Ghion-Daily

Ghion-Daily Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Ghion-Daily, Media/News Company, .

March 7, 2024 The Board of Directors International Monetary Fund 700 19th St. NW 20431 Washington, D.C. Subject: Urgent ...
09/03/2024

March 7, 2024
The Board of Directors
International Monetary Fund
700 19th St. NW 20431

Washington, D.C.

Subject: Urgent Appeal: Do Not Enable Violence – Deny Funding to Ethiopian Government

Dear Esteemed Representatives of the International Monetary Fund,

We, the undersigned members of a civic forum, would like to bring to your attention our urgent appeal to implore the International Monetary Fund to reconsider any plans to extend financial assistance to the Ethiopian government amidst the harrowing atrocities and crimes against humanity that it is continuing to inflict on the nation. It seems rather odd that the government is seeking financial assistance while it is building a white elephant project like a new palace costing as much as a reported $15B, and other vanity projects. Undertaking Such vanity projects while the people are languishing in dire economic conditions not only exacerbates their suffering but also undermines the credibility and effectiveness of any financial support provided.

የፋኖን ትግል ሂደት ፍሬም በማድረግ ረገድ .... ከድንዛዜ የመውጣትና ጠንካራ ትግል በቁርጠኝነት እንዲጀመር የእስክንድር ነጋ ወደ ሜዳ  መግባት ያደረገው አስታውፆ የቃላት ክምር ሊገልፁት አ...
08/01/2024

የፋኖን ትግል ሂደት ፍሬም በማድረግ ረገድ .... ከድንዛዜ የመውጣትና ጠንካራ ትግል በቁርጠኝነት እንዲጀመር የእስክንድር ነጋ ወደ ሜዳ መግባት ያደረገው አስታውፆ የቃላት ክምር ሊገልፁት አይችሉም::

08/01/2024

ከኦነግ መግለጫ አንዱ:-
⬇️

በኢትዮጵያና በሶማሊላንድ የወደብ ስምምነት ምክንያት በሶማሊያ በሚገኙ የኦሮሞ ማህበረሰብ አባላት ስደተኞች ላይ አደጋ ተጋርጧል፣ ይህን አደጋ ለማስቀረት አለማቀፉ ማህበረሰብና መንግስታት እንዲረባረቡ ሲል የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ጠየቀ። ኦነግ ትናንት ባወጣው መግለጫ ከኢትዮ ሶማሊላንድ ስምምነት ተከትሎ በሶማሊያና ሶማሊላንድ ያሉ ኢትዮጵያውያን የኦሮሞ ማህበረሰብ አባላትና ስደተኞች የጥቃት ኢላማ መሆናቸውን ገልጾ የሶማሊያ እና የኢትዮጵያ መንግስታት ያልተግባቡበትን ጉዳዩ በትዕግስትና በውይይት እንዲፈቱ ጠይቋል። ተመድ፣ የአፍሪቃ ህብረትና የአውሮፓ ህብረት በጉዳዩ ላይ ዲፕሎማሲያዊ ጫና እንዲያደርጉ አሳስቧል።

08/01/2024

ሸህ አብዱ ያሲን በተተኮሰባቸው ጥይት ተገደሉ‼️

በአዲስ አበባ ከተማ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 በአስኮ አዲስ ሰፈር የበድር መስጂድ ኢማምና ኸጢብ እንዲሁም በመስጂዱ የተለያዩ ኪታቦችን በማቅራት የሚታወቁት ሸይኽ አብዱ ያሲን የዒሻ ሶላት አሰግደው ወደቤታቸው ሲመለሱ ለጊዜው ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች በተተኮሰ ጥይት ተገድለዋል ።

ሸይኽ አብዱ ያሲን በጥይት ከተመቱ በኋላ አቤት ሆስፒታል ለሕክምና ቢወሰዱም ህይወታቸውን ማትረፍ አልተቻለም።

ሀሩን ሚዲያ አገኘሁት ባለው መረጃ መሰረት የወንጀሉ ፈጻሚ እና ምክንያት እስካሁን በትክክል እንዳልታወቀና ፖሊስ ሁኔታዉን ለማጠራት በአከባቢዉ እንደተገኘ የተነገረ ሲሆን በተጨማሪም የአዲስአበባ መጅሊስ ጉዳዩን ለማጣራት በቦታው መገኘቱ ተገልጿል።

08/01/2024
የኩሽ ጭንብልን አጥልቆ በኢትዮጵያ ወደብ ስም ለኦሮሚያ ሪፐብሊክ ግንባታ የሚታትረው የኦሮሞ ኃይል የመስፋፋት አጀንዳ ለአማራው ምኑም ነው። ይልቁንስ ለአማራው የህልውና አደጋ ሆኖ የባጀው ይህ...
08/01/2024

