የቅዱስ ገብርኤል ማኅበር St. Gabriel Association

የቅዱስ ገብርኤል ማኅበር St. Gabriel Association St. Gabriel Ethiopian Orthodox Tewahedo Church Association Gabriel Association of the Ethiopian Orthodox Church.

እንኳን አደረሰን!‹‹እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ›› (ሉቃ.፩፥፲፱)የሊቀ መልአኩ የቅዱስ ገብርኤል በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን።
29/12/2023

እንኳን አደረሰን!
‹‹እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ›› (ሉቃ.፩፥፲፱)

የሊቀ መልአኩ የቅዱስ ገብርኤል በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን።

ፈረንሳይ ለጋሲዮን ወይብላ ማርያም!እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አመታዊ ክበረ በዓል አደረሳችሁ!
28/06/2023

ፈረንሳይ ለጋሲዮን ወይብላ ማርያም!

እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አመታዊ ክበረ በዓል አደረሳችሁ!

ዘንዶውን አሸንፏል፤ስሙንም በክብር ፅፏል።እንኳን ለራማዉ ንጉስ ቅዱስ ሚካኤል አመታዊ ክበረ-በዓል አደረሳችሁ!
19/06/2023

ዘንዶውን አሸንፏል፤
ስሙንም በክብር ፅፏል።

እንኳን ለራማዉ ንጉስ ቅዱስ ሚካኤል አመታዊ ክበረ-በዓል አደረሳችሁ!

30/05/2023

የደብረ ምጥማቅ ጻድቃኔ ማርያም ዓመታዊ በዓልና የገዳሙ አዲስ ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ምርቃት በድምቀት ተከብሮ ውሏል።

የአማላጃችን የቅድስት ድንግል ማርያም ልጅ ይመስገን!

የደብረ ምጥማቅ ጻድቃኔ ማርያም ዓመታዊ በዓልና የገዳሙ አዲስ ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ምርቃት ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት  በተገኙበት በድምቀት ተከናውኗል። እግዚአብሔር ይመስገን!
29/05/2023

የደብረ ምጥማቅ ጻድቃኔ ማርያም ዓመታዊ በዓልና የገዳሙ አዲስ ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ምርቃት ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት በድምቀት ተከናውኗል።

እግዚአብሔር ይመስገን!

ሰበር ዜና *********የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ  የሦስቱን አባቶችና የ20ቹን መነኮሳት ውግዘት ከዛሬ 21/07/2015 ዓ/ም ጀምሮ ማንሳቱን በመግለጫው አሳወቀ።ውግዘቱ የተነሳላቸው ቤ...
30/03/2023

ሰበር ዜና
*********
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የሦስቱን አባቶችና የ20ቹን መነኮሳት ውግዘት ከዛሬ 21/07/2015 ዓ/ም ጀምሮ ማንሳቱን በመግለጫው አሳወቀ።
ውግዘቱ የተነሳላቸው ቤተ ክርስቲያን በሰጠቻቸው ማዕረግ እንዲጠሩም ገልጿል።
በዚህ መሠረት ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ ፣ብፁዕ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ብፁዕ አቡነ ዜና ማርቆስ ተብለው እንደሚጠሩና ወደ ነበረ የአባትነት ኃላፊነታቸው የሚመለሱ ሲሆን በይቅርታ የተመለሱት በቁጥር 20ዎቹ መነኮሳትም ቤተ ክርስቲያን በሰጠቻቸው የክህነት አገልግሎት እንዲያገለግሉ ሆኖ በምንኩስና ስማቸው እንዲጠራ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል።
EOTC

ካህኑ በድንጋይ ተወግረው ተገደሉ!***በአዲስ አበባ ኃይሌ ጋርመንት አካባቢ መጋቢት 14/2015 ዓ.ም ቀሲስ ዐባይ መለሰ የተባሉ ካህን ቅዳሴ ጨርሰው ወደ ቤታቸው በመሄድ ላይ እንዳሉ በድንጋ...
24/03/2023

ካህኑ በድንጋይ ተወግረው ተገደሉ!
***
በአዲስ አበባ ኃይሌ ጋርመንት አካባቢ መጋቢት 14/2015 ዓ.ም ቀሲስ ዐባይ መለሰ የተባሉ ካህን ቅዳሴ ጨርሰው ወደ ቤታቸው በመሄድ ላይ እንዳሉ በድንጋይ ተወግረው ሕይወታቸው ማለፉን የዐይን እማኞች ገለፁበአዲስ አበባ ኃይሌ ጋርመንት አካባቢ መጋቢት 14/2015 ዓ.ም ቀሲስ ዐባይ መለሰ የተባሉ ካህን ቅዳሴ ጨርሰው ወደ ቤታቸው በመሄድ ላይ እንዳሉ በድንጋይ ተወግረው ሕይወታቸው ማለፉን የዐይን እማኞች።
የሆርሲሳ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ የነበሩት ቀሲስ ዐባይ መለሰ ሕይወታቸው ሲያልፍ ችግሩ ታወቀ እንጂ አስቀድሞ በአካባቢው አገልጋዮች ላይ ዛቻ እና ማስፈራሪያ ይደርስ እንደነበር መረጃ ሰጭዎቻችን ገልፀዋል።
ካህኑ በድንጋይ ተደብድበው እያሉ ምስልና ቪዲዮ ለማስረጃ ለመያዝ ቢሞክሩም በአካባቢው የፀጥታ ኃይሎች ሞባይል እየተሰበሰበ መሰረዙንም ነግረውናል።
©ማኅበረ ቅዱሳን

25ቱ ግለሰቦች ግን የሰላም ጥሪውን ከመቀበል ይልቅ እስከአሁን ድረስ በሕገ-ወጥ አድራጐታቸው ቀጥለውና በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የተሰጠውን እግድ በመጣስ የአህጉረ ስብከትን ጽ/ቤት እየሰበ...
15/03/2023

25ቱ ግለሰቦች ግን የሰላም ጥሪውን ከመቀበል ይልቅ እስከአሁን ድረስ በሕገ-ወጥ አድራጐታቸው ቀጥለውና በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የተሰጠውን እግድ በመጣስ የአህጉረ ስብከትን ጽ/ቤት እየሰበሩ በመግባት በሌላቸው ሥልጣን ክህነት በመስጠት፣ በመዋቅራችን ላይ የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞችን በመመደብ በሕገ-ወጥ አድራጐታቸው በመቀጠል ላይ ይገኛሉ፡፡
***
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን
ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በቤተ ክርስቲያናችን የተከሰተውን ወቅታዊ ችግር አስመልክቶ በሕገ ቤተ ክርስቲያኑ አንቀጽ 19 ንዑስ ቁጥር 3 የሕግ ድንጋጌ መሠረት አስቸኳይ የምልዓተ ጉባኤ ስብሰባ በማድረግ ሕገ ቤተ ክርስቲያንን፣ ቀኖና ቤተ ክርስቲያንና አስተዳደራዊ ጥሰት በመፈጸም ጥር 14 ቀን 2015 ዓ.ም. በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት በሰዶ ዳጩ ወረዳ በሀሮ ባለወልድ ቤተ ክርስቲያን የተፈጸመውን ሕገ-ወጥ የኤጲስ ቆጶሳት ሹመት ሕገ ቤተ ክርስቲያንንና ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን የጣሰ ሕገ-ወጥ አድራጐት መሆኑን አጽንኦት በመስጠት በጉዳዩ ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ ፡-
ሕገ-ወጥ ሹመቱ ቀኖና ቤተ ክርስቲያንና ሕገ ቤተ ክርስቲያንን የጣሰ በመሆኑ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን፤
ሕገ-ወጥ ሹመቱን ያከናወኑት 3ቱ የቀድሞ ሊቃነ ጳጳሳትና ተሹመናል ባዮችን 25 ግለሰቦች ከዲቁና ጀምሮ ያላቸውን ሙሉ ሥልጣነ ክህነት በመሻር እና ከቤተ ክርስቲያኒቱ አባልነት በማውገዝ መለየቱ ፤
ምንም እንኳን የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ሁሉንም አውግዞ የለየ ቢሆንም እናት ቤተ ክርስቲያን ዘወትር ለሰላም በሯ ክፍት እንደመሆኑ መጠን የተወገዙት ግለሰቦች የቤተ ክርስቲያኒቱን የሰላም ጥሪ ተቀብለውና የተከናወነው ድርጊት ሕገ-ወጥ መሆኑን አምነው በቀኖና ቤተ ክርስቲያን መሠረት ለፈጸሙት ሕገ-ወጥ አድራጐት የሚሰጣቸውን ቀኖና ለመቀበል ፈቃደኛ ከሆኑና ይህንንም ሐሳባቸውን በጽሑፍ ለቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት በማቅረብ ሪፖርት ካደረጉ የቤተ ክርስቲያናችን የሰላም በር ክፍት መሆኑን የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ጥር 18 ቀን 2015ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ መግለጹን እናስታውሳለን፡፡

