የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት Butajira City Communication Office

  • Home
  • Ethiopia
  • Butajira
  • የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት Butajira City Communication Office

የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት Butajira City Communication Office The official Butajira city Gov't Communication fb page-ይህ ትክክለኛው የቡታጅራ ከተማ የመንግስት ኮሙኒኬሽን fb ፔጅ ነው፦

የስራ እድል ፈጠራ ምክር ቤቱ የተቋሙን የ2016 በጀት ዓመት የ9 ወር የስራ አፈፃፀም ላይ ውይይት አካሄደሚያዚያ 10/2016 (ቡታጅራ ኮሙኒኬሽን)የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር የስራ እድል ፈጠ...
18/04/2024

የስራ እድል ፈጠራ ምክር ቤቱ የተቋሙን የ2016 በጀት ዓመት የ9 ወር የስራ አፈፃፀም ላይ ውይይት አካሄደ

ሚያዚያ 10/2016 (ቡታጅራ ኮሙኒኬሽን)
የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር የስራ እድል ፈጠራ ምክር ቤት የስራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ጽ/ቤት የ2016 በጀት ዓመት የ9 ወራት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ገምግሟል።

በከተማዋ በስራ እድል ፈጠራ ዘርፍ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች አስመልክቶ ጠንካራ የስራ እንቅስቃሴዎች እንዲሁም በክፍተት የሚታዩና መሻሻል የሚገባቸው ነጥቦች ላው ውይይት ተደርጓል።

የተሻሉ ስራዎችን በማስቀጠል ክፍተቶችን ልዩ ትኩረት በመስጠት ለማስተካከል መስራት እንደሚገ ተጠቁሟል።

በመጨረሻም ባለድርሻ አካላት ዘርፉን ለመደገፍ ሲያደርጉት የቆየውን የስራ እንቅስቃሴ በመገምገም የቀጣይ አቅጣጫ በመያዝ መድረኩ ተጠናቋል።

የኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች ስራቸውን ለማስፋት፣ለማሳደግ የስራ ዕድልና የገበያ ትስስር ለመፍጠር በትኩረት እንደሚሰራ ተገለፀ፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡    ፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡   ...
18/04/2024

የኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች ስራቸውን ለማስፋት፣ለማሳደግ የስራ ዕድልና የገበያ ትስስር ለመፍጠር በትኩረት እንደሚሰራ ተገለፀ
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡ ፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡ ፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡ ፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ሚያዚያ 10/2016 (ቡታጅራ ኮሙኒኬሽን)
የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር ስራ አስፈፃሚዎች በሌማት ትሩፋት ከተማ ግብርና እና የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የስራ እንቅስቃሴ የመስክ ምልከታ አድርገዋል።

የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አብዱ አህመድ፣ ምክትል ከንቲባና የኢንተርፕራይዝ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደረጀ ራህመት እና በብልፅግና ጽ/ቤት የፖለቲካ ሪዮተዓለም ዘርፍ ኃላፊ አቶ ኑረዲን መሀመድ በሌማት ትሩፋት በከተማ ግብርና እና በወተት ማቀነባበሪያ ዘርፍ የተሰማሩ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የስራ እንቅስቃሴ የመስክ ምልከታ አድርገዋል።

የኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች በመካከለኛና በአነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ስራቸውን ለማስፋትና ለማሳደግ በተጨማሪም የስራ ዕድል እና የገበያ ትስስር እየገጠሙ ያሉ ችግሮች እና መፍትሄዎች ላይ ከማህበራቶች ጋር ውይይት አድርገዋል።

በውይይታቸውም የኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች ስራቸውን ለማስፋትና ለማሳደግ እንዲሁም የስራ ዕድልና የገበያ ትስስር ለመፍጠር በትኩረት እንደሚሰራ ተጠቁሟል።

በምስቅ ጉራጌ ዞን በቡታጅራ ከተማ  በሌማት ትሩፋት እየተሰራ ያለው ስራ በሀገር  ደረጃ ሞዴል የሚሆን መሆኑን ክቡር ሚኒስትር ገብረመስቀል ጫላ ገለፁ፦ሚያዚያ 9/2016 ቡታጅራበንግድና ቀጣና...
17/04/2024

በምስቅ ጉራጌ ዞን በቡታጅራ ከተማ በሌማት ትሩፋት እየተሰራ ያለው ስራ በሀገር ደረጃ ሞዴል የሚሆን መሆኑን ክቡር ሚኒስትር ገብረመስቀል ጫላ ገለፁ፦

ሚያዚያ 9/2016 ቡታጅራ
በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ገብረመስቀል ጫላ የተመራ ልዑክ በቡታጅራ ከተማ አስተዳደር ያደረገውን የመስክ ምልከታ አስመልክቶ ግብረ መልስ ሰጥቷል።

የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር አቶ ገብረመስቀል ጫላ በሌማት ትሩፋት እየተሰራ ያለው ስራ በሀገር ደረጃ ሞዴል የሚሆን መሆኑን ገልፀዋል።

በንብ ማነብ በማር ምርት እና ማቀነባበር በከተማዋ እየተሰራ ያለው ስራ በሀገር አቀፍ ደረጃ ሞዴል የሚሆን መሆኑን ገልፀው በተመሳሳይ በወተት ምርት በዶሮ እርባታና በእንቁላል ምርት የሚበረታታ ስራ እየተከናወነ መሆኑን ጠቁመዋል።
ምርታማነትን የበለጠ ለማሳደግ የዝርያ ማሻሻያ ላይ መስራት እንደሚገባ አመላክተዋል።

ሚኒስትሩ በቡታጅራ ከተማ አገልግል ህብረት ስራ ማህበር ለሌሎች ከተሞች ተሞክሮ የሚሆን ስራ እየሰራ መሆኑንም ገልፀዋል።
ከፍብሪካዎች ከመጋዘኖች ወደ ሰንበት ገበያ የሚመጡ ምርትቶች መኖራቸው፤አርሶ አደሩ በቀጥታ ገበያ አቅርቦ በተመጣጣኝ ዋጋ እየሸጠ መሆኑ የሚበረታታ ነው ብለዋል።

በመጨረሻም በምስራቅ ጉራጌ ዞን በቡታጅራ ከተማ በሌማት ትሩፋትና በሌሎች ስራዎች እየተገኘ ያለው ውጤት የዞኑና የከተማዋ አመራር የመንግስትን ኢኒሼቲቭ ወደ ተግባር በመግባት በዕቅድ እየመሩ እንደሆነ የሚያሳይ መሆኑንም ጠቁመዋል።

የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አብዱ አህመድ ገበያን ለማረጋጋት እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻሉ ነው የሌማት ትሩፋት ተግባር በትኩረት እየተሰራ በመሆኑ በቀን 23450 ሊትር ወተት ማምረት እንደተቻለ ገልፀዋል።

ከልማት ስራው ጎንለጎን በሁሉም ዘርፍ ህገ-ወጥነትን እና ህገ-ወጥ ንግድን በመከላከል ገበያን ለማረጋጋት በትብብር እየተሰራ እንደሆነ ጠቁመዋል።
በከተማዋ የመሰረተ ልማት ተደራሽ ለማድረግና የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሰራ እንደሆነም ገልፀዋል።

የምስራቅ ጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ክቡር ሙስጠፋ ሀሰን ለተጠቃሚው ዋጋ ለማረጋጋት የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል፤ ህገ -ወጥነትን ለመከላከል በትኩረት ይሰራል ብለዋል።

ለተጠቃሚው ዋጋ ለማረጋጋት የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል፤ ህገ -ወጥነትን ለመከላከል በትኩረት ይሰራል ብለዋል።
የዘገበው የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን ነው።

ሚያዝያ 09/2016ዓ.ም ቡታጅራ የምስራቅ ጉራጌ ዞን እግር ኳስ ቡድን የማረቆ ልዩ ወረዳ እግር ኳስ ቡድን 3:1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል። የእግር ኳስ ቡድናችን በምደቡ ያለምንም ሽንፈት ...
17/04/2024

ሚያዝያ 09/2016ዓ.ም ቡታጅራ

የምስራቅ ጉራጌ ዞን እግር ኳስ ቡድን የማረቆ ልዩ ወረዳ እግር ኳስ ቡድን 3:1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

የእግር ኳስ ቡድናችን በምደቡ ያለምንም ሽንፈት ሶስት አሸንፎ አንድ አቻ በመውጣት በ10 ነጥብ የሩብ ፍፃሜው መቀላቀሉን አረጋግጧል።

