Tewahido-ተዋህዶ Tube

Tewahido-ተዋህዶ  Tube Educational & Entertainment

https://youtu.be/tAPBvWWb1GY
27/08/2022

https://youtu.be/tAPBvWWb1GY

ይሂ የዘማሪ ሮቤል ድንቅ ና እጅግ ተወዳጅ ዝማሬ ከነ ግጥሙ የተዘጋጅ ነው

እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ጾመ ፍልሰታ ፍቺ በዓል በሰላምና በጤና አደረሰን አደረሳችሁ! በየትም ዓለም የምትኖሩ የክርስትና እምነት ተከታዮች ሰላምታችን ይድረሳችሁ፡፡ እመቤ...
22/08/2022

እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ጾመ ፍልሰታ ፍቺ በዓል በሰላምና በጤና አደረሰን አደረሳችሁ! በየትም ዓለም የምትኖሩ የክርስትና እምነት ተከታዮች ሰላምታችን ይድረሳችሁ፡፡



እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዚህ ምድር የኖረችው ስልሳ አራት ዓመት ነው፡፡ እነዚህ ዓመታት ሲተነተኑ ሦስት ዓመት በወላጆቿ ሐናና ኢያቄም ቤት፣ ዐሥራ ሁለት ዓመት በቤተ መቅደስ፣ ሠላሣ ሦስት ዓመት ከሦስት ወር ከልጇ ከወዳጇ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር አሥራ አምስት ዓመት ከሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ ጋር ነው፡፡

ያረፈችውም ጥር 21 ቀን በ50 ዓ.ም ነው፡፡ ባረፈችበት ወቅት ቅዱሳን ሐዋርያት ክቡር ሥጋዋን ለማሳረፍ ወደ ጌቴ ሴማኒ ሲሔዱ አይሁድ "ቀድሞ ልጇ በሦስተኛው ቀን ሞትን ድል አድርጎ ተነሣ፤ በአርባኛውም ቀን ወደ ሰማይ ዐረገ፤ ተመልሶም ይህን ዓለምን ለማሳለፍ ይመጣል እያሉ በማስተማር ሕዝባችንን ወስደውብናል፡፡ አሁን ደግሞ ዝም ብለን ብንተዋት እርሷም እንደ ልጇ ተነሳች እያሉ በማስተማር ሊያውኩን አይደለምን? ኑ! ተሰብስበን በእሳት እናቃጥላት" ብለው ክፉ ምክር ተማከሩ፡፡

ከመካከላቸውም ብርቱ ሰው የሆነው #ታውፋንያ የተባለ ቅድስት ሥጋዋን ከሐዋርያት ነጥቆ ለማስቀረት ክቡር ሥጋዋ ያለበትን የአልጋ ሸንኮር ሲይዝ በመልአከ እግዚአብሔር እጁ ተቆርጣ ከአልጋው ላይ ተንጠልጥላ ቀረች፤ ከዚህ የጥፋቱ ሥራው ተምሮ እመቤታችንን በመለመኑ እመቤታችን የተቆረጠች እጁን መልሳለታለች፡፡

ከዚህ በኋላ መልአከ እግዚአብሔር የእመቤታችንን የተቀደሰ ሥጋዋን ጌታችን ይወደው የነበረ ተብሎ የተነገረለት ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስን ይዞ በገነት በዕፀ ሕይወት ሥር አስቀመጠው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስም የሆነውን ሁሉ ለወንድሞቹ ቅዱሳን ሐዋርያት ነገራቸው፡፡ እነሱም የእመቤታችን ሥጋ በክብር ለማሳረፍ ካላቸው ጉጉት የተነሣ ከነሐሴ 1 ቀን ጀምሮ ሱባኤ ገቡ፡፡

ከሁለተኛ ሱባኤ ቆይታቸው በኋላ በአሥራ አራተኛ ቀናቸው ጌታችን የእመቤታችንን ትኩስ ሥጋ ሰጣቸው፡፡ ሐዋርያትም በዝማሬና በታላቅ ምስጋና በጌቴ ሴማኔ ቀበሯት፡፡ ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት ‹‹አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ አንተና የመቅደስህ ታቦት› › ተብሎ ትንቢት የተናገረውን ሲተረጉሙት ‹‹ፈጣሪያችን እግዚአብሔር ሆይ፥ ወደ መንግሥተ ሰማያት የምታሳርፈው የመቅደስህ ታቦት የሆነችውን ድንግል ማርያምን ይዘህ ተነሥ›› ብለው ያመሰጥሩታል፡፡ /መዝ. 131፥8/፡፡

የእመቤታችንን ቅድስት ሥጋዋን ሐዋርያት ሲቀብሯት በሀገረ ስብከቱ ሕንድ የነበረው ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ ከሀገረ ስብከቱ ሲመለስ እመቤታችን ስታርግ ያገኛታል ለምልክት እንዲሆነው ሰበኗን (የመግነዟን ጨርቅ) ተቀብሏት ይለያያሉ፡፡ ለወንድሞቹ ሐዋርያት ያየውን ይነግራቸዋል፡፡

ለበረከት የሰጠችውንም ሰበን ያካፍላቸዋል፤ ሐዋርያት ‹ ‹ዕርገቷን እንዴት እሱ ብቻ ተመልክቶ ለምን እኛ ይቀርብናል› › ብለው በዓመቱ ነሐሴ አንድ ቀን ሱባኤ ገቡ፡፡ ነሐሴ 16 ቀን የልባቸው መሻት ተፈጸመላቸው፡፡ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እመቤታችንን መንበር፣ ቅዱስ ጴጥሮስን ንፍቀ (ረዳት) ቄስ፣ ቀዳሚ ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስን ገባሬ ሰናይ (ዋና ዲያቆን) አድርጎ ቀድሶ ሁሉንም አቆረባቸው፡፡

በትኅትና የያዙት ሱባኤም የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን ዕርገቷን ለማየት አበቃቸው፡፡ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንም ይህን መሠረት አድርጋ ከነሐሴ 1-16 ጾመ ፍልሰታ በማለት ከሰባቱ አጽዋማት አንዱ አድርገን እንድንጠቀምበት ሥርዐት ሠራችልን፡፡

በነቢያና በሐዋርያት መሠረት ላይ የታነጽን ኦርቶዶክሳውያን የተዋሕዶ ልጆች በየዓመቱ ይህን ጾም በሱባኤ በማሳለፍ ከእመቤታችን ጸጋና በረከት ተሳታፊዎች እንሆናለን፤ ሆነናልም፡፡ የዓመት ሰዎች ይበለን፡፡

ከእመቤታችን ረድኤት በረከት ተቋዳሾች ያድርገን፡፡
አሜን!

ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!

https://youtu.be/kIeSZC8Z2xU
17/08/2022

https://youtu.be/kIeSZC8Z2xU

ከዐበይት በዓላት እንዱ የሆነው የደብረ ታቦር ወይም ብሄ በዓል አከባበር ና ማስረጃውlika and subscribe

17/08/2022

በዋዜማው የሠፈር ልጆች በየቤቱ እየዞሩ ሆያ ሆዬ! አሲዮ ቤሌማ እያሉ ይጨፍራሉ።

ቡሔ በሉ

ቡሔ በሉ |2| ሆ ልጆች ሁሉ ሆ

የኛማ ጌታ ሆ የአለም ፈጣሪ ሆ

የሰላም አምላክ ሆ ትሁት መሀሪ ሆ

በደብረታቦር ሆ የተገለፀው ሆ

ፊቱ እንደፀሀይ ሆ በርቶ የታየው ሆ

ልብሱ እንደ ብርሃን ሆ ያንፀባረቀው ሆ
.....................

ድምፅህን ሰማና በብሩ ደመና |2|

የቡሔው ብርሃን ለኛ በራልን |2|

…………………....

ያዕቆብ ዩሃንስ ሆእንዲሁም ጴጥሮስ ሆ

አምላክን አዩት ሆ ሙሴ ኤልያስ ሆ

አባትም አለ ሆ ልጄን ስሙት ሆ

ቃሌ ነውና ሆ የወለድኩት ሆ
.........................

ታቦር አርሞንኤም ሆ ብርሃን የታየባቸው ሆ

ከቅዱስ ተራራ ሆ ስምህ ደስ አላቸው ሆ

ሰላም ሰላም ሆየታቦር ተራራ ሆ

ብርሃነ መለኮት ሆ ባንቺ ላይ አበራሆ
.........................

በተዋህዶ ሆ ወልድ የከበረው ሆ

የእግዚአብሔር አብ ልጅ ወልደ ማርያም ነው
....................

ቡሔ በሉ ሆ ቡሔ በሉ ሆ

የአዳም ልጆች ብርሃንን ተቀበሉ

አባቴ ቤት ሆ አለኝ ለከት ሆ

እናቴም ቤት ሆ አለኝ ለከት ሆ

አጎቴም ቤት ሆ አለኝ ለከት ሆ

አክስቴም ቤት አለኝ ለከት ሆ

ተከምራል ሆ እንደ ኩበት ሆ
......................

የአመት ልምዳችን ሆ ከጥንት የመጣ ሆ

የተከመረው ሆ ከመሶብ ይውጣ ሆ

ከደብረ ታቦር ሆ ጌታ ስለመጣ ሆ

የተጋገረው ሆ ሙልሙሉ ይውጣ ሆ
......................

ኢትዮጲያውያን ሆ ታሪክ አላችሁ ሆ

ባህላችሁን ይዙ አጥብቃችሁ ሆ

ችቦውን አብሩት ሆ እንደ አባቶቻችሁ ሆ

ሚስጢር ስላለው ሆ ደስ ይበልስችሁ ሆ
...................

አባቶቶቻችን ሆ ያወረሱን ሆ

የቡሔን ትርጉም ሆ ያስተማሩን ሆ

እንድንጠብቀው ሆ ለኛ የሰጡን ሆ

ይህን ነውና ሆ ይስድረከቡን ሆ
.......................

ለድንግል ማርያም ሆ አስራት የሆንሽ ሆ

ቅዱሳን ጻድቃን ሆ የሙሉብሽ ሆ

ሁሌም እንግዶች ሆ የሚያርፉብሽ ሆ
.................

ለሐዋርያት ሆ የላከው መንፈስሆ

ዛሬም ለኢትዮጵያ ሆ ፀጋውን ያፍስ ሆ

በበጎ ምግባር ሆ እንድንታነፅ ሆ

በቅን ልቦና ሆ በጥሩ መንፈስ ሆ

በረከት ረድኤት ሆበሁላችን ይንፈስ

በዓለ ደብረ ታቦር እና ቡሄነሐሴ ፲፫ ቀን ፳፻፱ ዓ.ምጌታችን ምሥጢረ መለኮቱን ለገለጠበት ለበዓለ ደብረ ታቦር እንኳን በሰላም አደረሰን!ጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደ...
16/08/2022

በዓለ ደብረ ታቦር እና ቡሄ
ነሐሴ ፲፫ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም

ጌታችን ምሥጢረ መለኮቱን ለገለጠበት ለበዓለ ደብረ ታቦር እንኳን በሰላም አደረሰን!

ጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደብረ ታቦር ብርሃነ መለኮቱን፣ ክብረ መንግሥቱን መግለጡን በማሰብ በየዓመቱ ነሐሴ ፲፫ ቀን በዓሉ በድምቀት ይከበራል፡፡ ይህ በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን ዘንድ ‹ቡሄ› በመባል ይታወቃል፡፡ ቡሄ ማለት ‹መላጣ፣ ገላጣ› ማለት ነው፡፡ በአገራችን ክረምቱ፣ ጭጋጉ፣ ደመናው ተወግዶ የብርሃን ወገግታ የሚታይበት በዚሁ በዓል አካባቢ ስለ ኾነ በዓሉ ‹ቡሄ› ተብሎ ይጠራል፡፡ በዓለ ደብረ ታቦር ጌታችን ምሥጢረ መለኮቱን የገለጠበት፤ ብርሃን የታየበትና ድምፀ መለኮቱ የተሰማበ ዕለት ስለ ኾነ ‹የብርሃን› ወይም ‹የቡሄ› በዓል ይባላል፡፡

ቡሄ ሲመጣ የክረምቱ ጨለማነት አልፎ ወደ ብርሃን፣ ወደ ጥቢ የሚያመራበት፤ ወደ መፀው የሚገባበት፤ ወገግታ የሚታይበት፤ ሰማይ ከጭጋጋማነት ወደ ብሩህነት የሚሸጋገርበት ወቅት በመኾኑ ከቡሄ በኋላ የጠነከረ ክረምት አይኖርም፡፡ ‹‹ቡሄ ከዋለ የለም ክረምት፤ ዶሮ ከጮኸ የለም ሌሊት›› እንዲሉ፡፡ በአንዳንድ የአገራችን አካባቢዎች የቡሄ ዕለት ማታ ምእመናን ችቦ ያበራሉ፡፡ ይህም በደብረ ታቦር ለታየው ብርሃነ መለኮት ምሳሌ ነው፡፡ ሕፃናቱ ይህ በዓል ከመድረሱ በፊት ቀደም ብለው ጅራፍ ሲገምዱና ሲያጮኹ (ሲያኖጉ) ይሰነብታሉ፡፡ እናቶችም ለዚህ በዓል የሚኾን ዳቦ ለመጋገር ስንዴያቸውን ሲያጥቡ፣ ሲፈትጉ ይሰነብታሉ፡፡ በበዓሉ ዋዜማ (ነሐሴ ፲፪ ቀን) ሕፃናት በየቤቱ እየዞሩ ‹‹ቡሄ ና በሉ፤ ቡሄ በሉ፡፡ ቡሄ መጣ፤ ያ መላጣ፤ ቅቤ ቀቡት እንዳይነጣ …›› እያሉ ይጫወታሉ፡፡ በዚህ ጊዜ እናቶች ካዘጋጁት ዳቦ እያነሡ ይሰጧቸዋል፡፡ ሕፃናቱ ‹ቡሄ› የሚሉትም ዳቦውን ነው፡፡

ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን በገለጠበት ዕለት እረኞች ከብርሃኑ የተነሣ እየተገረሙና እየተደነቁ ወደ ቤት አልተመለሱም ነበር፡፡ የልጆቹን መዘግየት ያዩ ወላጆች ችቦ አብርተውና ዳቦ ይዘው ፍለጋ ወጥተዋል፡፡ ‹ቡሄ› ለሚሉ ልጆች ሙልሙል ዳቦ የሚሰጠውና በበዓሉ ችቦ የሚበራውም ከዚህ ታሪክ በመነሣት ነው፡፡ ለክርስትና ልጅ፣ ለአማች፣ ለምራት፣ ለዘመድ አዝማድ ዅሉ የቡሄ ዳቦ ይሰጣል፡፡ ልጆችም ዳቧቸውን እየገመጡ ጅራፍ ሲገርፉ ይውላሉ፡፡ የጅራፉ መጮኽ የድምፀ መለኮት ምሳሌ ሲኾን፣ ጅራፉ ሲጮኽ ማስደንገጡም ነቢያትና ሐዋርያት በድምፀ መለኮት መደንገጣቸውንና መውደቃቸውን ያስታውሳል፡፡

መምህረ ሐዋርያት ኢየሱስ ክርስቶስ ሦስቱን ተማሪዎቹን ጴጥሮስን፣ ያዕቆብንና ዮሐንስን ይዞ በደብረ ታቦር ምሥጢር መግለጡን በማስታዎስ የአብነት ተማሪዎች ከመምህራቸው ጋር በመኾን በዓለ ደብረ ታቦርን (ቡሄን) ያከብራሉ፤ ስሙን ይጠራሉ፡፡ የአብነት ተማሪዎች ‹‹ስለ ደብረ ታቦር›› እያሉ እኽል ከምእመናን በመለመንና ገንዘብ በማዋጣት ጠላውን ጠምቀው፣ ዳቦውን ጋግረው፣ ቆሎውን ቆልተው ለደብረ ታቦር ዕለት ሊያስቀድሱ የመጡትን ምእመናን በመጋበዝና እርስበርስ በመገባበዝ፣ እንደዚሁም ቅኔ በማበርከት በዓለ ደብረ ታቦርን በታላቅ ድምቀት ያከብራሉ፡፡ ይህም እስከ አሁን ድረስ በአብነት ትምህርት ቤቶች የሚሠራበት ነባር ትውፊት ነው፡፡

ነገር ግን በአንድ አካባቢዎች በተለይ በከተማ ዙሪያ በዓለ ደብረ ታቦር (ቡሄ) ሃይማኖታዊ ትውፊቱን የለቀቀ ይመስላል፡፡ ለዚህም ልጆች የሚጫወቱበት መዝሙር ግጥሙና ዜማው ዓለማዊ መልእክት የሚበዛበት መኾኑ፤ በወቅቱ ችቦ ከማብራት ይልቅ ርችት መተኮሱና በየመጠጥ ቤቱ እየሰከሩ መጮኹ፤ ወዘተ. የበዓሉን መንፈሳዊ ትውፊት ከሚያደበዝዙ ተግባራት መካከል የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ ከዚሁ ዅሉ ጋርም በዚህ በዓል ገንዘብ ለመሰብሰብ ብቻ የሚሽቀዳደሙ ነገር ግን የበዓሉን ታሪካዊ አመጣጥ የማያዉቁ ልጆችም ጥቂቶች አይደሉም፡፡

ስለዚህ ወላጆች ለልጆቻቸው የበዓለ ደብረ ታቦርን መንፈሳዊነት፣ የመዝሙሮቹን ያሬዳዊነትና አከባበሩን ከቤተ ክርስቲያን መምህራን በመጠየቅ ማስተማር፤ ልጆችም ከወላጆች ወይም ከመምህራን በመጠየቅ የበዓሉን አከባበር መረዳትና የዚህን በዓል መንፈሳዊ ትውፊት ሳይበረዝ ለትውልድ ማስተላለፍ ይገባቸዋል፡፡ ‹‹ድምፅህን ሰማና በብሩህ ደመና፤ የቡሄው ብርሃን ለእኛ በራልን …›› የሚለውንና ይህን የሚመስሉ መንፈሳውያን መዝሙራትን እየዘመሩ በየቤቱ በመዘዋወር የሚያገኙትን ዳቦና ገንዘብ ለነዳያንና ለቤተ ክርስቲያን የሚሰጡ ልጆችንም ማበረታታትና አርአያነታቸውን መከተል ይኖርብናል፡፡

https://youtu.be/M6fnWg1qy8U
13/08/2022

https://youtu.be/M6fnWg1qy8U

ኑ ወደ እግዚአብሔር ተመለሱ የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሣልሣዊ ድንቅ ትምህርት እንዴት መፀለይ እንዳለብን ፀሎት የሁሉም ነግር ቀዳሚ እንደሆነ የሚያሳይ ትምህርት ነውላይክ ና ሼር በማ...

13/08/2022

መልእክት ከዶ/ር ቤቴል ደረጄ
+++++
ዘማሪት ዘሪቱ ከበደ "ያድናል" እያለች በምትዘምርበት አዲስ የፕሮቴስታንት የመዝሙር ክሊፕ ላይ የእኔን ምስል የተመለከቱ በርካቶች ወዳጆቼ "ክሊፕ መሥራት ጀመርሽ እንዴ?" ከሚል ጥያቄ ጋር የቪዲዮ ክሊፑን ልከውልኛል።

ነገሩ እንዲህ ነው፤

ሰሞኑን ለግል ጉዳዬ በሄድኩበት ሕንጻ ሊፍት ውስጥ አንዲት ሴት አብራኝ ነበረች። ድንገት "ኢየሱስ ያድናል" ስትለኝ ቀና ብዬ አየኋት። ዘሪቱ ከበደ ነበረች። "እውነትሽን ነው ኢየሱስ ያድናል። የሚያድነው ግን በእውነት እና በሥራ ቃሉን በሕይወት ሲኖሩት እንጂ በምላሰ ብቻ ስሙን ስለጠሩት አይደለም" አልኳት።

ከሊፍቱ ከወጣን በኋላም ጥቂት እርምጃዎች እየተከተለችኝ "እውነትሽን ነው። የሚደንቅ ቃል አካፈልሽኝ" አለችኝ። ንግግራችንም በዚሁ አብቅቶ ወደየጉዳያችን አመራን። ደግሜም አላገኘኋትም።

አሁን እንደተረዳሁት ዘሪቱ እኔንም ሆነ ሌሎችን ስታናግረን በርቀት ሆነው በድብቅ ቪዲዮ የሚቀርጹ ሰዎች አሰማርታ ኖሯል። በኋላ የመዝሙር ክሊፗን ስትሠራ የአንዳችንንም ፈቃድ ሳትጠይቀን በድብቅ የተቀረጹ ምስሎቻችንን በቅንብር የመዝሙሯ ማጀቢያ አድርጋ አስገብታቸዋለች።

