KM+

KM+ ወቅታዊ፤ ታማኝ እና ሚዛናዊ መረጃ የሚያገኙበት ገጽ ነው!
(3)

ዜናKM+ሕዳር 03 2017 ዓ.ምበሶማሊ ክልል ለ2017 በጀት አመት የልማታዊ ሴፍትኔት      PSNP የስራ ማስፈፀሚ 14 ነጥብ 5 ቢሊዬን ብር ፀደቀ*********************በሶማሊ...
12/11/2024

ዜናKM+
ሕዳር 03 2017 ዓ.ም

በሶማሊ ክልል ለ2017 በጀት አመት የልማታዊ ሴፍትኔት PSNP የስራ ማስፈፀሚ 14 ነጥብ 5 ቢሊዬን ብር ፀደቀ

*********************
በሶማሊ ክልል ለ2017 በጀት አመት የልማታዊ ሴፍትኔት (PSNP) የስራ ማስፈፀሚ 14 ነጥብ 5 ቢሊዬን ብር ፀድቋል።

የሶማሊ ክልል የልማታዊ ሴፍትኔት ( PSNP) አብይ ኮሚቴ ስብሰባ በዛሬው እለት በጅግጅጋ ከተማ ተካሂዷል።

በሶማሊ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኢብራሂም ዑስማን ሰብሳቢነት የተካሄደው የልማታዊ ሴፍትኔት ( PSNP) አብይ ኮሚቴ ስብሰባ የፕሮጀክቱን የእቅድ አፈፃፀም እና የ2017 በጀት አመት እቅድ ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።

በመድረኩ ላይ አብይ ኮሚቴው በክልል ለ2017 በጀት አመት ለልማታዊ ሴፍትኔት ( PSNP) የስራ ማስፈፀሚ 14 ነጥብ 5 ቢሊዬን ብር አፅድቋል።

በሶማሊ ክልል ሁሉም ወረዳዎች ተግባራዊ እየተደረገ የሚገኘው የልማታዊ ሴፍትኔት ( PSNP) የህብረተሰቡን ህይወት በማሻሻል በኩል የጎላ ጠቀሜታ እንደሚያበረክት ተገልጿል።

 +ሕዳር 02 2017 ዓ.ምየሶማሊ ክልል ርዕሰ መስተዳድር በፋፈን ዞን ሀሮሬስ ወረዳ የስንዴ አጨዳ ስራዎችን ጎበኙ*****************የሶማሊ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፋ ሙሁመ...
11/11/2024

+
ሕዳር 02 2017 ዓ.ም

የሶማሊ ክልል ርዕሰ መስተዳድር በፋፈን ዞን ሀሮሬስ ወረዳ የስንዴ አጨዳ ስራዎችን ጎበኙ

*****************
የሶማሊ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ በፋፈን ዞን ሀሮሬስ ወረዳ የተጀመረውን የስንዴ አጨዳ ስራዎችን ጎብኝተዋል።

በሶማሊ ክልል ፋፈን ዞን ሀሮሬስ ወረዳ ምርቱ ለመሰብሰብ የደረሰው የስንዴ ሰብል ምርት በዘመናዊ መሳሪያዎች የመሰብሰብ ስራ እየተካሄደ የሚገኝ ሲሆን የሶማሊ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ በወረዳው የተጀመረውን የስንዴ አጨዳ ስራዎችን በትናንትናው ዕለት ተመልክተዋል።

በዚህ ወቅት ርዕሰ መስተዳደሩ የግብርና ምርታማነት ለማሳደግ የተያዘውን እቅድን ውጤታማ ለማድረግ እና በምግብ ሰብል እራስን ለመቻል ፓርቲው ፣ መንግስት ፣ እና ህዝቡ በጋራ እየሰሩ መሆናቸውን ገልፀዋል።

የስንዴ ልማት መርሐ-ግብር እና ሌሎች የግብርና ልማት ስራዎች የህዝቡን በምግብ ሰብል መቻልን በዘላቂነት ለማረጋገጥ ያለመ መሆኑን ነው ርዕሰ መስተዳድሩ የተናገሩት ።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ክልሉ ለእርሻ ልማት የሚሆን ለም መሬት ፣ ትላልቅ ወንዞችና ወጣት ሀይል ባለቤት በመሆን ይህንን በመጠቀም በተለያዩ የግብርና ልማት ስራዎች ላይ የተጠናከረ ስራ ቢሰራ ከውጭ እርዳታ ጠባቂነት ከመላቀቅ ባሻገር የተለያዩ ምርቶችን ወደ ውጪ የመላክ አቅም ላይ ለመድረስ እንደሚቻል አስገንዝበዋል።

በቀጣይ የዝናብ ወቅቶችን በመጠቀም በክልሉ በሚገኘው እምቅ ሀብቶች በመጠቀም የእርሻ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ መስራት እንደሚገባ ያሳሰቡት ርዕሰ መስተዳድሩ የክልሉ መንግስት በግብርና ስራ የተሰማሩ አካላትን ለማበረታትና አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን አረጋግጠዋል።

በሀሮሬስ ወረዳ ምርቱ እየተሰበሰበ የሚገኘው የስንዴ ምርት የወረዳው አርሶአደሮች ከክልሉ መንግስት ባገኙት ድጋፍ ያለሙት መሆኑን ነው የተገለፀው።

በፋፈን ዞን ሀሮሬሶ ወረዳ ከደረሰው የስንዴ ሰብል 1 ሚሊየን 10 ሺህ ኩንታል ምርት ይገኛል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ባጠቃላይ በፋፈን ዞን 3.5 ሚሊየን ኩንታል የስንዴ ምርት ይሰበሰባል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተገልጿል።

