Zalla Issipetetha

  • Home
  • Zalla Issipetetha

Zalla Issipetetha Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Zalla Issipetetha, News & Media Website, .

02/04/2022

Connect with what you love to make things happen. It’s Your World.

20/02/2022
08/11/2021
08/06/2020
08/06/2020

| የደቡብ መጨረሻ እና የጥናት ቡድኑ ታሪካዊ ስህተት
_______________________________
የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል በይፋ ከተመሰረተ የፊታችን ሰኔ 14 ሃያ ስምንተኛ ዓመቱን ይይዛል።
ኢህአዴግ መራሹ መንግስት ወደሥልጣን ከመጣ ወዲህ ካቋቋማቸው 9 ክልሎች አንዱ የሆነው ደቡብ ከሁለት አስርት ዓመታት በኋላ በተወለደበት ወር ሊከስም ዘንድ ዘንድሮ ግድ ብሎታል።

ሰኔ 14/1984ዓ.ም የተደረገውን የክልሉ ምክር ቤት ምርጫን ተከትሎ በወቅቱ የነበሩ 5 ክልሎችን አንድ ላይ በመሰብሰብ የተዋቀረው ደቡብ ዛሬ ተመልሶ ወደ5 የተለያዩ ክልሎች ሊከፋፈል ስለመሆኑ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው አካላት በመግለጽ ላይ ይገኛሉ።

በተለይም ትላንት ምሽት ዘ-ሀበሻ ከታማኝ የመረጃ ምንጬ አገኘሁት ባለው መረጃ መሰረት ክልል 1 ሲዳማ ለብቻው፤ ክልል 2 ኦሞቲክ፤ ክልል 3 የቀድሞ የሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዞኖች፤ ክልል 4 ምዕራብ ዞኖች እና ክልል 5 ጌዴኦ፣ አማሮ እና ቡርጂ በማለት ዘገባ ሰርቷል።

ምንም እንኳን ቀረበ ስለተባለው ምክረ-ሃሳብ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ እና ውስን የጥናት ቡድኑ አባላት ውጪ የሚያውቅ አካል ባለመኖሩ የዘ-ሀበሻ ዘገባ ሙሉ ለሙሉ እውነተኛ ነው የሚል ድምዳሜ ላይ መድረስ ባይቻልም ነገር ግን ይሄ ምክረ-ሃሳብ እንደተባለው ቢቀርብና በቅርቡ ለሚሰበሰበው የፌደሬሽን ም/ቤት ብይን እንዲሰጥበት ቢመራ በደቡብ ጉዳይ ከየትኛውም ግዜ በላይ ታሪካዊ ስህተት እንደተሰራ ይቆጠራል።

በተለይም ኦሞቲክ እና ጌዴኦ-አማሮ-ቡርጂ ተብለው የተቀመጡት 2 የክልል አወቃቀሮች ከአካባቢው ህዝብ ፍላጎት ውጪ የሆኑ ብቻ ሳይሆኑ አከባቢው በቀጣይ ያለመረጋጋት ቀጠና እንዲሆን የሚያደርጉ እጅግ አደገኛ ውሳኔዎች ናቸው።

ኦሞቲክን በተመለከተ ሙሉ የዎላይታ ህዝብ አደባባይ ወጥቶ አልፈልገውም ያለው፤ ድፍን የጋሞ እና ዳውሮ ህዝብ አምርሮ የተቃወመው የአቶ ሀይለማርያም እና ጀሌዎቻቸው ቡድናዊ ፕሮጀክት መሆኑ ይታወቃል። ከዚህን ቀደም ይሄ አደረጃጀት ተሞክሮ የበርካታ ንጹሃንን ህይወት ባጠፋ አሳዛኝ ፍጻሜ መደምደሙ የሚታወስ የቅርብ ግዜ ክስተት ነው።