እኔ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታይ ስሆን በማይመለከተች እምነት የእርሷን አመለካከት እንደተቀበልኩ አስመስላ የክሊፕ ማጀቢያ ማድረጓ ሳያንስ በሚዲያ ላይ አውጥታዋለች።

በየቢሮው እና ሱፐር ማርኬቱ ውስጥ ሰዎች እንዲጠነቀቁ "በካሜራ እይታ ውስጥ ነዎት" (You are under surveillance camera) ተብሎ በሚለጠፍበት ዘመን በመንገድ ላይ ያገኙትን ሰው ምስላቸው እየተቀረጸ መሆኑን እና ለምን አገልግሎት እንደሚውል ሳያሳውቁ በድብቅ ቪዲዮ ቀርጾ ለገበያ ማዋል ነውር ብቻ ሳይሆን የግለሰብን መብት የሚጋፋ ወንጀል ነው።

ዘማሪዋ በፍጥነት ምስሌን ከክሊፗ እንድታወጣው እየጠየኩ ወደፊትም ተመሳሳይ ሥህተት እንዳትፈጽም እመክራታለሁ። ይህ ባይሆን ግን መብቴን በሕግ ለመጠየቅ እገደዳለሁ።

ዶ/ር ቤቴል ደረጀ
በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ የማሕጸን ካንሰር ሰብ ስፔሺያሊስት

https://youtu.be/Ka4uqhwNo3Y
06/08/2022

https://youtu.be/Ka4uqhwNo3Y

የመጽሐፍ ቅዱስ ስሞችና ትርጉማችው #ኦርቶዶክስ Like and subscribe bemadreg beteseb yihunu

05/08/2022
https://youtu.be/hYoI9zC1BRM
05/08/2022

https://youtu.be/hYoI9zC1BRM

ፆመ ፍልሰታ ወይም የእመቤታችን ፆም በመባል የሚታወቅ ሲሆን አባቶቻችን ሐዋርያት የድንግል ማርያምን ትንሣኤ ለማዬት የፆሙት ፆም ነው እኛም ዳግም በርከትን ለማግኘት አንፆማለንlike and sub...

እንኳን ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ዑራኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል አደረሳችሁ! ዑራኤል የሚለው ስም `ዑር' እና 'ኤል' ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። ዑራኤል ማለት ትርጉሙ “የብርሃን ጌታ...
28/07/2022

እንኳን ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ዑራኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል አደረሳችሁ!

ዑራኤል የሚለው ስም `ዑር' እና 'ኤል' ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። ዑራኤል ማለት ትርጉሙ “የብርሃን ጌታ”፣ ”የአምላክ ብርሃን" ማለት ነው። ቅዱስ ዑራኤል ከ7ቱ ሊቃነ መላእክት አንዱ ሲሆን ከፍጥረተ ዓለም ጀምሮ በመብረቅና በነጎድጓድ ላይ የተሾመ መልአክ ነዉ። በመሆኑም መባርቅት ለጥጋብና ለበረከት እንዲበርቁ፣ ነጎድጓድም ለሰላም እንዲሆን ያሰማራል። መጽ/ሄኖክ 6÷2 ምሥጢረ ሰማይና እውቀትንም ሁሉ ለሄኖክ የገለጸለት የፀሀይን የጨረቃን የከዋክብትንና የሰማይ ሰራዊትን ብርሃንን የሚመራ እርሱ መሆኑን ለሄኖክ ነግሮታል። መጽ/ሄኖክ 28÷13

• ቅድስት ድንግል ማርያምን፣ ከልጇ ከአምላካችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ወደ ግብጽ ስትሰደድ መንገድ የመራ፤

• ክርስቶስ ለዓለም ቤዛ በተሰቀለ ጊዜ፣ ክቡር ደሙን በብርሃን ጽዋ ተቀብሎ፣ በብርሃነ መነሳንስ በዓለም ላይ የረጨ፤

•እውቀት ለተሰዎረባቸው ለነቢዩ ዕዝራ ሱቱኤል ጽዋ ጥበብን ያጠጣ፤

• አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በመልአኩ አማላጅነት ብዙ ድርሰት የደረሱት መልአኩ ቅዱስ ዑራኤል ጽዋ ሕይወትን ስላጠጣቸው ነው፣

• በቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ የተመሰረቱ ገዳማት በቅዱስ ዑራኤል መሪነት ነው፤

የመልአኩ የቅዱስ ዑራኤል በዓላት በዓመት 3 ናቸው።

• ጥር 22 በዓለ ሲመቱ፣

• መጋቢት 27 የጌታ ደሙን ለዓለም የረጨበት፣

• ሐምሌ 21 እና 22 ቅዳሴ ቤቱ የሚከበርበት።

በጸሎቱ ለተማጸነ ከአምላኩ በረከትን ምህረትን የሚያሰጥ አዛኝ እሩህሩህ መልአክ ነው።
የቅዱስ ዑራኤል አማላጂነት አይለየን፤ ሁላችንንም ይጠብቀን፡፡

ክፍል  4ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ እንደ አባት ይታይ ስለነበረ ታዴዎስን ወደ ሀገረ ስብከቱ ለማድረስ አብሮት ተጕዞ ነበር፡፡ ወደ ከተማዋ ሲጠጉም አንድ የሚያርሱ ሽማግሌ አገኙ፡፡ ሐዋርያቱ ወደ...
12/07/2022

