Gofer TUBE

Gofer TUBE Daily Media Monitoring -
This page is an Official page of gofer TUBE YouTube channel .

ሰበር መረጃየአሸባሪው ህወሓት አመራሮች የሚሰለጥኑበት እና የሚደበቁበት የቆላ ተንቤን በርሃ በጀግናው ሠራዊታችን ሙሉ በሙሉ ተያዘሱሌማን አብደላ
15/09/2022

ሰበር መረጃ

የአሸባሪው ህወሓት አመራሮች የሚሰለጥኑበት እና የሚደበቁበት የቆላ ተንቤን በርሃ በጀግናው ሠራዊታችን ሙሉ በሙሉ ተያዘ

ሱሌማን አብደላ

መስከረም 2 ቀን 1967 ዓ.ም አፄ ኃይለሥላሴ ከዙፋናቸው የወረዱት 48ተኛ ዓመት!  !___________________________________መስከረም 2, 1967 ዓ.ም የደርግ አባላት 13...
12/09/2022

መስከረም 2 ቀን 1967 ዓ.ም አፄ ኃይለሥላሴ ከዙፋናቸው የወረዱት 48ተኛ ዓመት! !
___________________________________
መስከረም 2, 1967 ዓ.ም የደርግ አባላት 13 ሆነው ወደ ቤተ-መንግሥት ሄዱና ጃንሆይ የአገዛዝ ዘመናቸው ማብቃቱን አረዷቸው፡፡ የደርግ አባላት ቤተ-መንግሥት ደርሰው ንጉሱን አስጠሯቸው፡፡

ንጉሱም በዝግታ ከፎቅ ላይ ወርደው በዙፋናቸው ላይ ሲቀመጡ የደርግ አባላት ደነገጡ፡፡ ሻምበል ደበላ ዲንሳ ደርግ የወሰነውን የውሳኔ ሃሳብ አነበቡ …

"ለሀገርና ለህዝብ ደህንነት ሲባል በዛሬው ዕለት ግርማዊ ቀዳማዊ አፄ ኃይለሥላሴ ከስልጣን ወርደዋል፤ ለደህንነትዎ ሲባልም አስተባባሪው ኮሚቴ ወዳዘጋጀልዎ ቦታ እንዲሄዱ ተወስኗል …" የሚል ይዘት ያለው ደብዳቤ አነበቡ፡፡

ሻምበል ደበላ ውሳኔውን አንበበው ሲጨርሱ ንባባቸውን ሲጀምሩ የሰጡትን ወታደራዊ ሰላምታ ደገሙ፡፡ ንጉሱም ዝም ብለው ቆዩና መናገር ጀመሩ፡፡

"ያነበባችሁትን ሰምተናል፤ የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገሥት ስንሆን ስም ብቻ አይደለም፡፡ ቢሆንም በየጊዜው የሚለዋወጠው ነገር ደግሞ ላገር የሚጠቅም ነገር እስካለበት…

የኢትዮጵያን ታሪክ ጠብቃችሁ ማልማት ከቻላችሁ የእኛ ታሪክ እዚህ ላይ ያበቃል፤ ካልቻላችሁ የእናንተ ታሪክ ያበቃና የእኛ ይቀጥላል ፤ አገራችንንና ሕዝባችንን በምንችለው አገልግለናል ፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ እድል የእኛን መወገድ የሚጠይቅ ከሆነ ስራችንን አቁመን ማንኛውንም ነገር ለመቀበል ዝግጁ ነን፤ ‹አሁን ተራው የእኛ ነው› ካላችሁ ኢትዮጵያን ጠብቁ›› በማለት ተናገሩ፡፡

… ከዚያም ንጉሱ ውብ በሆነችው ሮልስ ሮይስ መኪናቸው ሳይሆን ባረጀች ሰማያዊ ቮልስ ዋገን መኪና ተጭነው ወደ አራተኛ ክፍለ ጦር ግቢ ተወሰዱ፡፡
"ወደ ዋገን ወርደው ሲተኩ በሌላ" እንዲል ቴዲ አፍሮ ሰላም ዋሉ!!

Yoakin Bekele Pachi

ህወሐት ተጠፍንጎ ሲያዝ "ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ እደራደራለሁ" ብሏል። ባለፈው እንዳልነው እንደዚህ ጊዜ ከባድ ምት አርፎባቸው አያውቅም። በከባዱ ተለጥልጠዋል። ለፀጥታው ምክር ቤት "የUN ኃ...
12/09/2022

ህወሐት ተጠፍንጎ ሲያዝ "ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ እደራደራለሁ" ብሏል። ባለፈው እንዳልነው እንደዚህ ጊዜ ከባድ ምት አርፎባቸው አያውቅም። በከባዱ ተለጥልጠዋል። ለፀጥታው ምክር ቤት "የUN ኃይል ይግባልን" ብለው እንደጠየቁ ወዲያውኑ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በአፍሪካ ህብረት በኩል እንደራደራለን ማለታቸው ምን ያክል ጉዳት እንዳስተናገዱ አስረጅ ነው።

ህወሐት ድርድር ይበል እንጅ በሰጥቶ መቀበል መርህ የማያምን ገታራ ድርጅት ነው። ይኸው ትናንት ድርድር በሚል የተማፅኖ ደብዳቤ የጻፈ ቢሆንም ዛሬ በጠዋቱ በሱዳን በኩል ያለውን ኃይል አንቀሳቅሶ በቲያ (ሽኩሪያ) በኩል ወደ ቋራ እና ሽንፋ መስመር ሰርጎ ለመግባት እየተጋጋጠ ነው። በእርግጥ ወያኔ ድርድር ያለው ጉሮሮው ተሰንጎ ስለተያዘ ትንሽ ትንፋሽ ለማግኘት አስቦ ነው። በዚህ ሰሞን ማሰቢያ ጊዜ እንኳን ማግኘት አልቻሉም ነበር። ከፊት ከኋላ አጣድፈናቸዋል። ጀግናው የኢትዮጵያ ጦር እንደ ገና ዳቦ ከላይ ከታች ሲለበልባቸው ትንሽ እፎይታ ለማግኘት ሊጠሯት የማይወዷትን ድርድር የሚሏትን ቃል የምንግዴያቸውን ተነፈሱ።

ህወሐት ድርድር ሲል ማጭበርበር፣ ማምታታት፣ መሸወድ ማለቱ ነው። ለዚህ አጭበርባሪ ቡድን በምንም ሁኔታ እፎይታ መስጠት አይገባም። በእርግጥ ከአሁን በኋላ ሊገዳደረው የማይችለው ኃይል ስለገነባን ህወሐት በምንም ሁኔታ ሊያሰጋ የሚችል ቡድን አይደለም። ይሁን እንጅ ለትግራይ ህዝብ እፎይታ ሲባልም ህወሐት ፈፅሞ መሸነፍ አለበት። ይቺ ድርድር የሚላት ማዘናጊያም ብትሆን ብዙም ሩቅ የምታስጉዝ አይደለችም። ክሽከሻው ላይ ጠበቅ ማድረጉ ነው የሚያዋጣው።

በእርግጥ ህወሐትም ቢሆን ለቀለብ ሰፋሪዎቹ እኔ ድርድር እያልኩኝ የኢትዮጵያ መንግስት አሻፈረኝ ብሎ ወጋኝ ምናምን ለማለት ነው ይቺን ደብዳቤ የሞነጫጨረው። ህወሐት ልደራደር ቢል እንኳን የድርድሩን ቅድመ ሁኔታዎች በጀ ብሎ የሚቀበል አይደለም። እስከዚያው ድረስ ግን ጦራችንን ማጠናከራችንን አንቦዝንም። ዋናው ጉዳይ በእጃችን መተማመናችን ላይ ነው። ከዚያ ውጭ ነጮቹም ቢሆኑ ህወሐትን መሸከም ሲደክማቸው ከአንቀልባቸው ላይ አውርደው የሚጥሉት ስለሚሆን ብዙም አያሰጋንም። ብቻ የራስህን ኃይል በአስተማማኝ መንገድ መገንባትህን ቀጥል። ያኔ በየትኛውም ሁኔታ ለሚመጣ ኃይል አትበረግግም።

ይኸው ነው...!

22 ማዞሪያ፡ የደብረፅዮን የጦርነት ታክቲክ               የዓባይ፡ልጅ Esleman Abay"The 48 Laws of power” የተሰኘው የደራሲ ሮበርት ግሪን  መፅሐፍ፣ የአሸናፊነት ...
11/09/2022

22 ማዞሪያ፡ የደብረፅዮን የጦርነት ታክቲክ

የዓባይ፡ልጅ Esleman Abay
"The 48 Laws of power” የተሰኘው የደራሲ ሮበርት ግሪን መፅሐፍ፣ የአሸናፊነት 48 ዘዴዎችን ከፋፍሎ የያዘ ሲሆን፣ ደብረፂዮን የመዘዙት ቀቢፀ ተስፋዊ ካርታ ነው የሚባለው የሮበርት ግሪን ታክቲክ-22 የሚከተለውን ይዞ የምናገኘው ነው።

"ከባላጋራህ ስትነጻጸር ኃይልህ መዳከሙን በተገለፀልህ ማንኛውም ወቅት፣ ጦርነትህን አቁም፡፡ Use the surrender tactic: transform weakness into power የሥልጣን መወጣጫ መሰላልህ እንደተሰበረ ስታውቅ፣ እጅህን ስጥ! የሥልጣን ጆከር ካርታዎችህ እንደተበሉ ስታውቅ፣ ፈቅደህ ተማረክ፡፡
ለክብሬ፣ ለማንነቴ ብለህ አትዋደቅ፣ ቀን ካዘቀዘቀብህ እጅህን ስጥ፣ ዕድሜ ግዛ፣ እና አንሰራርተህ ውጋ!..የሚል..።
ይህ የደብረፂዮን ታክቲክ ነው ካልን ከዚሁ ጋር ጌታቸው ረዳ ከቀናት በፊት "ቂላቂል መግለጫ" እናስታውስ። ጌታቸው ረዳ ከሰማይ ጠቀስ የዛቻ ተራራው በአንዴ አቆልቁሎ ስለመሸነፍ ያወራበትን የቅርብ ጊዜ መግለጫው ታዲያ፣ በሮበርት ግሪን መፅሐፍ 21ኛው ታክቲክ ስር ልንመድበው የምንችለው ነው።
21ኛው የጦርነት ዘዴ ሮበርት ግሪን "በዙሪያህ ላሉት ቂል ምሰል፣ የዋህ ምሰል፣ ጮርቃ ምሰል፣ በምላስ የፈጠንክ፣ አላዋቂ ሰው ምሰል - Play a sucker to catch a sucker - seem dumber than your mark."

