Ethiopian Sport

Ethiopian Sport Ethiopian sport is sports news website which presents premiere leagues, athletics and other sports

Ethiopian sport is sports news website which presents premiere leagues, athletics and other sports in Amharic.

26/01/2024
ትንቀሳቃሹ ላይብረሪ በስተመጨረሻም አረፈ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ላይ በተጫዋችነት፣ ጋዜጠኝነት እና በመፅሐፍ ደራሲነት ለረጅም ዓመታት እጅግ ታላቅ ግልጋሎት ያበረከተው አንጋፋው ጋዜጠኛ ገነነ ...
23/01/2024

ትንቀሳቃሹ ላይብረሪ በስተመጨረሻም አረፈ

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ላይ በተጫዋችነት፣ ጋዜጠኝነት እና በመፅሐፍ ደራሲነት ለረጅም ዓመታት እጅግ ታላቅ ግልጋሎት ያበረከተው አንጋፋው ጋዜጠኛ ገነነ መኩርያ (ሊብሮ) ህልፈተ ህይወት ተሰምቷል።

ከተጫዋችነት ከተገለለ በኋላ ከ30 ዓመታት በላይ በስፖርት ጋዜጠኝነት ያሳለፈው ታሪክ አዋቂው ገነነ መኩርያ በጋዜጣ እና የኤሌክትሮኒክስ ሚድያዎች ላይ የሰራ ሲሆን በርካታ መፅሐፍትንም ለንባብ አብቅቷል።

ሊቨርፑል ከዩናይትድ ነጥብ ተጋርተዋል በእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ተጠባቂው መርሐ ግብር ሊቨርፑል ከማንችስተር ዩናይትድ  ያደረጉት ጨዋታ ያለምንም ጎል ተጠናቋል።ማንችስተር ዩናይትድ ያለፉትን ሶ...
17/12/2023

ሊቨርፑል ከዩናይትድ ነጥብ ተጋርተዋል

በእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ተጠባቂው መርሐ ግብር ሊቨርፑል ከማንችስተር ዩናይትድ ያደረጉት ጨዋታ ያለምንም ጎል ተጠናቋል።

ማንችስተር ዩናይትድ ያለፉትን ሶስት ጨዋታዎች ማሸነፍ አልቻለም።

ውጤቱን ተከትሎ ሊቨርፑሎች በ 38 ነጥብ ሁለተኛ ሲሆኑ ማንችስተር ዩናይትድ በ 28 ነጥብ 7ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል ።

የሸገር ደርቢ ተራዝሟል የቤቲንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አወዳዳሪ አካል ባወጣው መረጃ  በነገው ዕለት በኢትዮጵያ ቡና እና ቅዱስ ጊዮርጊስ መካከል በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩንቨርሲቲ ስታ...
08/12/2023

የሸገር ደርቢ ተራዝሟል

የቤቲንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አወዳዳሪ አካል ባወጣው መረጃ
በነገው ዕለት በኢትዮጵያ ቡና እና ቅዱስ ጊዮርጊስ መካከል በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩንቨርሲቲ ስታዲየም ከቀኑ በዘጠኝ ሰአት የሚደረገው ተጠባቂው የሸገር ደርቢ ጨዋታ ላልተወሰነ ጊዜ ተራዘሟል ሲል አሳውቋል።

በእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የአስራ አምስተኛ ሳምንት መርሐግብር ማንችስተር ዩናይትድ ቼልሲን 2ለ1 እንዲሁም አስቶን ቪላ ማንችስተር ሲቲን 1ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።👉 ማንቸስተር ዩናይ...
06/12/2023

በእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የአስራ አምስተኛ ሳምንት መርሐግብር ማንችስተር ዩናይትድ ቼልሲን 2ለ1 እንዲሁም አስቶን ቪላ ማንችስተር ሲቲን 1ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