በጨዋታ ብርቱ ፉክክር ማድረግ የቻለው የማረቆ ልዩ ወረዳ ከሶስት ከተጫወታቸው ጨዋታዎች አንድ አሽንፎ አንድ አቻ በመውጣት አንድ ሽንፈት አስተናግዶ በ4 ነጥብ በመያዝ ከምድቡ ለማለፍ ከከምባታ ዞን የሚያደርገው ጨዋታው ይጠብቃል።

በአሁኑ ሰዓት በምድቡ ሁለተኛው ጨዋታ ከምባታ ከቀቤና እያካሄዱ ይገኛል።

ዘገባው የምስራቅ ጉራጌ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

የመንግስት ኮሚኒኬሽን ከህዝብ የሚነሱ አስተያየቶች በአግባቡ በማሰባሰብና በመዘገብ በመንግሥት እና በህዝብ መካከለ  ያለውን ግንኙነት ማጠናከር እንደሚገባ ተገለፀ።ሚያዚያ 8/2016 ቡታጅራየቡ...
16/04/2024

የመንግስት ኮሚኒኬሽን ከህዝብ የሚነሱ አስተያየቶች በአግባቡ በማሰባሰብና በመዘገብ በመንግሥት እና በህዝብ መካከለ ያለውን ግንኙነት ማጠናከር እንደሚገባ ተገለፀ።

ሚያዚያ 8/2016 ቡታጅራ
የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር የመንግሥት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ከባለድርሻ አካላት ጋር የ9 ወር ዕቅድ አፈፃፀም ገምግሟል።

በመድረኩ ጽ/ቤቱ ካለበት ሀላፊነትና ተግባር አንፃር ከሚዘገቡ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች በተጨማሪ የህብረተሰቡ አስተያየት ተሰብስቦ በተለያዩ የሚዲያ አማራጮች መዝግብ እንደሚያስፈልግ ተገልጿል።

የጽ/ቤቱ ሀላፊ አቶ ሀይሉ ወ/ገብርኤል በበጀት ዓመቱ የተለያዩ የህዝብ ግንኙነት ስራ መሰራቱን ገልጸው በቀጣይም መረጃ በተቀላጠፈ መልኩ ተደራሽ ለማድረግ ተቋማት የተለየዩ ዝግጅቶች ሲኖሩ አስቀድመው ማሳወቅ እንዳለባቸው ተናግረዋል ።

በመድረኩ የተነሱ አስተያየቶች ለቀጣይ ግብአት የሚሆኑ መሆናቸው ገልጰዋል።

በጽ/ቤቱ የልማት እቅድ ክትትል ዝግጅት ቡድን መሪ አቶ ግዛቸው በለጠ በበጀት ዓመቱ በህትመት በኤሌክትሮኒክስና በገጸ-ለገጽ የተከናወኑ ተግባራት አቅርበው ውይይት የተደረገ ሲሆን ፈጣን መረጃ በማህበራዊ ሚዲያ በመልቀቅና ተከታይ በማፍራት የተሻለ አፈፃፀም እንደነበር አብራርተዋል።

ተሳታፊዎቹም ህብረተሰቡ በአንዳንድ ተቋማት ላይ የሚያነሷቸው ቅሬታዎች የሚዲያ ሽፋን እንዲያገኙ ቢደረግ የህትመት ውጤቶች ለሁሉም ሴክተር ተደራሽ መሆን እንዳለበት አስተያየት ሰጥተዋል ።

ተጨማሪ የመረጃ አማራጮቻችን፦
ቴሌግራም https://t.me/ButajiraCommunication/58
ፌስቡክ https://www.facebook.com/buta1921/
ዩቲዩብ
https://youtube.com/
ትዊተር https://mobile.twitter.com/ButajiraB
ኢንታግራም https://www.instagram.com/butajirab

ግንባር ቀደም የሆኑ ሴቶች የማህፀን ጫፍ ካንሰር ምርመራ አስፈላጊነት ላይ ግንዛቤ መፍጠር እንደሚገባቸው ተገለፀ።ሚያዚያ 8/2016 ቡታጅራ የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር የብልፅግና ፓርቲ  ሴቶች...
16/04/2024

ግንባር ቀደም የሆኑ ሴቶች የማህፀን ጫፍ ካንሰር ምርመራ አስፈላጊነት ላይ ግንዛቤ መፍጠር እንደሚገባቸው ተገለፀ።

ሚያዚያ 8/2016 ቡታጅራ
የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር የብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ ጽ/ቤት ከጤና ጽ/ቤት ጋር በመተባበር የማህፀን ጫፍ ካንሰር ምርማራ አስፈላጊነት እና የበሽታውን አስከፊነትን አስመልክቶ ግንዛቤ የሚፈጥር መድረክ አዘጋጅተዋል

በቡታጅራ ከተማ አስተዳደር የጤና ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ትዕግስት ተክሌ የማህፀን ጫፍ ካንሰር ለረዥም ጊዜ ምልክት ሳያሳይ ወደ አስከፊ ደረጃ የሚደርስ ስለሆነ ቅድመ ምርመራ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን አብራርተዋል።

በሽታው በመጀመሪያ ደረጃ ምንም አይነት ምልክት የሌለውና በምርመራ ብቻ የሚታወቅ ነው ለረዥም ጊዜ ምልክት ሳያሳይ በድንገት ለህመም የሚዳርግ መሆኑን ገልፀው ሁሉም እድሜያቸው የደረሱ ሴቶች ምርመራውን ማድረግ እንዳለባቸው አሳስበዋል።

በከተማዋ ምርመራውን የሚያደርጉ ጥቂቶች መሆናቸውን በመጠቆም ግንባር ቀደም የሆኑ ምርመራው እንዲደረግ መስራት እንዳለባቸው ጠቁመዋል።

በቡታጅራ ከተማ አስተዳደር በብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት የሴቶች ሊግ ጽ/ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሪት ሰብለ ተክሌ የበሽታውን አስከፊነት በሚገባ በመረዳት ቀድሞ ምርመራ በማድረግ ሌሎች ሴቶች ምርመራውን እንዲያደርጉ ግንባር ቀደም የሆኑ የመንግስት ሰራተኞችና የመሰረታዊ ድርጅት አባሎች ግንዛቤ ሊፈጥሩ እንደሚገባ ገልፀዋል።

በሽታውን ቀድሞ መካለካል እንዲቻል ምርመራው አስፈላጊ በመሆኑ ምርመራ ማድረግ ምርጫ የሌለው መሆኑን ጠቁመዋል።ከወሊድ ጋር በተያያዘም ግንዛቤ የመፍጠር ስራ እንደሚሰራ ገልፀው ቅድመ መከላከል ላይ ትኩረት ሊደረግ ይገባል ብለዋል።
የዘገበው የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን ነው
ተጨማሪ የመረጃ አማራጮቻችን፦
ቴሌግራም https://t.me/ButajiraCommunication/58
ፌስቡክ https://www.facebook.com/buta1921/
ዩቲዩብ
https://youtube.com/
ትዊተር https://mobile.twitter.com/ButajiraB
ኢንታግራም https://www.instagram.com/butajirab

ሚያዝያ 8/2016 ዓ.ም(የቡታጅራ መንግስት ኮሙኒኬሽን)በምስራቅ ጉራጌ ዞን በቡታጅራ ከተማ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ ለማድረግ የተለያዩ የግብርና ምርቶች በተመጣጣኝ ...
16/04/2024

ሚያዝያ 8/2016 ዓ.ም(የቡታጅራ መንግስት ኮሙኒኬሽን)
በምስራቅ ጉራጌ ዞን በቡታጅራ ከተማ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ ለማድረግ የተለያዩ የግብርና ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ እያቀረበ ነው

የኢፌድሪ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ገብረ መስቀል ጫላ እና ሌሎች የፌደራል ፣ የክልልና የዞን የመንግስት የስራ ኃሌፊዎች በቡታጅራ ከተማ የሌማት ትሩፋትና የኢንዱስትሪ ልማት ስራዎችን እንዲሁም የሰንበት ገበያ እንቅስቃሴ የመስክ ምልከታ አድርገዋል።

ሚኒስትሩ በመስክ ምልከታቸው ወቅት እንደገለፁት ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች በተመጣጣኝ ዋጋ የግብርና እና የኢንዱስትሪ ልማት ምርቶችን ለማስተሳሰር መንግስት የዘረጋው አሰራር ውጤታማ መሆኑን በተግባር ያሳየ ነው ብለዋል።