"አንተ ከነሱ በላይ ውስብስብ ሴራ እንደምታውጠነጥን ማወቅ የለባቸውም፡፡ በተለይ በሥልጣን መሠላል ላይ እየወጣህ ባለህበት ወቅት ከበላይህ ያሉት ሰዎች ሁሉ አንተን ከእነርሱ የባሰ ባለዝቅተኛ አዕምሮ አድርገው እንዲገምቱ ብዙ ፍንጮችን ስጣቸው፡፡ ደካማ ጎንህን አሳያቸው፡፡ መጽሐፍ ስትጽፍ አስሩን ምዕራፍ ጻፉልኝ በላቸውና በስምህ አሳትም። በጀርባህ ይሳለቁብሃል፡፡ በጉራ ወዳድነትህ ያላግጡብሃል።"

"..ብዙውን ቀላሉን ነገር ጥራና ምን ባደርግ ይሻለኛል ብለህ አማክራቸው፡፡ የምትናገረውን ጻፉልኝ በላቸው፡፡ የምታውቀውን መንገድ ምሩኝ በላቸው፡፡ እንደዚያ ስትሆን ታማኝ ውሻቸው አድርገው ይስሉሃል፡፡ ይህንን አውቀህ ፍጹም ገራገርና ተላላኪ ደደብ ምሰል! የላቀ አዕምሮ እንዳለህ በፍጹም አይመጣላቸውም። ጨርሰው ይተዉሃል፡፡
አንተ ግን መጥረቢያህን ለመሞረድ በቂ ጊዜ ታገኛለህ፡፡ ምቀኛና ጠላት አይኖርብህም፡፡ እነሱ በአንተ ሲሳለቁ፣ በመጨረሻ ወቅቱን ጠብቀህ ትስቅባቸዋለህ..።" አሁን ወደ ደብረፅዮን የ22 ማዞሪያ የስልጣን ታክቲክ እንመለስ..
"..በጦርነት ወቅት እንደምትሸነፍ እያወቅክ የወታደሮችን ህይወት በከንቱ ማስፈጀት፣ ከአንተ ጋር ዳግም ማንም እንዳይሰለፍልህ ያደርጋል፡፡ በጅልነትህ ሲሳለቅብህ ይኖራልንጂ።"
"መሸነፍህ እርግጥ በሆነበት ጦርነት ኃይልህን ለማስጨረስ በእልክ ገብተህ አትፈራገጥ፡፡ እጅህን ስጥ! ለመማረክ የሚይዝህ ክብር አይኑርህ፡፡ ይህን የምታደርገው ውርደትን ተመኝተህ ሳይሆን፤ ራስህን ለነገ ለማትረፍ ነው፡፡ ሌላ አመቺ ጊዜ ለመጠበቅ...፡፡"

"..ትክክለኛ አጋጣሚውን ስታገኝ፣ ዛሬ ማርኮህ ምህረት ለሰጠህም ቢሆን አትራራለት፡፡ ባለውለታህ እንደሆነ በተግባር አረጋግጥለት፡፡ በቃል ደረጃ ተገዛለት፡፡ እሱን የሚያስቆጣ ነገር ላይ በፍፁም አትገኝ፡፡ የኃይል አሰላለፉን አጥና፡፡ ሙሉ ትጥቆችህን አደራጅ፡፡ የተሸነፈ ሰው ከመመኘት ይታቀብ የሚል ህግ የለም። በግላጭ የማትጋፈጠውን፣ በህቡዕ ታከናውነዋለህ፡፡ እጅ መስጠት የሥልጣን ማግኛ ታክቲክ ነው እንጂ የዘለዓለም ቃልኪዳን አይደለም፡፡ መጀመሪያ እጅህን ስጥ፡፡ ከዚያ ኃይልህን በህቡዕ ዘርጋ፡፡ በዚህም በዚያም የማይታዩ ገመዶችን እየሳብክ አሸናፊህን እረፍት ንሳው.."

"..ላይ ላዩን ለጠላትህ አጎንብሰህ ስገድለት፡፡ ልብህን ግን እንደ ብረት አጠንክር። ይህን ዘዴ በሚገባ ከተወንከው ጠላትህን ልቡን ትማርከዋለህ፤ ይዘናጋል። ያኔ የምታደርገውን ታውቃለህ! ይህን ታክቲክ ስታውቅ፣ ይህን አንተ የምትተውነውን ትወና የሚተውንብህ ሌላ አሸንፈኸው ምህረት ያደረግክለት የቀድሞ ባላንጣህ ቢሆንስ ኖሮ? ብለህ አስበው፡፡ ለሚያንሰራራ ጠላት፣ በፍጹም እጅህን ለምህረት አትዘርጋ፤ እንደጀመርከው ጨርሰው!
ይህ ሕወሃታዊ ታክቲክ የአገልግሎት ጊዜው ያበቃው ሰሜን እዝን ባጠቃበት 2013 ላይ ነበር። ለሶስት አስርት አመታት የፈፀማቸው ወንጀሎች ችላ ተብለውለት፤ ምርጫም ሆነ ቅርጫ ልቡ እንዳዘዘው ከማድረግ የከለከለው አልነበረም። አራት ኪሎ እንደ ጓደኛ ስታናግረው ከመቀሌ የነበረው የሕወሃት አፃፋ የሳይቦርጅ አይነት ነበር። ተከታታይ ዛቻው ሰሞን እዝን ወደ ማጥቃት ተሻገረ። በሶስት ሳምንት ይዞታውን ቆላ ተምቤን ለማድረግ ተገደደ። የተውሶ ጉልበት ተላብሶ በከፈተው ዳግም ወረራ ብዙ ጥፋትና ውድመትን ወለደ....የህወሃት ታክቲክ 22 እዚጋ ነበር የተቀበረው። ከዛን ጊዜ ጀምሮ ደብረፂዮን አዘናግቶ የሚያርደው የዋህ በግ ሊገኝለት አልቻለም። በጣት የሚቆጠሩት ህወሃታዊ አዛውንቶች ምኞት ብቻ እስከ እለተ ቀብራቸው ይቀጥል ይሆናል፤ አርፋጁ የደብረፂዮን ታክቲክ-22 ውጤቱ የዜሮ ብዜት መሆኑን ድፍን ኢትዮጵያ ድምዳሜ ከሰጠበት ወራት ተቆጥረዋል።

እስሌማን ዓባይ #የዓባይልጅ

 ‼ ሕወሓት የተናጥል ተኩስ አቁም አደረገ‼የህወሓት መግለጫ ይዘትም በአፍሪካ ሕብረት ስር ለመደራደር መስማማቱን ይገልፃል↓ የትግራይ መንግስት የኢትዮጵያውያን ባጠቃላይ በተለይም የትግራይ ህዝ...
11/09/2022



ሕወሓት የተናጥል ተኩስ አቁም አደረገ‼
የህወሓት መግለጫ ይዘትም በአፍሪካ ሕብረት ስር ለመደራደር መስማማቱን ይገልፃል↓
የትግራይ መንግስት የኢትዮጵያውያን ባጠቃላይ በተለይም የትግራይ ህዝብ የተኩስ ድምጽ እንዳይሰማ፣የአስፈላጊ አገልግሎቶች እና ሰብአዊ እርዳታዎች መዘጋትና ስቃይና ስቃይ እንዳይሰማ ለማድረግ ከፍተኛ ፍላጎት አለው ።
ለዛም የትግራይ መንግስት በአፍሪካ ህብረት ጥላ ስር በሚደረገው ጠንካራ የሰላም ሂደት ላይ ለመሳተፍ ተዘጋጅቷል። ከዚህ ባለፈም ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር በተደረገው የእርስ በርስ ግጭት በአስቸኳይ እና በጋራ ስምምነት ለመታዘዝ ዝግጁ ነን። በእርግጥም የትግራይ መንግስት አሁን የተፈጠረውን ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት በተደጋጋሚ ጥረት አድርጓል። የትግራይ መንግስት ጦርነቱ እንዲቆም ቀድሞ በአንድ ወገን መፈጸሙ ለዚህ ማሳያ ነው።
በአፍሪካ ህብረት የሚመራ አስተማማኝ የሰላም ሂደት እንጠብቃለን። ይህ የሰላም ሂደት በጋራ ተቀባይነት ያላቸውን አሸምጋዮችንም ይጨምራል። ዓለም አቀፍ ታዛቢዎች ተዋዋይ ወገኖች እርስ በርስ መተማመን እንዲፈጥሩ፣ በሰላሙ ሂደት ላይ እምነት እንዲፈጥሩ እና የገባውን ቃል አፈፃፀም የሚደግፉ እና የሚቆጣጠሩ፣ እና ዓለም አቀፍ ባለሙያዎች ስለ ሰላም ሂደቱ ታማኝነት አስፈላጊውን መመሪያ እና ምክር ይሰጣሉ. ለዚህ አሳዛኝ ግጭት ዘላቂ መፍትሄ ማምጣት የምንችለው በሰላማዊ ውይይት ብቻ እንደሆነ እርግጠኞች ነን የሚል ነው።
የእርስ በርስ ግጭት መቆሙን ተከትሎ ቀጣዩ እርምጃ ሁሉን አቀፍ የሆነ የተኩስ አቁም ስምምነት ማጠናቀቅ እና ሁሉንም ያሳተፈ የፖለቲካ ውይይት አሁን ያለውን ግጭት መነሻ በማድረግ መፍትሄ መስጠት ነው።
የትግራይ መንግስት ሳይዘገይ ለማሰማራት የተዘጋጀ የድርድር ቡድን አቋቁሟል። ይህ ቡድን አቶ ጌታቸው ረዳ እና ጄኔራል ፃድቃን ገብረትንሳኤን ጨምሮ ወደፊት በሚደረገው ድርድር የትግራይን መንግስት የመወከል ስልጣን ተሰጥቶታል።
በአዲስ አመት እና በአዲስ ጅምር መንፈስ ትግሉን አቁመን ለሰላም እድል ሰጥተን ወደ ሰላምና ብልፅግና መንገድ እንጀምር። የሚል ነው።
ሱሌማን አብደላ

