GECH MEDIA

GECH MEDIA GECH ጌች ሚዲያ ወቅታዊ ዜናዎችን፣ ተዓማኒነት ያላቸው መረጃዎች በሳል የፖለቲካ ተንታኞች አተያዮች ከኢትዮጵያና ከአለም ዙሪያ በፍጥነት ይቀርቡበታል

የ "ጉማ አዋርድ" አዘጋጅ ዮናስ ብርሃነ ትናንት ምሽት በስካይ ላይት ሆቴል ከተካሄደው የሽልማት ስነ ስርአት በኋላ ለእስር ተዳርጓል። በስፍራው ከነበሩ ሰዎች በደረሰኝ መረጃ መሰረት ዮናስን ...
10/06/2023

የ "ጉማ አዋርድ" አዘጋጅ ዮናስ ብርሃነ ትናንት ምሽት በስካይ ላይት ሆቴል ከተካሄደው የሽልማት ስነ ስርአት በኋላ ለእስር ተዳርጓል።

በስፍራው ከነበሩ ሰዎች በደረሰኝ መረጃ መሰረት ዮናስን ሲቪል የለበሱ ደህንነቶች ከምሽቱ 5 ሰአት ገደማ ከነባለቤቱ አስረው ወስደዋቸዋል። ባለቤቱ ከጥቂት ቆይታ በኋላ ብትፈታም ዮናስ አንበሳ ጋራዥ አካባቢ በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ እንደሚገኝ ታውቋል።

በትናንትናው ፕሮግራም ላይ "ልጅ ማኛ" በሚል የምትታወቀው ቲክቶከር ባደረገችው ሜካፕ ምክንያት "ልጅቷን አምጡ" በሚል አዘጋጆቹ ተጠይቀው እንደነበር እና እስሩም ከእሱ ጋር ሊያያዝ እንደሚችል በስፍራው የነበሩ ግለሰቦች እና ሌሎች ምንጮች አረጋግጠውልኛል።

የኔ ጥያቄ:

- ሜካፕ ተቀብቶም ይሁን ፒካፕ ተኮናትሮ ሀሳብን ሰላማዊ በሆነ መንገድ መግለፅ በቃ ተከልክሏል?

- የፕሮግራሙ አዘጋጅ የተለያየ ልብስ ለብሶ እና ሜካፕ ተቀብቶ ለሚመጣው የሀገር ህዝብ ሁሉ ሀላፊነት አለበት?

ለህግ ማቅረብ ከተፈለገ አንዱ ማስረጃ ይሄ ነው!ያውም የፀጥታ አካላትን የደንብ ልብስ በለበሱ ሰዎች የሚፈፀም እንዲህ አይነት የጭካኔ ድርጊት ሊቆም ይገባል። #አሸባሪ መንግስት እንጂ ፋኖ አይ...
05/06/2023

ለህግ ማቅረብ ከተፈለገ አንዱ ማስረጃ ይሄ ነው!

ያውም የፀጥታ አካላትን የደንብ ልብስ በለበሱ ሰዎች የሚፈፀም እንዲህ አይነት የጭካኔ ድርጊት ሊቆም ይገባል።
#አሸባሪ መንግስት እንጂ ፋኖ አይደለም

 !አርበኛ ዘመነ ካሴ አራት አይና በሆኑ ፋኖዎች እጀባ እየተደረገለት ከሰባታሚት ማረሚያ ቤት ወጥቷል። የፋኖዎቹ ጥንቃቄ የሚገርም ነበር።እንቅስቃሴያቸውና ቅኝታቸው የሰለጠኑ ሪፐብሊካን ጋርድ ...
04/06/2023

!

አርበኛ ዘመነ ካሴ አራት አይና በሆኑ ፋኖዎች እጀባ እየተደረገለት ከሰባታሚት ማረሚያ ቤት ወጥቷል። የፋኖዎቹ ጥንቃቄ የሚገርም ነበር።

እንቅስቃሴያቸውና ቅኝታቸው የሰለጠኑ ሪፐብሊካን ጋርድ ይመስሉ ነበር።

ግንቦት 27 ቀን 2015 ዓ.ም.
GECH MEDIA

 #መገደል   #መገደል  አሳምነው ፅጌ በህይወት መያዝ ሳይሆን መገደል ነው ያለብት ብሎ ትዕዛዝ የሰጠው አብይ አህመድ እስክንድር ነጋ ባለበት ይገደል የሚል ትዕዛዝ ማስተላለፉ የሚደንቅ አይደ...
04/06/2023

#መገደል #መገደል
አሳምነው ፅጌ በህይወት መያዝ ሳይሆን መገደል ነው ያለብት ብሎ ትዕዛዝ የሰጠው አብይ አህመድ እስክንድር ነጋ ባለበት ይገደል የሚል ትዕዛዝ ማስተላለፉ የሚደንቅ አይደለም:: እስክንድር ነጋ ወይም ሌሎች ቢሰው በዋናነት ተጠያቂው የአማራ ወጣት እንጂ የጠላት ወታደር ወይም ዘረኛው አብይ አህመድ አይደለም:: እነሱማ አንዴ ጠላት ናቸው እኮ::

ማንኛውም ለህዝብ ትግል ሲል የተደራጀ ሀይል የጠላቱን የመንግስትን ሪሶርስ መጠቀም መጀመር አለበት:: የመንግስት ንብረቶች:- መኪናዎች:- ገንዘብ:- መድሃኒቶች እንዲሁም መሳሪያዎችን መጠቀም ትክክለኛው ፍትሃዊ መንገድ ነው::
አማራ የነቁ ልጆቹን እያስበላ ትግሉን ከዐ መጀመር ሊበቃው ይገባል።

አርቲስት ሜላት ዳዊት ከእስር ተፈታለች!!Melat Dawit Yazachew እንኳን ለቤትሽ አበቃሽ!
03/06/2023

አርቲስት ሜላት ዳዊት ከእስር ተፈታለች!!

Melat Dawit Yazachew እንኳን ለቤትሽ አበቃሽ!

 #ሰበር‼️ መልካም ዜና..🔥🔥አርበኛ ዘመነ ካሴን ፍርድ ቤቱ ነጻ ሰው ነህ ብሎታል።GEGECH MEDIAEGECH MEDIA
02/06/2023

#ሰበር‼️ መልካም ዜና..🔥🔥

አርበኛ ዘመነ ካሴን ፍርድ ቤቱ ነጻ ሰው ነህ ብሎታል።
GEGECH MEDIAEGECH MEDIA

በሥላሴ አንድነት ገዳም ከ200 በላይ በሚሆኑ መናኝ እናቶች ባሉበት ግቢ ላይ የተፈፀመውን የጦር ወንጀል የአማራ ህዝባዊ ግንባር በጥብቅ እንደሚያወግዝ አስታወቀ።የአማራ ህዝባዊ ግንባር በወቅታ...
31/05/2023

በሥላሴ አንድነት ገዳም ከ200 በላይ በሚሆኑ መናኝ እናቶች ባሉበት ግቢ ላይ የተፈፀመውን የጦር ወንጀል የአማራ ህዝባዊ ግንባር በጥብቅ እንደሚያወግዝ አስታወቀ።

የአማራ ህዝባዊ ግንባር በወቅታዊ ጉዳይ የሚከተለውን መግለጫ አውጥቷል:_

በሥላሴ አንድነት ገዳም ከ200 በላይ በሚሆኑ መናኝ እናቶች በሚገኙበት ግቢ ላይ በዛሬው ዕለት የተፈፀመውን የጦር ወንጀል የአማራ ህዝባዊ ግንባር በጥብቅ ያወግዛል።

ደብረኤልያስ ወረዳ በሚገኘው የሥላሴ አንድነት ገዳም ላይ 3 ሞርተሮችን ጨምሮ በተለያዩ ከባድና የቡድን መሳሪያዎች ጥቃት እየፈፀመ የሚገኘው የፌደራል መንግስቱ መከላከያ ኃይል፤ በገዳሙ ግቢ ውስጥ ከ200 በላይ መናኝ እናቶች የሚገኙበትን ግቢ በሞርተር በመምታት ለጊዜው ቁጥራቸው ያልታወቀ መነኮሳት አልቀዋል፤ሌሎችም ከፍተኛ ጉዳት አስተናግደዋል።

በዚህም ገዥው የኦህዴድ ብልፅግና ስርዓት ከባድ የጦር ወንጀል ፈፅሟል።

ይህ የጦር ወንጀል በገዳሙ መናኝ እናቶች ላይ የተፈፀመው በአካባቢው የመደበኛ ስልክ ጥሪም ሆነ የኢንተርኔት አገልግሎት በማቋረጥ ነው።

ይህ ድርጊት በአገር ውስጥም ሆነ በዓለም አቀፍ ህጎች ፍፁም የተከለከለ በመሆኑ፣ የዓለም አቀፍ ወንጀለኞች ፍ/ቤት(ICC) ጨምሮ የዓለም አቀፍ ማህበር ጉዳዩን በአጣዳፊ እንዲመለከተው እንጠይቃለን።

በጎጃም ደብረ ኤልያስ ጭፍጨፋ ሲፈፅም የቆየው የኦህዴድ ብልጽግና መከላከያ ሠራዊት ዛሬ ሸበል በረንታ፣ ዲማ ጊዮርጊስ፣ የትኖራ ፣ወጀል ዓባይ ፣በመርጦ ለማሪያም፣ደብረዎርቅ እና እሁዲት-ኢናባራ አየሁ መከላከያ እንዲገባ ወስኖ ተጨማሪ የጦር ወንጀል እንዲፈፀም እያደረገ ነው።

በተመሳሳይ በሰሜን ሸዋ እንሳሮ፣ራሳ፣መርሃ ቤቴ እና ይፋት ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሠራዊት በማሰማራት በአማራ ህዝብ ላይ ከፍተኛ የጦር ወንጀል በኦህዴድ/ብልፅግና የሚመራው ገዢ ስርዓት እየፈፀመ ነው።

መላው የአማራ ህዝብ በሠራዊቱ እየተፈፀመበት ያለውን የጦር ወንጀል በጋራ በመሆን ሊመክት ይገባል።

የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ፣ሚዲያዎች፣የሲቪክ ማህበራት፣የሰብዓዊ መብት ተቋማት እና ሌሎችን የንፁሃን ጭፍጨፋን በአፅኖት ሊመለከቱት ይገባል።

መንግስት ‹ በደብረ ኤሊያስ በቅድስት ሥላሴ ገዳም አካባቢ የጀመረውን በከባድ መሣሪያ የታገዘ መጠነ ሰፊ ጥቃት በአስቸኳይ እንዲያቋም › እናት ፓርቲ ጠየቀ፡፡ፓርቲው በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ...
31/05/2023

መንግስት ‹ በደብረ ኤሊያስ በቅድስት ሥላሴ ገዳም አካባቢ የጀመረውን በከባድ መሣሪያ የታገዘ መጠነ ሰፊ ጥቃት በአስቸኳይ እንዲያቋም › እናት ፓርቲ ጠየቀ፡፡

ፓርቲው በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ግንቦት 23 ቀን 2015 ዓ.ም ጋዜጣዊ መግለጫ አውጥቷል፡፡
በመግለጫውም ‹ መንግሥት በደብረ ኤሊያስ በቅድስት ሥላሴ ገዳም አካባቢ የጀመረውን በከባድ መሣሪያ የታገዘ መጠነ ሰፊ ጥቃት በአስቸኳይ በማቆም ለተፈጸመው ግድያና ለወደሙ ነዋያተ ቅድሳት ተጠያቂነት እንዲኖር፤ ስለጥቃቱ ሁኔታ ለእምነቱ ተከታዮች ማብራሪያ እንዲሰጥ እንዲሁም የተስተዋሉ ችግሮች ካሉም በሰላማዊ መንገድ ብቻ እንዲፈቱ › አሳስቧል።

መግለጫው ከግንቦት 18 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ጎጃም ደብረ ኤልያስ በሚገኘዉ የቅድስት ሥላሴ ገዳም አካባቢ በከባድ መሣሪያ የተደገፈ ጥቃት እየተካሄደ እንዳለና በዚህም ጥቃት በገዳሙ የሚገኙ መናንያን መገደላቸውን መረጃ ደርሶኛል ብሏል፡፡

በተመሳሳይ ወቅትም በአርሲ ሀገረ ስብከት በጢዮ ወረዳ በጨፌ ሚሶማ ቀበሌ ገበሬ ማኀበር ከአሰላ ከተማ በቅርብ ርቀት በሚገኘው በዴራ አማኑኤል አጥቢያ ቤተክርስቲያን ግንቦት 20 ቀን 2015 ዓ.ም ምሽት ላይ የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ካህናትና ምዕመናን፤ በታጣቂዎች በተሰነዘረ ጥቃት ዘግናኝ ጭፍጨፋና ግድያ እንደተፈፀመባቸው ገልጿል።

መግለጫው በሌላ በኩል የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በ"ሸገር ከተማ" ስም እያከናወነ ያለዉን አፍራሽ ተግባር በአስቸኳይ እንዲያቆም ጠይቋል፡፡

መግለጫው በጎሰኝነት ላይ የተመሰረተ ነው ያለው ሀገረ መንግስት አወቃቀር አካል የሆነው አዲስ አበባ ባለቤት አልባ ሁኗል ያለ ሲሆን ዙሪያውን በማጠር አዲስ አበባን እርባና ቢስ እናደርጋታለን የሚል የተጠና ፕሮጀክት ተግባራዊ መደረግ ከጀመረ መስበቱን ገልጿል፡፡