👉 ማንቸስተር ዩናይትድ 2 - 1 ቼልሲ
⚽️ ማክቶሚናይ 19' 69' ⚽️ ፓልመር 45'

👉 አስቶን ቪላ 1 - 0 ማንቸስተር ሲቲ
⚽️ ቤይሊ 74'

አርሰናል ጣፋጭ ድል አስመዘገበአሁን በተጠናቀቀ የ15ተኛው ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ አርሰናል ሉተን ታውንን  4ለ3 በማሸነፍ  መሪነቱን አጠናክሯል።                 ሉ...
05/12/2023

አርሰናል ጣፋጭ ድል አስመዘገበ
አሁን በተጠናቀቀ የ15ተኛው ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ አርሰናል ሉተን ታውንን 4ለ3 በማሸነፍ መሪነቱን አጠናክሯል።

ሉተን ታውን 3 - 4 አርሰናል

25' ⚽ ኦሾ 2 ⚽ ማርቲኔሊ
49' ⚽ አዴባዮ 45'⚽ ጄሱስ
57' ⚽ ባርክሌይ 60⚽ ሀቨርትዝ
90+5'⚽ ራይስ

አትሌት ሲሳይ ለማ ሪከርድ በመስበር አሸነፈ በስፔን ቫሌንሽያ ከተማ በተካሄደው ተጠባቂው የቫሌንሽያ የወንዶች ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያዊው አትሌት ሲሳይ ለማ በአሸናፊነት ማጠናቀቅ ችሏል።ኢትዮ...
03/12/2023

አትሌት ሲሳይ ለማ ሪከርድ በመስበር አሸነፈ

በስፔን ቫሌንሽያ ከተማ በተካሄደው ተጠባቂው የቫሌንሽያ የወንዶች ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያዊው አትሌት ሲሳይ ለማ በአሸናፊነት ማጠናቀቅ ችሏል።

ኢትዮጵያዊው አትሌት ሲሳይ ለማ 2:01:47 በመግባት የቦታውን ሪከርድ በማሻሻል ጭምር ውድድሩን በበላይነት ጨርሷል።

ኬንያዊው አትሌት አሌክሳንደር ሙቲሶ በ2:03:11 ሁለተኛ ደረጃን ይዞ ሲያጠናቅቅ ኢትዮጵያዊው አትሌት ዳዊት ወልዴ 2:03:48 በመግባት ሶስተኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቅ ችሏል።

በውድድሩ የተካፈለው ሌላኛው ኢትዮጵያዊ አትሌት ቀነኒሳ በቀለ 2:04:19 በመግባት አራተኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቅ ችሏል።

ዮናስ አበራ (ኦራ)

መድፈኞቹ የሊጉን መሪነት አጠናክረዋል በአስራ አራተኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ መርሐ ግብር አርሰናል ከዎልቭስ ጋር ያደረጉት ጨዋታ 2 ለ 1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ መሪነታቸውን አጠናክ...
03/12/2023

መድፈኞቹ የሊጉን መሪነት አጠናክረዋል

በአስራ አራተኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ መርሐ ግብር አርሰናል ከዎልቭስ ጋር ያደረጉት ጨዋታ 2 ለ 1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ መሪነታቸውን አጠናክረዋል።

የአርሰናልን የማሸነፊያ ግቦች ቡካዩ ሳካ እና ማርቲን ኦዴጋርድ ከመረብ ሲያሳርፉ ዎልቭስን ከሽንፈት ያልታደገውን ግብ ኩንሀ አስቆጥሯል።

አርሰናል ማሸነፉን ተከትሎ በጊዜያዊነት ሊጉን በአራት ነጥቦች ልዩነት መምራት ጀምሯል።

ዮናስ አበራ (ኦራ)

ማንችስተር ዩናይትድ ሽንፈት አስተናግዷል በአስራ አራተኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ መርሐ ግብር ኒውካስትል ዩናይትድ ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር ያደረጉት ጨዋታ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት ተ...
03/12/2023

