Habte Teferi page

Habte Teferi page መኖሬ በእግዚአብሔር እርዳታ ብቻ ነው!!!

18/09/2023

ጻድቅ በእግዚአብሔር ደስ ይለዋል፥ በእርሱም ይታመናል

02/09/2023
26/08/2023

06/08/2023

“በላባዎቹ ይጋርድሃል፥ በክንፎቹም በታች ትተማመናለህ፤ እውነት እንደ ጋሻ ይከብብሃል።”
— መዝሙር 91፥4

06/08/2023

ሰዶማዊነት፦በባህላችን ነውር በእምነታችን ኃጢአት፤በሃገራችን ወንጀል ነው!!

I am against homosexuality!
05/08/2023

I am against homosexuality!

04/08/2023

መዝሙር 129
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ እስራኤል፦ ከትንሽነቴ ጀምሮ ብዙ ጊዜ ተሰለፉብኝ ይበል፤
² ከትንሽነቴ ጀምሮ ብዙ ጊዜ ተሰለፉብኝ፤ ነገር ግን አላሸነፉኝም።
³ ኃጢአተኞች በጀርባዬ ላይ መቱኝ፥ ኃጢአታቸውንም አስረዘሙአት።
⁴ እግዚአብሔር ጻድቅ ነው፤ የኃጢአተኞችን አንገታቸውን ቈረጠ።

04/08/2023

“ነፍሱን ስለ ወዳጆቹ ከመስጠት ይልቅ ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር ለማንም የለውም።”
— ዮሐንስ 15፥13

29/07/2023

“እግዚአብሔር ዓለቴ፥ አምባዬ፥ መድኃኒቴ፥ አምላኬ፥ በእርሱም የምተማመንበት ረዳቴ፥ መታመኛዬና የደኅንነቴ ቀንድ መጠጊያዬም ነው።”
— መዝሙር 18፥2

27/07/2023

በቀናት ሁሉ የነገሰ፣ በአመታት ሁሉ የከበረና የተከበረ ፣ የዘመናት ሁሉ ንጉስ የናዝሬቱ ኢየሱስ ብቻ ነው!!

24/07/2023

ኑሮዬን የተአምራት አድርጎታል
የኔኮ ከሰው ሁሉ ለየት ይላል!

24/07/2023

“ሕፃን ተወልዶልናል፤ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናል፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል። ስሙም፣ ድንቅ መካር፣ ኀያል አምላክ፣ የዘላለም አባት፣ የሰላም ልዑል ይባላል።”
‭‭ኢሳይያስ‬ ‭9‬:‭6‬ ‭

07/07/2023

Yes I'm a Christian. Yes I make mistakes. Yes I fall.
Yes I struggle. I can be a mess. But I'm God's mess. The good news is that He’s making this mess into His masterpiece.

26/06/2023

ኤፌሶን 2
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁴ ነገር ግን እግዚአብሔር በምሕረቱ ባለ ጠጋ ስለ ሆነ፥
⁵ ከወደደን ከትልቅ ፍቅሩ የተነሣ በበደላችን ሙታን እንኳ በሆንን ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ሕይወት ሰጠን፥ በጸጋ ድናችኋልና፥
⁶-⁷ በሚመጡ ዘመናትም በክርስቶስ ኢየሱስ ለእኛ ባለው ቸርነት ከሁሉ የሚበልጠውን የጸጋውን ባለ ጠግነት ያሳይ ዘንድ፥ ከእርሱ ጋር አስነሣን በክርስቶስ ኢየሱስም በሰማያዊ ስፍራ ከእርሱ ጋር አስቀመጠን።
⁸ ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፤
⁹ ማንም እንዳይመካ ከሥራ አይደለም።
¹⁰ እኛ ፍጥረቱ ነንና፤ እንመላለስበት ዘንድ እግዚአብሔር አስቀድሞ ያዘጋጀውን መልካሙን ሥራ ለማድረግ በክርስቶስ ኢየሱስ ተፈጠርን።

Ephesians 2 (KJV)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁴ But God, who is rich in mercy, for his great love wherewith he loved us,
⁵ Even when we were dead in sins, hath quickened us together with Christ, (by grace ye are saved;)
⁶ And hath raised us up together, and made us sit together in heavenly places in Christ Jesus:
⁷ That in the ages to come he might shew the exceeding riches of his grace in his kindness toward us through Christ Jesus.
⁸ For by grace are ye saved through faith; and that not of yourselves: it is the gift of God:
⁹ Not of works, lest any man should boast.
¹⁰ For we are his workmanship, created in Christ Jesus unto good works, which God hath before ordained that we should walk in them.