መግለጫው አክሎም መንግስት "የሸገር ከተማ" ብሎ በሰየመው አካባቢ የሚኖሩ የተለያየ ቋንቋ ተናጋሪ ኢትዮጵያዉያንን የማፅዳት ዘመቻ ሃይ ባይ ሳይኖረው በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን ቤት አልባና ተመጽዋች አድርጓቸዋል ሲል ወንጅሏል።

መንግሥት ሕዝብን ፍትሐዊ በሆነ መንገድ ከመምራትና ከማስተዳደር ይልቅ በሕዝብ መከራና ሰቆቃ መሳለቅን መገለጫው አድርጎ ለመቀጠሉ ትልቅ ማሳያ እንደሆነም ገልጿል።

የኢትዮጵያ ሕዝብ መንደርና ከተማ መስርቶ በሚኖርበት አካባቢ ሁሉ ለሥጋዊ ፍላጎቱ መሟላት ከሚያደርገዉ ሩጫ አስቀድሞ መንፈሳዊ አገልግሎቱን የሚያገኝበትና የሚያከናዉንበት አብያተ እምነት ግንባታ ግንባር ቀደም ሥራዉ ነዉ ያለው መግለጫው አዲስ አበባን እርባና ቢስ ለማድረግ የታለመው የሸገር ከተማ ግንባታም እስካሁን 19 መስጂዶችን እንዲፈርሱ አድርጓል ብሏል፡፡

በዚህ ምክንያት ሕዝበ ሙስሊሙ ተቃዉሞዉን በሰላማዊ መንገድ ለመግለጽ በወጣበት የጁምዓ ሶላት ላይ የመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች በወሰዱት የኃይል እርምጃ ብዙዎች ለአካል ጉዳት መዳረጋቸውንና የሦስት ሰዎች ሕይወታቸዉ ማለፉ በመግለጫው ተነስቷል፡፡

ቤተክርስቲያኔ እንዲ ሆና በዚ መጠን ተደፍራ ከማየት በላይ ህመም የለም💔💔 አሁንም ካህናት ምእመናን እየተገደሉ መነኮሳት እየተደፈሩ ነዋየ ቅዱሳት እየተቃጠሉ ነው እባካቹ ሁላችንም የምንችለውን...
30/05/2023

ቤተክርስቲያኔ እንዲ ሆና በዚ መጠን ተደፍራ ከማየት በላይ ህመም የለም💔💔 አሁንም ካህናት ምእመናን እየተገደሉ መነኮሳት እየተደፈሩ ነዋየ ቅዱሳት እየተቃጠሉ ነው እባካቹ ሁላችንም የምንችለውን እናርግ🙏

ፍትህ ለፀጋ 🙏ምንድነው የተፈጠረው?ስለ ፀጋ እህቷንና ባለቤቷን አውርቻቸው አንጀት በሚበላ ሁኔታ እንዲህ አሉኝ:-  "ወሬ ስታመላልስ የነበረችው የስራ ባልደረባዋ ህፃን ልጅ አለኝ በሚል ሰበብ...
30/05/2023

ፍትህ ለፀጋ 🙏

ምንድነው የተፈጠረው?

ስለ ፀጋ እህቷንና ባለቤቷን አውርቻቸው አንጀት በሚበላ ሁኔታ እንዲህ አሉኝ:-

"ወሬ ስታመላልስ የነበረችው የስራ ባልደረባዋ ህፃን ልጅ አለኝ በሚል ሰበብ ትላንት በዋስ ተፈታ ቤቷ ገብታለች"

የ23ዓመቷ ፀጋ በላቸው በስራ ምክንያት ከወልቂጤ ወደ ሀዋሳ ሄዳ ተከራይታ ዳሽን ባንክ ስራ ከጀመረች ገና አንድ አመቷ ነው!

በስራ ባልደረባዋ አማካኝነት ስልኳን የተቀበለው ይህ ሰው በተደጋጋሚ ያስቸግራት እንደነበርና አግቷት እንደጠፋ መረጃውን መጀመሪያ የሰሙትም ከሷ ነው!

ፀጋ ከመጥፋቷ በፊት ለማናጀሯ "ምንም አይነት አደጋ ህይወቴ ላይ ቢደርስ በሷና በሱ ምክንያት ነው!እወቁልኝ" ብላም ተናግራለች!!

ከአንድ ወር በኋላ ስለሚደረገው ሰርጓ እየተዘጋጁ የነበሩት አባት ታመው አዲስ አበባ ሆስፒታል የሚገኙ ሲሆን መጥፋቷንም እስካሁን አላወቁም!!

አጋቹ ጉልበተኛ ከወር በኋላ ሊያገባት የተዘጋጀውን ሚስቱን ቀምቶ በተደጋጋሚ ባል ጋር እየደወለ ሲያስፈራራውና እገልሀለው ብሎ እየዛተበት ነው!ቤተሰብ ጋርም ለሽምግልና ተዘጋጁ በግድ አገባታለሁ ብሏቸዋል!!

የቤት እቃ እያሟሉ፣ስለጋብቻ የቤተክርስቲያን ትምህርት እየተማረች የነበረችው ፀጋ ሀገረሰላም ይዟት ሄዶ ለማምለጥ ስትሞክር እንደወደቀች ጭምር የአይን እማኞች ተናግረዋል!!

ከዛ በኋላ ግን መረጃ ቀድሞ እየደረሰው ከመድረሳቸው በፊት እየሸሸ ሲሆን

ሁላችንም ፀጋን እንደ እህታችን ቆጥረን ያለችበትን ልንጠቁምና ስለፍትህ ልንጮህ ይገባል

እባካችሁን ሼር በማድረግ የት እንዳሉ በቶሎ እንድረስበት🙏

Via Henok Fekadu

በፌስቡክ የሀሰት ዘመቻ ነው ንፁሃንን የሚያስሩት!ተሸ የታሰረው ትናንት ነው። ነገር ግን ከመታሰሩ በፊት በማህበራዊ ሚዲያ "በአስቸኳይ ይታሰር" ተብሎ ተዘምቶበታል። "የደህንነት የጋራ ግብረሃ...
30/05/2023

በፌስቡክ የሀሰት ዘመቻ ነው ንፁሃንን የሚያስሩት!

