Lets talk እንወያይ

Lets talk እንወያይ Political News

02/01/2024

ኮፊያ የሌለው ሁላ ባለድንኳኑን ከዝናብና ከፀሐይ እንዲጠለል እየመከረው ነው...

16/12/2023

አዲስ ተስፋ፣ አዲስ አብርሆት ወደ ታላቅ ከፍታ።

ከአራት የኢቢሲ ሰራተኞች ወልዶ የካደው አሉባልተኛ                                               ወገን አበበ የተባለው የኢቢሲ ሰራተኛ ከ4 የተቋሙ ሰራተኞች ወልዶ ...
10/09/2023

ከአራት የኢቢሲ ሰራተኞች ወልዶ የካደው አሉባልተኛ ወገን አበበ የተባለው የኢቢሲ ሰራተኛ ከ4 የተቋሙ ሰራተኞች ወልዶ የካደ መሆኑን የውስጥ ምንጮች እና የዚህ ድርጊት ተጠቂዎች ገልጸውልናል።በተቋሙ ዉስጥ የሚሰሩ ሴት ተቀጣሪዎች ላይ በተደጋጋሚ ትንኮሳ እንደሚያደርግም ከሰራተኞች የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ወገን አበበ ከሰሞኑ በኢቢሲ ውስጥ ከ400 በላይ ሰራተኞች ሀሰተኛ የትምህርት መረጃ አላቸው በማለት በተለያዩ የማህበራዊ ድርገጾች ሃሰተኛ መረጃ እያሰራጨ ያለው በፈጸመው የዲሲፒሊን ግድፈት ሊባረር ጫፍ ላይ በመድረሱ መሆኑን አረጋግጠናል። በዛሬው እለት ተቋሙ ባወጣው መረጃ ግን ግለሰቡ ከ25 ጊዜ በላይ ደሞዝ ተመላሽ የተደረገበት እንዲሁም በርካታ ክሶች እንዳሉበት ለማወቅ ተችሏል።

ጥፋትን በጥፋት መሽፈን አይቻልም ተቋሙ ተገቢውን ማጣራት አርጎ ለህዝብ ይፋ ያድርግ

በሽፋኑ የሚያወድሱትንም ገልጠው ሳያነቡ የሚተቹትንም አትስሟቸው በሌላው አለም መሪዎች ሲጽፉ ወዳጅም ጠላትም ደጋፊም ተቃዋሚም ለማንበብ ይራሯጣል። ምክንያቱም እነዚህ መጽሀፍቶች ለደጋፊው ድጋፉ...
21/03/2023

በሽፋኑ የሚያወድሱትንም ገልጠው ሳያነቡ የሚተቹትንም አትስሟቸው

በሌላው አለም መሪዎች ሲጽፉ ወዳጅም ጠላትም ደጋፊም ተቃዋሚም ለማንበብ ይራሯጣል። ምክንያቱም እነዚህ መጽሀፍቶች ለደጋፊው ድጋፉን ተቃዋሚውም ተቃውሞውን በአመክንዮ ለማስደገፍ ጥሩ አጋጣሚ ነው። በኛ ሀገር ግን ከዚህ የተለየ የሚጽፍ መሪ ሲገኝ እንደ እድል ከማየት ይልቅ ውስጡን ከፍቶ ሳያነበው መጻፉ ላይ ዲስኩር ሲዘበዝብ ይውላል። እውነቱን ልንገርህ ማንበብህ ለማወደስም ይሁን ለማንኳሰስ እድል ይሰጥሀልና እድሉ አያምልጥህ። ምክንያቱም ይህ መጽሀፍ የአንድ ሰው ሀሳብ ብቻ ሳይሆን የሀገር ታሪክ እና ሀሳብ ነው። ባልታወቀ ታሪክ እና ባለተገለጠ ሀሳብ ሁሉም ነገር ሚስጥር አድርጎ ከሚመራህ ይልቅ ሀሳቡን ገልጦ እና ታሪክን ጽፎ የሚያጋራህ መሪ ሲገኝ መጽሀፉን አፋፍ አድርገህ በማንበብ እድሉን ተጠቀምብት። ለመውደድም ለመጥላትም ምክንያት ታገኝበታለህ።

27/10/2022
ይህ አዲስ አበባ ነው!
30/09/2022

ይህ አዲስ አበባ ነው!

ኢትዮጵያ
07/07/2022

ኢትዮጵያ

ከንቱዎች ታቀቡ ‼️ሶስተኛው ዙር የጥፋት ድግስ  ይመክናል‼️♦️ስራ ማቆም ፣ቤት የመቀመጥ አድማ፣ አገልግሎት ማቋረጥ የጠላት ሴራ ነው ‼️♦️በሕዝብ ድምጽ  የተመረጠ መንግስት በቀለም አብዮት...
26/06/2022

