TOSA MEDIA ጦሳ ሚዲያ

  • Home
  • TOSA MEDIA ጦሳ ሚዲያ

TOSA MEDIA ጦሳ ሚዲያ TOSA MEDIA is a social media platform which disseminates its news and programs world wide via you tube and face book

12/05/2024

ኩራታችን/ መልካም የእናቶች ቀን

የ98 አመቷ አዛውንት በተኩስ መሃል 10 ኪሎሜትር በእግር ተጉዘው ከሩሲያ ጦር አመለጡ::"ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ተርፌያለሁ፣ ከዚህም እየተረፍኩ ነው" ሲሉ ስቴፋኒቫ ተደምጠዋል::የ98 አ...
12/05/2024

የ98 አመቷ አዛውንት በተኩስ መሃል 10 ኪሎሜትር በእግር ተጉዘው ከሩሲያ ጦር አመለጡ::
"ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ተርፌያለሁ፣ ከዚህም እየተረፍኩ ነው" ሲሉ ስቴፋኒቫ ተደምጠዋል::
የ98 አመት አድሜ ያላቸው የዩክሬን አዛውንት ሴት በተኩስ መሀል 10 ኪሎሜትር ርቀት በእግር ተጉዘው ከሩሲያ ጦር ማምለጣቸው አነጋጋሪ ሆኗል።
አዛውንቷ አሁን በሩሲያ ቁጥጥር ስር ከወደቀችው ኦቸርታዮን ተነስተው የዩክሬን ጦር ወደተቆጣጠረው ቦታ መድረስ ችለዋል።
የዩክሬን ፖሊስ ሰኞ እለት በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በለቀቀው ቪዲዮ ሊዲያ ስቴፋኒቫ የተባሉት ሴት ያለምግብ እና ውሃ እየወደቁ እና እየተነሱ መድረሳቸውን ይናገራሉ።
"ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ተርፌያለሁ፣ ከዚህም እየተረፍኩ ነው" ሲሉ ስቴፋኒቫ ምርኩዝ ተደግፈው አልጋ ላይ ቁጭ ብለው ሲናገሩ ተደምጠዋል።
"ምንም የቀረኝ የለም፤ ቀየየን በእግሬ ተጉዤ ለቅቄያለሁ"።
አዛውንቷ ሩሲያ በሀገራቸው ዩክሬን ላይ እያካሄደች ያለው ጦርነት ከሁለተኛው የአየም ጦርነት ጋር እንደማይመሳሰል ተናግረዋል።
"ቤቶች እየተቃጠሉ ነው፤ ዛfoች እየተነቀሉ ነው"በማለት የአሁኑን ጦርነት አስከፊት ገልጸዋል።
የዩክሬን የሀገር ውስጥ ሚኒስትር በጽረ ገጹ ላይ ባወጣው መግለጫ ሴትዮዋ በዩክሬን ጦር በሌሊት መገኘታቸውን እና ተፈናቃዮቹ ወደሚጠለሉበት ለወሰዳቸው ፖሊስ መስጠታቸውን ገልጿል።
ሚኒስቴሩ "የህግ አስፈጻሚ አካላት የሴትዮዋን ቤተሰቦች እያፈላለጉ ነው" ብሏል።
በፈረንጆች የካቲት 2022 የተጀመረው የሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት አሁንም ቀጥሎ እየተካሄደ ነው።

ቻይና የግመል ትራንስፖርትን ለማሳለጥ የትራፊክ መብራት ተከለች::ሚንግሻ በሚባለው የቻይናው አሸዋማ ስፍራ በጎብኚዎች የሚወደድ ሲሆን ግመል ደግሞ ዋነኛ የትራንስፖርት አማራጭ ነው::የዓለማችን...
12/05/2024

ቻይና የግመል ትራንስፖርትን ለማሳለጥ የትራፊክ መብራት ተከለች::

ሚንግሻ በሚባለው የቻይናው አሸዋማ ስፍራ በጎብኚዎች የሚወደድ ሲሆን ግመል ደግሞ ዋነኛ የትራንስፖርት አማራጭ ነው::
የዓለማችን ቁጥር ሁለት ልዕለ ሀያል ሀገር የሆነችው ቻይና የግመል ትራንስፖርትን ለማሳለጥ የትራፊክ መብራት ተክላላች፡፡
ሀገሪቱ የግመል ትራንስፖርት መጨናነቅ በሚታይበት ሰሜን ምዕራባዊ የሀገሪቱ አካባቢዎች ነው፡፡
ጋንሹ ተብሎ የሚጠራው ይህ ግዛት አሸዋማ እና ደረቃማ አካባቢ ሲሆን በዚህ ወቅት የሀገር ውስጥ እና የውጭ ሀገራት ጎብኚዎች የሚያዘወትሩት ቦታ ነው፡፡
አካባቢው አሸዋማ በመሆኑ ምክንያትም የግመል ትራንስፖርት ዋነኛ አማራጭ ሲሆን በዚህ ጊዜ የትራንስፖርት መጨናነቅ እንዳይፈጠር የትራፊክ መብራት ተክላለች፡፡
በዚህ አሸዋማ ስፍራ ከ2 ሺህ 400 በላይ ግመሎች ለትራንስፖርት የተዘጋጁ ሲሆን በየዕለቱ በ10 ሺህ የሚቆጠሩ ጎብኚዎች ወደ ስፍራው እያቀኑ ነውም ተብሏል፡፡
በተለይም ሚንግሻ የሚባለውን ተራራ ለመጎብኘት ጎብኚዎች ይህን አሸዋማ ስፍራ ለማለፍ የግድ ግመልን መጠቀም ግዴታ እንደሆነ ተገልጿል፡፡
አሁን ላይ ሚንግሻ ተራራ በየቀኑ በ20 ሺህ እና ከዛ በላይ ጎብኚዎች እየገበኙት ነው የተባለ ሲሆን ለግመል ትራንስፖርት አቅራቢ ቻይናዊያን ወቅቱ ትልቅ እድል ፈጥሮላቸዋል ተብሏል፡፡
በትራፊክ መብራቱ መሰረትም አረንጓዴ ሲበራ ግመሎቹ የሚጓዙ ሲሆን ቀይ ሲበራ ደግሞ እግረኛ ሰዎች እንዲጓዙ እየተደረገ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡
ቻይናዊያን ሀገራቸውን በመጎብኘት ከሌላው ዓለም የተሻለ ልምድ አላቸው የተባለ ሲሆን በዓለም የሰራተኞች ቀን ብቻ 240 ቻይናዊያን ወደ ሚንግሻ ተራራ ለጉብኝት አምርተዋል ተብሏል፡፡

የትዳር ፖለቲካ
12/05/2024

የትዳር ፖለቲካ

26/04/2024

ሁለት ወደ ፊት አንዳንድ ወደ ኋላ

26/04/2024

አስገራሚ ነው!!

26/04/2024

እየመጣን ነው!! We're coming!!

25/04/2024

ውዳሴ ማርያም / በዛወርቅ አስፋው

አቶ ነብዩ ተድላ አምባሳደር መለስ አለምን በመተካት የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ ሆነው ተሾሙ ::አቶ ነብዩ ተድላ አምባሳደር መለስ ዓለምን በመተካት የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ ...
21/03/2024

አቶ ነብዩ ተድላ አምባሳደር መለስ አለምን በመተካት የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ ሆነው ተሾሙ ::
አቶ ነብዩ ተድላ አምባሳደር መለስ ዓለምን በመተካት የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ ሆነው ተሾሙ። አምባሳደር መለስ አለም በነብዩ ተድላ የተተኩት ለትምህርት ወደ ውጭ አገር በማምራታቸው መሆኑን አዲስ ስታንዳርድ ከታማኝ ምንጭ አረጋግጧል።
አምሳደር መለስ፤ በሴኔ 2014 የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ ሆነው ከመሾማቸው በፊት ከ2010 ዓ/ም ጀምሮ በ #ኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር በመሆን አገልግለዋል።
አምባሳደሩን በመተካት ዛሬ ሳምንታዊ መግለጫ የሰጡት ነብዩ ተድላ፤ በ እና ድርጅት የ #ኢትዮጵያ ሚሲዮን ሆነው በመስራት ልምድ ያካበቱ ዲፕሎማት ናቸው። በተጨማሪም በተጨማሪም በ እና የኢትዮጵያ ኤምባሲ ዲፕሎማት ሆነው አገልግለዋል።
በቅርቡ አምባሳደር ታየ አፅቀሥላሴ የቀድሞ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በመተካት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው መሾማቸው ይታወሳል።

