አንድነት ሀይል ነው Unity is power

አንድነት ሀይል ነው Unity is power Public voice

15/04/2024
27/09/2023

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ረቡዕ መስከረም 16 ቀን 2016 ዓ.ም

"በበዓልም ሆነ በአዘቦት የእኛ እውነታዎች"

ተፋላሚ ነን ባዮች፣በውሸት እሩምታ ተኩሳቸው እንደ ቅጠል የምንረግፍ የሚመስላቸው ከራሳቸው ውጭ ሀገርና ዜጋ ግድ የማይላቸው "ከእኔ ወዲያ ላሳር" ባዮች መሆናቸውና፤እኩይ አላማቸው እንዳይሳካ ያደረግንባቸው መሆኑ።

በሙሉ አቅማቸው ሃያ አራት ሰዓት የሚያንደቀድቁት የውሸት ተኩሳቸው በሚተውላቸው የመጥፎ ጠረን ባሩድ ቢታፈኑም፤ውጤት አልባ ዒላማ ሳች የሀሰት ተኩሳቸውን በጭፍን መቀጠላቸው የቅዠታቸው ውጤት መሆኑን ጠንቅቀን ማወቃችን፤

ከሰሜን እስከ ደቡብ፣ከምስራቅ እስከ ምዕራብ በሀገራችን ሉዓላዊ ግዛት ስር ያሉ ብሄር ብሄረሰቦች ሁሉ የተውጣጣን እውነተኛ የኢትዮጵያዊ አንድነት አምሳያና መልክ ሆነን ሳለ የውሸት ጥይት ተኳሾች ይህንን እንደ ጸሃይ የፈነተወ ሃቅ መካዳቸው።

መካዳቸው ብቻ ሳይሆን እነሱ በአንዲት ውስን ስፍራ ጠበውና አጠር ሰርተው ሲያበቁ የራሳቸውን ነውር ለእኛ ሊሰጡንም ይዳዳቸዋል።

ምንም ሆነ ምን ግን የውሸት ጥይት ናዳ የሚያላላን የአገዳ አጥር አይደለንምና ስለ ኢትዮጵያ በተሟላ ኢትዮጵያዊ አንድነት በፅናት የቆምን መሆናችንን እኛ ባንናገርም፤ኢትዮጵያዊ ህብራዊ ውበትን የሚመሰክረው መልካችን የሚታይ ነው።

የውሸት ጥይት እሩምታ ተኳሾቹ፤የተኩሳቸው ቅሪት በሆነው መጥፎ ጠረን ባሩዳቸው ታፍነው በዚያው መፈነጋገላቸው አይቀሬ ነው።

ኢትዮጵያን ያልን የእውነት ዘማቾቹ እኛ ግን ሊያኮሰምኑ፣ ሊያኳስሷትና የጠላት መሳለቂያ እንድትሆን የዳዱላት ኢትዮጵያን አስከብረን፣አጽንተን እናዘልቃታለን።

በዓል ግድ የማይለን፤ደስታ የማይደልለን፣ያለንን ሁለንተናችንን ሁሉ ለሀገርና ህዝብ የሰጠን ነንና አይደለምና የውሸት እሩምታ ምንም ላይገታን በድል ጉዞ ወደፊት ቀጥለናል።

"የመውሊድና የደመራ በዓል አክባሪ
ኢትዮጵያዊያን ሁሉ መልካም በዓል ይሁንላችሁ"

በአስቻለው ሌንጫ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/channel/UCgcF4HWzgNZRsmMlUlb8ebQ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቴሌግራም
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official

26/09/2023
26/09/2023
26/09/2023

ከዘመን ወደ ዘመን፥ በ"ጋሪ ዎሮ"




ምርቃት፣ ለጋስነት፣ በአስተውሎት የተቀመሩ፥ በወግ የተሰደሩ ባህላዊ ትሩፋቶች ከፍ ብለው የሚንፀባረቁበት የአዲስ ፀሃይ መፈንጠቂያ፣ የሺናሾች መፈንደቂያ ምልክት ሆኖ "ጋሮ" ለዘመናት ዘልቋል። "ጋሪ ዎሮ" የአዲስነት እና የተስፋ ወቅት ነው ይላሉ ቦሮ ሺናሾች። "ዘመን ተለወጠ" ብሎ ከማለፍም በላይ ትልቅ ስፍራ ይሰጡታል፣ ዘለግ ላለ ጊዜ ያከብሩታል፥ እስኪደርስ ይጓጉለታል!

