Silta Mass Media

Silta waraba fc
24/12/2023

Silta waraba fc

Check out Mujib@jr's video.

ስልጤ ወራቤ እግር ኳስ ክለብ አሰልጣኝ ፀጋዬ ወንድሙን የክለቡ ዋና አሰልጣኝ አድርጎ  ሾማ!!የስልጤ ወራቤ እግር ኳስ ክለብ ሻሸመኔ ከነማን በ2015 ወደ ፕሪሚየርሊግ  ያሰገባውን አሰልጣኝ ...
21/12/2023

ስልጤ ወራቤ እግር ኳስ ክለብ አሰልጣኝ ፀጋዬ ወንድሙን የክለቡ ዋና አሰልጣኝ አድርጎ ሾማ!!

የስልጤ ወራቤ እግር ኳስ ክለብ ሻሸመኔ ከነማን በ2015 ወደ ፕሪሚየርሊግ ያሰገባውን አሰልጣኝ ፀጋዬ ወንድሙን የክለቡ ዋና አሰልጣኝ አድርጎ ሾማ!!

ስፖርት ክለቡ የውጤት ቀውስ ውስጥ መግባቱን ተከትሎ ባለፈው ሳምንት ሶስቱንም የክለቡ አሰልጣኞች ማሰናበቱ ይታወቃል። በዚሁ መሠረትም በዛሬው እለት ቦርዱ ባደረገው ስብሰባ በ2015 የውድድር ዓመት ሻሸመኔ ከነማን ወደ ፕሪሚየርሊግ ያስገባውን እና የቀድሞው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች ሆኖ ያገለገለውን አሰልጣኝ ፀጋዬ ወንድሙን የክለቡ ዋና አሰልጣኝ አድርጎ መድቧል።

አሰልጣኝ ጸጋዬ ወንድሙ የፊታችን ሰኞ ስልጤ ወራቤ ስፖርት ክለብ ከነቀምት አቻው ጋር በሚያደርገው ጨዋታ ቡድኑን የሚመራ መሆኑ በቦርዱ በኩል ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

21/12/2023
የኢንዱስትሪውን ፍላጎት መሠረት በማድረግ በመካከለኛ እና በአነስተኛ ደረጃ የሰለጠነ ብቁ የሰው ሀይል በመፍራት የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ተቋማት ሚና ከፍተኛ መሆኑን የማዕከላዊ ኢትዮጵ...
12/12/2023

የኢንዱስትሪውን ፍላጎት መሠረት በማድረግ በመካከለኛ እና በአነስተኛ ደረጃ የሰለጠነ ብቁ የሰው ሀይል በመፍራት የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ተቋማት ሚና ከፍተኛ መሆኑን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ቢሮ ሀላፊ አቶ ይርጋ ሀንዲሶ ገለፁ ።
በስልጤ ዞን አሊቾ ውሪሮ ወረዳ የቃዋቆቶ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ በአራት የተለያዩ የሙያ መስኮች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎችን አስመርቋል።

በምረቃ ፕሮግራም ላይ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የቃውቆቶ ኢንዱስትሪያል እና ኮንስትራክሽን ኮሌጅ ዲን አቶ ሸምሴ አወል ሀገራት ዛሬ ኢኮኖሚያዊ እድገት ብቁና የሰለጠነ ፣በራሱ የሚተማመን ፣ስራ ፈጣሪ የሰው ኃይል ግንባታ ላይ ትኩረት ተሰጥተው በመስራታቸው መሆኑን ተናግራዋል ።
የቀውቀቶ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ በበጀት አማቱ በመደበኛ መርሐ ግብር በ4 ዲፓርትመንቶች ከደረጃ 2 እስከ 4 ወንድ 15 ሴት 31 በድምሩ 46 ሰልጣኝ ተማሪዎችን ማስመረቅ መቻሉን ገልፀዋል ።

በምረቃ ፕሮግራም ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ቢሮ ሃላፊ አቶ ይርጋ ሀንዲሶ በመደበኛም ይሁን በአጫጭር ግዜ ፕሮግራሞች የሚሰጡ ስልጠናዎች ዋነኛ ግባቸው ዜጎች ስራ መስራት ብቻ ሰይሆን ስራ ፈጣሪ በመሆን ሀገራቸውን በብቃት መገልገል እንዲችሉ ለማድረግ መሆኑን ተነግረዋል ።

የኢንዱስትሪውን ፍላጎት መሠረት በማድረግ በመካከለኛ እና በአነስተኛ ደረጃ የሰለጠነ ብቁ የሰው ሀይል በመፍራት የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ተቋማት ሚና ከፍተኛ መሆኑንም ገልፀዋል ።

ሰልጠኞች በስልጠናው ሂደት የተለያዩ ችግሮችንና ውጣውረዶችን ተጋፍጠችሁ የተግባርና የንድፈ ሀሳብ ስልጠና በመውሰድ ለምረቃ በመብቃታችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።

