Neima Awole

Neima Awole Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Neima Awole, Publisher, .

30/08/2021
15/06/2021

ሾተላይ (የጽንስ መጨንገፍ)

በተለምዶ ሾተላይ በእንግሊዘኛው Rh-Incompatablitiy” በሚባለው ችግር ብዙ ሰዎች ወልደው መሳም ፈልገው ሳይችሉ መቅረታቸውን፣ በዚሁ ምክንያት አያሌ ቤተሰብ እንደተበተነ ሁላችንም የምናውቀው እውነታ ነው፡፡
ሾተላይ መፍትሄው ቀላል ሆኖ ሳለ በየአካባቢያችን የፈጠረው ቀውስ ቀላል አይደለም፡፡
የመጀመሪያው መፍትሄ ስለችግሩ ተዓማኒ እውቀት ማግኘት ነውና ይህንን መረጃ ለተከታዮቻችን እናደርሳለን፡፡

ሾተላይ ምንድን ነው?

ሾተላይ በመባል የሚታወቀው ክስተት ብዙ ጊዜ አንዲት እናት ከመጀመሪያ እርግዝናዋ በኃላ በተደጋጋሚ የሚከሰት የጽንሱ መጥፋት ነው።

ይህ ለምን ይሆናል?የሰዎች ደም በአራት መደብ ይከፈላል(A, B, AB, O) እነዚህ ደግሞ እያንዳንዳቸው በሁለት አበይት መደብ ይከፈላሉ፡ አር ኤች ፖዘቲቭ(Rh +) እና አር ኤች ኔጋቲቭ(Rh-)። ለምሳሌ፦ የአንድ ሰው የደም ዓይነት A+ ወይም A- ሊሆን ይችላል።
የሰው ማንነቱ ከእናቱና ከአባቱ በሚወስደው የዘር-መል ይወሰናል። የደም ዓይነትም በዚሁ መልክ እንወስዳለን።
ከአር ኤች ፖዘቲቭ(Rh +) አባት እና ከአር ኤች ኔጋቲቭ(Rh-) እናት የሚፈጠር ጽንስ አር ኤች ፖዘቲቭ(Rh +) የመሆን እድሉ የሰፋ ነው።
ሾተላይ የሚከሰተው አንዲት ሴት የደም ዓይነቷ አር ኤች ኔጋቲቭ (Rh-) ሆኖ ከዚህ በፊት አር ኤች ፖዘቲቭ( Rh +) የሆነ ደም ወደ ሰውነቷ ሲገባ ደሟ ውስጥ አር ኤች ፖዘቲቭ(Rh +) የሆኑ የደም ህዋሶችን የሚያጠፋ ንጥረ-ነገር በደሟ ውስጥ ይመረታል።

ይህ ንጥረ-ነገር አንዴ ከተመረተ በደሟ ውስጥ እስከ ህይወቷ ፍጻሜ ድረስ ይኖራል።

በመሆኑም በማህጸንዋ ውስጥ የያዘችው ጽንስ የደም ዓይነቱ አር ኤች ፖዘቲቭ ከሆነ የተመረተው ንጥረ-ነገር ጽንሱን እንደ ባእድ አካል ስለሚቆጥረው ያጠቃዋል።

በዚህም ምክንያት በተደጋጋሚ የምትይዘው ጽንስ የደም ዓይነቱ አር ኤች ፖዘቲቭ ከሆነ አስፈላጊውን ህክምና ካልተደረገላት ይሞትባታል።
የደም ዓይነቱ አር ኤች ኔጋቲቭ (Rh-) ከሆነ ግን በጤና ይወለዳል። ይህ እንዲሆን ግን የአባትየው የደም ዓይንት አር ኤች ኔጋቲቭ (Rh-) መሆን አለበት?
ሕክምናው1. የደም ዓይነቷ አር ኤች ኔጋቲቭ (Rh-) የሆነች እናት ሕክምናዋ በሆስፒታል ውስጥ መሆን አለበት።2. በደሟ ውስት ያለውን የንጥረ-ነገር መጠን መለካትና የጽነሷን የጉዳት መጠን በማየት ብዙ ሳይጎዳ እንዲወለድ ማድረግ።3. በሀገራችን በቅርቡ የተጀመረው ጽንሱ በማህጸን ውስጥ እያለ ደም በመለገስ እንዲያድግና እንዲወለድ ማስቻል።እንዴት እንከላከለው?1. ማንኛዋም ሴት ከማርገዟ ወይም ማንኛውንም ደም ከመውሰዷ በፊት የደም ዓይነቷን ማወቅ አለባት።2. የወንድ አጋሯን የደም ዓይነት ማወቅ አለባት።3. እርግዝና አር ኤች ፖዘቲቭ( Rh +) ከሆነ አጋሯ ከተፈጠረ መጀመሪያ በሚደረግላት ምርመራ (indirect coomb’s test) ንጥረ-ነገሩ አለመመረቱን ያረጋግጣል። እዳይመረት የሚከላከል መድኃኒት (Anti-D) 7ተኛ ወሯ ላይ ይሰጣታል። ከወለደች በኃላ የልጇ የደም ዓይነት አር ኤች ፖዘቲቭ( Rh +) ከሆነ በድጋሚ መድኃኒቱ ይሰጣታል።4. እርግዝናው ከማህጸን ውጭ ወይም በውርጃ ቢያበቃም መከላከያውን መድኃኒት መውሰድ አለባት።..