በቦሮ-ሺናሻ ወግ እና ባህል መሰረት "ጎርኮ" የተሰኘ ዋና የጎሳ መሪ እስከዛሬ ለደረሱት ውብ ባህላዊ ትሩፋቶች ዘላቂነት መተኪያ የሌለውን ሃላፊነት ተወጥቷል። የብሔረሰቡ አባላት "ጎርኮ" 'በሁሉም ላይ የመወሰን ስልጣን የተሰጠው ከፈጣሪ ነው' ብለው ስለሚያምኑ ውሳኔውን የመቀበል ግዴታ አለባቸው። ይህ የጎሳ መሪ የመጨረሻ ውሳኔውን የማሳለፍ ስልጣኑ ወግ፣ ታሪክ፣ ባህል እና ሐይማኖታዊ የክንዋኔ ጉዳይን በበላይነት እስከ መምራት ይደርሳል።

ይህንን በተዋረድ የመጣ አመክንዮ መነሻ በማድረግ ነው ቦሮ ሺናሻዎች መርቀው ከጨረሱ በኋላ ማሳረጊያውን "ሀኒየ ቦጎ ኖዳናዎ ጎርክኮስ ኪንዱዋ" በማለት መራቂ ሽማግሌዎቹ ያጎደሉት ቃል፣ የሳቱት ሀሳብ ቢኖር ጉድለታቸው "ከጎርኮ" ሙላት እንዲካፈል፣ ያልጠቀሱት ካለ ከእርሱ ጋር እንዲካተት ተናግረው ማሳረጊያ የሚያደርጉት።

ባህሉን፣ ወግ እና ልማዱን መርቆ፣ እንዳይጠፋ ጠብቆ፣ ሳት ያሉ ሂደቶች ሲያጋጥሙ አርሞና አርቆ ዘመን እንዲሻገር "ጎርኮ" ትልቅ ሚና ነበረው። በዚህ መሰረት ነው እንግዲህ ሺናሾች "ጋሪ ዎሮ"ን በየዓመቱ በጉጉት እየጠበቁ የሚያከብሩት። ማሳቸውን ተጋግዘው የሚያርሱትም ለቀጣዩ አዲሱ ዓመት የሙሉ ቀለባቸው ጅማሮ የእህሉን እሸት በጋሮ ላይ ለመቋደስ ስለሆነ ለዘር ሲሰናዱ ቀን የሚቆጥሩት "ለጋሮ ይደርሳል ወይ?" እየተባባሉ በመመካከር ነው።

"ጋሪ ዎሮ" እንደሌሎቹ በዓላት የአጭር ጊዜ ዋዜማ የለውም። መስከረም 16 ሊደርስ ሁለት ወር ሲቀረው ወጣቶች በህብረትም በተናጠልም መሰናዳት ይጀምራሉ። ወላጆችም እንዲሁ! የጋራ በሆነው አደባባይ "ጋሪ ጄባ" ላይ በነቂስ ወጥተው ወግና ልማዱን በጠበቀ አኳሃን "ጊጪንጋ" ወይም "ጉሪ ዱባ" የተሰኘውን እና ሌሎችንም ባህላዊ ጭፈራዎች ከመጫወታቸው በፊት ለኹለት ወራት የዝግጅት ጨዋታዎችን በየተራ እየዞሩ ያደርጋሉ።

ሙዚቃ እና ሺናሾች ቁርኝታቸው ጥብቅ ነው። ደስ ያለው ስሜቱን በግጥምና በዜማ አዋዝቶ ደስታውን ይገልፃል። ያዘነም ቢኖር የውስጥ ስብራቱን፣ በደሉን ወይም የህይወት ውጣውረዱን በዜማ እና በግጥም ፍንትው አድርጎ ያሳያል። ከሌሎቹ የባህላዊ ዘፈን ዓይነቶች "ጃዋ" የተሰኘው የክራር ዘፈን፣ ጉጫ፣ ጊጪንጋ እና ዳላሻ ተጠቃሽ ናቸው።

