የዓለም ሚዲያ

የዓለም ሚዲያ Being a voice for the voiceless

10/26/2025

ቆቱ ነኝ አሁንም ጮቄ አልወጣሁም ምናምን እያለ ሲያዝገን የከረመው ለካ ቦለል ያለ በር ተከፍቶለት ነው😁 ይሄው ይደፈርሳል ግን ይጠራል ሲል 1 ዓመት አለፈው የደፈረሰም ነገር የለ ምናልባት ግን ኩልል ብሎ የጠራ ነገር ነው ሚታየው. እሱም ተስፋ አልቆረጠ መረጃ ሚያቀብሉትም አልደከሙ !!!
ግን የትም አልደረሰ አንዳንዴ በ 50 +1 አለማመን ያንተን ጅልነትና ኢ-ዲሞክራሲያዊ ሂደት ያሳያል እንጅ ሌላ ምንም የሚያመጣ ነገር አለምኖሩን በማወቅ በቶሎ በሀሳብ ተግባብታችሁ ቅሬታም ካለ አስረድታችሁ ውጤታም ስራ ስሩ ወሬ የትም አያደርስም

10/26/2025

ከሰሞኑ አንዳንድ አካባቢዎች ከትግሉ ሶሻል ሚዲያ ላይ ከበረቱት ሰውች ጎጃም ላይ መንገጫገጭ እንዳለ እየሰማን ነበር ነገሩን ከስሩ ለማጥራት እንደሞከርኩት ለካ አንድ ጥይት እየተኮሱ ፎቶ በመነሳት ብዙ ሚሊዮኖችን ሲበሉ የነበሩበት ገመድ ተበጥሶ ነው ለካ😎 አሁን አንጃ በመፍጠር የትም እንደማይደረስ በደንብ የታወቀ ይመስለኛል ስለዚህ በሰለጠነ መንገድ ችግሮችን እየፈቱ ወደፊት መሄድ ስለሚሻል ያ የሚያዋጣ ይመስለኛል. ፖለቲካውንና ትግሉንም አሰልጥኑት በፈጠራችሁ ድሮ የቀረን መንገድ መከተል ለማንም አይጠቅምም ምናልባት ትግልን ከመቶተትና ተስፋ ከማስቆረጥ ውጭ !!!

ሁለተኛ ሞት ማለት ይሄ ነው🥲የልጅቷ ሀዘን ሳይረሳ ዘመጃ ታውጆ ቡሬና ፉነተ-ሰላም ላይ ታምር ይሰራል ብለን የሷንም ሀዘን ለመርሳት፣ ገዳዮችም ይሄን ነገር ሁለተኛ እንዳያስቡት ስንጠብቅ ጭራሽ...
10/21/2025

ሁለተኛ ሞት ማለት ይሄ ነው🥲
የልጅቷ ሀዘን ሳይረሳ ዘመጃ ታውጆ ቡሬና ፉነተ-ሰላም ላይ ታምር ይሰራል ብለን የሷንም ሀዘን ለመርሳት፣ ገዳዮችም ይሄን ነገር ሁለተኛ እንዳያስቡት ስንጠብቅ ጭራሽ ቀበሌ ተቆጣጥረው የባለም ቤተሰብ ለፌክ ዶክመንታሪያቸው እናትና አባትን እያስዋሹ ሲያስለቅሷቸው እንይ? እረ የኛስ ከፋ እንዴት አንድን ቀበሌ ደግሞም ብዙ ፖለቲካ ሚሰራበትን ቦታ እንኳን መከላከል ከበደን? ቤተሰብን ይዞ ማፈግፈግም ይቻላል እኮ !!!
ብቻ ግራ ያጋባል

ያሳዝናል !!!እህታችን የ ጎጃም ፋኖ እና አረንዛው ዳሞት ብርጌድ አባል ነበረች. ታዲያ በጠላት እጅ ስር ቆስላ ብትገባም ባሳደጋት ህዝብ መሀል እንደ በግ ስውነቷን በጭካኔ ...😢ነፍስ ይማር...
10/15/2025