የሰንበት ገበያ አምራቹን ከሸማቹ ጋር በቀጥታ በማገናኘት ህገ ወጥ ንግድን ለመከላከል ሚናው የጎላ መሆኑንም ጠቁመዋል።

እንደ ሚኒስትሩ ገለፃ በቀጣይ የምርት አቅርቦትን ያለማቋረጥ በተከታታይ እንዲቀርብ ሰፊ ስራ በመስራት የምርትን ተደራሽነት ከፍ እንዲል መስራት ይገባል ብለዋል።

በክልሉ ተዘዋውረው በተመለከቱባቸው አካባቢዎች በየደረጃው ያለው አመራር በቅንጅት እየሰራ እንደሚገኝ መታዘብ መቻላቸውን የተናገሩት ሚኒስትር ገብረ መስቀል በምርጥ ተሞክሮ የተለዩትን የማስፋፋት ስራ በቀጣይ በትኩረት እንደሚሰራም ገልፀዋል።

የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አብዶ አህመድ እንግዶቹን በመቀበል በከተማዋ ላይ የሚገኙና ሞዴል የግብርናና የኢንደስትሪ ቦታዎችን ተዘዋውረው አስጎብኝተዋል።

ከንቲባው በጉብኝቱ ወቅት እንደገለፁት በከተማዋ የኑሮ ውድነቱን ለማረጋጋት የሰንበት ገበያ ፈጥሮ አርሶ አደሩና ሸማቹ ማህበረሰብ በቀጥታ በማገኔኘት የፋብሪካና የግብርና ውጤቶች በተመጣጣኝ ዋጋ እንደሚቀርቡ ሰፊ ስሬዎች ተሰርቷል ብለዋል።

የሰንበት ገበያ በመጀመሩ ህብረተሰቡ ደስተኛ ከመሆኑም በላይ ለአርሶ አደሩም የገበያ ትስስር መፍጠር መቻሉንም ጠቁመዋል።
ይህም በቡታጅራ በከተማና በዙርያው በርካታ ሞዴል አርሶ አደሮች እንዲፈጠሩ ማነሳሳቱንም አሳስበዋል።

በከተማዋ የሰንበት ገበያን ከተጀመረ የቆየ ቢሆንም ተጠቃሚው በተግባር ለውጥ ማምጣት በመቻሉ የማስፋፋት ስራ እየተሰራ መሆኑንም ከንቲባው ገልፀዋል።

ሚያዚያ፦8/2016 ዓ.ም(ቡታጅራ ኮሙኒኬሽን)በሆስፒታሉ ለረጅም ጊዜ ተበላሽቶ የቆየው የራጅ ምርመራ ማሽን አሰርቶ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን አስታወቀየቡታጅራ አጠቃላይ ሆስፒታል ለረጅም ጊዜ...
16/04/2024

ሚያዚያ፦8/2016 ዓ.ም(ቡታጅራ ኮሙኒኬሽን)
በሆስፒታሉ ለረጅም ጊዜ ተበላሽቶ የቆየው የራጅ ምርመራ ማሽን አሰርቶ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን አስታወቀ

የቡታጅራ አጠቃላይ ሆስፒታል ለረጅም ጊዜ በብልሽት ምክንያት ተቋርጦ የነበረው የራጅ ምርመራ( X-ray) አግልግሎት መስጫ መሳርያ አሰርቶ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን አስታውቋል።

የተበላሸውን እቃ ከውጪ ለማስመጣት ባደረገው ጥረት ሆስፒታሉ ከአጋር ድርጅት ጋር ባለው የጠበቀ ግንኙነት የአለም አቀፍ የስነ-ተዋልዶ የስልጠና ማዕከል ያለውን የጠበቀ ግንኙነት በመጠቀምና በማስተባበር ብልሽት የገጠመውን መሳሪያ ከውጪ በማስመጣት ጥገና ተደርጎ አሁን ላይ በተሻለ ደረጃ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን አስታውቋል።

ሆስፒታሉ ተጠቃሚው ማህበረሰብ በቅርበት የተሟላ የህክምና አገልግሎት እንዲያገኝ ከዚህ በፊት ብልሽት የገጠመውን የኬሚስትሪ ማሽን ከአስመጭው ድርጅት ጋር በመነጋገር ከውጪ የተበላሸውን እቃ ለማስመጣት ባደረገው ጥረት እቃው በቅርብ ጊዜ እንደሚገባ እና ማሽኑ አስፈላጊውን ጥገና ተደርጎለት አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምርም ገልጿል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ የቡታጅራ አጠቃላይ ሆስፒታል የማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት ሆስፒታሉ የማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት በተለያዩ ጊዜያት ለማህበረሰብ የነፃ አገልግሎት እየሰጠ ሲሆንበተለያዩ ጊዜያት በቡታጅራ ከተማ አስተዳደር እና በመስቃን ወረዳ በሚገኙ አምስት ትምህርት ቤቶች 380 ተማሪዎች የአይን ምርመራ በማድረግ ችግር ላለባቸው 38 ተማሪዎች በዛሬው ዕለት በነፃ የአይን መነፅር ድጋፍ አድርጓል።

ሚያዝያ 07/2016 ዓ.ም (ቡታጅራ ኮሙኒኬሽን)የምስራቅ ጉራጌ ዞን እግር ኳስ ቡድን የምድቡን 3ኛ ጨዋታ ከቀቤና ልዩ ወረዳ ጋር አድርጎ ነጥብ ተጋርቶ ወጥቷል። ባለፉት 2 የምድብ ጨዋታዎች ...
15/04/2024

ሚያዝያ 07/2016 ዓ.ም (ቡታጅራ ኮሙኒኬሽን)
የምስራቅ ጉራጌ ዞን እግር ኳስ ቡድን የምድቡን 3ኛ ጨዋታ ከቀቤና ልዩ ወረዳ ጋር አድርጎ ነጥብ ተጋርቶ ወጥቷል።

ባለፉት 2 የምድብ ጨዋታዎች በድል ያጠናቀቀው የምስራቅ ጉራጌ ዞን እግር ኳስ ቡድን የዛሬው ጨዋታ ማሸነፍ ቢችል በምድቡ አለፊ መሆኑ ያረጋግጥ ነበር።

ተጋጣሚው የቀቤና ልዩ ወረዳ ቡድን ከትላንት በስቲያ በማረቆ አቻው ሽንፈት ያስተናገደ ሲሆን የምድብ ዛሬ ያደረገውን ጨዋታ የውድድሩ 2ኛው ጨዋታ ነው።

በሁለቱም ቡድኖች በኩል የተሻለ ዕድል ለማግኘት ብርቱ ፍክክር ቢያደርጉም ሙሉ የጨዋታው ክፍለ ጊዜ አንድ አቻ በሆነ ውጤት በመጠናቀቁ ነጥብ ተጋርተው ወጥተዋል።

የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር የ9 ወር እቅድ  አፈፃፀም በካቢኔ ደረጃ ግምገማ እያካሄደ ነው  ሚያዚያ፦7/2016ዓ.ም(የቡታጅራ ከተማ የመንግስት ኮሙኒኬሽን)የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር በ9 ወር ...
15/04/2024

የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር የ9 ወር እቅድ አፈፃፀም በካቢኔ ደረጃ ግምገማ እያካሄደ ነው
ሚያዚያ፦7/2016ዓ.ም(የቡታጅራ ከተማ የመንግስት ኮሙኒኬሽን)
የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር በ9 ወር ጊዜ የከናወኑ ተግባራት የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከብዶ አህመድ እና አጠቃላይ የከተማው የካቢኔ አባላት በተገኙበት እየተገመገመ ነው።

የሴክተር ኃላፊዎች በየቢሯቸው በ9 ወር የተከናወኑ ዋና ዋና እቅድ አፈፃፀም እያቀረቡ ሲሆን በሚታዩ ክፍተቶች እና በቀጣይ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮችን በመለየት ውይይት እንደሚደረጉባቸው ተገልጿል።

በቡታጅራ ከተማ የቲቢ በሽታ ልየታና ምርመራ ዘመቻ (TB cath up campain) መሰረታዊ ነጥብ እና ሂደት ላይ ለባለሙያዎች ኦረንቴሽን ተሰጠ፦ሚያዚያ 6/2016 ቡታጅራ የሚካሄደው የቲቢ ...
14/04/2024

በቡታጅራ ከተማ የቲቢ በሽታ ልየታና ምርመራ ዘመቻ (TB cath up campain) መሰረታዊ ነጥብ እና ሂደት ላይ ለባለሙያዎች ኦረንቴሽን ተሰጠ፦

ሚያዚያ 6/2016 ቡታጅራ
የሚካሄደው የቲቢ ልየታና ምርመራ ዘመቻ ቤት ለቤት መለየት የተሰወሩና ያልተገኙ በሽታዎችን ህክምና ለመስጠት የሚያስችል መሆኑ ተገለፀ።

