28/06/2024
በእንሴኖ ከተማ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የማስጀመሪያ ፕሮግራም ተካሄደ!!!
=============
እንሴኖ፤ሰኔ/21/2016 ዓ.ም
ዜጎችን ከተረጂነት አስተሳሰብ ለማለቀቅ፣የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የመንግስት የትኩረት መስክ በመሆን በባለፉት አመታት እየተተገበረ ይገኛል።
በተለይ በባለፉት ጊዜያት ሀገራችን ኢትዮጵያ በውጭ ወራሪ ሃይሎች እንዳትገዛ ህዝቧ እጅጉን ታግሎ ነፃነቷን አስረክቧል።
ይሁንና ድህነትን በማስወገድ ረገድ ክፍተቶች በመኖራቸው ዜጎች የምግብ ዋስትናቸውን አስተማማኝ ማድረግ አልቻሉም።
ይህን መሰረት በማድረግ ከለውጡ ማግስት የበጋና የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎትን መርህ አድርጎ በመያዝ ብዙ አቅመ ደካማ ወገኖችን እንዲረዱ ሆነዋል ።
በእንሴኖ ከተማ አስተዳደርም የበጋ በጎ ፈቃድ አገልግሎትን በመዝጋት የክረምት ወራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሃ ግብር በዛሬው ዕለት በይፋ ተጀምሯል።
በመርሃ ግብሩ ላይ የእንሴኖ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ዘይኑ ቃሲም የተገኙ ሲሆን መልዕክትም አስተላልፈዋል።
በዚህም መንግስት የህዝቡን ዘርፈ ብዙ ችግሮችን ለመፍታት ዕቅድ ይዞ እየሰራ ይገኛል ብለዋል።
በተለይ አቅመ ደካማ ግለሰቦችን ካሉበት የድህነት ህይወት ለማለቀቅ በምግብ እራሳቸውን እንዲችሉ እያደረገ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።
ይህን መሰረት በማድረግ ቤት የሌላቸው ወገኖችን ቤት የመገንባት፣ያረጁ ቤቶችን የማደስ እና የተለያዩ የቁሳቁስ ድጋፍ ሲያደርግ ቆይቷል በያዝነው የክረምት ወራት የበጎ አድራጎት ተግባራትን እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።
የከተማው የብልፅግና ፓርቲ የፖለቲካና ሪዮተ አለም ዘርፍ ሃላፊ አቶ ሸምሱ አደም በበኩላቸው፡-የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ስራዎች ሰውነትን የምንላበስበት የእርስ በእርስ መደጋገፋችንን፣መተባበራችንን እና አንድነታችንን የምናጠናክርበት ነው ብለዋል።
ለዚህ ደግሞ ጊዜው ክረምት በመሆኑ አቅመ ደካማ ወገኖች በብዙ የሚቸገሩበት በመሆኑ ተረባርበን በአረጋውያን ቤት እድሳት፣የምግብ ቁሳቁስ ድጋፍና ሌሎች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ስራዎች ላይ በመሳተፍ የበኩላችንን አስተዋጽኦ እናድርግ ብለዋል።
የእንሴኖ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ዩኒት ኃላፊ አቶ ያሲን ሸምሱ እንደተናገሩት፡-አዲስና ያረጁ የአረጋዊያንና አቅመ ደካሞች ቤት በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ለመስራት የቅድመ ዝግጅት ስራ መሰራቱን የገለፁ ሲሆን
ወጣቶችን መሰረት ያደረገ እንዲሁም ህዝብን በተለይ ጣሪና አቅመ ደካማ ወገኖችን የማገልገል ተግባር በትኩረት እየተሰራበት እንዲመገኝ አመላክተዋል።
የበጎ አድራጎት ስራው በብዙ ዘርፈ እንደሚተገበር በመግለጽ በበጋ ወቅትና በክረምት መርሃ ግብር እየተከናወነ ይገኛል ብለዋል።
በያዝነው የክረምት ወቅት የአረጋውያን ቤት እድሳትና አዲስ ግንባታ ለማከናወን ዝግጅት መደረጉን ተናግረዋል።
በመጨረሻም የእንሴኖ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ዘይኑ ቃሲም የአንዲት አቅመ ደካማ እናት ቤት ግንባታን አስጀምረዋል።