ያሳዝናል !!!
እህታችን የ ጎጃም ፋኖ እና አረንዛው ዳሞት ብርጌድ አባል ነበረች. ታዲያ በጠላት እጅ ስር ቆስላ ብትገባም ባሳደጋት ህዝብ መሀል እንደ በግ ስውነቷን በጭካኔ ...😢
ነፍስ ይማር ቃልም የለኝ

10/12/2025

Who is Belay Zemene? እንዴት ሰው እንደ እብድ ውሻ ሁሉንም መናከስ ልምድ ያደርጋል?
ይሄኔ እኮ በሰለጠነ ሀገር እየኖረ ነው እንደዚህ ሚሆነው. እረ ባካችሁ ፖለቲካውን ከባልቴት ወሬ ከፍ አድርጋችሁ ስቀሉት. ይሄ ሁሉንም መናከስ ፖለቲካ አከሰረ እንጅ አልጠቀመም ከበቂ በላይ የተማርነበት ይመስለኛል. ፖለቲካችንን አዘምኑት ስለ ህዝባችን ብላችሁ !!!

ካንድ ተከታያችን የተላከ ...አስታውሳለሁ አርበኛ ዘመነ ካኔ በታሰረበት ጊዜ ለስራ ጉዳይ ባህርዳር ሂጀ ነበር. አዲዳስ ቱታ ከነ ግጣሙ ነው የለበሰው እና ቡና እየጠጣን ከሁላ የተቀመጠው ያኔ...
10/08/2025

ካንድ ተከታያችን የተላከ ...
አስታውሳለሁ አርበኛ ዘመነ ካኔ በታሰረበት ጊዜ ለስራ ጉዳይ ባህርዳር ሂጀ ነበር. አዲዳስ ቱታ ከነ ግጣሙ ነው የለበሰው እና ቡና እየጠጣን ከሁላ የተቀመጠው ያኔ ሙሉ አዲዳስ ቱታ ለብሶ የነበረው(ማርሸት) በጣም እየጮሀ ነበር የሚያወራው እዛ የነበሩ የጸጥታ አካላቶችም ገርሟቸው ዞረው እያዩት ነበር የሚያወራውም ልዩ ሀይሉ ፈርሶ አድማ ብተና ሚባለው እየዞረ በሚያረጋገብት ጊዜ ነበርና እንዴት ፋኖ መሳሪያ ጎጃም ያለን መከላከያን እየቀማ መጣጠቅ እንደነበረበት ነበር. ሰው ሁሉ አይፈራም እንዴ ብሎ ይገረም ነበር እኔን ጨምሮ የጸጥታ አካላቶችም እያዩት ገርሟቸው ይስቁ ነበር. ድፍረቱን እያደነቅሁ ሁሌ ይገርመኝ ነበርና አንድ ቀን እሱን ቱቷ ለብሶ መግለጫ ሲሰጥ ሳየው አሀ አንተ ነበርክ እንዴ በሚል ፈገግ አልኩ...

ማሩ ብዙ ጊዜ ይሳሳታል አንደበተ ርቱ ቢሆንም ግን ሁሌም ሚገርመኝ ተሳስተሀል ሲባል ለመታረም ዝግጁ ነው. እንኳን ተወለድክ ጀግናው !!!