በቡታጅራ ከተማ አስተዳደር ጤና ጽ/ቤት ለአስር ተከታታይ ቀናት ለሚደረገው የቲቢ እና የስጋ ደዌ በሽታ ልየታና ምርመራ ዘመቻ ለባለሙያዎች ኦረንቴሽን ተሰጥቷል።
የ2016 ዓ/ም የቲቢ በሽታ ተግባር አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ውይይት ተደርጓል።

በቡታጅራ ከተማ የጤና ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ትዕግስት ተክሌ ዘመቻው የተሰወሩና ያልተገኙ በሽታዎችን ቤት ለቤት በመለየት ልየታና ምርመራ በማድረግ በጤና ተቋም ህክምና ለመስጠት እንደሆነ ገልፀዋል።

በተመሳሳይ ተጋላጭ የሆኑና እድሜያቸው ከ15 ዓመት በታች የሆኑ ህፃናትና ታዳጊዎች የቲቢ በሽታ ክትባት ይሰጣቸዋል።
በመሆኑም የበሽታውን ስርጭት የሚከላከል ፣ታማማሚዎች ህክምና እንዲያገኙ እንዲሁም ህፃናት እና ታዳጊዎች እንዳይጠቁ የሚያስችል ዘመቻ መሆኑን አብራርተዋል።

የቲቢ እና የስጋ ደዌ በሽታ የልየታና ምርመራ ዘመቻ በማዕከታዊ ኢትዮጲያ ክልል ከሚያዚያ 7/2016 ጀምሮ ይካሄዳል በዚሁ መርሃ-ግብር በቡታጅራ ለሚደረገው ዘመቻ ነው ኦረንቴሽን የተሰጠው።

በቡታጅራ ከተማ ጤና ጽ/ቤት የበሽታ መከላከል እና ጤና ማጎልበት ዋና ስራ ሂደት ዳይሬክቶሬት አቶ መንሱር ረሻድ ዘመቻው አጠቃላይ የሚሰራበት ሂደት መሰረታዊ ነጥቦችን ላይ ግንዛቤ የሚያዝበትን ኦረንቴሽን ሰጥተዋል።

አቶ መንሱር በከተማዋ ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን ጠቁመው በዘመቻው የሚሳተፉ ባለሙያዎች በተፈጠረላቸው ግንዛቤ መሰረት ከዘመቻው የታሰበው ውጤት እንዲመዘገብ ከተማዋ በመሰል የጤና ልየታ ስራ ከሀገር እና ከክልል ግንባር ቀደም መሆኗን ለማስቀጠል በትኩረት መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል።

የጽ/ቤቱ የቲቢ እና የስጋ ደዌ በሽታ ፎካል አቶ አህመድ ሀደም የ2016 የ9 ወር የቲቢ ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት አቅርበው ውይይት ተደርጓል።
የቀበሌ የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች የተቋማት የቲቢ እና ስጋ ደዌ በሽታ ፎካሎች የሆስፒታል የላብራቶሪ ባለሙያዎች ተገኝተዋል።
የዘገበው የቡታጅራ ከተማ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ነው
ተጨማሪ የመረጃ አማራጮቻችን፦
ቴሌግራም https://t.me/ButajiraCommunication/58
ፌስቡክ https://www.facebook.com/buta1921/
ዩቲዩብ
https://youtube.com/
ትዊተር https://mobile.twitter.com/ButajiraB
ኢንታግራም https://www.instagram.com/butajirab

"ኢትዮጵያውያን የሰላምን ዋጋ መረዳትና ችግሮችን በውይይት የመፍታት ባህል ማዳበር ይኖርብናል" - ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ********************እኛ ኢትዮጵያውያን የሰላምን ዋጋ ...
13/04/2024

"ኢትዮጵያውያን የሰላምን ዋጋ መረዳትና ችግሮችን በውይይት የመፍታት ባህል ማዳበር ይኖርብናል" - ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ
********************

እኛ ኢትዮጵያውያን የሰላምን ዋጋ መረዳትና ችግሮችን በውይይት የመፍታት ባህል ማዳበር ይኖርብናል ሲሉ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ገለጹ።

ይህ የተገለጸው ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በስዊዘርላንድ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጋር በባዝል ከተማ ውይይት ባደረጉበት ወቅት ነው።

ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በስዊዘርላንድ ባዝል ከተማ በተካሄደው 3ኛው ዓለም ዓቀፍ የትብብር መድረክ ላይ ለመሳተፍ ወደ ስፍራው ባቀኑበት ወቅት ነው በስዊዘርላንድ ነዋሪ ከሆኑ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር ውይይቱን ያካሄዱት።

በወቅቱም ፕሬዝዳንቷ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ዳያስፖራው ከሀገሩ ጋር ያለውን ትስስር ማጠናከርና ተሳትፎውንም ማሳደግ እንደሚገባው ገልፀዋል፡፡

እኛ ኢትዮጵያውያን የሰላምን ዋጋ መረዳትና ችግሮችን በውይይት የመፍታት ባህል ማዳበር ይኖርብናል ያሉት ፕሬዝዳንቷ ይህ እንዲሳካ ሁሉም የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ እንደሚገባ አሳስበዋል።

በውይይቱ ተሳታፊ የነበሩ የዳያስፖራ አባላትም በበኩላቸው ከፕሬዝዳንቷ ጋር የሚወያዩበት መድረክ በመመቻቸቱ ምስጋናቸውን ገልጸው፣ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ የተለያዩ አስተያየቶችና ጥያቄዎችን አንስተዋል።

የውይይት መድረኩን በጋራ የመሩት በጄኔቫ የኢፌዴሪ ቋሚ መልክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር አምባሳደር ፀጋአብ ከበበው በበኩላቸው፤ የውይይቱ ተሳታፊዎች አስተያየታቸውንና ጥያቄዎችን በግልፅ በማቅረብ የነቃ ተሳትፎ ማድረጋቸው ተገቢና ሊበረታታ የሚገባ መሆኑን መግለፃቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል፡፡

የሚሲዮን ጽ/ቤቱም ከዳያስፖራው ማህበረሰብ ጋር በትብብር ለመስራትና የዳያስፖራውን ሁለገብ ተሳትፎ ለማሳደግ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አምባሳደር ፀጋአብ ከበበው አረጋግጠዋል።
ከ EBC

"በየሴክተሩ ያሉ ምርጥ ተሞክሮዎችን በመለየት ቀምሮ ማስፋፋት ያስፈልጋል"- አቶ አንተነህ ፍቃዱሚዪዚያ 5/2016በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የማህበራዊ ክላስተር በክልሉ በአስሩም መዋቅር ያካሄ...
13/04/2024

"በየሴክተሩ ያሉ ምርጥ ተሞክሮዎችን በመለየት ቀምሮ ማስፋፋት ያስፈልጋል"- አቶ አንተነህ ፍቃዱ

ሚዪዚያ 5/2016
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የማህበራዊ ክላስተር በክልሉ በአስሩም መዋቅር ያካሄደውን ሱፐርቪዥን ስራ በወራቤ ከተማ ገምግሟል።

በግምገማ መድረኩ ማጠቃለያ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር፣ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አንተነህ ፍቃዱ እንደገለፁት በየሴክተሩ ያሉ ምርጥ ተሞክሮዎችን በመለየት ቀምሮ ለሌላው ማስፋፋት ያስፈልጋል።

በትምህርቱ ዘርፍ የትመህርት ጥራትን ለማምጣት ዘርፈ ብዙ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን የጠቆሙት ኃላፊው በክልል አቀፍና ሀገር አቀፍ ፈተናዎች ተማሪዎችን ወጤታማ ለማድረግ ክልላዊ የሞዴል ፈተና መዘጋጀቱንም ተናግረዋል።

ከትምህርት ቁሳቁስ አቅርቦት ጋር ተያይዞ ያሉ ችግሮችን ለመቅረፍ ትምህርት ቤቶች የውስጥ ገቢያቸውን ሊያሳድጉ ይገባል ሲሉም አሳስበዋል።

የጤና ኤክስቴንሽን ስራን አስመልክቶ ያለው እንቅስቃሴ የሚበረታታ መሆኑን የገለፁት ኃላፊው የማህበረሰብ ጤና መድህን ገቢ አሰባሰብ ጥሩ አፈፃፀም ላይ እንደሚገኝም አብራርተዋል።