የኩሽ ጭንብልን አጥልቆ በኢትዮጵያ ወደብ ስም ለኦሮሚያ ሪፐብሊክ ግንባታ የሚታትረው የኦሮሞ ኃይል የመስፋፋት አጀንዳ ለአማራው ምኑም ነው። ይልቁንስ ለአማራው የህልውና አደጋ ሆኖ የባጀው ይህ ፋሽስት ኃይል አደጋ የሆነባቸው ሁሉ አጋሮቻችን ናቸው። በጋራ ስርዐቱን ትቢያ ለማልበስ የትኛውንም አጋጣሚ እድል እናደርጋለን‼️

እንደ አማራ በዚህ የደቡብ ምስራቅ ቀጠና የሚመጣ ውጥረት በቀዳሚነት የአካባቢው ተስፋፊ የኦሮሞ ልሒቃን እየጋገሩት ያለ ፥ ሲላቸው የኩሽ ሕብረት ፥ ሲላቸው የኦሮሚያ ሪፐብሊክ በሚል የጀመሩት አጀንዳ መሆኑን መረዳት ይገባል።

የሰሜን ኢትዮጵያ ክልሎችን በማውደም የቀሩት ላይ ነፃ ቁጥጥር እናደርጋለን ብለው የተነሱ "የቀይ ባህር ኢሬቻ ናፋቂዎች" የኢትዮጵያውያንም የአፍሪካ ቀንድም ስጋት መሆናቸው ሊታወቅ ይገባል።

በኢትዮጵያ ስም እና በአገራዊ ጥቅም ሽፋን ከዚህ ጠላት ጎን አንሰለፍም ‼

08/01/2024

ጎንደር

ጎንደር ላይ ቢሊዮን በጀት መድበው፣ በሺዎች የሚቆጠር ሚኒሻ አሠልጥነው፣ በርካታ ደህንነት አሠማርተው፣ ይሄን ያህል ታጣቂ እጅ አሠጠነ ብለው ወንጀለኛ እና ሚሊሻ ሰብስበው ፕሮፖጋንዳ ቢሠሩም፣ አብዮታዊ ቄስ የሀይማኖት አባት ባለሃብት አሠማርተው ግንባር ቢልኩም፣ በአጠቃላይ ጎንደርን ከሌላው ለመነጠል የዕውቀት ጣሪያቸውን ቢጠቀሙም ፋኖ በድንገተኛ ኦፕሬሽን የደከሙበትን አፈር ከድሜ በማስበላት በአንዴ ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ ድልን ይቀዳጅባቸዋል።

ጠላት ብልፅግና እና ዩኒፈርም ለባሽ ካድሬው ዛሬ ጎንደር ጎሃ ሆቴል በታጎረበት ምን ብናደርግ ይሻላል ብሎ ሲያነሳ ሲጥል ቢውልም ሀሳባቸው ሳይሰበሰበ በመቅረቱ ባህርዳር ላለው ዜሮ ሪፖርት በማቅረብ ባህርዳር ያለው የብልፅግና ቡድን ከብልፅግና ጀነራል እና ደህንነት ተብየዎች ጋር አዲስ የኦፕሬሽን ዕቅድ ለማውጣት እየዶለተ ነው። የነገ ሰው ይበለን የፋኖ ደህንነት መረጃውን መንትፎ ያደርሰናል። በብልፅግና እና አምሳያ ደህንነትና ጀነራሎቹ out samart የሚደረግ ትውልድ የለም።

ድል ለፋኖ‼

የዛሬ ዓመት በርግጠኝነት የገናን በዓል አራት ኪሎ እናከብራለን!!"በዚህ የሰዓት ገና ለተመቸው አንጂ እኛ ምቾተኛ አይደለንም ። ብስኩትም አሮበት ደረቅ ሬሽን አሮበት እየታገለ ያለ አለ ሆኖም...
08/01/2024

የዛሬ ዓመት በርግጠኝነት የገናን በዓል አራት ኪሎ እናከብራለን!!

"በዚህ የሰዓት ገና ለተመቸው አንጂ እኛ ምቾተኛ አይደለንም ። ብስኩትም አሮበት ደረቅ ሬሽን አሮበት እየታገለ ያለ አለ ሆኖም በሚያኮራ ሁኔታ በመንፈስ የጠገበ በታላቅ ጀግነት ተላብሶ የሚፋለሙ ጀግኖች የተሞላ ነው ። በእርግጠኝነት የዛሬ ዓመት የገና በዓልን ያለጥርጥር በአራት ኪሎ እናከብራለን ስንል እንደ ተራ የመንግስት ገለባ በፕሮፖጋንዳ የምናወራው ሳይሆን በተጠናቀቀ የተነበበ እልህ አስጨራሽ ስትራቴጂ እና ጀግንነት ነው "