ክፍል 4
ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ እንደ አባት ይታይ ስለነበረ ታዴዎስን ወደ ሀገረ ስብከቱ ለማድረስ አብሮት ተጕዞ ነበር፡፡ ወደ ከተማዋ ሲጠጉም አንድ የሚያርሱ ሽማግሌ አገኙ፡፡ ሐዋርያቱ ወደ ሽማግሌው ጠጋ ብለው የእግዚአብሔር ሰላምታ ሰጧቸው፡፡ የሚበላ ነገር ያላቸው እንደሆነም ጠየቋቸው፡፡ ሽማግሌው ገበሬም ደግ ነበሩና ‹‹ከቤት እስካመጣላችሁ ድረስ በሬዎቼን ጠብቁልኝ›› ብለው ወደ መንደር ገቡ፡፡ ሐዋርያቱም ‹‹የተጠመዱትን በሬዎች ተቀምጦ መመልከት ሐፍረት ነው›› አሉና ታዴዎስ ማረስ ጀመረ፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስም የስንዴውን ዘር አነሣ፡፡ ‹‹ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ! በረከትህ በዚህ እርሻ ላይ ትውረድ›› ብሎ ጸለየ፡፡ ታዴዎስም ‹‹የምድር በረከት በዚች እርሻ ይታይ ዘንድ አምላኬ ሆይ ፈቃድህ ይሁን›› አለ፡፡ 30 ትልም አረሱና የስንዴውን ቡቃያ ዕለቱን ወዲያው አበቀሉት፡፡ ወዲያውም ዕለቱን ዐይንን የሚማርክ የስንዴ እሸት ሆኖ ታየ፡፡ አረጋዊው ገበሬ ሲመለስ የእርሻውን መለምለም ተመልክቶ አደነቀና ‹‹ጌቶቼ እናንተ እነማን ናችሁ? በእውነት እናንተ ከሰማይ የወረዳችሁ አማልክት ናችሁ›› ብሎ በእግራቸው ሥር ወደቀ፡፡ ሐዋርያቱ ግን ‹‹እኛ የአምላክ ባሪያዎች እንጂ አማልክት አይደለንም›› ብለው የመጡበትን ምክንያት ነግረውት ወንጌልን አስተማሩት፡፡ ገበሬውም እየተደነቁ እሸቱን ታቅፈው ለቤተሰባቸው ሊያሳዩ ወደ ቤታቸው ሮጡ፡፡ የከተማዋ ሰዎችም ነገሩ ገርሟቸው ከበቧቸው፡፡ ሽማግሌው ገበሬም ያዩትንና የሰሙትን ሁሉ ተረኩላቸው፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ በማናቸውም ነገር ፈጣንና ቀልጣፋ ነበር፡፡ በቤተ ክርስቲያን ታሪክ መሠረት ቅዱስ ጴጥሮስ በፍልስጤም፣ በሶርያ፣ በጳንጦን፣ በገላትያ፣ በቀጰዶቅያ፣ በቢታንያ እና በሮሜ ወንጌልን ሰብኳል፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ በሮሜ አንድ ዓመት ከቅዱስ ጳውሎስ ጋር ካስተማረ በኋላ የሮሜ ክርስቲያኖች እየበዙ ከመምጣታቸውም በላይ የክርስትናው ጉዞ እስከ ሮማ ባለሥልጣናት ደረሰ፡፡ በትምህርቱና በተአምራቱ ካመኑት መካከል የሮማ ንጉሥ ባለሟልና የቅርብ ወዳጅ የሆነው አልታብዮስ ሚስቱ ክርስቲያን በመሆኗ በታላቅ ሀዘን ተለያዩ፡፡ በርካታ ሴቶችም አብረዋት ወደ ክርስትናው ዓለም ገቡ፡፡ የኔሮን የቅርብ ባለሥልጣናት የሆኑት የአልቢኖስና የአግሪጳ ሚስቶች ወደ ክርስትናው ገቡ፡፡ በዚህን ጊዜ ኔሮን ንጉሠ ሮማ በቅንዓት ተነሣባቸው፡፡ ኔሮን በሮም የነገሠው በ54 ዓ.ም ነው፡፡ በመንግሥቱ መጀመሪያ ደግ ሰው ነበረ፡፡ ነገር ግን በነገሠ በዓመቱ የጨካኝነት ዐመሉ ብቅ ማለት ጀመረና የአባቱን ልጅ አስገደለ፡፡ በ59 ዓ.ም ደግሞ እናቱን በመርዝ ገደለ፡፡ በ63 ዓ.ም እያስተማረ ያሳደገውን መምህሩን፣ በ62 ዓ.ም የልጅነት ሚስቱን አግታሺያን አስገደለ፡፡ ከእርሷም በኋላ ያገባትን ሚስቱን ፓፒያንም እንዲሁ ገደላት፡፡ ኔሮን በ64 ዓ.ም እርሱ ከከተማው ወጣ ብሎ በሚገኘው ቤተ መንግሥቱ ተቀምጦ የሮማን ከተማ እሳት ለቀቀባትና የሮም ሕዝብ በደረሰው አደጋ እጅግ መቆጣቱን ሲመለከት በክርስቲያኖች አመካኘ፡፡ በዚህም የተነሣ በሮማ ከተማ ሁለት ዓይነት ወሬ መናፈስ ጀመረ፡፡ ‹‹የሮማ አማልክት በክርስቲያኖች ሃይማኖት ስለተቆጡ በከተማዋ እሳት አዘነቡባት›› የሚለው የመጀመሪያው ሲሆን ‹‹ክርስቲያኖች ሆን ብለው ከተማዋን አቃጥለዋታል›› የሚለው ደግሞ ሁለተኛው ወሬ ነበር፡፡
የከተማው መጋየት ያበሳጨው የሮማ ሕዝብ፣ ክርስቲያን የሆነውን ሁሉ እያወጣ መግደሉን ተያያዘው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ በዚህ ሰዓት በእሥር ቤት ነበርና ተሰይፎ ዐረፈ፡፡ ይቀጥላል ........