 +ጥቅምት 30 2017 ዓ.ምየጅግጅጋ ከተማ የኮሪደር ልማት የከተማውን እደገት ለማፋጠን የሚያስችል መሆኑን የጅግጅጋ ከተማ ነዋሪዎች ገለፁ************************* በጅግጅጋ ከ...
09/11/2024

+
ጥቅምት 30 2017 ዓ.ም

የጅግጅጋ ከተማ የኮሪደር ልማት የከተማውን እደገት ለማፋጠን የሚያስችል መሆኑን የጅግጅጋ ከተማ ነዋሪዎች ገለፁ

*************************
በጅግጅጋ ከተማ እየተካሄደ የሚገኘው የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት የከተማውን እደገት ለማፋጠን እና ህብረተሰቡን ዘመናዊ የመሰረተ ልማት ተጠቃሚነትን የሚያሳድግ መሆኑን የጅግጅጋ ከተማ ነዋሪዎች ገልፀዋል።

በሶማሊ ክልል ጅግጅጋ ከተማ በተመረጡ አካባቢዎች የኮሪደር ልማት ፕሮጀክትን ተግባራዊ ለመድረግ ዕቅድ ተይዞ ወደስራ የተገባ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ በከተማው የተጀመሩ የኮሪደር ልማት ስራዎችን ለማፋጠን እየተሰራ ይገኛል ።

አስተያየታቸውን ለሶማሊ ክልል የብዙሀን መገናኛ ኤጀንሲ የሰጡ የጅግጅጋ ከተማ ነዋሪዎች በጅግጅጋ ከተማ የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት ስራ መጀመሩ እንዳስደሰታቸው ጠቁመው ፕሮጀክቱ የጅግጅጋ ከተማን ዕድገት ለማፋጠንና ለከተማው ነዋሪዎች ዘመናዊና ምቹ መሠረተ ልማት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ያስችላል ብለዋል።

በአሁኑ ጊዜ የጅግጅጋ ከተማ ግንባር ቀደም የንግድና የኢንቨስትመንት ማዕከል እየሆነች መምጣቷን የጠቆሙት ነዋሪዎቹ በከተማው የተጀመረው የኮሪደር ልማት የከተማውን ልማትና እድገት በማፋጠን በኩል የጎላ ጠቀሜታ ያበረክታል ብለው እንደሚጠብቁ ተናግረዋል።

ነዋሪዎቹ በከተማው እየተካሄደ ያለው የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት ስኬታማ እንዲሆን የበኩላቸውን አስተዋፆ እንደሚያበረክቱ ገልፀዋል።

 +ጥቅምት 30 2017 ዓ.ምበ300 ሚሊየን ብር ወጪ ማስፋፊያ የተደረገለት የጎዴ ከተማ ሆስፒታል ለአገልግሎት ክፍት ሆነ ***********************የሶማሊ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ...
09/11/2024

+
ጥቅምት 30 2017 ዓ.ም

በ300 ሚሊየን ብር ወጪ ማስፋፊያ የተደረገለት የጎዴ ከተማ ሆስፒታል ለአገልግሎት ክፍት ሆነ

***********************
የሶማሊ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፋ ሙሁመድ በ300 ሚሊየን ብር ወጪ ማስፋፊያ የተደረገለትን የጎዴ ከተማ ሼክ ኢብራሂም አብደላ አጠቃላይ ሆስፒታልና አዲስ የተገነባውን የኦክስጂን ማዕከል መርቀው ለአገልግሎት ክፍት አደረጉ።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ በዚህ ወቅት ሆስፒታሉ ማሻሻያና የኦክሲጂን ማምረቻ ማዕከሉ ግንባታ መንግሥት ለጤና አገልግሎት መሻሻል የሚያደርገውን ጥረት እንደሚያሳይ ገልጸዋል።

የጤና አገልግሎት ጥራትን እንደሚያሳድግም ጨምረው ተናግረዋል።

ሆስፒታሉ አዳዲስ የተኝቶ መታከሚያ ክፍሎች፣ የእናቶችና ህፃናት ማዕከል፣ የአስቸኳይና ልዩ ህክምና ክፍሎች፣ የህክምና ቁሳቁሶች እንዲሁም የአገልግሎት መስጫ ማዕከልን ማካተቱ ተገልጿል።

በሆስፒታሉ የተደረገው የማስፋፊያ ሥራ የነበረውን የህሙማንና የታካሚዎች መጨናነቅ ይቀንሳል ተብሏል።

የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሙሳ አህመድ በበኩላቸው ሆስፒታሉና የኦክስጂን ማምረቻ ማዕከሉ በጎዴ ከተማ ሥር የሚገኙ የጤና ማዕከላትን ጨምሮ በሸቤሌ ዞንና አጎራባች ዞኖች የጤና አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ የጎላ ጠቀሜታን ያበረክታሉ።

የኦክስጂን ማምረቻ ማዕከሉ በጅግጅጋ ከተማ ካለው ማዕከል ቀጥሎ በክልሉ ሁለተኛው መሆኑን ጠቅሰው፤ በቀን 150 ሲሊንደሮች የማምረት አቅም እንዳለው ጠቁመዋል።

በሆስፒታሉ ማስፋፊያ የምርቃት ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የክልል፣ የሸቤሌ ዞንና የጎዴ ከተማ አስተዳደር አመራሮች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የከተማዋ ነዋሪዎችና የአጋር አካላት ተወካዮች ተገኝተዋል ።

ዜናKM+ጥቅምት 29 2017 ዓ.ም"ሕብረብሔራዊ አንድነታችንን በማፅናት የኢትዮጵያን ከፍታ እናረጋግጣለን!" ወ/ሮ ከሪማ አሊ | የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት ምክትል አፈጉባኤ ********...
08/11/2024

