Neba man

Neba man ከሀገር ውስጥ እንዲሁም ከውጪ ወቅታዊና ተዓማኒነት ያላቸውን ዜናዎችን ፡ልዩ ክስተቶችን እና መረጃዎችን ማድረስ።

15/07/2024
" አዲስ እና ሰፋ ያለ መንግሥት ለመመሥረት ከሕዝቤ ጋር ውይይት አደርጋለሁ ! " - ሩቶ_______________¶_______________________የኬንያ ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ካቢኔያቸ...
11/07/2024

" አዲስ እና ሰፋ ያለ መንግሥት ለመመሥረት ከሕዝቤ ጋር ውይይት አደርጋለሁ ! " - ሩቶ
_______________¶_______________________
የኬንያ ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ካቢኔያቸውን በመበተን ሚኒስትሮቻቸውን ከስልጣን ያባረሩት ሕዝቡ ያነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ መሆኑን አሳውቀዋል።

ሩቶ ፥ " ኬንያውያንን በመስማት ካቢኒዬን መርምሬ ነው የወሰንኩት " ብለዋል።

" አዲስ እና ሰፋ ያለ መንግሥት ለመመሥረት ከሕዝቤ ጋር ውይይት አደርጋለሁ " ሲሉም አሳውቀዋል።

ከሥራቸው የማይባረሩት ምክትል ፕሬዝዳንቱና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው የሚያገለግሉት የካቢኔው ዋና ፀሐፊ ሥልጣናቸው ላይ ይቆያሉ።

ሌሎቹ በጠቅላላ የካቢኔያቸው አባላት ሚኒስትሮች ተባረዋል።

የፋይናንስ ረቂቅ ሕጉን ተከትሎ ፥ " ግብር ሊጨመርብን አይገባም በቃን ! ፣ ተጨማሪ ግብር አንከፍልም፣ ሕጉ ኑሮው ያስወድድብናል " በማለት ወጣቶች በማህበራዊ ሚዲያ የጀመሩት ተቃውሞ ወደ አደባባይ ተቃውሞ ተሸጋግሮ የ39 ሰዎች ህይወት ከጠፋ በኋላ ሩቶ ሕጉን ሰርዘውታል።

ምንም እንኳን ሕጉ ሙሉ በሙሉ ቢሰረዝም ተቃውሞው አላበቃም።

ፕሬዜዳንቱ ባልተለመደ ሁኔታ ከተቃዋሚ ወጣቶች ጋር በኦንላይን (X) ምንም አይነት ገደብ የሌለው ግልጽ ሕዝባዊ ውይይት አድርገው ነበር ፤ ያም ቢሆን ሕዝባዊ ጥያቄውን አላስቆመውም።

ፕሬዜዳንቱ በሙስና የተዘፈቁ ሚኒስትሮችን ጠራርገው እንዲያባርሩና ካቢኔውን እንዲበትኑ ጥሪ ሲቀርብ ነበር።

ይህን ተከትሎ ዛሬ ፕሬዜዳንቱ ካቢኔያቸውን በትነዋል። " የሕዝቤን ድምጽ በመስማት ነው እርምጃውን የወሰድኩት " ብለዋል።




ሳፋሪኮም የደንበኞቹን መረጃ ለመንግስት አሳልፎ እንዳልሰጠ ገልጸ።____________________________________በኢትዮጵያ ሁለተኛው የቴሌኮም አገልግሎት ሰጪ የሆነው ሳፋሪኮም  የደ...
26/06/2024

ሳፋሪኮም የደንበኞቹን መረጃ ለመንግስት አሳልፎ እንዳልሰጠ ገልጸ።
____________________________________
በኢትዮጵያ ሁለተኛው የቴሌኮም አገልግሎት ሰጪ የሆነው ሳፋሪኮም የደንበኞቹን መረጃ ለኢትዮጵያ መንግስት አልሰጠሁም ብሏል።