በምረቃ ፕሮግራሙ ለይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አሊ ከድር በሀገራችን የቴክኒክ እና ሙያ ስልጠና ዘርፍ በተሰጠው ልዩ ተልእኮ በክህሎት የዳበረ ፣ስራ ፈጣሪ እና ገበያ ተኮር ስርዓትን በመከተል በዘርፉ የበቃ የሰው ሃይል ለመፍጠር እየተሰራ መሆኑን አንስተዋል ፡፡

የቴክኒክ እና ሙያ ትምህርት ስልጠና ተቋማት የሚሰጡትን ስልጠና በማስፋት ከስልጠናው በተጨማሪ የስራ ፈጠራ ማእከል በማድረግና በተገቢው ተግባራዊ በማድረግ የማህበረሰባችንን የልማት እድገት ማፋጠን ይገባል ብለዋል፡፡

የአልቾ ውሪሮ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አማን ከድር በበኩላቸው ሀገራት ለስማዘገቡት ፈጣን ኢኮኖሚያዊ እድገት ሚስጥር የተማረ በእውቀት የዳበረና የቴክኖሎጂ ክህሎት የለው ትውልድ ለመፍጠር ኢንቨስት በማድረግ መሆኑን ገልፀው ሰልጣኞች በኮሌጅ ቆይታቸው ወቅት የቀሰሙትን ክህሎት ወደ ተግባር በመቀየር የማህበረሰቡን ችግር ለመፍታት የበኩላቸውን ሀላፊነት ሊወጡ እንደሚገባ አሳስበዋል ፡፡

የቀውቀቶ ኮንስትራክሽንና ኢንደስትሪያል ኮሌጅ ውጤታማ እንዲሆን እና የተቋሙ ተልእኮ እውን እንዲሆን ሁሉም አካላት በቅንጅት መስራት ያስፈልጋል ያሉት አቶ አማን ወጣቶች በተከፈቱ የስልጠና ዘርፎች ራሳቸውን በማብቃት የሙያ ባለቤት መሆን እንዳለባቸው መልእክት አስተላልፈዋል።

ኮሌጁ በመጀመሪያው ዙር ምረቃ በአራት የተለያዩ የሙያ መስኮች ለመጀመሪያ ጊዜ ያሰለጠናቸውን 15 ሴትና 31 ወንዶች በድምሩ 46 ሰልጣኞች አስመርቋል።

የዕለቱ ተማራቂ ተማሪዎች በበኩላቸው በተማረቁባት የሙያ ዘርፍ የማህበረሰቡን ችግር በሚቀርፉ የስራ ዘርፎች ለይ በመሰማራት የሚጠበቅባቸውን ለመወጣት መዘጋጀታቸውን ገልፀዋል ።

በምረቃ ፕሮግራም ላይ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ቢሮ ዋና ሀላፊ ክቡር አቶ ይርጋ ሀንዲሶ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ ዋና ሀላፊው ክቡር አቶ ሽመልስ ዋንጎሮ፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት የማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ክቡር አቶ አብዱልዋሪስ ጀማል፣ የስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ አሊ ከድር፣ የስልጤ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ሀላፊ አቶ ቀድሩ አብደላና ሌሎች የክልልና የዞን ከፍተኛ አመራሮ፣ የሀይማኖት አባቶች ፣የሀገር ሽማግሌዎች ፣የተማረቂ ተማሪዎች ቤተሰቦችን ጨምሮ ሌሎች ጥሪ የተደረገለቸው እንግዶች ተገኝተዋል። via ሙጂብ ጁሀር

29/10/2023

የስልጤ ሕዝብ ከሚገባዉ በላይ አልጠየቀም!
••••••••••••••••••••••••••••••
❝የስልጤ ሕዝብ ከሚገባዉ በላይ አልጠየቀም። የስልጤ ሕዝብ የራሱን እንጂ የሌላ ስጡኝ አላለም። የስልጤ ሕዝብ የሚለዉ ዉክልናዬ ተነፍጓል፣ ማንነቴ ተረግጧል፤ ባህልና እምነቴ አልተከበረም••• እንጂ በልዩ ሁኔታ ከመብቱ ውጭ የማልቀስና የመጠየቅ ታሪክና ልምድ ፈጽሞ ኖሮት አያዉቅም።

በቀድሞ በ (54ቱ) በደቡብ ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ማንነቱ፣ እምነቱ፣ ባህልና እሴቱ በተሻለ ሁኔታ ተከብሮለት የነበረዉ ታላቁ የስልጤ ሕዝብ በሀገሪቱ ፖለቲከዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ትጋት ዉስጥ ድርሻዉ ከፍ ያለ መሆኑን እሙን ነዉ።❞ Mujib Amino