በመሆኑም የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የሰላም በሩን ክፍት በማድረግ ትዕግስት የተሞላበት ጥረት ቢያደርግም የሰላም ጥሪውን ተቀብሎ ለቀኖና ቤተ ክርስቲያን ከመቅረብ ይልቅ በሕገ-ወጥ አድራጐታቸው በመቀጠል ሕጋዊ የቤተ ክርስቲያናችን መዋቅር የሆኑትን አህጉረ ስብከት ጽ/ቤትና የብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትን መንበረ ጵጵስና ቁልፍ በመስበር የንብረትና የመዋቅር ወረራ በመፈጸም በሕገወጥ አድራጐታቸው በመቀጠላቸውና በተከፈተው የሰላም በር ተጠቅመው ለሰላም ዝግጁ ባለመሆናቸው ቤተ ክርስቲያናችን በሀገሪቱ ሕግ የተረጋገጠ ሕጋዊ ሰውነት ያላት ጥንታዊትና ታሪካዊት ቤተ ክርስቲያን እንደመሆኗ መጠን ሕጋዊቱን ቤተ ክርስቲያን በሕገ-ወጥ መንገድ ተቋሞቿ የተያዙባት መሆኑን በመግለጽ መንግሥት ያለበትን ሕግን የማስከበር ኃላፊነት በመወጣት ተቋማዊ ክብራችንና ሕጋዊ ባለቤትነቷን እንዲያረጋግጥ ያደረገችውን የሰላም ጥሪ ተከትሎ ክቡር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት በቅድሚያ በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ መሪነት ከቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የተወከሉ ብፁዓን አባቶችን በማነጋገርና ለቀጣይ የውይይት አቅጣጫ በሰጡት አመራር ከቅዱስ ሲኖዶስ የተወከሉ ብፁዓን አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች እንዲሁም የቀድሞውን ሦስቱን ሊቃነ ጳጳሳት ራሳቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተገኙበት በተደረገው ሰፊ ውይይት በ10 ነጥቦች ላይ የጋራ ስምምነት መድረሱን እናስታውሳለን፡፡

እናት ቤተ ክርስቲያን በተደረሰው ስምምነት መሠረት አሥሩን የስምምነት ነጥቦች ተግባራዊ ለማድረግ ዝግጁ መሆኗን በመግለጫ አረጋግጣና በሮቿን ክፍት አድርጋ ለሰላም ከፍተኛ ጥረት በምታደርግበት ወቅት ሦስቱ የቀድሞ ሊቃነ ጳጳሳት የሰላም ጥሪውን ተቀብለው በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ መሪነት ወደ ጽርሐ መንበረ ፓትርያርክ የመጡ ቢሆንም 25ቱ ግለሰቦች ግን የሰላም ጥሪውን ከመቀበል ይልቅ እስከአሁን ድረስ በሕገ-ወጥ አድራጐታቸው ቀጥለውና በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የተሰጠውን እግድ በመጣስ የአህጉረ ስብከትን ጽ/ቤት እየሰበሩ በመግባት በሌላቸው ሥልጣን ክህነት በመስጠት፣ በመዋቅራችን ላይ የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞችን በመመደብ በሕገ-ወጥ አድራጐታቸው በመቀጠል ላይ ይገኛሉ፡፡

በመሆኑም የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት በአዲስ አበባና በአካባቢው የሚገኙ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት የሆኑትን ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ለስብሰባ በመጥራት መጋቢት 6 ቀን 2015 ዓ.ም. ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ ላይ ሦስቱ የቀድሞ ብፁዓን አባቶች በአካል ቀርበው በሰጡት ቃል በተከናወነው ድርጊትና ድርጊቱን ተከትሎ በተፈጸሙት ክስተቶች ማዘናቸውንና በቀጣይ ሕገ-ወጥ ድርጊቱን እንደሚቃወሙና በቀኖና ቤተ ክርስቲያን የቅዱስ ሲኖዶሱን መመሪያ አከብረው ለመሥራት ዝግጁ መሆናቸውን የገለጹ ሲሆን ቅዱስ ሲኖዶሱም የሦስቱን የቀድሞ አባቶች ሐሳብ በመቀበል ጉዳዩን አስመልክቶ በሰፊው ከተወያየ በኋላ የሚከተለውን የሰላም ጥሪ አስተላልፏል፡፡
በዚህም መሠረት፡-
ሦስቱ የቀድሞ ሊቃነ ጳጳሳትን በተመለከተ በስምምነቱ መሠረት ወደ ጽርሐ መንበረ ፓትርያርክ መጥተው በበዓታቸው ተወስነው እየኖሩ ስለሆነ ደመወዛቸው እንዲከፈላቸው እንዲደረግ፣

ሃያ አምስቱን ግለሰቦችን በሚመለከት ምንም እንኳን በሕ-ወጥ አድራጐታቸው የቀጠሉ ቢሆንም ቤተ ክርስቲያናችን ለሀገሪቱ ሰላም ካላት የጸና አቋም አንጻር አሁንም በድጋሚ ለመጨረሻ ጊዜ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፊት በተደረሱት 10 የስምምነት ነጥቦች መሠረት ከዛሬ መጋቢት 6 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ ባሉት አምስት ቀናት ውስጥ የሰላም ጥሪውን ተቀብለው በጽሑፍ ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ሪፖርት እንዲያደርጉና በቤተ ክርስቲያናችን ቀኖና መሠረት ከብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ቀኖናቸውን ተቀብለው እንዲፈጽሙ፣

ክቡር የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድና የኦሮምያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፕሬዝደንት ክቡር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ለሰላም ስምምነቱ ላደረጉት አስተዋጽኦ ቤተ ክርስቲያናችን ምስጋናዋን እያቀረበች በቀጣይ በተደረሰው 10 የስምምነት ነጥቦች መሠረት ሕገ-ወጦቹ ግለሰቦች የሰላም ጥሪውን ተቀብለው ለሕግ ተገዥ እንዲሆኑ የበኩላቸውን መንግሥታዊ ሚና እንዲወጡ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ጥሪዋን በድጋሚ ታስተላልፋለች፡፡

