29/06/2024
አውደርዕዩ "ዓለም አቀፍ ኢትዮ- አውቶሞቲቭ ትራንስፖርት ኤክስፖ" የተሰኘ ሲሆን ከሰኔ 26 እስከ ሰኔ 2 ቀን 2016 ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ ይካሄዳል።
ከውደርዕዩ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ከኢትዮ አውቶ ቴክ ትሬዲንግ ጋር በመተባበር የተዘጋጀ መሆኑም ተመላክቷል።
የሚኒስቴሩ የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ስራ አስፈጻሚ ወይዘሮ አመለወርቅ ህዝቅኤል እንደገለፁት፥ የአውደርዕዩ ዋና አላማ በትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ዘርፍ ላይ እየተሰሩ ያሉትን ዋና ዋና ተግባራት ማስተዋወቅ እና ባለድርሻ አካላትን እርስ በእርስ ማገናኘት ነው።
በተጨማሪም ዘርፉን ለማዘመን የሚያግዙ የቴክኖሎጂ የፈጠራ ውጤቶች ያሏቸው ግለሰቦችና ተቋማት የፈጠራ ውጤታቸውን እንዲያሳዩ እድል ለመስጠት ያስችላልም ተብሏል።
ከዚህ ባሻገርም በአጠቃላይ በትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ዘርፍና በአውቶሞቲቭ ኢንዱስትሪው ላይ ያሉትን ለውጦችና የዘርፉን ማነቆዎች በተመለከተ የፓናል ውይይት የሚካሄደበት መሆኑ ተጠቅሷል።
የኢትዮ አውቶቴክ ትሬዲንግ ላለፈው አንድ አመት ዝግጅት ሲያደርግ መቆየቱን የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር አዲስ አለማየሁ ተናግረዋል።
ዋና ስራ አስኪያጁ በዘርፍ የቴክኖሎጂ እና የእውቀት ሽግግርን በማጠናከር ብክለትን የሚቀንሱ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችና ሌሎች አዳዲስ ውጤቶች ለእይታ የሚቀርቡበት ይሆናል ብለዋል።
ሐበሻ ጣዕም