የሀገሪቱን የመረጃ ጥበቃ ህግ መሰረት በማድረግ የደንበኞቹን ነፃነት እንደሚያከብር እና በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ካልሆነ በስተቀር የትኛውንም የደንበኞቹን መረጃ ለሌላ አካል አሳልፎ እንደማይሰጥ ኩባንያው በመግለጫው አስታውቋል።

ሳፋሪኮም የደንበኞችን መረጃ ለመንግስት እንዲያቀርብ እስካሁን የፍርድ ቤት ትዕዛዝ እንዳልደረሰው አስረድቷል።

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የደንበኞቹን ሚስጥራዊነት ያለው መረጃ ለኢትዮጵያ መንግስት አጋርቷል ተብሎ በማህበራዊ ሚዲያ እየተወራ ነው። ኩባንያው ዛሬ በዚህ መግለጫ ሁሉንም አሉባልታዎች ውድቅ አድርጓል ።

ዣቪ የባርሳ ዋና አሰልጣኝ ሆኖ እንደሚቀጥል ተገለፀ።______________________________________በጥር ወር የባርሴሎና ዋና አሰልጣኝ ዣቪ በውድድር ዘመኑ መጨረሻ ቡድኑን የመል...
25/04/2024

ዣቪ የባርሳ ዋና አሰልጣኝ ሆኖ እንደሚቀጥል ተገለፀ።
______________________________________
በጥር ወር የባርሴሎና ዋና አሰልጣኝ ዣቪ በውድድር ዘመኑ መጨረሻ ቡድኑን የመልቀቅ ፍላጎት እንዳላቸው አስታው ነበር።

ነገር ግን፣ ብዙም ሳይቆይ፣ ዣቪ ውሳኔውን እንደለወጠ እና ከአሁን በኋላ ከቡድኑ ጋር መስራታቸውን እንደሚቀጥሉ ዘገባዎች ቀርበዋል እነዚህ መረጃዎች ኦፊሴላዊ ማረጋገጫ አላቸው።

እ.ኤ.አ. ኤፕሪል 25 ላይ አሰልጣኙ ውሳኔውን ያሳወቀው በ Xavi እና በባርሴሎና አለቃ ጆአን ላፖርታ መካከል በተደረገ ጋዜጣዊ መግለጫ ነበር።

“ዛሬ ዣቪ የባርሳ የመጀመሪያ አሰልጣኝ ሆኖ እንደሚቀጥል ሳበስር ደስ ብሎኛል። በዋና አሰልጣኝነት መስራቱን እንደሚለቁ ገልፀው ነበር አሁን ግን ጥሩ ዜና አግኝቻለሁ እናም ይህንን ሥራ ለመቀጠል ፍላጎት እንዳለው ገልጿል እናም ይህ ለባርሳ ጥሩ ዜና እንደሆነ እርግጠኞች ነን።

ምንጭ-daily sport

09/04/2024

ኢድ ሙባረክ!!

29/03/2024
23/03/2024
በቅርቡ ይለቀቃል !!
09/11/2023

በቅርቡ ይለቀቃል !!

አንዳንድ ሀብታም ከመንግስትም በላይ ነው--------------------------------------መንግስት ኢንተርኔት ዘጋብህ ? ችግር የለም ።ወራሪዋ እስራኤል ፡ ጋዛን ወደ ፍርስራሽ ስት...
28/10/2023

አንዳንድ ሀብታም ከመንግስትም በላይ ነው
--------------------------------------
መንግስት ኢንተርኔት ዘጋብህ ? ችግር የለም ።

ወራሪዋ እስራኤል ፡ ጋዛን ወደ ፍርስራሽ ስትቀይር መሰረተ ልማቶች ወድመዋል ።በዚህ ኢሰብአዊ በሆነ የቦንብ ድብደባ. . መብራትና ውሀ ብቻ ሳይሆን ምንም
አይነት የኢንተርኔት አገልግሎት እንዳይሰራ በመደረጉ መኖሪያቸው ፈርሶና ፡በግዳጅ እንዲፈናቀሉ የተደረጉ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ፍልስጤማውያን የእርዳታ
ያለህ እያሉ ነው ።