21/02/2024

ተወዳጁ ጌታቸው ካሳ ነፍስህ በሰላም ትረፍ
አልበቃኝም ገና ጨርሶ፣
ቀንና ሌት ልቤ ገስግሶ፤

10 በከፍተኛ ድብርት ተጠቂ የአፍሪካ ሀገራት::በአፍሪካ ከ30 ሚሊየን በላይ ሰዎች በድብርት ምክንያት የአዕምሮ ጤናቸው መናጋቱ ይነገራል::በአለማቀፍ ደረጃ ከ280 ሚሊየን በላይ ሰዎች በከፍ...
21/02/2024

10 በከፍተኛ ድብርት ተጠቂ የአፍሪካ ሀገራት::
በአፍሪካ ከ30 ሚሊየን በላይ ሰዎች በድብርት ምክንያት የአዕምሮ ጤናቸው መናጋቱ ይነገራል::
በአለማቀፍ ደረጃ ከ280 ሚሊየን በላይ ሰዎች በከፍተኛ ድብርት ውስጥ እንደሚገኙ የአለም ጤና ድርጅት መረጃ ያሳያል።

በአፍሪካ ከ30 ሚሊየን በላይ ሰዎች በድብርት ምክንያት የአዕምሮ ጤናቸው መናጋቱ ይነገራል።
ዋይዝቮተር የተሰኘ የጥናት ተቋም ይፋ ባደረገው ጥናትም በአፍሪካ የሚከሰቱ የድብርት ህመሞች ከኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ጉዳዮች ጋር የተያያዙ መሆናቸውን ጠቅሷል።
ተቋሙ ባወጣው የአለማቀፍ የድብርት ምጣኔ ደረጃ ግሪክ፣ ስፔንና ፖርቹጋል ከፊት ተቀምጠዋል።
ከእስራኤል ጋር ጦርነት ውስጥ ያለችው ፍልስጤም፣ ቱኒዚያ፣ ባህሬን፣ ሞሮኮ፣ ኢራን፣ ሊዩቲኒይያ እና ዩክሬን እስከ 10ኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል።
የድብርት ህመም በተለያዩ ምክንያቶች እንደሚከሰት የሚነገር ሲሆን፥ በድንገት የሚከሰት ከባድ ሀዘን፣ አካላዊና ጾታዊ ጥቃቶች እንዲሁም ከማህበረሰብ መገለል ድብርት ከሚያስከትሉ ጉዳዮች በቀዳሚነት ይነሳሉ።
ሴቶችም ከወሊድ ጋር በተያያዘ ለድብርት ሊጋለጡ እንደሚችሉ ጥናቶች ያመለክታሉ።
የስራ አጥነት፣ የኑሮ ውድነትና ሌሎች ከኢኮኖሚ ጋር የተያያዙ ፈታኝ ጉዳዮችም ለድብርት በማጋለጥ ረገድ ትልቅ ድርሻ እንዳላቸው ነው አፍሪካ ቢዝነስ ኢንሳይደር የዘገበው።
ዋይዝቮተር የተሰኘ የጥናት ተቋም ይፋ ባደረገው ጥናትም በአፍሪካ የሚከሰቱ የድብርት ህመሞች ከኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ጉዳዮች ጋር የተያያዙ መሆናቸውን ጠቅሷል።
ድህነት፣ ስራ አጥነት፣ የብድር ጫና እና የዋጋ ንረት ከትምህርትና ጤና ክብካቤ አቅርቦት ክፍተት ጋር ተዳምረው የሚሊየኖችን ህይወት መረበሻቸውንና በርካቶችን ለድብርት ማጋለጣቸውን ነው ጥናቱ የሚያሳየው።
በአህጉሪቱ ስለድብርት ያለው ግንዛቤ አናሳ መሆንና ከአዕምሮ ጤና ጋር በተያያዘ ማህበረሰቡ የያዛቸው ልማዳዊ እሳቤዎች በድብርት የሚሰቃዩ ሰዎች ችግራቸውን ለመግለጽና መፍትሄ ለመፈለግ እንዲቸገሩ አድርጓል ይላል።
ዋይዝቮተር ባወጣው የአለማቀፍ የድብርት ምጣኔ ደረጃ ግሪክ፣ ስፔንና ፖርቹጋል ከ1ኛ እስከ 3ኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል። ሀገራቱ የገጠማቸው የኢኮኖሚ ቀውስም ዜጎቻቸው ለከፍተኛ ድብርት እንዲጋለጡ በማግረግ ቀዳሚውን ድርሻ ይወስዳል ተብሏል።
ኢትዮጵያን 133ኛ ደረጃ ላይ ያስቀመጠው ተቋሙ በአፍሪካ ከፍተኛ ድብርት የሚታይባቸውን 10 ሀገራት እና አለማቀፍ ደረጃቸውን እንደሚከተለው ዘርዝሯል፦
1. ቱኒዚያ - 5ኛ

2. ሞሮኮ - 7ኛ

3. ጋቦን - 15ኛ

4. ሊቢያ - 23ኛ

5. ዲአር ኮንጎ - 32ኛ

6. ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ - 36ኛ

7. ኢኳቶሪያል ጊኒ - 40ኛ

8. ሞሪሺየስ - 41ኛ

9. ኡጋንዳ - 47ኛ

10. ደቡብ አፍሪካ - 48ኛ

ሰላም የተከበራችሁ ቤተሰቦቻችን፤ለበርካታ ወራት በሙከራ ላይ የነበረው ‹‹ ጦሳ ሚዲያ ›› በተለያዩ የሚዲያ አማራጮች በሙሉ አቅም ለመውጣት ዝግጅታችንን ጨርሰናል፡፡በቀጣዩ ሊንክ በመግባት የጦ...
16/02/2024

ሰላም የተከበራችሁ ቤተሰቦቻችን፤ለበርካታ ወራት በሙከራ ላይ የነበረው ‹‹ ጦሳ ሚዲያ ›› በተለያዩ የሚዲያ አማራጮች በሙሉ አቅም ለመውጣት ዝግጅታችንን ጨርሰናል፡፡በቀጣዩ ሊንክ በመግባት የጦሳ ሚዲያ የዩቲዩብ ቻናልን ሰብስክራይብ በማድረግ አቅም እንድትሆኑን እንጠይቃለን፡፡
‹‹ ዕይታ በከፍታ›› ጦሳ ሚዲያ

well come to Tosa Media Tosa Media is a digital media platform. Visit our you tube channel and get daily news and entertainment programs

በደላንታ ቆሞ የነበረው 20 ማዕድን አውጪዎች ከገቡበት  ፍርስራሽ ውስጥ የማውጣት ስራውን ዳግም ለማስጀመር ጥረት እየተደረገ ነው ተባለ::በደቡብ ወሎ ደላንታ ወረዳ ኦፓል ለማውጣት በሚል በቁ...
16/02/2024

በደላንታ ቆሞ የነበረው 20 ማዕድን አውጪዎች ከገቡበት ፍርስራሽ ውስጥ የማውጣት ስራውን ዳግም ለማስጀመር ጥረት እየተደረገ ነው ተባለ::
በደቡብ ወሎ ደላንታ ወረዳ ኦፓል ለማውጣት በሚል በቁፋሮ ላይ የነበሩ 20 ወጣቶች መሬቱ ከተደረመሰባቸው ስምንት ቀን ሆኗቸዋል

በደላንታ ቆሞ የነበረው 20 ማዕድን አውጪዎች ከገቡበት ፍርስራሽ ውስጥ የማውጣት ስራውን ዳግም ለማስጀመር ጥረት እየተደረገ ነው ተባለ

በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን ደላንታ ወረዳ 018 ቀበሌ ልዩ ስሙ አለኋት ተብሎ በሚጠራ ስፍራ ነበር ኦፓል ማዕድን በማውጣት ላይ የነበሩ ወጣቶች መውጫ ስፍራ በአለት የተደፈነባቸው፡፡

ህጋዊ እውቅና ተሰጥቷቸው በማህበር ተደራጅተው ኦፓል በማውጣት ላይ የነበሩ እነዚህ ወጣቶች ቁጥራቸው 20 ሲሆን ከመሩት በህይወት ለማትረፍ የአካባቢው ማህበረሰብ እስከ የካቲት 6 ቀን 2016 ዓ.ም ተቋርጦ ነበር።