ከንቱዎች ታቀቡ ‼️ሶስተኛው ዙር የጥፋት ድግስ ይመክናል‼️
♦️ስራ ማቆም ፣ቤት የመቀመጥ አድማ፣ አገልግሎት ማቋረጥ የጠላት ሴራ ነው ‼️
♦️በሕዝብ ድምጽ የተመረጠ መንግስት በቀለም አብዮት ሴራ አይወርድም‼️
♦️ሁሉም ዜጋ ለሀገሩ መከበርና መታፈር በጽናት ይቁም‼️
አትፍረክረክ ‼️ለጠላት ሴራ አትንበርከክ ‼️ጽና ‼️
ክረምቱ እያስገመገመ መግባቱን ተከትሎ እየተደረገና እያየን ያለነው ጥፋትና ሴራ ጠላቶቻችን ወጥነው አቅደው በጊዜ ስሌት እየተገበሩት ያሉት ሀገር አውዳሚና አጥፊ ሴራ ነው። ሁለቱን ግዙፍ የሀገር ማፍረስና የመበተን ሴራዎች ወያኔና ሸኔን አሰልፈው የመሩት ሱዳን ግብጽና ምእራባውያን ናቸው። ሴራቸው ከሽፏል‼️
የመጀመሪያው የጥፋት ምእራፍ ጠቅላይ ሚኒስትሩን በመግደል ወያኔ መንበረ ስልጣኗን ለማስቀጠል ያደረገችው የአብዮት አደባባዮ ሴራ መክኗል። በቡራዩ ዘረፋና ጭፍጨፋ ለማካሄድ የሞከሩትም ሸኔና ወያኔ ነበሩ። ከሽፏል። ቀጣዩ በቤተመንግስት አግአዚን አስገብቶ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ገድሎ መፈንቅለ መንግስት በማድረግ ስልጣን ለመያዝ በተጠና መንገድ ያቀናጁት ወታደራዊ እንቅስቃሴ ብስለት በተመላበት አካሄድ በጠቅላይ ኤታማዦር ሹሙ ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ ፈጣን አመራር ከሽፏል። ቀጣዩ የወያኔና የሸኔ ጥምር ሴራ ከአብዲ ኢሌ ጋር በመሆን ከመቀሌ ከሀዲ ወንበዴዎች አመራር እየተቀበለ በጅጅጋ ውድመትና እልቂት ከፈጠረ በኃላ አልሻባብን አስገብቶ የመገንጠሉን አዋጅ በሬድዮ ለማሰማት ተዘጋጅቶ እያለ በፈጣን ሁኔታ መከላከያ ገብቶ አምክኖታል።
በተመሳሳይ ሰአት ወያኔዎችም አብዲኢሌን ተከትለው ተገንጥለናል ለማለት ተዘጋጅተው የነበረ ቢሆንም እንደማያዋጣ ሲረዱት የጦርነት ዝግጅታቸውን ቀጠሉ።
ወያኔና ሸኔ በደቡብ በምእራብ በመሀል ሀገር በሰሜን በወኪሎቻቸው አማካኝነት ከፍተኛ ደም ማፋሰስን አካሄዱ። የንጹሀን ሕይወት ተቀጠፈ። ንብረት ወደመ። መከላከያ ያለእረፍት በአራቱም ማእዘናት እየተወነጨፈ ሴራውን አመከነ። የወለጋው የሸኔ እንቅስቃሴ የሚመራው በወያኔ ነው። ሰፊ የማጥራት ስራ ቢሰራም በሽምቅ ውጊያ ውስጥ አሸማቂው ኃይል ተነቃናቂና ቋሚ ቦታ ይዞ የማይዋጋ ስለሆነ ለአደን ያስቸግራል።
( Hit and run ) መተህ ተሰወር ፣ የጠላት ኃይል ሲያይል አትዋጋ፣ጠላት በሌለበት ቦታ መኖርህን ለማሳወቅ እርምጃ ውሰድ፣ ገለህ ዘርፈህ አውድመህ ተሰወር፣ የበቀል እርምጃዎችን ውሰድ፣ ትላንት በታየህበት ቦታ ደግመህ አትታይ፣ ሌላና ያልተጠበቀ ቦታ ላይ ሄደህ እርምጃ ውሰድ፣ የምትወስዳቸው እርምጃዎች በጭካኔ የተሞሉ ይሁኑ ይህ ሕዝቡ ተቀጥቶ መንግስት ላይ እንዲነሳ ያደርገዋል ...ወዘተ ይላል "The ABC of GURELLA WAR FARE " አሁን እየሆነ ያለውም ይሄ ነው። ይቀለበሳል‼️ ከነመፍትሄው ወደ መጨረሻው እመለስበታለሁ።
🔴ሁለተኛው የተደራጀ የተቀናጀ የወያኔና የሸኔ አገር አፍራሽ ምእራፍ ወያኔ በ215 በተለያዩ የትግራይ ቦታዎች ላይ ይገኙ በነበሩ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የሰሜን እዝ ላይ በድንገተኛና ባልተጠበቀ ሁኔታ ማጥቃት በመሰንዘር ከፍተኛ ጭፍጨፋና ግድያ ያካሄደበት ነው። ሴኮ መብረቃዊ ማጥቃት ያለው በአረመኔነት በፋሽስትነት የተሞላ ዘግናኝ ጭፍጨፋ በሠራዊታችን ላይ አካሂደዋል። በአጸፋ ማጥቃት ሠራዊታችን በሁሉም አቅጣጫ የጦር ጫፍ ማጥቃት በማድረግ በ15 ቀናት ጊዜ ወያኔን ጠራርጎ ሲመታው ወደቆፈረው ምሽግ ፈርጥጦ ገባ። በዋሻው ውስጥ ሲደራጅ ከርሞ እንደገና በሕዝብ ማእበል ማጥቃት ሰነዘረ። በዚህ ጊዜ ሠራዊታችን ኃይሉን በሙሉ ወደኃላ በመሳብ ገዢ መሬቶችን ተቆጣጥሮ ቆየ። እንደገና ወያኔ በአማራውና በአፋር ክልል ከፍተኛ ወረራዎችን ዝርፊያዎችን ግድያዎችን አካሂዶ ሰፊ መሬቶችን ተቆጣጥሮ እስከ ሸዋ ዘለቀ። ጠላት ወገን ከሚለው ወረዳ በራቀ ቁጥር ጠልቆ ወደ ውስጥ ሲገባ የሰው ኃይሉና ድርጅት አቅርቦቱ እየተመናመነ ሄደ። ሠራዊታችን ሰፊ ማጥቃት ሰንዝሮ ከገባበት መሬት እየጠራረገ አስወጣው። ወያኔ ሽንፈቱን አምኖ ላለመቀበል ለሰላም ስል ለቅቄ ጦሬን ወደ መቀሌ መልሻለሁ አለ። እንደገና ባገኘው አጋጣሚ ሰፊ ሠራዊት ማሰልጠኑን ማስታጠቁን ቀጥሎ በተላላኪዎቹ አማካኝነት በቤኒሻንጉል፤ በጋምቤላና በወለጋ በሸኔና በሌሎቹም ታጣቂዎች አማካኝነት መጠነ ሰፊ ጭፍጨፋ አካሄደ። የዚህ ግብ ከላይ እንደገለጽኩት ሕዝብ በመንግስት ላይ ተስፋ ቆርጦ እሪ ብሎ አምጾ እንዲነሳ ማድረግ ነው። የጠላትህን ሴራና አካሄድ ጠንቅቀህ ካላወክ፣ ችግር በተነሳ ቁጥር መንግስትን የምትኮንን የምታወግዝ ብቻ ከሆነና ለተፈጠረው ችግር መፍትሄ ለማስገኘት ከመንግስት ጎን ቆመህ መታገል ካልቻልክ የጠላትህን ሕልምና ፍላጎት በቀላሉ አሳካህለት ማለት ነው። በእርጋታና በአስተውሎት ከጥላቻና ከፓለቲካ ስካር ወጥተህ ማሰብ ከቻልክ በአንድነትህ ጸንተህ ከቆምክ ሁሉም ችግር ይፈታል። የጠላትም እቅድ ይከሽፋል‼️
🔴የተጀመረው ሶስተኛው የጥፋት ምእራፍ ‼️
በጦርነት ያልቻሉትን በመከፋፈል እርስ በእርስ በማባላት ሕዝብና መንግስትን ሆድና ጀርባ አድርገን አመጽ አስነስተን በሀገሪቱ ስርአተአልበኝነት እንዲሰፍን አድርገን እናፈርሳታለን ብለው ጀምረውታል።
የብሔርና የኃይማኖት ግጭትን በስፋት ማቀጣጠል፣ ፍጅት መፈጸም፣ ይኼን ተከትሎም አመጽ ረብሻ ሁከት እንዲነሳ ማድረግ፣ ሁሉም ነገር ከቁጥጥር ውጪ እንዲሆን በማድረግ ስርአተ አልበኝነት ሰፍኖ መንግስት ማፍረስ፣ በራሳቸው ተላላኪዎች የሽግግር መንግስት ማቋቋም በሂደት በዚህም ኢትዮጵያን ማፍረስ ነው ግቡ። ሲሰሩበት ኖረዋል። ሰዎች አሰልጥነዋል። አዘጋጅተዋል። በተለምዶ ምእራባውያኑ መንግስታትን ሀገራትን ለማፈራረስ የሚጠቀሙበት የቀለም አብዮት የሚሉት መሆኑ ነው።
የስራ ማቆም አድማ ፣ቤት ውስጥ ስራ ትቶ የመቀመጥ አድማ ሁሉ የዚሁ ሀገር ገዳይ ሴራ አካል ናቸው።
ሕዝቡን የማሸበርና ፍርሀት የመልቀቅ ፕሮፓጋንዳ መንዛት፣ ከተማዋን በመረበሽ የትራንስፓርትና የንግድ አገልግሎት በማቋረጥ ሰላማዊ ሰልፍ በመውጣት ውጥረት ማንገስ ከሴራዎቹ ጥቂቶቹ ናቸው። ለዚሀሰ አስፈጻሚዎች ከፍተኛ በጀት ይመድባሉ። በሌላም በኩል በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ሸኔ ኦነግ የፈጸመው አይነት የወንጀል ድርጊት ሊፈጸም ስለሚችል ሕዝቡ ነቅቶ በመደራጀት ከመንግስት ጎን ሆኖ አካባቢውን ሰፈሩን መንደሩን ቀን ከለሊት መጠበቅ አለበት። የአዲስ አበባና አጎራባች ከተሞች ጥበቃ መጠናከር ይገባዋል። የስራ ማቆም አድማና ሰላማዊ ሰልፍ የሚባል ነገር ለማድረግ የሚሞክሩ ሁሉ የተቀናበረው ሴራ አካል ስለሆኑ ቢሰበሰቡ ይመከራል።
ኢትዮጵያ በጫጫታ፣ በግርግር ፣በእብደትና በጩሀት አትፈርስም። መንግስትን መወንጀሉ በምንም መልኩ ለችግሩ መፍትሄ አይደለም። ለችግሩ መፍትሄ የሚሆነው ዋነኛውን ጠላታችንን አውቀን፣ ሊከፋፍለን ያሴረውን ተረድተን ሁላችንም ተባብረን ተደጋግፈን አብረን በጋራ ቆመን ስንመክት የጠላትን ሴራ ስናከሽፍ ብቻ ነው‼️
ለዚህ ሴራ ዋነኛ ተዋናዮቹ ተላላኪና ሀገር ሻጭ ምሁራን፣ በመንግስት ስልጣንና ሠራተኛነት ተመሳስለው አድፍጠው ያሉ የቀበሮ ባሕታውያን፣ በሚዲያው ውስጥ የሚሰሩ በጋዜጠኝነት ስም የሚነግዲና በኃላፊነት የተቀመጡ አስመሳዮች፣ የተለያዩ በኤንጂኦ ስም የተቋቋሙና በሽፋን የሚሰሩ ዶላር የሚዘንብላቸው፣ የመንግስትን ቁጥጥር ለማለፍ ለጥፋት ስራ ማስኬጃቸው በቀጥታ ከኤምባሲና ከግለሰቦች ገንዘብ የሚሰጣቸው ሰዎች ናቸው። ሌሎቹ ተዋናዮች ዮቲዮበሮችና አክቲቪስቶች የማሕበራዊ ሚዲያው የጠላት ዲጂታል ሠራዊት ነው። ለዚህ ስራ ከውጭ የመጡ ሰዎች በምእራባውያን ኤምባሲዎች በኩል በመንግስት ላይ ለማነሳሳት ሰፊ ስልጠና ሲሰጡ ፣ ጋዜጠኞችን ተጠቅመው ማሕበር እስከ ማቋቋምና እስከ መርዳት ሲደርሱ መንግስት የት ነበር ? አረ እባካችሁ ንቁ...ወሬው ይብቃ...ወደስራ ግቡ ሰው አታስፈጁ...አይንና አፍንጫችሁ ስር ሲዶለት የት ነበራችሁ ? አጃኢብ ያሰኛል !! ቀድሞ መገኘት ነው ስኬት !!
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አንድ ሰው ነው። ስንት ቦታ ይሆናል ? የሀገርን ኃላፊነት ሁሉም በጋራ ካልተወጣው አንድ ሰው ብቻውን ምን ማድረግ ይችላል ? እንዲህ አይነት የጨነቀ ነገር ነው የገጠመን። ለሁሉም ዛሬም ወደፊትም ከመሪያችን ጎን በጽናት እንቆማለን። በወሬ አሉባልታና በሽብር የምትፈርስ ሀገር የለችንም። ብዙ ሚሊዮኖች ጸንተው ቆመው ይጠብቋታል። ክፋውንም ቀን በድል እንሻገራለን። አዲስ አበባ ላይ ተደብቆና ተመሳስሎ ቀን የሚጠብቀው የወያኔና የሸኔ ኃይል ከያለበት ታስሶ ይመንጠር። የቀንና የለሊት ጥበቃው ይጠናከር። ቀበሌ፣ ዞን፤ ክፍለከተማ ክልል ድረስ እንደ በፊቱ ነዋሪውን ያሳተፈ ጥበቃ ከፓሊስ ጋር ተቀናጅተው ያካሂዱ። ጠላት አልተኛም። እኛም አንተኛ። ዘመቻው አልቋል ብሎ መሸላለሙ ይብቃ ። መቼ ነው ያለቀው ? እንዲህ አይነቱ ራስን ማታለል ይቁም። ተጎጂዎቹ እኛው ነን።
♦️እንበርታ እንጠንክር..ለቅሶና ጫጫታው ይብቃ ‼️
♦️በመከራ የማንፈታ፣ በችግርና በማእበል የማንናወጥ እንደደአለት የጸናን ብርቱ ሕዝብ ነን ‼️
♦️ድል ለኢትዮጵያና ለልጆቿ ‼️
ጃተማ አባቢያ
የማትንበረከከዋ ኢትዮጵያ

