19/08/2023
ዓለማችን በእለቱ
አሜሪካ
አሜሪካ በኒዮርክ እና አንዳንድ የሀገሪቱ ከተሞች ቲክቶክን በመንግስት ኮምፒዩተሮች አገልግሎት ላይ እንዳይውል ገደብ ጣለች።
ቲክቶክ በመንግሥት መገልገያ ኮምፒዩተሮች ላይ አገልግሎት ላይ እንዳይውል ያገደችው ኒዮርክ ከደህንነት ሥጋት ጋር በተያየዛ እንደሆነም ለማወቅ ተችሏል።
ኢሲያ
ህንድ አንዳንድ የሩዝ ምርት ከሀገር ውጭ መላክን አገደች
ምክንያት ደግሞ የእህል ዋጋ ንረት፣የዋጋ ግሽበትና የሩዝ ምርት እጥረት እንዳይገጥማት በመሥጋት መሆኑን አልጀዚራ ዘግቧል።
በዓለማችን ሩዝ በመላክ ቀዳሚ የሆነችው ህንድ የሩዝ ምርት ወደ ወጭ መላክ መቆሟን ተከትሎ በዓለም የሩዝ ዋጋ ጣራ ነክቷል ተብሏል።
መካከለኛ ምስራቅ
በጋዘ ሰርጥ የሚኖሩ 9 ፍልስጤማዊያን ሴቶች ታሪካቸውን ፣ ባህላቸውንና ቅርሳቸውን ለመጠበቅና ለማቆየት ያለ ድካም ይሰራሉ።
በበጎ ፈቃደኝነት ሥራውን የሚከውኑት ሴቶቹ የቆዩ መጽሃፍትን ወደ ዲጂታል በመቀየር ለተመራማሪዎች ምቹ ሁኔታ ይፈጥራልም ብለዋል
አዎሮፓ
ዴንማርክ እና ደች ለዩክሬን ኤፍ 16 የጦር ጀት ድጋፍ አደረጉ
ድጋፉ ለዩክሬን እንዲተላለፍ አሜርካ መፍቀዱን ቢቢሲ ዘግቧል።
የዩክሬኑ ፕሬዝደንት ቭላድምር ዞለንስክ ለተደረገላቸው ድጋፍ አመሥግነው ፣ከራሺያ የሚመጣባቸውን ጦር ለመመከት እንደሚረዳቸው ተናግረዋል።
አፍርካ
የብሪክስ አባል ሀገራት በሚቀጥለው ሳምንት በደቡብ አፍሪካ ጉባኤ ያካሄዳሉ ተባለ ።
በጉባኤው አዳዲስ አባል ሀገራት እንደሚሳተፉ የተጠቆመ ሲሆን የተቋሙ መመሥረት ከምእራባዊያን ጫና ለመላቀቅ ፋይዳው ትልቅ እንደሆነ ስነገርለት ቆይቷል።
በጉባኤው የሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላድምር ፑቲን እንደማይሳተፉ እየተነገረ ይገኛል። ምክንያቱ ደግሞ በዩክሬን ጦርነት ፈጽመውታል በተባለው የሰብኣዊ ወንጀል የሥር ማዘዣ ስለወጣባቸው ነው ተብሏል።
ደቡብ አፍርካ ከአፓርታይድ ነጻ እንዲትወጣ የያኔዋ የሶቭየት ህብረት የአሁኗ ሩሲያ የማይተካ ሚና መጨዎቱዋን አፍሪካ ኒውስ ዘግቧል