬንቶ ፍርድ ቤት ሰኞ ዕለት በዋለው ችሎት ጋናዊው ሱሌይማንን በነፍስ ማጥፋት ወንጀል 15 ዓመት ከስምንት ወር እንዲሁም አራት ዓመት ከአራት ወር ወሲባዊ ጥቃት በመፈጸም ፍርድ አስተላልፎበታል።

በተወሰነው ቅጣት ቤተሰቧ ደስተኛ አይደለም።

ኢትዮጵያ ውስጥ የምትገኘው የአጊቱ እህት ሀወኒ ኤዳዎ ጉደታ ለቢቢሲ በሰጠችው ቃል ቤተሰቧ ፍርድ ቤቱ በገዳዩ ላይ ያሳለፈው የእስር ቅጣት በቂ ነው ብሎ እያምንም ብላለች።

ሀወኒ ኤዴዎ " ምንም እንኳን ቅጣቱ እሷን የሚመልሳት ባይሆንም፣ ከተፈጸመው ወንጀል አኳያ ውሳኔው በቂ አይደለም። እኛ የእድሜ ልክ አስራት ይፈረዳል ብለን ጠብቀን ነበር" ስትል ለቢቢሲ ተናግራለች።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል።በዛሬው እለት የካቲት 8 ቀን 2014 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋ...
15/02/2022

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል።

በዛሬው እለት የካቲት 8 ቀን 2014 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች በመስቀል አደባባይና በጃንሜዳ ባህረ ጥምቀት ቦታዎች በቀረቡ ጥያቄዎች ላይ የጋራ ውይይት ማድረጋቸውን ገልፀዋል።

ውይይቱ በፍጹም ቅን ልቡና፣ መደማመጥና መግባባት በተሞላበት ስሜት መካሄዱ ተገልጿል።

በውይይቱ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የመስቀል አደባባይና የጃንሜዳ ባሕረ ጥምቀትን በተመለከተ የተነሱትን ጥያቄዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ የጋራ ኮሚቴ በማቋቋም ቀጣይ ውይይቶችን መሠረት በማድረግ የማያዳግም ምላሽ ለመስጠት የጋራ ስምምነት ላይ ተደርሷል።

ወደፊት ቤተ ክርስቲያንና የከተማ አስተዳደሩ በልማት፣ በሰላምና በተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ተቀራርበው እንደሚሰሩ ይፋ ገልፀዋል።

14/02/2022



የቱርክ መንግስት ለቅድመ እና ድኅረ ምሩቃን የ2022 ነፃ የትምህርት ዕድል ክፍት አድርጎ አመልካቾችን እየተቀበለ ነው።

ነፃ የትምህርት ዕድሉ ለመጀመሪያ፣ 2ኛ፣ 3ኛ እና የምርምር ዲግሪ ፕሮግራሞች ለሚያመለክቱ የሚሰጥ ነው።

የዕድሉ ተጠቃሚ ተማሪዎች ወጪያቸው በቱርክ መንግስት የሚደገፍ ነው።

ከጥር 12 ቀን 2014 ዓ/ም የጀመረው የማመልከቻ ጊዜው የፊታችን የካቲት 13/2014 ዓ.ም ያበቃል።

ለማመልከት ይህን https://turkiyeburslari.gov.tr/ ማስፈንጠሪያ ይጫኑ።

የሩሲያና የፈረንሳይ መሪዎች የተወያዩበት ጠረጴዛ 4 ሜትር የረዘመው የፕሬዝዳንት ፑቲንን ለመጠበቅ ነው- ክሬምሊንየሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን እና የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮ...
12/02/2022

የሩሲያና የፈረንሳይ መሪዎች የተወያዩበት ጠረጴዛ 4 ሜትር የረዘመው የፕሬዝዳንት ፑቲንን ለመጠበቅ ነው- ክሬምሊን

የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን እና የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ከሰሞኑ በሞስኮ ተገናኝተው በዩክሬን ጉዳይ ላይ በተወያዩበት ወቅት በመካከላቸው የነበረው የጠረጴዛ ርቀት በበርካቶች ዘንድ መነጋሪያ ሆኖ ከርሟል።

የሩሲያው ክሬምሊን ቤተ መንግስት፤ የጠረጴዛው ርቀት የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኤል ማክሮን የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ለማድረግ ፍቃደኛ ባለመሆናቸው ነው ብሏል። እርምጃው የተወሰደውም የፕሬዝዳንት ፑቲንን ጤንነት ለመጠበቅ ነው ብሏል።

ፈረንሳይ በበኩሏ በፕሬዚዳንት ማክሮን የኮሮና ምርመራ ያላደረጉት ዘረ መላቸው (DNA) ሩሲያዎች እጅ እንዳይገባ ለመጠንቀቅ እንደሆነ አስታውቃለች።

ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ከመስቀል አደባባይ ፤ወይብላ ማርያም እና ባንዲራ  ጋር ተያይዞ ለተነሱት ጥያቄዎች የሰጡት ማብራርያ፤-👉  በመጀመርያ በመስቀል አደባባይ የፕሮቴስታንት አማኞች የጠ...
11/02/2022

ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ከመስቀል አደባባይ ፤ወይብላ ማርያም እና ባንዲራ ጋር ተያይዞ ለተነሱት ጥያቄዎች የሰጡት ማብራርያ፤-
👉 በመጀመርያ በመስቀል አደባባይ የፕሮቴስታንት አማኞች የጠየቁት የገቢ አሰባሰብ ፕሮግራም ፍቃድ ሰጥተናል፡፡
👉 ፕሮግራሙ ሊካሄድ አንድ ቀን ሲቀረው አንድ ከፕሮግራሙ ጋር ግንኙነት በሌለው ሰው እንወርሳለን የሚል ሃሳብ ተንፀባረቀ፡፡
👉 ይህም በኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ዘንድ ቁጣ የፈጠረ በመሆኑ ግንኙነት ስናደርግ ይህን ያለው ከፕሮግራሙ ጋር ግንኙነት የሌለው ሰው መሆኑን ነግረናቸው ፤ ነገር ግን በዚህም ወገን ያለው አባባልና እሱን መሰረት አድርጎ የተፈጠረውን ስሜት ሁለቱም ሃይ ሊባሉ ይገባል አልናቸው፡፡
👉 ነገር ግን ጉዳዩ ጠንከር እያለ ሲሄድ በፕሮግራሙ እለት ተገኝተን ይሄ አደባባይ የሁላችንም ነው በማለት ማንም ወራሽ እና ተወራሽ እንደሌለ የሚጠቁም መልእክት አስተላለፍን
👉 ይህ አባባል በዛ መድረክ ሲነገር የመጀመርያ አልነበረም፤ ሌሎችም ተናግረዋል፡፡ እኔ ራሴ ደጋግሜ በተለያዩ ፕሮግራሞች ተናግርያለሁ፡፡
👉 ስለዚህ ጉዳዩን አሁን እንዲባባስ ያደረገው የተጫጫኑ ስሜቶች በመኖራቸው ምክንያት ነው፡፡
👉 ስለዚህ ጥያቄው ሲገፋ ያልነው በህጋዊና ሰላማዊ መንገድ እንፍታ ነው ያልነው፡፡ በመረጃና በማስረጃ መፍታት የሚቻልባቸው ብዙ አማራጮች አሉ፡፡
👉 ከአደባባይ ጋር በተያያዘ የውጪ ብቻ ሳይሆን የራሷ የራሷ የኢትዮጵያ ልምድም ጭምር አለ፡፡
👉 ግንኙነት ለማድረግ ከመጀመርያው አንስቶ ብዙ ጥረት ተደርጓል ፤ከመጀመርያው የፓትርያርኩ መታመም አንስቶ በተለያዩ ምክንያቶች ተራዝሟል፡፡
👉 እኔ በግሌ ፓትርያርኩ ጋር በመሄድም ጉዳየን በሰላማዊና ህጋዊ መንገድ እንፍታ ብዬ አነጋግርያለሁ፡፡ ልዩነት አልነበራቸውም፡፡ ይህንን ሃሳባችሁን በደብዳቤ አስገቡልን አሉን ይህንንም አድርገናል፡፡
👉 ከዚህ ቀደም አስፈላጊ በሆነ ጊዜ ሁሉ እኛ ወደነሱ እሄዳለን ፤እነርሱም ወደእኛ እየመጡ በርካታ ጉዳዮችን ፈትተናል፡፡
👉 ዛሬ እንኳን ግንኙነት ቀጠሮ አለ ስለተባለ የተወሰነው እዚህ ሆነን ጉባኤውን እናስኪድ ሌሎቻችን ደግሞ እዛ እንሂድ ብለን ተከፋፍለን ነው የሄዱት፡፡
👉 እኛ ከሃይማኖት ጋር ፉክክር የምናደርግ መሪዎች አይደለንም!!
👉 ወይብላ ማርያም ጋር የተከሰተው ክስተት አሳዛኝና መሆን ያልነበረበት ጉዳይ ነበር፡፡እኛም ከልባችን አዝነናል።
👉 በምንም መንገድ ታቦት ውጪ ማደር አልነበረበትም፡፡
👉 ጉዳዩ አሁን በህግ ተይዟል፡፡ እውነታውን አውቀን በህግ ተጠያቂ እስካላደረግን ድረስ ይቅርታ ብቻውን በቂ አይደለም፡፡
👉 ከባንዲራ ጋር ተያይዞ የሚነሱ የተለያዩ ሃሳቦች አሉ፡፡ ይህ ጉዳይ የብሄራዊ ምክክር አጀንዳችን ይሆናል፡፡ በዚህ ምክንያት ጥልም ግጭትም በፍፁም አንፈልግም፡፡ ሰውም እንዲሞት አንፈልግም!! ጉዳዮችን ሁሉ ከፖለቲካ ዝንባሌ ጋር ማያያዝም ተገቢ አይደለም፡፡

Address

Tunisia Avenue
Addis Ababa
0000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiomereja ኢትዮመረጃ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Ethiomereja ኢትዮመረጃ:

Videos

Share


Other Social Media Companies in Addis Ababa

Show All