ከዛሬ ፎቶዎች መካከል የአፍሪካ ቀንድ ሲስቀቅ
09/06/2022

ከዛሬ ፎቶዎች መካከል
የአፍሪካ ቀንድ ሲስቀቅ

20/05/2022

ብሔራዊ ደህንነት የተካሔደው እጅግ ጠቃሚ ነው

30/04/2022

ከጀግኖች መንደር

የዩሃንስ ቧያለው ለከት ያጣ ወሬ መስማት በራሱ ይቀፋል !!እውነት እንነጋገር ከተባለ ከዘመነ ኢህአዴግ ጀምሮ ለአማራ ህዝብ ያበረከተው አስተዋፅኦ አለ ? እስኪ ይሄ ነው የሚባል ስራ አሳዩኝ ...
23/04/2022

የዩሃንስ ቧያለው ለከት ያጣ ወሬ መስማት በራሱ ይቀፋል !!

እውነት እንነጋገር ከተባለ ከዘመነ ኢህአዴግ ጀምሮ ለአማራ ህዝብ ያበረከተው አስተዋፅኦ አለ ? እስኪ ይሄ ነው የሚባል ስራ አሳዩኝ ?

እኔ ዬሃንስ ቧያለውን የምገልፀው ማንም ምኑ ያልሆነ ስልጣኑን እና ዝናውን ለማስጠበቅ ብቻ የሚጮህ ቁራ ነው።
ዬሃንስ ቧያለው ማለት እጅግ ከልክ በላይ የሚጠጣ የፓርቲ ድስፕሊን የሌለው የማንንም ልቃሚ አጀንዳ ይዞ የሚጮህ መድረክ የማይመርጥ ከንቱ የሆነ ግለሰብ ነው። ሰዎች ስለ ዬሃንስ ቧያለው ሲያወሩ ይገርመኛል !

አንድም ጠብ የሚል ቁምነገር ያልሰራ ስው የአማራ ህዝብ ወኪል ሁኖ ሲዘባርቅ መስማት በሽታ ነው።
አሁንም ደግሜ ደግሜ ስለዬሃንስ ቧያለው የምናገረው በዘመነ ኢህአዴግም ሆነ በዘመነ ብልፅግና የአማራን ህዝብ እንዲፈናቀል እንዲታረድ እና እንዲሳደድ የደገስው ክፍት እንደሆነ አስረግጨ መናገር እችላለሁ። አሁን ላይ የዬሃንስ መንገድ የአማራ ህዝብ መንገድ አይደለም !!

አማራ መሪውን ያከብራል። ነገር ግን ጥቂት የሚባሉ ወለፈንዲዎች ተከትለውት ይሆናል ግን መንገዱ ግሃነም የሚከት የሞኛሞኝ ጨዋታ ነው።
መሪ የሚያስተዳድረውን ለምን ጎበኘ ብሎ የሚሞላፈጥበት አግባብም አይታየኝም። ህዝቡ የሚመራውን ያውቃል። በተለይ ደግሞ የአማራ ህዝብ በታሪኩ ማን ምን አደረገ የሚለውን የሚያውቅ አስተውሎት ያለው ህዝብ ነው። ዬሃንስ ስርዓት መያዝ አለበት መንግስትም ለጥቂት ወለፈንዲ ተከታዬች ብሎ ስርዓት ከማስያዝ መቆጠብ የለበትም። ዳፋው ዙሮ ዙሮ ለህዝብ እና ለመንግሥት ስለሆነ በተለይ ደግሞ የድሃ ልጆች ለሆኑ የአማራ ወጣቶች የከፋ ነው። እንግዲህ ከትላንት ተምረናል የአማራ ወጣት ማገዶ የሚሆንበት ጊዜ ላይ አይደለንም።
በቃህ ዬሃንስ ቧያለው አርፈህ መጠጥህን ጠጣ ጣጣ አታምጣብን በምላስህ ያጣናቸውን የአማራ እንቁ መሪዎች አንረሳቸውም !!

ሁለቱ የኢትዮጵያ ረጅሞች።
04/04/2022

ሁለቱ የኢትዮጵያ ረጅሞች።

በሰውዬው መጸሀፍ ስል ሰውዬው ያሳወቀን መሀመድ ሀሰን በሌላ አዲስ ስር ብቅ ብሏል
02/04/2022

በሰውዬው መጸሀፍ ስል ሰውዬው ያሳወቀን መሀመድ ሀሰን በሌላ አዲስ ስር ብቅ ብሏል

Coming soon‼️‼️👇👇

የትዝታው ንጉሥ በመልካም ሁኔታ ላይ ይገኛል:: ረዥም ዕድሜ እንመኝልሃለን::
28/03/2022

የትዝታው ንጉሥ በመልካም ሁኔታ ላይ ይገኛል::
ረዥም ዕድሜ እንመኝልሃለን::

ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ በእንባ ተሞልታ ያቀረበችው ተማፅኖ ፦" ... የሀገራችን ጉዳይ ያመናል ሁላችንንም። ... ሁላችንንም የትግራይ እናቶች አባቶች ፤ እናቶቻችን አባቶቻችን ናቸው ።...
24/03/2022

ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ በእንባ ተሞልታ ያቀረበችው ተማፅኖ ፦

" ... የሀገራችን ጉዳይ ያመናል ሁላችንንም። ... ሁላችንንም የትግራይ እናቶች አባቶች ፤ እናቶቻችን አባቶቻችን ናቸው ። በእርግጠኝነት ደግሞ ነገ ሌላ ቀን ነው ኢትዮጵያ ታርቃ አንድ ሆና ትቆምና የኢትዮጵያን ባንዲራ ታውለበልባለች።

ስለዚህ አይክፋችሁ ክብር ይገባችኃል። በብዙ ፈተናዎች አልፋችሁ በብዙ ተፅእኖ አልፋችሁ የኢትዮጵያን ባንዲራ ከፍ ስላደረጋችሁ በጣም እናመሰግናለን።

ትግራይ ትላንትም ብትሆን ኢትዮጵያ ናት ፤ ዛሬም ኢትዮጵያ ናት ፤ ነገም ኢትዮጵያ ነች ስለዚህ እባካችሁ መሪዎቻችን እባካችሁ...እባካችሁ ... እባካችሁ ተጠቅማችሁ አይደለም ፤ ተጎድታችሁ ኢትዮጵያን አንድ አድርጓት እባካችሁ !!! ከእግዚአብሔር ጋር ትችላላችሁ። ስለዚህ መሪዎቻችን ተጎድታችሁ ለኢትዮጵያ ብላችሁ ፣ ለህዝብ ብላችሁ እናተ አንድ ካደረጋችሁ ኢትዮጵያ አንድ ትሆናለች።
.. ስፖርት ወንድማማችነት ፣ ፍቅር ፣ ሰላም ነው!! ለሰላም ፣ ለፍቅር ቆመው እነዚህ ልጆች ምንም ሳይበግራቸው ለዚህ ውጤት በቅተዋልና አሁንም ቢሆን ክብር ይገባቸዋል። እናከብራችኃለን። በእርግጠኝነት ቤተሰቦቻችሁ የት እንዳሉ ታውቃላችሁ ግድ የላችሁም እንወዳችኃለን እናከብራችኃለን ፤ እንደልጆቻችን ነው አሁንም የምናያችሁ ስለሆነም ትግራይ ዛሬ ብቻዋን አይደለችም ከኢትዮጵያ ጋር ነች፤ ነገም ከኢትዮጵያ ጋር ትሆናለች።