በተደረሰው ስምምነት መሠረት በሕገ-ወጥ መንገድ አህጉረ ስብከትና መንበረ ጵጵስና ሰብረው የያዙ ግለሰቦችን በተመለከተ በየደረጃው ያሉ የመንግሥት አካላት ተገቢውን የሕግ ማስከበር ሥራ በመሥራት ከቤተ ክርስቲያናችን ይዞታ በማስወጣት ለቤተ ክርስቲያናችን ሕጋዊ የሥራ ኃላፊዎች በማስረከብ የቤተ ክርስቲያኒቱ የእለት ከእለት ተግባርና ሐዋርያዊ አገልግሎት ያለምንም የጸጥታ ሥጋት እንዲከናወን እንዲሁም በተደረሰው ስምምነት መሠረት እስከአሁን መፈታት ሲገባቸው በእስር ላይ የሚገኙ የቤተ ክርስቲያኒቱ የሥራ ኃላፊዎችና ምእመናን እንዲፈቱ ቤተ ክርስቲያናችን ጥሪዋን ታስተላልፋለች፡፡

ሃያ አምስቱን ግለሰቦች በሚመለከት ከኦሮምያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ርእሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ጋር በተደረገው ውይይት ክቡር ርእሰ መስተዳድሩ በተደረሰው 10ሩ ስምምነት ነጥቦች መሠረት ሃያ አምስቱንም ግለሰቦች አጠቃልዬ ወደ አዲስ አበባ አመጣቸዋለሁ በማለት በገቡት ቃል መሠረት በአሁኑ ሰዓት ግለሰቦቹ በክልሉ መንግሥት አማካኝነት ወደ አዲስ አበባ መግባታቸውን ስለሰማን የክልሉ መንግሥት በገባው ቃል መሠረት ለፈጸመው አድራጐት ቤተ ክርስቲያናችን እያመሰገነች ያልገቡትንም ግለሰቦች በአጭር ጊዜ ውስጥ በተገባው ቃል መሠረት እንዲገቡ እንዲደረግ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፣
ውግዘቱን በሚመለከት ውግዘቱን የማንሳት ሥልጣን የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ እንደመሆኑ መጠን ሁሉም የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ለመጋቢት 21 ቀን 2015ዓ.ም. ተጠቃለው ወደ መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት እንዲመጡ ጥሪ ተላልፏል፣
መጋቢት 6 ቀን 2015ዓ.ም.
አዲስ አበባ
ኢትዮጵያ

"እኔ ተዋሕዶ ድምፅ ነኝ! እናንተስ?" በሚል መሪ ቃል የሚካሄደው ጉባኤ ሰዓታት ቀርተውታል።ማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥንን በመደገፍ ዘመቻውን በመቀላቀል ለመደገፍጎ ፈንድ ሚ ማስፈንጠሪያ https...
12/03/2023

"እኔ ተዋሕዶ ድምፅ ነኝ! እናንተስ?" በሚል መሪ ቃል የሚካሄደው ጉባኤ ሰዓታት ቀርተውታል።
ማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥንን በመደገፍ ዘመቻውን በመቀላቀል ለመደገፍ
ጎ ፈንድ ሚ ማስፈንጠሪያ
https://www.gofundme.com/f/gtbbd?utm_source=customer...
ወገን ፈንድ ማስፈንጠሪያ
https://www.wegenfund.com/.../enee-yatawaahhedo-demetse.../
የባንክ አካውንት ቁጥር አማራጮች
****
ንግድ ባንክ 1000010822657 (BETH.TEW.SENBET.TBET MAHIB.KID
+++++++++++++++++++++++++
ወጋገን ባንክ 39595010103
+++++++++++++++++++++++++
አቢሲንያ ባንክ 4753388
+++++++++++++++++++++++++
ዳሸን ባንክ 0088872166011
+++++++++++++++++++++++++
አዋሽ ባንክ 01304800017700
±++++++++++++++++++++++
አሐዱ ባንክ 0003488710101
+++++++++++++++++++++
አማራ ባንክ 9900017695658
+++++++++++++++++++++
ኦሮምያ ኅብረት ስራ ባንክ 1033100028173

እኔ የተዋህዶ ድምጽ ነኝ!እናንተስ? የኦርቶዶክሳውያንን ኅብረት የሚያሳይ ዘመቻ እነሆ ዛሬ ተጀምሯል። እናንተም ከኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ጎን በመቆም አጋርነታችሁን አሳዩ፤ ዘመቻውንም እንድት...
09/03/2023

እኔ የተዋህዶ ድምጽ ነኝ!
እናንተስ?
የኦርቶዶክሳውያንን ኅብረት የሚያሳይ ዘመቻ እነሆ ዛሬ ተጀምሯል።
እናንተም ከኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ጎን በመቆም አጋርነታችሁን አሳዩ፤ ዘመቻውንም እንድትቀላቀሉ በእግዚአብሔር ስም ጥሪ እናቀርባለን።

03/03/2023

በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ጠቅላይ ቤተ ክህነት የተሰጠ መግለጫ

ኦርቶዶክሳውያን ማልቀስ ከጀመርን ቆይተናል:: አስለቃሽ ጭስ አያስፈልገንም ነበር:: ወደ እግዚአብሔር ሊያለቅስ ለወጣ ሰላማዊ ሕዝብ ምን አስለቃሽ ጭስ ያስፈልገዋል?ዲያቆን ሔኖክ ሀይሌ
02/03/2023

ኦርቶዶክሳውያን ማልቀስ ከጀመርን ቆይተናል:: አስለቃሽ ጭስ አያስፈልገንም ነበር:: ወደ እግዚአብሔር ሊያለቅስ ለወጣ ሰላማዊ ሕዝብ ምን አስለቃሽ ጭስ ያስፈልገዋል?

ዲያቆን ሔኖክ ሀይሌ

ከመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በተተኮሰ አስለቃሽ ጭስ በመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን  የነበረው ክብረ በዓል ሳይጠናቀቅ መቋረጡ ተገለጸ::****በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በ...
02/03/2023

ከመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በተተኮሰ አስለቃሽ ጭስ በመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን የነበረው ክብረ በዓል ሳይጠናቀቅ መቋረጡ ተገለጸ::
****
በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ዓመታዊውን የሊቀ ሰማዕት ቅዱስ ጊዮርጊስ እና 127ኛውን የዓድዋ ድል መታሰቢያ ክብረ በዓል ለማክበር በርካታ ሕዝበ ክርስቲያን ከየአቅጣጫው ተሰብስቦ እንደነበረ ተገልጿል።
ታቦታተ ሕጉ ከመንበረ ክብራቸው ወጥተው የዑደት ሥነ ሥርዓት ከተፈጸመ በኋላ ክብረ በዓሉ እየተከናወነ ባለበት ወቅት ከመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ወደ ቅጽረ ቤተ ክርስቲያኑ በተወረወረ አስለቃሽ ጭስ የበዓሉ ሥነ-ሥርዓት ሳይጠነቀቅ ታቦታተ ሕጉ ወደ መንበረ ክብራቸው ተመልሰዋል ተብሏል።

ወደቅጽረ ቤተክርስቲያኑ በሚያስገቡ ሁለቱም መግቢያ በሮች በተወረወረው አስለቃሽ ጭስ በርካታ ምዕመናን በመጎዳታቸው ራሳቸውን ስተው ወደ ሆስፒታል እንደተወሰዱ ከቦታው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል ሲል የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት/Addis Ababa Diocese በፌስ ቡክ ገጹ አስነብቧል።