የደቡብ ወሎ ኮሙንኬሽን መምሪያ ሀላፊ አቶ እያሱ ዮሀንስ ለአልዐይን እንዳሉት የወጣቶቹን ህይወት ለመታደግ የወረዳው እና የአካባቢው ማህበረሰብ ሌት ተቀን በፈረቃ እየቆፈረ እንደነበር ነገር ግን መልክዓ ምድሩ ለቁፋሮ አመቺ አለመሆኑን ተከትሎ ተጨማሪ ሰው ላለማጣት በሚል ቁፋሮው ከአቅም በላይ ነው ተብሎ ቆሞ እንደነበር ተናግረዋል።

ይሁንና የደቡብ ወሎ ዞን አስተዳድር ለደላንታ ወረዳ ባደረገው የባለሙያ በደላንታ ቆሞ የነበረው 20 ማዕድን አውጪዎች ከገቡበት ፍርስራሽ ውስጥ የማውጣት ስራውን ዳግም ለማስጀመር ጥረት እየተደረገ ነው ብለዋል።
ወጣቶቹ ጥር 30 ቀን 2016 ዓ.ም ሌሊት ላይ ማዕድኑን ለማውጣት እየቆፈሩ እያሉ መውጫቸው በዓለት የተዘጋባቸው ሲሆን በአካባቢው በተመሳሳይ ስራ ላይ የተሰማሩ ወጣቶች ጉዳዩን ለህዝብ አሳውቀዋል፡፡
ከዚህ ቀን ጀምሮም ወጣቶቹን ለመታደግ የደላንታ ወረዳ እና የአካባቢው ማህበረሰብ በዘመቻ እየቆፈረ ነው የተባለ ሲሆን ወጣቶቹ ያሉት በግምት 750 ሜትር ርቀት ላይ ይሆናልም ተብሏል፡፡
እስካሁን በተደረገው ጥረትም ከ50 ሜትር በላይ ርቀት ቁፋሮ እንደተቆፈረ የተናገሩት ሀላፊው ቦታው አለታማ እና የቁፋሮ ማሽን ለማስገባት አመቺ አለመሆኑ ጥረቱን ፈታኝ አድርጎታል ሲሉም አክለዋል፡፡
ከሶስት ዓመት በፊት በተመሳሳይ ኦፓል ማዕድን በማውጣት ስራ ላይ የነበሩ10 ወጣቶች ተመሳሳይ አደጋ አጋጥሟቸው አራቱ በህይወት መገኘት ችለው ነበር ያሉት አቶ እያሱ በተደረገው ርብርብ ከ11 ቀናት እልህ አስጨራሽ ቁፋሮ በኋላ ሁሉንም ወጣቶች በህይወት ማግኘት መቻሉንም ተናግረዋል፡፡
አቶ እያሱ አክለውም ወጣቶቹን በህይወት ለማትረፍ እየተደረገ ያለው ጥረት አበረታች መሆኑን ተናግረው በመጪዎቹ ቀናት ውስጥ ሁሉንም ወጣቶች በህይወት ለመታደግ ተስፋ እንዳላቸውም ገልጸዋል፡፡

ዳቦ ለመግዛት ሱቅ የተላከውን የ8 ዓመት ልጅ አግተው ቤተሰቦቹን 1 ሚሊዮን ብር የጠየቁ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ:: በሸገር ከተማ አስተዳደር ሱሉልታ ክፍለ ከተማ ዳቦ ለመግዛት ሱቅ የተላ...
16/02/2024

ዳቦ ለመግዛት ሱቅ የተላከውን የ8 ዓመት ልጅ አግተው ቤተሰቦቹን 1 ሚሊዮን ብር የጠየቁ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ::

በሸገር ከተማ አስተዳደር ሱሉልታ ክፍለ ከተማ ዳቦ ለመግዛት ሱቅ የተላከውን የ8 ዓመት ህፃን ልጅ አግተው በመውሰድ ወላጆቹን 1ሚሊየን ብር የጠየቁ አምስት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የሱሉልታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ አስታወቀ፡፡
የሱሉልታ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የወንጀል ምርመራ ዋና ክፍል መርማሪ ም/ኢንስፔክተር ተርፌሳ ነጋሳ ለብስራት ሬድዮና ቴሌቪዥን እንደተናገሩት የወንጀል ድርጊቱ ጥር 8 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 1፡30 ላይ ተፈጽሟል፡፡ ዳቦ ለመግዛት ሱቅ የተላከው የ8 ዓመት ታዳጊ የእናቱ የቅርብ ዘመድ የሆነች ግለሰብ ችብስ እገዛልሀለው በማለት ወደ ጫንጮ ከተማ በድብቅ አንድ ቤት ውስጥ አግታ ወስዳዋለች፡፡
ተጠርጣሪዋ ግለሰብ ከሌሎች አራት ግብራበሮቿ ጋር በመሆን ያገቱትን የ8ዓመት ልጅ ከጫንጮ ከተማ ወደ ምዕራፍ ሸዋ ዞን ኤጀርሳ ለፎ በተባለ ወረዳ በድብቅ እንዳስቀመጡት ታዉቋል፡፡አንደኛ ተጠርጣሪ እና የታገተው ልጅ የቅርብ ዘመድ የሆነችው በምስራቅ ሸዋ ዞን አጀርሳ ለፎ ወረዳ ለሁለተኛ ተጠርጣሪ አስረክባ ወደ ሱሉልታ በመመለስ ሁኔታውን ስትከታተል እንደነበር ታውቋል፡፡
ሌሎች አራቱ ተጠርጣሪዎችም በተለያዩ ጊዜያት ለ8 ዓመቱ ልጅ እናት በመደወል 1ሚሊየን ብር በአስቸኳይ ካላመጣሽ ልጅሽን በህይወት አታገኚውም ብለው በማስፈራራታቸው ጉዳዩን ለፖሊስ ማሳወቋንም ተናግረዋል፡፡ፖሊስ ባደረገው ክትትል አንደኛ ተጠርጣሪ በጫንጮ ከተማ በቁጥጥር ስር ውላ የጠቆመቻቸው አራቱ ተጠርጣሪዎችም ካገቱት የ8 ዓመት ታዳጊ ልጅ ጋር በምዕራብ ሸዋ ዞን ኤጀርሳ ለፎ ወረዳ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተናግረዋል፡፡
የሱሉልታ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ተጠርጣሪዎቹ ላይ የምርመራ መዝገቡን አጠናቆ ለዓቃቢ ህግ የላከ ሲሆን በቅርብ ጊዜያትም በ5 ተጠርጣሪዎች ላይ ውሳኔ እንደሚሰጥ የሱሉልታ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የወንጀል ምርመራ ዋና ክፍል መርማሪ ም/ኢንስፔክተር ተርፌሳ ነጋሳ ጨምረው ለብስራት ሬድዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል፡፡

በአሜሪካ አንድ የቀዶ ጥገና ሮቦት ሐኪም በህክምና ስህተት ሰው ገድሏል::ለሕክምና ስህተቱ ሆስፒታሉ ሳይሆን ሮቦት ሐኪሙን የሰራው ኩባንያ ክስ ተመስርቶበታል::የዓለማችን ልዕለ ሀያል ሀገር በ...
11/02/2024