11/09/2022

2015

11/09/2022
በቦሌ አራብሳ ሁለት ሕፃናቶችን የገደለችው የቤት ሰራተኛ! በሕግ ቁጥጥር ስር ውላለች‼👇👇👇ምስሏን ለማየት  #ቴሌግራም ላይተጨማሪ ምስል ለማየት በቴሌግራም t.me/nuEnazegt.me/nuEn...
02/09/2022

በቦሌ አራብሳ ሁለት ሕፃናቶችን የገደለችው የቤት ሰራተኛ! በሕግ ቁጥጥር ስር ውላለች‼
👇👇👇
ምስሏን ለማየት #ቴሌግራም ላይ

ተጨማሪ ምስል ለማየት በቴሌግራም
t.me/nuEnazeg
t.me/nuEnazeg
t.me/nuEnazeg

ለወላጅ ብቻ ሳይሆን ለሁሉም ያማል(ሁላችንም ጥንቃቄ እናድርግ)ዛሬ አዲስ አበባ ቦሌ አራብሳ ኮንዶምኒየም በቤት ሰራተኛ ህይወታቸውን ያጡት የሚያሰስቱ ልጆች እነዚህ ናቸው።የ2 እና የ4 ዓመት ...
01/09/2022

ለወላጅ ብቻ ሳይሆን ለሁሉም ያማል
(ሁላችንም ጥንቃቄ እናድርግ)

ዛሬ አዲስ አበባ ቦሌ አራብሳ ኮንዶምኒየም በቤት ሰራተኛ ህይወታቸውን ያጡት የሚያሰስቱ ልጆች እነዚህ ናቸው።የ2 እና የ4 ዓመት ህፃናት ናቸው።እናትና አባት ሠራተኛዋን አምነው ልጆቻቸውን ሰጥተው ስራ ሄዱ፣ተጠርተው ሲመጡ ትንሿን በስለት ትልቋን በገመድ አንቃ ህይወታቸው ሊቀጠፍ ችሏል ።ምን ይባላል መፅናናቱ አብዝቶ ይስጣችሁ።

የቪዲዮና ድምፅ መረጃዎችን ለማግኘት
ቴሌግራም t.me/nuEnazeg

 ቡረሀን አልፋሽጋ ነው። ከመጠን በላይ እየደነፋ ነው። ጦራችን አሳማኝ የሆነ እርምጃ ይወስዳል ብሏል። በርግጥም ጀነራሉ ይሄንን ባለበት ቅፅበት ጦሩ የንፁህ ኢትዮጵያዊያን ቤት በከባድ መሳሪያ...
27/06/2022


ቡረሀን አልፋሽጋ ነው። ከመጠን በላይ እየደነፋ ነው። ጦራችን አሳማኝ የሆነ እርምጃ ይወስዳል ብሏል። በርግጥም ጀነራሉ ይሄንን ባለበት ቅፅበት ጦሩ የንፁህ ኢትዮጵያዊያን ቤት በከባድ መሳሪያ እየደበደበ አምሽቷል። ተዋጊ ጀቶቹ ዝቅ ብለው አልፋሽጋ መሬት ላይ ሲበሩ አምሽተዋል።
ይህንን ጦርነት በቀላሉ ማየት የለብንም። 30"ሺ በግብፅና በሱዳን የሰጠነው የህወሓት ሳምሪ ቡድን ከፊት ሆኖ በግብፅ መሳሪያ እየተዋጋን ነው። አላማው የወልቃይትን በር አስከፍቶ ከህወሓት ጋር መገናኘት ነው። በተቻለ መጠን ጥንቃቄም ይሁን የመልስ ምት መስጠት አለብን። አሁን መንግስት በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ለመፍታት እየጣረ ነው። የማይሳካ ከሆነ ግን ሁላችን እናልቃታለን እንጅ አገራችንን ሲያፈርሱት ማየት የለብንም። የኢትዮጵያ ህዝብ መንግስት የሚሰጠውን መግለጫ በተጠንቀቅ ሆነህ ጠብቅ።
ሱሌይማን አብደላ

 ለኢትዮጵያ እንቁምኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብን 3ኛ ዙር ልትሞላ ነው። ይሄንን ዙር ሞልታ ብትተወው እንኳን የሕዳሴው ግድብ ሥራውን ይቀጥላል። ያም ማለት ኢትዮጵያ የላይኛው ተፋሰስ ብቻ ሳትሆን ...
27/06/2022