ዜናKM+
ጥቅምት 29 2017 ዓ.ም

"ሕብረብሔራዊ አንድነታችንን በማፅናት የኢትዮጵያን ከፍታ እናረጋግጣለን!"
ወ/ሮ ከሪማ አሊ | የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት ምክትል አፈጉባኤ

****************

ለመንግስት ሰራተኞች አራተኛ ዙር የብልጽግና ፓርቲ አባላቶች የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጠ።
የህልም ጉልበት ለእመርታዊ እድገት በሚል መሪ ቃል ለድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት እና ተጠሪ ተቋማት፣ለግብርና ውሃ ማዕድን ኢነርጂ ቢሮ፣ለሴቶች ህፃናት ማህበራዊ ጉዳይ እና እስፖርት ኮምሽን፣ለትምህርት ቢሮ የፓርቲው አባላቶች የአቅም ግንባታ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል ።

የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ከሪማ አሊ ለሁለት ቀናት የሚሰጠው ስልጠና ላይ አባላቶች በንቁ መሳተፍ አለባቸው ሲሉ ተናግረዋል።

ከስልጠናው በምታገኙት ልምድ ተነስታችሁ በቀጣይ ስራቹሁ እና በማህበራዊ ሂወታቹ ህብረብሔራዊ አንድነታችንን በማፅናት የኢትዮጵያን ከፍታ ማረጋገጥ ይገባቸዋል ሲሉ ተናግሯል ።

የህልም ጉልበት ለእመርታዊ እድገት በሚል መሪ ቃል እየተሰጠ የሚገኘው የመንግስት ሰራተኞች አራተኛ ዙር የብልጽግና ፓርቲ አባላቶች የአቅም ግንባታ ስልጠና ለሁለት ቀናት የሚቆይ ይሆናል ።

 +ጥቅምት 29 2017 ዓ.ምየቀድሞ የሀረሪ ብዙሀን መገናኛ ኤጀንሲ ስራ አስኪያጅ የነበሩት አቶ መሀመድ ሻሽ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ***********የቀድሞ የሀረሪ ብዙሀን መገናኛ ኤጀንሲ ...
08/11/2024

+
ጥቅምት 29 2017 ዓ.ም

የቀድሞ የሀረሪ ብዙሀን መገናኛ ኤጀንሲ ስራ አስኪያጅ የነበሩት አቶ መሀመድ ሻሽ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ
***********
የቀድሞ የሀረሪ ብዙሀን መገናኛ ኤጀንሲ ስራ አስኪያጅ የነበሩት አቶ መሀመድ ሻሽ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ።

አቶ መሀመድ ሻሽ የክልሉ ብዙሀን መገናኛ ኤጀንሲን በስራአስኪያጅነት መምራትን ጨምሮ በክልሉ የተለያዩ የስራ ሀላፊነቶች ላይ በመስራት ለረጅም አመት አገልግለዋል።

KM+ በአቶ መሀመድ ሻሽ ህልፈት የተሰማውን ሀዘን እየገለፀ ለቤተሰቦቻቸውና ወጃድ ዘመዶቻቸው መፅናናትን ይመኛል።

 +ጥቅምት 29 2017 ዓ.ምበሶማሊ ክልል  የሸበሌይ ሪዞርት ፕሮጀክት ግንባታ 71 ከመቶ መደረሱን  ተገለፀ*********************በሶማሊ ክልል ፋፈን ዞን  ሸበሌይ ወረዳ እየተገነ...
08/11/2024

+
ጥቅምት 29 2017 ዓ.ም

በሶማሊ ክልል የሸበሌይ ሪዞርት ፕሮጀክት ግንባታ 71 ከመቶ መደረሱን ተገለፀ
*********************
በሶማሊ ክልል ፋፈን ዞን ሸበሌይ ወረዳ እየተገነባ የሚገኘው የሸበሌይ ሪዞርት ፕሮጀክት ግንባታ 71 ከመቶ መደረሱን ተገልጿል።

በሶማሊ ክልል የሸበሌይ ሪዞርት ፕሮጀክት ግንባታ አፈፃፀም ግምገማ እና በሲቲ ዞን የኤረር ጎታ የተፈጥሮ ፍል ውሀ እና ቤተ-መንግስት መልሶ ግንባታ ዲዛይን የቀረበበት የውይይት መድረክ በጅግጅጋ ከተማ ተካሂዷል።

በሶማሊ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኢብራሂም ዑስማን ሰብሳቢነት በተካሄደው የውይይት መድረኩ ላይ በብልፅግና ፓርቲ የሶማሊ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሀላፊ ኢ/ር መሀመድ ሻሌ ፣ የመስኖ እና የቆላማ አከባቢዎች ሚኒስትሩ ዶ/ር አብርሀም በላይ እና ሌሎች የክልሉ መንግስት አመራሮች ተገኝተዋል።

በአሁኑ ጊዜ የሸበሌይ ሪዞርት ፕሮጀክት ግንባታ 71 ከመቶ መደረሱን ተገልጿል።

በመድረኩ ላይ የሸበሌይ ሪዞርት ፕሮጀክት ግንባታ አፈፃፀም ሪፖርት የቀረበ ሲሆን በፕሮጀክቱ እየተካሄዱ የሚገኙ የንፁህ መጠጥ ውሀ ፣የመንገዶች ግንባታ እና ሌሎች ስራዎች የስራ ሂደት ተገምግሟል።

ከዚህ በተጨማሪም በመድረኩ ላይ ግንባታው የሚጀመረው በሶማሊ ክልል ሲቲ ዞን ኤረር ወረዳ የኤረር ጎታ የተፈጥሮ ፍል ውሀ እና ቤተ-መንግስት መልሶ ግንባታ ዲዛይን ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል ።

