የአለም ዋንጫ እና የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ጨዋታዎችን ጨምሮ በታሪክ የማይረሱ በርካታ ተአምራዊ ጨዋታዎችን በመሀል ዳኝነት መምራት ችለዋል።
ጣሊያናዊው የመሀል ሜዳ ዳኛ ፔርሉጂ ኮሊና ከመሯቸው ጨዋታዎች ሁሉ በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ ማንችስተር ዩናይትድ ባለቀ ሰአት ባየርን ሙኒክን አሸንፎ ሻምፒዮን የሆነበትን ጨዋታ መቼም አይረሱትም።
በ1998/99 በካምፕ ኑ በተደረገው የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ የእግር ኳስን እውነተኛ ገፅታ ማየታቸውንም ጨዋታውን የመሩት ፔርሉጂ ኮሊና ይናገራሉ።
አዘጋጅ፦አዲሱ ቢረዳ
አቅራቢ፦ጅላሉ አወል
እንግሊዝ በአሰልጣኝነት እና በተጨዋችነት ካፈራቻቸው ድንቅ የእግር ኳስ ሰዎች መካከል አንዱ ነበር።
በተጨዋችነት ዘመኑ ለተለያዩ የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ክለቦች ተጫውቶ ያሳለፈ ኮከብ ነው ቴሪ ቬናብልስ።
አመለሸጋው የእግር ኳስ ኮከብ ቬናብልስ ከስፖርቱ ባለፈ በስነ ፅሁም አንቱታን ማትረፍ ችሏል።
አዘጋጅ፦አዲሱ ቢረዳ
አቅራቢ፦ብሩክ ድንቁ
ከልጅነቱ ሲደግፈው እና ሲያልመው ለነበረው አርሰናል ፊርማውን ቢያኖርም በመጀመሪያዎቹ አመታት ነገሮች የተስተካከሉ ሊሆኑለት አልቻለም ነበር።
በኪሊያን ምባፔ አባት እገዛ ያደገው ፈረንሳዊው የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ዊሊያም ሳሊባ ወላጅ እናት እና አባቱን በተወሰነ የጊዜያት ልዩነት ነበር ያጣው።
ለሚወደው ክለብ አርሰናል ፊርማውን ባኖረበት የመጀመሪያዎቹ አመታት የተቸገረው ምርጡ ተከላካይ ዊሊያም ሳሊባ አሁን በመድፈኞቹ ቤት የማይነካው ተጨዋች ሆኗል።
አዘጋጅ፦ወንድማገኝ ፀጋዬ
አቅራቢ፦ብሩክ ድንቁ
እግር ኳስን ለመጫወት ወደ ሜዳ ስትወጣ ሴት በመሆኗ ከማህበረሰቡ ይደርስባት የነበረውን ትችት ተቋቁማ በአለም እግር ኳስ ከታዩ ድንቅ ሴት ተጨዋቾች መካከል አንዷ መሆን ችላለች።
የእግር ኳስ ጥበበኞች መፍለቂያ ከሆነችው ከብራዚል የተገኘችው ማርታ በፓሪስ ኦሎምፒክ የመሳተፍ ህልም አላት።
የብራዚል ብሔራዊ ቡድን የምንግዜም ምርጥ ተጨዋቾች መካከል አንዷ የሆነችው ማርታ በዚህ የውድድር ዘመን መጨረሻ ራሷን ከእግር ኳሱ አለም እንደምታገል መናገሯ ይታወሳል።
አዘጋጅ፦አዲሱ ቢረዳ
አቅራቢ።፦ሀመልማል ዋለ
ሁለቱ ክለቦች የከተማ ተቀናቃኝነት ባይኖራቸውም በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ በጉጉት ከሚጠበቁና ትልቅ ፉክክር ከሚታይባቸው ጨዋታዎች መካከል አንዱ ነው።
#በሰር_አሌክስ_ፈርጉሰን እና #በአርሰን_ቬንገር የአሰልጣኝነት ዘመን የሁለቱ ክለቦች ፍጥጫ ከ90 ደቂቃም በላይ ትርጉም አለው #ማንችስተር_ዩናይትድ #ከአርሰናል።
አሁን ሁለቱ ቡድኖች ወቅታዊ ብቃታቸው የተራራቀ ቢሆንም እሁድ ምሽት በኦልድትራፎርድ የሚያደርጉት ጨዋታ ከወዲሁ ተጠባቂ ሆኗል።
አዘጋጅ፦ወንድማገኝ ፀጋዬ