EOTC

በሻሸመኔ በጸጥታ ኃይሎች ድጋፍ ሰጪነትና በአጣና ተቀጥቅጦ በሐዋሳ ሆስፒታል የሕክምና እርዳታ ሲደሰግለት የነበረው አስቻለው ባረጋ ሱረታ ዛሬ በሰማዕትነት ማረፉን ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ የሲዳማ ክ...
11/02/2023

በሻሸመኔ በጸጥታ ኃይሎች ድጋፍ ሰጪነትና በአጣና ተቀጥቅጦ በሐዋሳ ሆስፒታል የሕክምና እርዳታ ሲደሰግለት የነበረው አስቻለው ባረጋ ሱረታ ዛሬ በሰማዕትነት ማረፉን ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ የሲዳማ ክልል አማሮ ጌዲኦ እና ቡርጂ የምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት ላቀ ጳጳስ በኃዘን መረጃውን አድርሰውናል

ቅዱስ ፓትርያርኩን ጨምሮ ብፁዓን አባቶች ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ውይይት እያካሔዱ ይገኛሉ።
10/02/2023

ቅዱስ ፓትርያርኩን ጨምሮ ብፁዓን አባቶች ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ውይይት እያካሔዱ ይገኛሉ።

በወቅታዊ ጉይ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የተላከ!ከኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን የቅድስት መንበር የክርስቲያኖች አንድነት ጳጳሳዊ ቢሮ  እናከኢትዮጰያ ካቶሊካዊት ቤተ-...
10/02/2023

በወቅታዊ ጉይ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የተላከ!
ከኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን የቅድስት መንበር የክርስቲያኖች አንድነት ጳጳሳዊ ቢሮ እና
ከኢትዮጰያ ካቶሊካዊት ቤተ-ክርሰሰቲያን ጳጳሳት ጉባኤ።

10/02/2023
09/02/2023

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

በስመ አብ፤ ወወልድ፤ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ከጥር ፳፱ እስከ የካቲት ፩ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም ለ ፫ ተከታታይ ቀናት ...
09/02/2023

በስመ አብ፤ ወወልድ፤ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ከጥር ፳፱ እስከ የካቲት ፩ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም ለ ፫ ተከታታይ ቀናት በመላው ዓለም የታወጀው የነነዌ ፆም እና ምሕላ መጠናቀቅን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ::

| በትንቢተ ዮናስ በሰፊው እንደተጠቀሰው የነነዌ ሰዎች በእግዚአብሔር ፊት ላይ ስለአመጹ እና ግብራቸውም በእግዚአብሔር ፊት አጸያፊ በሆነ ጊዜ እግዚአብሔር ዮናስን “ተነስተህ ወደዚያች ወደ ታላቂቱ ከተማ ወደ ነነዌ ሂድ፤ ክፋታቸውም ወደ ፊቴ ወጥቷልና በእርስዋ ላይ ስበክ” በማለት አዘዘው፡፡ ትንቢተ ዮናስ ምዕ ፩ ቁጥር ፪ ዮናስም ድምፁን ከፍ አድርጎ ለነነዌ ሰዎች የእግዚአብሔርን ቃል ሲሰብክ “የነነዌ ሰዎች እግዚአብሔርን አመኑ፤ ለጾም አዋጅ ነገሩ፤ ከታላቁም ጀምሮ እስከ ታናሹ ድረስ ማቅ ለበሱ፡፡ ወሬውም ወደ ነነዌ ንጉሥ ደረሰ፤ እርሱም ከዙፋኑ ተነስቶ መጎናጸፊያውን አወለቀ ማቅም ለበሰ፤ በአመድም ላይ ተቀመጠ፡፡ አዋጅም አስነገረ፤ በነነዌ ውስጥ የንጉሡንና የመኳንንቱን ትእዛዝ አሳወጀ፤ እንዲህም አለ ሰዎችና እንስሶች፤ ላሞችና በጎች አንዳችን አይቅመሱ፣ አይሰማሩ፣ ውኃንም አይጠጡ፤ ሰዎችና እንስሶችም በማቅ ይከደኑ፣ ወደ እግዚአብሔርም በብርቱ ጩኸት ይጩኹ፤ ሰዎችም ሁሉ ከክፉ መንገዳቸውና በእጃቸው ካለው ግፍ ይመለሱ፡፡ እኛ እንዳንጠፋ እግዚአብሔር ተመልሶ ይጸጸት እንደሆነ ማን ያውቃል፡፡ እግዚአብሔርም ከክፉ መንገዳቸው እንደተመለሱ ሥራቸውንም አየ፤ እግዚአብሔርም ያደርግባቸው ዘንድ በተናገረው ክፉ ነገር ተጸጽቶ አላደረገውም” ትንቢተ ዮናስ ፫፡ ፭-፲

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንም ይህን የነነዌ ሰዎች ፆም መነሻ በማድረግ የነነዌ ሰዎችን በምሕረቱ የጎበኘ አምላክ እኛንም በምሕረቱ ይቅር ይለን ዘንድ በየዓመቱ በአዋጅ በመፆም አምላካችንን ስንማጸንበት ኖረናል፡፡ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባዔ በጥር ፳፮ ቀን ፳፻፲፭ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ በወሰነው መሠረት የካቲት ፩ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም የተጠናቀቀው የነነዌ ፆምና ምሕላ ልዩ በሆነ በመንፈሳዊ የንስሐ ጸሎት በሰላም ተጠናቋል፡፡
በምሕላውም ከብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ጀምሮ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፤ ካህናት፤ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፤ አገልጋዮች እና ምእመናን እንደነነዌ ሰዎች ጥቁር ለብሰን ጠዋትና ማታ በጸሎት ፤ በምሕላ፤ ቀን በቅዳሴ እንዲሁም በሰባቱ የጸሎት ጊዜያት ፈጣሪያችንን ስንለምን እና ስንማጸን የቆየንበት ምክንያት በቤተክርስቲያናችን ላይ የመጣው ፈተና እጅግ በጣም ከባድ በመሆኑ ነው፡፡
በዚህ የጾምና የንስሐ ወቅት ምእመናን ልጆቻችን የአባቶቻችሁን ጥሪ ሰምታችሁ፤ የሹመኞችን ማዋክብና እስር ሳትፈሩ ጥቁር ለብሳችሁ ጠዋትና ማታ በጾምና በምሕላ፣ ቀን በቅዳሴ በቤተክርስቲያን ቅጥር እየተገኛችሁ ለአምላካችን ያቀረባችሁትን ጸሎት እና ምሕላ እግዚአብሔር ሰምቶ ለችግራችን መፍትሄ፣ ለሀገራችን ሰላምን እንደሚሰጠን እምነታችን ጽኑ ነው፡፡ እናንተም ምእመናን የቤተ ክርስቲያንን ጥሪ ሰምታችሁ ለሃይማኖታችሁ፣ ለሀገራችሁ አንድነትና ሰላም ያላችሁን ጥልቅ ፍቅር ስለገለፃችሁም ያገኘነው መንፈሳዊ ብርታት ሳንገልፅላችሁ አናልፍም፡፡