ለኢትዮጵያ እንቁም
ኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብን 3ኛ ዙር ልትሞላ ነው። ይሄንን ዙር ሞልታ ብትተወው እንኳን የሕዳሴው ግድብ ሥራውን ይቀጥላል። ያም ማለት ኢትዮጵያ የላይኛው ተፋሰስ ብቻ ሳትሆን የላይኛው ወሳኝ አካል ትሆናለች ማለት ነው።
ይሄንን ወሳኝ የሀገር ግብ ለማምከን ግብጽና ሱዳን ከአንዳንድ የምዕራብ ሀገሮች ጋር ሆነው የግመሉን ጀርባ የሚሰብረውን የመጨረሻውን ጭነት ኢትዮጵያ ላይ ለመጣል እየተረባረቡ ነው።
ብዙ ጊዜ የአካባቢ ጥበቃ ጉዳይ ከአፋቸው የማይጠፋው ምዕራባውያን፣ ኢትዮጵያ ለምታካሂደው አረንጓዴ ዐሻራ የገንዘብ ድጋፍ ሲጠየቁ " ግብጽ ተቃውሞ ስላላት እንቸገራለን" ነው ያሉት። ግብጾች አረንጓዴ ዐሻራን የኢትዮጵያን አፈር ለማስቀረት የተጀመረ ዘመቻ ነው ብለው ነው የሚወስዱት። ግድቡን ማስቀረት ባይችሉ እንኳን በደለል እድሜውን ወይም ዐቅሙን ማሳጠር አንዱ ዓላማቸው ነው። ትግሉ ብዙ መልክ ነው ያለው።
ግብጽና ሱዳን ከአንዳንድ የምዕራብ ሀገሮች የመረጃና የዲፕሎማሲ ድጋፍ በማግኘት ከ4 አካላት ጋር ይሠራሉ። አሠልጥነው በሳዑዲ ተመላሽ ስም ካስገቧቸው አካላት፤ ከአሸባሪ የውጭ ኃይሎች፣ ከአሸባሪ የሀገር ውስጥ ተቋማት እና ከሱዳን ታጣቂዎች ጋር።
በሳዑዲ በረሃ ያሠለጠኗቸውን የኢትዮጵያ ስደተኞች ለማስገባት ከፍተኛ የዲፕሎማሲ ጫና ፈጥረው ነበር። በማኅበራዊ ሚዲያ በታገዘ ዘመቻ የኢትዮጵያውያን ኅሊና እንዲጨነቅ አድርገው ተጽዕኖ ፈጥረዋል። እንደ አልሸባብ ያሉትን አሸባሪዎች በምሥራቅ ኢትዮጵያ ለማስገባት ሞክረዋል። የደቡብ ሱዳን ታጣቂዎች በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ በጋምቤላ በኩል ጫና እንዲፈጥሩ ድጋፍ ተደርጎላቸዋል። የሕወሓት ሰዎች በጁባ በኩል ገብተው ረብጣ ብር እያከፋፈሉ ይሄንን ሲሠሩ ነው የከረሙት። የሸኔ፣ የጋምቤላና የጉሙዝ አሸባሪዎች ሥልጠና ወስደው በሳተላይት መረጃ እየተመሩ በግብጽ ድጋፍ የምዕራቡን ድንበር ፋታ እንዲነሡ ተልከዋል። በአማራ ክልል ያሉ፣ ታጣቂ ነን ባዮችም ከውስጥ ሆነው እንዲረብሹ ሥራ ተሰጥቷቸዋል።
የሱዳን ወታደሮች በኢትዮጵያ የሰሜን ምዕራብ ድንበር ጫና ለመፍጠር ትንኮሳ ጀምረዋል።
በኢትዮጵያውያን ስም እየተጻፉ ከግብጽ የሚመነጩ የማኅበራዊ ሚዲያ ዘመቻዎች በውስጥ በሚገኙ አጋጋዮች እየታገዙ የፕሮፓጋንዳ ሥራውን አጧጡፈውታል። በየአካባቢው ዐመጽ ለመቀስቀስ የወጠኑት ሤራ አልይዝ ሲላቸው፣ የጊምቢውን ጭፍጨፋ ለማውገዝ የተደረጉ እንቅስቃሴዎችን "ዐመጽ" ብለው እስከመጥራት ደርሰዋል።
የዚህ ሁሉ ዓላማ ሁለት ነው። ኢትዮጵያውያንን በሐሳብ መከፋፈልና የመከላከያ ሠራዊቱን መወጠር። በፕሮፓጋንዳ ሥራው ኢትዮጵያውያንን በመከፋፈል፣ በጠላቶቻቸው ላይ አንድ ሆነው እንዳይቆሙ ለማድረግ ሁለት ዘዴዎች ታቅደዋል። በተገኘው አጋጣሚ ንጹሐንን በመግደል የሕዝቡን እፎይታ መንሣት የመጀመሪያው ነው። ከሰሞኑ የታየው የምዕራብ ወለጋ አሰቃቂ የአማራዎች ጭፍጨፋ የዚህ አካል ነው። የተፈለገው መግደል ብቻ ሳይሆን በአሰቃቂ ሁኔታ በመግደል ሕዝቡን ማሸበር ነው። መጀመሪያ በሱማሌ ክልል አልሸባብ ሞክሮ ከሸፈበት፤ በመቀጠል በጋምቤላና በደምቢዶሎ አካባቢ ተሞክሮ ከሸፈ። በመጨረሻ በቀቢጸ ተስፋ የጊምቢው ጭፍጨፋ ተፈጸመ። በሌሎች አካባቢዎች ሊፈጸሙ የነበሩ ክሥተቶችም በጸጥታ አካላት በየቀኑ እየከሸፉ ነው። የሚያመልጡ አይኖሩም ብሎ መገመት ግን አይቻልም።
የፕሮፓጋንዳው ሌላው አካል ከግብጽ በሚመነጩና በኢትዮጵያ ተላላኪዎች በሚታገዙ የማኅበራዊ ሚዲያ ባንዳዎች የሚሠራ ነው። እምነትንና ብሔርን መሠረት ያደርጋል። በብሔሮች መካከል ብጥብጥ ለመፍጠር እየተሠራ ነው። የኦርቶዶክስ እና የእስልምና እምነቶችን ወደ ግጭት ለመክተት የታቀዱ ሤራዎች አሉ። ዋና ዋና የእምነቱ አስተማሪዎችን በመጠቀም ብጥብጥ መፍጠር። እነዚህ ሁሉ አንጀት መጎተቻ ናቸው።
የዚህ ድምር ውጤት ሠራዊቱ ስትራቴጂካዊ ቦታ ይዞ ለከፋው የሉዓላዊነት ግድጅ እንዳይሠማራ ለማድረግ ነው። እዚህም እዚያም በመተንኮስ ሠራዊቱን ከድንበር ወደ መንደር ለማውረድ። ይሄንን ለማሳካት በማኅበራዊ ሚዲያ ዘመቻ ተጀምሯል። በተለይም ወሳኝ ከሚባሉ አካባቢዎች ሠራዊቱ ወደ ግጭት ቦታዎች እንዲሳብ ለማድረግ እየተሠራ ነው። የሠራዊታችንን ዐቅምና የዝግጁነት ልክ ጠላቶቻችን ጠንቅቀው ያውቁታል። ካለፈው ጦርነት በኋላ የኢትዮጵያ ሠራዊት የት ደረጃ ላይ እንዳለ ከወዳጆቻችን በላይ ጠላቶቻችን እየመረራቸውም ቢሆን ያውቁታል። ያላቸው አማራጭ ለተጨማሪ ዝግጁነት ፋታ እንዳያገኝ መወጠር ነው ብለው አምነዋል። በዚህ በዚያ ሞከሩ። እምቢ አላቸው። አሁን የንዴት ሥራቸውን ሊሠሩ ተነሥተዋል።
ይህ ሁሉ የኢትዮጵያን እግር ሰብሮ ሽባ የማድረግ ዕቅድ የሚከሽፈው የጠላትን ዕቅድ ተረድቶ፣ አንድ ሆኖ በመቆም ነው። አመራሩ እጁንና ልቡን ንጹሕ አድርጎ፣ በጎጥና በጥቅም ከመጓተት ወጥቶ ግዳጁን ይወጣ። አካባቢውን ይጠብቅ፤ ያስጠብቅ፤ ከከፋፋይ ሐሳቦች ይታቀብ። ሕዝቡም ወገቡን አሥሮ፣ ሐሞቱን አኮሳትሮ ለየአካባቢው ዘብ ይቁም። የወገን ሞት ያማል። ሕመሙም የአጥንት ሕመም ነው። በአንድ በኩል የተጎዱትን እየረዳን፣ በሌላ በኩል የሌሎችን ጉዳት ለማስቀረት አንድ ሆነን መሥራት አለብን። የዘመድ ቄስ እንሁን። እየፈታን እናልቅስ። ለኢትዮጵያ እንቁም።
በዚህ ወቅት ኢትዮጵያን ለመታደግ፣ ከጸጥታ አካላት ጋር አንድ ሆነን ከመቆም የተሻለ ምንም አማራጭ የለም። ጥርሳችንን ነክሰን ወሳኝ ምዕራፎቻችንን የግድ እንሻገር።
via daneyel keberet

   ❗ Share አድርጉትና ቢያንስ ያላወቁ እውነታውን ይወቁ ! እደግመዋለሁ ኡዝር የለህም ! ዛሬም ከሌሎች ባንኮች ጋር ኢስላማዊ የባንክ ስርአትን እፈፅማለሁ ብለህ ታስብ ይሆን ? ሌሎች ባ...
18/06/2022



Share አድርጉትና ቢያንስ ያላወቁ እውነታውን ይወቁ !
እደግመዋለሁ ኡዝር የለህም ! ዛሬም ከሌሎች ባንኮች ጋር ኢስላማዊ የባንክ ስርአትን እፈፅማለሁ ብለህ ታስብ ይሆን ? ሌሎች ባንኮች እውነት ኢስላማዊ የባንክ አገልግሎት እየሰጡኝ ነው ብለህ ራስህን ታታልል ይሆን ?! ከላ !
እየውልህ ወዳጄ በኢትዮጵያ ውስጥ ከዚህ በፊት ኢስላማዊ ወይንም ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት የሚሰጥ አንድም ባንክ የለም ። ሲቢኢ ኑር ።፣ አቢሲኒያ አሚን ፣ ዳሽን ሸሪካ ፣ ኦሮሚያ ህብረት ባንክ አልሁዳ ፣ ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ሁሉም ፌክ ናቸው ። ሿሿ !!
ሁለት ምሳሌ ላንሳላችሁ !
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከኢስላማዊ የባንክ አገልግሎት የሰበሰበው ብር ከ 60 ቢሊዮን ብር በላይ ደርሷል ። 60 ቢሊዮን ብር !! ከዚህ ውስጥ ከወለድ ነፃ ስንቱን ብር እንዳበደረው ታውቃላችሁ ? 6 ቢሊዮን ብሩን ብቻ !! ቀሪውን 54 ቢሊዮን ብር ያበደረው በወለድ ነው ። ካንተ በነፃ ወስዶ በአመት 17 % ይሰበስብበታል ። ከወለድ ነፃ ብድር ሲጠየቅ ግን የለኝም እያለ ይመልስሃል ። እና አንተ እዚያ ያስቀመጥከው ገንዘብ ለነማን ይበደር መሰለህ ? አላህ እርም ላደረጋቸው ለመጠጥ ፋብሪካዎች እና ለሌሎች ሀራም ቢዝነሶች ። ታዲያ አንተ እዚያ ባስቀመጥከው ገንዘብ ተጠያቂ የማትሆን ይመስልሃል !!??
ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ ( ኦሮሚያ ባንክ ) በወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ራሱን መሪ አድርጎ ያቀርባል ። ግና እውነት እውነት እላችሗለሁ በሼሪው ቢመዘን የሚሰጠው አገልግሎት አንድም የሼሪአ መስፈርት አያሟላም ። ሿሿ ነው !
ሌሎችም ባንኮች እንደዚያው ናቸው ከወለድ ነፃ በሚል የዳቦ ስም ከሰበሰቡት ገንዘብ በወለድ ያበድራሉ ከየትኛውም ተቀማጭ በላይ ከፍተኛ ትሮፍ ያጋብሱበታል ።
እስከዛሬ ኢስላማዊ ባንክ ስሌለሉና አማራ ስላልነበረህ እነዚህ ባንኮች ላይ ስታስቀምጥ ኖርክ እሺ ኡዝር ነበረህ ማለት ነው ።
ግና ዛሬ ምን ኡዝር አለህ ??
ከሼሪአ ውጭ በሌላ በምንም መልኩ አገልግሎት የማይሰጡ ባንኮች ተቋቁመውልህ አንተን ለማገልገል እየጠበቁህ እያለ አንተ እነርሱን ረግጠህ የመሄድ ህሊናዊስ ሀይማኖታዊስ ሞራል ይኖርህ ይሆን ? አዎ ዘምዘምና ሂጅራ የተቋቋሙት በሼሪአ የሚሰሩትም በሼሪአ ፣ የቆሙትም ለሼሪአ ነው ። ያንተው ላንተው የተቋቋሙ ተቋሞችህ ናቸው ።
አንተ እነዚህን ባንኮች ትተህ ከሄድክ ማን መጥቶ ተቋሞችህን ጠንካራ እንዲያደርግልህ ትፈልጋለህ ። አላህ አንድን ባለሀብት ሰው የሚጠይቀው ከየት አመጣኸው ብቻ ብሎ አይደለም ከምን አደረስከው ብሎም ጭምር እንጅ ! እና ሌሎች ባንኮች ላይ ስታስቀምጥ የገንዘብህ መዳረሻ ሪባ መሆኑን እወቅ ! ባንኩ ካንተ ተበድሮ ለሪባ ሲያበድረው አንተ ሪባ አበዳሪ ሆንክ ማለት ነው ።
ልብ በል ሪባ አበዳሪ ከሪባ ተበዳሪ የበለጠ በአላህ የሚያስጠይቅ ከባኢር ወንጀል ነው ።
እና እልሃለሁ ራስህን ከሪባ ነፃ አውጣ ! ገንዘብህን ከሪባ ነፃ በሆኑት ዘምዘምና ሒጅራ ባንኮች አስቀምጥ ። ተቋሞችህን አጠናክር ! የባንኮቹ ባለቤት አንተው ራስህ ነህ !
via
ቴሌግራም