"ጋሮ" "እስኪደርስ ያለው የኹለት ወራት ጥበቃው በዘፈን እና በፌሽታ የታጀበ ነው። ወጣቱም አዛውንቱም "ለጋሪ ዎሮ አንድ ወር ቀረው...ኹለት ሳምንት ቀረው..." ወዘተ...እየተባባሉ በተስፋ ይጠባበቃሉ። ታድያ ግን በጋሪ ዎሮ ላይ የሚቀርቡ እሸቶች በዓይነት በዓይነታቸው እንክብካቤ እየተደረገላቸው ይቆያሉ። የጓሮ እሸት ደርሶ ሲጎመራ፣ የማሳውም እህል ለአይን በሚስብ ትዕይንት በነፋሱ ሞገድ እየተጫወተ እያበበ ሲፈነድቅ ሺናሾች ደስታቸው ወደር ያጣል።

በዚህ ወቅት ወደ ጋሪ ዎሮ የሚደረገው ግስጋሴ እየተቃረበ ነውና ዜማዎቹም ይሄንኑ የሚያንፀባርቁ ይሆናሉ። በቦሮ ሺናሻዎች ዘንድ ባህላዊ ዜማ እና "ጋሮ" መሳ ለመሳ የሚሄዱ ናቸው፡፡ "ጋሮ" ባህላዊ ስርዓቱንና ጊዜው ጠብቆ እንዲከበር "ጎርኮ" በጥብቅ የወሰነበት ምክንያት ቤተሰብ፣ ዘመድ አዝማድ ተቀራርቦ የሚወያይበት፣ አንድ ጎሳ ከዋናው ግንዱ ጋር ተራርቆ እንዳይኖር በዓመት አንድ ጊዜ የሚገናኙበት ዕድል እንዲሰፋ ነው።

ምክንያቱ ይህ ብቻ አይደለም! በዘመዳሞች መካከል ጋብቻ እንዳይፈፀም፣ የብሔረሰቡ አባላት እርስበርስ እንዲተዋወቁ፣ የተጣሉ ካሉ እርቀ ሰላም እንዲያወርዱ፣ ተከታዮች አንጋፋዎቻቸውን አውቀው እንዲያከብሩ ለማድረግም ጭምር ነው። የብሔረሰቡ አባላት በሁሉም ረገድ አንድነታቸውን በማጠናከር የሚመጡባቸውን ፈተናዎች በተባበረ ክንድ እንዲከላከሉ በማሰብ የብሔረሰቡ ዋና መሪ "ጎርኮ" ስልጣኑን ተጠቅሞ በመወሰን ለትውልድ አሻግሯል፡፡

የዓመት ሙሉ ጥበቃ፣ ወደ አዲስ ዘመን የመሻገር ከፍተኛ መሻት እና የኹለት ወራቱ ዝግጅት እውን የሚሆኑበት ጊዜ ሲቃረብ የመጨረሻ የመሰናዶ ምዕራፍ ላይ ይደርሳሉ። ምሽት በየቤቱ እየተዞረ የሚደመር ግንድ፣ ከተለያዩ የእንጨት ዓይነቶች ተሰባስቦ በጥንቃቄ ይቀመጣል። የእንጨቶቹ ውፍረትም የተመጠነ ሆኖ ቢያንስ አንድ የ15 ዓመት እድሜ ያለው ታዳጊ ማንሳት የሚችለው እንዲሆን ተደርጎ ይዘጋጃል።

ሺናሾች በከፍተኛ ዝግጅት በጉጉት የጠበቁት ቀን ሲደርስ በዕለቱ አመሻሹን "ጊንድ ጌዳ" ወይም "ኪንድ ኪንድሻ" የተሰኘው ስነስርዓት ከ"ሚሽ ቂራ" ጋር በየቤቱ እየተዞረ ይከናወናል። ምሽቱን ሲደመር ያደረው ግንድ ንጋት አካበቢ ለሚከናወነው ችቦ የመለኮስ "ታው ጨሽ ሚሳ" ወይንም "ጨሽ ኮሻ" በር ከፋች ነው። "ዎርጋዌ..." ለሚሉት "ዎሮ ቦረ..ዎሮ ቦሬረ." እያሉ ታላላቆች ይመርቋቸዋል።