በእግዚአብሔር ቸርነት፣ በእናታችን በቅድስት ድንግል ማርያም እና በቅዱሳን አማላጅነት፣ በመላእክት ተራዳኢነት በፍፁም ፍቅርና አንድነት የያዝነውን ጸሎት እና ምሕላ አጠናቀናል፡፡ ችግራችንን ለአምላካችን በለቅሶ እና በጩኸት ነግረናል፡፡ ከዚህ በኋላ መከራው ቢጸና፣ የመከራው ጊዜ እንኳን ቢረዝም እግዚአብሔር በመከራ ውስጥ ሊያፀናን እና ሊያበረታታን አስቦ በመሆኑ በፍፁም አንናወጽም፡፡ ከእነኚህ መከራዎች በኃላም ታሪክን ጽፈን ሃይማኖታችንን ጠብቀን እና አስጠብቀን በመንፈሳዊ ጽናት እና ተጋድሎ እንሻገራለን፡፡
ጥቃቱ የቤተ ክርስቲያንን እውነት በካዱና በእውነተኛዋ ቤተ ክርስቲያን መካከል ነው፡፡ ይህም የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ሃይማኖት፤ ቀኖና እና አስተዳደራዊ ሕግጋትን ጥሰው ሕገወጥ የጳጳሳት ሢመት በመደረጉ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት ቅዱስ ሲኖዶስ በሕገ ቤተ ክርስቲያንና በቀኖና ቤተ ክርስቲያን መሠረት በጥር ፲፰ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም ይህን ጥሰት የፈፀሙትን ግለሰቦች አውግዛ ከቤተ ክርስቲያን ኅብረት የለየቻቸው ቢሆንም ጉዳዩ ከግለሰቦቹ በላይ በመንግሥት ስልጣን ላይ ባሉና ጽንፈኛ በሆኑ ፖለቲከኞች እንዲሁም የሌላ እምነት ተከታዮች ጭምር የሚደገፍ በመሆኑ ቤተ ክርስቲያንን ከፍተኛ ዋጋ እያስከፈላት ይገኛል፡፡

እየተፈጸመ ያለው ድርጊት በሰማያዊ መንፈሳዊ ዓለምና በምድራዊ ሥጋዊ ዓለም መካከል ስለሆነ በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥም የቤተ ክርስቲያን ክብርና ተቋማዊ ልዕልና ተደፍሯል፡፡ የቤተክርስቲያን ቅጥሮች መሣሪያ በያዙ አካላትና በመንግሥት የጸጥታ መዋቅር በኃይልና በጉልበት ተወሯል፡፡ ሊቃነ ጳጳሳት አባቶች ለብዙ ዓመታት ከኖሩበት አህጉረ ስብከት ያለአንዳች የሕግ መሠረት በጸጥታ መዋቅሮች ተባረዋል፡፡ በነጻነት የመንቀሳቀስ መብቶቻቸው ተገድቦም በግዞት ወደ አዲስ አበባ እንዲመለሱ ተደርገዋል፡፡ ወደ አህጉረ ስብከታቸውም ተመልሰው መግባት እንዳይችሉ እቀባ ተደርጎባቸዋል፡፡ ካህናት አባቶች እና ምእመናንም ያለአንዳች የሕግ መሠረት በየእስር ቤቱ ያለበቂ ምክንያት በሕገወጥ መንገድ ታጉረዋል፡፡ በጸጥታ ኃይል ከመጠን በላይ ከመደብደባቸው የተነሳ የሞት፣ የከባድ እና ቀላል አካል ጉዳት እንዲደርስባቸው ምክንያት ሆኗል፡፡ በአጠቃላይም በመንግሥት ኃይሎች ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ተፈፅሞባቸዋል፡፡
ቤተ ክርስቲያን ይህ ሁሉ በደል ቢፈጸምባትም ናዛዜ ሕዙናን የሆነው አምላካችን ለቤተ ክርስቲያናችን እና ለሀገራችን መፍትሔ እንዲያመጣልን፣ መንግሥትም ወደ ልቡ ተመልሶ ቤተክርስቲያንን እንዲያከብርና እንዲጠብቅ በሚል ሰላማዊ በሆነ ሁኔታ ይህን ጾም የነነዌ ሰዎች እንዳደረጉት ጥቁር ለብሰን በፍፁም ኃዘን ወደ አምላካችን እንድንጮህ ቅዱስ ሲኖዶስ ትእዛዝ ባስተላለፈበት ማግስት በሻሸመኔ ደብረ ስብሐት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ሕገወጡን ቡድን በኃይል ለማስገባት በመንግሥት የጸጥታ መዋቅሮች በተወሰደ አሰቃቂ እርምጃ እስከ አሁን በደረሰን መረጃ ቁጥራቸው ከ፴ በላይ የሚሆኑ ካህናትን እና አገልጋዮችን ጨምሮ የቤተ ክርስቲያናችን ልጆች ቅጥሯ አይደፈርም፣ ቤተክርስቲያን በተወገዙ ግለሰቦች አትረክስም በሚል ለሃይማኖታቸው ሰማእትነትን ተቀብለዋል፡፡ ቁጥራቸው ከፍተኛ የሆኑ ልጆቿም በደረሰባቸው ከባድ እና ቀላል የአካል ጉዳት ምክንያት በሕክምና ላይ ይገኛሉ፡፡ ከዚህ ሁሉ በደል በኋላም እስከ አሁን ድረስ የሞቱትን በአግባቡ መቅበርና የተጎዱትን በበቂ ሁኔታ ማሳከም ሳንችል ቀርተናል፡፡ እነዚህ ሰማዕታት በዚህ ኃጢያት በበዛበት ዘመን ለቤተክርስቲያን እስከሞት ድረስ በመታመን ለቤተ ክርስቲያንና ለምእመናን የጽናት ተምሳሌት በመሆናቸው ቤተክርስቲያን ስትዘክራቸው ትኖራለች፡፡ እንዲሁም ቤተ ክርስቲያን በልጆቿ ላይ እየደረሰ ባለው ሞት፤ እርዛት፤ እስራት እና መልከ ብዙ በሆነው መከራ ብታዝንም ለክርስትና እውነተኛነት ምስክሮች የሆኑ አዳዲስ ቅዱሳን ሰማእታትን በማግኘቷም እጅግ ደስ ትሰኛለች፡፡

ጾሙ ከተጀመረም በኋላ ሕዝቡ ወደ አምላኩ እንዳይጮህ እና እንዳይጸልይ ለማወክ የሕዝብ አስተዳዳሪ ሆነው የተሾሙ የመንግሥት ሹማምንት ሊያገለግሉት ኃላፊነት የተቀበሉበትን የሀገሪቱን ሕግ ጥሰው ምእመናን ልጆቻችን ጥቁር ለብሰው ወደ መሥሪያ ቤት እንዳይገቡና በመንግሥት ቢሮዎችም አገልግሎት እንዳያገኙ በተለይም በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት እና አንዳንድ በፌዴራል እና በከተማ መስተዳድር ቢሮዎች ጥቁር የለበሱ እና በሀዘን ላይ ያሉ ልጆቻችንን በማሠር ሲያንገላቱ በዓይናቸው ያዩ ምስክሮች አረጋግጠውልናል፡፡ በዚህም ሹማምንት ስልጣናቸውን ቤተ ክርስቲያንን ለማጥቃት እየተጠቀሙበት መሆኑን እና ለቤተ ክርስቲያናችንም ሆነ ለሕዝበ ክርስቲያኑ ከፍተኛ ንቀት እና ጥላቻ ያላቸው መሆኑን ተረድተናል፡፡
ይህ በቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ እየደረሰ ያለው መከራና በደል በዚህ ዘመን በጉልህ የሚጠቀስ የቤተ ክርስቲያን የስደትና የመከራ ጊዜ ነው፡፡ ይህ የቤተ ክርስቲያን የስደትና የመከራ ጊዜ በቤተ ክርስቲያኒቱ የታሪክ መዝገብ እና በመጽሐፈ ስንክሳር ተመዝግቦ ይቀመጣል፡፡ ለትውልድም ይተላለፋል፡፡ ይህ የፈተና ዘመን ያልፋል፤ ነገር ግን በዚህ ታሪክ ውስጥ ከእውነት ጎን የቆማችሁ ስማችሁ በታሪክ እና በወርቅ ቀለም ሲፃፍ በቤተክርስቲያን ላይ መከራ ያበዛችሁ ክፉ ታሪካችሁን ዛሬ በእጃችሁ ጽፋችሁ አልፋችኋል፡፡