አሜሪካ ትግራይን ለመጥቀም አይደለም፤ ኢትዮጵያንም ለመጥቀም አይደለም ለመበተን ነውና H.R. 6600 የሚባልው አሁን ሊፀድቅ በመንገድ ላይ ያለው መሪዎቻችን ስለህዝባችን አይተው ፤ ስለወደፊት ኢትዮጵያ አይተው ከተስማሙ H.R. 6600 የሚፀድቅበት ምክንያት የለውም።

ህዝባችን ከመንግስቶቻችን ጎን ቆሞ ሁላችንም የትግራይ ህዝብ የኢትዮጵያ ህዝብ እኔ የትግራይ ህዝብ እና የኢትዮጵያ ህዝብ ስል ምቾት አይሰማኝም እንደኢትዮጵያ ነው ሁላችንም የምናየው ፤ ሁሉም ብሄር ብሄረሰቦቻችን ኢትዮጵያ ናቸው ፤ ትላንትናም ተባብረውና ኢትዮጵያውያን እዚህ ያበቁትና ነገም ዛሬም እንተባበር ኢትዮጵያን አንድ እናድርጋት።

እኛ ልጆቻችሁ ከኦሮሞ የመጣ፣ ከአማራ የመጣ፣ ከትግሬ የመጣ፣ ከጉራጌ ከየትም የመጣው ለዚህ ነው አንዷን ባንዲራ ከፍ ያደረግነው ስለሆነም ብሄር ሳንለን፣ ሃይማኖት ሳንለይ፣ ፆታ ሳንለን፤ ባንዲራችንን ያነሳነው ስለተባበርን ነው፤ በፅናት ስለቆምን ነው። ለእናተም አያቅትም የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስትም የኢትዮጵያ መንግስትም እባካችሁ ...ስለስለነገዋ ኢትዮጵያ አንድነት፣ ስለብልፅግናዋ ፣ ስለእድገቷ፣ ስለሰላሟ፣ እባካችሁ አያቅታችሁም እኛም ከጎናችሁ አለን ስፖርት ሰላም ነው ፤ ስፖርት ፍቅር ነው ብለናል ተያይዘን ኢትዮጵያን አንድ እናድርጋት። እግዚአብሔር ደግሞ አንድ ያድርግልን። "

" ዶላር የሚታመን መገበያያ አይደለም "  ቭላድሚር ፑቲን (እለታዊ የኢትዩትዩብ መረጃዎች)የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ሀገራቸው ከዚህ በኋላ ወደ አውሮፓ የሚደረገው የጋዝ ሽያጭ በሩሲ...
23/03/2022

" ዶላር የሚታመን መገበያያ አይደለም " ቭላድሚር ፑቲን
(እለታዊ የኢትዩትዩብ መረጃዎች)
የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ሀገራቸው ከዚህ በኋላ ወደ አውሮፓ የሚደረገው የጋዝ ሽያጭ በሩሲያ ገንዘብ "ሩቢል" እንዲሆን ወስነዋል።
የዚህ ውሳኔ ተግባራዊነትም በፍጥነት እንደሚከናወን ሩስያ ማስታወቋን RT ዋቢ አድርጎ አል አይን ዘግቧል።
RT እንደዘገበው ሞስኮ ከዚህ በኋላ ከአሜሪካ እና ከአውሮፓ ጋር " በዩሮም ሆነ በዶላር የመገበያየት ስሜት የላትም " ካሉ በኋላ ዶላር የሚታመን የመገበያያ ገንዘብ እንዳልሆነ ተናግረዋል።
የሀገሪቱ ማዕከላዊ ባንክ እና የካቢኔ አባላት ከአውሮፓ ጋር በሩብል የሚካሄደውን ግብይት በተመለከተ በአንድ ሳምንት ውስጥ ውሳኔ እንዲያስቀምጡ ትዕዛዝ ተሰጥቷል።
ፕሬዝዳንት ፑቲን ምንም እንኳን የተለያዩ ሀገራት የሩሲያን ሀብት ቢያግዱም ሀገራቸው ግን በገባችው ውል መሰረት ነዳጅ ማቅረቧን እንደምትቀጥል ገልጸዋል።
ምንጭ፡- አል አይን

ተመስገን በደሳለኝና በመሰለኝ የሚፅፋቸው ትንታኔዎች ሲጋለጡ!ጎልማሳው ተመስገን ደሳለኝ ትናንት በአፍላነቱ የተራመደባቸው የጋዜጠኝነት ዳገቶችና ቁልቁለቶች ዛሬ ለመንፏቀቅም ከብደውታል። አቅመቢ...
21/03/2022

ተመስገን በደሳለኝና በመሰለኝ የሚፅፋቸው ትንታኔዎች ሲጋለጡ!

ጎልማሳው ተመስገን ደሳለኝ ትናንት በአፍላነቱ የተራመደባቸው የጋዜጠኝነት ዳገቶችና ቁልቁለቶች ዛሬ ለመንፏቀቅም ከብደውታል። አቅመቢስነቱንና መክሸፉን ለመጋረድ፣ ብሎም በዚህ ብዙ ተንታኝ በሞላበት የሚዲያ መንደር ውስጥ ለመጉላትና የተሻለ ኮፒ ለመሸጥ፣ የሚቀለው ሀሜትና አሉባልታ ላይ መዋል ማደር አምጥቷል። ከግዜ ወደ ጊዜ ከእውነት እየሸሸ አሉባልታዎችን እየለቃቀመ እውነት እንዲመስሉ የቃላትና የገለፃ ሜካፕ እየቀባባ ጥቂቶችን እያታለለ እንደሆን እየታዘብን ነው።

በግሌ በተከታታይ መፅሄቶቹ ላይ ሽያጭን መሰርት ያደረጉና በአንድ ሕዝብ ጥላቻ የሰከሩ ፅሁፎቹን በጥንቃቄ ተከታትዬ፣ የውሸትነታቸውንና የቅጥፈታቸውን ልክ ስለተገነዘብኩ፣ ቀድሞ በዘመነ ወያኔም እየፃፈ ሲያስነብበን የነበረውን ከጥቂት ጫፍ በቀር ሌላው ነጭ ውሸት ሊሆን እንደሚችል ማመን ጀምሬያለሁ። ሞክንያቱም የማውቀውን እውነት ከዋሸኝ የማላውቀንማ እንዴት ላምነው እችላለሁ?

ለምሳሌ እውነቱን በቅርበት የማውቀውን የኢትዮጲያ ብሮድካስት ኮርፓሬሽን (ኢቢሲ)ን የተመለከተ ቅጥፈቱን ላንሳ። በፍትሕ መጽሄት ቅፅ176

ሰበር ዜና! የቤኒሻንጉል ክልልን እንደ ጎላን ኮረብታ(የእስራኤልና ሶሪያ) የግጭት አጀንዳ መፈልፈያ ለማድረግ የሱዳን እና ግብጽ ወታደራዊ እና ደህንነት ሃይላት አዲስ እቅድ ተጋለጠ ።  : የ...
19/03/2022

ሰበር ዜና!

የቤኒሻንጉል ክልልን እንደ ጎላን ኮረብታ(የእስራኤልና ሶሪያ) የግጭት አጀንዳ መፈልፈያ ለማድረግ የሱዳን እና ግብጽ ወታደራዊ እና ደህንነት ሃይላት አዲስ እቅድ ተጋለጠ ።

: የህዳሴ ግድብ ውሃ ሙሊት ሶስተኛ ዙር ፕሮግራም መጀመር ዋነኛ የሱዳን እና ግብጽ ጥፋት ሃይሎች የሰሞኑ መሰብሰቢያ ምክንያት ሲሆን ፤ በተለያዩ መድረኮች ግብጽ የኢትዮጵያን ህልውና እንደተፈታተነች ሆኖም ሱዳን ግን በበቂ አልታገለችም የሚል ወቀሳ በውይይቱ ተነስቷል። በዚህ የሶስተኛውን ዙር ውሃ ሙሌት በማስመልከት የተደራጀ ሃይል ውስጥ በሱዳን የግብጽ ኤምባሲ ቆንስላ ጣሪቅ ፋውዚ ቤኒሻንጉልን እንደ ዋነኛ የጥፋት ድልድይ ለመጠቀም የተጠናከረ ስራ እየሰሩ እንደሆነም አስታውቀዋል።