በዘመናዊ መንገድ የሚገነባው የኤረር ጎታ የተፈጥሮ ፍል ውሀ እና ቤተ-መንግስት በክልሉ 2ኛው የቱሪዝምና ሪዞርት ማዕከል እንደሚሆን ነው የተገለፀው።

የሶማሊ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኢብራሂም ዑስማን በመድረኩ ላይ ግንባታው በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ የሚገኘውን የሸበሌይ ሪዞርት ፕሮጀክት ግንባታን እንዲፋጠን አቅጣጫዎችን ሰጥተዋል።

ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ በክልሉ በቀጣይ ግንባታው የሚጀመረው የኤረር ጎታ የተፈጥሮ ፍል ውሀ እና ቤተ-መንግስት መልሶ ግንባታ የክልሉን ኢኮኖሚና ልማትን በማፋጠን በኩል የጎላ አስተዋፆ እንደሚያበረክት ገልፀዋል።

ዜናKM+ጥቅምት 28 2017 ዓ.ምየዋቤ ሸበሌ ወንዝ ሞልቶ ባስከተለው የጎርፍ አደጋ በሶማሊ ክልል ሸበሌ ዞን  ወረዳዎች ላይ ጉዳት አደረሰ*********************** የዋቤ ሸበሌ ወ...
07/11/2024

ዜናKM+
ጥቅምት 28 2017 ዓ.ም

የዋቤ ሸበሌ ወንዝ ሞልቶ ባስከተለው የጎርፍ አደጋ በሶማሊ ክልል ሸበሌ ዞን ወረዳዎች ላይ ጉዳት አደረሰ
***********************
የዋቤ ሸበሌ ወንዝ ሞልቶ ባስከተለው የጎርፍ አደጋ በሶማሊ ክልል ሸበሌ ዞን በሚገኙት ወረዳዎች ላይ ጉዳት ማድረሱን ተገልጿል።

የዋቤ ሸበሌ ወንዝ ባስከተለው የጎርፍ አደጋ በክልሉ ሸበሌ ዞን ቀላፎ ፣ ሙስታሂልና ፌርፌር ወረዳዎች በሚገኙ ቀበሌዎች ጉዳት ያደረሰ ሲሆን ወንዙ በተለይም በቀላፎ ወረዳ ባሉ ሰባት ቀበሌዎች ያደረሰው የጎርፍ አደጋ በንብረት እና በመኖሪያ ቤቶች ላይ ጉዳት ማድረሱን ነው የተገለፀው ።

በሸበሌ ዞን የጎርፍ አደጋው የተከሰተባቸው ወረዳ አመራሮች በጎርፍ አደጋው ውስጥ የሚገኙ ነዋሪዎችን ለመደገፍ ርብርብ እያደረጉ መሆናቸውን ተገልጿል።

 +ጥቅምት 26 2017 ዓ.ምየሶማሊ ክልል ርዕሰ መስተዳድር በኢትዮጲያ የUNOCHA ዋና ዳይሬክተር የተመራ የልዑክ ቡድን ጋር ተወያዩ***************የሶማሊ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አ...
05/11/2024

+
ጥቅምት 26 2017 ዓ.ም

የሶማሊ ክልል ርዕሰ መስተዳድር በኢትዮጲያ የUNOCHA ዋና ዳይሬክተር የተመራ የልዑክ ቡድን ጋር ተወያዩ
***************
የሶማሊ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ በኢትዮጲያ የUNOCHA ዋና ዳይሬክተር ፓውል ሀንድሊ የተመራ የተለያዩ ለጋሽ ድርጅቶች የልዑካን ቡድን ጋር ተወያይተዋል።

በኢትዮጲያ የUNOCHA ዋና ዳይሬክተር ፓውል ሀንድሊ የተመራ የተለያዩ ሀገራት ለጋሽ ድርጅቶች ያካተተ የልዑካን ቡድን በዛሬው ዕለት ጅግጅጋ ገብቷል።

የልዑካን ቡድኑ ከሶማሊ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ ጋር ውይይት አካሂደዋል።

ቡድኑ በቀጣይ በሶማሊ ክልል ወረዳዎች ተግባራዊ የተደረጉ የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶችን ተዘዋውረው እንደሚጎበኝ ተገልጿል።

 +ጥቅምት 25 2017 ዓ.ም የሀገራችንን ብልፅግና ማረጋገጥ የሚቻለው የሳይበር ደህንነት ቴክኖሎጂንና የሳይበር ደህንነት ሉአላዊነትን ማስጠበቅ የሚያስችል አቅም መፍጠር ሲቻል መሆኑ ተገለፀ*...
04/11/2024

+
ጥቅምት 25 2017 ዓ.ም

የሀገራችንን ብልፅግና ማረጋገጥ የሚቻለው የሳይበር ደህንነት ቴክኖሎጂንና የሳይበር ደህንነት ሉአላዊነትን ማስጠበቅ የሚያስችል አቅም መፍጠር ሲቻል መሆኑ ተገለፀ

**********************

"የቁልፍ መሠረተ ልማት ደህንነት ለዲጂታል ሉዓላዊነት" በሚል መሪ ቃል 5ኛው ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር የማጠቃለያ መርሐ ግብር በድሬዳዋ አስተዳደር በዛሬው ዕለት መካሄድ ጀምሯል።

በዚህም በመድረኩም ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር ለእንግዶች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክታቸውን በማስተላለፍ የዲጂታል ኢትዮጲያ 2030 እቅድ የሀገሪቱ ኢኮኖሚ ለመፍጠርና በክህሎት ላይ የተመሰረተ ኢንዲሆን ያስችላል ሲሉ ተናግረዋል።

ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር አያይዘውም የሀገራችንን ብልፅግና ማረጋገጥ የሚቻለው የሳይበር ደህንነት ቴክኖሎጂንና የሳይበር ደህንነት ሉአላዊነትን ማስጠበቅ የሚያስችል አቅም መፍጠር ሲቻል መሆኑን ገልፀዋል::

