Ibnu Abdlber alhabeshiy

Ibnu Abdlber alhabeshiy ስለ እውነት መቆም እውነትን ያጸናል ።ራስን ለትልቅ አላማ ማጨት ትልቅ ያደርጋል።
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏 I am IbnuAbdlber Alhabeshiy .I have abig dream.I will achieve unbelievable goal.follow me.

Let us Start your dream with me.
.Don't hate me. Please help me .Please stand with me.

25/02/2024

ሰላም ጓዶች የሚከራይ መኪና የምታውቁ የጃር ውሃ የሚጭን መኪና እፈልጋለሁ።ክፍት ያልሆነ ሙስሊም አከራይ ይበልጥ ደስ ይለኛል።
የምንሰራው እዚው አዲስ አበባ የምንቀዳው ፋም ውሃ ሸገር ከሚገኘው ፋብሪካ ነው።
የምታውቁ ወይም ባለቤቶች ካላቹ
በ ቴሌግራም
በ coment /
@0939166068
ወይም@0943593331
🚚🚚🚚🚚🚚🚚🚚🚚🚚🚚🚚🚚

03/12/2023
03/12/2023

እንዲ ምናለቅስላቸው አፍ አለኝ ብለው ይሰድቧቸዋል።Abdlhafiz Abdlber Alhabeshiy

Ibnu Abdlber alhabeshiy

ጉራጌን ብልግና በማስተማር ቀዳሚ ማድረግ አይቻልም ⚠️⚠️⚠️⚠️⚠️⚠️⚠️⚠️⚠️⚠️⚠️⚠️⚠️ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከ ሌሎች ወደ ኋላ ከሚያስቡ ሰዎች እየተኮረጁ ወደ ጉራጌ ማህበረሰብ ለማስረጽ የ...
28/11/2023

ጉራጌን ብልግና በማስተማር ቀዳሚ ማድረግ አይቻልም
⚠️⚠️⚠️⚠️⚠️⚠️⚠️⚠️⚠️⚠️⚠️⚠️⚠️
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከ ሌሎች ወደ ኋላ ከሚያስቡ ሰዎች እየተኮረጁ ወደ ጉራጌ ማህበረሰብ ለማስረጽ የሚደረጉ ሙከራዎች እጅግ አሳዛኝ ናቸው።ይህ ጉዳይ ደግሞ ይበልጥ የከፋ የሚያደርገው ያውቃሉ ተብሎ በትግል ስም በማህበረሰቡ ስማቸው ያስመዘገቡ የሚዲያ ተሳትፏቸውም ቀላል የማይባሉ ናቸው።
"የ አላዋቂ ሳሚ ንፍጥ ይለቀልቃል " እንደ ሚባለው ምን ለማህበረሰቡ ሚጠቅም ነገር ያመጡ ይመስል በቁንጅና ውድድር ተብሎ ራቆት መሄድ እንደወንጀል ለሚፈርጅ ማህበረሰብ #ብልግና ሊያስተምሩት ደጁ ድረስ መጥተዋል።ሰሞኑ በተዘጋጀውና የሚል ስያሜ የተሰጠው መድረክ #ያበሳጫል ።ለዚያ ንጹህ ማህበረሰብ ፕሮግራም አዘጋጅቶ መቅረብ አሳፋሪ ተግባር ነው።
ከዚ ፕሮግራም ህጻናትና ታዳጊዎች ምን አይነት አራያ እየተደገሰላቸው እንደሆነ ሲታሰብ እውነትም ጉዳዩ ሳይውል ሳያድር #ተዉዉዉ ሊባል ይገባል።በዚ መድረክ በእንግድነት የቀረቡ ሰዎች ለቦታው ማይሆኑ እና ፍጹም እነሱን ማይመጥን ተግባር ነው የፈጸሙት ።
#ሌላው አስደንጋጩ ደሞ አንዳንድ ሙስሊም ሰዎችም የፕሮግራሙ አዳማቂ እና አስተዋዋቂ ሆነው ከፊት መሰለፋቸው ነው። #ይህ ወደ ዝሙት ሚጣሩበት እና የማህበረሰብ እሴት ሚሸረሸርበት ድግስ ላይ መሳተፋችሁ ለምን ይሆን?እናንተ በምታደርጉት እያንዳንዱ #የሃራም ፣የወንጀል ተሳትፎ ሙስሊሞች ላይ አሉታዊ ተጽኖ እንደ ሚደርስ እንዴት ዘነጋችሁት?
#በመጨረሻም ሁሉንም የአካባቢያችን ተወላጆች እንደነዚ አይነት ከእኛ ማህበረሰብ መልካም እሴቶች የሚቃረኑ እና ህዝቡን ለውዳቂ ተግባራት ሚገፋፉ ነገሮች በጋራ እያወገዝን መልካም አራያነታችንን እንድናሳይ ለሁሉም የአካባቢው ተወላጅ ጥሪዬን አቀርባለሁ።
ነኝ ከጉራጌ(ጌታ)