ተሸ የታሰረው ትናንት ነው። ነገር ግን ከመታሰሩ በፊት በማህበራዊ ሚዲያ "በአስቸኳይ ይታሰር" ተብሎ ተዘምቶበታል። "የደህንነት የጋራ ግብረሃይል" ወዘተ የሚባለው ስብስብ በማህበራዊ ሚዲያ ነው የሚያስረው። ኢትዮጵያ ከዚህ ዝቅጠት ደርሳለች።

አሁን የትህነግና ኦነግ ተራ ፌስቡከኛ "በአስቸኳይ ይታሰር ሳልልብህ" እያለ ሰውን ገንዘብ መቀበል የሚችልበት እድል በመንግስት ተመቻችቶለታል።

ይህ ሰው በጦርነቱ ወቅት ከሰራዊቱ ጋር ለአገሩ ዘምቷል። የአገሩን ባህል ያስተዋውቃል። ያስጎበኛል። ነገር ግን የትህነግና ኦነግ ተራ ፌስቡከኛና የሀሰት ገፅ በሀሰት የዘመተበት ሁሉ ለደህንነት ግብረ ኃይል እንደ ተጨባጭ ማስረጃ ነው።
Viva Getachew Shiferaw

ሜላት ዳዊት 5000ብር ዋስትና አሲዛ እንድትወጣ ፍርድ ቤት ወሰነ!!የአዲስ አበባ ፖሊስ አርቲስት ሜላት ዳዊትን በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ  3ኛ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት አቅርቦ ፍርድ...
30/05/2023

ሜላት ዳዊት 5000ብር ዋስትና አሲዛ እንድትወጣ ፍርድ ቤት ወሰነ!!

የአዲስ አበባ ፖሊስ አርቲስት ሜላት ዳዊትን በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 3ኛ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት አቅርቦ ፍርድ ቤቱ የ14 ቀን ጊዜ እንዲሰጠው ጠይቋል።

የአርቲስት ሜላት ዳዊት ጠበቃ አዲሱ ጌታነህ ሜላት ፈፀመችው የተባለው ድርጊት ወንጀል ካለመሆኑም በተጨማሪ ፖሊስ ተጨማሪ ጊዜ እንዲሰጠው በቂ ምክንያት አላቀረበም ከዚህ በፊት በተሰጠውም ጊዜ የተለየ ስራ አልሰራም በማለት በዋስትና እንድትለቀቅ ፍርድ ቤቱን ጠይቀዋል።
የግራ ቀኙን ክርክር የሰማው ፍርድ አርቲስት ሜላት ዳዊት 5000 ብር አሲዛ እንደትወጣ ትእዛዝ አስተላለፏል!!

🔥 ‼️በብዙ ስራዎቹ የምናውቀው አርቲስት ተሾመ አየለ (ባላገሩ ) ዛሬ በአፋኙ ቡድን መታሰሩን አረጋግጠናል። ተሼ ድሃ ሲከፋው የማይወድ ጀግና ወንድማችን ነው። ዛሬ አማራነቱ አሳስሮታል።   ...
29/05/2023

🔥 ‼️

በብዙ ስራዎቹ የምናውቀው አርቲስት ተሾመ አየለ (ባላገሩ ) ዛሬ በአፋኙ ቡድን መታሰሩን አረጋግጠናል። ተሼ ድሃ ሲከፋው የማይወድ ጀግና ወንድማችን ነው። ዛሬ አማራነቱ አሳስሮታል።
ዘማቾች በአሸባሪነት ተፈርጀው እየተሳደዱ ይገኛል ።

በውድቅት ሌሊት ከቤታቸው የሚታፈኑ አማራዎች ወደ ሕጋዊ ፖሊስ ጣቢያዎች ሳይገቡ፣ ለሕግ ሳይቀርቡ፣ ከጨለማ የማሰቃያ ቤቶች ውስጥ ተዘግቶባቸውና ለቤተሰብ አድራሻቸውን መናገር ተከልክለው ለወራት...
28/05/2023

በውድቅት ሌሊት ከቤታቸው የሚታፈኑ አማራዎች ወደ ሕጋዊ ፖሊስ ጣቢያዎች ሳይገቡ፣ ለሕግ ሳይቀርቡ፣ ከጨለማ የማሰቃያ ቤቶች ውስጥ ተዘግቶባቸውና ለቤተሰብ አድራሻቸውን መናገር ተከልክለው ለወራት ሲሰወሩ፣
እንዲሁም ጥፍራቸውና ጥርሳቸው በጉጠት እየተነቀለ፣ ገላቸው በዱላ እየተተለተለ ሲመረመሩ.... መክረማቸው ወደ ሚዲያ ወጥቶ እያነጋገረ ቢሆንም ኢሰመኮ ግን ስቃያቸውን ሰምቶ ሊደርስላቸው ቀርቶ የተለመደውን የውግዘት መግለጫ እንኳን ሊጽፍላቸው አልደፈረም።

ኢሰመኮ ሆይ የዛሬ ዝምታህ የነገ ወንጀልህ መሆኑን እንዳትዘነጋው።

Share
Daniel Bekele
Human Rights Commission
Human Rights Watch

ኤርዶኻን ምርጫውን አሸንፈዋል!ረጀብ ጣይብ ኤርዶኻን በቱርክ ለሁለተኛ ዙር የተካሄደውን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በማሸነፍ በድጋሚ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት መሆናቸውን አረጋግጠዋል። ከ20 ዓመታት በላይ ...
28/05/2023

ኤርዶኻን ምርጫውን አሸንፈዋል!

ረጀብ ጣይብ ኤርዶኻን በቱርክ ለሁለተኛ ዙር የተካሄደውን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በማሸነፍ በድጋሚ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

ከ20 ዓመታት በላይ ቱርክን የመሩት ኤርዶኻን በዛሬው ዕለት በተካሄደው ሁለተኛ ዙር ምርጫ ብርቱ ተፎካካሪያቸው የነበሩትን ከማል ኪሊዳሮግሉን በማሸነፍ ነው ሀገሪቱን ለቀጣይ አምስት ዓመታት መምራታቸውን ያረጋገጡት ሲል አልጀዚራ ዘግቧል።

የተለያዩ ሀገራት መሪዎችም ለፕሬዚዳንቱ የእንኳን ደስ አለዎ መልእክት እያስተላለፉ ይገኛሉ ።

‹‹የደረሰብንን ስቃይ ቃላት አይገልጹትም፤ በኤሌክትሪክ ቶርች ተደርገናል፣ ጥፍራችን ተነቅሏል፤ በቀዝቃዛ ውሃ እየተነከርን ተገርፈናል፤ አሁንም በአፍና በአፍንጫው ደም የሚፈሰው ታሳሪ አለ›› ...
28/05/2023

‹‹የደረሰብንን ስቃይ ቃላት አይገልጹትም፤ በኤሌክትሪክ ቶርች ተደርገናል፣ ጥፍራችን ተነቅሏል፤ በቀዝቃዛ ውሃ እየተነከርን ተገርፈናል፤ አሁንም በአፍና በአፍንጫው ደም የሚፈሰው ታሳሪ አለ›› በፌደራል ፖሊስ የሚገኙ እስረኞች

የሰብአዊ መብት ጥሰት መፈፀሙን ኢትዮ 251 ሚዲያ በደሠሰው መረጃ መሠረት አዲስ አበባ ፌድራል ፖሊስ ኮሚሽን በሚገኘው እስር ቤት የኢትዮ 251 ሚዲያ ዘጋቢ ተገኝቶ የደረሰባቸውን ሁሉ ጠይቆ ያጠናቀረው ዘገባ ነው።