የዛሬው መድረክ የአስተሳሰብና የተግባር አንድነትን በመፍጠር በድሬዳዋ አስተዳደር ቀልጣፋ አገልግሎትን ተደራሽ በማድረግ ስማርት ሲቲ ለመፍጠር የሚደረገውን ጉዞ እንደሚያግዝም ከንቲባ ከድር ጠቁመዋል።

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ በበኩላቸው በአሉ ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ ውጪ በድሬዳዋ መከበሩን ተናግረዋል::በድሬዳዋ አስተዳደር በአሉ በደመቀ ሁኔታ እንዲከበር ላደረገው ትብብርም አመስግነዋል::

ተየሳይበር ደህንነት እና የዲጂታል መታወቂያ ለዲጂታል ኢኮኖሚ ጉዞ ወሳኝ መሆኑን ወ/ ሮ ትግስት አብራርተዋል::

አሁን ባለንበት ነባራዊ ሁኔታ ጠንካራና የበለፀገ ዲጂታል ኢኮኖሚ ለመገንባት በምናደርገው ጥረት የሀገራችንን የሳይበር ደህንነትና የዲጂታል ሉአላዊነት ማረጋገጥ እንዲሁም ስለዲጂታል መታወቂያ ለዜጎች ግንዛቤ በመስጠትና አገልግሎቶችን ከዲጂታል መታወቂያ ጋር ማስተሳሰር ይገባል ሲሉ ወ/ሮ ትግስት ተናግረዋል።

በመድረኩ"በዲጂታል ኢኮኖሚ ጉዞ የሳይበር ደህንነትና የዲጂታል መታወቂያ ሚና" በሚል ርዕስ ውይይት የተካሄደ ሲሆን መርሀ ግብሩ ነገም ቀጥሎ ይውላል::!

 +ጥቅምት 25 2017 ዓ.ምየሶማሊ ክልል የተለያዩ የስራ ሀላፊዎች ገረዎን ከጉነገዶ ጋር የሚያገናኘውን የመንገድ ፕሮጀክትን ጎበኙ**********************የሶማሊ ክልል ርዕሰ መስተ...
04/11/2024

+
ጥቅምት 25 2017 ዓ.ም

የሶማሊ ክልል የተለያዩ የስራ ሀላፊዎች ገረዎን ከጉነገዶ ጋር የሚያገናኘውን የመንገድ ፕሮጀክትን ጎበኙ

**********************
የሶማሊ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ጽ/ቤት ሀላፊ ዶ/ር ሁሴን ሀሺ ፣ የክልሉ የመስኖ እና ተፋሰስ ልማት ቢሮ ሀላፊ አቶ መሀመድ ፋታህ ፣ የጀረር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አህመድ ሁሴን እና የገነገዶ እና ደገሀቡር ወረዳ አመራሮች 52 ኪሎ ሜትር የሚሸፍነውን የገረዎን -ጉነገዶ የመንገድ ፕሮጀክት የስራ ሂደትን ተመልክተዋል ።

የመንገድ ፕሮጀክቱ በአከባቢው የሚገኙ አርሶአደር የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ለማድረግ የሚያስችል እና የገነገዶ እና የደገሀቡር ወረዳዎች ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎችን በማፋጠን በኩል የጎላ ጠቀሜታ እንደሚያበረክት ተጠቅሷል።

እስካሁን የመንገዱ ግንባታ 37 ኪሎ ሜትር የሚሆነው መገንባቱን የተገለፀ ሲሆን አሁን ላይ ባጠቃላይ የመንገድ ፕሮጀክቱ አፈፃፀም 80 ከመቶ መጠናቀቁን ተገልጿል።

 +ጥቅምት 24 2017 ዓ.ምበኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ የተመራ ልኡካን ቡድን ድሬዳዋ ከተማ ገባ******************"ቁልፍ የመሰረ...
03/11/2024

+
ጥቅምት 24 2017 ዓ.ም

በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ የተመራ ልኡካን ቡድን ድሬዳዋ ከተማ ገባ

******************

"ቁልፍ የመሰረተ-ልማት ደህንነት ለዲጂታል ሉአላዊነት" በሚል 5 ኛው ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር ከጥቅምት አንድ ጀምሮ እየተከበረ ሲገኝ ይህንንም አስመልክቶ ሀገራዊ የሳይበር ደህንነት ፖሊሲ ትግበራ እና የባለድርሻ አካላት ሚና በሚል ርዕስ ከክልልና ከከተማ አስተዳደር አመራሮችና ከባለድርሻ አካላት ጋር የተዘጋጀ የምክክር መድረክ ላይ ለመሳተፍ ነው ወ/ሮ ትዕግስት ወደ ድሬዳዋ የገቡት::

በዚህም ጥቅምት 25 እና 26/2017 አ.ም ውይይት የሚደረግ ሲሆን በነገው እለት በዲጂታል ኢኮኖሚ የሳይበር ደህንነትና የዲጂታል መታወቂያ ዙሪያ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋረ ውይይት እንደሚደረግ ከወዲሁ ታውቋል::

በወ/ሮ ትግስት አምዴ የተመራው ልኡካን ቡድን ድሬዳዋ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርስ በድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህና በሌሎችም የመስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል።

 +ጥቅምት 24 2017 ዓ.ም"ሚጁ ኦግበሩ" የተሠኘው በመምህርና ጸሀፊ አወል ሰኢድ የተጻፈ የኦሮምኛ የስነ ጽህፍና የወግ መጸሐፍ ተመረቀ።***********በዚህ መጸሐፍ የኦሮሞ ባህልና ወጎች...
03/11/2024