ማንችስተር ዩናይትድ ሽንፈት አስተናግዷል

በአስራ አራተኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ መርሐ ግብር ኒውካስትል ዩናይትድ ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር ያደረጉት ጨዋታ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት ተጠናቋል።

የኒውካስትልን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ አንቶኒ ጎርደን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

ዮናስ አበራ(ኦራ)

  ከታች ያለውን የቲክቶክ ቪዲዩ በመንካት አርሰናል ከ ማን ሲቲ የፊታችን እሁድ የሚያደርጉትን ጨዋታ ውጤት ገምተው ይሸለሙ ። መገመት የምትችሉት ከታች ባያያዝኩላችሁ የቲክቶክ ቪዲዮ በኮሜንት...
05/10/2023



ከታች ያለውን የቲክቶክ ቪዲዩ በመንካት አርሰናል ከ ማን ሲቲ የፊታችን እሁድ የሚያደርጉትን ጨዋታ ውጤት ገምተው ይሸለሙ ።

መገመት የምትችሉት ከታች ባያያዝኩላችሁ የቲክቶክ ቪዲዮ በኮሜንት መስጫው ላይ ነው ።

65 likes, 45 comments. “ይገምቱ ና ይሸለሙ”

   #አርሰናል ከ  ከታች ያለውን የቲክቶክ ቪዲዩ በመንካት አርሰናል ከ ማን ሲቲ የፊታችን እሁድ የሚያደርጉትን ጨዋታ ውጤት ገምተው ይሸለሙ ።መገመት የምትችሉት ከታች ባያያዝኩላችሁ የቲክቶክ...
05/10/2023



#አርሰናል ከ

ከታች ያለውን የቲክቶክ ቪዲዩ በመንካት አርሰናል ከ ማን ሲቲ የፊታችን እሁድ የሚያደርጉትን ጨዋታ ውጤት ገምተው ይሸለሙ ።

መገመት የምትችሉት ከታች ባያያዝኩላችሁ የቲክቶክ ቪዲዮ በኮሜንት መስጫው ላይ ብቻቸ ነው ።

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

68 likes, 47 comments. “ይገምቱ ና ይሸለሙ”

የብራይተን ነዋሪዎች በኢትዮጵያዊው አትሌት ሀይሌ ስም ቡና ማቅረብ ጀምሩበብራይተን ነዋሪነታቸውን ያደረጉ እንግሊዛዊያን በኢትዮጵያዊው ጀግናው አትሌት ሀይሌ ገብረስላሴ ስም " ሀይሌ ኮፊ " የ...
28/09/2023

የብራይተን ነዋሪዎች በኢትዮጵያዊው አትሌት ሀይሌ ስም ቡና ማቅረብ ጀምሩ

በብራይተን ነዋሪነታቸውን ያደረጉ እንግሊዛዊያን በኢትዮጵያዊው ጀግናው አትሌት ሀይሌ ገብረስላሴ ስም " ሀይሌ ኮፊ " የተሰኘ ቡና ለሯጮች እና ለአትሌቶች መሸጥ መጀመራቸው ተገልጿል።

ለሽያጭ የሚቀረበው " ሀይሌ ኮፊ " ምርት " Premium Ethiopian Coffee " የሚል መገለጫ እንደሚኖረውም ሲታወቅ ከትላንትናው ዕለት ጀምሮ ለተጠቃሚዎች ለሽያጭ መቅረቡ ተዘግቧል።

ከ6ተኛ ሳምንት ጨዋታዎች ከተጠናቀቁ ቡሃላ የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ የደረጃ ሰንጠረዥ ለውጥ አስተናግዷል1. ማን ሲቲ 18 ነጥብ2. ሊቨርፑል 16 ነጥብ3. ብራይተን 15 ነጥብ4. ቶተንሀም 1...
25/09/2023