በዚህ አጋጣሚ ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት እና ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውጭ ሌሎች የክልል ርዕሳን መስተዳድሮችና ከተሞች በተለይም የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር፤ የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት፤ የሲዳማ ክልላዊ መንግስት፣ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት፤ የሱማሌ ክልላዊ መንግሥት፤ የቤንሻንጉል ክልላዊ መንግሥት፣ የሐረሪ ክልላዊ መንግሥት፣ የአፋርና ጋምቤላ ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት፤ በጎፋ ዞን የሳውላ ከተማ እና ሌሎች ስማቸውን ያልጠቀስናቸው መንግሥታዊ ተቋማት የቤተ ክርስቲያናችንን ጥሪ በመከተል በአግባቡ ሕግና ሥርዓትን ለማስከበር የወሰዳችሁ ፍትሐዊ እና ሕጋዊ መፍትሔዎችን እናደንቃለን፣ በቤተ ክርስቲያንም ስም እናመሰግናለን፡፡ እንዲሁም ሀዘናችሁ ሀዘናችን ነው ብላችሁ ከጎናችን የተሰለፋችሁ አኃት አብያተ ክርስቲያናት፤ የሃይማኖት ተቋማት፣ ድርጅቶች እና ጉባኤያት፤ የእስልምና እምነት ተከታዮች፤ በእምነት የማትመስሉን ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ስላደረጋችሁልንና ስለምታደርጉልን እርዳታና ትብብር በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ስም እናመሰግናለን፡፡
ጸሎተ ምሕላውን ስናውጅ መንግሥት ሕግ አክብሮ እንዲያስከብር፣ የቤተክርስቲያኒቱን ክብር እና ልዕልና እንዲያከብር፣ በሃይማኖታችን የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ መግባቱን እንዲያቆምና ወደ ውስጡ ማየት እንዲችል ነበር::

ይህ ድርጊት እስከ አሁን ድረስ ግን መንግሥት ለዘመናት ሕጋዊ ተቋም እና የሀገር ባለውለታ የሆነችውን ቤተ ክርስቲያንን ከመስማት እና ችግሯን ከመቅረፍ ይልቅ የማዋከቡን ሥራ አጠናክሮ ቀጥሎበታል፡፡ በዚህም መንግሥት ችግሮችን ኃላፊነት ተሰምቶት እንዲፈታ ያደርገዋል የሚል እምነት ቢኖረንም አገዛዙ ግን ከጊዜ ወደ ጊዜ ልቡ መደንደኑን መመልከታችን በእጅጉ ልባችንን ሰብሮታል፡፡

በተለይም ቤተ ክርስቲያናችን ያወጀችው የ፫ ቀናት ጸሎትና ምህላ በአግባቡ እንኳን ሳይጠናቀቅ ከመንግሥት ደኅንነት የጋራ ግብረ-ኃይል ወቅታዊ የፀጥታ ጉዳይን አስመልክቶ በየካቲት ፩ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም የተሰጠው የሰልፍ ክልከላ መግለጫ መንግሥት አሁንም ችግሩን ለመፍታት ሳይሆን ቤተክርስቲያኒቱን ለአንዴና ለመጨረሻ ለማውደምና ቤተ ክርስቲያኒቱን ለማጥፋት የታወጀ አዋጅ መሆኑን በጽኑ እንድናምን አድርጎናል፡፡
በመግለጫውም፡-
፩ኛ. በእምነቱ አባቶች በተመሳሳይ መልኩ ሰልፍ ተጠርቷል በማለት መጥቀሱ የቤተክርስቲያን የመጨረሻው አካል የሆነው ቅዱስ ሲኖዶስ አውግዞ የለያቸውን አካላት የእምነቱ ተከታይ ማድረግ ብቻ ሳይሆን መብት ያላቸው ሕጋዊ አካላትና የቤተ ክርስቲያን አባቶች አድርጎ መጥራቱ አሁንም ላይ ማብራርያ ለመስጠት መሞከሩ የቤተ ክርስቲያኒቱን ክብር የሚነካ እና የሚያጠለሽ እንዲሁም ሕግና ሥርዓትን ከማስከበር ይልቅ ለሕገ ወጦች ጠበቃ ሆኖ የሚከራከረው መንግሥት መሆኑን ጭምር ለመረዳት ችለናል፡፡

በመሆኑም ቤተክርስቲያን በመንግሥት የደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል ተሰጠ የተባለው መግለጫ የቤተ ክርስቲያናችንን ሕጋዊ መብት የገፈፈ እና ሕገ ወጥ መግለጫ በመሆኑ ቤተ ክርስቲያን አትቀበለውም፡፡
፪ኛ. ጉዳዩን የውጪ እና የውስጥ ጠላቶች የፈጠሩት ነው በማለት የተለመደውን ፖለቲካዊ ቅርፅ ለማስያዝ መሞከርም ቤተክርስቲንያንም ሆነ ሕዝብን መናቅ በመሆኑ የምንቀበለው አይሆንም፡፡ ቤተ ክርስቲያን በተለይ ላለፉት ፬ ዓመታት በሀሰተኛ ትርክት ልጆቿ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል መከራን ሲቀበሉ ችግሮችን በሆደ ሰፊነት ችላ ያለፈችው የሀገር መሠረት እንዳይናጋ፣ ቅጥሯ እንዳይደፈር በማሰብና በሀገር አንድነት ላይ ባላት የማይናወጽ ጽኑ አቋም ምክንያት መሆኑን መንገር ለቀባሪው ማርዳት ነው፡፡ ጉዳዩ ግልፅ የሆነ የመንግሥት ጣልቃ ገብነት ሆኖ እያለና መፍትሄውም በመንግሥት እጅ የሚገኝ ብቻ መሆኑ እየታወቀ የፖለቲካ ቅርፅ ለማስያዝ መሞከር ችግሩን ያባብሰው እንደሆን እንጂ አይፈታውም፡፡
በሰሞኑም ቤተ ክርስቲያናችን በመዋቅር የምትመራ እና ልጆቿም ድምጽዋን አውቀው በአግባቡ የሚሰሟት መሆኑ እየታወቀ ሆነ ተብሎ ቃላት አጠቃቀሙ እንኳን ኦርቶዶክሳዊ ያልሆነ የሀሰት እና ጸብ አጫሪ የሆኑ መልእክቶችን በአደባባይ የተለጠፉ መሆናቸውን ሲታይ ምን ያህል ጉዳዩን ላልተገባ ፖለቲካዊ ጥቅም እንደተፈለገ ለመረዳት ችለናል፡፡ ይህ ተለጠፈ የተባለውም ሕገ ወጥ ጽሑፍ የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ያልሆነና ፈጽሞም ሊሆን የማይችል መሆኑን ጭምር ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡
፫ኛ. የትኛውም ሰልፍ በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍል ማድረግ አይቻልም በማለት የተደረገው ክልከላን በተመለከተም ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ ከዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ውስጥ መሠረታዊ መብት ሆኖ የተጠቀሰ እና በሕገ መንግሥቱም አንቀፅ ፴ ላይ በግልጽ የተደነገገ በመሆኑ መንግሥት ራሱ የሚመራበትን ሕገ መንግሥት ማክበርና ማስከበር ይኖርበታል፡፡ ቤተ ክርስቲያን ላይ ከላይ የተጠቀሰው ከፍተኛ መከራና በደል ምክንያት ከብዙ ሺህ ዓመታት በላይ ጸንታ የመጣችን ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን በእኛ በልጆቿ ዘመን ስትፈርስ ዝም ብሎ መመልከት በጭራሽ የሚታሰብ አይሆንም፡፡