+
ጥቅምት 24 2017 ዓ.ም

"ሚጁ ኦግበሩ" የተሠኘው በመምህርና ጸሀፊ አወል ሰኢድ የተጻፈ የኦሮምኛ የስነ ጽህፍና የወግ መጸሐፍ ተመረቀ።
***********
በዚህ መጸሐፍ የኦሮሞ ባህልና ወጎች፣እንዲሁም እሴቶች ታሪካዊ አመጣጣቸውን እና ለልጀች የሚነገሩ ስነቃሎችና አፈታሪኮች ተካተውበታል።

የስነጽሀፍ መምህርና የሆኑት ደራሲ አወል ሠይድ ለምርቃት ባበቁት በዚህ "ሚጁ ኦግ-በሩ" የሚል ርዕስ ባለው መጽሀፍ ውስጥ ያካተቷቸው ይዘቶች የኦሮሞ ባህላዊ እሴቶች ባሉበት ተጠብቀው እንዲቆዩና ለትውልድ ሊተላለፋ አንደሚገባቸው ያትታል።

በዚህ የመጽሀፍ ምረቃ መረሐ ግብር ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የከንቲባው ተወካይና የከንቲባ ጽህፈት ቤት ሀላፊው አቶ ገበየሁ ጥላሁን በንግግራቸው እንደገለጹት ሀገር በሁለንተናዊ መስኮች ለማሳደግ በሚደረገው ጥረት የቀደሙ አባቶችን ትውፊት፣ ወግና ባህል በሚገባ ሰንዶ ለተከታዩ ተውልድ ማስተላለፍ ይገባል። በመሆኑም ተተኪው ትውልድ ወግና ባህሉን በሚገባ እንዲያውቅ ለማድረግም በመሰል ጸሐፍት የሚፈጸሙ ትውልድ የሚያንጹ የጥበብ ሥራዎች መጠናከር አለባቸው ነው ያሉት።

የኦሮምኛ ቋንቋን ባህልና ወግ ከትውልድ ትውልድ ለማቀባበልም ይህ መጽሀፍ ትልቅ አሰተዋጽኦ እንዳለውም ነው አቶ ገበየሁ የገለጹት።

በመርሐግብሩ ላይ የሐይማኖት አባቶች፣ አባገዳዎች፣ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና ነዋሪዎች ተገኝተዋል።

ደራሲው "ሚጁ ኦግ-በሩ" ከተሰኘው ካሁኑ ሥራቸው ባሻገር ቀደም ሲል ጽፈው ለህትመት ያበቋቸው ሶስት መጻህፍትን በጥቅሉ አራት መጻህፍትን ያበረከቱ ሲሆን አንድ የወጥ ፊልም ስክሪፕት ድርሰት ጨርሰው ለዝግጅት እየተሰናዱ መሆናቸውን ለጣቢያችን ያደረሱን መረጃ ያመለክታል ሲል የዘገበው የመስተዳደሩ መገናኛ ብዙሃን ኤጀንሲ ነው።

 +ጥቅምት 22 2017 ዓ.ምየሶማሊ ክልል የከተማ ልማትና ግንባታ ቢሮ አመራሮች በቀብሪዳሀር ከተማ እየተካሄዱ ያሉ  የልማት ፕሮጀክቶችን ጎበኙ*********************የሶማሊ ክልል ...
01/11/2024

+
ጥቅምት 22 2017 ዓ.ም

የሶማሊ ክልል የከተማ ልማትና ግንባታ ቢሮ አመራሮች በቀብሪዳሀር ከተማ እየተካሄዱ ያሉ የልማት ፕሮጀክቶችን ጎበኙ
*********************
የሶማሊ ክልል የከተማ ልማትና ግንባታ ቢሮ የተለያዩ የስራ ሀላፊዎች በቀብሪዳሀር ከተማ እየተካሄዱ የሚገኙ የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል።

የክልሉ የከተማ ልማትና ግንባታ ቢሮ የተለያዩ ስራ ሀላፊዎች ቡድን በቆራሄ ዞን ቀብሪዳሀር ከተማ የተካሄዱ እና እየተካሄዱ የሚገኙ የልማት ፕሮጀክቶች ምልከታ አካሂደዋል።

የሶማሊ ክልል የከተማ ልማትና ግንባታ ቢሮ ምክትል ሀላፊ ኢ/ር አብዲ ኢድ ዳሂዬ ከቀብሪዳሀር ከተማ አመራሮች ጋር በመሆን በከተማ ከባለፈው አመት ወደ 2017 በጀት አመት የተሻገሩ ነባርና አዲስ የልማት ፕሮጀክቶችን የስራ ሂደትን እና የተጠናቀቁ ፕሮጀክቶችን አገልግሎት ለማስጀመር የተከናወኑ ስራዎችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

ጉብኝቱ በቀብሪዳሀር ከተማ ተግባራዊ የተደረጉ የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶችን ክትትል እና ቁጥጥር ለማድረግና በከተማው የሚገኙ ቢሮዎች የአገልግሎት አሰጣጥ የስራ ሂደት እና የጥራት ሁኔታን ለመመልከት ያለመ መሆኑን ተገልጿል። ዘገባውን ከክልሉ መገናኛ ብዙሃን ኤጀንሲ አግኝተነዋል።

ዜናKM+ጥቅምት 22 2017 ዓ.ምበድሬዳዋ አሸዋ የገበያ ስፍራ  በተከሰተው የእሳት አደጋ የተጎዱ ወገኖችን በፍጥነት መልሶ ለማቋቋም የተሰሩ ስራዎች ተገመገሙ*****************በድሬዳ...
01/11/2024