ከ6ተኛ ሳምንት ጨዋታዎች ከተጠናቀቁ ቡሃላ የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ የደረጃ ሰንጠረዥ ለውጥ አስተናግዷል
1. ማን ሲቲ 18 ነጥብ
2. ሊቨርፑል 16 ነጥብ
3. ብራይተን 15 ነጥብ
4. ቶተንሀም 14 ነጥብ
5. አርሰናል 14 ነጥብ
6. አስቶን ቪላ 12 ነጥብ
7. ዌስትሃም 10 ነጥብ
8. ኒውካስትል 9 ነጥብ
9. ማን ዩናይትድ 9 ነጥብ
10. ክሪስታል ፓላስ 8 ነጥብ
11. ፉልሃም 8 ነጥብ
12. ኖቲንግሃም 7 ነጥብ
13. ብሬንትፎርድ 6 ነጥብ
14. ቼልሲ 5 ነጥብ
15. ኤቨርተን 4 ነጥብ
16. ወልቭስ 4 ነጥብ
17. በርንማውዝ 3 ነጥብ
18. ሉተን ታውን 1 ነጥብ
19. በርንሌይ 1 ነጥብ
20. ሼፊልድ 1 ነጥብ

ፋንታሲ ለምትጫወቱ የተከፈተ የቲክቶክ ቻናል 👇👇👇
31/08/2023

ፋንታሲ ለምትጫወቱ የተከፈተ የቲክቶክ ቻናል 👇👇👇

Check out አናንያ ፈለቀ FFM's video.

 ኢትዮጵያን ለመወከል የሚደረገው የአትሌቶች ምርጫ የአትሌቶችን ወቅታዊ ብቃት፣ ውጤት እና በዋናነት ደግሞ ኢትዮጵያን ማዕከል ያደረገ መሆኑን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ረዳት ...
24/08/2023



ኢትዮጵያን ለመወከል የሚደረገው የአትሌቶች ምርጫ የአትሌቶችን ወቅታዊ ብቃት፣ ውጤት እና በዋናነት ደግሞ ኢትዮጵያን ማዕከል ያደረገ መሆኑን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ አስታወቀች ።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ አያይዛም " ጥላሁን ስላዘንክ ፤ ስለተበሳጨህ በጣም ይቅርታ የምለው በጣም ስላለቀሰ ስላዘነ ነው እንጂ መብቱን አልነካንም ፤ እሱን አስወጥተን ማንንም አላስገባብም። ሁሉም ባላቸው ሰዓት እና በብቃታቸው ነው የገቡት " ስትል ተናግራለች ።

ደራርቱ እንደ አመራር እና እንደ እናት በተፈጠረው ነገር አዝኛለሁ ፤ ይቅርታም እላለሁ ስትል ተናግራለች።

" የአትሌቱን መብት ነክተን አላስቀረነውም 4ኛ በመሆኑ ብቻ ነው ያስቀረነው " ስትልም አክላለች።

ውሳኔዎች ሲተላለፉ በኮሚቴ ተነጋግረን ለሀገር የሚበጀውን ነው ያለችው ደራርቱ እኔ ብቻዬን ማንም የማስገባትም ሆነ የማስወጣት መብት የለኝም ብላለች።

አትሌት ጥላሁን ኃይሌ በ5000 ሜትር ውድድር ተመርጦ ወደ ሀንጋሪ ከተጓዘ በኃላ ፤ ትላንት በውድድሩ ላይ እንደማይሳተፍ እና በሱ ምትክ በሪሁ አረጋዊ መካተቱን ሊያውቅ ችሏል።

በዚህም እጅግ ሀዘን ውስጥ የገባ ሲሆን " የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዜዳንት ደራርቱ የሰራችብኝን ግፍ የኢትዮጵያ ህዝብ ይፍረደኝ " ብሏል።