የሴቶች የልማት ህብረትን ለማጠናከር ቅንጅታዊ አሰራርን ማጠናከር ይገባል ሲሉም አሳስበዋል።

የቴክኖሎጂን አጠቃቀም ለማጎልበት ለአመራሩ የግንዛቤ ማስጨበጫ የሚሰጥ መሆኑን የተናገሩት አቶ አንተነህ ዲጂታላዜሽንን ለማስፋፋት በቀጣይ በየተቋማቱ ዌብ ሳይት እንደሚለማም ገልፀዋል።

የቴክኖሎጂ ሽግግሩ እንዲጎለብትም በትምህርት ቤቶች መካከል የፈጠራ ክህሎት ለማካሄድ መታቀዱንም ኃላፊው ጠቁመዋል።

የሀሰት መረጃን በመለየት የእርምት እርምጃ እንዲወሰድ ከማድረግ አኳያ የክልሉ ፐብሊክ ሰርቪስ በትኩረት እየሰራ መሆኑንም አስታውሰዋል።

በድጋፋዊ ክትትሉ እንደ ክፍተት የተለዩትን የዕቅድ አካል ማደረግ ይገባል ያሉት አቶ አንተነህ ጥናት የሚፈልጉ ጉዳዮችን በመለየት በቀጣይ ጥናት ማካሄድ ያስፈልጋል ሲሉም አሳስበዋል።

መረጃው ክልሉ የመንግስት ኮመሙኒኬሽን ነው

የሚያጋጥሙ አለመግባባቶችን መንግስት ከሀገር ሽማግሌዎችና ከሀይማኖት አባቶች ጋር በምክክር እና በውይይት መፍታት ዋንኛው አላማ መሆኑን የሰላም ሚኒስቴር ገለፀ=======    ==========...
13/04/2024

የሚያጋጥሙ አለመግባባቶችን መንግስት ከሀገር ሽማግሌዎችና ከሀይማኖት አባቶች ጋር በምክክር እና በውይይት መፍታት ዋንኛው አላማ መሆኑን የሰላም ሚኒስቴር ገለፀ
======= ========== =====
ሚያዚያ፦5/2016 ዓ.ም(የቡታጅራ ከተማ መንግስት ኮሙኒኬሽን)
የሰላም ሚኒስቴር ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ጋር በመተባበር "የሀይማኖት ተቋማትና ሌሎች ባለ ድርሻ አካላት ለሰላም ግንባታ የሚኖራቸው ሚና" በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀ በቡታጅራ ከተማ የምክክር መድረክ ተካሄዷል።

በውይይት መድረኩ ላይ የተገኙት የኢፌድሪ የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ከይረዲን ተዘራ እንደገለጹት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሚያጋጥሙ አለመግባባቶችን መንግስት ከሀገር ሽማግሌዎችና ከሀይማኖት አባቶች ጋር በምክክር እና በውይይት መፍታት በመቻሉ ክልሉ ሰላማዊ እንዲሆን አስችሎታል ብለዋል።

በኢትዮጵያ እየተመዘገበ ያለው እድገት ያላስደሰታቸው አካላት ከብዙ በጎ ነገሮች ውስጥ አንጓለው መጥፎ ነገር በመፈለግ በሀገሪቱ የሰላም እጦት እንዳለ በመገናኛ ብዙሀን አማካኝነት ዘመቻ እያካሔዱ ይገኛሉ ብለዋል።

በሀገሪቱ በሁሉም አካባቢዎች አንጻራዊ ሰላም መኖሩን የተናገሩት ሚኒስትር ዴኤታው ለዚህም መንግስት በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አብዶ አህመድ የእንኳን ደህና መጣችሁ ባደረጉት ንግግር ቡታጅራ ከተማ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የከተማና ኢንዱስትሪ ክላስተር ብሎም የምስራቅ ጉራጌ ዞን መቀመጫና እምብርት ላይ የምትገኝ ውብና የሰላም ሰገነት አበረታች በሆነ እድገት ላይ የምትገኝ የመቻቻል ተምሳሌት ከተማ ናት ብለዋል፡፡

ቡታጅራ ከተማ አንድም ኮሽታ አስተናግዳ የማታውቅ ሰላም የሰፈነባት በከተማዋ 24 ሰዓት በነፃነት እንቅስቃሴ የሚደረግባት የፍቅር ከተማ ናትም ብለዋል፡፡

ይህ ስኬት መንግስት ከማህበረሰቡ ጋር ተናቦና ተቀራርቦ በመስራቱ የተገኘ መሆኑን ጠቅሰው ህዝቡ የከተማችን የሰላም ደጀን ነው ብለዋል፡፡

የሀይማኖት ተቋማት እርስ በዕርስ ከመቻቻል ባለፈ የሰላም ጉዳይ የዘወትር አስተምህሮ አካል አድርገው በመንቀሳቀሳቸውና ከመንግስት ጎን ሆነው በማገዛቸው ከተማችን ሰላሟ እንዲጠበቅ ትልቅ አስተዋፅኦ ማድረጉንም ጠቅሰዋል፡፡

የከተማው ወጣቶች ማንኛውም ጥያቄ እና ቅሬታ በሰለጠነ መንገድና በሰከነ ሁኔታ ከመጠየቅ ባለፈ በከተማው ሰላም ላይ የሚደራደርም ሆነ የከተማውን ሰላም ለማወክ የሚንቀሳቀስ ግለሰብም ሆነ ቡድን የማይታገስ የወጣት አደረጃጀት በመኖሩ ወጣቶች ሴቶች ምሁራኖች የከተማው ሰላም በአትኩሮት የሚከታተሉት የሚጠብቁ ቁልፍ ጉዳይ አድርገው መያዛቸው እጅጉን ጠቅሞናል ብለዋል፡፡

የፀጥታና የፍትህ ተቋሞቻችን ላይ የሚሰራው አንፃራዊ አቅም ያለው ስራ እንደተጠበቀ ሆኖ ችግሮች ሲፈጠሩ ስህተትን በስህተት ለመፍታት ከመሞከር ይልቅ "ፈራገዘኘን ባህላዊ ዳኝነት" ጨምሮ የተለያዩ ባህላዊ የሽምግልና የዳኝነት ስርዓቶች በመጠቀም በሰከነ ሁኔታ በሀገር ባህል እጅግ ብስለት በተሞላበት መንገድ ችግሮች የሚፈቱበት አካሄድ ከተማችን አስተማማኝ ሰላም እንዲኖር ትልቅ ሚና እየተጫወተ ይገኛል ብለዋል፡፡

በመድረኩ ላይ የኢፌድሪ የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ከይረዲን ተዘራ(ዶ/ር)፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተመስገን ካሳ ፣የምስራቅ ጉራጌ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ሙስጠፍ ሀሰን ፣የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አብዶ አህመድና ሌሎች የፌደሬል የክልል ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

ሚያዝያ 05/2016 ዓ.ም ቡታጅራየምስራቅ ጉራጌ ዞን እግር ኳስ ቡድን በውድድሩ ሁለተኛው ድሉን አስመዝግቧል።1ኛው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል  ልዩ ልዩ ጨዋታዎች፣ የባህል ስፖርቶች ውድድር ...
13/04/2024

ሚያዝያ 05/2016 ዓ.ም ቡታጅራ
የምስራቅ ጉራጌ ዞን እግር ኳስ ቡድን በውድድሩ ሁለተኛው ድሉን አስመዝግቧል።

1ኛው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ልዩ ልዩ ጨዋታዎች፣ የባህል ስፖርቶች ውድድር እና የባህል ፌስቲቫል የሶስተኛው ቀን ውሎው በተለያዩ ውድድሮች ቀጥሎ ውሏል።

ምስራቅ ጉራጌ ዞን እግር ኳስ ቡድን በምድቡ ሁለተኛ ጨዋታ የሃላባ አቻው በማስተናገድ ሁለት ለአንድ በሆነ ውጤት በማሸነፍ በተከታታይ ባስመዘገባቸው ድሎች 6 ነጥብ በመሰብሰብ የምድብ አናት ላይ መቀመጥ ችሏል።

በምድብ 1 #ስልጤ ዞን እግር ኳስ ቡድን ከሃዲያ ዞን ጠዋት ⏰3:00 ባደረጉት ጨዋታ ጎል ሳያስተናግዱ በአቻ ውጤት ተለያይተዋል።

በሌላ የምድቡ ጨዋታ ጉራጌ ዞን የም ዞን አንድ ለዜሮ በማሸነፍ የሶስት ነጥብ ባለቤት ሆኗል።

ምድቡን ሃዲያ ዞን በአራት ነጥብ ሲመራ ጉራጌ ዞንና ጠምባሮ ልዩ ወረዳ በእኩል ነጥብና የግብ ዕዳ በሁለተኛ ደረጃ ሲይዙ ተስተካካይ ጨዋታ የሚቀረው የስልጤ ዞን በአንድ ነጥብ አራተኛ የም ዞን ባደረጋቸው ሁለት ጨዋታዎች ተሸንፎ የደረጃ ሰንጠረዡ ግርጌ ተቀምጧል።