10/04/2025

ነገረ መካነ-ሰላም
አሁን ደግሞ አንድ የፋኖን ትግል ያጓትታል ብለው ያሰቡትን አጀንዳ ጎትተዋል. ከዚህ በፊት ሞክረውም ውጤታማ ሆነው ለጊዜውም ቢሆን ያልገባውን አማራ ሸውደው መጠፋፋትን አስከትለዋል.
አንድ ሙስሊም አማራ ከሞተ የስልጤውም በለው ሌላው አካባቢ ሙስሊም ሙሾ ለማውረድ አይዘገይም. ይሄም ደግሞ ሙስሊም አማራውን በማስገለል የአማራን ህዝብ ለማዳከም ሁሌም ምኞታቸው ስልሆነ ነው. አስቡት መስጊድ ውስጥ መከላከያው ሲደበቅ ኖርማል ነው. መስጊድ ላይ ምሽግ ሰርቶም ወደ ፋኖ ሲተኩስ ኖርማል ነው ፋኖ መስጊድ ውስጥ የተደበቀን ሀይል ከመታ የሙስሊም ጥላቻ ይባላል🥲 ሙስሊም ካድሬም መሆን ይቻላል ፋኖ ካድሬን ሲቀጣ ግን ለምን?
ለማነኛውም አማራ ክልል ውስጥ የሆነ ነገር ሲፈጠር ሙሉውን የኢትዮጵያ ህዝብ ወክለው ዲፕሎማትና ሚኒስተር የሆኑትም ከ100K በላይ ተከታይ ያላቸው ነገርየውን ቢያጦዙትም በዚህ ጊዜ ለእንደዚህ አይነት እርባና ቢስ ፕሮፖጋንዳ ሚሸወድ ሙስሊም አማራ ይኖራል ብየ አላስብም.
ምንም ጥፋት የሌለበት ንጽህ ሙስሊም ከተገደለ ግን እዛው ያሉት ፍኖዎች ከኔ በላይ ፍትሀዊ ስለሆኑ ተገቢውን እርምጃ እንደሚዎስዱ እርግጠኛ ነኝ !!!

ሻለቃ ይንገስ ብርሀኑ ይባላል 9ኛ ክፍለ-ጦር የአባይ ሸለቆ ብርጌድ ሰብሳቢ ነው. ጎጃምን ከወሎ ቤተ አማራ ጋር የሚያገናኘውን በረሀ ጠላት ሊደፍረው አይደለም ዞሮ እንዳያየው ያደረገ ጥንቅቅ ...
10/03/2025

ሻለቃ ይንገስ ብርሀኑ ይባላል 9ኛ ክፍለ-ጦር የአባይ ሸለቆ ብርጌድ ሰብሳቢ ነው. ጎጃምን ከወሎ ቤተ አማራ ጋር የሚያገናኘውን በረሀ ጠላት ሊደፍረው አይደለም ዞሮ እንዳያየው ያደረገ ጥንቅቅ ያለ ጀግና ነው. አሁን ደግሞ ከጎረቤቶቹ ምዕራብ-ወሎ ፋኖዎች ጋር ክፍለ ጦሩን ይዞ መካነ ሰላምን በወታደራዊ ሰላምታ እየጠየቃት ነው. ለኔ ፋኖዎች ከአካባቢያቸው ራቅ ብለው ለሚሰሩት ስራ ትልቅ አክብሮት አለኝ ምክኒያቱም እንደዚህ አይነት ስራ ምትሰራው እዛ አካባቢ ካሉት ጋር ስትግባባ ብቻ ነው. ስንቱ በጥቅም የጎጡን ፋኖ ሲገድልና እንዳላይህ ሲባባል እየዋለ ለመከረኛው ህዝብ ድል እስኪያደርጉ ተስፋ ይሆንን ዘንድ ከተማውን በወንድ ግብር ሲጎበኙት ያስደስታል. ከሰፈር ራቅ ብሎ ሲሆን ደግሞ ልብ ያሞቃል. ብቻ በርቱ ...