አቅራቢ፦ ብሩክ ድንቁ
ድንቅ የእግር ኳስ ችሎታ ቢኖረውም እግር ኳስን በላቀ ደረጃ ለመጫወት ብዙ መስዋዕትነት ከፍሏል።
በአንድ ወቅት እግር ኳስን መጫወት በማቆም ትምህርት ለመማር እና ወታደር ለመሆን ጥያቄ ቢያቀርብም ጥያቄው ተቀባይነት ሳያገኝ በመቅረቱ በህይወቱ ተስፋ ቆርጦ የነበረም ተጨዋች ነው።
በየመጠጥ ቤቱ እየሄደ በመረበሹ ከምሽት ሶስት ስአት በኃላ እንዳያመሽ በመከልከሉ ቡድኑ የማታ ጨዋታ ካለው በጊዜ ቤቱ እንዲገባ ተቀይሮ ይወጣም ነበር ይህ ሰው ጃሚ ቫርዲ ነው።
ቫርዲ ሌስተር ሲቲ ሻምፒዮን ሲሆን ትልቅ አስተዋጽኦ ነበረው።ሌስተር ሲቲ አሁንም በቫርዲ እገዛ ከሻምፒዮን ሺፑ ወደ ፕሪምየር ሊጉ መመለስ ችሏል።
ወንድማገኝ ፀጋዬ ያዘጋጀውን ደምሰው ሀይለሚካኤል ያቀርበዋል።
በልጅነቱ ቤተሰቦቹ ሊያሳድጉት ባለመፈለጋቸው ቢጥሉትም አለም ሁሉ ከሚያስታውሳቸው የእግር ኳስ ኮከቦች ተርታ ስሙን ማስፈር የቻለ ኮከብ ነው።
ፈረንሳዊው ኮከብ ፍራንክ ሪበሪ በልጅነቱ ፊቱ ላይ ባለው ጠባሳ ምክንያት የሚደርስበት ትንኮሳ አስቸጋሪ ባህሪ ተላብሶ እንዲያድግ አድርጎታል።
ፍራንክ ሪበሪ በእግር ኳስ ህይወቱ ካሳያቸው ድንቅ ብቃቶቹ አንፃር የባሎንዶር ሽልማት እየተገባው የተነፈገ ተጨዋች ነው።
አዲሱ ቢረዳ ያዘጋጀውን ብሩክ ድንቁ።
በአውሮፓ ታላላቅ ሊጎች ውስጥ ከሚጠበቁ የደርቢ ጨዋታዎች መካከል አንዱ ነው ደርቢ ዴላ ሚዶኒና።
የገንዘብ አቅም እና የመደብ ልዩነት ደርቢውን ከአመታት በፊት ከፍተኛ ውጥረት ውስጥ አስገብተዋታል።
ሁለቱ የጣሊያን ክለቦች ብዙ የሚያለያያቸው ነገር ቢኖርም አንድ የሚያደርጋቸው ትልቅ ምክንያት አለ።
ዛሬ ምሽት 3፡45 ጁሴፔ ሜዛ ላይ የሚደረገው ደርቢ ዴላ ማዶኒና ከወዲሁ ተጠባቂ ሆኗል።
ወንድማገኝ ፀጋዬ ያዘጋጀውን በአለም እንዳለ።
ሁሌም የማይዘነጋ በርካታ ቤተሰቦችን በታትኖ ባስቀረው እና ህፃናትን ያለ ወላጅ ሜዳ ላይ በጣለው የሱናሚ አደጋ አንድ የሰባት አመት ህፃን ልጅ ለ19 ቀናት በዛ አደገኛ ስፍራ ለመቆየት ተገደደ።
የሱናሚው ልጅ ማርቱኒስ ቀዩን የፖርቹጋል ማልያ ለብሶ ለ19 ቀናት ሲሰቃይ ቆይቶ በስካይ ቴሌቪዥን ሰራተኞች አማካኝነት ወደ ህክምና ስፍራ ተወስዶ በድጋሚ የመኖርን እድል አገኘ፣ዶክተሮቹም ለተጨማሪ አንድ ቀን ቢዘገይ በህይወት እንደማይኖር ተናገሩ።
አለማችን በታሪኳ ካስተናገደችው እጅግ አስከፊ ከሆነው አደጋ በተአምር የተረፈውን ህፃን ቀጣይ ህይወት የተቃና ለማድረግ ፖርቹጋላዊውን ኮከብ ክርስቲያኖ ሮናልዶን የቀደመ አልነበረም።
የሱናሚው ልጅ ማርቱኒስም ቢሆን ለክርስቲያኖ ሮናልዶ ልዩ ፍቅር አለው ሁሌም ሮናልዶን ያመሰግናል።
ወንድማገኝ ፀጋዬ ያዘጋጀውን ብሩክ ድንቁ ያቀርበዋል።
በ1960ዎቹ እና 70ዎቹ ጎልተው ከወጡ ተጨዋቾች መካከል አንዱ ነው።አብዛኛውን የጨዋታ ዘመኑን ለአንድ ክለብ ብቻ ተጫውቶ አሳልፏል።
በሁለት የአፍሪካ ዋንጫ መድረክ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን በመወከል የተጫወተ አንጋፋ ተጨዋች ነው ንጉሴ ገብሬ።
አዲሱ ቢረዳ ያዘጋጀውን አለም እንዳለ ያቀርብልናል