በምድብ ሁለት ማረቆ ልዩ ወረዳ ከቀቤና አቻው በአሁኑ ሰዓት ጨዋታዎች እያካሄዱ ይገኛሉ።

ዘገባው የምስራቅ ጉራጌ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

ሚያዚያ፦5/2016(ቡታጅራ)የሰላም ሚኒስቴር ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ጋር በመተባበር "የሀይማኖት ተቋማትና ሌሎች ባለ ድርሻ አካላት ለሰላም ግንባታ የሚኖራቸው ሚና" በሚ...
13/04/2024

ሚያዚያ፦5/2016(ቡታጅራ)
የሰላም ሚኒስቴር ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ጋር በመተባበር "የሀይማኖት ተቋማትና ሌሎች ባለ ድርሻ አካላት ለሰላም ግንባታ የሚኖራቸው ሚና" በሚል መሪ ሀሳብ የምክክር መድረክ በቡታጅራ ከተማ እየተካሄደ ነው

የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አብዶ አህመድ እንግዶችን ወደ ውቧና የሰላም ሰገነት ወደ ሆነቺው ቡታጅራ ከተማ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር አድርገዋል።

በመድረኩ ላይ የኢፌድሪ የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ከይረዲን ተዘራ(ዶ/ር)፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተመስገን ካሳ ፣የምስራቅ ጉራጌ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ሙስጠፍ ሀሰን ፣የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አብዶ አህመድና ሌሎች የፌደሬል የክልል ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

ሚያዝያ 04/2016እሰካሁን ፍፃሜ ባገኙ ሶስት የአትሌቲክስ ውድድሮች ማለትም የወንዶችና ሴቶች 10,000 እና የሴቶች 1500 ውድድር !1ኛ = ምስራቅ ጉራጌ ዞን 1 ወርቅ 2 ብር በድምሩ 3...
12/04/2024

ሚያዝያ 04/2016
እሰካሁን ፍፃሜ ባገኙ ሶስት የአትሌቲክስ ውድድሮች ማለትም የወንዶችና ሴቶች 10,000 እና የሴቶች 1500 ውድድር !

1ኛ = ምስራቅ ጉራጌ ዞን 1 ወርቅ 2 ብር በድምሩ 3 ሚዳሊያ
2ኛ - ስልጢ ዞን - 1 ወርቅ 1 ብርና 1 ነሃስ በድምሩ 3 ሜዳሊያዎች
3ኛ = ጉራጌ ዞን = 1 ወርቅና 1 ነሃስ በድምሩ 2 ሜዳሊያ ሰብስቧል

2ኛ ቀኑን በያዘ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሉ ልዩ ልዩ ስፖርቶች እና የባህል ስፖርት ውድድርሚያዚያ 4/2016 ቡታጅራ- ፍፃሜ ያገኘ የአትሌቲክስ ውድድርበ10,000 ሜትር በወንዶች1ኛ- ከጉራጌ...
12/04/2024

2ኛ ቀኑን በያዘ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሉ ልዩ ልዩ ስፖርቶች እና የባህል ስፖርት ውድድር

ሚያዚያ 4/2016 ቡታጅራ
- ፍፃሜ ያገኘ የአትሌቲክስ ውድድር
በ10,000 ሜትር በወንዶች
1ኛ- ከጉራጌ ዞን በቀለ ተክሉ 32:16:32
2ኛ- ከምስራቅ ጉራጌ ዞን የኔነህ አስማረ 32:27:98
3ኛ- ከጉራጌ ዞን ሳሙኤል ገደፉ 32:29:75

በ10,000 ሜትር ሴቶች
1ኛ- ከስልጤ ዞን ፋይዛ ኑረዲን 50:04:13
2ኛ- ከስልጤ ዞን ኑሪያ ሸረፋ 50:11:61 በመሆን ሲያጠናቅቁ ሌሎች ዞኖኛ የ10,000 ሜትር ተወዳዳሪ ሴቶችን አላቀረቡ።
የሩጫ ውድድሩንም የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዘሪሁን እሸቱ እና የምክትል ቢሮ ኃላፊና ስፖርት ዘርፍ ኃላፊ አቶ መዘረዲን ሁሴን በውድድሩ ተገኝተው አስጀምረውታል።

መረጃው የምስራቅ ጉራጌ ዞን መንግሥት ኮምኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

የቡታጅራ ከተማ የደጋፊዎች ማህበር ለከተማው እግር ኳስ ክለብ የመለያ ድጋፍ አደረገ=============    =========  =====ሚያዚያ፦4/2016 ዓ.ም(የቡታጅራ ከተማ መንግስት ኮሙኒ...
12/04/2024

የቡታጅራ ከተማ የደጋፊዎች ማህበር ለከተማው እግር ኳስ ክለብ የመለያ ድጋፍ አደረገ
============= ========= =====
ሚያዚያ፦4/2016 ዓ.ም(የቡታጅራ ከተማ መንግስት ኮሙኒኬሽን)
የቡታጅራ ከተማ የደጋፊዎች ማህበር ለቡታጅራ እግር ኳስ ክለብ 21 ሺህ ብር ወጪ በማድረግ ሙሉ የቡድኑ አባላት የመለያ ድጋፍ አድርገዋል።

ድጋፉን የከተማው የደጋፊዎች ማህበር ፕሬዝዳንት አቶ ሚፍታ ወደዶ ለከተማው ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ ለአቶ ነጋሽ መሐመድ አስረክበዋል።

የደጋፊዎች ማህበር ሰብሳቢ አቶ ሚፍታ ወደዶ መለያውን ባስረከቡበት ወቅት እንደገለፁት ማህበሩ ቡድኑን ከመደገፍ ጎንለጎን በቁሳቁስ በገንዘብና በተለያዩ ድጋፎችን እንደሚያደርግ ገልፀዋል።

የድጋፍ ገንዘቡን ከቡታጅራ ከተማ መናኽርያ አካባቢ በፍቃደኝነት ከሚቆረጥ ገንዘብ እንዲሁም የተለያዩ ከካላት ባደረጉት ድጋፍ መሆኑን አቶ ሚፍታ ተናግረዋል።

የደጋፊዎች ማህበሩን ይበልጥ በማጠናከር ለዋናው ቡድን ከሚያደርገው ድጋፍ በተጨማሪ ለታዳጊ ቡድኑ ድጋፍ ያደርጋልም ተብሏል።

የደጋፊ ማህበሩ ይህ ገንዘብ እንድንሰበስብና ለቡድኑ ድጋፍ እንድናደርግ ትልቅ አስተዋፅኦ ላደረገልን ለቡታጅራ ከተማ ትራንስፖርት ጽ/ቤት አመስግነዋል።

የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ነጋሽ መሐመድ የደጋፊ ማህበሩ የቡታጅራ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ያለበትን ጉድለት ለመሙላት ያደረጉት ጥረት አመስግነው በቀጣይ ማህበሩ ይበልጥ እንዲጠናከርና ቡድኑ በሁለንተናዊ አቅሙ ሙሉ እንዲሆን በቅርበትና በትኩረት መስራት እንዳለበት ጠቁመዋል።

የቡታጅራ እግር ኳስ ክለብ በአንደኛ ሊግ ላይ ምድብ "ለ"ተመድቦ የሁለተኛ ዙር ውድድሩን አርባምንጭ ከተማ ላይ እያደረገ ሲሆን አሁን ላይ በደረጃ ሰንጠረዡ ፊት ካሉ ቡድኖች ጋር በትንሽ ነጥብ ርቆ 4ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

ተጨማሪ የመረጃ አማራጮቻችን፦
ቴሌግራም https://t.me/ButajiraCommunication/58
ፌስቡክ https://www.facebook.com/buta1921/
ዩቲዩብ
https://youtube.com/
ትዊተር https://mobile.twitter.com/ButajiraB
ኢንታግራም https://www.instagram.com/butajirab

ሚያዚያ፦4/2016 ዓ.ም(ቡታጅራ)የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ልዩ ልዩ ጨዋታና የባህል ስፖርት ውድድር 2ኛ ቁኑን ሲያስቆጥር ጉራጌ ዞን በጠምባሮ ልዩ ወረዳ 1ለ0 ሲሸነፍ ሀድያ ዞን የም ዞንን...
12/04/2024