የምሥራቅ አማራ ፋኖ አዛዝ ሻለቃ ዋርካው ምሬ ወዳጆ።

08/01/2024

በጎንደር ከተማ አይባ ኪዳነምህረት፣ ፆር ማርያም፣ ሸዋ ዳቦ፣ ማረሚያ ቤቱ እና አንገረብ እንዲሁም በገንፎ ቁጭ እና በህዳሴ አከባቢ በአሁን ሰዓት እልህ አስጨራሽ ግብግብ እየተካሄደ መሆኑን በስፍራው የሚገኙ ምንጮች አረጋግጠዋል።

08/01/2024

ከሸዋ ጠቅላይ ግዛት የፋኖ የዕዝ አመሰራረትን በተመከለተ የተሰጠ መግለጫ
*****************************************************

1. በሸዋ ጠቅላይ ግዛት ለሚንቀሳቀሱ ማናቸውም የፋኖ አደረጃጀትና ጥሪ ማድረግና ምላተ ጉባኤውን ባለበት የድርጅት እና የዕዝ ምስረታውን መፈፀም እንደሚገባ የጋራ አቋም ይዘናል።

2. በድርጅታዊ ፅንስ ሃሳብ መስማማት እና በመሪ ድርጅት ኮማንድ ስር በጋራ መስራትን አስፈላጊነት መተማመን ችለናል።

3. የትግሉ ደጋፊ የሆኑትን የዲያስፖራ የሙህራን ሚና በመለየት የጋራ አቋም መያዝና የሚኖራቸውን ቀጣይ ሚና ይፋ ማድረግ እንደሚገባ ከስምምነት ላይ ተደርሷል። ድርጅታዊ መርህን ተከትሎ መስራት እንደሚገባ የጋራ አቅጣጫ አስቀምጠናል።

4. የዕዙ መስረታ እውን እስኪሆን ድርጅቶቹ በጋራ የሚመሩት አስተዳድራዊ እና ወታደራዊ የጋራ ግብረሃይል ማቋቋምን አሁናዊ እውነት በቂ ግምገማ አካሂደው የትግባራ ሂደት ተጀምሯል። ስለዚህም ከዛሬ ታህሳስ 25/2016 ዓ/ም አንስቶ ሁለቱም ድርጅቶች በትብብር የሚሰሩ መሆኑን በጋራ በፈረሙት ቃለ ጉባኤ አፅድቀዋል። በሸዋ ጠቅላይ ግዛት ከፍተኛ ተጋድሎ ለፈፀሙት እና አሁንም በመፈፀም ለሚገኙ አደረጃጀቶች ይህንን የአንድነት መንገድ በማቀላጠፍ ጥራት ያለው የትግል መስመር በመፍጠር ለአማራ ህዝብ ሁለንተናዊ ጥያቄዎች ለመመለስ የሚደረገውን በቀና ተመልክተው በአፋጣኝ ድርጅታዊ እና ወንድማዊ ምላሽ በመስጠት በጋራ እንድንሰራ ጥሪ እናቀርባለን። በዚህ አጋጣሚ በሌሎች ጠቅላይ ግዛት ለሚንቀሳቀሱ የፋኖ አደረጃጀቶችም በተመሳሳይ በአንድ ዕዝ ስር በመግባት ድርጅቶቹ በሚያቀርቡት ሰነድ እና የተለያዩ ተደራሽነቶችን ባማከለ መልኩ ለመላው የአማራ ህዝብ ታማኝነት ያለው የሚጠቅም ድርጅት መስራት ላይ ውሳኔ አሳልፈናል።

በአጠቃላይ በጋራ ዕዝ መመስረትና እና ባንድ ላይ ለመስራት ውሳኔ ላይ ደርሰናል ክብር ለተሰው ፋኖዎች ድል ለአማራ ህዝብ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት።

ታህሳስ 25/2016 ዓ/ም
ሸዋ
አዲስአበባ

ማሳሰቢያ:- ይህ ዕዝ ለመመስረት የመጨረሻው ምዕራፍ ሲሆን በአንድ ዕዝ ሁሉም የሸዋ ፋኖዎች እንዲጠቃለሉ የቀረበ መግለጫ ነው።

ለወደፊት ሁሉም አደረጃጀቶች ወደ አንድ ዕዝ ተስማምተው በመጡ ጊዜ የአመራር አደረጃጀቶችን ይፋ የሚደረግ ይሆናል።

ይህንን የአንድነት ጥሪ በመላው ሸዋ ያለ የፋኖ አደረጃጀት ሁሉን የሚመለከት በመሆኑ በትላንትናው ዕለት በተቋቋመው ዕዝ ስር እንድትካተቱ ጥሪ ቀርቧል።

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ghion-Daily posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Videos
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share