ዜናKM+
ጥቅምት 22 2017 ዓ.ም

በድሬዳዋ አሸዋ የገበያ ስፍራ በተከሰተው የእሳት አደጋ የተጎዱ ወገኖችን በፍጥነት መልሶ ለማቋቋም የተሰሩ ስራዎች ተገመገሙ
*****************

በድሬዳዋ አሸዋ የገበያ ስፍራ በተከሰተው የእሳት አደጋ የተጎዱ ወገኖችን በፍጥነት መልሶ ለማቋቋም የድሬዳዋ አስተዳደር ኮሚቴዎችን በማዋቀር በርካታ ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ የሚታወቅ ነው ያለው የአስተዳደሩ መገናኛ ብዙሃን በዛሬው ዕለትም ኮሚቴው በእሳት አደጋው የተጎዱ የንግዱን ማህበረሰብ መልሰው ወደ ስራ ለማስገባት እየተሰሩ የሚገኙ ስራዎችን ሂደት ገምግሟል ሲል ዘግቧል::

በዚህም በአደጋው የተጎዱ የንግዱን ማህበረሰብ መልሶ ለማቋቋም እየተሰሩ የሚገኙ ስራዎችን ሪፖርት ኮሚቴው በማድመጥ ገምግሟል::

በዚህም ከ80 እስከ 85 ፐርሰንት የሚሆኑ የንግዱ ማህበረሰብ ወደ ስራ መግባታቸው ከመድረኩ የተገለፀ ሲሆን ሀብት የማሰባሰቡ ስራም በተጠናከረ መልኩ እየተሰራ እንደሆነና ይሄም ተጠናክሮ እንዲቀጥል የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ ተናግረዋል::

በአደጋው የተጎዱ ወገኖችን ለመርዳት በተለያዩ ጊዜ ቃል የገቡ የማህበረሰቡ ክፍሎች ቃላቸውን ተግባራዊ እንዲያደርጉና ሌሎችም ማህበረሰቦች ለተጎጂ ወገኖች ድጋፍ እንዲያበረክቱ ከመድረኩ ጥሪ ቀርቧል::

በአደጋው የተጎዱ ወገኖችን መልሶ ለማቋቋም በአስተዳደሩ በተከፈቱት አካውንቶች ማለትም

1.የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000637750201
2.ዳሽን ባንክ 5009786342011
3. አዋሽ ባንክ 013211367855100 እና
4. የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ 1001300318808 የሂሳብ ቁጥር በተጨማሪም በአቢሲንያና በራሚስ ባንክ ብሎም በተለያየ መልኩና በአይነትም ድጋፉ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ከመድረኩ ጥሪ ቀርቧል፡፡

 +ጥቅምት 22 2017 ዓ.ምየሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ኦርዲን በድሪ ሁለተኛውን ዙር የኮሪደር ልማት ስራ አስጀመሩ። *****************የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ...
01/11/2024

+
ጥቅምት 22 2017 ዓ.ም

የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ኦርዲን በድሪ ሁለተኛውን ዙር የኮሪደር ልማት ስራ አስጀመሩ።
*****************

የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ በዛሬዉ እለት ሁለተኛ ዙር በከተማ የኮሪደር ልማት ስራ አስጀምረዋል።

የሀረር ከተማ ታሪካዊነቷን ባለቀቀ መንገድ በከተማ እና በገጠረ የኮሪደር ልማት ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ርዕሰ መስተዳድር አቶ አርዲን በድሪ ገልፀዋል።

በ2017 በ3 ዘርፎች የሚከናወኑ የኮሪደር ልማት ስራ መሆናቸዉን ያነሱት ርዕሰ መስተዳደሩ በከተማ፣በገጠር እና በጁገል አለም አቀፍ ቅርስ መሆናቸዉን ተናግረዋል።

በጀጎል አለም አቀፍ የሚሰራዉ የኮሪደር ልማት ስራ ታሪካዊነቱን በጠበቀ መልኩ የሚከናወን መሆኑን ገልፀዋል።

የሚከናወነዉ የኮሪደር ልማት ስራ የእግረኛ መንገድ፤ የተሽከርካሪ፤ የሳይክል፤ የመንገድ መብራቶች እና የተለያዩ የዉበት ስራዎች መሆናቸዉን ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል።

በገጠር የሚከናወኑት የኮሪደር ልማት ስራዎች የተለያዩ የመንገድ መሰረተ ልማት እና የዉበት ስራዎች መሆናቸዉንም እስታውቀዋል ።

ከዚህ በተጨማሪም የኮሪደር ልማት ስራ ዋና አላማዉ የመኖሪያ ስፍራዎችን ምቹ የማድረግ እና የቅርስ ከተማ የሆነችዉን ሀረር ከተማን ለቱሪስት ሳቢ እንድትሆን ያለመ እንደሆነ ገልፀዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ አክለዉም ታሪካዊቷ ሐረር ከተማ መልማት ባለባት ልክ አለመልማቷን በመግለፅ የኮሪደር ልማት ስራዉ ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ በትልቅ ተነሳሽነት በመከናወኑ ትልቅ ለዉጦች እንደታዩ ተናግረዋል።

ለዚህ ስራ መሳካትም የከተማዉ እና የገጠሩ ማህበረሰብ የኔነት ስሜት ተሰምቶት አስፈላጊዉን ትብብር ማድረጋቸዉን በመግለፅ አሁንም ቀጣይነት እንዲኖረዉ አሳስበዋል።

በሁለተኛዉ ዙር ከተጀመረዉ የኮሪደር ልማት ስራ ከኢማም አህመድ እስታዲየም እስከ እንደራሴ ያለዉ በራስ አቅም የሚከናወን መሆኑን ተናግረዋል።