ሚያዚያ፦4/2016 ዓ.ም(ቡታጅራ)
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ልዩ ልዩ ጨዋታና የባህል ስፖርት ውድድር 2ኛ ቁኑን ሲያስቆጥር
ጉራጌ ዞን በጠምባሮ ልዩ ወረዳ 1ለ0 ሲሸነፍ ሀድያ ዞን የም ዞንን 5ለ1 በሆነ ውጤት አሸንፏል።
የሁለተኛ ቀን ውድድሩ ሲቀጥል አሁን በዚህ ሰዓት ሀላባ ዞን ከማረቆ ልዩ ወረዳ አንድ አቻ ሆነው የመጀመርያ አጋማሽ ተጠናቆ የሁለተኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጀምሯል።
መርሀ ግብሩ በነገው ዕለት ሲቀጥል
ጥዋት 3 ሰዓት ስልጤ ዞን ከሀድያ ዞን
5 ሰዓት ጉራጌ ዞን ከየም ዞን
7 ሰዓት ምስራቅ ጉራጌ ዞን ከሀላባ ዞን እንዲሁም 9 ሰዓት ላይ ቀቤና ልዩ ወረዳ ከማረቆ ልዩ ወረዳ ጋር ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
ተጨማሪ የመረጃ አማራጮቻችን፦
ቴሌግራም https://t.me/ButajiraCommunication/58
ፌስቡክ https://www.facebook.com/buta1921/
ዩቲዩብ
https://youtube.com/
ትዊተር https://mobile.twitter.com/ButajiraB
ኢንታግራም https://www.instagram.com/butajirab

ተማሪዎች ችግር ፈቺ የሆኑ የፈጠራ ስራ በማከናወን የድርሻቸውን እየተወጡ እንደሆነ ተገለፀ።ሚያዚያ 3/2016 ቡታጅራበቡታጅራ ከተማ የመምህራን እና የተማሪዎች የሳይንስና የፈጠራ ስራ ኤግዝቢሽ...
11/04/2024

ተማሪዎች ችግር ፈቺ የሆኑ የፈጠራ ስራ በማከናወን የድርሻቸውን እየተወጡ እንደሆነ ተገለፀ።

ሚያዚያ 3/2016 ቡታጅራ
በቡታጅራ ከተማ የመምህራን እና የተማሪዎች የሳይንስና የፈጠራ ስራ ኤግዝቢሽን የእውቅና እና ሽልማት ስነ-ስርዓት ተካሄዷል።

የቡታጅራ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ከሳይንስና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት በመተባበር የተዘጋጀው የሳይንስና የፈጠራ ስራ ኤግዚቢሽን ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን ተከትሎ ነው ስነ-ስርዓቱ የተካሄደውደ፤

የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ የተከበሩ አቶ አብዱ አህመድ ተማሪዎች በፈጠራ ስራ የማህበረሰቡን ችግር ለማቃቃለል የሚያግዝ ተግባር በመስራት የድርሻቸውን ለመወጣት ጥረት እያደረጉ መሆኑን ገልፀዋል።

የሳይንስና የፈጠራ ስራ የማህበረሰቡን ችግር በዘላቂ ለመቅረፍ እንጂ ለውድድር ብቻ መሆን የለበትም በመሆኑም የተሻሉትን በመለየት በመደገፍ ለውጤት ማብቃት የሚችሉ ቴክኖሎጂዎችን መጠቀም ይገባል።

በመሆኑም ጥራታቸው ተግባሮቻቸው ውጤማ ሆኖ የማህበረሰቡን ችግር በዘላቂ እንዲቀረፍ ባለድርሻዎች ጥረት ሊያደርጉ እንደሚገባ አመላክተዋል።

በቡታጅራ ከተማ አስተዳደር የትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ ተወካይ አቶ ዑመር ናስር ትምህርት ቤቶች ይዘውት የቀረበው የፈጠራ ስራ በቴክኖሎጂ በማገዝ ሀገራችን የጀመረችውን የሳይንስና የኢኖቬሽን መሰረት ሊሆን እንደሚችል ገልፀዋል።

በመሆኑም የውጭ ምንዛሬን በሀገር ውስጥ ጥሬ እቃ በመጠቀም አምራች ዜጋ ለመፍጠር የፈጠራ ስራን አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል።
ትምህርት ቤቶች ለዚህ ልዩ የሆነና ቀጣይነት ባለው መልኩ መስራትና ተማሪዎችን ማሰራት እንደሚገባቸውም አሳስበዋል።

በቡታጅራ ከተማ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሀይሉ ዘውዴ የሳይንስና የፈጠራ ስራ የተማሪዎችን የተፈጥሮ ሳይንስ የትምህርት ዘርፍ የሚያሻሽልና ችግር ፈቺ የሆኑ ስራዎችን ማስገኘት የሚያስችል መሆኑን አብራርተዋል።

የሳይንስና የፈጠራ ስራ ጥረት የሚጠይቅ ነው ፤ለዚህም ባለድርሻ አካላት ከፍተኛ ጥረት በማድረጋቸው የተሳካ በመሆኑ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

# በተካሄደው የሳይንስና የፈጠራ ስራ ኤግዚቢሽን ውድድር የተማሪ እና የመምህራን ደረጃ፦

ከ1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች #የተማሪ ደረጃ፦
1ኛ ከድር አህመድ እና ኑርሀሰን ከመቂቾ
2ኛ አኒያ አህመድ ከዶቦ ጡጦ ት/ቤት
3ኛ ሙዓዝ ከድር ከሴራና ት/ቤት

ከ2ተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት #የተማሪ ደረጃ፦
1ኛ እዮብ ባንተሁን ከመቂቾ ሚሊኒየም ት/ቤት
2ኛ ዚዳን ሙስጠፋ ከበህር ት/ቤት
3ኛ ዘይነብ ጀማል ከመሰናዶ ት/ቤት

ከ1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት #የመምህራን ደረጃ፦
1ኛ መ/ር ሙባረክ ሸረፋ ከሸዋበር ት/ቤት
2ኛ መ/ር ቡዙነህ አረጋሀኝ ከመቂቾ ት/ቤት
3ኛ መ/ር ዑመር ከድር ከዶቦ ጡጦ ት/ቤት

ከ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት # የመምህራን ደረጃ፦
1ኛ መ/ር አደራው የሺዋስ ከቡታጅራ መሰናዶ ት/ቤት
2ኛ መ/ር ሸረፋ ወልዩ ከመቂቾ ሚሊኒየም
3ኛ መ/ር መሀመድ ዑመር ከመቂቾ ሚሊኒየም በመሆን ተጠናቋል።
የዘገበው የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን ነው

ተጨማሪ የመረጃ አማራጮቻችን፦
ቴሌግራም https://t.me/ButajiraCommunication/58
ፌስቡክ https://www.facebook.com/buta1921/
ዩቲዩብ
https://youtube.com/
ትዊተር https://mobile.twitter.com/ButajiraB
ኢንታግራም https://www.instagram.com/butajirab

ሚያዝያ 3/2016 ዓ.ም ቡታጅራየማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ልዩ ልዩ ጨዋታ፣ የባህል ስፖርቶች ዉድድርና የባህል ፌስቲቫል የማስጀመሪያ ፕሮግራም እየተካሄደ ይገኛል።መርሃ-ግብሩ ማስጀመሪያ የማዕ...
11/04/2024

ሚያዝያ 3/2016 ዓ.ም ቡታጅራ

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ልዩ ልዩ ጨዋታ፣ የባህል ስፖርቶች ዉድድርና የባህል ፌስቲቫል የማስጀመሪያ ፕሮግራም እየተካሄደ ይገኛል።

መርሃ-ግብሩ ማስጀመሪያ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የከተማ ልማት ክላስተር አስተባባሪ እና የክልሉ ከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ስንታየሁ ወ/ሚካኤል ፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ እና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አንተነህ ፍቃዱ፤ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ረዳት የመንግስት ተጠሪና የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ይግለጡ አብዛ፤ የክልሉ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዘሪሁን እሸቱ፤ የምስራቅ ጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሙስጠፋ ሀሰን፤ የክልልና የዞን ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

በምስራቅ ጉራጌ ዞን ቡታጅራ ከተማ መሰናዶ ትምህርት ቤት በሚገኘው ሜዳ የሚካሄደው የክልሉ የመጀመሪያ የሆነው ይህ የስፖርትና ባህል ውድድር ሻሞፒዮና ከሚያዝያ 03 - ሚያዝያ 14/2016 ለተከታታይ 14 ቀናት እንደሚካሄድ ታዉቋል።

በዉድድሩ ከ7ቱ ዞኖችና 3 ልዩ ወረዳዎች የተወጣጡ ስፖርተኞች ባህላዊና ዘመናዊ የስፖርት ዓይነቶች ውድድሮች የሚካሄዱ መሆኑ ተጠቁሟል።