 ተጠናቀቀ ! እንኳን ደስ አለን!! ሀገራችን አሸንፋለች🇪🇹 ኢትዮጵያ 2-0 ግብፅ 🇪🇬 Ethiopia 2-0 Egypt Full time(ዳዋ ሁቴሳ 21' / ሽመልስ በቀለ 40')
09/06/2022


ተጠናቀቀ !
እንኳን ደስ አለን!! ሀገራችን አሸንፋለች
🇪🇹 ኢትዮጵያ 2-0 ግብፅ 🇪🇬
Ethiopia 2-0 Egypt Full time
(ዳዋ ሁቴሳ 21' / ሽመልስ በቀለ 40')

 መንግስት አለምአቀፉ የቁርአን ውድድር ከገጽታ ግንባታ እና ከቱሪዝም አንጻር በማየት ተገቢውን ትኩረት ሊሰጠው ይገባል።  በመጪው እሁድ በአዲስ አበባ ስቲዲዮም የሚካሄደው ዓለም አቀፍ የቁርዓ...
08/06/2022



መንግስት አለምአቀፉ የቁርአን ውድድር ከገጽታ ግንባታ እና ከቱሪዝም አንጻር በማየት ተገቢውን ትኩረት ሊሰጠው ይገባል።
በመጪው እሁድ በአዲስ አበባ ስቲዲዮም የሚካሄደው ዓለም አቀፍ የቁርዓን እና የአዛን ውድድር ላይ ለመገኘት ከ56 በላይ ሀገራት የትወጣጡ ተወዳዳሪዎች እና እንግዶች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።
መንግስት ይህ አለም አቀፍ ውድድር እንደ መልካም አጋጣሚ በመቁጠር ለአገር ገጽታ ግንባታ ሊጠቀምበት ይገባል። እንግዶቹ እንደ ቱሪስት በአገሪቷ ለሚኖራቸው ቆይታ የሚያወጡት ወጪ (ገንዘብ) ተጨማሪ ጥቅም ነው። እንደ ቱሪስት በመቁጠርም የአገሪቷ የተሪስት መስሕብ ቦታዎች እንደጎበኙ በማድረግም ተጨማሪ ገቢ ማገኘት ይቻላል።
በመሆኑም መንግስት ለዚህ አለምአቀፍ ውድድር ትኩረት ሊሰጠው ይገባል። ይህም:
1) ለእንግዶቹ አቀባበል በማድረግ
2) በውድድሩ መክፈቻ ላይ በመገኘት የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር በማድረግ
3) ውድድሩ የተሳካ ይሆን ዘንድ አስፈላጊው ጥበቃ እና አቅርቦት በማድረግ
4) ውድድሩ ተገቢው አገር አቀፍ እና አለም አቀፍ የሚዲያ ሽፋን እንዲያገኝ በማድረግ
5) ውድድሩ ሲያልቅ ለተወዳዳሪዎች አሸኛኘት በማድረግ
Via Abdurahim


የቪዲዮ መረጃዎችን ለማግኘት
https://www.youtube.com/channel/UCpOINfXANvOHa0oHCkq5gog

 *በበጋ እርሻ ብቻ ከ 600,000 ሺህ በላይ መሬት በሰብል ተሸፍኗል*ዘንድሮ ምንም አይነት ስንዴ ወደ ሀገር ውስጥ አላስገባችም*በሚቀጥለው አመት ከ2 ሚሊዮን ቶን በላይ የምግብ እህል ወደ ...
07/06/2022



*በበጋ እርሻ ብቻ ከ 600,000 ሺህ በላይ መሬት በሰብል ተሸፍኗል
*ዘንድሮ ምንም አይነት ስንዴ ወደ ሀገር ውስጥ አላስገባችም
*በሚቀጥለው አመት ከ2 ሚሊዮን ቶን በላይ የምግብ እህል ወደ ጎረቤት ሀገር ይላካል

ሩሲያ ከ 2014 በፊት ማለትም ክራይሚያን ከመውረሯ በፊት የአለማችን ቀዳሚዋ የምግብ እህሎች ሸማች ሀገር ነበረች ። የዜጎቿን የምግብ ፍላጎት የምታሟላው ከውጭ ሀገራት በማስገባት ነበረ ። ግና ክራይሚያን በወረረች ጊዜ አብዛኛውም የአለም ምግብ እህል የሚያመርቱት አሜሪካና የአውሮፓ ሀገራት በሩሲያ ላይ የምግብ አቅርቦትን ጨምሮ በርካታ ማእቀቦችን ጣሉባት ። ይህ ለሩሲያ የለውጥ ነጥብ ( Turning point ) ነበረ ።

የሩሲያ መንግስት አንድ ቁርጠኛ ውሳኔ ወሰነ ። ሩሲያ ከዚህ በሗላ አንድትም የምግብ እህል አታስገባም እንደውም ከራሳችን አልፈን ለአለም መትረፍ የሚችልን ምግብ ማምረት አለብን በማለት ። ይህ ውሳኔ ተፈፀመ ። ሩሲያ ራሷን በምግብ ለመቻል ሁለት አመትም አልፈጀባት ።
ከሁሉ የሚያስገርመው ግን ሩሲያ ያን ውሳኔ ከወሰነች ከአራት አመት በሗላ በአለማችን ቁጥር አንዷ የምግብ ላኪ ሀገር ሆነች - አሜሪካን እና ካናዳን በመብለጥ ጭምር ። ዛሬ ቢሊዮኖች የሩሲያ የምግብ አቅርቦት ጥገኞች ናቸው ። ሩሲያ ከ 37 ሚሊዮን ቶን በላይ ለአለም በማቅብ ቢሊዮኖችን መመገብ የሚያስችልን አቅም ተጎናፅፋለች ! ምስጋና ለዚያ የምእራባውያን ማእቀብ እንዲሁም ፈተናን ወደ ፀጋ ለለወጡ መሪዎቿ ይግባና !

ሀገራችን ኢትዮጵያ እና መንግስቷ እየሄደችበት ያለው ሁኔታ ያንን የሩሲያን የምርታማነት አብዮት የሚያስታውስ ነው ። አዎ ልክ እንደ ሩሲያ ሁሉ ምእራባውያን እኛን በስንዴ ሊያስፈራሩን በምግብ እገዳ ሊቀጡን ብዙ ጥረዋል ። በዚያ ላይ በሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት ምክንያት የስንዴ አቅርቦት በመስተጓጎሉ ምርቱን ወደሀገር ውስጥ ማስገባትም የማይቻል አድርጎታል ። ከዚያ አልፎ ያለፍንበት የርስበርስ ጦርነት በብዙ መልኩ ምርታማነታችንን ጎድቶታል ።

ግና መንግስታችን ልክ እንደሩሲያ ሁሉ ይህንን የፈተና ጊዜ በደ እድል ቀየረው ። ዛሬ ኢትዮጵያ በታሪኳ አይታ የማታውቀው የስንዴ ሰብል ምድሯን ሸፍኗል ። በበጋ እርሻ ብቻ ከ 600,000 ሺህ በላይ መሬት በሰብል መሸፈኑን መስማት በእውነቱ የሚያስደንቅ ነው ። በዚህም በሚሊዮን የሚቆጠር ቶን የምግብ እህል ይጠበቃል ።

በሚገርም ሁኔታ ኢትዮጵያ ዘንድሮ ምንም አይነት ስንዴ ወደ ሀገር ውስጥ አላስገባችም ። ይህም የውጭ ከፍተኛ ምንዛሬን ከማስቀረቱም በላይ የምግብ እህል የዋጋ ግሽበት እንዳይፈጠር አድርጎታል ። ኢትዮጵያ በዚህ አመት በምግብ ራሷን ትችላለች ።

በሚቀጥለው አመት ደግሞ ከሁለት ሚሊዮን ቶን በላይ የምግብ እህል ወደ ጎረቤት ሀገር የመላክ እቅድ አላት ። ይህ የማይታመን የግብርናችን ስኬት ነው !

ልብ በሉ !
ኢትዮጵያ እስካሁን መታረስ ከሚችለው 75 ሚሊዮን ሔክታር መሬት ውስጥ እያረሰች ያለቺው 15 ሚሊዮን ሔክታሩን ብቻ ነው ። ያ ማለት ኢትዮጵያ ያላትን መሬት በአግባቡ ከተጠቀመችበት መላው አፍሪካን መመገብ ትችላለች ማለት ነው ። ይህ ደግሞ በአላህ ፈቃድ ይሳካል !!
via Seid Mohammed Alhabeshiy


የቪዲዮ መረጃዎችን ለማግኘት
https://www.youtube.com/channel/UCpOINfXANvOHa0oHCkq5gog

 ፒያሳ ወርቅ ቤቶች ጀርባ በደረሰ የእሳት አደጋ የ15 አባወራ ቤቶች ወደሙ!በአዲስ አበባ በአራዳ ክፍለ ከተማ ፒያሳ ልዩ ስሙ ወርቅ ቤቶች ጀርባ ዛሬ ከቀኑ 9ሰዓት ከ37 ደቂቃ ላይ በደረሰ ...
06/06/2022


ፒያሳ ወርቅ ቤቶች ጀርባ በደረሰ የእሳት አደጋ የ15 አባወራ ቤቶች ወደሙ!