"ጨሽ ሚሳ" ወይም "ጨሽ ኮሻ" የሚከናወንበት የጋሪ ዎሮ የመጀመሪያው ቀን "ዮንጎስ ጉራ" በመባል ይታወቃል፡፡ ይህ ሥነ-ሥርዓት ከንጋቱ 11፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ረፋዱ 4፡00 ሰዓት ድረስ የሚፈፀም ሲሆን ችቦ የሚቃጠልበትም ቦታ ሲደርሱ ከአዋቂ እስከ ህፃን በእሳቱ ዙሪያ እየዞሩ ይጨፍራሉ።

በለምለሙ የክረምት ወቅት የተዘሩ የጓሮ አትክልቶች በባህሉ መሰረት የደመራው ዕለት ከየቤቱ ተሰባስበው ይቀርባሉ። ይህ ስርዓት ወደ መጠናቀቁ ሲቃረብ "ጋሪ ቱላ" ወይም የችቦን አመድ ከአከባቢው ታዋቂና አንጋፋ የሆነ ግለሰብ ለሴቶች በደረታቸው ላይ ለወንዶች በግንባራቸው ላይ በማድረግ በምርቃት የጧቱ ስነስርዓት ይቋጫል።

ረፈድ ሲል ደግሞ ሁሉም ባህላዊ ልብሱን ለብሶ "ጋሪ ጄባ" የጋሮ አደባባይ ላይ "ጋሪ ቱላ" እየዞሩ ቀኑን ሙሉ ሲጨፍሩ ይውላሉ። "ዮንጎስ ጉራ" በተባለው ቀን "ማስባራ" ወይም ያገቡም ያላገቡም ሴቶች አንድ ላይ በመሆን "አፈረ...አፈረ...አፋሴ ገዮረ ፁንቤ ጊጣ" እያሉ እያዜሙ የዘመድ ቤት በሙሉ ያዳርሳሉ፡፡ በዚህም የመጀመሪያው ቀን "ጋሮ" በዓል "ዮንጎስ ጉራ" ይጠናቀቃል።

"ጊትል ጋራ" ወይም ሁለተኛው የጋሮ ቀን በማግስቱ ይቀጥልና በመጀመሪያው የጋሮ ዕለት ከአቅም በላይ በሆነ ችግር የ"ጋሪ ጊንዳ" ሥነ-ሥርዓት በቤቱ ያልፈፀመ አባወራ "ጋሪ ጊንድ ኪንድሻ" ስርዓት ይፈፅማል። ስርዓቱም ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት እስከ ሌሊቱ 6፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ የሚከናወን ሆኖ በበቂ ምክንያት ካልሆነ በስተቀር የመጀመሪያዋ ቀን የጋሮ በዓል አከባበር ተለይቶ "ጋሪ ጊንዶ" ማድረግ ፍፁም የተከለከለ ነው።

"ሜይ ዴና" ወይም "ኬዝል ጋራ" የተሰኘው ከ"ጊትል ጋራ" ቀጥሎ በከፍተኛ ጭፈራ ታጅቦ በአባቶች ምርቃት ይጠናቀቃል። ከዚህ በኋላ ግን የጋሪ ዎሮ መቋጫ ምዕራፍ ወደ ሆነው "ጋሪ ዴራ" ወይም አራተኛ የ"ጋሮ" ቀን ይይሻገራሉ። "ጋሪ ዴራ" ከሌሎች በዓይነቱና በአሰራሩ ለየት የሚያደርገው ዋናው የጋሮ በዓል ከወጣ ከአንድ እስከ ሁለት ወር ባለው ጊዜ ውስጥ ጥቅምት ወይም ህዳር ላይ መካሄዱ ነው፡፡

"ጋሪ ዴራ"ን የሚያዘጋጀው አባወራ በሀብት እና በዝና ከአካባቢው የላቀ ስፍራ ያለው ሊሆን ይገባል። በዚህ በዓል ላይ "እያኬ" እና "ዳላሻ" የተባሉ ዘፈኖች መሳጭ በሆነ መንገድ ይዘፈናሉ "ፌራ" በተሰኘ ባህላዊ የሙዚቃ መሳሪያ የታጀበ ዘፈንም ለበዓሉ ታዳሚዎች ይቀርባል። በዚህ ልዩ የጋሮ ድግስ ላይ ደጋሹ ከሚኖርበት አካባቢ አልፎ ራቅ ባለ ቦታ የሚገኙ የቅርብ ዘመድና ወዳጆቹ ይታደማሉ።