ሆኖም ምንም አይነት የኢንተርኔት ግንኙነት ስለሌለ የተባበሩት መንግስታትን ጨምሮ ብዙ የሰብአዊ እርዳታ ተቋማት ለነዚህ የጋዛ ነዋሪዎች እርዳታ ማድረስ
አልቻሉም ።

እና ይህ ችግር የሆነባቸው ተቋማትና ፡ ተፅእኖ ፈጣሪ ግለሰቦች የ Space x ን ባለቤት ኤሎን መስክን ፡ አግዘን ሲሉ ጠየቁት ።

ለተቸገሩ ሰወች ለመድረስ የመገናኛ መሳሪያዎች ወሳኝ ናቸውና የእስራኤል መንግስት የከለከለንን የኢንተርኔት አገልግሎት ፡ አንተ ስጠን አሉት ።

በነገራችን ላይ ኤለን መስክ ወደ ጠፈር ባመጠቃቸው ብዛት ያላቸው ሳተላይቶች አማካኝነት የሚሰራው የStarlink የኢንተርኔት አገልግሎት ፡ የትኛውም መንግስት ማፈን እና ማቋረጥ አይችልም ።

እናም ይህ የሰብአዊነት ጥያቄ የቀረበለት ኤለን መስክ ፡ ከጥቂት ሰአታት በፊት ፡በጋዛ ለሚሰሩ የሰብአዊ እርዳታ ድርጅቶችና ፡ ለራሱ ለተባበሩት መንግስታት
ጭምር ፡ የኢንተርኔት አገልግሎት ለመስጠት ፈቃደኛ መሆኑን አስታውቋል ።....

tesfaye

ፍልስጤማውያን ዛሬ በአልናስር ሆስፒታል ለጁምዓ ሰላት ተሰባስበዋል።__________________________ፍልስጤማውያን እስራኤል ጋዛን በአየር መደብደብ ከጀመረች በ21 ኛው ቀን  ጋዛ ዉስ...
27/10/2023

ፍልስጤማውያን ዛሬ በአልናስር ሆስፒታል ለጁምዓ ሰላት ተሰባስበዋል።
__________________________
ፍልስጤማውያን እስራኤል ጋዛን በአየር መደብደብ ከጀመረች በ21 ኛው ቀን ጋዛ ዉስጥ በሚገኘው አልናስር ሆስፒታል ጁምአ ሰላት ለመስገድ ተሰባስበዋል።

በእስራኤል ጦር የተከበቡና ያለምንም ማቋረጥ ለሶስት ተከታታይ ሳምንታት የቦምብ ድብደባ ናዳ ሲወርድባቸው የቆዩት ሰፈሮች ሙሉ በሙሉ ወድመዋል።

በዚህ ድብደባ ከ 7000 በላይ ፍልስጤማውያን ተገድለዋል እንዲሁም ከፍተኛ የሆነ ሰብዓዊ ቀውስ ተከስቷል።

በሁለት እጁ የሁለት ልጆቹን ጀናዛ ይዞ የሚሄድ ጠንካራ አባት ያለባት ሀገር ፍልስጤም ብቻ ናት የአላህ ድል አድራጊ አድርጋቸው
26/10/2023

በሁለት እጁ የሁለት ልጆቹን ጀናዛ ይዞ የሚሄድ ጠንካራ አባት ያለባት ሀገር ፍልስጤም ብቻ ናት የአላህ ድል አድራጊ አድርጋቸው

Address

Butajira

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:00
Tuesday 09:00 - 17:00
Friday 09:00 - 17:00
Saturday 09:00 - 17:00
Sunday 09:00 - 17:00

Telephone

+251966515051

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Neba man posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Share