በአዲስ አበባ በአራዳ ክፍለ ከተማ ፒያሳ ልዩ ስሙ ወርቅ ቤቶች ጀርባ ዛሬ ከቀኑ 9ሰዓት ከ37 ደቂቃ ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ የ15 አባወራዎች ቤቶች መውደማቸውን የእሳት አደጋ ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቃል፡፡

የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለብስራት ሬድዮ እንደተናገሩት በአደጋው አንድ የኮሚሽኑ የአደጋ ጊዜ ሰራተኛ እና ሁለት ነዋሪዋች ላይ በጭስ በመታፈናቸው ጉዳት ደርሶባቸዋል ብለዋል።

የእሳት አደጋው የደረሰበት ቦታ ከወርቅ ቤቶቹ ጀርባ ሲሆኑ ቤቶቹ እጅግ የተጠጋጉ፣ የኤሌክትሪክ ዝርጋታቸው እና ቤቶቹ የተሰሩበት ግብዐቶች ውድመቱን ከባድ አድርጎታል። በተጨማሪ የቆዩ ነባር ቤቶች በመሆናቸው አደጋው ሰፊ ሆኖ የበርካታ አባወራ ቤቶች እንዲወድሙ እንዳደረገው ተነግሯል።

ወደ ወርቅ ቤቶቹ እሳቱ እንዳይዛመት እና ከፍተኛ የንብረት ውድመት እንዳይደርስ የኮሚሽኑ ሰራተኞች መትጋታቸውን አቶ ንጋቱ ጨምረው ተናግረዋል።አደጋውንም ለመቆጣጠር 75 የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች የተሳተፋ ሲሆን አስር የእሳት አደጋ ተሽከርካሪዋች 83ሺ ሊትር ውሃ አንድ ውሃ ጫኝ ተሽከርካሪ ከመንገዶች ባለስልጣን ጥቅም ላይ ውለዋል።እሳቱን ለመቆጣጠር አንድ ሰዓት ከሰላሳ ደቂቃ ፈጅታል።


የቪዲዮ መረጃዎችን ለማግኘት
https://www.youtube.com/channel/UCpOINfXANvOHa0oHCkq5gog

 ቢትኮይን ምንድነው ?አሁን ላይ የአንድ ቢትኮይን ዋጋ በብር 3,000,000 (ሶስት ሚሊዮን) የኢትዮጵያ ብር ነው።አሁን ላይ በብላክ ማርኬት አንድ የአሜሪካን ዶላር 1 USD $ ከብር 82 ...
06/06/2022



ቢትኮይን ምንድነው ?
አሁን ላይ የአንድ ቢትኮይን ዋጋ በብር 3,000,000 (ሶስት ሚሊዮን) የኢትዮጵያ ብር ነው።
አሁን ላይ በብላክ ማርኬት አንድ የአሜሪካን ዶላር 1 USD $ ከብር 82 እስከ 90 ብር የኢትዮጵያ ብር እየተሸጠ ነው።

ቢትኮይን የክሪፕቶግራፊ ቴክኖሎጂን የሚጠቀም አዲስ አይነት የዲጂታል የገንዘብ አጠቃቀም እና አከፋፈል ስርዓት ወይንም በሌላ አጠራሩ የክሪፕቶከረንሲ አሰራር ነው። ክሪፕቶግራፊ ማለት ባጭሩ በመረጃ መረብ አማካኝነት በኮምፒውተሮች መካከል ለሳይበር ጥቃት እንዳይጋለጡ የመሰወር ወይንም ሚስጥራዊ የማድረግ ሂደት ነው።

ሳቶሺ ናካሞታ በሚባለው ማንነቱ በማይታወቅ የኮምፒውተር ባለሙያ በ 2009 ዓ.ም. የተፈጠረው ቢትኮይን ማንም በነፃ የሚጠቀመው "open source" ሶፍትዌር ነው።
ቢትኮይን በሁለት ሰው መካከል የዲጂታል የገንዘብና የክፍያ ልውውጥ የሚካሄድበት "peer-to-peer" አሰራር ሲሆን፣ የክፍያ ስርዓቱ ያለገንዘብ ተቋም ጣልቃገብነት ይፈፀማል።

ይህ የዲጂታል ገንዘብ እንደተለመደው አይነት ገንዘብ የወረቀት ቅርፅ የሌለው ሲሆን፣ ልውውጡ የሚፈፀመው ለዚህ ተብለው በተዘጋጁና በኢንተርኔት በተያያዙ ኮምፒውተሮች (distributed computing) አማካኝነት ነው።

ቢትኮይን ረቂቅ ቴክኖለጂን በመጠቀም ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፍ (peer-to-peer technology) ምንም ጣልቃ ገብነት (ባንክ ወይም ወሳኝ ባለስልጣን) ሳያስፈልግ የሚዘዋወር ገንዘብ ነው:: ዝውውሩም በህብዝ ማህደር (public distributed ledger ) ብሎክ ቼይን ውስጥ (Block chain) በግልጽ ይመዘገባል::

የገንዘብ ዝውውሩን የሚያጸድቁት ኮምፒውተሮች ናቸው:: ለዚህም ቢትኮይን ማይኒንግ እጅግ በርካታ ኮምፒተሮች ስራ ላይ ውለዋል:: ቢትኮይን ማይነርስ የተባሉ ሰዎችም አገልግሎት ሰጪዎች ሆነዋል::

ባለሙያዎቹ ቢትኮይን ለመዘረፍ ቀላል አይደለም ይላሉ:: ሆኖም ከመረጃ መዝባሪዎች (ሀከሮች) ሊያመልጥ ግን አልቻለም:: ገንዘብ ሲተላለፍ ለአገልግሎቱ በአንጻራዊነት ዝቅተኛ ክፍያ ይጠየቃል:: የሆነው ሆነና ወደፊት ባንኮችን የመተካት ሚና ሊኖረው ስለሚችል ለነባሩ የባንክ ስርአት አስጊ (ራስ ምታት) መሆኑ አልቀረም:: ከቁጥጥር ውጪ ስለሆነ የሀገራት ገንዘብ ዝውውር ላይም አደጋ ደቅኗል::
via legal service


የቪዲዮ መረጃዎችን ለማግኘት
https://www.youtube.com/channel/UCpOINfXANvOHa0oHCkq5gog

 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክን ቢትኮይን, ፊያስ እና ወዘተ. . የተሰኙ ክሪፕቶከረንሲዎች በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ታግደዋል:: በኢትዮጵያ እንደ ክሪፕቶ ከረንሲ፣ ቢትኮይን እና የመሳሰለው ምናባ...
06/06/2022



የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክን ቢትኮይን, ፊያስ እና ወዘተ. . የተሰኙ ክሪፕቶከረንሲዎች በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ታግደዋል::
በኢትዮጵያ እንደ ክሪፕቶ ከረንሲ፣ ቢትኮይን እና የመሳሰለው ምናባዊ ንብረትን (ዲጂታል መገበያያ ገንዘብ) ለግብይት ወይም ለክፍያ መጠቀም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዕውቅና ያልተሰጠው ድርጊት በመሆኑ ህብረተሰቡ ከእንደዚህ አይነት ሕገ-ወጥ ተግባር እራሱን እንዲጠብቅ ባንኩ አሳስቧል።
የኢትዮጵያ የገንዘብ መደብ ብር እንደሆነና በብሔራዊ ባንክ በሌላ አኳኋን ካልተፈቀደ በስተቀር በሀገሪቱ የሚከናወኑ ማናቸውም የገንዘብ ግንኙነቶች ሁሉ የሚከፈሉት በብር እንደሚሆን የብሔራዊ ባንክ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 591/2000 በግልጽ እንደሚደነግግ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አስታውቋል።


የቪዲዮ መረጃዎችን ለማግኘት
https://www.youtube.com/channel/UCpOINfXANvOHa0oHCkq5gog

 የአ/አ ፖሊስ መርማሪ ከ15 ቀን በፊት በአዲስ አበባ ከተማ በሞሴ ሆቴል ከ8ኛ ፎቅ ህይወቷ አልፎ ስለተገኘችው በሀናን መሐመድ ግድያ ወንጀል ፍቅረኛዋ ተጠርጥሮ በቁጥጥር ስር ውሎ ሰፊ የምር...
30/05/2022



የአ/አ ፖሊስ መርማሪ ከ15 ቀን በፊት በአዲስ አበባ ከተማ በሞሴ ሆቴል ከ8ኛ ፎቅ ህይወቷ አልፎ ስለተገኘችው በሀናን መሐመድ ግድያ ወንጀል ፍቅረኛዋ ተጠርጥሮ በቁጥጥር ስር ውሎ ሰፊ የምርመራ ስራ እያከናወነ መሆኑን ለችሎቱ አስታውቋል።

የሟች የአሟሟት ሁኔታን ለማጣራት ለአስከሬን ምርመራ እንዲደረግ ጠይቆ ውጤት እየተጠባበቀ መሆኑን የገለጸው መርማሪ ፖሊስ ተጨማሪ ማስረጃዎችን ለማቅረብ እንዲያስችለው የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ እንዲሰጠው ፍርድ ቤቱን ጠይቋል።