በአሜሪካ አንድ የቀዶ ጥገና ሮቦት ሐኪም በህክምና ስህተት ሰው ገድሏል::
ለሕክምና ስህተቱ ሆስፒታሉ ሳይሆን ሮቦት ሐኪሙን የሰራው ኩባንያ ክስ ተመስርቶበታል::
የዓለማችን ልዕለ ሀያል ሀገር በሆነችው አሜሪካ ሳንድራ ሱልትዘር የተሰኘች እንስት በፍሎሪዳ የምትኖር የአንጀት ህመም ተሰምቷል ነበር ወደ ሆስፒታል ያመራችው፡፡
በዚህ ሆስፒታል ውስጥ ተቀጥሮ የሚሰራ የቀዶ ጥገና ሮቦት ሐኪም ደግሞ ሳንድራን እንዲያክም ሀላፊነት ተሰጥቶት ነበር ይላል የኒዮርክፖስት ዘገባ፡፡
ይህ ሮቦት ሐኪምም ሳንድራን የአንጀት ቀዶ ህክምና አገልግሎት እየሰጣት እያለ በፈጸመው የሕክምና ስህተት ህይወቷ አልፏል ተብሏል፡፡
ሮቦት ሐኪሙ በሳንድራ ቀጭን አንጀት ላይ በፈጸመው ስህተት ምክንያት ለሞት ተዳርጋለች የተባለ ሲሆን ክሱ በባሏ እንደተመሰረተ ተገልጿል፡፡
ይህን ሮቦት ሰርቶ ለሆስፒታሉ የሸጠው ዳቪንቼ የተሰኘው የቴክኖሎጂ ኩባንያ ክሱ ተመስርቶበታል የተባለ ሲሆን ሮቦቱ ለሰራው ቸልተኝነት እና ጥራቱን ያልጠበቀ ምርት ወደ አገልግሎት በማስገባት ካሳ እንዲከፍልም ተጠይቋል፡፡
ሮቦቱ በታካሚዋ ላይ የህክምና ስህተት እንደፈጸመ ኩባንያው ያውቅ ነበር የተባለ ሲሆን ይህን አውቆ ታካማዊ ህይወቷ ከማለፉ በፊት ተጨማሪ ህክምና እንድትወስድ ለሆስፒታሉም ሆነ ለታካሚዋ አላሳወቀምም ተብሏል፡፡
ሮቦቱ የቀዶ ጥገናውን ሲያከናውን ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ሀይል ተጠቅሟል የተባለ ሲሆን በዚህ ምክንት ቀጭን አንጀቷ ላይ የከፋ ጉዳት እንዲደርስባት ማድረጉን ኩባንያው እያወቀ ሀላፊነቱን እንዳልተወጣ ተገልጿል፡፡

11/02/2024

አጼ ሚኒሊክ በAI ያስተላለፉት መልዕክት/ኢትዮጵያ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የደረሰችበት ደረጃ

ቴዲ አፍሮ በመኪና አደጋ ይሞታል፡ያለው ፓስተር ራሱ በመኪና አደጋ ሞተ።በዲላ ከተማ ሰፊ የሆነ የህዝብ አመኔታን ያተረፈው ፓስተር ጆ ፡ቴዲ አፍሮ በ2016 ዓ.ም ይሞታል ብሎ የተናገረ ቢሆንም...
11/02/2024

ቴዲ አፍሮ በመኪና አደጋ ይሞታል፡ያለው ፓስተር ራሱ በመኪና አደጋ ሞተ።
በዲላ ከተማ ሰፊ የሆነ የህዝብ አመኔታን ያተረፈው ፓስተር ጆ ፡ቴዲ አፍሮ በ2016 ዓ.ም ይሞታል ብሎ የተናገረ ቢሆንም ፤በዛሬው ዕለት ከዲላ ወደ አዲስ አበባ በገዛ መኪናው በመጓዝ ላይ ሳለ በደረሰበት የመኪና አደጋ ህይወቱ ማለፉ ታውቋል።
ፓስተር ጆ የ 34 ዓመት ወጣት'የአንድ ሴት ልጅ አባት ነው።
Via - Roha Media

በደቡብ ወሎ በኦፓል ማዕድን ማውጫ ጉድጓድ ውስጥ የተቀበሩ ሰዎች ሦስት ቀን ሆናቸው::በአማራ ክልል በደቡብ ወሎ ዞን ደላንታ ወረዳ የኦፓል ማዕድን በማውጣት ላይ ሳሉ ዋሻ የተደረመሰባቸውን በ...
11/02/2024

በደቡብ ወሎ በኦፓል ማዕድን ማውጫ ጉድጓድ ውስጥ የተቀበሩ ሰዎች ሦስት ቀን ሆናቸው::
በአማራ ክልል በደቡብ ወሎ ዞን ደላንታ ወረዳ የኦፓል ማዕድን በማውጣት ላይ ሳሉ ዋሻ የተደረመሰባቸውን በርካታ ሰዎች ለማትረፍ የሚደረገው ጥረት ያለ ውጤት ለሦስተኛ ቀን መቀጠሉን የአካባቢው ባለሥልጣናት ለቢቢሲ ተናገሩ።
በአካባቢው ባለው አስቸጋሪ መልክዓ ምድራዊ ሁኔታ ምክንያት ቁፋሮ በተሽከርካሪ ማድረግ ባለመቻሉ በዚህ መስክ ልምድ እና መሳሪያ ያላቸው ለነፍስ አድን ጥረቱ ላይ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።
ሐሙስ ጥር 30/2016 ዓ.ም. ሌሊት የኦፓል ማዕድን በቁፋሮ ለማውጣት ሲሞክሩ ነበር የተባሉ ማዕድን አውጭዎች ላይ ዋሻው ተንዶ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ሰዎች የተቀበሩ ሲሆን፣ ስላሉበት ሁኔታ እስካሁን የታወቀ ነገር የለም።
የደቡብ ወሎ ዞን ኮሚዩኒኬሽን በገደላማ አካባቢ ያለው የማዕድን ማውጫ ዋሻ የተደረመሰባቸው ሰዎች ቁጥር ከ20 በላይ ነው ያለ ሲሆን፣ የአካባቢው ባለሥልጣናት ግን ትክክለኛው አሃዝ ማወቅ አስቸጋሪ ነው ይላሉ።
የዋሻው መደርመስ አደጋ ያጋጠመው ባለፈው ሐሙስ ለአርብ አጥቢያ ከሌሊቱ ስድስት ሰዓት በኋላ እንደነበረ ለቢቢሲ የተናገሩት የደላንታ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አያሌው በሪሁን፣ የሰዎቹን ሕይወት ለማትረፍ ላለፉት ሦስት ተከታታይ ሌት እና ቀን ጥረት እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።
አደጋው የደረሰው በደቡብ ወሎ ዞን ደላንታ ወረዳ ውስጥ በምትገኘው 018 አለኋት ተብላ በምትጠራ ቀበሌ ውስጥ ቆቅ ውሃ በተባለ ስፍራ ላይ ነው።
ዋሻው ተደርምሶ የተቀበሩት ሰዎች በሌሊት ወደ ስፍራው መሄዳቸው ለአደጋው መከሰት እና ቁጥራቸውም በትክክል ላለመታወቁ ምክንያት መሆኑን አስተዳዳሪው ተናግረዋል።
የደቡብ ወሎ ዞን ዋና አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ አሊ መኮንን ለቢቢሲ እንደገለጹት አካባቢው ገደላማ በመሆኑ እና ከዚህ ቀደም የኦፓል ማዕድን ለማውጣት የተቆፈሩት ዋሻዎች አደገኛ በመሆናቸው ለአካባቢው ነዋሪዎች ማስጠንቀቂያ ሲሰጥ ነበር።
የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ አያሌው፤ አደጋው መከሰቱ ከታወቀ በኋላ የአካባቢው ነዋሪ በዋሻው ስር የተቀበሩትን ሰዎች ሕይወት ለማትረፍ ጥረት እያደረገ ቢሆንም ከስፍራው መልክዓ ምድራዊ አቀማመጥ አስቸጋሪነት የተነሳ የሚፈለገውን ያልህ መንቀሳቀስ እንዳልተቻለ አመልክተዋል።
ባለፉት ቀናት ከአምስት መቶ በላይ ሰዎች በነፍስ አድን ሥራው ላይ እገዛ ለማድረግ ወደ ስፍራው ቢያቀኑም ወደ ዋሸው ለማምራት የሚያስችለው መንገድ ጠባብ እና በአንድ ጊዜ ከአስር ሰዎች በላይ ማስገባት ባለመቻሉ ጥረታቸው አዝጋሚ ሆኗል።
በተጨማሪም ከዚህ በፊት በተደረጉ ቁፋሮዎች ምክንያት የአካባቢው የመሬት አቀማመጥ ጠንካራ ባለመሆኑ የነፍስ አድን ጥረት በሚያደርጉት ሰዎች ላይ ጭምር አፈሩ ስለሚናድ ሌላ ስጋት መፍጠሩን አቶ አያሌው አመልክተዋል።
የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ አሊ መኮንን የቁፋሮ ሥራውን በማሽን ለማገዝ ፍላጎት ቢኖርም የአካባቢው ገደላማነት “እንኳን ቆፋሪ ተሽከርካሪን ቀርቶ ሰዎችን በበቂ ሁኔታ ለማስገባት አመቺ አይደለም” ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
ከአደጋው መከሰት በኋላ ወደ ዋሻው በሌሊት አምርተዋል የተባሉ ሰዎች ቁጥር ግምት ከ10 በታች ሲሆን፣ ከነዋሪዎች በኩል የተለያዩ አሃዞች እንደሚወጡ የወረዳው አስተዳዳሪ ገልጸዋል።
በአካባቢው ከሚገኙ ነዋሪዎች በተጨማሪ ከአጎራባች ቦታዎች የኦፓል ማዕድን ለማውጣት የመጡ ሰዎች ሊኖሩ እንደሚችል የታመነ ሲሆን፣ ቁጥሩን ግን ይህ ነው ብሎ ለመናገር አዳጋች መሆኑን አቶ አያሌው ለቢቢሲ ተናግረዋል።
ነገር ግን ሰዎች የጠፉባቸው ነዋሪዎች ምናልባት በዋሻ ውስጥ ሊሆኑ እንደሚችሉ በመገመት ወደ ስፍራው እንደሚመጡ አመልክተዋል።
የዞኑ ኮሚዩኒኬሽን ግን “ከ20 በላይ ወጣቶች” በዋሻው ውስጥ ተቀብረዋል ብሏል።
የተደረመሰው ዋሻ ከ750 ሜትር በላይ ርዝመት ያለው መሆኑ የተነገረ ሲሆን፣ ውስጥ ሳሉ የተደረመሰባቸውን ሰዎች ለማውጣት ለዋሻው መግቢያ ቅርበት ባለው የውስጠኛ ክፍል በኩል ቁፋሮ እየተደረገ መሆኑን ሁለቱም የአካባቢው ባለሥልጣናት ተናግረዋል::
የአካባቢው አስተዳዳሪዎች ከነዋሪዎች ጋር በመሆን ከሚንሸራተተው አፈር ጋር እየታገሉ አርብ እና ቅዳሜ በተደረጉ ቁፋሮዎች ወደ ዋሸው ውስጥ ብዙም ለመዝለቅ ባለመቻላቸው እስካሁን ውጤት እንዳላገኙ ተገልጿል።
የአካባቢው ዋና አስተዳዳሪ አቶ አያሌው በሪሁን “ሰው ከመሬት በታች ከእነ ሕይወቱ ተቀብሮ ያለንበት ሁኔታ እጅግ አሳዛን ነው” በማለት ከመሬት በፍርስራሽ የተቀበሩ ሰዎችን በማውጣት ልምድ እና ቴክኖሎጂ ያላቸው ወገኖች በፍጥነት ድጋፍ እንዲያደርጉላቸው ተማጽነዋል።
በደቡብ ወሎ ዞን ውስጥ የሚገኘው የደላንታ ወረዳ ለጌጣጌጥ ሥራ ተፈላጊ የሆነው የኦፓል ማዕድን የሚገኝበት ስፍራ ሲሆን፣ በርካታ ሰዎች ደኅንነቱ ባልተጠበቀ ሁኔታ ማዕድኑን በማውጣት ለገበያ ያቀርባሉ።
በዚህም አካባቢ የኦፓል ማዕድን ማውጫ ጉድጓድ ተደርምሶ በሰው ላይ ጉዳት ሲያደርስ የመጀመሪያው አለመሆኑን የደላንታ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አያሌው አስታውሰው፣ ከዚህ በፊት በሕይወት እና በአካል ላይ ጉዳት ደርሷል ብለዋል።
በአንድ ወቅም ዋሻ ተደርምሶበት ለሰባት ቀናት የቆየ ግለሰብ በቁፋሮ መውጣቱን በማንሳት አሁን አደጋው የደረሰበት አካባቢ ምንም እንኳን አስቸጋሪ ሁኔታዎች ያሉበት ቢሆንም፣ ሰዎቹ በሕይወት እንደሚተርፉ ተስፋ አድርገዋል።
ሦስተኛ ቀኑን የያዘው የነፍስ አድን ጥረት የሚፈለገውን ያህል እንዳልተፋጠነ በመጥቀስ ከነዋሪው ጋር በመሆን በቻሉት አቅም ሁሉ የተቀበሩትን ሰዎች ሕይወት ለማትረፍ ጥረታቸው እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