ለኢትዮ 251 ሚዲያ አስተያየታቸውን የሰጡት ግፉኣን የሚከተለውን ብለውናል፡፡ እኛም ጥሬ ሃቆቹን እና ዘጋቢው የተመለከተውን ብቻ ወደ እናንተ አቅርበናል።

 ‹‹የደረሰብንን ስቃይ ቃላት አይገልጹትም፡፡ አሁን ስንታሰር ህዝቡ ሊጨነቅ ይችላል፡፡ ለእኛ ግን በማሰቃያ ቦታው የደረሰብንን ስንመለከት ይህ ፖሊስ ጣቢያ የቅንጦት ቤታችን ነው›› የአንደኛው አስተያየት፤

 ሌላኛው አስተያየት ሰጪ ደግሞ፤ ‹‹በደረሰብኝ ድብደባ መተንፈስ ተቸግሬያለሁ›› ሲል ተናግሯል፡፡ ዘጋቢያችን በአካል ተገኝቶም የኢንጂነሩን ስቃይ ተመልክቷል፡፡

 በአይን እንደተመለከትነው አንዷ እህታችን እስካሁን በአፍና በአፍንጫዋ ደም እየፈሰሳት ነው።

 በግርፋት ብዛት ራሳቸውን የሳቱና ምግብ መመገብ የማይችሉ አሉ፡፡ በኤሌክትሪክ ቶርች የተደረገ አለ፤ በቀዝቃዛ ውሃ እየተነከረ የተገረፈም አለ፣ ጥፍሩ የተነቀለም አለ፡፡ ይህን ሁሉ ግርፋት መቋቋም ያልቻሉ ወንድሞቻችን ምግብ መመገብም ሆነ ራሳቸውን መቆጣጠር ተስኗቸው እላያቸው የሚጸዳዱም አሉ፡፡ "የእኛ ስቃይ የማይታያቸው ገራፊዎቻችን ሆን ብለው ህክምና ከልክለውናል"፡፡

 በተጨማሪም፤ ‹‹28ታችን ወደ ፖሊስ ጣቢያ መጣን እንጂ አሁንም በማሰቃያ ቤቱ መከራቸውን እያዩ ያሉ በሺዎች የሚቆጠሩ ወንድሞቻችን አሉ፡፡ እነዚህ ወንድሞቻችን ከአጣዬ፣ ሽዋሮቢት፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ጎጃም፣ ጎንደር እና አዲስ አበባ በግፍ ታፍነው የተወሰዱ ናቸው፡፡

ሲሉ በጋራ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

እነዚህ 28 የአማራ ተወላጆች ከ13 ቀን እስከ 21 ቀን በጨለማ ክፍል ውስጥ እንደነበሩ እና ከዚህ ሁሉ ግፍ እና ስቃይ በኋላ ወደ ፌድራል ፖሊስ ኮሚሽን ወደ ሚገኘው እስር ቤት እንደተዛወሩ ገልጸዋል።

Ethio 251
Mulugeta Anberber

28/05/2023

መከላከያ ሰራዊቱ ለአንድ ብሄር መሆኑን ስላረጋገጣችሁልን እናመሰግናለን !!

"የመከላከያውን ሸክም እናቅል። ሰልፍ እና መፈክር ይቁም"(አቶ ታዬ ደንደአ )
28/05/2023

"የመከላከያውን ሸክም እናቅል። ሰልፍ እና መፈክር ይቁም"
(አቶ ታዬ ደንደአ )

"በህግ ስም የደሀን ቤት እና የእምነት ተቋምን ማፍረስ ልክ አይደለም"*******************************************************(አቶ ታዬ ደንደአ)በዚህ አምስት ...
27/05/2023

"በህግ ስም የደሀን ቤት እና የእምነት ተቋምን ማፍረስ ልክ አይደለም"
*******************************************************
(አቶ ታዬ ደንደአ)
በዚህ አምስት አመታት ውስጥ አ.አ ዚርያ ያለውን የቱለማ ህዝብ መሬት በገበሬ ስም የዘረፈው.ማን እንደሆነ እናውቃለን። በሚልየን ዘርፎ ለሴት ገንዘብ የሚበትነው እና ውስኪ ሲገለብጥ የሚያድረውም ማን እንደሆነ እናውቃለን።

ህገ-ወጥ ግንባታን ማስቆም ጉልበት እና ንብረት ሳይባክን ነበር።መሬት ሲቸበቸብ ፣ቤት ሲሰራ በዝምታ ታልፎ እንዲሁም ውሃ እና መብራት ሰጥቶ የሀገር ሀብት ከፈሰሰ በኋላ በህግ ስም ተከልሎ የደሀን ቤት እና የእምነት ተቋማትን ማፍረስ አግባብ አይደለም።

በአዲስ አበባ እና በደብረ ኤሊያስ የተፈፀሙትን ጥቃቶች በጥብቅ እናወግዛለን!የአማራ ሕዝባዊ ግንባር(አሕግ)/ Amhara Popular Front (APF)(ግንቦት 19 ቀን 2015 ዓ.ም.)በአማ...
27/05/2023

በአዲስ አበባ እና በደብረ ኤሊያስ የተፈፀሙትን ጥቃቶች በጥብቅ እናወግዛለን!

የአማራ ሕዝባዊ ግንባር(አሕግ)/ Amhara Popular Front (APF)

(ግንቦት 19 ቀን 2015 ዓ.ም.)
በአማራ ጥላቻ እና ጥቃት ላይ የበቀለው ዘረኛው ስርዓት ፣ በአማራው ሕዝብ ላይ ላለፉት 30 ዓመታት ሲያደርሰው የኖረው ሁለንተናዊ ጥቃት ወደለየለት የዘር ጭፍጨፋ እና የኃይማኖት ተቋማት ጥቃት ተሸጋግሯል። ለዚህ በወለጋ ካለው ሁኔታ በተጨማሪ፣ ግንቦት 18 እና 19 2015 ዓ.ም በአዲስ አበባ በሙስሊም ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ላይ፣ በደብረ ኤሊያስ (ጎጃም) ደግሞ፣ በስላሴ እና በተክለ ኃይማኖት ገዳማት ላይ በከባድ የጦር መሣሪያዎች የተፈፀሙት “መንግስታዊ” ጥቃቶች ዓይነተኛ ማሳያዎች ናቸው።

ግንቦት 18 እና 19 2015 ዓ.ም በሁለት አቅጣጫ ወደ ደብረ ኤሊያስ የገባው የመከላኪያ ኃይል፣ "ለፋኖ እርዳታ ታደርጋላችሁ" በሚል መነሻ፣ ላለፉት ወራት በ”መንግስት” ታጣቂዎች ተከቦ በቆየው የስላሴ አንድነት ገዳም ላይ የከባድ መሣሪያ ተኩስ በመክፈት የጦር ወንጀል ፈፅሟል። በዚህም መሠረት፣ የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጭምር ይህንን ጉዳይ በአንክሮ እንዲመለከተው እንጠይቃለን። እንዲሁም፣ በዛሬው ዕለት "ፋኖን ይደግፋል" ወደ ተባለው ተክለኃይማኖት ገዳምም ወታደራዊ ኃይል በማስገባት እና መንገድ በመዝጋት መንግሥት ተብዬው ወረራ ፈፅሟል። ይህ መግለጫ እስከወጣበት ግዜ ድረስ፣ የደረሰው ጉዳት በትክክል አልታወቀም።