ይህን በደላችንን ለዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ለማሳወቅ እና መንግሥትም ከሚያደርገው ጣልቃ ገብነትና አፈና ወጥቶ ሕግ እንዲያከብር እና እንዲያስከብር የጠራነው የየካቲት ፭ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም ሰላማዊ ሰልፍም መንግሥት ተገቢውን ጥበቃ በማድረግ እንድናከናውን መፍቀድ አሊያም የጠየቅናቸውን ሕገ መንግሥታዊ ጥያቄዎቻችንን በአግባቡ እና አንድ በአንድ መመለስ አማራጭ የሌለው መፍትሔ መሆኑን ደግመን ደጋግመን ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡

በዚህ ሂደት ውስጥም የሚደርስብንን ሞት፣ መከራና ስደት እኛ አባቶች ከመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ጋር ደስ ብሎን የምንቀበለው እንጂ ቤተ ክርስቲያናችን እና ሀገራችን ስትፈርስ ቆመን የምንመለከት፣ ዝም የሚል አንደበትና የሚሸከም ኀሊና የማይኖረን መሆኑን በአጽንዖት እናሳስባለን፡፡
መንግስት ከአጉል እልከኝነቱ ወጥቶ ከሕገ ወጦቹ ግለሰቦች ጋር በመተባበር በአደባባይ እየፈጸመ ያለውን የሕግ ጥሰት ዛሬን ጨምሮ በቀጣዮቹ ፪/ሁለት/ ቀናት ውስጥ እንዲያቆም እና ሕግ እና ሥርዓትን እንዲያስከብር፣ በኃይል የወረራቸውን መንበረ ጵጵስና እና አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ለቆ ለቤተክርስቲያኒቱ ሕጋዊ መዋቅር እንዲያስረክብ፣ ያለአግባብ ያሠራቸውን ካህናት እና ምእመናን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲለቅ፣ ቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ ለፈፀመው በደል በአደባባይ ይቅርታ እንዲጠይቅ፤ በካህናት እና ምእመናን ላይ ለደረሰው ሞት እና የአካል ጉዳት ተገቢውን ካሳ እንዲክስ እና የወደሙ ንብረቶቿን እንዲጠግን በጥብቅ እንጠይቃለን ፡፡

መንግሥት በዚሁ አካሄድ ሕግ እየጣሰ እና የቤተ ክርስቲያኒቱን ክብር እና ልእልና እያዋረደ የሚቀጥል ከሆነ ቤተ ክርስቲያን መንግሥት የጣሰውን ሕግ መሠረት በማድረግ መብቷን ለማስከበር እስከአሁን ድረስ ፍጹም ሰላማዊ የሆነውን እንቅስቃሴዋን አድማሱን በማስፋት በየካቲት ፭ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም ለማድረግ ያቀደችውንና ያሳወቀችውን ሀገር አቀፍ እና ዓለም አቀፍ ሰላማዊ ሰልፍ ያለማንም ከልካይነት በራሷ አደባባይ የምታከናውን መሆኑን እያሳወቅን መንግሥትም ድርሻው ሰልፉ ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ መንግሥታዊ ኃላፊነቱን በአግባቡ መወጣት ብቻ መሆኑን እያሳሰብን ዛሬም ቢሆን መንግሥት ቆም ብሎ በማሰብ ከእኛ ከአባቶች ጋር ሃይማኖታዊ፣ ቀኖናዊና መንፈሳዊ የአስተዳደር ሥርዓታችንን ባልጣሰ መልኩ ለመነጋገር እና ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት ጥረት ካደረገ በውይይት ለመፍታት መንፈሳዊ በራችን ክፍት መሆኑንም እናሳውቃለን፡፡
ከዚህ ውጭ ግን በሁለቱ አባቶች መካከል የተፈጠረ ችግር እየተባለ የሚነገረው ፖለቲካዊ ጨዋታ የመንግሥት እንጂ በሀገሪቱ ሕጋዊ ሰውነት የሌላቸውና ከቤተ ክርስቲያን የተለዩ ግለሰቦች ጋር ማነጻጸር ሕገ መንግሥታዊም ሆነ ሞራላዊ የሕግ መሠረት የለውም፡፡

ስለዚህ ቤተ ክርስቲያናችን የጠራችውን ሰላማዊ እና ሕጋዊ የሆነ የመብት ጥያቄ የማፈን ሂደትን በጥብቅ እንቃወማለን፡፡
የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን እስከአሁን ባደረጋችሁት ጽናትና ተጋድሎ ሃይማኖታችሁንና ቅድስት ቤተ ክርስቲያንችሁን እንዳላሳፈራችሁ ሁሉ አሁንም ከስሜታዊነት በወጣ ሁኔታ በከፍተኛ ጽናት እና ጥንካሬ የአባቶቻችሁን ድምጽ ብቻ እንድትሰሙ፣ ቤተ ክርስቲያንን በየአጥቢያችሁ ተደራጅታችሁ እንድትጠብቁ፤ ለአባቶቻችሁ መንፈሳዊ ጥሪ ፈጣን ምላሽ እንድትሰጡ፣ እየመጣው ላለ መከራና ስደት ለመንፈሳዊ ተጋድሎ እንድትዘጋጁና በፍፁም መንፈሳዊ ጨዋነት በአንድነት የመጣብንን ፈተና እንድትወጡ አደራ እያልን አባታዊ መልእክታችንን እያስተላለፍን ሰላማዊ ሰልፉን በተመለከተም በአጭር ጊዜ ውስጥ ዝርዝር መግለጫ የምንሰጥ መሆኑን እያሳውቅን በዚህ ጥቃት መስዋእትነት የከፈሉ እና ያረፉ ልጆቻችንን ነፍሳቸውን በአጸደ ገነት በክብር ያሳርፍልን እያልን ጸሎተ ፍትሐትም በየደረጃው የሚከናወን መሆኑን እያሳወቅን በተለያዬ ጊዜ ዛሬን ጨምሮ በወለቴ እና በሰበታ ከተሞች የደረሰውን የአካል ጉዳት እና ሞት እግዚአብሔር ምህረት እና መጽናናቱን ያድልልን፡፡ እግዚአብሔርም ገድላችሁን፣ ጽናታችሁንና ጸሎታችሁን ይቀበል፤ የቅዱሳን አምላክ ከሁላችን ጋር ይሁን፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
“እግዚአብሔር ሀገራችንን ይባርክ”
የካቲት ፪ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም.
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

09/02/2023

ቀጥታ ሥርጭት ከመንበረ ፓትርያርክ የቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ

በሻሸመኔ የቀጠለው ግፍ!***የደብረ ስብሐት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ የሆኑት ቀሲስ ጥዑመ ልሳን ምሥጋናው ሕገ ወጡን ቡድን በሚደግፉ የኦሮሚያ የጸጥታ ኃይሎች የዱላ ድብደባ ሰለ...
09/02/2023