" የሀገሬን ባንዲራ ከፍ ለማድረግ ብዙ ውጣ ውረድ ስለፋ ስደክም ቆይቼ የተሻለ ብቃት ኖሮኝ ፌዴሬሽኑ በሰራብኝ ግፍ ተቀንሻለሁ " ያለ ሲሆን " አሰልጣኝ ሁሴን ሽቦ ነው ፌዴሬሽኑን እየመራ ያለው ማለት ይቻላል ልጄ ይሮጥልኛል ብሎ በሪሁ አራተኛ ወጥቶ ገብቶ እንዲወዳደር ተደርጓል " ሲል ቅሬታው አቅርቧል።

" ቀን እና ማታ በአጥንት እስክቀር ድረስ የለፋሁበት እንጀራዬን እንዲህ መደረጉን ህዝቡ ይወቅልኝ ፤ ፌዴሬሽኑ ውስጥ የሚሰራውን ግፍ ህዝብ ይወቅልኝ " ብሏል።

" ፌዴሬሽኑን የሚመሩት አትሌት የነበሩ ናቸው እነሱ ሲመጡት ውስጥ ያለው አሰራር ይሻሻላል ቢባልም ጭራሽ በነሱ ባሰ፤ ስም አለም ሚዲያውን እንቆጣጠራለን ታዋቂ ነን ፤ ህዝቡን ማሳመን እንችላለን ብለው ይሄን ሁሉ ግፍ የሚያደርጉት እነሱ ናቸው " ሲል አክሏል።

ይህን የአትሌቱን ቅሬታ በተመለከተ ዛሬ መግለጫ የሰጡት የፌዴሬሽን አመራሮች ምርጫው ብቃትን መሰረት ያደረገ ሀገርንም ይጠቅማል በሚል እንጂ ማንንም አስወጥቶ የማስገባት ጉዳይ አይደለም፤ በሪሁ የተሻለ ሰዓት ስላለው ብቃቱም ጥሩ ስለሆነ ነው የገባው ብለዋል።

አትሌት ጥላሁን ኃይሌ የማይወዳደር ከሆነ ለምን እንዲሄድ እንደተደረገ ሲገልፁም ፤ ምናልባት በሪሁ የሆነ ነገር ቢሆን የሱ መኖር አስፈላጊ ነው ፤ ተጠባባቂ አትሌት ሁኔም ይኖራል ይህ ድሮም የነበረ አሰራር ነው ሲሉ አስረድተዋል።

Tikvah sport

አትሌት ሰለሞን ባረጋ ሲያነባ ታይቷል 😥አትሌት ሰለሞን ባረጋ በአለም ሻምፒዮናው 3ኛ ወጥቶ የነሐስ ሜዳሊያ በማግኘቱ ከውድድሩ በኋላ በእምባ ታጅቦ ሲያለቅስ ታይቷል።ቪዲዮውን ተመልከቱ👇👇👇👇👇...
23/08/2023

አትሌት ሰለሞን ባረጋ ሲያነባ ታይቷል 😥

አትሌት ሰለሞን ባረጋ በአለም ሻምፒዮናው 3ኛ ወጥቶ የነሐስ ሜዳሊያ በማግኘቱ ከውድድሩ በኋላ በእምባ ታጅቦ ሲያለቅስ ታይቷል።

ቪዲዮውን ተመልከቱ
👇👇👇👇👇👇

https://youtube.com/shorts/T2kRlWMrFW0?si=mRN4hcnjZ-Ag_8x

😰በሀገራችን በሚሊዮን የሚከፈልባቸው ት/ቤቶች እንዳሉ ያውቃሉ ????🤑በርካታ የአርቲስቶት እና የባለሀብት ልጆች የሚማሩባቸው ውድ እና አለም አቀፍ ትምህርት ቤቶች በአዲስ አበባ በላሚቷ የዩት...
22/08/2023

😰በሀገራችን በሚሊዮን የሚከፈልባቸው ት/ቤቶች እንዳሉ ያውቃሉ ????