ይሄን ጀብድ እያዩ አለመኩራት አይቻልም. ወሎ ቤተ አማራ ሁሌም በስራቸው አይታሙም. ከፈተኛ ዝግጅት ያደርጋሉ ከእቅዳቸው በላይ ይፈጽማሉ. በጠንካራ አደረጃጅቱ እንደ ምሳሌ ሲጠቀስ የነበረውን ...
09/24/2025

ይሄን ጀብድ እያዩ አለመኩራት አይቻልም. ወሎ ቤተ አማራ ሁሌም በስራቸው አይታሙም. ከፈተኛ ዝግጅት ያደርጋሉ ከእቅዳቸው በላይ ይፈጽማሉ.
በጠንካራ አደረጃጅቱ እንደ ምሳሌ ሲጠቀስ የነበረውን የምዕራብ አማራ ክፍል ደግሞ በውስጡ በተሰገሰጉ ባንዳዎችና የገንዘባና የዝና ታጋይ እየተፈተነ መመናመኑን ቀጥሎበታል. ጭራሽ ባንዳ ማረክነ እያሉ ሲያደነቁሩን ቆይተው በ1 ሚሊዮን እንደቀየሩት ተነግሯል እንግዲህ ምን ይባላል. ለትግሉ ብለው ህይወታቸውን ያጡን እያሰቡ ከማንባት ሌላ ምን ይደረጋል. ራስን መፈተሽና ግምገማ ፍቱን መድሀኒት ነው.
በነገራችን ላይ ትልቅ ድል ሚገኘው ከልብ ሲታገሉ ነው አንዳንድ ቦታ ድል ሚርቀውም ሳይሞት ለፈንድና ለሪፖርት ሚሆን ጥይት አጩሆ ለመመለስ ሲሞከር ነው. ትግል እንዴት ነው ካልክኝ የዛሬውን የቤተ አምሀራ ተጋድሎና አብይን አቋርጠው ዳሞት የዘለቁ የቢዛሞ ፋኖዎችን ምሳሌ እነግርሀለው. ለነገሩ በሰባሰቡ አንድም በማገት ወይም ለግዳጅ የተሰጠን ጥይት ተሽጦ የተጠራቀመን ብር ሳይበላ ወዴት?😎 ይህን ስል አላስፈላጊ መስዋትነትን መክፈልን እየደገፍኩ አይደለም ቢቻል አንድም የወገን ሀይል አይሙት !!

አንዳንዴ ይሄን ማያልፍለት የአማራ ፖለቲካ ላለመስማት እፈልግና እርቃለሁ ግን ደግሞ ምንም ያልጎደለባቸው እንደነ ሻለቃ አባይ አይነት ሰውን ማጣት ደግሞ ጦሱ እንደማይለቅህ ያስታውስሀል. ሰማዕ...
09/23/2025

አንዳንዴ ይሄን ማያልፍለት የአማራ ፖለቲካ ላለመስማት እፈልግና እርቃለሁ ግን ደግሞ ምንም ያልጎደለባቸው እንደነ ሻለቃ አባይ አይነት ሰውን ማጣት ደግሞ ጦሱ እንደማይለቅህ ያስታውስሀል. ሰማዕቱ ሻለቃ አባይ ዴንድ(ወንበርማ) አካባቢ የሰራህው ስራ ዘላለም ያስታውስሀል.

ይህን እያየም እኔ መሪ ካልሆንኩ ብሎ በየቀበሌው ሲታኮስ የሚውለውን ፈጣሪ ልቦና ይስጠው እንጅ ምን ይባላል.
እግዚያብሄር ነፍስህን ይማረው !!!

09/13/2025

መግለጫውኮ በጣም ትክክል ነው. ሚዛንም ይደፋል እኔ እንደው በደፈናው ትምህርት ይፈቀዳል ከሚባል እንደዚህ በቅድመ ሁኔታ ቢሆን ይሻላል ባይ ነኝ ግን መግለጫውን መጀመሪያ ከለጠፈው አካባቢ ውጭ ሁሉም ዝም ካለ የድርጅቱን ስም መጠቀም አያስፈልግም ነበር !!!

09/13/2025

የአፋብሀ ነገር አንዳንድ ባለ ትዳርን ያስታውሳል ለሰው ሲታዩ ሚግባቡ ይመስላሉ ግን ቤታቸውን በደንብ ለሚያውቀው ነገር ስራቸው ሁሉ ድብልቅልቅ ያለ 😎

Address

Los Angeles, CA

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የዓለም ሚዲያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share