18/06/2023

ብርቱ ፡ ተብሎ ፡ ታምኖበት ፡ ልብም ፡ በእርሱ ፡ ላይ ፡ ተጥሎ
አለልኝ ፡ ለእኔ ፡ እያለ ፡ መኖር ፡ ሲመኝ ፡ ተዘልሎ
የተደገፈው ፡ ሸንበቆ ፡ መሆኑን ፡ እንዲያው ፡ ሳያውቀው
ድንገት ፡ ተሰብሮ ፡ ወደቀ ፡ የዚያ ፡ ሰው ፡ መተማመኛው

አኔማ/እኔ ፡ ግን ፡ በላዬ ፡ ላይ ፡ ንጉሴን ፡ ሾሜያለሁ
አልፈራ ፡ አልደነግጥ ፡ በክንዱ ፡ እኮራለሁ (፪x)

ኩራት ፡ ኩራት ፡ አለኝ ፡ ብኮራስ ፡ ምናለ
እመካለሁ ፡ እኔስ ፡ ብመካ ፡ ምናለ
አንበሳው ፡ ኢየሱስ ፡ የእኔ ፡ ሆኖ ፡ የለ
ኃይለኛው ፡ ኢየሱስ ፡ ቤቴን ፡ ሞልቶት ፡ የለ
ኃይለኛው ፡ ኢየሱስ ፡ የእኔ ፡ ሆኖ ፡ የለ
ወዳጄ ፡ ኢየሱስ ፡ ቤቴን ፡ ሞልቶት ፡ የለ

እንዳንተ ፡ ያለ ፡ ከቶ ፡ የለምና
በሰማይ ፡ በምድር ፡ አልተገኘምና
ይብዛልህ ፡ ዛሬም ፡ ምሥጋና
ይብዛልህ ፡ ነገም ፡ ምሥጋና (፪x)

ዓይኔ ፡ አረፈብህ ፡ ወዳጄ ፡ በምንም ፡ የማትረታ
ወረት ፡ አታውቅም ፡ እንደሰው ፡ በጐ ፡ ነህ ፡ ሁሌ ፡ የእኔ ፡ ጌታ
ዘመናት ፡ ሲፈራረቁ ፡ አልተቀየረም ፡ መውደድህ
ሁሉን ፡ በጆችህ ፡ ይዘሃል ፡ ታስመካለህ ፡ ቢመኩብህ

በልቤ ፡ ሾሜሃለሁ ፡ ከፍ ፡ ብለህ ፡ ደምቀህ ፡ ታይ
እንዳንተ ፡ የለምና ፡ በምድር ፡ በሰማይ (፪x)

ኩራት ፡ ኩራት ፡ አለኝ ፡ ብኮራስ ፡ ምናለ
እመካለሁ ፡ እኔስ ፡ ብመካ ፡ ምናለ
አንበሳው ፡ ኢየሱስ ፡ የእኔ ፡ ሆኖ ፡ የለ
ኃይለኛው ፡ ኢየሱስ ፡ ቤቴን ፡ ሞልቶት ፡ የለ
ኃይለኛው ፡ ኢየሱስ ፡ የእኔ ፡ ሆኖ ፡ የለ
ወዳጄ ፡ ኢየሱስ ፡ ቤቴን ፡ ሞልቶት ፡ የለ

እንዳንተ ፡ ያለ ፡ ከቶ ፡ የለምና
በሰማይ ፡ በምድር ፡ አልተገኘምና
ይብዛልህ ፡ ዛሬም ፡ ምሥጋና
ይብዛልህ ፡ ነገም ፡ ምሥጋና (፪x)

በመከራ ፡ ቀን ፡ ቢጠሩት ፡ አለሁኝ ፡ የሚል ፡ ልብ ፡ ሞልቶ
ግራ ፡ ለገባው ፡ መጠጊያ ፡ ሚደግፍ ፡ እጁን ፡ ዘርግቶ
መተማመኛ ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ ተፈትኖ ፡ አልፏል ፡ በብዙ
ደጋግ ፡ እጆቹን ፡ አይተናል ፡ ደካማዎቹን ፡ ሲያግዙ

አለልኝ ፡ ይሄ ፡ ጌታ ፡ የማይጥል ፡ የማይከዳ
ሰባራን ፡ የሚጠግን ፡ ወዳጅ ፡ ነው ፡ በምድረበዳ (፪x)

ኩራት ፡ ኩራት ፡ አለኝ ፡ ብኮራስ ፡ ምናለ
እመካለሁ ፡ እኔስ ፡ ብመካ ፡ ምናለ
አንበሳው ፡ ኢየሱስ ፡ የእኔ ፡ ሆኖ ፡ የለ
ኃይለኛው ፡ ኢየሱስ ፡ ቤቴን ፡ ሞልቶት ፡ የለ
ኃይለኛው ፡ ኢየሱስ ፡ የእኔ ፡ ሆኖ ፡ የለ
ወዳጄ ፡ ኢየሱስ ፡ ቤቴን ፡ ሞልቶት ፡ የለ

እንዳንተ ፡ ያለ ፡ ከቶ ፡ የለምና
በሰማይ ፡ በምድር ፡ አልተገኘምና
ይብዛልህ ፡ ዛሬም ፡ ምሥጋና
ይብዛልህ ፡ ነገም ፡ ምሥጋና (፰x)