ተጠርጣሪ ከድር ሀሰን በበኩሉ ከጂማ መጥተው በሆቴል እንደነበሩ ገልጾ ሟች ሀናን መሐመድ የሚወዳት ፍቅረኛው መሆኗንና ህይወቷ እስካለፈበት ሰዓት በመካከላቸው ምንም አይነት ጸብም ሆነ ጭቅጭቅ እንደሌለ ለፍርድ ቤት አብራርቷል።

በማህበራዊ ሚዲያ የሚናፈሰውን ወሬ በተሰማ ቁጥር በየጊዜው እየተጠራሁ እጠየቃለው እውነቱ ግን ሀናን የማፈቅራት ሚስቴ ናት እሷ ነጋዴ ናት ዕቃ ገዝቼ እንድመጣ አዛኝ በሰላም ተነጋግረን ፊቴን ታጥቤ ከሆቴሉ በደረጃ በኩል ነው የወረድኩት ስወጣ ባለቤቴ ደህና ነበረች ወጥቼ ሄጄ 2:00 ሰዓት ላይ በስልክ ደውላ በአስቸኳይ ተመለስ አለቺኝ ከዛ ስልኩን ዘጋች እኔም ለሆቴሉ ማናጀር ደውዬ ምን እንደሆነች እንዲጠይቅልኝ ነገርኩት በኋላ ላይ የሆቴሉ ማናጀር ደውሎ ለኔ መንገር ፈርቶ ደህና ናት ፈጥነህ ና አለኝ ከዛ እሷን ወደ ቤተዛታ ወስደዋት ነበር ቤተዛታ ስደርስ ህይወቷ አልፎ አገኘኋት ወዲያው ፖሊስ ጣቢያ ሄጄ እንዲያጣሩልኝ አመለከትኩ ሲል ለፍርድ ቤቱ አብራርቷል።

ከዚህ በፊትም በተደጋጋሚ እራሴን አጠፋለው እያለች ትናገር እንደነበር የገለጸው ተጠርጣሪ በማላታይን እራሷን ለማጥፋት በተደጋጋሚ ሞክራ እንደነበር ቤተሰቦቿ እንደሚያውቁ ለችሎቱ አስረድቷል።

በዕለቱ ሆቴል ውስጥ የተፈጠረውን ሁኔታ ከሆቴሉ ካሜራ ላይ የተንቀሳቃሽ ምስል አይተው ማጣራት እየተቻለ እኔ ታስሬ የምወዳትን የሚስቴን አስከሬን ተቀብዬ መቅበር አልቻልኩም ሲል ለፍርድ ቤቱ አብራርቷል። በፖሊስ በኩል የተንቀሳቃሽ ካሜራ ማስረጃ እንደተቀበለና እንዳልተቀበለ ከፍርድ ቤቱ ለተነሳ ጥያቄ አለመቀበሉን የገለጸው መርማሪው ተንቀሳቃሽ ምስል እንደሚቀበል ገልጿል።

ጉዳዩን የተከታተለው የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 1ኛ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት የተጠርጣሪ የወንጀል ተሳትፎ ተለይቶ እንዲቀርብ ትዕዛዝ በመስጠት ለተጨማሪ ምርመራ ለፖሊስ የ 11 ቀን ጊዜ ፈቅዷል። የምርመራ ውጤት ለመጠባበቅ ለሰኔ 3 ቀን 2014 ዓ/ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰቷል።
via ጋዜጠኛ ታሪኩ አዱኛ


የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://www.youtube.com/channel/UCpOINfXANvOHa0oHCkq5gog

 በሃሰተኛ ገንዘብ ነዳጅ ቀድቶ ለማምለጥ የሞከረው አሽከርካሪ ከቆመ ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨቱ ህይወቱ ማለፉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገለፀ፡፡                     *******የትራፊክ...
27/05/2022



በሃሰተኛ ገንዘብ ነዳጅ ቀድቶ ለማምለጥ የሞከረው አሽከርካሪ ከቆመ ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨቱ ህይወቱ ማለፉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገለፀ፡፡
*******
የትራፊክ አደጋው የደረሰው ግንቦት 18 ቀን 2014 ዓ/ም ከሌሊቱ 6፡30 ሰዓት ገደማ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ልዩ ቦታው ሚካኤል አደባባይ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው ፡፡
የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 1- 30262 አ.አ የሆነ ተሽከርካሪ ከጀሞ 1 አቅጣጫ ወደ ሚካኤል አደባባይ እየተጓዘ 67 ማዞሪያ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሚገኝ ነዳጅ ማደያ ውስጥ ነዳጅ ሊቀዳ መግባቱን በአዲስ አበባ ፖሊስ የትራፊክ አደጋ ምርመራ ቲም ሃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ስጦታው ወልዴ ገልፀዋል፡፡
አሽከርካሪው ነዳጅ ከቀዳ በኋላ አምስት ባለ 100 መቶ ሀሰተኛ የብር ኖቶችን ለነዳጅ ማደያው ሰራተኛ ሰጥቶ በሚሄድበት ወቅት ነዳጅ ቀጂው የብሮቹን ትክክለኛነት በመጠራጠሩ ሊያስቆመው መሞከሩን የጠቀሱት ምክትል ኢንስፔክተር ስጦታው አሽከርካሪው ግን በፍጥነት በማሽከርከር ለማምለጥ ጥረት ሲያደርግ መንገድ ዳር ቆሞ ከነበረ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3A- 60203 አ.አ ከሆነ አይሱዙ ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨቱ ህይወቱ ማለፉን ተናግረዋል፡፡ በወቅቱ አብረውት ተሳፍረው የነበሩ 2 ግለሰቦች ላይም ከባድ የአካል ጉዳት በመድረሱ ተጎጂዎቹ በህክምና ላይ እንደሚገኙ ምክትል ኢንስፔክተር ስጦታው ወልዴ አስረድተዋል፡፡

via ዘገባ፡- ም/ኢንስፔክተር እመቤት ሃብታሙ
ፎቶ ግራፍ፡- የአዲስ አበባ ፖሊስ ፎረንሲክ ማስረጃ አሰባሰብ ም/ዳይሬክቶ


የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://www.youtube.com/channel/UCpOINfXANvOHa0oHCkq5gog

27/05/2022



የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝደንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጂ ኡመር እድሪስ በወቅታዊ የምክር ቤቱ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ እየሰጡ ነው

*** ስለድምጽ ጥራቱ ይቅርታ እየጠየቅን ጥራት ያለውን ቪዲዩ ዩቱዩብ ቻናላችን ላይ ያገኙታል


የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://www.youtube.com/channel/UCpOINfXANvOHa0oHCkq5gog

  ሞስኮን ከጉባ ያገናኘው የዋሽንግተን ሴራየሩሲያ ዩክሬይን ጦርነት በግድባችን ጉዳይ ይመጣል የሚል ግምት ይኖር ዘንድ መጠበቅ ላያስፈልገን ይችል ይሆናል። ዛሬ ላይ ሆነን፤ ያኔ ሩሲያ ወታደራ...
27/05/2022


ሞስኮን ከጉባ ያገናኘው የዋሽንግተን ሴራ

የሩሲያ ዩክሬይን ጦርነት በግድባችን ጉዳይ ይመጣል የሚል ግምት ይኖር ዘንድ መጠበቅ ላያስፈልገን ይችል ይሆናል። ዛሬ ላይ ሆነን፤ ያኔ ሩሲያ ወታደራዊ ዘመቻዋን በዩክሬይን በጀመረችበት ወቅት "አርፋችሁ ተቀመጡ" የሚሉ ድምፆች እዚሁ ከሚገኙ ዜጎች ሲወረወሩ ነበር። ያንን ብልጣብልጥ የተኩላ ምክር ዛሬ ላይ በትውስታ ብቻ የምናነሳው አይደለም። ይልቁንም "ልሙጥ ገለልተኛ ሁኑ" ሲሉን ከነበሩት ውስጥ የተወሰኑት አንድም አስበውበት/ሲቀጥልም ተልእኮ ተቀብለው እንደነበር ማሳያዎች ወገግ ይሉ ጀምረዋል። ዜጎች በማህበራዊ ሚዲያ የሚያንፀባርቁትን አተያይ/opinion ምእራባዊያን በዚህ ደረጃ ዋጋ ሰጥተው ባንዳ ለማሰማራት ያበቃቸዋል ወይ? የሚል ጠያቂ እንደማይኖር ልገምት። ድንገት ከመጣም ጥያቄውን በጥያቄ ለመመለስ "የዲጂታል ዘመቻን እየመረጡ ሲያፍኑ ኢትዮጵያዊ ድምፆች ላይ ብሎም የሩሲያ ደጋፊ ሀሳቦችን ጭምር መሆኑ ከምን የመነጨ ይመስልሃል?" ብቻ ማለት በቂ ነው።

የታላቁ ህዳሴ ግድብ አለመግባባትን ለመፍታት ሶስቱ ሀገራት ኢትዮጵያ ግብፅ እና ሱዳን ላለፉት ሁለት ወራት በአቡዳቢ ድርድር ሲያደርጉ መቆየታቸው ተሰምቷል። ስለዚሁ ጉዳይ ከወራት በፊት የወጡ ዘገባዎችን ማጋራቴ ይታወሳል። በወቅቱ ይህን የኤምሬትስ የሶስትዮሽ ኢኒሼቲቭ ሱዳን እንጂ ካይሮ አሻፈረኝ ማለቷ ነበር የተዘገበው። የማታ ማታ ግን የአቡዳቢም ጥያቄ ተቀብላ እድሏን ስትሞክር መቆየቷ አሁን ላይ ይፋ ሆኗል።