ትራምፕ ሩሲያ የኔቶ አባልነት ክፍያቸውን የማይፈጽሙ አገራትን እንድታጠቃ “አበረታታለሁ” አሉ::ዶናልድ ትራምፕ በምዕራባዊያን ወታደራዊ ጥምረት ሕግ ገንዘብ የማይከፍሉ የሰሜን አትላንቲክ ጦር ...
11/02/2024

ትራምፕ ሩሲያ የኔቶ አባልነት ክፍያቸውን የማይፈጽሙ አገራትን እንድታጠቃ “አበረታታለሁ” አሉ::
ዶናልድ ትራምፕ በምዕራባዊያን ወታደራዊ ጥምረት ሕግ ገንዘብ የማይከፍሉ የሰሜን አትላንቲክ ጦር ትብብር ማኅበር (ኔቶ) አባል አገራትን እንድታጠቃ “እንደሚያበረታቱ” ተናገሩ።
በአንድ ወቅት ለኔቶ ኃላፊ ክፍያቸውን የማይፈጽሙ አባላት በሩሲያ ጥቃት ቢደርስባቸው ጥበቃ አናደርግም ብያቸዋለሁ የሚሉት ትራምፕ ሩሲያ “የፈቀደችውን እንድታደርግ እንደሚያበረታቱ” ተናግረዋል።
የኔቶ ቃለ-መሐላ እንደሚለው አንድ አባል አገር ጥቃት ቢደርስባት ጥምረቱ እርምጃ ይወስዳል።
ዋይታ ሐውስ የቀድሞው ፕሬዝዳንት የሰጡት አስተያየት “አስገራሚ እና አስፈሪ ነው” ብሏል።
ቅዳሜ ዕለት በሳውዝ ካሮላይና ግዛት ለደጋፊዎቻቸው ንግግር ያሰሙት ትራምፕ፣ ስለኔቶ አስተያየት የሰጡት በጥምረቱ ስብሰባ ላይ እንደሆነ ገልጸዋል።
እሳቸው እንደሚሉት የአንድ “ትልቅ አገር” መሪ ክፍያ መፈጸም ባይችል እና ከሩሲያ ጥቃት ቢፈጸምበብ ምን ሊገጥመን ይችላል ብለው ጥያቄ አቅርበው ነበር።
አክለው እኒህ መሪ ይህ ቢሆን ዩናይትድ ስቴትስ ታግዘናለች ወይ ብለው መጠየቃቸውን አውስተዋል።
“እኔ እንዲህ አልኩ፡ 'መክፈል አትችልም?' 'አቅምህ አይችልም?'፤ እኔ ልጠብቅህ አልችልም፤ እንዲያውም የፈለጉትን እንዲያደርጉ ነው የምገፋፋቸው። መክፈል አለብህ።”
የዋይት ሐውስ ቃል አቀባይ የቀድሞው ፕሬዝዳንት “ጨካኝ አመራሮች አጋሮቻችንን እንዲወሩ እያበረታቱ ነው” ብለው አስተያየታቸው “አስገራሚ እና አስፈሪ ነው” መሆኑን ተናግረዋል።
ቃል አቀባዩ አክለውም የቀድሞው ፕሬዝዳንት አስተያየት “የአሜሪካን ብሔራዊ ደኅንነት አደጋ ላይ የሚጥል፤ ዓለም አቀፍ መረጋጋትን የሚያቃውስ እና ኢኮኖሚያችንን የሚያናጋ ነው” ብለዋል።
ሪፐብሊካን ፓርቲን ወክለው በሚቀጥለው ዓመት በሚደረገው የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እንደሚሳተፉ ትልቅ ግምት የተሰጣቸው ትራምፕ የኔቶ ነቃፊ ናቸው።
ኔቶን አሜሪካ የ30 አገራትን ደኅንነት ለመጠበቅ በርካታ ሚሊዮን ዶላሮች የምትገፈግፍበት ጥምረት ነው ብለው ያስባሉ።
ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከሥልጣን ከወረዱ በኋላ ነው ሩሲያ በአውሮፓውያኑ 2022 በሙሉ ኃይሏ ዩክሬንን የወረረችው።
ጦርነቱ ከተጀመረ በኋላ የኔቶ አባል ላልሆነችው ዩክሬን አሜሪካ የሰጠችው ድጋፍ ከፍተኛ ነው ሲሉ በተጋጋሚ ትችት አሰምተዋል።
አሜሪካ ከየትኛው አገር በላቀ ለዩክሬን ትልቅ የገንዘብ ድጋፍ አድርጋለች።
ጦርነቱ ከተጀመረ በኋላ ባለው ጊዜ ብቻ አሜሪካ ለዩክሬን 44 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ ማድረጓን ባለፈው ታኅሣሥ ዋይት ሐውስ ያወጣው ዘገባ ያሳያል።
ነገር ግን የአሜሪካ ኮንግረስ የሪፐብሊካን ፓርቲ አባላት ከያዝነው የአውሮፓውያኑ ዓመት ጀምሮ አሜሪካ የምታደርገው ድጋፍ እንዲቋረጥ አድርገዋል።
ትራምፕ በቅዳሜው ንግግራቸው የኮንግረስ አባላት የወሰዱትን እርምጃ አወድሰው የፕሬዝዳንት ባይደን ዕቅድ “ድብልቅልቅ ያለ ነው” ሲሉ ተችተዋል።
የቀድሞው ፕሬዝዳንት ትራምፕ እና የወቅቱ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በሚቀጥለው የአሜሪካ ምርጫ እንደሚፋጠጡ ይጠበቃል።