በዚህ አጠቃላይ ከ2 ሺህ 8 መቶ በላይ ስፖርተኞች ተሳታፊ እንደሚሆኑ ይጠበቃል።

የምስራቅ ጉራጌ ዞን ባህላዊና ዘመናዊ የስፖርት ዓይነቶች በማሳተፍ በሻምፒዮናው ጠንካራ ተፎካካሪ ለመሆኑ መዘጋጀቱን ተመላክቷል።

በአሁኑ ሰዓት ከተለያዩ ዞኖችና ወረዳዎች የመጡ ተወዳዳሪዎች የባህል ፌስቲቫል እያሳዩ ይገኛሉ።

በመክፈቻው ጨዋታ ምስራቅ ጉራጌ ዞን እግር ኳስ የከምባታ አቻው ከደቂቃዎች በኃላ የሚካሄድ ይሆናል።

ዘገባው የምስራቅ ጉራጌ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለኢደ-አል-ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ የቡታጅራ የኤሌክትሪክ አገልግሎት መስጫ ማዕከል ፦የቡታጅራ የኤሌክትሪክ አገልግሎት መስጫ ማዕከል ለመላው...
09/04/2024

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለኢደ-አል-ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ የቡታጅራ የኤሌክትሪክ አገልግሎት መስጫ ማዕከል ፦

የቡታጅራ የኤሌክትሪክ አገልግሎት መስጫ ማዕከል ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን 1445 ኛው የኢድ-አልፈጥር ረመዳን በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያለ ፤

በዓሉን ምክንያት በማድረግ ነገ ማለትም ሚያዚያ 2/2016 በካርድ ቅድመ-ክፍያ ለሚጠቀሙ ደንበኞቻችን ቀኑን ሙሉ በስራ ሰዓት ካርድ የመሙላት አገልግሎት የምንሰጥ መሆኑን ከወዲሁ እናሳውቃለን።

መልካም በዓል!
Eid Mubarak!
የቡታጅራ የኤሌክትሪክ አገልግሎት መስጫ ማዕከል

ተጨማሪ የመረጃ አማራጮቻችን፦
ቴሌግራም https://t.me/ButajiraCommunication/58
ፌስቡክ https://www.facebook.com/buta1921/
ዩቲዩብ
https://youtube.com/
ትዊተር https://mobile.twitter.com/ButajiraB
ኢንታግራም https://www.instagram.com/butajirab

ለመላው  የእስልምና እመነት ተከታዮች እንኳን ለ1ሺ 445ተኛው የኢድ አል-ፈጥር  በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን!! የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር የብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት የፖለቲካ እና የር...
09/04/2024

ለመላው የእስልምና እመነት ተከታዮች እንኳን ለ1ሺ 445ተኛው የኢድ አል-ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን!!

የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር የብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት የፖለቲካ እና የርዮት ዓለም ኃላፊ አቶ ኑረዲን መሀመድ

የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር የብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት የፖለቲካ እና የርዕዮት ዓለም ኃላፊ አቶ ኑረዲን መሀመድ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች ለ1ሺ 445ኛው የኢድ አል-ፈጥር በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በመልዕክታቸው ህዝበ ሙስሊሙ በተቀደሰው የረመዳን በፆም ወቅት የነበረው የአብሮነት የእዝነትና የመረዳዳት ብሎም የእህትማማችነትና የወንድማማችነት እሴት ጎልቶና ተውቦ የታየበት ወቅት መሆኑን ገልፀው፦
ይህ የአብሮነት ተግባር ከፆሙም በኋላ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት በመልዕክታቸው አስተላልፈዋል።

ወትሮውም የከተማችን ማህበረሰብ ለአብሮነትና ለወንድማማችነት የማይታማው ሕዝባችን በአሉን ሲያከብር የደከሙ ወገኖችን ድጋፍ የምናደርግበት ሰላማችንን የምናፀናበት አንድነታችንን የምንገነባበት እና ብሎም የከተማችንን ሰላም እንደ ዓይናችን ብሌን በዘላቂነት የምናስጠብቅበት እንዲሆን እመኛለሁ ብለዋል።

በድጋሚ ለመላው የእሰልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1445ኛው የኢድ-አልፈጥር በዓል በሰላምና በጤና አደረሳችሁ
እያልኩ በዓሉ የሰላምና የፍቅር የአንድነት የብልፅግና እንዲሆን እመኛለሁ!!

Eid Mubarak
ሚያዚያ 2016 ቡታጅራ

በቡታጅራ ከተማ የትምህርት ጽ/ቤት የሳይንስና የፈጠራ ስራ ኤግዚብሽን ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታወቀ፦ሚያዚያ 1/2016 ቡታጅራበቡታጅራ ከተማ አስተዳደር "በሳይንስና ቴክኖሎጂ የዳበረ ትው...
09/04/2024

በቡታጅራ ከተማ የትምህርት ጽ/ቤት የሳይንስና የፈጠራ ስራ ኤግዚብሽን ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታወቀ፦

ሚያዚያ 1/2016 ቡታጅራ
በቡታጅራ ከተማ አስተዳደር "በሳይንስና ቴክኖሎጂ የዳበረ ትውልድ እንፍጠር" በሚል መሪ ቃል 14 የመንግስትና የግል ትምህርት ቤቶች የተሳተፉበት የሳይንስና የፈጠራ ስራ ኤግዚቢሽን ወድድር ተካሄዷል።

በቡታጅራ ከተማ የትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ ተወካይ አቶ ዑመር ናስር የፈጠራ ስራ ተማሪዎች በትምህርት ያገኙትን እውቀት ወደ ተግባር የሚቀይሩበት ይበልጥ በመረዳት ትኩረት እንዲሰጡ እና በራሳቸው እንዲተማመኑ የሚያስችል እንደሆነ አመላክተዋል።

የተማሪዎችን የፈጠራ ችሎታን የሚያጎለብት የቴክኖሎጂ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ የሚያግዝ በመሆኑ የፈጠራ ስራ ቴክኖሎጂን ማጠናከር እንደሚገባ ገልፀዋል።

የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አብዱ አህመድ በምልከታየው ወቅት እንደገለፁት ወጪ ቆጣቢ ተብለው የተለዩትን ድጋፍ በማድረግ ወደገበያ ለማውጣት እንደሚመቻች እና በቴክኖሎጂ የተደገፉትን በመለየት በዘላቂነት እንዲያስቀጥሉ ድጋፍ የሚደረግ መሆኑን ገልፀዋል።
ትምህርት ቤቶችም ለተሻሉ ስራዎች እውቅና እና ማበረታቻ በመስጠት ማስቀጠል እንዳለባቸውም ጠቁመዋል።

ከቡታጅራ ከተማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት ጋር በመተባበር የተዘጋጀና ጽ/ቤቱ ትብብር እንዳደረገላቸው አቶ ዑመር ናስር ገልፀዋል።

አቶ ዑመር በመጨረሻም መምህራንና ተማሪዎች እንደትምህርት ቤት የተዘጋጁበትን ያቀረቡበት ኤግዚቢሽን እንደሆነ ጠቁመው በቀጣይ ሀሙስ አጠቃላይ ተሳታፊዎች በተገኙበት የእውቅናና የሽልማት ስነ-ስርዓት እንደሚያደርጉ ገልፀዋል።

ከየትምህርት ቤቶች ተሰርቶ የቀረበው የፈጠራ ስራ ከትምህርት ጽ/ቤቱ እና ከከተማው ሳይንስና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት የተውጣጣ የዳኞች ኮሚቴ በሚሰጡት ውጤት መሰረት የተሻለ የሆነው ለዞን ይቀርባል ብለዋል።

በቡታጅራ ከተማ አስተዳደር የብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት የሪዮተ አለም ዘርፍ ኃላፊና ረዳት የመንግስት ተጠሪ አቶ ኑረዲን መሀመድ የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊና ረዳት የመንግስት ተጠሪ አቶ መኮንን አሰፋ የዞን እና የከተማ አስተዳደር የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ምልከታ አድረገዋል።

የዘገበው የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን ነው

ተጨማሪ የመረጃ አማራጮቻችን፦
ቴሌግራም https://t.me/ButajiraCommunication/58
ፌስቡክ https://www.facebook.com/buta1921/
ዩቲዩብ
https://youtube.com/
ትዊተር https://mobile.twitter.com/ButajiraB
ኢንታግራም https://www.instagram.com/butajirab

Address

Butajira

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት Butajira City Communication Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Share