12/07/2022

ክፍል 2
ዮሐ 6፡66-68፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ ጌታችንን በጣም ይወድ ነበር፡፡ ፍቅሩ ግን ቅንዓት የተቀላቀለበት በመሆኑ ጌታችን ለደቀ መዛሙርቱ የሞቱን ነገር ቀድሞ ሲነግራቸው አይሁንብህ በማለት ተከራክሯል። ማቴ 16፡23፡፡ በኋላም «ሁሉም በአንተ ቢሰናከሉ እኔ ከቶ አልሰናከልም» ብሎ በራሱ ቅንዓት ተማምኖ ተናግሮ ነበር፡፡ ጌታችን «ዶሮ ሳይጮህ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ» እያለው እንኳን «ከአንተ ጋር መሞት እንኳን የሚያስፈልገኝ ቢሆን ከቶ አልክድህም» በማለት ተከራክሯል፡፡ ማቴ 26፡34፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ አስቀድሞ የተናገረውን ቃል ለመጠበቅ ሞክሮ ነበር፡፡ ጌታችን ዛሬ «የሰው ልጅ ተላልፎ ይሰጣል» ብሎ አስተምሮአቸው ነበርና መከላከያ ይሆነኛል ብሎ ሠይፍ ደብቆ ይዞ ነበር፡፡ የሮም ጭፍሮችም ጌታችንን ለመያዝ ሲጠጉ የሊቀ ካህናቱን ባርያ (ማልኰስን) በሰይፍ ጆሮውን ቆረጠው፡፡ ዮሐ 18፡10፡፡ ጌታችን ግን ሞቱ በፍቃዱ ለድኅነተ ዓለም ነውና «ሰይፍህን ወደ ሰገባው መልስ›› ሲል ገሠጸው፡፡
ቅዱስ ጴጥሮስ የሚታወቅበት ሌላው ትልቁ ነገር ንስሓው ነው፡፡ ጌታችን በአይሁድ እጅ ከተያዘ በኋላ ጌታው አስቀድሞ ‹‹ትክደኛለህ›› ብሎ የነገረው መድረሱንና አምላኩን በመካድ መበደሉን እንዳወቀ ከግቢው ወጥቶ ተንሰቅስቆ አለቀሰ፡፡ በፍጹም ንስሓም ተመለሰ፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ በዕድሜው ታላቅነት በሐዋርያት ዘንድ እንደ አባት ይታይ ስለነበር ጌታችን ከተሰቀለ በኋላ ሐዋርያቱን ሊመግብ ወደሚያውቀው ሙያ ዓሳ ወደ ማስገሩ ተሠማራ፡፡ ጌታችንም አስቀድሞ የመረጠው እርሱ ነውና ቢክደው እንኳን በንስሐ በመመለሱ ንስሐውን መቀበሉን ዛሬም እንደሚወደው ይገልጽለት ዘንድ ዓሣ በሚያጠምድበት በጥብርያዶስ ባሕር ተገለጠለት፡፡ ሦስት ጊዜ ክዶት ነበርና ቀኖና ሰጠው፡፡ አሁን ቅዱስ ጴጥሮስ በራስ መተማመኑ እንዳላዋጣው ዐውቆአልና «ትወደኛለህን?» ተብሎ ሲጠየቅ «አንተ ታውቃለህ» ነበረ መልሱ፡፡ የራሱ ዕውቀት የት እንዳደረሰው ያውቃልና ጌታችንም በቀልን የሚተው ነውና ዛሬም እንደሚወደው በንስሓ ተመልሷልና ዛሬም ለእርሱ የሰጠውን ክብር እንደማያጐድልበት ሲነግረው (ግልገሎቼን አሰማራ፣ ጠቦቶቼን ጠብቅ፣ በጐቼን አሰማራ» በማለት ምእመናንን ልጆቹን በአደራ አስረከበው፡፡ ዮሐ 21፡15-17፡፡ ከዚያም በሞቱ እንዴት አድርጐ እግዚአብሔርን እንደሚያከብረው ነግሮት ወደ ሰማያት ዐረገ፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ በይሁዳ ምትክ ሌላ ሐዋርያ እንዲመረጥ ሐሳብ ያቀረበ እርሱ ነበር። የሐዋ 1፡16-23፡፡ በበዓለ ሃምሳም ለደቀመዛሙርቱ መንፈስ ቅዱስ በወረደላቸው ጊዜ ለተሰበሰቡት አይሁድ አፈ ጉባዔ ሆኖ ወንጌልን የሰበከ በአንዲት ዕለት ሦስት ሺህ ምእመናንንም አሳምኖ የመጀመሪያዋን አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን በኢየሩሳሌም የመሠረተ እርሱ ነው፡፡ የሐዋ 2፡14-37፡፡ አስቀድሞ ፈሪ የነበረውና በሊቀ ካህናት ቀያፋ ግቢ ጌታውን የካደው ቅዱስ ጴጥሮስ የመንፈስ ቅዱስን ኃይል ካገኘ በኋላ ግን በአይሁድ ሸንጐ ድውይ ፈወስክ ተብሎ በተከሰሰ ጊዜ በድፍረት ስለ መድኃኔዓለም ክርስቶስ መሰከረ፡፡ የሐዋ 4፡1-22፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ ቆርነሌዎስን በማጥመቅ ወንጌልን ለአሕዛብ አስቀድሞ የሰበከው ሐዋርያ ነው። የሐዋ 10፡1-11፡፡
ሐዋርያው ልዑል እግዚአብሔር ባደለው ጸጋ ጥላው እንኳን ድውያንን ይፈውስ ነበር፡፡ የሐዋ 5፡15፡፡ በሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 15 ላይ እንደተጠቀሰው በ50 ዓ.ም አካባቢ በኢየሩሳሌም በተደረገው የሐዋርያት ሲኖዶስ ከአንጾኪያ ክርስቲያኖች ለቀረበው ጥያቄ የመጀመሪያውን መልስ የሰጠው እርሱ ነበር፡፡ ስለ ቅዱስ ጴጥሮስ መልክና ቁመና ጥንታዊያን መዛግብት እንደሚከተለው ያቀርቡታል። ይቀጥላል...

12/07/2022

ሐምሌ 5 ጴጥሮስ ወጳውሎስ
ብርሃናተ ዓለም ጴጥሮስ ወጳውሎስ
ክፍል አንድ
ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስ፡- በአራማይክ ኬፋ፣ በግሪክ ጴጥሮስ ማለት ‹‹ዓለት›› ማለት ነው፡፡ አንድም ጴጥሮስ ማለት የሃይማኖት መሠረት ማለት ነው፡፡ ማቴ 16፡18፡፡
ቅዱስ ጴጥሮስ የመጀመሪያ ስሙ ስምዖን ሲሆን ጌታችን ኬፋ ብሎ ሰይሞታል፡፡ በገሊላ ባሕር ዳር በምትገኘው በቤተሳይዳ ተወለደ፡፡ ትውልዱ ከነገደ ሮቤል ሲሆን አባቱ ዮና ይባላል፡፡ የተወለደው በገሊላ አውራጃ በቤተ ሳይዳ ነው፡፡ ከአምስት ዓመቱ ጀምሮ ያደገው በቅፍርናሆም ነው፡፡ ጴርቴዋ የምትባል ሚስት የነበረችው ሲሆን የሚተዳደረው ዓሣ በማጥመድ ነበር፡፡ ከወንድሙ ከእንድርያስ ጋር ዓሣ ከሚያጠምድበት ተጠርቶ ሐዋርያ ሆኗል፡፡
ለደቀመዛሙርነት ሲመረጥ ዕድሜው 53 ዓመት እንደነበረ ይነገራል፡፡ ወደ ጌታችን ያመጣውም ወንድሙ እንድርያስ ነው፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ፣ በርናባስ እና ወንጌላዊው ማርቆስ ቤተ ዘመድ ናቸው፡፡ የማርቆስ አባት አርስጦቡሎስ እና በርናባስ በእናት የሚገናኙ ወንድማማች ናቸው፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ ያገባው የበርናባስንና የአርስጦቡሎስን እኅት ስለነበር በጋብቻ ይዛመዳሉ፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ ለሐዋርያነት ሲጠራ መተዳደሪያው የነበረውን መረቡንና ታንኳውን እንዲሁም አባቱን እርግፍ አድርጐ ትቶ ጌታውን የተከተለ ሐዋርያ ነው፡፡ የመጀመሪያ ስሙ ስምዖን ሲሆን ይህንንም እናቱ በነገዿ ስም ያወጣችለት ነው፡፡
በቂሳርያ ከተማ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ «ማን ትሉኛላችሁ?» ብሎ በጠየቀ ጊዜ «አንተ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ» ብሎ ለአይሁድ ሊቃውንት የተሰወረውን ምሥጢረ ተዋሕዶ ገልጦ በመመስከሩ ጌታችን «አንተ ጴጥሮስ ነህ» ብሎታል ይህም በላቲን ቋንቋ ዓለት ማለት ነው፡፡ በአርማይክ ደግሞ ኬፋ ይባላል፡፡ በመቀጠልም ቅዱስ ጴጥሮስ ይህን ሲመልስ ከጌታችን ዘንድ የተሰጠው መልስ ‹‹በሰማያት ያለው አባቴ እንጂ ስጋና ደም ይህን አልገለጠልህምና ብፁዕ ነህ፣ እኔም እልሃለሁ አንተ ጴጥሮስ ነህ፣ በዚህችም ዓለት ላይ ቤተክርስቲያኔን እሠራለሁ የገሃነም ደጆችም አይችሉአትም፡፡ የመንግስተ ሰማያትንም መክፈቻዎች እሰጥሃለሁ፣ በምድር የምታስረው ሁሉ በሰማያት የታሰረ ይሆናል፤ በምድር የምትፈታው ሁሉ በሰማያት የተፈታ ይሆናል›› የሚል ነው፡፡ ይኸውም በወቅቱ የነበሩ ሐዋርያትና በኋላም በእርሱ እግር የሚተኩትን ካህናት አባቶችን ወክሎ የተቀበለው እጅግ አስደናቂና ቃልኪዳን ነው፡፡
ቅዱስ ጴጥሮስ ከአዕማድ ወይንም የምሥጢር ሐዋርያት ከሚባሉት ከእነ ዮሐንስ እና ያዕቆብ ጋር በመጀመሪያ የሚቆጠር ነው፡፡ ከሐዋርያት ሁሉ ቀደም ቀደም የማለት ባሕርይ ነበረው፡፡ ጌታችን በጥብርያዶስ ባሕር ላይ ሌሊት በእግሩ ሲመጣ ቢመለከት ‹‹ወደ አንተ እመጣ ዘንድ እዘዘኝ›› በማለት ካስፈቀደ በኋላ ወደ ጌታ ለመምጣት መንገድ ጀምሮ በመሐል ጥርጣሬ ገባውና መስጠም ስለጀመረ ጌታችን «ያመንክ እንጂ ያላመንክ አትሁን» ብሎ ገሥጾ ከመስጠም አድኖታል፡፡ ማቴ 14፡22-33፡፡ በቅፍርናሆም ጉባኤ ጌታችን ምሥጢረ ቍርባንን ሲያስተምር አይሁድ ስላልገባቸው ወደ ኋላ አፈገፈጉ፡፡ ከደቀ መዛሙርቱም «ብዙዎቹ ወደ ኋላ ተመለሱ» በዚህን ጊዜ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ «እናንተ ደግሞ ልትሄዱ ትወዳላችሁ?» ብሎ ሐዋርያትን ጠየቃቸው፡፡ በዚህ ሰዓት «ጌታ ሆይ ወደ ማን እንሄዳለን? አንተ የዘለዓለም የሕይወት ቃል አለህ፣ እኛስ አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ እንደሆንክ እናምናለን» በማለት ሐዋርያትን ወክሎ የመለሰ እርሱ ነው፡፡