የታላቁ የስልጤ ሕዝብ ዉክልና የት ሄዶ ነዉ?••••••••••••••••••••••••••••••Mujib Aminoማዕክላዊ ኢትዮጵያ ተብሎ በተሰየመዉ አዲሱ አወቃቀር ላይ የዚህን ስራ ወዳድ፣ ጠን...
13/10/2023

የታላቁ የስልጤ ሕዝብ ዉክልና የት ሄዶ ነዉ?
••••••••••••••••••••••••••••••
Mujib Amino

ማዕክላዊ ኢትዮጵያ ተብሎ በተሰየመዉ አዲሱ አወቃቀር ላይ የዚህን ስራ ወዳድ፣ ጠንካራ፣ ታጋይ ና ታማኝ፤ ለአገር ነጻነትና ሉዓላዊነት በተደረገ እንቅስቃሴ ከፊት ለፊት ለተሰለፈዉ ታላቁ የስልጤ ሕዝብ በሁሉም መመዘኛዎች ዉክልና ተነፍጓል።

ምናልባት ሰኔ 11/2012 የሲዳማ ክልል ስልጣንም በይፋ ሲረከብ ዉክልናዉ ወደዛ ሄዶ ይሆን?

ወይስ ህዳር 14፤ 2014 የደቡብ ምዕራብ ክልል ሲመሰረት የክልሉ ምክር ቤት አባላት ዉስጥ ሳናውቀዉ ስልጣንን አግኝተዉ ይሆን?

ዘንግተነዉ ከሆነ ደግሞ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አደረጃጀት ላይ ዉክልናችን ተቀምጦ ኖሯል?

ዉክልናችሁ ከላይ በተገለጹት በቀድሞ የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል በነበሩ ዞኖች ዉስጥ አይደለም ብላችሁ ከሞግታችሁ የት ነዉ ያለነዉ? ግራ ቢገባን፣ ባህልና እሴታችንን ማንነታችንና እምነታቻንን ፈልገን ፍልገን ብናጣዉ ወዴት ይሆን ብለን መፈለጋችን ነዉ።

በመጨረሻ የተዋቀረዉ የማዕክላዊ ኢትዮጵያ ዉስጥ ፍለጋችንን ቀጥለናል። ከ 54 ብሔረሰቦች የሚልቁበት የነበረዉ በቀድሞ የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ዉስጥ የማንነት፣ የባህልና እሴት ዉክልና የነበረዉ የስልጤ ታላቅ ሕዝብ በማዕክላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዉስጥ ማንነቱና እምነቱን፣ ሕዝቡና ትጋቱን፣ አቅምና ጉልበቱን... በዜሮ አባዝተዉ ሕዝባችን የማይቀብለዉና ሊቀበለዉ ያልፈቀደዉን ኢ-ሕገ መንግስታዊ መዋቅር ይፋ አድርገዋል።

ለቀድሞ የደቡብ ክልል እድገትና ብልጽግና፣ መሰረተ ልማትና፣ ከፍታና ጥንካሬ፣ ...ወዘተረፈ ለበርካታ ማህበራዊና ፖለቲካዊ መዳበር ከፍተኛ ድርሻ የነበረዉ የስልጤ ማህበረሰብ እነሆ በማዕክላዊ ኢትዮጵያ ክልል 1ድም የወሳኝና የሰዉ ኀይል አደረጃጀት ላይ ዉክልና አጥቶ የበይ ተመልካች ሆኗል።

ይህ ታላቅ ሕዝብ፣ ዉክልና ያጣበት የትኛዉም መዋቅር ከእድገት የሰነፈ፣ ከልማት የራቀ፣ ከመራጋጋትና ከሰላም የላቀ በመሆን ጉዞዉን ቁልቁል ማድረጉ እሙን ለመሆኑ ከፊት ለፊታችን የሚመጡት ጊዜያት የሚያሳዩ ይሆናል።

በሀገር ዉስጥና ከሀገር ውጪ፣ በከተማና በገጠር፣ በንግድና በትምህርት፣ በስልጣንም ላይ ይሁን ተራዉ ማሕበረሰብ የማዕክላዊ ኢትዮጵያ ክልል አደረጃጀትን እዉቅና ነፍጓል።

እንደማህበረሰብ ያልተቀበልነዉ አደራጀጀት ከማስተክከልና ከመከለስ ውጪ አማራጭ የለዉም። ይህን አልቀብልም ያለ አካል በህዝብ/በማህበረሰብ ላይ በግዴታ የመጫን/የማስገደድ/...አምባገነንነትን ለመመለስ የሚደረግ ሙከራ በመሆኑ ዳግም አምባገንነትን የማስቆም ስራ እንሰራለን! ኢንሻ አሏህ

#አምቤዉ
#ሀርዴ
#እለዉፈርና
#ቡቹኩል

Address

Addis Ababa
Ababa
NO

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Silta Mass Media posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share