24/04/2024
እጅግ የተከበሩ የዓለም ሎሬት ሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ መኖሪያ ቤት እና ስቱዲዮ ጥገና ሊደረግለት ነው።
እጅግ የተከበሩ የዓለም ሎሬት ሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ መኖሪያ ቤት እና ስቱዲዮ የጥገና ስራ ለማከናወን የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ከ ቢዋይ ኤምቲ ኮንትራክተር እና ዳሎል አማካሪ ድርጅት መካከል የተቋሙ የበላይ ኃላፊዎች በተገኙበት በ15/08/2016 ዓ.ም የስራ ርክክብ ተደርጓል።
በፕሮግራሙ ላይ መልእክታቸውን ያስተላለፉት የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው ቅርሱ የነበረውን አሻራና ይዘት በጠበቀ መልኩ የቅርስ ጥገና መርሆዎችን በተከተለ መንገድ በጥንቃቄ መከናወን እንዳለበት ገልፀው፡፡የጥገና ስራው በተያዘለት የአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ጥራቱን ጠብቆ መጠገንና ለሃገር ተጨማሪ የገቢ ምንጭ መሆን እንደሚኖርበት አሳስበዋል፡፡
በመጨረሻም ስራ ተቋራጩ ይህን ታሪካዊ ቅርስ ጥገና ማድረግ በመቻላቸው እድለኛ እንደሆኑ ገልጸው ስራውን በተፈለገው ጊዜና ጥራቱን በጠበቀ መልኩ አከናውነው እንደሚያስረክቡ ቃል ገብተዋል፡፡
_____
ፈጣንና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፤ የእፍታ መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾችን ይቀላቀሉ! መረጃዎችን ለሌሎች ያጋሩ ሀሳብ አስተያየትዎን ይስጡ።
👇👇👇👇👇👇👇👇
የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://youtube.com/-Subscrib?si=yxWZnPB9dVumDLX1
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/efitamedia
የተመረጡ አጫጭር የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የፌስቡክ አካውንታችንን ይከተሉ
https://www.facebook.com/profile.php?id=61558303567204