መብሉና መጠጡ እንደልብ ከተዳረሰ በኋላ ባህላዊ ዘፈኖች መቅረብ ይጀምራሉ። ከጧቱ 3: 00 ሰዓት ገደማ ጀምሮ እስከሚቀጥለው ቀን ንጋት ጨዋታው እንደደራ ያድርና "ዳምቢ ዴራ" ቀጥሎ ይከናወናል። በዚህም ደጋሹ አባወራ የሚወጣበት አልጋ የሚመስል ሰረገላ ተሰርቶ ደጋሽ አባወራው ከሶስት ታዋቂ ሽማግሌዎች "ኢምባ" የተባለውን የሙዚቃ መሳሪያ የሚጫወት ሰው ተጨምሮ ሥነ-ሥርዓቱ ይጀመራል።

ሽማግሌዎችም የዓለምን ነባራዊ ሁኔታ፣ የሺናሻ ወግ፣ ልማድና ባህል "ኔማ" ጠንቅቀው የተረዱ፣ ለሌላውም በውል የሚያስረዱ፣ ከማህበረሰቡ ዘንድ አመኔታና ቅቡልነት ያላቸው ሊሆኑ ይገባል። ስርዓቱ አለም ላይ እየተስተዋለ ያለውን ክስተትም በቃል እየጠሩ የሚመርቁበት ሥነ-ሥርዓት ሲሆን ከዚህ ስርዓት ፍፃሜ በኋላ የቦሮ-ሺናሻ የጋሮ በዓል ፍፃሜውን ያገኛል።

ሌሎች ባህላዊ ጨዋታዎች ጊዜያቸውንና ሁኔታዎችን ጠብቀው ዓመቱን ሙሉ ይቀጥላሉ! የዚህ ዓመት "ጋሪ ዎሮ" ይዞት የመጣውን አዲስ ዘመን ለሚቀጥለው "ጋሪ ዎሮ" ያስረክባል። ዘመኑ በአባቶች ምርቃት ተሞልቶ በሙላትና በደስታ እንዲዘልቅ ያደረገ ፈጣሪ ምስጋና ይቀርብለታል!!

"ዎርጋዌ..ዎሮ ቦሬረ"
"ጋው ኤዋሪሽ ጄኖን ቤዌረ"

25/09/2023
25/09/2023

ዛሬም ነገም አገራችን የተደቀነባትን ችግር ማለፊያ መንገዱ ወንድማማችነት ብቻ ነው!

ወንድማማችነት የዘመናዊነት መገለጫ ነው፡፡ ወንድማማችነት እርስ በእርስ መተማመንን፤ መተሳሰብን የሚፈጥር ነው፡፡ እርስ በእርስ መተሳሰብ ሲኖር መደጋገፍ ይኖራል፡፡

አገራችን በታሪኳ እጅግ ፈታኝ የሚባሉ ወቅቶችን አሳልፋለች፡፡ አሁንም እያሳለፈች ትገኛለች፡፡ በየጊዜው የሚገጥማትን ችግር በጽናት ማለፍ የቻለችው በህዝቦቿ የተባበረ ክንድ እና አይበገሬነት ነው፡፡

ወንድማማችነት የአገራችንን ህዝብ የሚያስተሳስር የህልውናችን መሰረት ነው፡፡ በወንድማማችነት ስሜት መደመር ለአገራችን ዘላቂ ሰላም ይበጃል። የአገራችን ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች የጋራ ጥቅም የሚከበረው በወንድማማችነት ስሜት በጋራ ስንደመር ብቻ ነው፡፡

25/09/2023

ከጎንደር ከተማ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ኮማንድ ፖስት የተሰጠ መግለጫ

የጠላት ኀይል ለእሁድ አጥቢያ ከሌሊት 10:00 ጀምሮ ወደ ጎንደር ከተማ ሰርጎ በመግባት አንድ ፖሊስ ጣቢያ ላይ ጥቃት ለመሰንዘር የሞከረ ሲሆን የፀጥታ መዋቅራችን አኩሪ ተጋድሎ አድርጎ ጥቃቱን አክሽፎታል።