18/06/2023

“በአንተ ላይ ታምናለችና በአንተ ለምትደገፍ ነፍስ ፈጽመህ በሰላም ትጠብቃታለህ።”
— ኢሳይያስ 26፥3

You will keep him in perfect peace, Whose mind is stayed on You, Because he trusts in You. Isaiah 26:3

16/06/2023

"ጻድቅ እንደ ዘንባባ ያፈራል፥
እንደ ሊባኖስ ዝግባም ያድጋል።"
መዝ 92:12

13/06/2023

“እስራኤል ሆይ፥ ምስጉን ነህ፤ በእግዚአብሔር የዳነ ሕዝብ እንደ አንተ ማን ነው? እርሱ የረድኤትህ ጋሻ፥ የከፍተኛነትህም ሰይፍ ነው። ጠላቶችህም ይገዙልሃል፤ አንተም ከፍታቸውን ትረግጣለህ።”
— ዘዳግም 33፥29

06/06/2023

“ብዙ ምርኮ እንዳገኘ በቃልህ ደስ አለኝ።”
— መዝሙር 119፥162

“Akka nama boojuu guddaa argatee, ani wanta ati jettutti nan gammada.”
— Far. 119:162

“I rejoice at thy word, as one that findeth great spoil.”
— Psalms 119:162 (KJV)

31/05/2023

“ለእስራኤልም እንደ ጠል እሆነዋለሁ እንደ አበባም ያብባል፥ እንደ ሊባኖስም ሥሩን ይሰድዳል።”
— ሆሴዕ 14፥5

በእውነት በእናንተ ዝማሬዎች ተባርከናል እና ብሩካን ሁኑ።
25/05/2023

በእውነት በእናንተ ዝማሬዎች ተባርከናል እና ብሩካን ሁኑ።

21/05/2023

I am a witness about the salvation of Jesus.

21/05/2023

you're perfect bro. No choice at all & We are born to worship God.

15/05/2023

“የእግዚአብሔር ስም የጸና ግምብ ነው፤ ጻድቅ ወደ እርሱ ሮጦ ከፍ ከፍ ይላል።”
— ምሳሌ 18፥10

12/05/2023

“አትታበዩ፥ በኩራትም አትናገሩ፤ እግዚአብሔር አዋቂ ነውና፥ እግዚአብሔርም ሥራውን የሚመዝን ነውና፥ ከአፋችሁ የኵራት ነገር አይውጣ።”
— 1ኛ ሳሙኤል 2፥3

12/05/2023

“ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ።”
ፊልጵስዩስ 4፥13

11/05/2023

ቸርነትህና ምህረትህ በህይወቴ ዘመን ሁሉ ይከተሉኛል!!!

አሁን እነኳን ብሞትወዴት እንደምሄድ ጠንቅቄ አዉቃለሁ በጌታ ላይ ያለኝ መተማመን እስከዚህ ድረስ ነዉ።
11/05/2023

አሁን እነኳን ብሞት
ወዴት እንደምሄድ
ጠንቅቄ አዉቃለሁ
በጌታ ላይ ያለኝ
መተማመን እስከዚህ ድረስ ነዉ።

published April 19 ,2020Endale W/Giorgis(PR) MEDANE D**K SITOTA 2019Cornerstone bandKingdom Sound Choir Web site...

10/05/2023

Welcome Jossy! We miss it

09/05/2023

ትቼለታለዉ የኔን ጉዳይ
ትቼለታለዉ የኔን ታሪክ
ይፈተዋል ማህተሙን
ለሰው ግራ የገባውን
ይችለዋል ከባባዱን
ሰው ሁሉ ያልቻለውን

02/05/2023

ኢየሱስ በቂ ነዉ!!

Send a message to learn more

01/05/2023

ሰላም ለሁላችሁ ይሁን በጌታ የተወደዳችሁ በምለቃቸው መዝሙሮቼ እንደምትባረኩና እንደምትጽናኑ አምናለው። ደግሞ በሌላም ጊዜ የምለቃቸውን መዝሙሮቼ ወደናንተ እንዲደርስ ሰብስክራይብ....

01/05/2023
29/04/2023

1ኛ ቆሮንቶስ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁶ ወንድሞች ሆይ፥ መጠራታችሁን ተመልከቱ፤ እንደ ሰው ጥበብ ጥበበኞች የሆኑ ብዙዎች፥ ኀያላን የሆኑ ብዙዎች፥ ባላባቶች የሆኑ ብዙዎች አልተጠሩም።
²⁷ ነገር ግን እግዚአብሔር ጥበበኞችን እንዲያሳፍር የዓለምን ሞኝ ነገር መረጠ፤ ብርቱንም ነገር እንዲያሳፍር እግዚአብሔር የዓለምን ደካማ ነገር መረጠ፤
²⁸ እግዚአብሔርም የሆነውን ነገር እንዲያጠፋ የዓለምን ምናምንቴ ነገር የተናቀውንም ነገር ያልሆነውንም ነገር መረጠ፥
²⁹ ሥጋን የለበሰ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት እንዳይመካ።

Address

Addis Ababa
Ababa
251

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Habte Teferi page posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Habte Teferi page:

Share