ከዚህን ቀደም የደቡብ መልሶ ማደራጀት ሥራ በህዝቦች መካከል ቁርሾ እና መቃቃርን በማያስከትል መንገድ እንዲፈጸም እፈልጋለሁ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይሄንን እብደት የተሞላበት ምክረ ሃሳብ ለወትሮ ከዙሪያቸው ጠፍተው ከማያውቁት የቀድሞው ጠ/ሚ ተቀብለውት ከሆነ አንድ ጉዳይ ልናስታውሳቸው እንወዳለን። አቶ ሀይለማርያም ሀገርን ምስቅልቅል ውስጥ ከተው በቃኝ ብለው ወንበራቸውን ከማስረከባቸው አስቀድሞ የደቡብ ክልል ፕሬዝደንት በነበሩበት ወቅት ክልሉን ትርምስ ውስጥ ከተው ከሀዋሳ የኮበለሉ፤ በሥልጣን ዘመናቸው አንድም ቀን ዞር ብለው ወዳላዩት ዳውሮ እና ጎፋ ተጉዘው ቅስቀሳ ሲሰሩ የቆዩበት እና ዛሬ እንደአዲስ የሚያቀነቅኑት “ኦሞቲክ”፤ እንዳይሞት እንዳይድን አድርገው አሽመድምደው የጣሉ ሰው ናቸው።

በመሆኑም ጋሞ እና ወላይታ ዞኖችን በአንድ ክልል ማዋቀር ሲዳማ እና ወላይታን በአንድ ክልል ከመዋቀር በላይ አደገኛ መሆኑን በመረዳት ይህንን ታሪካዊ ስህተት ከመስራት መቆጠብ ይገባል።

በተመሳሳይ መቶ በመቶ በሆነ ድምጽ 1ኛም፣ 2ኛም፣ 3ኛም ምርጫዬ ከጋሞ ጋር በክልል መደራጀት ነው በሚል ውሳኔ ያሳለፈውን የአማሮ ህዝብ፤ ምርጫና ፍላጎቱን ወደጎን በመተው በድንበር ከማይገናኘው ጌዴኦ ዞን ጋር በክልል ለማደራጀት መሻት ዓላማው ሌላ በመሆኑ የብልጽግናው መንግስት ቆም ብሎ ሊያስብ ይገባል።

በዚህ አጋጣሚ ዛሬ እና ነገ በሚደረገው ስብሰባ ላይ ከ3 ሚሊዮን በላይ የጋሞ ህዝብን የወከላችሁ ባለሥልጣናት፤ እንዲሁም ምርጫችሁን በልተው ኩታ ገጠም ካልሆነ አካባቢ ጋር በሀይል ሊጠረንፋችሁ የሚፈልጋችሁ የአማሮ ወረዳ ተወካዮች የትኛውንም ዓይነት ዘመናዊ ባርነትን የሚያመጣ ውሳኔን በመቃወም ለህዝባችሁ “የቁርጥ-ቀን ልጆች” መሆናችሁን እስከመጨረሻው እንድታረጋግጡ የከበረ ጥሪ ይቀርብላችኋል !በዚህም ህዝባችሁ ከጎናችሁ ይሰለፋል!

[The views and opinions expressed in this publish are those of D.Aklilu Ezo.]

20/05/2020
18/05/2020

| ደቡብን መልሶ የማደራጀት ዕቅድ ዳግም ፈተና ገጥሞታል።
__________________________________
የዶ/ር ዐቢይ አስተዳደር 56 ሆኖ መኖር ይብቃን ያሉትን የደቡብ ክልል ዞኖች መልሶ በአዲስ የክልል መዋቅር ለማደራጀት ተደጋጋሚ ህዝባዊ ውይይቶችን ከማካሄድ፤ አጥኚ ብሎም አጣሪ ኮሚቴዎችን እስከማዋቀር ድረስ ጥረቶችን እያደረገ መሆኑ ይታወቃል።

80 አባላትን ያካተተው ኮሚቴ ከባለፈው ጥር ወር አንስቶ ሲያካሂድ የቆየውን ጥናት አጠናቆ አሁን ላይ ያለውን የደ/ብ/ብ/ህ ክልልን ወደ 3 የተለያዩ የክልል መዋቅሮች መበተን የሚል ምክረ-ሃሳብ ማቅረቡ ይታወሳል።

እነሱም የቀድሞ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አካል የነበሩትን ዞኖች አንድ ላይ ማደራጀት፤ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ዞኖችን በጋራ ማደራጀት እና የኦሞ ወንዝን ተከትሎ ያሉ ዞኖችን በተመሳሳይ በአንድ ክልል ማዋቀር የሚሉት ናቸው።