🤑በርካታ የአርቲስቶት እና የባለሀብት ልጆች የሚማሩባቸው ውድ እና አለም አቀፍ ትምህርት ቤቶች በአዲስ አበባ በላሚቷ የዩትዩብ ቻናል ያገኙታል ።

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

/mariyam ...

ሻኬሪ ሪቻልድሰን የአለማችን ፈጣኗ ሴት  ትናንት ምሽት በተደረገ በሴቶች የ100 ሜትር ፍፃሜ ውድድር አሜሪካዊቷ አትሌት ሪቻልድሰን 10.65 በመግባት የአለም ሻምፒዮና መሆን ችላለች ።    ...
22/08/2023

ሻኬሪ ሪቻልድሰን የአለማችን ፈጣኗ ሴት

ትናንት ምሽት በተደረገ በሴቶች የ100 ሜትር ፍፃሜ ውድድር አሜሪካዊቷ አትሌት ሪቻልድሰን 10.65 በመግባት የአለም ሻምፒዮና መሆን ችላለች ።

#አትሌቲክስ

ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ለወርቅ ሜዳሊያ ይፋለማሉ       በሀንጋሪ ቡዳፔስት እየተደረገ ያለው 19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬም ሲቀጥል ኢትዮጵያዊያን  አትሌቶቻችም ተጠባቂ የፍፃሜ ...
22/08/2023

ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ለወርቅ ሜዳሊያ ይፋለማሉ



በሀንጋሪ ቡዳፔስት እየተደረገ ያለው 19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬም ሲቀጥል ኢትዮጵያዊያን አትሌቶቻችም ተጠባቂ የፍፃሜ ውድድራቸውን ያደርጋሉ።

ምሽት 4:30 ላይ የ1500ሜ ሴቶች ፍፃሜ ሲደረግ
አትሌት ድርቤ ወልተጂ እና ብርቄ ሀየሎም በርቀቱ የሚሳተፉ ይሆናል ።

በቡዳፔስት የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የመጀመሪያ ቀን ውሎ ከኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ጋር ከፍተኛ ፉክክር ያደረገችው በትውልድ ኢትዮጵያዊ በዜግነት ለኔዘርላንዳዊቷ ሲፋን ሀሰን ምሽት 4:30 ላይ በሚደረገው የሴቶች 1500 ፍፃሜ ተሳታፊ ነች ።

ምሽት 4:42 የሚጠበቀው የወንዶች የ 3000ሜ መሰናክል ፍፃሜ ላይ ኢትዮጵያዊያኑ አትሌትቶች ጌትነት ዋለ እና ለሜቻ ግርማ የሚሳተፋ ሲሆን አትሌት ለሜቻ ግርማ በኦሪገን የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በዚህ ርቀን የብር ሜዳሊያ ማምጣቱ ይታወሳል ።

ድል ለሀገራችን ኢትዮጵያ

አሁን በተደረገ የወንዶች 10ሺ ሜትር ፍፃሜ ኢትዮጵያዊው ሰለሞን ባረጋ 3ኛ ሆኖ በማጠናቀቅ ለሀገሩ የነሃስ ሜዳልያን አስገኝቷል ። ሌላኛው ኢትዮጵያዊ አትሌት በረሁ አረጋዊ ውድድሩን ሰለሞንን...
20/08/2023

አሁን በተደረገ የወንዶች 10ሺ ሜትር ፍፃሜ ኢትዮጵያዊው ሰለሞን ባረጋ 3ኛ ሆኖ በማጠናቀቅ ለሀገሩ የነሃስ ሜዳልያን አስገኝቷል ።

ሌላኛው ኢትዮጵያዊ አትሌት በረሁ አረጋዊ ውድድሩን ሰለሞንንበመከተል አራተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል ።

ውድድሩን ኡጋንዳዊ አትሌት ጆሹዋ ቺፕቴጌ በአንደኝነት አጠናቋል ።

እንኳን ደስ አለን

ዛሬስ የትናንቱ ድል በወንዶችም ይደገም ይሆን ????በ10ሺ ሜትር ወንዶች ፍፃሜ ዛሬም ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች  ሁለተኛውን ወርቅ ሜዳሊያ ለማምጣት ይፉለማሉ ። በሀንጋሪ  ቡዳፔስት እየተካሄደ...
20/08/2023

ዛሬስ የትናንቱ ድል በወንዶችም ይደገም ይሆን ????