የቀድሞው የኔዘርላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር እና ሚስታቸው በአንድ ጊዜ ህይወታቸው አለፈ::ኔዘርላድን ለአምስት ዓመታት በጠቅላይ ሚኒስትርነት የመሩት ድራይስ ቫን አጅት እና ሚስታቸው በ93 ዓመታቸ...
10/02/2024

የቀድሞው የኔዘርላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር እና ሚስታቸው በአንድ ጊዜ ህይወታቸው አለፈ::
ኔዘርላድን ለአምስት ዓመታት በጠቅላይ ሚኒስትርነት የመሩት ድራይስ ቫን አጅት እና ሚስታቸው በ93 ዓመታቸው ህይወታቸው አልፏል::
ባልና ሚስቶቹ በሆስፒታል እጅ ለእጅ እንደተያያዙ ባንድ ጊዜ ህይወታቸው አልፏል ተብሏል::
ድራይስ ቫን አጅት አውሮፓዊቷ ኔዘርላንድን ከፈረንጆቹ 1977 እስከ 1982 ባሉት አምስት ዓመታት ውስጥ በጠቅላይ ሚኒስትርነት አገልግለዋል፡፡
በቀዝቃዛው ጦርነት ወቅት ኔዘርላንድ ገለልተኛ አቋም እንድትይዝ አድርገዋል በመባል የሚታወቁት እኝህ ጠቅላይ ሚኒስትር በተወለዱ በ93 ዓመታቸው ህይወታቸው እንዳለፈ የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል፡፡
ለ70 ዓመታት ያህል በትዳር የኖሩት እነዚህ ባልና ሚስቶች በእድሜ ምክንት በተከሰተ የማይድን በሽታ ተጠቅተው ነበር የተባለ ሲሆን በህክምና እርዳታ ከዚህ ዓለም እንዲገላገሉ ተደርገዋልም ተብሏል፡፡
የህክምና ባለሙያዎች በሶስት ልጆቻቸው ፈቃደኝነት ሁለቱን ባልና ሚስቶች እጅ ለእጅ እንደተያያዙ ከስቃይ እንዲያርፉ እና ህይወታቸው እንዲያልፍ ማድረጋቸው ተገልጿል፡፡
በበርካታ የአውሮፓ ሀገራት በማይድን ስቃይ እና ህመም ውስጥ ያሉ ሰዎች በራሳቸው ፈቃድ አልያም በቤተሰባቸው መልካም ፈቃድ አማካኝነት ህይወታቸው እንዲያልፍ የሚፈቅድ ህግ ያላቸው ሲሆን ኔዘርላንድም ይህን ህግ ካጸደቁ ሀገራት መካከል አንዷ ናት፡፡
የኔዘርላንድ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ቫን አጅት የእስራኤል ደጋፊ የነበሩ ሲሆን በ1999 ወደ ቴልአቪቭ ተጉዘው ከጎበኙ በኋላ ግን በይፋ ድጋፋቸውን ለፍልስጤም አድርገው ቆይተዋል፡፡
ከጉብኝታቸው በተጨማሪም ለፍልስጤማዊያን ነጻነት የሚያግዝ ተቋም የመሰረቱ ሲሆን አውሮፓዊን ፍልስጤምን እንዲደግፉ ጥሪ ሲያደርጉም ነበር፡፡
የኔዘርላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ማርክ ሩት በእሳቸው የአመራር ጊዜ በሳል ውሳኔዎችን እንዳሳለፉ እና ሀገራቸው በእሳቸው እንደምትኮራ ተናግረዋ

የቻይና ሳይንቲስቶች ህጻን አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሰሩ::ይህች ህጻን ከአራት ዓመት እውነተኛ ህጻን ጋር ተመሳሳይ ባህሪ አላት ተብሏል::በቤጂንግ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የተሰራች...
10/02/2024

የቻይና ሳይንቲስቶች ህጻን አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሰሩ::
ይህች ህጻን ከአራት ዓመት እውነተኛ ህጻን ጋር ተመሳሳይ ባህሪ አላት ተብሏል::
በቤጂንግ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የተሰራችው ይህች አዲስ ፈጠራ ለመጀመሪያ ጊዜ በአውደርዕይ ላይ ለጎብኚዎች ቀርባለች
የወቅቱ የቴክኖሎጂ ፉክክር የሆነው አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ወይም ሰው ሰራሽ አስተውሎት በየሀገሩ አዳዲስ ፈጠራዎች ይፋ እየሆኑ ሲሆን ቻይናም የመጀመሪያውን ህጻን አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ይፋ አድርጋለች፡፡
ህች ህጻን ከሶስት እስከ አራት ዓመት እድሜ ካላት እውነተኛ የሰው ልጅ ጋር ተቀራራቢ አስተሳሰብ ይኖራታልም ተብሏል፡፡
አዲሱ ፈጠራ የህጻናትን ባህሪ ለማጥናት አይን ገላጭ ይሆናል የተባለ ሲሆን ህች ህጻን የራሷ የሆነ ደስታ፣ ሀዘን እና ንዴት አይነት ስሜቶች እንዳላትም ተገልጿል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም ይህች አዲስ ፈጠራ ከሰዎች ጋር መግባባት እንድትችል ተደርጋ ተሰርታለች የተባለ ሲሆን የሰዎችን አካላዊ እንቅስቃሴ እና ቃላት ልውውጥ መሰረት አድርጋ ምላሽ ትሰጣለችም ተብሏል፡፡
የቤጂንግ ጠቅላላ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በቀጣይ ተጨማሪ ማሻሻያዎችን በማድረግ ቀስ በቀስ ሌሎች ፈጠራዎችን ይፋ እንደሚያደርግም አስታውቋል፡፡
ለዓለማችን ስጋት ሆናል የተባለው አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ጥብቅ ቁጥጥር ካልተደረገበት ለሰው ልጆች መጥፋት ምክንት ሊሆን እንደሚችል ተመራማሪዎች በተደጋጋሚ ማስጠንቀቃቸው ይታወሳል፡፡
በፈረንጆቹ 2050 ላይም 40 በመቶ የዓለማችን ስራዎች በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ እንደሚያዙ ከአንድ ወር በፊት የተካሄደው የዓለም ኢኮኖሚ ጉባኤ አስታውቆ ነበር፡፡

ማዳጋስካር ለአካለ መጠን ያልደረሱ ህጻናትን የሚደፍሩ ወንዶች ብልት እንዲሰለብ ሕግ አወጣች::ማዳጋስካር ለአካለ መጠን ያልደረሱ ህጻናትን በመድፈር ጥፋተኛ የተባሉ ወንዶች ብልት እንዲሰለብ ያ...
09/02/2024