07/06/2020

#ራስን መሆን

“አስመሳይ ማንነት ይዤ ለዚያ ማንነት ከምወደድ፣ እውነተኛ ማንነቴን ኖሬ ለዚያ ማንነት #ብጠላ ይሻለኛል”

ራስን መሆን ማለት፣ ማንነትን ተቀብሎ፣ ሳይደባብቁና ሌላውን ሰው ለመሆን ሳይሞክሩ #በነጻነት መኖር ማለት ነው፡፡ ራስን የመሆን ጉልበት የሚመነጨው ማንነቴን የሰጠኝ ፈጣሪ እንደሆነና ይህም ማንነቴ ትክክለኛ እንደሆነ ከማመን ነው፡፡

አንዳንድ ሰዎች ራሳቸውን ስለማይቀበሉ ራሳቸውን ሆነው መኖር አይችሉም፡፡ ራሱን መቀበል ያስቸገረው ሰው ላይ የሚታየው የመጀመሪያው ምልክት ራስን አለመሆን ነው፤ የማይቀበሉትን ማንነታቸውን ለውጠው ለመታየት ሲሞክሩ ራሳቸውን ያገኙታል፡፡ ማንነትታችንን በመቀበል ስንደላደል ግን ቀና ብለን መኖር እንጀምራለን፡፡አንተ' አንተ ነህ በቃ ሌላውን መሆን አትችልም ባለህ በተሰጠህ ተፈጥሮ ዛሬህን አሳምር።ሌላውን ለመሆን ስትሞክር መሆን የምትችለውን ሳትሆን ትቀራለህ ያ ማለት ከሁለት ያጣ ትሆናለህ ማለት።

ራስህን ለመሆን መውሰድ የምትችላቸው እርምጃዎች፡-

1. መለወጥ ወይም ማሻሻል የምችለውን መለወጥና ማሻሻል፡፡

በማንነቴ ላይ የማልቀበለውን ነገር ለማሻሻል ጤናማ መንገዶችን መሞከሩ ክፋት አይኖረውም፤ ከተሳካልኝ፡፡ ቁም ነገሩ፣ አሻሻልኩትም አላሻሻልኩት ራሴን ወደ መቀበል መምጣቴና ጤናማ የሕብረተሰቡ አካል ሆኜ መኖሬ ነው፡፡

2. መለወጥ ወይም ማሻሻል የማልችለውን መቀበል፡፡

መልኬን፣ አወላለዴንና የመሳሰሉትን አሁን የሆንኩትን ማንነት ለመቀየር አስቸጋሪ እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡ ምርጫዬ አንድ ነው፣ ራሴን ተቀብዬ፣ በጥሩ ልብ በደስታና በሰላም መኖር፡፡

3. ስለ ሁሉም ነገር አዎንታዊ አመለካከት ማዳበር፡፡

አዎንታዊነት መገለጫው ብዙ ነው፡፡ ከመንፈሳዊ እምነትህ አንጻር ስለሁሉም ነገር አምላክን ማመስገን፣ ከሁኔታዎችህ አንጻር ደግሞ ትክክል አይደሉም በምትላቸው ነገሮች እንኳን ሳይቀር ደስተኛ መሆን፣ ሰዎችን ማመስገንና የመሳሰሉት ሁኔታዎች ይነካል

በቅንነት ሼር ያድርጉ

ማሻሻል ወይም ጥፋት ካለ እናንተው አስተምሩን። ከናንተው ለናንተው ነው የምናቀርበው።

ይህ ከደራሲያን አለም ፔጅ ነው

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Neima Awole posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share