26/11/2023
13/11/2023

ወደ ከፍታ በምታደርገው ጉዞ ያሉ መሰናክሎች ብዙ ናቸው።በብዙ ነገሮች ትፈተናለህ።በብዙ ምክንያቶች ወደ ኋላ እንድትል ትገደዳለህ።ከስራ ባልደረባ በሚገጥምህ ፣ቤተሰብህ ወይም ጓደኛህ ለማስደሰት ከምትወስደው እርምጃ እና አላስፈላጊ ይሉኝታ፣ያለህበትን ከባቢ አለመመቸት ትልቅ ሳንካ ናቸው።ዝንጉነት ሊፈጠር ይችላል ጊዜ ሳይፈጅ መመለሱ በጉዞህ ላይ አወንታዊ ተጽኖ ይፈጥራል።አንተ ጉዞህን ቀጥል ውድቀትህ በሌላ ሸፍነህ ወደ አሰብክበት ማማ በብዙ መንገዶች ለመድረስ ጣር አላህ ከ አንተ ጋር ነውና።ይሆኑኛል ብለህ ምትላቸው አካላት አልሆን ሲሉህ !ግንኙነትህን አጢነው።መርህ አለው ወይስ የለውም?ተስፋ አለው ወይስ የለውም?ያዋጣል ወይስ አያዋጣም?ከባድ ጥያቄ ቢሆንም መልስ ይፈልጋሉ።በተለይ ግን በዙሪያችን ቦታ የምንሰጣቸው ሰዎች አንዳንዴ እንደ ተነቀለ stove ቀዝቀዝ ይላሉ ።ልትታገሳቸው ትችላለህ እየበዛ ሲሄድ እየመረረ ይመጣል።ይሄን ጊዜ መርህ አልባው የጋራ ጉዞ እየመነመነ ይመጣል።ምናልባትም ንቀት ይመስላል።የነሱን በጎን አድርገህ አንተ በርታ በል።አዳዲስ የስኬት በሮች ማንኳኳትህ ቀጥል፣ያሉህን ሰዎች ብታጣ/ባታገኝ የተሻለ ሰው ፍጠር።ጊዜያቸው ያልደረሱ እቅዶች ማሰብን ቆም አድርገህ ወቅቱን የዋጀ ስራ ላይ ተሰማራ።አንድ እውነት አትርሳ ያንተ ስኬቴና ውድቀት ሚወሰነው በአላህ እንጂ በማንም አይደለም።ያለ አንተ መኖር አልችልም የሚሉ ሰዎች ሞኞች ናቸው።ያለ አንተ መኖር፣ማደግ፣መስራት ይችላሉ።አንተ ብትቀር ከሌሎች ጋርም ይኖራሉ።
IbnuAbdlber Alhabeshiy
page:https://www.facebook.com/profile.php?id=100063693378708
Facebook account :https://www.facebook.com/abdl.hafiz.79
Tj,account:
Umma,life:https://ummalife.com/IbnuAbdlber

ስለ እውነት መቆም እውነትን ያጸናል ።ራስን ለትልቅ አላማ ማጨት ትልቅ ያደርጋል።
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏

16/06/2023

በዓለም በድህነቷ የምትታወቅ ሀገር ይዘን፣ድሃ ጠልተን እንዴት ይሆናል ?!
ኢኮኖሚያችን አደጋ ላይ ወድቆ መንግስት አዲስ ሰራተኛ የምቀጥርበት በጀት የለኝም በሚልበት ሀገር ህገ -ወጥ ድሃ የሚል ጨካኝ አመራሮች እጅግ ያሳዝናሉ ።

ከድሃዎች ሁሉ ድሃ ማለት ሰብዓዊነት ያልፈጠረባቸው የአእምሮ ድሃዎች ናቸው

አስርቱ የዙልሂጃ ቀናት ወርቃማ ቀናቶችጌታችን አላህ በራሱ ካላቃቸው እና ካከበራቸው አራት ወራቶች መካከል የዙልሒጃ ወር አንዱ ነው:: ከቀናቶች ሁሉ ብልጫ ያላቸው አስር ቀናቶችም ያሉት በዚሁ...
16/06/2023

አስርቱ የዙልሂጃ ቀናት ወርቃማ ቀናቶች

ጌታችን አላህ በራሱ ካላቃቸው እና ካከበራቸው አራት ወራቶች መካከል የዙልሒጃ ወር አንዱ ነው:: ከቀናቶች ሁሉ ብልጫ ያላቸው አስር ቀናቶችም ያሉት በዚሁ በተከበረው የዙልሒጃ ወር ውስጥ ነው::

እነዚህ አስር ውድ ቀናቶችም ጌታችን አላህ(ሱወ) ምሎባቸዋል::

የአላህ መልዕክተኛ (الله عليه وسلم) እንዲህ ብለዋል፤

ጃቢር ኢብኑ ዓብዲላህ ባስተላለፉት ሀዲስ የአላህ መልዕክተኛ الله عليه وسلم እንዲህ ብለዋል «ከዱንያ ቀናት ሁሉ ብልጫ ያላቸው፤ አስርቱ የዙልሂጃ ቀናት ናቸው » አልበዛር እና አልሐይሰሚይ ዘግበዉታል አልባኒም ሰሂህ ብለዉታል (ሰሂሁል ጃሚዕ 1133)

በነዚህ ውድ ቀናቶች የሚሰሩ መልካም ስራዎች አላህ ዘንድ እጅግ ተወዳጅ እና በላጭ ናቸው::

ከኢብኑ ዓባስ በተዘገበ ሀዲስ የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል፤ «በነዚህ አስር ቀናቶች ውስጥ ከሚፈጸም መልካም ስራዎች በበለጠ መልካም ስራዎች አላህ ዘንድ የተወደዱ የሚሆኑባቸው ቀናት የሉም፤ “በአላህ መንገድ ላይ የሚደረግ ጂሀድም ጭምር?” ተባሉ። እርሳቸውም፤ “ራሱንና ንብረቱን ይዞ ወጥቶ ምንም ያልተመለሰለት ሰው ሲቀር ጂሀድም ከዚህ አይበልጥም” አሉ።» ቡኻሪ ዘግበውታል

በመሆኑም እነዚህን ውድ ቀናቶች በተገቢው መልኩ ልንጠቀምባቸው ይገባል:: በነዚህ ውድ ቀናቶች ከሚወደዱ ኢባዳዎች መካከል:-


1. ጾም ከስራዎች ሁሉ በላጭ ነውና በእነዚህ ቀናት መጾም እጅግ የተወደደ ነው። የአላህ መልዕክተኛ ዘጠኙን የዙልሂጃ ቀናት ይጾሙ እንደነበር ተዘግቧል። (አስረኛው ቀን ግን ዒድ ስለሆነ አይጾምም)

2. ዚክሮችን ማብዛት ቁርዓን መቅራት ፤ አላህን ማመስገን (አልሀምዱሊላህ) ፣ ተክቢር፣ ተስቢህ(ሱብሀነላህ) እና ተህሊል (ላ ኢላሀ ኢለላህ)፤ ኢባዳዉን ለማስታወስና የአላህን ስም ከፍ ለማድረግ በተለያዩ አጋጣሚዎች ድምጽን ከፍ አድርጎ እነዚህን ዚክሮች ማድረግ ይወደዳል።