ማዳጋስካር ለአካለ መጠን ያልደረሱ ህጻናትን የሚደፍሩ ወንዶች ብልት እንዲሰለብ ሕግ አወጣች::
ማዳጋስካር ለአካለ መጠን ያልደረሱ ህጻናትን በመድፈር ጥፋተኛ የተባሉ ወንዶች ብልት እንዲሰለብ ያወጣችው ሕግ እንዲሻር ተጠየቀ።
አገሪቷ ህጻናትን በመድፈር ጥፋተኛ ሆነው የተገኙ ግለሰቦች በኬሚካል እና ቀዶ ህክምና ብልታቸው እንዲሰለብ ሕግ ማውጣቷ ተቀባይነት እንደሌለው ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋም አምነስቲ አስታውቋል።
ሕጉንም “ኢ ሰብዓዊነትን የተላበሰ፣ ጭካኔ የተሞላበት እና የሰውን ልጅ የሚያዋርድ ነው” ሲል አምነስቲ ፈርጆታል።
ባለፈው ወር የአገሪቱ ፕሬዚዳንት አንድሪ ራጆሊካ በወንጀለኛ መቅጫ ሕጉ ላይ ማሻሻያዎችን አቅርበዋል።
በዚህም ማሻሻያ መሰረት ለአካለ መጠን ያልደረሱ ህጻናትን በመድፈር ጥፋተኛ ሆነው የተገኙ ግለሰቦች በኬሚካል እና በቀዶ ህክምና ብልታቸው እንዲሰለብ የሚጠይቅ ቅጣት ነው።
እነዚህ ማሻሻያዎችም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ዘንድ ተቀባይነትን አግኝተዋል።
በማዳጋስካር የመደፈር ወንጀሎች በአብዛኛው ሪፖርት እንደማይደረጉ አምነስቲ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
ይህም ተጎጂዎች እና ቤተሰቦቻቸው የበቀል ጥቃት ይደርስብናል በሚል ስጋት፣ ማኅበረሰቡ ያገለናል እንዲሁም በፍትህ ሥርዓቱ ላይ እምነት በማጣት እንደሆነም የአምነስቲ የምስራቅ እና ደቡባዊ አፍሪካ ዳይሬክተር ቲገሬ ቻጉታህ ገልጸዋል።

በዚህም ምክንያት ወንጀለኞች ነጻ የሚሆኑበት ሁኔታ መንሰራፋቱን አውስተዋል።
ሆኖም ለአካለ መጠን ያልደረሱ ህጻናትን በመድፈር ጥፋተኛ ሆነው የተገኙ ግለሰቦችን በኬሚካል እና በቀዶ ህክምና ብልታቸውን በመስለብ መቅጣት “ኢ ሰብዓዊነትን የተላበሰ፣ ጭካኔ የተሞላበት እና የሰውን ልጅ የሚያዋርድ እና ችግሩንም የማይቀርፍ ነው” ሲሉም ነው ዳይሬክተሩ የገለጹት።
ዳይሬክተሩ አክለውም “ይህ ሕግ ማሰቃየትን እና ሌሎች እንግልቶችን ተግባራዊ በማድረግ ቀጠናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ድንጋጌዎችን የሚጥስ ነው” ብለዋል።
“የሰብዓዊ መብት ድንጋጌዎችን የሚጣረስ እንዲሁም ከማዳጋስካር ሕገ መንግሥታዊ ድንጋጌዎች ጋር የሚቃረን ነው” ሲሉም አጽንኦት ሰጥተውታል።

09/02/2024

እቴ ይስጥሽ ----በእውቀቱ ስዩም

ቱርካዊቷ በሳምንት አንዴ እንኳን ሰውነቱን አይታጠብም ያለችውን ባሏን ፍቺ ጠይቃለች::ተከሳሹ ለአምስት ተከታታይ ቀናት ልብሱን አይቀይርም የሚል ክስም ከሚስቱ ቀርቦበታል::ክሱን የተመለከተው ...
09/02/2024

ቱርካዊቷ በሳምንት አንዴ እንኳን ሰውነቱን አይታጠብም ያለችውን ባሏን ፍቺ ጠይቃለች::
ተከሳሹ ለአምስት ተከታታይ ቀናት ልብሱን አይቀይርም የሚል ክስም ከሚስቱ ቀርቦበታል::
ክሱን የተመለከተው ፍርድቤትም የፍቺ ጥያቄውን ተቀብሎ፥ ተከሳሹ 16 ሺህ 500 ዶላር ካሳ እንዲከፍል ወስኗል::
የስሟ የመጀመሪያ ፊደሎች “ኤ ዋይ” መሆናቸው የተነገረላት ሚስት ያቀረበችው ክስ በአንካራ በሚገኘው 19ኛ የቤተሰብ ችሎት እየታየ መሆኑን የቱርክ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
“ባሌ በሰባት ወይም አስር ቀናት ውስጥ አንዴ ብቻ ነው ሰውነቱን የሚታጠበው፤ ላብ ላብ ይሸታል፤ አንድ ልብስን ከአምስት ቀናት በላይ ሳይቀይር ይለብሳል፤ ጥርሱንም በሳምንት አንዴ ወይ ሁለቴ ነው የሚቦርሸው” ብላለች ከሳሽ ሚስት።
በዚህም ጤናዋም ሆነ ትዳራቸው አደጋ ላይ መውደቁን በመጥቀስ ፍቺ መጠየቋ ተሰምቷል። ምስክር ሆነው የቀረቡት የጋራ ወዳጆቻቸውና የስራ ባልደረቦቹም ግለሰቡ ንጽህናውን እንደማይጠብቅ በአንድ ቃል መመስከራቸው ነው የተነገረው።
ግለሰቡ ንጽህናውን አለመጠበቁ በስራ ቦታም ቅሬታ መፍጠሩን ባልደረቦቹ ለፍርድቤት አስረድተዋል።
ክሱን የተመለከተው ችሎትም የፍቺ ጥያቄ ተቀብሎ የግል ንጽህናውን ባለመጠበቅ ትዳሩ የፈረሰበት ባል 500 ሺህ የቱርክ ሊራ ወይም 16 ሺህ 500 ዶላር ካሳ እንዲከፍል ወስኗል።
የከሳሿ ጠበቃ ሰነም ዪልማዘል “የትዳር አጋሮች በጋራ ለሚመሩት ህይወት ሃላፊነት አለባቸው፤ የግል ንጽህናን አለመጠበቅ ለፍቺ ሊዳርግ እንደሚችል ማወቅ ተገቢ ነው” ሲሉ ለቱርኩ ጋዜጣ ሳባህ ተናግረዋል።
ሰውነትን ያለመታጠብና ንጽህናን ያለመጠበቅ ጉዳይ በተደጋጋሚ ለትዳር መፍረስ ምክንያት ሲሆን ይታያል።

የታዋቂው እግርኳስ ተጨዋች ፔሌ ልጅ ነኝ ያለች ሴት አስከሬኑ ተቆፍሮ እንዲወጣ ጠየቀች።የታዋቂው ብራዚላዊ እግርኳስ ተጨዋች ፔሌ ልጅ ነኝ ያለች ሴት አስከሬኑ ተቆፍራ እንዲወጣ እና የዲኤንኤ ...
09/02/2024

የታዋቂው እግርኳስ ተጨዋች ፔሌ ልጅ ነኝ ያለች ሴት አስከሬኑ ተቆፍሮ እንዲወጣ ጠየቀች።
የታዋቂው ብራዚላዊ እግርኳስ ተጨዋች ፔሌ ልጅ ነኝ ያለች ሴት አስከሬኑ ተቆፍራ እንዲወጣ እና የዲኤንኤ ወይም የዘረመል ምርምራ እንዲካሄድ ጠይቃለች።
ስካይ ኒውስ የብራዚል ሚዲያን ጠቅሶ እንደዘገበው ማሪያ ዶ ሶኮሮ አዝቬዶ የተባለች ሴት የፔሌ ስምንተኛ ልጅ መሆኗን እና ለልጆቹ ከሰጠው 60 በመቶ ሀብት ድርሻ እንደሚገባት ተናግራለች።
በሙሉ ስሙ ኢድሰን አራንቴስ ዶ ናሲሜንቶ በመባል የሚታወቀው ባለፈው ታህሳስ ወር ህይወቱ ያለፈው ፔል በንዛዜ ወቅት ስምንት ልጆች እና አንድ በአካል ያላገኛት ሴት ልጅ እንዳለችው ተናግሯል ተብሎ ይታመናል።
ፔሌ የአባትነት ምርምራ ለማድረግ ተስማምቶ የነበረ ቢሆኖም፣ ምርመራው ሳይካሄድ በመሞቱ ምክንያት የማሪያ የህግ ጠበቃ አስከሬኑ ተቆፍሮ እንዲወጣ ሊጠይቅ ችሏል።
ነገርግን የሶስት ጊዜ የአለም ዋንጫ አሸናፊ የሆነው ፔሌን ባለቤት የወከለው ጠበቃ ጥያቄው "ምክንያታዊ ያልሆነ" እና "የማይሆን" ነው ብሏል።
ስለጉዳዩ ለመጀመሪያ ጊዜ በአደባባይ የተናገረችው ማሪያ እናቷ ማርገዟን ለፔሌ በፍጹም አልነገረችውም ብላለች።
ማሪያ በፈረንጆቹ 2019 ምርመራ እንዲደረግ ፈልጋ የነበረ ቢሆንም፣ በኮኖና ወረርሽኝ እና በፔሌ የጤና ችግር ምክንያት ሳይሳካ ቀርቷል።
ከፔሎ ልጆች አንዱ የሆነው እና የውርስ ጉዳዩን በበላይነት የሚመራው ኢዲንሆ "ምርመራው ተካሂዶ እህታችን አለመሆኗ ተረጋግጧል" የሚል መልስ ሰጥቷል::