አሁን በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ በቤኒሻንጉል እና ምዕራብ ኢትዮጵያ ፤ሱዳንን አዋሳኝ በሆኑ ቦታዎች፤ የሚከሰቱ ማንኛውንም የቀውስ ምንጮች ሱዳንም ሆነ ግብጽ በበቂ እየተጠቀሙበት እንዳልሆነ በመውቀስ ሙሉ ቀውስ በአዋሳኝ ክልሎች እና የኢትዮጵያ ድንበሮች እንዲቀጣጠል የሎጀስቲክ ድጋፍ ተጠናክሮ የጦር መሳሪያዎችም በበቂ እንዲታደል በዚሁ የጥፋት ሃይል ምክክር ተወስኗል። ከዚህ ጋር ተያይዞ የፕሮፓጋንዳውን ስራ ግብጽ ለመከወን በአዲስ መልክ እየተንቀሳቀሰች እንዳለች ነገርግን በኢትዮጵያውያን እርስ በእርስ ግጭት ላይ ሊያጠነጥን እንደሚገባ ለዚህም የትኛውንም አይነት ክፍያ ለመክፈል ዝግጁ እንደሆነች አሳውቃለች ። አንድ የግብፅ መረጃ ሃላፊ እንደተናገሩት “በራሳቸው የተለያዩ የውስጥ ችግር ላይ ዋነኛ ተዋናይ የሆኑትን አካላት በከፍተኛ ሁኔታ ማንቀሳቀስ እንደሚገባ” ግብጽን ወክለው ለሱዳን አስረድተዋል። በትግራይ ያለውን ግጭት በተለይ ወደ ግድቡ ጉባ እና ቤኒሻንጉል ክልል ባጠቃላይ ማሻገር እጅግ ጠቃሚ ስትራቴጂ እንደሆነም የግብጽ መረጃ ሃይላት ከሰሞኑ በነበሩ ስብሰባቸው አጠናክረው ተናግረዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ከሰሞኑ በቤኒሻንጉል ተፈፀመ የተባለውን እጅግ ዘግናኝ በህይወት ያለ ሰውን የማቃጠል ጭካኔ በአለም አቀፍ ተቋማት ፣ ኤምባሲዎች እና ቴድሮስ አድሃኖም /+/ ፓትሪያርክ አቡነ ማቲያስ ጭምር በማቀጣጠል አለም አቀፍ የቀውስ ፕሮፓጋንዳው ንቅናቄ ማዕከል እንዲሆን ማድረግ እንደሚገባ ይኸው የግብፅ እና ሱዳን የብሉናይል ክልል ሚሽን ተልዕኮ ፈፃሚዎች አቅደው እየተገበሩት ይገኛል። ግድቡን በቀጥታ ከማውገዝ እና በግብጽና ሱዳን ድርቅን ይፈጥራል ከማለት ይህንን የኢትዮጵያውያን እርስ በእርስ ግጭት ማቀጣጠል እጅግ አዋጭ መንገድ እንደሆነም በተለያዩ የኻርቱም የጋራ ምክክሮቻቸው ላይ አንስተዋል።

ሀገራችንን በሁሉም መስክ ከተከፈተባት ጥቃት መከላከል የሁላችንም ሃላፊነት ሊሆን ይገባል። ለጠላቶቻችን አጀንዳ የሚፈጥር ማንኛውንም “ሰይጣናዊ እርምጃ” በማውገዝ ሁሉንም ጉዳዮች በሰከነ እና በትኩረት መከታተል አቋመ መያዝ ከሁሉም ዜጋ ይጠበቃል ። ሀገራችንን የሚያፈርሱ አካላት የትም ቢመካከሩ ይጋለጣሉ። ሰላማችንን ማስጠበቅ የምንችለውም እኛው ኢትዮጵያውያን በመከባበር እና በመደጋገፍ ስንቆም ብቻ ይሆናል ። ሀገር በጥቂት ጨካኞች አትገለጥም አትወገዝም።

ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !

እርጉም  ቅጠል!የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቴን ያጠናቀቅኩት በጥሩ ውጤት ነበር፡፡ ወደ ሁለተኛ ደረጃ ሳልፍ ግን ከአፍላ ወጣትነት ዕድሜ ጋር ተደማምሮ መሰለኝ አዳዲስ ነገሮችን ለመሞከር እሯሯጥ ...
17/03/2022

እርጉም ቅጠል!

የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቴን ያጠናቀቅኩት በጥሩ ውጤት ነበር፡፡ ወደ ሁለተኛ ደረጃ ሳልፍ ግን ከአፍላ ወጣትነት ዕድሜ ጋር ተደማምሮ መሰለኝ አዳዲስ ነገሮችን ለመሞከር እሯሯጥ ጀመር፡፡ አዳዲስ ነገሮችን ለማወቅ መሯሯጥ ባልከፋ ነበር፤ ችግሩ ግን ጠቃሚውንና ጎጂውን አለመለየቱ ነበር ፡፡

ቤተሰቦቼም ቢሆኑ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቴን ውጤት በማየት የእኔን ሁለተኛ ደረጃ ትም/ቤት በጥሩ ውጤት አጠናቅቄ ዩኒቨርስቲ የምገባበትን ጊዜ በጉጉት ይጠባበቃሉ፡፡

እኔ ግን ደብተር ይዤ እወጣለሁ፡ ደብተሬን ይዤ እመለሳለሁ እንጂ ውሎዬ ግን ትም/ቤት ሣይሆን ሌላ ቦታ ነበር፡፡ እንደ አራዳ መለኪያ መስፈርት የወሰድነው ጫት መቃምና ሲጋራ ማጨስ ከመሰል ጓደኞቼ ጋር የዕለት ተዕለት ተግባራችን ሆነ፡፡ ትምህርቱ ተረሳ እኔም ተስፋ ቆርጨ ሥራዬ መቃም፣ መጠጣትና ማጨስ ሆነ፡፡

መቃሚያና የማጨሻ ሳጣ ቤት ያለውን ዕቃ መሸጥ ጀመርኩ ፡፡በመጨረሻ አባቴ ሁለተኛ ቤት እንዳልደርስ፣ ብደርስ ግን ህይወትህን አጠፋዋለሁ አለኝ ፡፡ ዛቻው ይበልጡኑ እልህ አጋባኝ፡፡ እናቴ በአባቴ ላይ ተጽዕኖ አድርጋ ወዶ ሳይሆን ጓደኞቼ በትምህርቱ ውጤት ቀንተው መድሃኒት አድርገውበት ነው ብላ በየጸበሉ ይዛኝ ትዞር ጀመር፡፡ያም አልሆን አለ፡፡ የጤናዬ ሁኔታ ከድጡ ወደ ማጡ ቀጠለ። የማስታወስ አቅም አጣሁ፣ የሰውነት ሚዛኔን መጠበቅ ተሳነኝ፡፡ ነፈዝኩ፤ በትክከል ማሰብ ተሳነኝ፡፡ ይባሠ ብለው በእግረ ሙቅ አስረው ከቤት እንዳልወጣ አደረጉኝ፡፡ እቅመው የነበረው ጫት ፣ አጨሰው የነበረው ሽሻና ሲጋራ ሲቀር የበለጠ አሳበደኝ፡፡ ልብሴን መቀዳደድ ፤በፊቴ ያገኘሁትን ሰው መሳደብ ሥራየ ሆነ ፡፡ የወለደ አይጥልም እንዲሉ አባቴ አማኑኤል ሆስፒታል አስገባኝ ፡፡

ከሁለት ወር በኋላ ሙሉ በሙሉ ባልድንም መድሃኒቱን በባለሙያ እየታገዝኩ እየወስድኩ ራሴን ማወቅ ችያለሁ፡፡ በሱስ መጠመድ በራስ አለማዘዝ ነው፡፡ ለሱስ ባሪያ መሆን ነው ፡፡ ስሙኝ ወንድሞቼ በዚያች እርጉም ቅጠል ማለቴ (ጫት) የተጀመረው ሱስ ውሎ አድሮ ሽሻውን ሲጋራውን እያልኩ ለአደንዛዥ ዕጽ ተገዥ ሆኜ ከማንም ጋር በተለይ ከሴት አዳሪዎች ጋር ያደረኩት ጥንቃቄ የጎደለው ወሲብ ለኤች አይቪ ቫይረሱ አጋለጠኝ፡፡ ያም አልበቃ ብሎ እኔን ለማዳን ቤተሰቦቼን ያለ የሌለ ንብረታቸውን አሽጪ ለድህነት ዳረኩ ፡፡የወጣትነት ዕድሜዬን ያንን እምቅ ኃይል ሳልጠቀምበት እና የቤተሰቦቼን ከእጅ ወደአፍ ኑሮ ሳላሻሽል በከንቱ አሳለፍኩ፡፡ ዛሬ ቆም ብዬ ሳሥብ እንደ እግር እሳት ያቃጥለኛል፡፡ትዝ ይለኛል ጫት እሳት የነበረውን የወጣት ጉልበት ለማዳ ድመት ያደርግና ፍራሽ ለፍራሽ ሲያልፈሰፍስ ያውላል ፡፡ ሥራ ወዳድ የነበረን ሰው ሳይሰራ በምኞት ጋላቢ ያደርጋል፡፡እንደ ጉም በማይጨበጥ ምኞት ሌት ከቀን ያባዝናል ፤ ያሳብዳል ፤ ውሃ ሲወስድ እያሳሳቀ ነው አይደል የሚባለው ፡፡ ምን ያደርጋል የፈሰሰ ውሃ አይታፈስ ወገኖቼ፤ ከእኔ ተማሩ የወጣትነት እድሜአችሁን በአደንዛዝ ዕጽ ሱስ ተጠምዳችኁ ራሳችኁን እታሰቃዩ ከዚች እርጉም ቅጠል እራሳችሁን እራቁ፡፡

👉 ከታሪኩ ምን ተማራችሁ ? ሃሳብ አስተያየታችሁን አካፍሉን?
👉 አደንዣዥ እፅ ከሚያስከተለዉ ጉዳት ጋር ተያይዞ ምን ተረዳችሁ?