በመጀመሪያ ዙር በተሰራዉ የኮሪደር ልማት ስራ ለወጣቱ የስራ እድል ከመፍጠር አኳያ ትልቅ ሚና እንደነበረዉ ገልፀዋል።

ከተያዘዉ የኮሪደር ልማት ስራ ዉስጥ በከተማ የኮሪደር ልማት ከቀይ መስቀል እስከ አራተኛ 1.7 ኪ/ሜ ፣ ከጁኒየር ት/ቤት እስከ እንደራሴ 1 ኪ/ሜ እና ከእንደራሴ እስከ ቢራ ፋብሪካ 1.1 ኪ/ሜ እርዝማኔ ያለዉ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ተጀምሯል ሲል የዘገበው የክልሉ መገናኛ ብዙሃን ኤጀንሲ ነው ።

 +ጥቅምት 22 2017 ዓ.ምየአርሶ አደሩን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ የሚያደርገውን ድጋፍና ክትትል አጠናክሮ እንደሚቀጥል  የሀሮማያ ዩንቨርስቲ አስታወቀ፡፡ *************ዩንቨርስቲ...
01/11/2024

+
ጥቅምት 22 2017 ዓ.ም

የአርሶ አደሩን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ የሚያደርገውን ድጋፍና ክትትል አጠናክሮ እንደሚቀጥል የሀሮማያ ዩንቨርስቲ አስታወቀ፡፡
*************
ዩንቨርስቲው በምስራቅ ሀረርጌ ዞን ግራዋና ኩርፋጨሌ ወረዳዎች በምርመር እያባዛ ያለውን የስንዴ እና ሌሎች ሰብሎችን የምርጥ ዘር ምርምር ስራን ጎብኝተዋል።

ሀሮማያ ዩንቨርስቲ በምስራቅ ሀረርጌ ዞን ኩርፋ ጨሌ እና ግራዋ ወረዳዎች የስንዴ እና ሌሎች የእህል ምርጥ ዘር የማባዛት ስራ ጉብኝት አካሂደዋል፡፡

በዩንቨርስቲው የምርምርና ማህበረሰብ ጉዳይ ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር ኢሳቅ ዩሱፍ በወረዳዎቹ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ እየተሰራ ያለው ስራ አበረታች መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ስራዎቹን ለማጠናከር ና አርሶ አደሩ ተጠቃሚ እንዲሆን አስፈላጊውን ድጋፍ የሚያደርግ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
የግብርና ቴክኖሎጂን በአግባቡ ከመጠቀም አንፃር ባለሙያዎች ና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት መስራት እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡

የግረዋ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ጃፋር አብዶሽ ዩንቨርስቲው የአርሶአደሩን ኑሮ እንዲሻሻል እያደረገ ያለው ድጋፍ አበረታች ለውጥ እያመጣ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ድጋፉ ምርትና ምርታማነት እንዲሻሻል እያገዘ መሆኑን ገልፀው ወረዳውም አስፈላጊውን ትብብር የሚያደርግ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በኩርፋ ጨሌና ግረዋ ወረዳዎች ከአካባቢው አየር ንብረት ጋር የሚጣጣሙ የስንዴ ፣ገብስ ፣ምስር፣ባቄላ፣ ጤፍ ና የተለያዩ የእህል ዘሮች እየለሙ ይገኛል፡፡

 +ጥቅምት 22 2017 ዓ.ም"ፓርቲያችን ብልፅግና ድህነትን በማቃለል ዘላቂ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በትኩረት እየሰራ ይገኛል" አቶ አብዱልሀኪም ኡመር *********ብልፅግና ፓርቲ ድህነ...
01/11/2024

+
ጥቅምት 22 2017 ዓ.ም

"ፓርቲያችን ብልፅግና ድህነትን በማቃለል ዘላቂ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በትኩረት እየሰራ ይገኛል" አቶ አብዱልሀኪም ኡመር
*********

ብልፅግና ፓርቲ ድህነትን በማቃለል ዘላቂ የምግብ ዋስትናን በቤተሰብ ደረጃ ለማረጋገጥ በትኩረት እየሰራ ይገኛል ሲሉ የሐረሪ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ አብዱልሀኪም ኡመር ተናገሩ

በክልሉ ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ንቅናቄ አካል የሆነው ቴክኒካል ኮሚቴ በቀጣይ ትኩረት አቅጣጫዎች ላይ መክረዋል።

በምክክር መድረኩ ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለመሸጋገር በሚደረገው ጥረት የባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ አሰራር ወሳኝ መሆኑን የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ አብዱልሀኪም ኡመር ተናገሩ።

በተለይም በግብርናው ዘርፍ የተጀመሩ ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ ምግብ ዋስትናችንን በማረጋገጥና ከተረጂነት ለመላቀቅ ቅንጅታዊ ርብርብ እንደሚደረግ ተናግረዋል ።

በተጨማሪም በግብርናና በግብርና ውጪ ባሉት የልማት ስራዎች በማስፋት ከተረጂነት ወደ ምርታማነትን ማሸጋገር እንደሚገባ አንስተዋል።

በተለይም በውሃ ፣ በጤና ፣ በግብርናና በስራ እድል ፈጠራ በሁሉም አከባቢዎች ተደራሽ በማድረግ ዜጋ ተኮር ስራዎችን ማጎልበት እንደሚገባ ተናግረዋል።

ደህነትን በማቃለል በዘላቂነት የምግብ ዋስትናን በቤተሰብ ደረጃ በማረጋገጥ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት እንደሚሰራ ተናግረዋል ።

ከተረጂነት ወደ ምርታማነት በሚደረገው ሽግግር የባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊና የቀጣይ ትኩረት አቅጣጫዎችና የሚተገበሩ እቅዶች ላይ ሰፊ ውይይት በማድረግ አቅጣጫ መቀመጡን ከቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቱ ይፋዊ የፌስቡክ ገፅ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

Address

Jijiga

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when KM+ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Share