በ10ሺ ሜትር ወንዶች ፍፃሜ ዛሬም ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ሁለተኛውን ወርቅ ሜዳሊያ ለማምጣት ይፉለማሉ ።

በሀንጋሪ ቡዳፔስት እየተካሄደ የሚገኘው የ19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የሁለኛ ቀን ውሎ ዛሬም ሲቀጥል የ10ሺ ሜትር የወንዶች ፍፃሜ ከወዲሁ ልክ እንደ ትናንቱ የሴቶች 10ሺ ከወዲሁ ቀልብ ስቧል ።

እሁድ ነሐሴ 14/2015 ዓ.ም

👉 የወንዶች 10,000 ሜትር 🚨የፍፃሜ ውድድር ከምሽቱ 1:25 ሲካሄድ ሀገራቸውን ኢትዮጵያን ወክለው ከሚወዳደሩ አትሌቶች ወስጥ

በሪሁ አረጋዊ
ሰለሞን ባረጋ
ይስማው ድሉ

👉 ቀን 12፡05 የሚደረገው የሴቶች 1500 ሜትር ግ/ፍፃሜ

ኢትዮጵያን የሚወክሉ አትሌቶች

ሂሩት መሸሻ
ብርቄ ኃየሎም
ድርቤ ወልተጂ

👇👇👇👇👇👇👇👇

https://youtube.com/shorts/N9yGdr6MYGI?si=G75HNo8JL9Um8L9R

በዜግነት ኔዘርላንዳዊቷ ትውልደ ኢትዮጵያዊዋ አትሌት ሲፈን ሀሰን ከቢቢሲ ጋር ባደረገችው ቆይታ በውድድሩ በጉዳፍ ፀጋይ ተገፍትራ እንደወደቀች ተናግራለች ። ቪዲዮውን በድጋሚ በደንብ ማየት ከፈ...
20/08/2023

በዜግነት ኔዘርላንዳዊቷ ትውልደ ኢትዮጵያዊዋ አትሌት ሲፈን ሀሰን ከቢቢሲ ጋር ባደረገችው ቆይታ በውድድሩ በጉዳፍ ፀጋይ ተገፍትራ እንደወደቀች ተናግራለች ።

ቪዲዮውን በድጋሚ በደንብ ማየት ከፈለጉ

👇👇👇👇👇👇👇👇

https://youtu.be/N9yGdr6MYGI?si=u99zToBE_okqN2LP

የነጉዳፍ እና የሲፋን ሀሰንን ታሪክ የማይረሳውን ትንቅንቅ ለመመልከት ከቻች ያለውን ሊንክ በመጫኝ ይመልከቱ👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
20/08/2023

የነጉዳፍ እና የሲፋን ሀሰንን ታሪክ የማይረሳውን ትንቅንቅ ለመመልከት ከቻች ያለውን ሊንክ በመጫኝ ይመልከቱ

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

የዛሬው ልብ አንጠልጣይ ድራማ ይደገም ይሆን ???ጉዳፍ ፣ ለተሰንበት ግዳይ እና ኔዘርላንዳዊቷ ሲፋን ሀሰን በድጋሚ በ5000 ሜትር ይገናኛሉ ።  #አትሌቲክስ
19/08/2023

የዛሬው ልብ አንጠልጣይ ድራማ ይደገም ይሆን ???