"ችግር አልባ ጉዞ የለም! ከእኔ እና ከእናንተ የሚጠበቀው ዋናው ነገር የራዕያችን መንገደኛ እንሁን፣ ለራዕያችን ስኬት እንትጋ፣ ለራዕያችን ስኬት አብረን እንቁም!! የእንቅፋቶቻችን፣ የችግሮቻ...
17/03/2022

"ችግር አልባ ጉዞ የለም! ከእኔ እና ከእናንተ የሚጠበቀው ዋናው ነገር የራዕያችን መንገደኛ እንሁን፣ ለራዕያችን ስኬት እንትጋ፣ ለራዕያችን ስኬት አብረን እንቁም!! የእንቅፋቶቻችን፣ የችግሮቻችን እና የአደናቃፊዎቻችን እስረኛ አንሁን።"

ዶ/ር ዐቢይ አህመድ
የብልፅግና ፓርቲ ፕሬዝዳንት

 !በቡና ቤት ሕይወቷ ቤቲ ሁሌም የማትረሳውና ትምህርት ያገኘችበት ገጠመኝ አላት፡፡ አንድ ጊዜ ጎንደር እያለች ነው ስለኮንዶም ብዙም ሳታውቅ፤ አንድ ደምበኛ የሚፈለገውን አሟልቶ ይዞት ወደነበ...
15/03/2022

!

በቡና ቤት ሕይወቷ ቤቲ ሁሌም የማትረሳውና ትምህርት ያገኘችበት ገጠመኝ አላት፡፡ አንድ ጊዜ ጎንደር እያለች ነው ስለኮንዶም ብዙም ሳታውቅ፤ አንድ ደምበኛ የሚፈለገውን አሟልቶ ይዞት ወደነበረው መኝታ ክፍል ይዟት ገባ፡፡ ከዚያም ገንዘብ ልጨምርልሽና በሌጣው (አለኮንዶም) እንውጣ (እናድርግ) ይላታል፡፡

ቤቲም እርግዝና እና ኤችአይቪን በጣም ስለምትፈራ ‹በምንም አይነት መንገድ አይሆንም፤ የተስማማንበት ሒሳብ ይበቃኛል› ብላ ያለኮንዶም እንደማትወጣ (እንደማታደርግ) ትነግረዋለች፡፡ ደምበኛውም ጥንቃቄ በማድረጓ አድንቋት ሊፈትናት እንጂ እሱም ያለኮንዶም እንደማይጠቀም ያሳምናታል፡፡ ቀጥሎም ኮንዶም ከኪሱ አውጥቶ አገላብጦ ካሳያት በኋላ አብረው ይተኛሉ፡፡ እሱ ኮንዶም ማጥለቅ ሲጀምር እሷ አፈረችና ፊቷን አዞረች፡፡ በዚህን ጊዜ ኮንዶሙን ያደረገ አስመስሎ ወሲብ ማድረግ ጀመሩ፡፡ ቤቲ ከዚህ በፊት ከምታውቀው የአልጋ ላይ ቆይታ የተለየ አይነት ስሜት ሲሰማት ኮንዶም ማድረጉን በጥርጣሬ ጠየቀችው፡፡ ኮንዶም ማድረጉንና የተጠቀመው ኮንዶም አይነት ስስ ከመሆኑ የተነሳ እንደማያስታውቅ ነገራት፡፡ እሷም ሞቅታ ነበራትና አመነችው፡፡ ሆኖም ስሜቱን ካረካ በኋላ በጣም ስለወደዳትና በመኝታ ቆይታቸውም ስለተደሰተ ኮንዶም አለመጠቀሙን ገለጸላት፡፡ ቤቲ በድርጊቱ በጣም ብትበሳጭም ስህተቷን ማረም ባትችልም ከክስተቱ ግን ትምህርት ከመውሰድ ውጭ በጊዜው ምንም ማድረግ አልቻለችም፡፡ ከቤቲ ገጠመኝ ምን ተማራችሁ? ስለ ኮንዶም አጠቃቀም ያላችሁን ሀሳብና አስተያየት ብታካፍሉን? እንወያይበት።

የሚኒሊክ ሃውልት ካልፈረሰ ለውጥ የመጣ የማይመስለው ኦሮሞጃዋር በሞት ካልተቀጣ ለውጥ የመጣ የማይመስለው አማራበመለስ ስም ታቦት ካልተቀረፀ ለውጥ የመጣ የማይመስለው ትግሬብሄር የሚለው ቃል ከ...
13/03/2022

የሚኒሊክ ሃውልት ካልፈረሰ ለውጥ የመጣ የማይመስለው ኦሮሞ
ጃዋር በሞት ካልተቀጣ ለውጥ የመጣ የማይመስለው አማራ
በመለስ ስም ታቦት ካልተቀረፀ ለውጥ የመጣ የማይመስለው ትግሬ
ብሄር የሚለው ቃል ከመዝገበ ቃላት ላይ ካልተሰረዘ ለውጥ የመጣ የማይመስለው አዲሳበቤ
ይሄን ሁላ ነው አብይ አንድ አድርጎ ለመምራት እየሞከረ ያለው!

አያሳዝንም ወይ?

Sura D Qayel

በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ የአስከሬን ሽኝት ስነስርዓት ላይ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን፣ ክብርት ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች ...
12/03/2022

በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ የአስከሬን ሽኝት ስነስርዓት ላይ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን፣ ክብርት ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ፣ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ ፣ የብልፅግና ፓርቲ ዋና ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ አደም ፋራህ ተገኝተዋል፡፡

ከአንች ውጭ ሌላ አላውቅም ጆሮዎቼ  ለይምሰል ይስማሉ እንጂ፤ ከሚጮኸው ሙዚቃ ይልቅ በውስጤ የሚጮኸው ብሶት፣ ቁጭት እና ጸጸት ህሌናየን ወጥሮ ይዞታል። የተቀጠረሁበት ሆቴል ባለቤት ባንኮኒውን...
11/03/2022

ከአንች ውጭ ሌላ አላውቅም

ጆሮዎቼ ለይምሰል ይስማሉ እንጂ፤ ከሚጮኸው ሙዚቃ ይልቅ በውስጤ የሚጮኸው ብሶት፣ ቁጭት እና ጸጸት ህሌናየን ወጥሮ ይዞታል። የተቀጠረሁበት ሆቴል ባለቤት ባንኮኒውን ተደገፈው በትላልቅ ዐይናቸው የሚጠጣውን በሞቅታ የሚለፈልፈውን እና የሚተክዘውን በጎሪጥ ይመለከታሉ። እኔም ከተቀመጥሁበት ወንበር ሳልንቀሳቀስ በሐሳብ ባህር ሰጥሜ ወደ ትላንት ሕይወቴ ተጉዣለሁ ፡፡

የዛሬዋ ሆቴል አስተናጋጅ የትናንቷ ጎበዝ ተማሪ ነኝ፡፡ ሕይወቴ የተቀየረው በአንድ ጀንበር ነው፡፡ ትዝ ይለኛል በአፍላ እድሜየ ከትምህርት ውጭ የማላስብ ብዙ ተስፋ ያለኝ ገና በመጀመሪያ ደረጃ ተማሪ እያለሁ ኢንጅነር የመሆን ህልም ሰንቄ የተነሳሁ ያነንም ለማሳካት ጠንክሬ የማጠና ነበርኩ፡፡ ወላጆቼ በጣም የሚኮሩብኝ በመምህራን ዘንድ የተወደደሁ ለሌሎች ምሳሌ የነበረሁ በጣም ጎበዝ ልጅ፣ ዳሩ ምን ዋጋ አለው ያ እነደ ወረቀት ነጭ የነበረው የልጅነት ስብናየ በዚህ አለም እድፍ ያለተነካካ ገላየ በቅጽበት ከመስመሩ ወጣ ፡፡

ቀኑ ትዝ ይለኛል ማክሰኞ ነበር የሚያመር ውብና ለግላጋ ወጣት ጓደኛየን ማርቲ ብሎ ጠራት እና መጥቶ ተቀላቀለን። ማርታ ጋር በደንብ እንደሚተዋወቁ ከሰላምታቸው ያስተውቃል፡፡ ልጁ ከላይ እሰከ ታች እየተመለከተኝ ‹በጣም ታምሪያለሽ እንዳንቺ አይነት ቆንጆ እዚህ ትምህርት ቤት አለ እንዴ ? ጠየቀኝና ኤሪሚያሥ እባላለሁ ብሎ እጁን ዘረጋልኝ፤ የሽመቤት አለሁት በድንጋጤ እና ሀፍረት በተቀላቀለበት ስሜት ማርታ የባጡን የቆጡን እየቀባጠረች ሳናውቀው ሰፈር ድረስ ሸኝቶን ተመለስ ፡፡