ዓብዱላህ ኢብኑ ዑመር ባስተላለፉት ሀዲስ ነብዩه እንዲህ ብለዋል፤«ከእነዚህ አስር ቀናት በበለጠ አላህ ዘንድ ታላቅ የሆኑና መልካም ስራ እጅግ የተወደደባቸው ቀናት የሉም፤ ስለዚህ ተህሊል ተክቢር እና ተህሚድ አብዙ» አል ኢማም አህመድ ዘግበውታል

3. ሐጅ ማድረግ በነዚህ ቀናት ውስጥ ከሚፈጸሙ መልካም ስራዎች መካከል ሐጅ ማድረግ ይገኝበታል፤ በነዚህ አስር ቀናት አቅሙ ለቻለ ሰው የሐጅ ዒባዳ ላይ ተገኝቶ በተገቢው መልኩ ከፈጸመው በአላህ ፍቃድ ከተከታዩ የአላህ መልዕክተኛه ብስራት ድርሻ ይኖረዋል፤

ከአቡ ሁረይራ በተላለፈ ሀዲስ የአላህ መልዕክተኛه እንዲህ ብለዋል፤ «ከወንጀል የራቀና ተቀባይነት ያለው ሐጅ (አል-ሐጅ አል-መብሩር) ምንዳው ጀነት እንጂ ሌላ አይደለም፡፡» ቡኻሪና ሙስሊም ተስማምተውበታል

4. ኡድሂያ- በነዚህ አስር ቀናት ከተወደዱ ተግባሮች መካከል ኡድሂያን በማረድ ወደአላህ መቃረብ ነው።
ኡድሂያን ለማረድ ያቀደ ሰው የዙልሂጃ ወር ከገባ ጥፍሩንና ጸጉሩን መቁረጥ የለበትም::

5. የፈርድ ሰላቶችንን ጠብቆ በጀምዓ መስገድ፣ የሱና እና የለሊት ሰላቶችን ማብዛት

6. ለወላጆች መልካም መዋል

7. ለተቸገሩ ወገኖች ሰደቃ ማብዛት

8. የታሰረን ወይም የታመመን ሰው መጠየቅ፣

9. ዝምድናን መቀጠል፣

10. ለራሳችንም ለሀገራችንም ለኡማውም በብዛት ዱዓን ማብዛት ያስፈልጋል።

11. ተውበት ማድረግ

በነዚህ ውድ ቀናቶች ከተጠቀሱት ውጪ ያሉትንም መልካም ስራዎች በሙሉ መስራት ምንዳው ላቅ ያለ ነው::

እነዚህን ወርቃማ ቀናቶች በኢባዳ ከሚያሳልፉት አላህ ያድርገን
©️

03/06/2023

30/05/2023

We’ve detected that JavaScript is disabled in this browser. Please enable JavaScript or switch to a supported browser to continue using twitter.com. You can see a list of supported browsers in our Help Center.

27/05/2023
Aselamualeykum werahmetulahi weberekatu 🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏وَعَدَ اللَّهُ الَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ ۙ لَهُم مَّغْ...
26/05/2023

Aselamualeykum werahmetulahi weberekatu
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏

وَعَدَ اللَّهُ الَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ ۙ لَهُم مَّغْفِرَةٌ وَأَجْرٌ عَظِيمٌ

እነዚያንም ያመኑትንና በጎ ሥራዎችን የሠሩትን አላህ (ገነትን) ተስፋ አደረገላቸው፡፡ ለእነርሱ ምሕረትና ታላቅ ምንዳ አላቸው፡፡
I wish happy working day!!
Jumua mubarek🍒🍒🍒

Address

Addis Ababa

Telephone

+251939166068

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ibnu Abdlber alhabeshiy posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Ibnu Abdlber alhabeshiy:

Videos

Share