ይሄ ጥናት በቀረበበት ወቅት የጋሞ ዞን እና ኮንታ ልዩ ወረዳ ተወካዮች ባሰሙት የተቃውሞ ድምጽ ጉዳዩ እንደገና እንዲታይ አጣሪ ኮሚቴ እንዲዋቀር ተደርጓል። በመሆኑም ከ3ቱ የክልል መዋቅር ምክር ሃሳቦች ውስጥ 3ኛውና “የኦሞ ህዝቦች ክልል” የተባለው ከፍተኛ ተቃውሞ የተነሳበት ሆኗል።

ይህ የክልል አደረጃጀት ምክረ ሃሳብ ተቃውሞ ሊነሳበት የቻለው ዋንኛ ምክንያት እንደዚ የሚባል አደረጃጀትን የመረጠ ህዝብ ወይም ዞን አለመኖሩ ነው። ኦሞቲክ የሚባል ክልል እንዲመስረት እንፈልጋለን አሉ ተብለው የተጠቀሱት ጎፋ፣ ጋሞ፣ ዳውሮ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ወላይታ፣ ኮንሶ፣ አማሮ፣ ደራሼ፣ አሌ፣ ቡርጂ ዞኖች እንዲያውም በተቃራኒው “ኦሞቲክ” የሚባልን አደረጃጀት መስማት እንኳን የማይፈልጉ ናቸው።

ለምሳሌ የዳውሮ ዞን ኦሞቲክ በሚባል ክልል ከመደራጀት ደቡብ ምዕራብ ዞኖች ጋር መደራጀት ይሻላል በሚል ወደዛው አቅንቷል። የአማሮ ወረዳም የኮሬ ህዝብ በድንበር ከማይገናኘው የጌዴኦ ዞን ጋር አይደራጅም፤ የራሳችንን የልዩ ዞን መዋቅር ካልሰጣቹን ከጋሞ ዞን ጋር በክልል አደራጁን የሚል አቋምን አንጸባርቋል።

የጎፋ ዞን፣ ኮንሶ ዞን፣ ደቡብ ኦሞ ዞን፣ ደራሼ እና አሌ ህዝቦችም በተመሳሳይ የኦሞቲክ ክልል ሀሳብን እንደማይቀበሉት ተሰምቷል።

ምንም እንኳን የኦሞቲክ ክልልን ጉዳይ እያራገቡ የሚገኙት የወላይታ ዞን ካድሬዎች ቢሆኑም አብዛኛው የወላይታ ህዝብ ግን በተመሳሳይ ኦሞቲክ የሚባል አደረጃጀትን ማየት አይፈልግም። የጋሞ ዞንም ከሃመሳ ወንዝ ማዶ ክልል መሆን የማይታሰብ መሆኑን በማያወላዳ መልኩ በተደጋጋሚ ገልጿል።

ይህንን ተከትሎ ኦሞቲክ ወይም ወጋጎዳ የክልል መዋቅር መሉ ለሙሉ ህዝባዊ ተቃውሞ በማስተናገዱ እውን ሊሆን የሚችልበት አንዳችም ዕድል እንደሌለው ታውቋል። ይሄ ጉዳይም ደቡብን ከ4 ቦታ በላይ መሸንሸን አያዋጣም የሚል አቋም ላለው የፌደራል መንግስት ትልቅ ፈተና ሆኗል።

ይሄ የክልል መዋቅር ተቀባይነት ያጣበት እና የተጠላበት ምክንያት ከዚህ ቀደም አርባ ምንጭን ዋና ከተማው ያደረገው የኦሞቲክ ክልል የፈረሰው ዛሬ ከሞተበት መቃብር ቆፍረው ለማውጣት እየጣሩ በሚገኙት ፖለቲከኞች በመሆኑ እና የአደረጃጀቱ መመለስ የአከባቢውን ህዝቦች ዳግም ወደከፋ መቃቃር ውስጥ የሚከት በመሆኑ እንደሆነ በመገለጽ ላይ ይገኛል።

ውበታችን
18/05/2020

ውበታችን

08/03/2020

Selam

chigirachin menged new yemitebaber linisera agizun bezi dewil 0923296630
04/01/2020

chigirachin menged new yemitebaber linisera agizun bezi dewil 0923296630

04/01/2020

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Zalla Issipetetha posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share