ከዛን ቀን ጀምሮ እኔና ኤርሚያሥ በጣም ተቀራረበን ሣንተያይ ውለን ማደር አንችለም፡፡ ኤርሚያስ በጣም ጥሩ ዘና የሚያድርግ ልጀ ነው፡፡ እኔም ቀስበቀስ በጣም አየወደደሁት መጣሁ። ሳላየዉ ማድረ አልችል፡፡ ኤርሚያሥ የሚሰራው አባቱ ድርጅት ሲሆን ት/ቱን ከአስረኛ ክፍለ ላይ እንዳቆመ ነግሮኛል ፡፡ በአጭር ጊዜ ጣፋጭን ሂወትን አሳየኝ። ሚጢጢ ልቤን በሀሴት አጥለቀለቃት የሚገርመው ከ1ኛ እሰከ 8ኛ ክፍል አንደኛ አንደኛ ነበር የምወጣው ከኤርሚያስ ጋር በተዋወቀሁት ጊዜ የ9ኛ ክፍል ተማሪ ነበርሁ በዛው አመት ዉጤቴ በጣም አሽቆለቆለ፡፡

ታደያ ዛሬ ላለሁበት ሕይወት የመጀመሪያ ምዕራፍ የሆነው ታሪኬ ተጀመረ ፍቅር በተሞላበት ንግግር ግንኙነት እንድናደረግ ጠየቀኝ። በመጀመሪያ በጣም ፈርቼ ስለነበር እምቢ ስል ተቃዎመሁት አሱም ሳያሥገድደኝ ሌላ ግዜ እንደሚደርስ ገልፆልኝ ተወኝ፡፡ በጣም ታማኝ እና አፍቃሪ ነው ብየም እንዳስብ አደረገኝ ፡፡ ግንኙነታችንም ከበፊቱ በተሻለ መንገድ ቀጠለ ፡፡ትምህርቴ ግን መከታተለ አልቻለሁም ነበር ፡፡ ከብዙ የፍቅረ ቀናቶች በኋላ ቃላተ ሳያወጣ ምንም ሳያስገድደኝ እኔም ሳልግደረደር ታማኝና ሀቀኛ በሚመስል ማንነቱ ተታልየ አብሬው ተኛሁ፡፡

ድንግልናየን ገሰሰው፡፡ እኔም የማገባው አሱን ነው በማለት ራሴን አሳምኘ በተፈጠረው ነገር ብዙም ሳልከፋ ቀናት አለፉ። ቀኖች ባለፉ ቁጥር ግን ኤርሚያስ ከእኔ የሚርቅበትን ምክንያት በመፈለግ ይሸሸኝ ጀመር፡፡ ከተለያዩ ሴቶች ጋር በመሆነ የተለያ ቦታ ይታይ ጀመር። የእኔ ሕይወት ግን መከራ እና ስቃይ የተሞላበት ሆነ፡፡

ከትምህርቴም ተከታታይ ቀን በመቅረቴ ተባረርኩ፡፡ ወላጆቼ በእኔ ምክንያት አንገታቸውን ደፉ፡፡ በኤርሚያስ ንዴትና እልህ ገና በለጋ እድሜየ ከብዙ ወንዶች ጋር መውጣት ጀመረሁ። ልክ እንደ ኤርሚያስ ከአንተ ውጭ ሌላ ወንድ አላውቅም ፡፡የመጀመሪያየ ነህ እያለሁ ብዙዎችን በማታለል ልጅነቴን የወሲብ አዘቅት ውስጥ ከተትሁት ፡፡ በዚህ ድርጊቴ የተማረረው አባቴ ያለ እድሜው በብስጭት ሞተ ፡፡ እናቴም አልችል ስትል ከቤት አባረረችኝ ዛሬ ላይ ያለሁበትን ሁኔታ ለመርሳት እያልሁ እጠጣለሁ ፡፡

ታዲያ በዚህ ሆቴል ብዙ ታደጊዎች እንደኔ እየተታለሉ ወሲብ የሚፈጽሙ ብዙዎች ናቸው፡፡ ለአንዳንዶች የእኔን ታሪክ በመንገር ከመንገዳቸው እንዲመለሱ እነግራቸዋለሁ፡፡ በዚህ ዘመን ብዙወቻችን እየተሸወድን ያለው ከአንች ውጭ ሌላ አላውቀም ከአንት ውጭ ሌላ አላውቅም በሚሉ እንደ ኤርሚያስ ባሉ አፈ ጮሌዎች ነው፡፡

እኔ በአሁኑ ሰዓት ተመርምሬ ራሴን አውቂያለሁ የኤችይቪ ቫይረስ በደሜ ውስጥ አለ፡፡ አሁን ከማንም ጋር ወሲብ አለፈፅምም፡፡ ራሴን ለማሰተዳደር ስል እዚሁ ሆቴል ውስጥ በመሰተንግዶ እስራለሁ፡፡የፈሰሰ ውሃ አይታፈስ እንደሚሉ ያለፈ ሂወቴን ባልመልሰውም ለሌሎች ግን ከእንደዚህ አይነት ነገር ራሳቸውን በመጠበቅ ትምህርታቸው ላይ ብቻ እንዲያተኩሩ እመክራቸዋለሁ፡፡

ከታሪኩ ምን ተረዳን ? ስነቶቻችሁ ከታሪኩ ጋር የሚያመሳስል ህይወት አላችሁ? እንወያይበት

ይህ የአማራ ክልል ጤና ቢሮ መልእክት ነው

👉( God of war )- አሜሪካን ያስደነገጠው የቻይና ቦንብ ጣይ አውሮፕላን !!🇨🇳🇨🇳🇨🇳🇨🇳🇨🇳🇨🇳🇨🇳👉ቻይና ይህንን በአይነቱ ተወዳዳሪ የለውም የተባለለትን ቦንብ ጣይ አይሮፕላን በድብቅ ...
10/03/2022

👉( God of war )- አሜሪካን ያስደነገጠው የቻይና ቦንብ ጣይ አውሮፕላን !!
🇨🇳🇨🇳🇨🇳🇨🇳🇨🇳🇨🇳🇨🇳
👉ቻይና ይህንን በአይነቱ ተወዳዳሪ የለውም የተባለለትን ቦንብ ጣይ አይሮፕላን በድብቅ ስትሰራ ከቆየች በኋላ ጊዜው አሁን በማለት ይፋ አድርጋዋለች። ስሙንም "God of war" ስትል ሰይማዋለች። " God of war " የተሰኘው Xian H-20 ቦንብ ጣይ አይሮፕላን 5000 mile ነዳጅ መሙላት ሳይጠበቅበት የሚጓዝ ሲሆን ይህም የትኛውንም የአሜሪካ ጦር ጣቢያ ወደ አመድነት መቀየር ያስችለዋል።
👉በተለይም GUAM የሚገኘው የአሜሪካ የአየርና የባህር ጦር ጣቢያ የቻይና ቀዳሚ ኢላማ ነው። " God of war " የኑክሌር ቦንብን ተሸክሞ ከፈለገው ቦታ ላይ ካለ ራዳር እይታ አራግፎ የተሰጠውን ኢላማ እንዳልነበረ የሚያደርግ ነው። ይህ አውሮፕላን ከዚህ በተጨማሪ ሺህ ኪሎሜትሮችን ከድምፅ ፍጥነት በብዙ እጥፍ በበለጠ የሚምዘገዘጉ Hypersonic ሚሳኤሎችን የሚታጠቅ ነው።
👉ይህ የቻይና ቦንብ ጣይ አውሮፕላን ካለምንም የራዳር እይታ የአሜሪካን የጦር ጣቢያዎችና የኑክሌር ማከማቻዎች ማውደም የሚችል ነው። ይህ አውሮፕላን 8,500 ኪሎሜትሮችን ማጥቃት የሚችል ሲሆን በአንድ ጊዜ በርካታ የኑክሌር ቦንብን ተሸክሞ ማጥቃት ይችላል።
👉ቻይና ወታደራዊ ግስጋሴዋ በጣም አስደንጋጭ በሆነ ፍጥነት እየተመነጠቀ ሲሆን በጥቂት አመታት ውስጥ ከአለማችን በጦር ሃይል ቀዳሚዋ ትሆናለች ተብሏል። ቻይና ከዚህ ውጭ በምንም አይነት ጥቃቶች የማይሰጥሙ የጦር አውሮፕላን ተሸካሚ መርከቦችን በስፋት እያመረተች ትገኛለች።
👉ብዙ የጦር ጠበብቶች ይህንን የአሁኑን የቻይናን ግኝት የአለምን የሀይል ሚዛን የሚለውጥ በማለት እየገለፁት ሲሆን ቻይና የአሜሪካን የኑክልየር ጣቢያዎች ማውደም የሚያስችሏት የተራቀቁ የጦር ግኝቶች ላይ በስፋት እየሰራች ትገኛለች።
👉በዚህም በ Guam የሚገኘውን የአሜሪካ የኑክሌር ጣቢያ ማውደም እንደምትችል ያረጋገጠን ቴክኖሎጂ በእጇ ያደረገች ሲሆን " Guamkiller " ስትልም ሰይማዋለች። 🙏
Mihreteab G Desta