በሻሸመኔ የቀጠለው ግፍ!
***
የደብረ ስብሐት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ የሆኑት ቀሲስ ጥዑመ ልሳን ምሥጋናው ሕገ ወጡን ቡድን በሚደግፉ የኦሮሚያ የጸጥታ ኃይሎች የዱላ ድብደባ ሰለባ ከሆኑ አባቶች መካከል አንዱ ናቸው።
በአሁኑ ሰዓት በሻሸመኔ 010 ፖሊስ ጣቢያ በእስር ላይ ያሉት አገልጋዩ ከፍተኛ ደም እየፈሰሳቸው ቢሆንም ሕክምና እንዳያገኙ ተከልክለዋል።

ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል - Tewahedo Media Center - TMC

ዜና እስር***የቀጨኔ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን የአካባቢ ወጣቶች የሆኑ ዘካርያስ ዓለማየሁና ጸጋ ደምሴ የተባሉ ኦርቶዶክሳውያን ወጣቶች በትላንትናው ዕለት ታሥረዋል።ወጣቶቹ በአሁኑ ሰዓት ሾላ...
09/02/2023

ዜና እስር
***
የቀጨኔ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን የአካባቢ ወጣቶች የሆኑ ዘካርያስ ዓለማየሁና ጸጋ ደምሴ የተባሉ ኦርቶዶክሳውያን ወጣቶች በትላንትናው ዕለት ታሥረዋል።
ወጣቶቹ በአሁኑ ሰዓት ሾላ የካ ፖሊስ ጣቢያ ታሥረው የሚገኙ ሲሆን ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡም ተገልጿል።
ወጣቶቹን ለእሥር ያበቃቸው ምክንያት በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ወጣቶችን ታነሳሳላችሁ የሚል እንደሆነም ነው ።
© ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል

09/02/2023

በወለቴ ቅዱስ ዮሐንስ ቤተክርስቲያን በከባድ መሳሪያ የታገዘ ድብደባ እየተፈፀመ ይገኛል እስከ አሁን ሁለት ሰዎች እንደተመቱ መረጃዎች ቢያሳዩም ከፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል ግን የታየ ምላሽ የለም!

ሻሽመኔ ሰማዕታቱን ሸኘች!በረከታቸው ይደርብን!
08/02/2023

ሻሽመኔ ሰማዕታቱን ሸኘች!
በረከታቸው ይደርብን!

08/02/2023

የነነዌ ፆም የምህላ ፕሮግራም በአዲሱ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን - ጥር 30 / 2015 ዓ.ም

ሰብዓዊ መብታችንን ማክበር የተሳነው መንግስት ፤ የልብሳችንን ቀለም ሊመርጥልን አይችልም !ብፁዕ አቡነ ሄኖክ ሊቀ ጳጳስ***ብፁዕነታቸው በማኅበራዊ ሚዲያ የትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክ...
08/02/2023

ሰብዓዊ መብታችንን ማክበር የተሳነው መንግስት ፤ የልብሳችንን ቀለም ሊመርጥልን አይችልም !
ብፁዕ አቡነ ሄኖክ ሊቀ ጳጳስ
***
ብፁዕነታቸው በማኅበራዊ ሚዲያ የትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት በሻሸመኔ ከተማ በኦሮሚያ ክልል መንግስት የጸጥታ ኃይሎች ኦርቶዶክሳውያንን ከክልሉ የማጽዳት ዘመቻ የሚመስል ኢሰብዓዊ እና ኢሕገመንግስታዊ ድርጊት መፈፀሙ መላው ኦርቶዶክሳውያንን ያሳዘነ ድርጊት ነው ሲሉ ገልፀዋል።

አያይዘውም ለሕዝብ የተቋቋመው መንግስት የሕዝብን ሰብዓዊ መብት አለማክበሩ ሳያንስ በአንዳንድ አካባቢዎች ፣ ብሎም መንግስት በሚመራቸው ተቋማት ውስጥ የሚሠሩ ሠራተኞች ኦርቶዶክሳውያን መልበስ የምትችሉት እኔ የመረጥኩላችሁን ብቻ ነው በሚል ቅዱስ ሲኖዶስ ያወጣውን ቀኖናዊ ትዕዛዝ ምዕመናን እንዳይፈጽሙ ብሎም እንዲሸማቀቁ በማድረግ እያካሄደ ያለው አፈና ዲሞክራት ነኝ ከሚል መንግስት የማይጠበቅ ፣ መብታችንን የረገጠ እና ከቀደሙ አፋኝ መንግሥታት ሥርዓት የተለየበትን ሁኔታ ለመገንዘብ የሚያዳግት ተግባር ነው ።

ኦርቶዶክሳውያን ምዕመናን ከምን ጊዜውም በላይ ቅዱስ ሲኖዶስ የሚሰጠውን መመሪያ እና አቅጣጫ ብቻ በመከተል የመብት ጥያቄያችን በተግባር እስከሚመለስ እና የመኖር መብታችንን እስከምናረጋግጥ ድረስ በሰላማዊ መንገድ ትግላችንን እንድንቀጥል እያሳሰብን ፤ የጸጥታ አካላትም ለሚያልፍ ጊዜ የማያልፍ ጠባሳ ከመጣልና ሰላማዊ ክርስቲያኖችን ከማሳደድ እንድትቆጠቡ እንጠይቃለን ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ተ.ሚ.ማ

ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል ሕዝባቸውን ለማረጋጋትና ለማጽናናት ወደ ሀገረ ስብከታቸው ለመሄድ  ጂማ አየር ማረፊያ ሲደርሱ  የኦሮምያ ፖሊሶች በመቀበል ኬላ አልፈው ወደ መንበረ ጵጵስናቸው  እንዳይሄ...
07/02/2023

ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል ሕዝባቸውን ለማረጋጋትና ለማጽናናት ወደ ሀገረ ስብከታቸው ለመሄድ ጂማ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የኦሮምያ ፖሊሶች በመቀበል ኬላ አልፈው ወደ መንበረ ጵጵስናቸው እንዳይሄዱ በመከልከል ወደ አዲስ አበባ ለመመለስ አየር ማረፊያ እንዲቆዩ አድርገዋል::

ብፁዕነታቸው የደቡብ ምዕራበ ኢትዮጵያ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ኃላፊ ናቸው::

@ማኅበረ ቅዱሳን

አክሱም ፅዮን ማርያም
06/02/2023

አክሱም ፅዮን ማርያም

ጸሎተ ምሕላ በደብረ ምጥማቅ ሰዓሊተ ምሕረት ቅድስት ማርያምና ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ቤተ ክርስቲያን
06/02/2023

ጸሎተ ምሕላ በደብረ ምጥማቅ ሰዓሊተ ምሕረት ቅድስት ማርያምና ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ቤተ ክርስቲያን

Address

Addis Ababa
<<NOT-APPLICABLE>>

Telephone

+12026189927

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የቅዱስ ገብርኤል ማኅበር St. Gabriel Association posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to የቅዱስ ገብርኤል ማኅበር St. Gabriel Association:

Videos

Share

Our Story

zikkir.org - Ethiopian Orthodox Tewahedo Church is the largest video sharing site of Ethiopian Orthodox Tewahedo Church.It includes Official videos Ethiopian Orthodox Tewahedo Church Mezmur, sermons,preaching, history of the church, stories of martyrs and saints.

Nearby media companies



You may also like