12/07/2022

እንኳን ለቅዱስ ጴጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት፣ ለቅዱስ ጳውሎስ ብርሃነ ዓለም፣ ለአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ፣ ለቅዱሳን 72ቱ አርድእት (ዛሬ ኹሉም ይታሠባሉ)፣ ለቅዱስ ሳቁኤል ሊቀ መላእክት፣ ለቅድስት መስቀል ክብራ (የቅዱስ ላሊበላ ሚስት)፣ ለቅዱሳን ዘደብረ ዓሣ እንዲኹም ለቅዱሳት አንዕስት (ዴውርስ: ቃርያ: አቅባማ: አቅረባንያና አክስቲያና-የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታዮች) ዓመታዊ የመታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችኹ 🙏

ዳግመኛም ዛሬ ሐምሌ 5 ቀን ቅዱስ ዮሐኒ ኢትዮጵያዊ፣ ቅዱስ አሞኒ ዘናሒሶ እንዲኹም ቅድስት አውጋንያ (ሰማዕትና ጻድቅ) ወርኃዊ መታሰቢያቸው ነው 🙏🙏🙏

አምላከ ቅዱሳን በቃልኪዳናቸው ይማረን 🤲 አሜን!

🌿🌿🌿🌼🌼🌼🌿🌿🌿🌼🌼🌼

https://youtube.com/shorts/PMzrBFcjNzs?feature=share
01/07/2022

https://youtube.com/shorts/PMzrBFcjNzs?feature=share

"አባት ለልጆቹ እንደሚራራ እንዲሁ እግዚአብሔር ለሚፈሩት ይራራል" / መምህር ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ (መዝሙረ ዳዊት 103: 13) Dianko henok haile የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ....

https://youtube.com/shorts/oguLLpGIJCQ?feature=share
18/06/2022

https://youtube.com/shorts/oguLLpGIJCQ?feature=share

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ /ለክርስቲያኖች ምክር የእትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ ሥርዓት የጠበቁ መዝሙሮች, ስብከቶች, ሥርዓተ ቅዳሴ, የሠርግ መዝሙሮች, እና ትምህርቶች የተዋህዶ ልጆ.....

https://youtube.com/shorts/3waF96aDsgM?feature=share
17/06/2022

https://youtube.com/shorts/3waF96aDsgM?feature=share

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ / ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል የእትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ ሥርዓት የጠበቁ መዝሙሮች, ስብከቶች, ሥርዓተ ቅዳሴ, የሠርግ መዝሙሮች, እና ትምህርቶች የተዋህ...

Watch "ስለ ቅድስት ድንግል ማርያም / ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ  " on YouTubehttps://youtube.com/shorts/hgDtJu9wM_I?feature=share
14/06/2022

Watch "ስለ ቅድስት ድንግል ማርያም / ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ " on YouTube
https://youtube.com/shorts/hgDtJu9wM_I?feature=share

ስለ ቅድስት ድንግል ማርያም / ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ ልጆች በማረግ ቤተሰብ ይሁኑ

የዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ እና ሳምራዊት ደመቀ የተክሊል ጋብቻ ስነ-ስርዓት በድምቀት ተፈፀመ።
11/06/2022

የዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ እና ሳምራዊት ደመቀ የተክሊል ጋብቻ ስነ-ስርዓት በድምቀት ተፈፀመ።

https://youtu.be/uMtjM91kWgg
23/05/2022

https://youtu.be/uMtjM91kWgg

ታላቅ ጉባዔ/ በልቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍየተዋህዶ ልጆች አርጉ

አድስ አበባ  ቅድስት  ልደታ  ቤተክርስቲያን https://youtu.be/xWMJ_uGpTPU
10/05/2022

አድስ አበባ ቅድስት ልደታ ቤተክርስቲያን
https://youtu.be/xWMJ_uGpTPU

ETHIOPIAN NEW ORTHODOX SIBKET BY MEHRETEAB ASEFA አንድ ሰው አንንድን ሰው በዘሩ ከሰደበው ሰይጣን ነው ማለት ነው thsi channel

https://youtu.be/eQ0725gxTKw
28/04/2022

https://youtu.be/eQ0725gxTKw

ዲ/ን ሔኖክ ሀይሌ ስለ እመቤታችን ስለ ቅድስት ድንግል ማርያም

08/04/2022

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
' ኪራላይሶን [አቤቱ ማረን] '
ኪራላይሶን፡..ኪራላይሶን፡..ኪራላይሶን፡(3)
ኪራላይሶን፡ ኪራላይሶን፡....አማኑኤል ጌታ፣
ኪራላይንሶ፡ ኪራላይሶን.....በጥፊ ተመታ፣
ኪራላይሶ፡ ኪራላይሶን.......አለምን ሊታደግ፣
ኪራላይሶን፡ ኪራላይሶንን....ተነዳ እንደበግ፣
ኪራላይሶን፡ ኪራላይሶን.....አዳምን ሊፈውስ፣
ኪራላይሶን፡ ኪራላይሶን...... ቆመ ከጵላጦስ፣

