10/04/2020
በኢትዮጵያ ደረጃቸውን የጠበቁ የፊት ጭንብሎች በስፋት ለማምረት እየተሰራ ነው
የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚረዱ ደረጃቸውን የጠበቁ የፊት ጭንብሎች በአገር ውስጥ በስፋት ለማምረት እየተሰራ መሆኑን የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ገለጹ።
በሥራቸው ባህሪ ከተለያዩ ሰዎች ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያላቸው ሰዎች የፊት ጭንብልና ጓንት አዘውትረው እንዲጠቀሙ ሚኒስትሯ ምክረ ሃሳብ ለግሰዋል።
የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ለኢዜአ እንደተናገሩት፤ ደረጃቸውን የጠበቀ የፊት ጭንብል በአገር ውስጥ እንዲመረት ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅርበት እየተሰራ ነው።