ይህን ፈርጀ ብዙ የህልውና ጥቃት ተቀምጠን የምናመልጠው፣ ከሌሎች በመጠበቅ የምናስቀረው፣ በአጥቂዎቻችን በጎ ፈቃድ የሚቆም አይደለም። ዛሬ በአማራ፣ በወለጋ፣ በአዲስ አበባ እና በሌሎችም አካባቢዎች የሚካሄዱት የዘር እና የኃይማኖት ጥቃቶች፣ ኢትዮጵያን እንደ ሀገር የማጥፋት ግብ የሰነቁ ናቸው። ስለሆነም፣ ይህንን ጥፋት መመከት የዘር ጥቃት እየተፈፀመበት የሚገኘው የአማራ ግዴታ ብቻ ሳይሆን፣ ኃይማኖታቸውን እና ሀገራቸውን የሚወዱ የመላ ኢትዮጰያዊያንም ግዴታ ጭምር ነው። ይህንን ኃላፊነት ለመወጣት መነሻውን አማራ፣ መዳረሻውን ኢትዮጰያ አድርጎ የተነሳው "የአማራ ሕዝባዊ ግንባር" (አሕግ) የሕልውና ትግል እያደረገ ይገኛል። በመሆኑም፣ በአማራ ክልል፣ አዲስ አበባ እና በመላው ኢትዮጵያ ያላችሁ ሁሉ፣ በግልና በአደባባይ በሚደረግላችሁ ጥሪ ትግሉን ለመቀላቀል ራሳችሁን እንድታዘጋጁ እናሳስባለን።

ግንቦት 18 እና 19 2015 ዓ.ም በአዲስ አበባ እና በደብረ ኤሊያስ የተፈፀሙትን “መንግስታዊ” ጥቃቶች በጥብቅ እያወገዝን፣ መንግስት ተብዬው በኃይማኖት ተቋማት ላይ የሚፈፅመውን ጥቃቶች እና በደብረ ኤሊያስ እያካሄደ የሚገኘውን ወታደራዊ ዘመቻ እንዲያቆም በጥብቅ እናስጠነቅቃለን።

የአማራ ሕዝባዊ ግንባር(አሕግ)/ Amhara Popular Front (APF)

ተጨማሪ 15 ቀናት ተሰጠባቸው!! በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙት መምህርት መስከረም አበራ፤ በሌላ መዝገብ ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው፤ ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ አስፋው ተጨማሬ 15 ቀናት...
26/05/2023

ተጨማሪ 15 ቀናት ተሰጠባቸው!!

በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙት መምህርት መስከረም አበራ፤ በሌላ መዝገብ ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው፤ ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ አስፋው ተጨማሬ 15 ቀናት ተፈቅዶባቸዋል።

ጋዜጠኞቹ ዛሬ ግንቦት 18 ቀን 2015 ዓ.ም በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ኛ ወንጀል ችሎት የግዜ ቀጠሮ የቀረቡ ሲሆን ከሳሽ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ "የጊዜ ቀጠሮ ተዘግቶ የክስ መመስረቻ 15 ቀናት ይፈቀድልኝ "ሲል ለፍርድ ቤቱ በፅሑፍ እና በቃል አቅርቧል።

የተከሳሾች ጠበቆችም ተጨማሪ ጊዜ ሊሰጥ አይገባም ብለው የተከራከሩ ሲሆን ፍ/ቤቱም አቃቤ ሕግ የጠየቀውን ክስ የመመስረቻ 15 ቀናት ፈቅዷል። ቀጠሮም ለሰኔ 3 ቀን 2015 ዓ.ም ተቀጥሯል!!

መረጃው የ Natnael Ye ነው።

ከቃሊቲ ማረሚያ ቤት ለማምለጥ በተደረገ ሙከራ፤ ቢያንስ አምስት ታራሚዎች ቆስለው መያዛቸውን የዓይን እማኞች ተናገሩበአዲስ አበባ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት የሚገኙ የተወሰኑ ታራሚዎች ትላንት ለሊት ለ...
25/05/2023

ከቃሊቲ ማረሚያ ቤት ለማምለጥ በተደረገ ሙከራ፤ ቢያንስ አምስት ታራሚዎች ቆስለው መያዛቸውን የዓይን እማኞች ተናገሩ

በአዲስ አበባ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት የሚገኙ የተወሰኑ ታራሚዎች ትላንት ለሊት ለማምለጥ ባደረጉት ሙከራ፤ አንድ እስረኛ ሲገደል ቢያንስ አምስቱ መቁሰላቸውን እና አንዱ ሳያይዝ መቅረቱን የአይን እማኞች እና የአካባቢ ነዋሪዎች ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናገሩ። ከቃሊቲ ማረሚያ ማዕከል የማምለጥ ሙከራ መደረጉን ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ያረጋገጠው የፌደራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ግን ያመለጠ እስረኛ “የለም” ብሏል።

ከአስር ዓመት እና ከዚያ በላይ የተፈረደባቸው እስረኞችን ከሚያስተናግደው ከቃሊቲ ማረሚያ ቤት የማምለጥ ሙከራ የተደረገው፤ ለዛሬ አጥቢያ ትላንት ረቡዕ ግንቦት 16፤ 2015 ለሊት አስር ሰዓት ገደማ መሆኑን “ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ያነጋገረቻቸው አንድ የአይን እማኝ እና አምስት የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል። የማምለጥ ሙከራውን ያደረጉት እስረኞች ብዛት 11 መሆኑን ከማረሚያ ቤት ፖሊሶች መስማታቸውን ነዋሪዎቹ አክለዋል።

እንደ ነዋሪዎቹ ገለጻ እስረኞቹ ከማረሚያ ቤቱ አምልጠው መውጣታቸውን ተከትሎ፤ በትንሹ ለአንድ ሰዓት ያህል የቆየ ተኩስ በአካባቢው ሲሰማ ቆይቷል። ድርጊቱ በተፈጸመበት ሰዓት በስራ ምክንያት በአካባቢው እንደነበሩ የተናገሩ አንድ የዓይን እማኝ በበኩላቸው፤ ተኩሱ ይበልጥ ጎልቶ ይሰማ የነበረው በማረሚያ ቤቱ መግቢያ ላይ ባለው አስፓልት መንገድ ላይ እና ተሻግሮ ባሉት አካባቢዎች እንደነበር አስረድተዋል።

insider

ፕሬዚዳንት ፑቲን ለአፍሪካ ቀን የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉየሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሜር ፑቲን ለአፍሪካ ሀገራት መሪዎች እና መንግስታት እንዲሁም ህዝቦች "ለአፍሪካ ቀን የእንኳን...
25/05/2023

ፕሬዚዳንት ፑቲን ለአፍሪካ ቀን የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሜር ፑቲን ለአፍሪካ ሀገራት መሪዎች እና መንግስታት እንዲሁም ህዝቦች "ለአፍሪካ ቀን የእንኳን አደረሳችሁ" ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

የአፍሪካ ህብረት የተመሰረተበት 60ኛ ዓመት በዛሬው ዕለት ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ይገኛል፡፡

ፑቲንም የምስረታውን 60ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በመልዕክታቸውም አፍሪካውያን ቅኝ አገዛዝን ያሸነፉበት የነፃነት ፣የሰላምና የብልፅግና ምኞቶችን ያቀፈ ድል ማሳያ ለሆነው የአፍሪካ ቀን እንኳን አደረሳችሁ ብለዋል።

የአፍሪካ መንግስታት በጋራ ባደረጉት ጥረት ለአካባቢያዊ ቀውሶች የጋራ ምላሽ ለመስጠት የሚያስችሉ ዘዴዎችን እና የቀጣናዊ ውህደት ሂደትን ማስጀመራቸውን ጠቅሰዋል።

በተጨማሪም ለአህጉሪቱ ማህበበረ -ኢኮኖሚያዊ ዕድገት እና አፍሪካ በዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ ያላት ሚና እንዲያድግ አስተዋጽኦ ማድረጋቸውንም ነው ያነሱት።

ፑቲን በመልዕክታቸው ሩሲያ ከአፍሪካ አጋሮች ጋር ያላትን ወዳጅነት ለማጠናከር ሁልጊዜ ልዩ ትኩረት እንደምትሰጥም አጽንኦት ሰጥተዋል።

በፈረንጆቹ 2019 ለመጀመሪያ ጊዜ የተካሄደው የሩሲያ - አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤም ሩሲያ ከአህጉሪቱ ጋር ያላትን ዘርፈ ብዙ ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከሩን ተናግረዋል፡፡

ሁለተኛው የሩሲያ - አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ በመጭው ሐምሌ ወር በሴንት ፒተርስበርግ እንደሚካሄድ የገለጹት ፕሬዚዳንቱ፥ ጉባኤው ሩሲያ ከአፍሪካ አጋሮች ጋር በፖለቲካ፣ ንግድ እና ኢኮኖሚ፣ ሳይንሳዊ እና ቴክኒካል፣ ሰብአዊ ድጋፍን ጨምሮ በሌሎችም አዳዲስ ዘርፎች ያላትን ትብብር ለማሳደግ እንደሚያግዛትም ነው የገለጹት።

The social media activist Ermias Mekuria has been kidnapped on May 12,2023 and his where about is still unknown.   East ...
25/05/2023

The social media activist Ermias Mekuria has been kidnapped on May 12,2023 and his where about is still unknown.



East and Horn of Africa Human Rights Defenders Project
Ethiopian Human Rights Commission
Abiy Ahmed Ali
Ethiopian Federal Police

 በባህር ዳር ከነማ ደጋፊዎች ላይ የቦምብ ጥቃት ተሰነዘረበባህርዳር ከነማ እግር ኳስ ክለብ ደጋፊዎች ላይ  የቦንብ ጥቃት ተሰንዝሯል። ጉዳት የደረሰው ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ለመጫወት ከባህርዳ...
25/05/2023


በባህር ዳር ከነማ ደጋፊዎች ላይ የቦምብ ጥቃት ተሰነዘረ

በባህርዳር ከነማ እግር ኳስ ክለብ ደጋፊዎች ላይ የቦንብ ጥቃት ተሰንዝሯል። ጉዳት የደረሰው ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ለመጫወት ከባህርዳር ወደ ሀዋሳ በመጓዝ ላይ እያሉ መሆኑ ተሰምቷል::

አደጋው የደረሰው ገና ከተማውን በመውጣት ላይ እንዳሉ ጥዋት 1:50 ሰዓት አካባቢ ነው ተብሏል።

የክለቡ ደጋፊዎች ላይ ጉዳት መድረሱም ተጠቁሟል::
የባህርዳር ከነማ እግርኳስ ክለብ ደጋፊዎች ክለቡ በሀዋሳ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር የሚያደርገውን ጨዋታ ለመከታተል በመጓዝ ላይ እያሉ ቦንብ የተወረወረባቸው ብለዋል።

😯የ180 አካል ጉዳተኞች የስራ ቦታቸው በለሊት ፈረሰበአዲስ አበባ ከረሜላ ፋብሪካ አካባቢ ለ14 ዓመት በቦታው ላይ በመስራት ራሳቸውን ና ቤተሰቦቻቸው ሲያስተዳድሩ የነበሩ 180 የሚሆኑ አካል...
24/05/2023

😯

የ180 አካል ጉዳተኞች የስራ ቦታቸው በለሊት ፈረሰ

በአዲስ አበባ ከረሜላ ፋብሪካ አካባቢ ለ14 ዓመት በቦታው ላይ በመስራት

ራሳቸውን ና ቤተሰቦቻቸው ሲያስተዳድሩ የነበሩ 180 የሚሆኑ አካልጉዳተኞች

በለሊት አፍራሽ ግብረ ሀይል መጥቶ የሰራ ቦታቸውን አፍርሶ እቃቸውን በመውሰድ አካል ጉዳተኞቹን ከፍተኛ ችግር ውስጥ ጨምሯቸዋል

አካል ጉደተኞቹም የአዲስ አበባ ከንቲባ ቢሮ ሲሄዱ እኛ የምናውቀው ነገር የለም ሂዱ ከዚህ ብለዋቸዋል

አካል ጉዳተኞቹም ለኢትዮጵያ ህዝብ

* እሺ ምን ሰርተን እንብላ ?
* ምንስ እንሁን ?
* ወዴትስ እንሂድ ?

 #የአማራ ተወላጆች አፈና እና የኦሮሙማው የቅሌት ጉዞ!በተለያዩ ሀገራዊና ማህበራዊ ጉዳዮችና ኪነ ጥበባዊ የትወና ስራዎች ሁሌም ከፊት የምትገኘዋን  #አርቲስት ቤዛዊት መስፍንን # አፍንዋታል...
24/05/2023

#የአማራ ተወላጆች አፈና እና የኦሮሙማው የቅሌት ጉዞ!
በተለያዩ ሀገራዊና ማህበራዊ ጉዳዮችና ኪነ ጥበባዊ የትወና ስራዎች ሁሌም ከፊት የምትገኘዋን #አርቲስት ቤዛዊት መስፍንን # አፍንዋታል!