   መስፍን ወደ ፊልድ ልሄድ ስለሆነ ሻንጣዬን አዘጋጂልኝ ሲል  ልጁን ሰናይትን ያዛታል፡፡ ሰናይትም እሺ አባዬ ለፊልድ የሚያስፈልግህን ሁሉ አዘጋጅልሃለሁ ብላ ተነሳችና አባቷ ወደ ፊልድ ይዞ...
10/03/2022



መስፍን ወደ ፊልድ ልሄድ ስለሆነ ሻንጣዬን አዘጋጂልኝ ሲል ልጁን ሰናይትን ያዛታል፡፡ ሰናይትም እሺ አባዬ ለፊልድ የሚያስፈልግህን ሁሉ አዘጋጅልሃለሁ ብላ ተነሳችና አባቷ ወደ ፊልድ ይዞ የሚሄደውን ሁሉ ማሰናዳት ጀመረች፡፡

የሚወስደውን ልብስ የሚወስደውን የፀረ-ኤችአይቪ መድኃኒት ሁሉን ነገር በሚገባ አዘጋጀች፡፡ አባቷም ልጁ ያዘጋጀችለትን ሁሉ አየና ሁሉንም በአግባቡ እንዳሰናዳች ካረጋገጠ በኋላ ሰንዬ አመሰግናለሁ፤ ከተዘጋጀለት ሻንጣ የፀረ-ኤችአይቪ መድኃኒቱን አውጥቶ ይህን አሁን አልወስደውም። አሁን በጣም ጤነኛ ነኝ፤ በዛ ላይ ደግሞ ብዙ ቀን ፊልድ ላይ አልቆይም አላት፡፡

ምነዉ አባትዬ! መድኃኒቱን መውሰድ ጀምረህና ያንን ሁሉ ችግር ካለፍክና ይህን ያህል የተሻለ ጤናማነት ሲያላብስህ ፀረ-ኤችኤይቪ መድኃኒት አልወስድም ትለኛለህ?
አቶ መስፍን(አባት)- አዎ...... ዛሬ ላይ በእርግጠኝነት የምነግርሽ ምንም አይነት የህመም ስሜት ከዉስጤ የለም ጤናማነት ይሰማኛል፡፡

ሰናይት(ልጅ)- በመገረም ስሜት አባቷን እያየች ተዉ እንጂ አባቴ!! እንዲህ አይባልም ስህተት ነዉ ፡፡ የፀረ-ኤችአይቪ መድኃኒቱ በአግባቡ መዉሰድ መጀመርህ የተሻለ ሰዉ ሲያደርግህ እንደገና አላዋቂ ሰዉ ትሆናለህ? መድኃኒቱን እንድትጀምር ወደ ሀኪም ቤት ስትሄድ ይህ መድኃኒት ከተቋረጠ ወደ ማይመለስ የጤና ችግር እንደምትገባ ሀኪሙ ምክር እንደሰጠህ የነገርከኝን!....... ዘነጋህው?
አቶ መስፍን- ልክ ነሽ ልጄ በቀደም ለቼክ አፕ ወደ ሀኪም ቤት ስሄድ ሀኪሜ አሁን ያለሁበት ሁኔታ መልካም እንደሆነ ስለነገሩኝ እና ከዚህ በኋላም መድኃኒቱን ባቆምም ጤንነቴን በምግብና በስፖርት እጠብቃለሁ ብየ ነዉ እንጅ እሱማ!!!......

ሰናይት-ተሳስተሀል አባዩ ሀኪሙ ያለህበትን የጤና ደረጃ ነገረህ እንጅ መድኃኒቱ ይቋረጥ አላሉህም፡፡ በማንኛዉም መንገድ መድኃኒት ማቋረጥ ጤና ችግር ያመጣል እንጅ መፍትሄ አይሆንም፡፡ አሁንም መድኃኒቱን መዉሰድ አለብህ ፣በመስክ ላይ የምታደርገው ቆይታ ልክ የሚሆንህንም መድኃኒትህን አዘጋጅቼልሃለሁ ይዘህ መሄድ አለብህ!፡፡
በነዚህ ነጥቦች እንወያይ የፀረ-ኤችአይቪ መድኃኒት ጤነኝነት ተሰማኝ ተብሎ ይቋረጣል?

በመድኃኒቱ መውሰዳችንን ለቤተሰብ ግልፅ ማድረግ ጠቀሜታ ምንድን ነው?

ስንቶቻችን ለጤንነታችን ሀኪም የሚለንን በአግባቡ እንተገብራለን? ያላችሁን ተሞክሮ ሃሳብ አስተያየት አካፍሉን

ይህ የአማራ ክልል ጤና ቢሮ መልዕክት ነው

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ- የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዝደንትብልጽግናን ኢትዮጵያ ውስጥ ማረጋገጥ ከፈለግን፣ኢትዮጵያን በልዕልና ማማ ማቆም ከፈለግን፣ኦሮሞም፣አማራን፣ትግሬም፣ሲዳማም፣ሱማ...
10/03/2022

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ- የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዝደንት

ብልጽግናን ኢትዮጵያ ውስጥ ማረጋገጥ ከፈለግን፣ኢትዮጵያን በልዕልና ማማ ማቆም ከፈለግን፣ኦሮሞም፣አማራን፣ትግሬም፣ሲዳማም፣ሱማሌም፣አፋርም፣ወላይታም፣ስልጤም፣ጉራጌም ሌሎች ህዝቦችም በእኩልነት የሚሳተፉበት፣በእኩልነት የሚጠቀሙበት ማድረግ ካልቻልን ቢበዛ የ25 ዓመት ብልጠት እንጂ ዘላቂ ድል ማምጣት አንችልም፡፡

መላው የብልጽግና አባላት፣መላው የፓርቲያችን ደጋፊዎች መገንዘብ ያለባቸው ኢትዮጵያ ወደ ብልጽግና መውጣት የምትችለው ሁሉም ኢትዮጵያዊያን በእኩልነት፣በፍቅር፣በወንድማማችነት ተከባረው ተፈቃቅደው ተዋደው መትጋት ሲችሉ ብቻ በመሆኑ ተረኝነት ብለው የሚያስብም፣ተረኝነት ብሎ የሚያውጅም ካለ የኢትዮጵያን ብልጽግና በአጭር የሚያስቀር ስለሆነ እኛ ብልጽግናዎች መላው የኢትዮጵያ ህዝብ በአንድ ልብና መንፈስ ተሳስረን ሁሉንም የምንጠቅም፣ሁሉንም የምናገለግል፣ሁሉንም የምንወድና ለሁሉም የምንቆም መሆን ይጠበቅብናል፡፡

 #ያስተውሉ ኤችአይቪ በደሙ ውስጥ ያለ ሰው በደሙ ውስጥ ያለውን የቫይረስ መጠን የማይታይ ደረጃ ለማድረስ የሚከተሉትን የተሳሳቱ አመለካከቶችን ማረም ያስፈልጋል፡-👉ከኤችአይቪ ድኛለሁ ብሎ መድ...
01/03/2022

#ያስተውሉ

ኤችአይቪ በደሙ ውስጥ ያለ ሰው በደሙ ውስጥ ያለውን የቫይረስ መጠን የማይታይ ደረጃ ለማድረስ የሚከተሉትን የተሳሳቱ አመለካከቶችን ማረም ያስፈልጋል፡-

👉ከኤችአይቪ ድኛለሁ ብሎ መድሃኒት ማቋረጥ፤
👉ኤችአይቪ በደም ውስጥ አለመታየት ማለት ሌሎች በግብረስጋ ግንኙነት የሚተላለፉ በሽታዎች አይተላለፉም ማለት አይደለም፡፡ ስለሆነም ጥንቃቄ የጎደለው ወሲብ ለብዙ ችግር ያጋልጣል (ያልተፈለገ እርግዝና)፤
👉በአንድ ጊዜ ምርመራ አለመገኘት ማለት አይተላለፍም ማለት አይደለም፡፡ ቢያንስ ለ6 ወር ተመሳሳይ ውጤት ማሳየት ይኖርበታል፡፡
👉የፀረ-ኤችአይቪ መድሃኒት ቁርኝት ችግር ካለ የቫይረሱ ቁጥር በአጭር ጊዜ ስለሚጨምር ወደ ሌላው የመተላለፍ እድሉ ከፍተኛ ነው፡፡

ስለሆነም ኮንዶምን ሁልጊዜና በአግባቡ መጠቀም፤ የጸረ-ኤችአይቪ ቅድመ መከላከል መድሃኒት እና ሌሎች ጥንቃቄዎቸች መቋረጥ የለባቸውም!!

Address

22
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Lets talk እንወያይ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Lets talk እንወያይ:

Videos

Share