06/02/2024
አቢሲንያ ባንክ Bank of Abyssinia የተሰጠዉን ጊዜ በመጠቀም ይቅርታ ጠይቋል
ከአቢ ሲንያ ባንክ የስራ ኃላፊዎች ጋር በተደረገ ንግግ ር መሰረት የባንክ ሰራተኛዉ ላይ የዲሲፒሊን እርምጃ ተወስዷል።
••••••••••••••••••••••••••••••
Mujib Amino
የአቢ ሲንያ ባንክ አለምገና ቅርንጫፍ አከባቢ የተፈጸመዉ ኀይማኖታዊ ትንኮሳና ንቀት የተሞላበት ድርጊት ከባንኩ አሰራርና አላማ እንዲሁም ምንም አይነት መብትና ግዴታ ባልኖረበት ተጨባጭ ሁናቴ የተከናወነ የነዉር ድርጊትና ጥላቻ ሕዝባችንን ያስቆጠ በመሆኑ የአቢ ሲንያ ባንክ የስራ ኃላፊዎች ይቅርታ እንዲጠይቁና ድርጊቱን የፈጸመዉ ሰራተኛም እምርጃ እንዲወሰድ መጠየቃችን ይታወሳል።
ባለፉት ቀናት ከባንኩ የስራ ኃላፊዎችና ከሚምለከታቸዉ አካላት ጋር ንግግር ካደረግን ቡኃላ በዛሬው እለት የአቢሲንያ ባንክ ሕዝበ ሙስሊሙን ከፍ ያለ ይቅርታ ጠይቋል።
በድርጊቱ የተሳተፈዉን የባንኩ ስራተኛ ላይም የዲሲፒሊን እርምጃ መዉሰዱን በኦፊሲዬላዊ ገጹ ላይ ገልጿል።
የአቢ ሲንያ ባንክ የስራ ኃላፊዎች ጉዳዩን እልባት ለመስጠትና ከሕዝበ ሙስሊሙ ጋር ግንኙንታቸዉን ለማጠናከር የሄዱብትን መንገድ እያደነቀ፣ በሌሎች ጊዜያት መሰል ድርጊቶች እንዳይፈጸሙ ጥንቃቄ እንዲያደርግ እናሳስባለን። እናመሰግናለን።