ጉዳፍ ፣ ለተሰንበት ግዳይ እና ኔዘርላንዳዊቷ ሲፋን ሀሰን በድጋሚ በ5000 ሜትር ይገናኛሉ ።

#አትሌቲክስ

ኢትዮጵያ በአንድ ፍፃሜ ብቻ በሜዳሊያ ሠንጠረዥ በአሜሪካ ተበልጣ ከአለም ሁለተኛ ሆናለች ።
19/08/2023

ኢትዮጵያ በአንድ ፍፃሜ ብቻ በሜዳሊያ ሠንጠረዥ በአሜሪካ ተበልጣ ከአለም ሁለተኛ ሆናለች ።

ሲፋን ሀሰን የወደቀችበት አጋጣሚ
19/08/2023

ሲፋን ሀሰን የወደቀችበት አጋጣሚ

እንኳን ደስ አለሽ ሀገሬሬ 🇪🇹🇪🇹🇪🇹አትሌት ጉዳፍ ፀጋዬ ደሟን አፍስሳ ለሀገሯ ወርቅ አመጣች እንኳን ደስ አላችሁ ። በቡዳፔስት የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በሴቶች 10ሺ ሜትር ፍፃሜ ኢትዮጵ...
19/08/2023

እንኳን ደስ አለሽ ሀገሬሬ 🇪🇹🇪🇹🇪🇹

አትሌት ጉዳፍ ፀጋዬ ደሟን አፍስሳ ለሀገሯ ወርቅ አመጣች እንኳን ደስ አላችሁ ።

በቡዳፔስት የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በሴቶች 10ሺ ሜትር ፍፃሜ ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ከ 1 እስከ 3 ድረስ ተከታትለው በመግባት በቡዳፔስት የአለም ሻምፒዮና ለኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ወርቅ ብር እና ነሀስ አስገብተዋል ።

1ኛ ጉዳፍ ፀጋዬ
2ኛ ለተሰንበት ግደይ
3ኛ እጅጋአየሁ ታዬ

በውድድሩ ተጠብቃ የነበረች በትውልድ ኢትዮጵያ በዜግነት ኔዘርላንዳዊቷ ሲፋን ሀሰን እስከ መጨረሻው ድረስ ከጉዳፍ ጋር ብትተናነቅም አደናቅፏት ወድቃ ለገሯ ሜዳሊያ ሳታመጣ ቀርታለች

እንኳን ደስ አላችሁ 🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

በ10 ሺ ሜትር ፍፃሜ ኢትዮጵያን የሚወክሉ አትሌቶች ታውቀዋል ። የሀንጋሪ ቡዳፔስት የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ በእለተ ቅዳሜ ጅማሮውን ሲያደርግ በዓለም የአትሌቲክስ ቤተሰቦች ዘንድ በጉ...
19/08/2023

በ10 ሺ ሜትር ፍፃሜ ኢትዮጵያን የሚወክሉ አትሌቶች ታውቀዋል ።

የሀንጋሪ ቡዳፔስት የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ በእለተ ቅዳሜ ጅማሮውን ሲያደርግ በዓለም የአትሌቲክስ ቤተሰቦች ዘንድ በጉጉት የሚጠበቀው የሴቶች 10000 ሜትር ፍፃሜ ከወዲሁ የብዙሃኑን ቀልብ ስቧል ።

ዛሬ ምሽት 3:55 ላይ ለሚደረገው የሴቶች 10000 ሜትር የፍጻሜ ውድድር ኢትዮጵያን ወክለው የሚሳተፉ አራት አትሌቶች ከወዲሁ ሲታወቁ አትሌት ለተሰንበት ግደይ ፣ አትሌት ጉዳፍ ፀጋዬ ፣ አትሌት እጅጋየው ታዬ እና አትሌት ለምለም ሀይሉ ሀገራቸውን ወክለው የሚሳተፉ አትሌቶች ናቸው ።

Ananiya Feleke

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian Sport posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Ethiopian Sport:

Videos

Share