19/04/2024
ክርስቶስ ጣልቃ ገብቶ ቅጣቱን በራሱ ላይ ወሰደና፣
በኀጢአተኞች ላይ ይደርስ የነበረውን ፍርድ ተሸከመ፡፡
በገዛ ደሙ የእግዚአብሔር ጠላቶች እንዲሆኑ ያደረጓቸውን
ኀጢአቶች ደመሰሰ፡፡ በዚህም አብን አስደሰተ.. የአብን
ፍቅርና መለኮታዊ ሞገስ ለማግኘት የምንመለከተው ክርስቶስን ብቻ ነው.. እርሱ ኅሊናችንን ከኩነኔ ነጻ አድርጓልና “የሰላም ንጉሥ' (ኢሳይያስ 9፥6)፣ እንዲሁም
“ሰላማችን" (ኤፌሶን 9፥6) ተብሎ ተጠርቷል።
ይህን መንገዱን የምንጠይቅ ከሆነ ፣ እግዚአብሔርን ደስ
በሚያሠኘው መሥዋዕት በኩል መቅረብ አለብን። እግዚአብሔር ፣ ቁጣውን ለማብረድ ኢየሱስ ባቀረበው
አንድያ የስርየት መሥዋዕት ብቻ ደስ አይሠኝም ብሎ
የሚያምን ሰው ፣ አሁንም ከእግዚአብሔር ቁጣ በታች
ነው፡፡ በዐጭሩ፣ ለራሳችን ሰላምን መፈለግ ያለብን በቤዛችን በክርስቶስ ሥቃይ ወስጥ ብቻ ነው፡፡
ጆን ካልቪን
(Institutes of the Christian Religion 2.16.2)