አርቲስት ቤዛዊት መስፍን እውነተኛ ፣የሁሉ አርዓያ የሆነች፣ ለህዝብ የምትሰራ ፣ለህዝብ የምትኖር ለኢትዮጵያ የምታገለግል ትክክለኛ መስፈርቱን ያሟላች ፅኑ አርቲስት ናት።
አሸባሪው የህወኃት ቡድን በወረረ ጊዜ ጉንቱ ባለስልጣናት ቤተሰቦቻየውን ሲያሸሹ ወደ ትግል ሜዳ ወርዳ ለመስዋእትነት ራሷን ያዘጋጀች ፣ በሴነቷ ተፈትና ያለፈች እንቁ አማራ ናት።

ለማንኛውም ኢትዮጵያ ሀገሬ ሞኝ ነሽ ተላላ
የለፋልሽ ቀር የበደለሽ በላ ነውና ተረቱ ቤዛ
ባለሽበት ሰላም ሁኝ! ያለቀሽላት የረዳሻት ቀን ተሌት ያስታወሻት አገር በከሃዲዎች እጅ ብትወድቅም ነገ ሌላ ቀን ነው።

እንደጨለመ አይቀርም፤ ይነጋል።

24/05/2023

መንግስታችን ሃላላ ኬላ:ጎርጎራ ኬላ እንዲሁም ኮይሻና ቅንጡ ቤተመንግስቶችን እየስራሁ ነው በሚልበት በዚህ ወቅት በርካታ አርሶአደሮች በማዳበሪያ እጥረት ማጣፊያው አጥሯቸው ለአቤቱታ ባህር ዳር እየተመሙ ነው:: በዚህ አካባቢ የማውቀውን አነሳሁ እንጅ በሃገር ደረጃም ችግሩ እጅግ አሳሳቢ እንደሆነ እየስማን ነው:: What a paradox!Priority የሚባል ነገር በPP የለም?

"እናትነቴ ከፖሊስነቴ በለጠብኝ"* መሬት ላይ ተጥሎ የተገኘን የአንድ ወር ህፃን ለማትረፍ የሞከረችው ረዳት ሳጅን፦   | በድሬዳዋ ከተማ ቀበሌ 09 ገንደ-ገራዳ ድልድይ አንድ ነገር ተፈጠረ፡...
23/05/2023

"እናትነቴ ከፖሊስነቴ በለጠብኝ"

* መሬት ላይ ተጥሎ የተገኘን የአንድ ወር ህፃን ለማትረፍ የሞከረችው ረዳት ሳጅን፦

| በድሬዳዋ ከተማ ቀበሌ 09 ገንደ-ገራዳ ድልድይ አንድ ነገር ተፈጠረ፡፡ ገና አንድ ወር የሆነው ህጻን ተጥሎ እሪታውን ቢያሰማም ሰሚ ያገኘው ግን ሰአቱ ገፍቶ ምሽት ላይ ነበር፡፡

በአካባቢው የህጻን ድምጽ የሰማችው የአካባቢው ነዋሪ ወ/ሮ ፋጡማ ድምጹን ፦ወደ ሰማችበት ድልድይ ስር ስትሄድ ያገኘችው ነገር እጅግ እንዳስደነገጣት ትናገራለች፡፡

አንድ ወር ገደማ የሚሆነው ህጻን በጨርቅ ተጠቅልሎ ድረሱልኝ እያለ እሪታውን ያሰማ ነበር ፡፡ የተጣለውን ህጻን እንዳየችው በእናትነት ፍቅር ከወደቀበት አንስታው ወደ ቤት ይዛው ትሄዳለች ነገር ግን ይዛው የሄደችው እናት የምትሰጠው ነገር አልነበራትም እናም ለሊቱን ያለምንም ጡት በቤቷ ያሳልፋል፡፡ ግለሰቧ ወድቆ ያገኘችውን ህጻን ለፖሊስ ለመስጠት በማለዳ ነበር የደረሰችው ፖሊስ ጣቢያ፡፡

የፖሊስ መሬት ፖሊስ ጣቢያ መርማሪ ረ/ሳ ቤተልሄም ምትኩ ግለሰቧ በመጣች ወቅት በስራ ገበታዋ ላይ ነበረች፡፡"ልጁን ሳየው ውስጤ ተረበሸ" የምትለው ረ/ሳ ቤተልሄም "በወቅቱ ህጻኑ ምንም ምግብ ባለመመገቡ ተዳክሞ ነበር" ትላለች።

"እናም የሆነ ነገር እንዲሰጠው ብጠይቅም ይዛው የመጣችው ግለሰብ ምንም ነገር እንደሌላት፤ ለሊትም ምንም ጡት እንዳልጠባ ነገረችኝ" በማለት አክላ "ይሄ ልጅ አይናችን እያየ ህይወቱ ማለፍ የለበትም" ያለቸው ቤተልሄም "እናትነቴ ገፍቶኝ ለህጻኑ ጡት ማጥባት እንዳለበኝ አሰብኩኝ እናም አጠባሁት ወዲያው ልጁ ብርታት አግኝቶ ነቃ" ትላለች፡፡

የሁለት ዓመት ሴት ልጅ እንዳላት የምትናገረው ረ/ሳ ቤተልሄም ምትኩ ልጄን ጡት እያጠባኋት በመሆኑ ይሄ አጋጣሚ ሲከሰት ለህጻኑ ጡቷን ልታጠባው እንደቻለች ተናግራለች፡፡

በአሁኑ ወቅት የተገኘው ህጻን በሙሉ ጤንነት ላይ እንደሚገኝና ፖሊስ ጉዳዩን እያጣራ መሆኑ ከድሬዳዋ ፖሊስ የተገኘው መረጃ ያስረዳል።

ታስራለች😯* በደሴ ለተፈናቀሉት ኢትዮጵያውያን ወገኖቿ  1.5 ሚሊዮን ብር እንዲሁም በደብረብሀን ለተፈናቀሉት 50 ሺህ በመሰብሰብ የምትታወቀው* ሀገሯን የምትወደው* የአንድ ልጅ እናት የሆነች...
23/05/2023

ታስራለች😯

* በደሴ ለተፈናቀሉት ኢትዮጵያውያን ወገኖቿ 1.5 ሚሊዮን ብር እንዲሁም በደብረብሀን ለተፈናቀሉት 50 ሺህ በመሰብሰብ የምትታወቀው

* ሀገሯን የምትወደው
* የአንድ ልጅ እናት የሆነችው

ሜላት ዳዊት ታስራለች

አሁንም ቢሆን አፋኝ ቡድን ህግ ና መርህን በመከተል የዜጎች የመናገር መብት እንዲይከብር

በአስቸኳይ እጣርቶ በቶሎ እንዲለቃት
በትህትና በጭዋነት እንጠይቃለን

እባካችሁ ልጅ ያለ እናት ና አባት ማስቀርት አቁሙ

🙏🙏🙏

Address

Addis Ababa
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when GECH MEDIA posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Share