የጸጥታ መዋቅራችን ንፁሃን እንዳይጎዱ በማድረግ የጠላት ኀይል አመራሮችን ጨምሮ ከ50 በላይ ሙትና ቁስለኛ በማድረግ እንዲሁም የተወሰነው ደግሞ የወገን ኀይልን ምት መቋቋም አቅቶት እንዲፈርጠጥ ሆኗል።

ይህ ሆኖ እያለ ጎንደርን ተቆጣጠርን በማለት የሚነዛው የሀሰት ፕሮፖጋንዳ እንዳለ ማየት ችለናል። ነገር ግን ይህ ዓላማ የሌለው ኀይል ንፁሃንን ከማሰቃየትና ክልላችንን ሰላማዊ እና የተረጋጋ እንዳይሆን ከዚህም ከዚያም በመተንኮስ ግጭት ውስጥ በመግባት የልማታችን አደናቃፊ ኀይል ከመሆን ያለፈ ግብ የሌለው ሲሆን በቀጣይም ሕግ የማስከበር ሥራችንን ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል።

ሕዝባችንም ለሰጠን ድጋፋ ከልብ እያመሰገን ቀጣይም በዘላቂነት የተለመደውን ድጋፍ እንዲያደርግ እና የአካባቢውን ሰላም ከጸጥታ መዋቅራችን ጋር ሆኖ እንዲጠብቅ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን!

ወቅቱ የሚጠይቀውን መስዋእትነት በመክፈል ለሕዝባችን ዘላቂ ሰላም እናጎናፅፍለን!

መስከረም 13/2016 ጎንደር

22/09/2023
22/09/2023

የመደመር መንገዳችን ያለ ልዩነት ለሁሉም ዜጎቻችን የተዘረጋ አዲስ የብርሃን መንገድ ነው፡፡ መዳረሻ ግባችን ብልጽግና ነው። ብልጽግና ንጋት እንጂ ሌት ሆኖ ማንንም አይጋርድም፣ አይሸፍንምም፡፡ በትኅትና የማይበርድ ቁጣ፣ በልግስና የማይጠወልግ ስስት፣ በደግነት የማይሰበር ክፉት፣ በመደመር የማይጠገን ልዩነት፣ በብልጽግና የማይኮሰምን እርዛት፣ በሐቅ የማይረታ ሐሰት አለመኖሩን ዐውቀን በጽናት ጉዟችንን እንቀጥላለን፡፡

የብልፅግና ፓርቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ዐቢይ አህመድ

22/09/2023
21/09/2023

አዲስ አበባ ውስጥ የብልፅግና መንግስት እያካሄደው ያለው ምንነቱ ያልታወቀ ተግባር

21/09/2023
21/09/2023

ዋነኛ ዓላማችን ህብረ-ብሔራዊነቱ የተጠበቀ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ማህበረሰብ መገንባት ነው !

የፓርቲያችን ዋነኛ ዓላማ ህብረ-ብሔራዊነቱ የተጠበቀ አንድ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ማህበረሰብ መገንባት ነው። ህብረ-ብሔራዊ ስንል የብሔር፣ የኃይማኖት ወይም ሌላ ማንነቶችን የአቀፈና ማንንም ያላገለለ ማህበረሰብ ማለታችን ነው።

የፓርቲያችን ህብረ-ብሔራዊነት በሁሉ-አቀፍነት፣ በብዝኃ-ልሳንነት እና በአሳታፊነት ሊገለጽ ይገባል ብሎ ፓርቲያችን ያምናል። ህብረ-ብሔራዊ አንድነት ብዝኃነትን እንደ ፀጋ የሚመለከት ለሁሉም ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ዕውቅና የሚሰጥና ከአላቸው የታሪክ ትስስር፣ ተመሳሳይ አሁናዊ ሁኔታ፣ የጋራ ጥቅም እና ተስፋ በመነሣት ጠንካራ ህብረትና ትብብር ሊኖራቸው ይገባል የሚል ዕሴት ነው።

ህብረ-ብሔራዊ አንድነት፣ ማንነታችን እርስ በርሱ የተጋመደ፣ የተሰናሰለ እና የተዋሃደ መሆኑን አመላካች ነው። ህብረ-ብሔራዊ አንድነት፣ ዕጣ ፈንታችን እጅጉን የተቆራኘ መሆኑን በመገንዘብ ለጋራ ዓላማና ግብ አብረን መቆም፣ አብረን መስራት፣ መደጋገፍ እና መተጋገዝ እንደ ሚገባን የሚያስገነዝብ አመለካከት ነው።

የብልፅግና ፓርቲ ፕሮግራም (2014) ገፅ 10

21/09/2023

የምስራቅ ጉራጌ ዞን የካቢኒ ሹመት
5 ስራ አስፈፃሚ
1. አቶ ሙስጠፋ ሀሰን - ዋና አስተዳደር
2. አቶ ደሱ አበጋዝ - ምክትል አስዳዳሪ እና ግብርና መምሪያ
3. አቶ መሰለ ጫካ - ዋና የመንግስት ተጠሪ
4. አቶ ሀሰን ከድር - ምክትል የመንስት ተጠሪ እና አደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ
5. አቶ መሰረት ሽፋ - ምክትል የመንግስት ተጠሪ እና ፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊ ሆነው ተሹመዋል።
በመቀጠል የምስራቅ ጉራጌ ዞን የመምሪያ ሀላፊዎች ዝርዝር እነሆ
1-ታጁ ነስሩ - ኮንስትራክሽን ፅ /ቤት
2-ዘነበ ደበላ -ኢንቨስትመንት
3-መሀመድ አማን -ውሀና ማዕድን
4-ሰለሞን ጉስሳ -ጤና መምሪያ አላፊ
5-አህመዲን ደድገባ -ሰራተኛና ማህበራዊ ፅ /ቤት
6-ተካልኝ ንጉሴ -ፀጥታና ሰላም
7-ፋሲካ ስርሞሎ - ፍትህ መምሪያ ኋላፊ
8-ሲቲ ሙስጠፋ -ሴቶች ጉዳይ ኋላፊ
9-አብርሀም ጠና -ፕብሊክ ሰርቪስ ኋላፊ
10-ነጋልኝ አለሙ -ቴክኒክና ሙያ ኋላፊ
11-አለማየሁ ጎሳዬ -ትራንስፓርትና መንገድ ልማት
12- የሽል ጌታ በላይነህ -ገቢዎች
13- ባህሩ አሰፋ - ኮሚኒኬሽን ኋላፊ
14- አህመድ ኑሪ -ወጣቶችና እስፓርት
15-አብድረህማን አንደግባይ -ፋይናንስ መምሪያ አላፊ
16-ብሩክታይት ፀጋዪ -ባህል እና
17-ዘነበ መዶ -ሳይንስና ቴክኖሎጂ
18-ዘሪሁን ለማ -አካባቢና ደን ጥበቃ
19-ፈለቀ አስፋው -ፕላንና ልማት መምሪያ
20-ነስሩ ጀማል -ትምህርት መምሪያ
21- ቤተልሄም ታደሰ -ንግድና ገበያ ልማት
22-አህመዲን ጀማል - ስራ እድል ፈጠራ እና ኢንተርፕራይዝ

20/09/2023

ሪያል ማድሪድ ዩኒየን በርሊንን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ምሽቱን በተካሄደው የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የምድብ ማጣሪያ ጨዋታ ሪያል ማድሪድ ተጋጣሚውን ዩኒየን በርሊንን 1 ለ 0 አሸንፏል።

ጁዲ ቤሊንግ ሃም በተጨማሪ ሰዓት የማድሪድን ብቸኛ ጎል ከመረብ አሳርፏል፡፡

በሌላ በኩል ኮፕንሀገን ከጋላታሳራይ ጋር ሁለት አቻ በሆነ ውጤት ተለያይተዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

20/09/2023
20/09/2023

እንግዲያው ፈታ በሉ

Address

SNNPR
Butajira
WORABE

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when አንድነት ሀይል ነው Unity is power posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to አንድነት ሀይል ነው Unity is power:

Videos

Share