>ፕሬዝዳንቱ ልጃቸው የሞተበትን ቀን ማስታወስ አልቻሉም የሚለውንም የምርመራ ውጤት አይቀበሉትም::የአሜሪካው ፕሬዝደንት ባይደን የማስታወስ ችሎታየ አሪፍ ነው ሲሉ ለስፔሻል ካውንስሉ መልስ መል...
09/02/2024

>
ፕሬዝዳንቱ ልጃቸው የሞተበትን ቀን ማስታወስ አልቻሉም የሚለውንም የምርመራ ውጤት አይቀበሉትም::
የአሜሪካው ፕሬዝደንት ባይደን የማስታወስ ችሎታየ አሪፍ ነው ሲሉ ለስፔሻል ካውንስሉ መልስ መልስ ሰጥተዋል::
የሜሪካው ፕሬዝደንት ባይደን የማስታወስ ችሎታየ አሪፍ ነው ሲሉ ለስፔሻል ካውንስሉ መልስ መልስ ሰጥተዋል።
ፕሬዝደንቱ ጥብቅ ሚስጥራዊ መረጃዎችን በአግባቡ አልያዙም እንዲሁም ወሳኝ ሁነቶች ማስታወስ ተስኗቸዋል የሚለውን የምርመራ ውጤት አጣጥለውታል።
ባይደን በትናንትናው እለት በሰጡት ድንገተኛ መግለጫ "የማስታወስ ችሎታየ አሪፍ ነው" ማለታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።
ፕሬዝዳንቱ ልጃቸው የሞተበትን ቀን ማስታወስ አልቻሉም የሚለውንም የምርመራ ውጤት አይቀበሉትም።
መርማሪው ባይደን በ2017 ከምክትል ፕሬዝደንትነት ሲሰናበቱ ጥብቅ ሚስጥራዊ መረጃዎችን ይዘው ወጥተዋል ብሏል።
ነገርግን መርማሪው ፕሬዝደንት ባይደንን እንደማይከሳቸው ገልጿል።
በፕሬዝደንት ባይደን ላይ ምርመራ ያካሄዱት የፍትህ ዲፖርትመንት ስፔሻል ካውንስል ሮበርት ሁር ባይደን ከምክትል ፕሬዝዳንትነት ስልጣን ከለቀቁ በኋላ በአፍጋኒስታን ከነበረው ጦርነት ጋር የተያያዙ ጥብቅ የወታደራዊ እና የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ መረጃዎች ይዘው ተገኝተዋል ብለዋል።
345 ገጽ ያለው የምርመራ ውጤት ፕሬዝደንቱ የማስታወስ ችሎታ ውስንነት እንዳለበት የሚያሳይ ነው።
ሁር በምርመራው ሂደት የ81 አመቱን ፕሬዝደንት አምስት ጊዜ ቃለመጠይቅ አድርገውላቸዋል።
ስፔሻል ካውንስሉ እንዳሉት ፕሬዝደንቱ ምክትል ፕሬዝደንት የሆኑበትን ወቅት (2009-2017) እና ከበርካታ አመታት በፊት ልጃቸው ቢዩ የሞተበትን(2015) ማስታወስ አልቻሉም።
ፕሬዝደንት ባይደን በማስታወስ ችሎታቸው ላይ ጥያቄ የፈጠረውን የምርመራ ውጤት ስሜታዊ ሆነው አጣጥለውታል።
ሚስጥራዊ መረጃዎችን ለምን እቤታቸው እንዳስቀመጡ ሲጠየቁ፣ ፕሬዝደንቱ ስራተኞቻቸውን ተጠያቂ አድርገዋል። ፕሬዝዳንቱ ሰራተኞቻቸው ሚስጥራዊ

እስራኤል በውጊያ ላይ ከሞቱ ወታደሮች የወንድ ዘር ፍሬ መሰብሰቧን አስታወቀች፡፡ከሀማስ ጋር እየተደረገ ባለው ጦርነት የሞቱ 91 ወታደሮች የዘር ፍሬያቸው ተሰብስቧል::ህይወታቸው ያለፉ ወታደሮ...
09/02/2024

እስራኤል በውጊያ ላይ ከሞቱ ወታደሮች የወንድ ዘር ፍሬ መሰብሰቧን አስታወቀች፡፡
ከሀማስ ጋር እየተደረገ ባለው ጦርነት የሞቱ 91 ወታደሮች የዘር ፍሬያቸው ተሰብስቧል::
ህይወታቸው ያለፉ ወታደሮች የዘር ፍሬያቸው የሚሰበሰበው ራሳቸውን እንዲተኩ ለማድረግ ነው ተብሏል::
ከአራት ወር በፊት የተጀመረው የእስራኤል-ሐማስ ጦርነት አሁንም እንደቀጠለ ሲሆን ከ27 ሺህ በላይ ፍለስጤማዊያን ሲገደሉ እስካሁን ቁጥሩ ያልተወቁ የእስራኤል ወታደሮችም ተገድለዋል፡፡
የእስራኤል መንግስት ወደ ፍልስጤም የላካቸው ወታደሮች በሐማስ እየተገደሉበት ሲሆን ከሞቱ ወታደሮች የወንድ የዘር ፍሬያቸውን መሰብሰቡ ተገልጿል፡፡
እንደ ጀሩሳሌም ፖስት ዘገባ ከሆነ የ91 ወታደሮች የዘር ፍሬ በቤተሰባቸው እና ሚስቶቻቸው ወይም ፍቅረኞቻቸው ፈቃድ መሰረት የዘር ፍሬያቸው በሳይንሳዊ መንገድ ተሰብስቧል፡፡
የተሰበሰበው ይህ የዘር ፍሬ ልጅ እንዲወልዱ አልያም ልጅ የመውለድ ፍላጎት ላላቸው ሴቶች ጥቅም ላይ ይውላል ተብሏል፡፡
የእስራኤል የህክምና ባለሙያዎች ከሀማስ ጋር ሲዋጉ ህይወታቸው ያለፈ ወታደሮችን የዘር ፍሬ የሚሰበስበው ህይወታቸው ባለፈ በ48 ሰዓታት ውስጥ እንደሆነ በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡
ፍቅረኛ አልያም ሚስት የሌላቸው በውጊያ ላይ የሞቱ ወታደሮችን የዘር ፍሬ በቅርብ ቤተሰባቸው ፈቃድ መሰረት የሚሰበሰብ ሲሆን ፈቃደኛ ለሆኑ ወይም የወንድ የዘር ፍሬ ለሚፈልጉ ሴቶች ይለገሳልም ተብሏል፡፡
የእስራኤል ሐማስ ጦርነት አሁንም የቀጠለ ሲሆን ጦርነቱ እንዲቆም የተለያዩ ጥረቶች በመደረግ ላይ ቢሆኑም ቋሚ የተኩስ አቁም እንዲኖር በእስራኤል ላይ የሚደረገው ጫና እንደቀጠለ ይገኛል፡፡
የዓለማችን 35 በመቶ ንግድ መስመር የሆነው ቀይ ባህር በዚሁ ጦርነት ምክንያት የስጋት ቀጠና የሆነ ሲሆን ዓለም አቀፍ መርከቦችም በስጋት ምክንያት ጉዟቸውን እየሰረዙ ናቸው፡፡
በቀይ ባሕር ትራንስፖርት ተጠቃሚ ከሆኑ ሀገራት መካከል ግብጽ ከስዊዝ ካናል የምታገኘው ገቢ በ46 በመቶ ቀንሶብኛል ማለቷ ይታወሳል፡፡

Address

Po. Box 15542

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when TOSA MEDIA ጦሳ ሚዲያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Videos
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share