ኪራላይሶን፡.....ኪራላይሶን፣...ኪራላይሶን፡(3)
ኪራላይንሶ ኪራላይሶን........እጁን ቸነከሩት፣
ኪራላይሶን፡ ኪራላይሶ.....አጥንቱን ቆጠሩት፣
ኪራላይሶን፡ ኪራላይሶንን..የእሾህ አክሊል ደፍቶ፣
ኪራላይሶን፡ ኪራላይሶን.........ገዳዩን እረቶ፣
ኪራላይሶን፡ ኪራላይሶን .......የሁላችን በደል፣
ኪራላይሶን፡ ኪራላይሶን...ተሻረ በእርሱ ቁስል፣

ኪራላይሶን....ኪራላይሶን... ኪራላይሶን፡(3)
ኪራላይሶን፡ ኪራላይሶን........እጣ ተጣጣሉ፣
ኪራላይሶን፡ኪራላይሶን........ልብሱን ተካፈሉ፣
ኪራላይሶን፡ ኪራላይሶን........ለፍርድ ተወሰደ፣
ኪራላይሶን፡ ኪራላይሶን ........እንደበግ ታረደ፣
ኪራላይሶን፡ ኪራላይሶን.....ለብሶ ከደም ሜዳ፣
ኪራላይሶን፡ ኪራላይሶንን.......ተከፈለ እዳ፣

ኪራላይሶን.... ኪራላይሶን...... ኪራላይሶ፡ (3)
ኪራላይንሶ፡ ኪራላይሶን...ሆምጣጤ አጠጡት፣
ኪራላይሶን፡ ኪራላይሶን......በገመድ ጎተቱት፣
ኪራላይሶን፡ ኪራላይሶን......በወንበዴው ፈንታ፣
ኪራላይሶን፡ ኪራላይሶን........ተሰቀለ ጌታ፣
ኪራላይሶን፡ ኪራላይሶን......ሁሉም ዘበቱበት ኪራላይሶን፡ ኪራላይሶን......በዘላለም ህየወት፣
ኪራላይሶን..... .ኪራላይሶን......ኪራላይሶን፡
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

https://youtu.be/xWMJ_uGpTPU
06/04/2022

https://youtu.be/xWMJ_uGpTPU

ETHIOPIAN NEW ORTHODOX SIBKET BY MEHRETEAB ASEFA አንድ ሰው አንንድን ሰው በዘሩ ከሰደበው ሰይጣን ነው ማለት ነው thsi channel

04/04/2022

በኤድስና በረሃብ ከመሞት ሰውረን። ቸር አምላክ ሆይ በእስር
ቤት ያለ ፍርድ የሚማቅቁትን ፍትህ በማጣት በገዥዎች ቀንበር ሥር ወድቀው የሚሰቃዩትን ሁሉ ተመልክተህ ነፃ አውጣ። ምድራችንን እያናወጠ ካለው
የዲያብሎስ አሰራር፤ እርሱም ዘረኝነት፣ ደም እፍሳሽነት፣ ሽብርተኝነት፣
መናፍቅነት ታደገን።በመከራችን ጊዜ ካንተ በቀር የሚረዳን፤ በሀዘናችንና
በችግራችን ጊዜ የሚታደገን የለምና ይቅር በለን። በአንድ ልጅህ በጌታችን
በመድሃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ከነርሱም ጋር ትክክል በሆነ በመንፈስ ቅዱስ ስም ዛሬም ዘወትርም ለዘላለሙ አሜን።

✔ታድያ እንዴት ነው ሥርዓቱ ከተባለ እንደሚከተለው።
ሥርዓተ ምህላ ጸሎት መመሪያ
1. 150 ዳዊት በማደል ይደገማል፤
2. የዘወትር ጸሎት በአማርኝ ይደረሰል፤
3. ወዳሴ ማርያም መልከአ ማርያም መልከአኢየሱስ ይደገማል፤
4. ተዓምረ ማርያም ይነበብና እግዚአብሔርን አመስግኑ የሚለው መዝሙር
ይባላል፤
5. አቤቱ ማረን ይቅር በለን 6 ጊዜ ይደረሳል፤
6. አድህነነ ከማዓቱ ሰውረነ በምህረቱ በእንተ ማርያም ወላዲቱ 6 ጊዜ
ይደረሳል፤
7. ስምአነ አምላክነ ወመድኃኒነ 6 ጊዜ ይደረሳል፤
8. ኪራላይሶን 6 ጊዜ ይደረሳል፤
9. እግዚኦ ማሃሪነ ክርስቶስ 12 ጊዜ ከዕጣን ጋር፤
10. በዕንተ ማርያም መሃሪነ ክርስቶስ 12 ጊዜ፤
11. በዕንተ ሚካኤል 3ጊዜ፤
12. በዕንተ ገብርኤል 3ጊዜ፤
13. በዕንተ ሩፋኤል ወ ኡራኤል 3ጊዜ፤
14. በዕንተ መላዕክት 3ጊዜ፤
15. በዕንተ ነቢያት 3ጊዜ፤
16. በዕንተ ሐዋርያት 3ጊዜ፤
17. በዕንተ ጸድቃን ወቅዱሳን 3ጊዜ፤
18. በዕንተ ሰማዕታት ወጊዮርጊስ 3ጊዜ፤
19. በዕንተ ሕጻናት መሃሪነ ክርስቶስ 3ጊዜ፤
20. ማዕጠንት ይታጠናል ከላኛው እስከ ታቸኛው ወለል፤
21. ተንስኡ ለጸሎት በማለት ጸሎታ ወንጌል ይጸለያል አራቱ ወንጌል ይነበባል፤
22. ቅዱስ ተብሎ የሠርክ ኪዳን ይደረስና ይታረጋል፡፡
23. የንስሐ መዝሙሮች ይዘመራሉ



የእግዚአብሔር፣ቸርነት የድንግል ማርያም አማላጅነት፣ የቅዱሳን መላእክት
ተራዳኢነት፣ የጻድቃን፣የሰማዕታት፣ የቅዱሳን ሐዋርያት፣ የቅዱሳን አበው
መነኮሳት፣ የቅዱሳት አንስት፣ የደናግላንና የቅዱሳን ሁሉ ምልጃና ቃል- ኪዳናቸው ባለንበት ከሁላችን ጋር ይሁን ይቆየን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ለዘበቅዱሳኒሁ ይሴባሕ ይእዜኒ ወዘልፈኒ ወለዓለም ዓለም አሜን፡፡ ወአሜን
ለይኩን ለይኩን፡፡

Address

Addis Ababa
Addis Ababa
1000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Tewahido-ተዋህዶ Tube posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Share