01/07/2024
ሰኔ 24 /2016ዓ.ም *****የተክለ ሀይማኖት ከተማን ለማሳደግ የህብረተሰቡ አስተዋፅኦ ወሳኝ መሆኑ ተገለፀ።
ከተማውን ለማሳደግ በህብረተሰቡ እና በመንግሥት በርካታ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን የማዘጋጃ ቤቱ ስራ አስኪጅ አቶ ገብሬ ዘበርጋ ገልጸዋል።
በ2016 በጀት ዓመት ማዘጋጃ ቤቱ እቅድ መሠረት በማድረግ በርካታ ስራዎች መሰራታቸው ገልፀው ከእንዚህም ውስጥ ከ640 ካሬ በላይ የንግድ እና ከ800 ካሬ ለመኖሪያ መሬት በሊዝ ማስተላለፍ መቻሉን አመላክተዋል።
በተጨማሪም ለኢንቨስትመንት የሚሆን መሬት ተዘጋጅቶ የጠየቀ አለመኖሩን እና የውስጥ ለውስጥ የመንገድ ከፍታ ስራ እንዲሁም የቢሮ ግንባታ መሰራቱ ገልፀዋል።
የመድረኩ ተሳታፊዎች በመንግሥት በኩል ኔት ወርክ ከማስፋፋት አንፃር ለተደረገው ድጋፍ እና የከተማው እድገት ለማፋጠን እየተሰራ ላለው ተግባር ምስጋና በማቅርብ ከውሃ፣ ከማብራት፣ከመንገድ አንፃር ከፍተኛ ችግር መኖሩን አንስተዋል።
የምሁር አክሊል ወረዳ የመንግስት ዋና ተጠሪ የሆኑት አቶ ከበደ ሳህል በህብረተሰቡ የውይይት መድረክ ተገኝተው በማዘጋጃ ቤቱ አቅም የተሰሩ ስራዎች የሚበረታቱ መሆናቸውን ገልፀው የመንግስት እና የህብረተሰብ ቅንጅት ለከተማ እድገት ወሳኝ ነው ብለዋል።
ማህበረሰቡ ዘመናዊ ኑሮ እንዲኖር የከተማው እድገትና የመሠረት ልማት መሟላት እንዳለባቸው እና ከተማ ሊያድግ የሚችለው በነዋሪዎች ተሳትፎ ስለሆነ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በትኩረት እና በቅንጅት መስራት አለበት ሲሉም ገልፀዋል።
ሌላው በውይይት መድረኩ የተገኙት የምሁር አክሊል ወረዳ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ፅ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ሰይፈ ይልማ በተክለ ሀይማኖት ማዘጋጃ ቤት በጣም በርከታ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን አንስተው ማህብረሰቡ ለከተማው እድገት አጋዥ መሆኑን ገልፀዋል።
ማዘጋጃ ቤቶች በራሳቸው ገቢ ስለሚተዳደሩ የገቢ አማራጭን በተገቢው መንገድ ማስፋት ይጠበቅባቸዋል በማለት የተነሳው የገበያ ችግር መፍታት ያለበት ህዝቡ መሆኑን እና ወደ ሌላው የሚሄደውን ገቢ በውይይት እና በቅንጅት በመስራት ገቢውን ማሳደግ እንደሚቻል ገልፀዋል።
የምሁር አክሊል ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ብስራት ገብሩ በውይይቱ ማጠቃለያ የተጀማመሩ መልካም ስራዎች መኖራቸው አንስተው የህብረተሰቡ ተሳትፎ ወሳኝ እንደሆነ ገልፀው ከተማውን ለማሳደግ መንግስት እና ህብረተሰቡ በቅንጅት መስራት አለባቸው በማለት እየተሰሩ ስራዎች እውቅና መሰጠት ያስፈልጋል ብለዋል።
የተክለ ሀይማኖት የውሃ ችግር የሚታወቅና መንግስት ከረጂ ድረጅት ጋራ በመወያየት እየተሰራ መሆኑን አንስተው የኮተ ቀበሌ እየተገነባ ያለው ውሃ አንድ ቦኖ ለተክለ ሀይማኖት መሆኑን ጠቅሰው ለዘላቂ የህብረተሰቡን የውሃ ችግር ለመፍታት ታቅዶ እየተሰራ መሆኑንና በየቤቱ ለማስገባት የሚሰራ እንደሆነ ገልፀዋል።
የመንገድ ስራን በተመለከተ ውስጥ ለውስጥ የተሰራው ጥሩ መሆኑን ገልጸው ማዘጋጃ ቤቱ ይብልጥ መስራት እንዳለበት አመላክተዋል።
የመብራት ችግር ወደ ወረዳው ሲገባ ከመጀመሪያው ችግር መኖሩን አንስተው በዘላቂነት ችግሩን ለመፍታት እየተሰራ መሆኑን ገልፅዋል።
ከስራ ዕድል ፈጣራ አንፃር ወጣቱ እየስራ ያለው ተግባር የተሻለ መሆኑን ገለፅው በግብርና በእንስሳት እርባታ ዘርፍ የሚሰሩ በርካታ የስራ ዕድል መኖሩን በመገንዘብ በሌሎች ስራዎች መሰማራት መቻል አለባቸው ብለዋል።
ገበያውን ሠላማዊ እና በቂ ምርት እንዲኖረው በማድረግ እንዲሁም አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ተገቢን አቀባበል በማድረግ ገበያ እንዲኖር ማድረግ ይጠበቃል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፏዋል ሲል የዘገበው የምሁር አክሊል ወረዳ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው