Abdu sultan / አብዱ ሱልጣን

Abdu sultan / አብዱ ሱልጣን رَبِّ ٱشْرَحْ لِى صَدْرِى وَيَسِّرْ لِىٓ أَمْرِى
pageun follow ያድርጉ

09/03/2024

✍በአምናው ፆም ካጋጠመኝ ነገር ኢማሙ የተራዊህ የመጀመሪያውን ረክዓ ጨርሶ ሩኩዕ እስኪወርድ ድረስ Fb የሚጎረግር...
#መህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀማችንን እናስተካክል፡፡

06/03/2024

Shout out to my newest followers! Excited to have you onboard! አቡ ኡካሻ, Tofiq Redi, Ahmed Musema, Reshad Kemal, አሽራፉዲን ነስር

✍ኢታይ ኩትብ ጴንጣጦ ለኛይ ሰብ ምን ያይላን የስናዱኒይኮ የቴራነን   ለኢኮ ኡመተው በቀተሊ ያለን ተጪፖትዋ ተስናዶት ያትኬሻን
11/02/2024

✍ኢታይ ኩትብ ጴንጣጦ ለኛይ ሰብ ምን ያይላን የስናዱኒይኮ የቴራነን ለኢኮ ኡመተው በቀተሊ ያለን ተጪፖትዋ ተስናዶት ያትኬሻን

10/02/2024

Shout out to my newest followers! Excited to have you onboard! Salman Bezu, ዩስራ ኡሚ, Shemsu Haji Nuriye, Zeyne Geleto, B Măň B Măň

 ~* ልጅ ሆይ! ስለ ወላጅ ሐቅ ክብደት ሲነገር አይክበድህ። የወላጅን ሐቅ በመጠበቅ ከወላጅ በላይ የሚጠቀመው ልጅ ነው።* ሚስት ሆይ! ስለ ባል ሐቅ በተደጋጋሚ ሲነገር አይደብርሽ። የባልን ...
03/01/2024


~
* ልጅ ሆይ! ስለ ወላጅ ሐቅ ክብደት ሲነገር አይክበድህ። የወላጅን ሐቅ በመጠበቅ ከወላጅ በላይ የሚጠቀመው ልጅ ነው።
* ሚስት ሆይ! ስለ ባል ሐቅ በተደጋጋሚ ሲነገር አይደብርሽ። የባልን ሐቅ በመጠበቅ ከባል በላይ የምትጠቀመው ሚስት ናት።
* ባል ሆይ! ስለ ሚስት ሐቅና ኃላፊነትህን ስለ መወጣትህ ሲነገር አትሰላች። የሚስትን ሐቅ በመጠበቅ ከሚስት በላይ የሚጠቀመው ባል ነው።

~ ማንም ቢሆን በፈጣሪው የተጣለበትን ሐቅ ቢወጣ ከሚያከብረውና ከሚንከባከበው አካል በላይ የሚጠቀመው ራሱ ነው። ደግሞም በፈጣሪ የተጣለብንን አደራ ለመወጣት ሲያደርጉ እናደርጋለን፣ ሲተው እንተዋለን ዓይነት የ 'ሰጥቶ መቀበል' ሂሳብ ውስጥ መግባት የለብንም። አባትህ ቢበድልህ የበደል ሂሳብ ውስጥ አትግባ። በወንጀል እስካላዘዘህ ድረስ በምትችለው ከጎኑ ሁን። ከሌሎችም አንፃር እንዲሁ።
ደግሞም "ወንዶች አላህን ፍሩ!" ማለት ለወንዶች መቆርቆር እንጂ ወንዶችን ማጋለጥ አይደለም። "ሴቶች አላህን ፍሩ" ሲባልም እንዲሁ ሴቶች አቧራ ሊያስነሱ አይገባም። ምክር እንጂ ስድብ አይደለምና።
በተረፈ መልካም ብንሰራ በመልካም ስራችን ከማንም በላይ የምንጠቀመው እኛ ነን። መጥፎም ብንሰራ እንዲሁ። ኃያሉ ጌታ እንዲህ ይላል፦

{إِنۡ أَحۡسَنتُمۡ أَحۡسَنتُمۡ لِأَنفُسِكُمۡۖ وَإِنۡ أَسَأۡتُمۡ فَلَهَاۚ}
"መልካም ብትሠሩ ለነፍሶቻችሁ መልካምን ሠራችሁ። መጥፎንም ብትሠሩ በነርሱ (በነፍሶቻችሁ) ላይ ነው።" [አልኢስራእ፡ 7]
=
ibnu munewor

01/01/2024
Worabe Comprehensive Specialized Hospital ወራቤ ኮምፕርሄንሲቭ እስፔሻላይዝድ ሆስፒታል
28/12/2023

Worabe Comprehensive Specialized Hospital ወራቤ ኮምፕርሄንሲቭ እስፔሻላይዝድ ሆስፒታል

07/10/2023

✍መላው የወራቤ ፖሊ ቴክኒክ ተመራቂዎች እንኳን ደስ ኣላችሁ

23/09/2023

✍የአላሀ ሉክተኘ ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም ሂንኩ ኢሎን:-[የኘ አምር ዬለቢ ብለ ያሼ ሰብ ቢልከ መቅበልነት ኤለይ፡፡] ኢማሙ ሙስሊም ኢወዱያን

             አንቺ አላህን ፈሪ የጌታዋን ትእዛዝ አክባሪ የሆንሽው ሙተነቂቧ እህቴ ሆይ ኒቃብ ማለት የማንነትሽ መለያ ፣ የሰብእናሽ ጌጥ ፣ የኢማንሽ ነፀብራቅ ፣ ላንቺ በኒካሕ ከተፈቀ...
14/09/2023



አንቺ አላህን ፈሪ የጌታዋን ትእዛዝ አክባሪ የሆንሽው ሙተነቂቧ እህቴ ሆይ ኒቃብ ማለት የማንነትሽ መለያ ፣ የሰብእናሽ ጌጥ ፣ የኢማንሽ ነፀብራቅ ፣ ላንቺ በኒካሕ ከተፈቀደ ውጪ ያለ በተቃራኒ ፆታ ፍላጎት የሰከረ መንገደኛ አካልሽን እንዳያይ የምትሸፍኝበት የኢማን ልብስ እንጂ የፖለቲካ ሸቀጥ ቸርቻሪዎች ሲፈልጉ ልበሺ ብለው አሰልፈው ፎቶ እያነሱ ሲፈልጉ አውልቀሽ ቦርሳ ውስጥ ክተችው የሚሉበት ተራ ጨርቅ አይደለም ። ኒቃብ መልበስ መለኮታዊ የሆነውን መመሪያ ማክበር ስለሆነ ዒባዳ ነው ።
ዒባዳ ደግሞ ኢኽላስና ሙታበዓ ያስፈልገዋል ። ኢኽላስ ማለት ወደ አላህ የምትቃረቢበት አምልኮ በመሆኑ ንያሽን አስተካክለሽ የምትለብሽው የኢማን ልብስ መሆኑን አውቀሽ ለአላህ ብለሽ መልበስ ማለት ነው ። በእልህና በቲፎዞ ወይም እገሊት ስለለበሰች በሚል በስሜታዊነት የሚለበስ ተራ ልብስ አይደለም ። ሙታበዓ ማለት የአላህ መልእክተኛ ባዘዙበት መልኩ መፈፀም የሳቸውን መመሪያ በኒቃብ ዙሪያ መከተል ማለት ነው ።
ኒቃብ የላይ አካልሽን የሚሸፍን ሲሆን የማንነትሽ ምልክት ነው ። በአለባበስሽ የአላህን መመሪያ አክብረሽ በሌሎች ተግባሮችሽ የዚህን የክብርና ኢማን ልብስ የማይመጥን ተግባር ከመፈፀም መቆጠብ ይገባሻል ። ለዚህ ደግሞ ዲንሽን መማርና ህግጋቶቹን ጠንቅቀሽ ማወቅ ግድ ነው ።
የኒቃብሽን ክብር የምታስጠቢቂው አላህ ያዘዘሽን መልእክተኛው ስሪው ያሉሽን በመስራት እንጂ ኢኽዋኖች ከምእራባዊያን በወረሱት የቃረደ ነውጥ ውስጥ በመግባት ለዚህም ሰበብ በመሆን አይደለም ። ኒቃብ የለበሰች ሴት ከፊትና ለመጠበቅ እንጂ ለፊትና ሰበብ መሆን የለባትም ። ኒቃብ ለብሰሽ ጌታሽን ማምለክና እሱ ያዘዘሽን መፈፀም አትችይም የሚልሽ አካል አይሆንም ብለሽ ዋጋ ከከፈልሽ ከነሱመያ ትመደቢያለሽ ። ኒቃብ ለብሰሽ ለፖለቲካ ሸቀጥ ቸርቻሪዎች ጥቅምና ፍላጎት የእነርሱን ሸሪዓ የጣሰ መመሪያና ትእዛዝ አከብራለሁ ብለሽ ለፊትና ሰበብ ከሆንሽ የሁለት ሀገር ውርደት ነው የሚጠብቅሽ ። በመሆኑም አንቺ በኒቃብ ውስጥ ያለሽው እንቁ የኢማን ነፀብራቅ ሆይ ኒቃብሽን እወቂው, ክብሩን አስጠብቂ, አላማውን እወቂ እነዚህ አንቺንና እህቶችሽን ኒቃብ ለብሳችሁ በሰልፍ እንድትወጡ አድርገው ፎቶ ቀርፀው ከጎንሽ ነኝ እያሉ ለሚዲያ ፍጆታ የሚያውሉ አካላት ያንቺንና የእህቶችሽን እንዲሁም የዲናችሁን ክብር የሚያስደፍሩ ናቸው ።
መሪዎቻቸው በድምፃችን ይሰማ በዚሁ መልኩ እህቶችን አደባባይ አውጥተው እኔ አቡበከር ነኝ ፣ እኔ ያሲን ኑሩ ነኝ ፣ እኔ ካሚል ሸምሱ ነኝ እንዲሉ ካደረጉ በኋላ ዋጋ አስከፍሏል ። እነዚያ እህቶች ኒቃባቸው የከሀዲያን ጫማ መጥረጊያ ጅልባባቸው እሳት ማቀጣጠያ ሆኖ አናታቸው እየተነረተ ያ የተከበረው ፊታቸው የኢስላም ጠላት ከሀዲያን ጫማ ጥፊ መለማመጃ ሆኗል ። ያውም በፆም ምድር የሚያፈጥሩበትን ውሃና ዳቦ ከመስጠት ይልቅ በአፍጥር ሳአት ራቁታቸውን በቀዝቃዛ ውሃ ነክረው እያወጡ ምራቃቸው እየተፉባቸው እራሳቸውን እንዲጠሉ አድርገውዋቸዋል ። ውሃ ሲሉ ሽንት እንዲጠጡ ተደርገዋል ። ወላሂ ይህን ስፅፍ እንባ ከሰራ አካላቴ ወደ አይይኔ እየተገፈታተረ ነው ። ምክንያቱም እነዚያን እህቴቼ በአይነ ህሌናዬ እያየኋቸው ስለሆነ ። በዚህ አላበቃም የኒቃብ ለባሽዋ እህቴ ስቃይ እነዚያ በሰው ምስል የተፈጠሩ የሸይጣን ስብእና የተላበሱ አውሬዎች በየተራ ሰክረው እየመጡ ያን አላህን ሲፈራ የነበረውን አካል እርቃን አድርገው ደመነፍሳዊ ስሜታቸውን አርክተውበት ያቺን የኢስላም ልጅ ሙተነቂብ እህቴን ገላዋን ብቻ ሳይሆን ዲንዋን, ስብእናዋን, ክብሯን, ህሌናዋን ደፍረው ከለሊቱ 9 ሳአት ላይ በጣረ ሞት ላይ ሆና በፓንትና በጡት መያዣ ከእህቶቿ ጋር አስፋልት ላይ ጥለውዋቸዋል ።
አካለ ስንኩል የሆኑ ፣ በኤሌክትሪክ ተቃጥለው ደርቀው የሞቱ ፣ አይነ ስውር የሆኑ ፣ የጀርባ አጥንታቸው ተቀጭቶ የአልጋ ቁራኛ የሆኑት ቤት ይቁጠራቸው ። እነዚህ ናቸው የዛሬዎቹ የእነሞር ተረኞች መሪዎች ። እነዛ መሪዎች በዛ ሸቀጥ ባተረፉት ትርፍ ዛሬ በv8 ይሄዳሉ ። በቤተመንግስት አይነት ቤት ይኖራሉ ። ከኢትዮዽያ 20 ሀብታሞች ተርታ ስማቸው ለማስመዝገብ ቀና ደፋ ይላሉ ። የኛዎቹ የእነሞር የኢኽዋን እርዝራዦች የአለቆቻቸውን የዱንያ ህይወት እየቋመጡ በሚመስል መልኩ አንቺን የእነሞርዋ ሙተነቂብ አደባባይ አውጥተው የፖለቲካ ሸቀጥ ሊያደርጉሽ ይፈልጋሉ ተጠንቀቂ ።
በመጨረሻም የራስሽን የኒቃብሽንና የዲንሽን ክብር ለመጠበቅ ምን ማድረግ እንዳለብሽ ኢስላም ያዘዘሽን ለጥቆማ ያክል በዚህ ሊንክ ገብተሽ አንብቢ

⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️

https://t.me/bahruteka/3085

እህቴ ሆይ ኢስላም አንቺን በዚህ ሲያዝሽ ያንቺን ክብር ለመንካት መብትችን ለማሳጣት ወይም ደረጃሽን ዝቅ ለማድረግ አይደለም ። ነገር ግን ክብርሽን ለመጠበቅና አንቺን የልቅና ማማ ላይ ለማስቀመጥ ነው ። ምክንያቱም ሴት የነብያቶች, የአንሷሮችና ሙሀጂሮች, የብርቅዬ የኢስላም ሊቃውንቶች እንደነ ሐሰኑል በስርይ ፣ አውዛዕይ ፣ ኢማሙ ማሊክ ፣ ኢማሙ ሻፍዕይ ፣ ኢማሙ አሕመድ ፣ ኢብኑ ተይሚያ ፣ ኢብኑል ቀይም ፣ ሙሐመድ ኢብኑ ዐ/ወሃብ እናት ስለሆነችና እነዚህን ቤት ሆና ኮትኩታ አንፃ ያሳደገች ስለሆነች ነው ። ለሙተነቂብ ሴት ልጅ ከዚህ በላይ ምን ክብር አላት? ከዚህ በላይ ለኡማው ምን ትጠቅማለች ? እህቴ ሆይ ኒቃብሽን እወቂው ክብሩንም ጠብቂው ።

አላህ የቀደምቶች ተምሳሌት የምትሆኚ ያድርግሽ ።

https://t.me/bahruteka

23/08/2023

✍መጮህ ከጀመርን ሳምንት ሊሞላን ነው ምን አዲስ ነገር ፈጠርን? ከነበርንበት ፈቀቅ ብለናል? እስኪ አፈፃፀማችንን እንገምግም፡፡

 የአፋልጉኝ ➖➖➖➖➖➖➖ተፈላጊዋ ወይዘሮ ፋጤ ቅናቶ ጀማል ትባላለች አድራሻ በስልጤ ዞን በጦራ ከተማ አስተዳደር የመልተሜ ቀበሌ ነዋሪ ናት ።በዕለተ ቅዳሜ ነሀሴ 13/2015ዓ.ም ከጠዋቱ 3 ...
22/08/2023


የአፋልጉኝ
➖➖➖➖➖➖➖
ተፈላጊዋ ወይዘሮ ፋጤ ቅናቶ ጀማል ትባላለች አድራሻ በስልጤ ዞን በጦራ ከተማ አስተዳደር የመልተሜ ቀበሌ ነዋሪ ናት ።በዕለተ ቅዳሜ ነሀሴ 13/2015ዓ.ም ከጠዋቱ 3 : 30 አካባቢ ከቤት እንደወጣች ልትመለስ አልቻለችም ። ተፈላጊዋ ባለ ትዳር እና የአንድ ልጅ እናት ናት

ተፈላጊዋ ወይዘሮ ፋጤ የመንፈሳዊ ህክምና ማለትም ቁራን እየተቀራበት እንደነበረ ቤተሰቦቹ ተነግሯል

ተፈላጊዋ ኒቃቢስት ስትሆን በዕለቱም ለብሳ የወጣችው ልብስ-ጥቁር ጂልባብ እና ከውስጥ ለብሳው የነበረው ቀሚስ ሮዝ ቀለም ቀምስ ስሆን ተጫምታ የነበረው ጫማ ወርቃማ ሲልፖር ቀለም ያለው እንደሆነ ተገልጿል ።

ወይዘሮ ፋጤ ጀማልን ያየ ወይም ያለችበትን የሚያውቅ በስልክ ቁጥር 0910688074 ሰብሬ
0949031509 ተውፊቅ
0926122143 ቅናቶ ላይ ደውሎ ቢያሳውቁን ወሮታ ከፋይነን ይላሉ ቤተሰቦቹ

 ፡፡✍ከሰምኑ የመዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጋር በተያያዘ  በስራ ወዳዱ እና ጨዋው የስልጤ ህዝብ ላይ ታላቅ የ ፖለቲካ በደል እንደተፈፀመበት ለማንም ግልፅ የወጣ ጉዳይ ነው፡፡ይህንንም ተከትሎ ...
21/08/2023

፡፡
✍ከሰምኑ የመዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጋር በተያያዘ በስራ ወዳዱ እና ጨዋው የስልጤ ህዝብ ላይ ታላቅ የ ፖለቲካ በደል እንደተፈፀመበት ለማንም ግልፅ የወጣ ጉዳይ ነው፡፡ይህንንም ተከትሎ በመህበራዊ ሚዲያ ብዙዎች ቅሬታቸውን እያሰሙ ይገኛሉ በተለይም አንዳንድ አክቲቪስት ነን ባዮች የስልጤን ህዝብ እነሱ በፈለጉት መንገድ ሊነዱት ሲሞክሩ እያየን ነው እሄ ደሞ እንደግሌ ምንም ውጤት የሚያመጣ አይመስለኝም ፡፡
እውነት ነው አንዳንዴ ጩሀት መፍትሔ ሊያመጣ ይችላል ነገር ግን መፍትሔ የሚያመጣው እንደዚህ አይነቱ ሰይሆን በጥበብ የተሞላ ሲሆን ነው፡፡እንደሚታወቀው ሰሞኑኑን ካምባታዎች ሲጮሁ ቄሮዎች ብቻ አልነበረም ሲቃወሙ የነበሩት የዞኑ ም/ቤት ጭምር የፍትሃዊነት ችግር እንዳለና እንደማይቀበለው አፅድቆ ነበር ላዛም ነው ለውጥ ያመጡት፡፡የኛዎቹ ደሞ አብዛኛዎቹ ተስማምተው ነው የመጡት ያ ማለት ትግሉ አይደግፉም ማለት ነው፡፡
ስለዚህ ትክክለኛውን ፍትህ ለማግኛት
➊ከተቻላ አመራሮች ትግሉን እንዲደግፉ ቢቻል አስቸኳይ ጉባዔ ጠርተው አቋማቸውን ግልፅ እንዲያደርጉ ማድረግ
➋ካልሆነ ደግሞ ሌሎች የፖለቲካ ምሁራንን በማማከርና የተሻለውን መንገድ በመምረጥ በጋራ ትግል ማድረግ የተሻለ ይመስለኛል እንደዛ ካልሆነ ማንም መፃፍ ስለቻለ በ facebook መጥቶ ሰላማዊ ሰልፍ ውጡ ,መንገድ ዝጉ ስላለ ይህ ህዝብ ተነስቶ የሚያደርግ ሞኝ አይምሰላችሁ፡፡

☞ሳጠቃልለው የተናጥል ጉዞ ይቅርብን ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ይበዛል የኛ አመራሮች ችግር ኣለባቸው መብትህን ስለጠየክ ብቻ ከርቸሌ ሊያወርዱህ ይችላሉ ስለዚህ በተናጥል ከመታገል ከምሁራን በመመካከር የሚያዋጣውን መንገድ በተቀነጀ መልኩ ማጧጧፍ የተሻለ ይመስለኛል ሰላም ሁኑ!!

Address

Butajira

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Abdu sultan / አብዱ ሱልጣን posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Share