የግብፅ ብዙሃን መገናኛ የሆነው ማርሳድ እንዲሁም አልአረቢ የተለያዩ ባለስልጣናትን በማነጋገር ባቀረቡት ሪፖርት መሰረት በአቡዳቢ ሸምጋይነት በህዳሴ ግድቡ ቴክኒካል ጉዳዮች ላይ ያተኮረው ድርድር ያለ ስምምነት ተቋጭቷል ነው ያለው።

አልአረቢ ከግብፅ ዲፕሎማቲክ ምንጮቼ የሰማሁት ነው በማለት እንዳስነበበው ሲል የካይሮ ልዑካን በአቡዳቢ ቆይታቸው የተለመደውን አስገዳጅ ስምምነት ኢትዮጵያ ትፈርም ዘንድ ሲሞግቱ ነበር። ይሁንና በሁለት ዙር ሁለት ወራት ውስጥ በተካሄደው ድርድር ኢትዮጵያ የግብፅን ጥያቄ አሁንም ውድቅ አድርጋለች። ከዚህ ባሻገርም ግብፅ ስለ ግድቡ ሙሊት መረጃ ከኢትዮጵያ ይደርሳት ዘንድ ጠይቃ ነበር። በተጨማሪም የግድቡን ሙሉ ዲዛይን በማቅረብ ስለ ግድቡ ደህንነት ለመምከር አጀንዳ አስይዛ ነበር። ይሁንና ኢትዮጵያ ስለ ሶስተኛው ዙር ሙሊት ብቻ መረጃ እንደምትሰጣቸው መግለጿ ተዘግቧል። በተረፈ በግድቡ ደህንነትም ሆነ ዲዛይኑን በተመለከተ መረጃ እንደማትሰጥ ለግብፅ ልኡካን አስረግጣለች ነው የተባለው።

የአቡዳቢው የድርድር ሂደት በተመለከተ ካይሮ ለዋሽንግተን ማብራሪያ እግር በእግር ስታደርስ መቆየቷን ያስነበቡት አልአረቢ እና ማርሳድ የአቡዳቢው ድርድር ባለመስማማት መቋጨቱን ተከትሎ ግብፅ ለዋሽንግተን ባለስልጣናት አቤቱታቸውን ማሰማታቸው ነው የተነገረው።
በዚህም የአሜሪካ ብሔራዊ ደህንነት አማካሪ ለሆኑት ጃክ ሱሊቫን በቅርቡ ማለትም ግንቦት 11 2022 ካይሮን በጎበኙበት ወቅት ፕሬዚዳንት አልሲሲ በቀጣይ ሰኔ አጋማሽ ይቀጥላል በተባለው ሶስተኛ ዙር የአቡዳቢ ድርድር ላይ ኢትዮጵያ ግትር አቋሟን እንድትቀይር ብሎም አስገዳጅ ስምምነት እንድትፈርም ዋሺንግተን ከፍ ያለ ጫና ታደርግ ዘንድ መጠየቃቸው ተነግሯል። በምላሹ ጃክ ሱሊቫን ግብፅ በግድቡ ድርድር የጠየቀችውን ፍላጎቷን ዋሽንግተን ትረዳት ዘንድ ከሩሲያ ጋር ያላትን ግንኙነት እንደገና መከለስ አለባት ብለዋቸዋል።
በነገራችን ላይ ግብፅ በሩሲያ ዩክሬይን ጉዳይ ወደ አሜሪካ በተወሰነ ደረጃ ደግሞ ገለልተኛ ለመምሰል የሞከረ አቋም ስታሳይ እንደነበር ይታወሳል። በሌላ በኩል ባለፈው ክረምት የፀጥታው ምክር ቤት በታላቁ ህዳሴ ግድብ አጀንዳ ባካሄደው ጉባኤ ሩሲያ ኢትዮጵያን በመደገፏ ካይሮ ከሞስኮ የነበራትን የኑክሌር ልማት ስምምነት እንዲቋረጥ ማድረጓም አይዘነጋም። ይሁንና ካይሮ ከሩሲያ የጀመረችውን የኑክሌር ግንባታ ለመቀጠል ከወር በፊት በሚያዚያ ወር ምክክር ያደረገችው በዩክሬይኑ ቀውስ መሀል መሆኑ እዚጋ ታሳቢ ይሆናል።

ዋሽንግተን የዩክሬይኑን ካርታ በህዳሴ ግድቡ በኩል ካይሮን ልታጫውታት በሞከረችበት "የማይከበር ቃል ኪዳኗ" ተከታዩን የሞት አማራጭ ነበር ግብፅ እንድትቀበል የጠየቀችው። ይኸውም የደህንነት አማካሪው ጄክ ሱሊቫን "ካይሮ ከሞስኮ ያላትን ዘርፈ ብዙ ግንኙነት ማቋረጥና ሩሲያ በዩክሬይን የምታደርገውን ዘመቻ አውግዛ የአሜሪካን አቋም ሙሉ በሙሉ መደገፍ አለባት።" ሲሉ ለአልሲሲ መናገራቸውን የግብፁ የመረጃ ምንጭ አስፍሯል።

via እስሌማን ዓባይ የዓባይልጅ


የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://www.youtube.com/channel/UCpOINfXANvOHa0oHCkq5gog

 ’’ወደ ሰላም መምጣት ከሚፈልግ አካል ጋር ለመስራት ዝግጁ ነኝ’’ ጃዋርአቶ ጃዋር መሀመድ (የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ምክትል ሊቀመንበር) ከእስር ከተፈቱ በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ " ኡቡንቱ...
26/05/2022



’’ወደ ሰላም መምጣት ከሚፈልግ አካል ጋር ለመስራት ዝግጁ ነኝ’’ ጃዋር

አቶ ጃዋር መሀመድ (የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ምክትል ሊቀመንበር) ከእስር ከተፈቱ በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ " ኡቡንቱ ቲቪ " ለተሰኘ የማህበራዊ መገናኛ Exclusive ቃለ ምልልስ ሰጥተዋል።

በዚሁ ቃለ ምምልስ ወቅት አቶ ጃዋር ከተጠየቁት ጥያቄዎች አንዱ እሳቸውን በተመለከተ ሲናፈሱ የነበሩ አሉባልታዎችን እንዲያጠሩ ነው " አቶ ጃዋር ከገዢው ፓርቲ ጋር መስራት ጀምሯል፣ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ተገናኝቷል የተፈታውም ለዚህ ነው ፤ አሁንም እየሰራ ያለው የመንግስትን ስራ ነው " ስለሚባሉት ጉዳዮች ግልፅ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
አቶ ጃዋር መሀመድ ፦

" እኔም ሰማቸዋለሁ አሉባልታዎቹን ። እኔ ከማንም ጋር የግል ቁርሾ የለኝም። የታሰርኩትም ቢሆን በፖለቲካ ልዩነት እንጂ በግል ፀብ አይደለም። ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር አልተገናኘንም፤ ሊያገኘኝ ከፈለገ ግን ሁሌም ዝግጁ ነኝ። ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ብቻ ሳይሆን / ከዐቢይ ጋር ብቻ ሳይሆን ከመሮም ጋር፣ ከደብረፅዮንም ጋር ከሁሉም በአሁን ወቅት በሀገራችን ባለው ግጭት ውስጥ እየተሳተፉ ካሉ ኃይሎች ጋር ተገናኝቶ ሀገራችንን ከጦርነት አስወጥቶ ወደ ሰላም እና ልማት ለመመለስ እድሉ ከተገኘ ከማናቸውም ጋር ለመስራት፣ ከማናቸውም ጋር ለመተባበር ፣ ከማናቸውም ጋር ለመነጋገር በማንኛውም ቦታ እና ሁኔታ ለመነጋገር ዝግጁ ነኝ።
እኔ ማልፈቅደው ግን ከማናቸውም ጋር አብሬ ጦርነት ማፋፋም አልፈልግም፤ ከማናቸውም ጋር።

ሁሉም በጦርነት ውስጥ እየተሳተፉ ያሉ ይሁኑ በጦርነት ውስጥ ያልተሳተፉ ያሉ ምሁራን እና ሊህቃን ወደ ሰላም ጠረጴዛ መምጣት አለባቸው ብዬ አምናለሁ፤ ከአንዳቸውም ጋር ግላዊ ጠብ የለኝም። ስለዚህ ገዥው ፓርቲ ሀገር እየገዛ ነው ያለው ፤ ሀገር እያስተዳደረ ነው ያለው ፣ ሀገሪቷ ለገባችበት ችግር ትልቁን ድርሻ የሚወስደው ገዢው ፓርቲ ነው፤ እንደመሪም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ነው ፤ ወደ መፍትሄ የምንገባ ከሆነ የእነሱ ተሳትፎ፣ የእነሱ ፍቃደኝነት ወሳኝ ነው።
ስለዚህ እንደ ፖለቲካ ፓርቲ አመራርም እንደ እዚህች ሀገር ዜጋም በሰላም ጉዳይ ላይ የሀገራችንን እጣፈንታ ወደፊት ማስተካከል ላይ ከገዢው ፓርቲም ጋር ሆነ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ሆነ፣ የተለያዩ ድርጅቶች ከሚመሩ ቅድም እንዳልኩት ከደብረፅዮን ሆነ ፣ ከፃድቃን ሆነ፣ ከመሮም ሆነ፣ ከገመቹ ሆነ፣ ከተፈራ ማሞ ሆነ ፣ ከይልቃል ከፋለ ጋርም ሆነ ከማንኛውም ጋር ለመስራት ዝግጁ ነኝ፤ የሀገራችን አመራርም ለዚህ መዘጋጀት መቻል አለበት።

ሀገራችን ያለችበት ሁኔታ ለምን ከእከሌ ጋር ተነጋገርክ፣ እከሌ ሳይጣን ነው እከሌ መልአክ ነው በማለት እንደማያዋጣ ላለፉት 4 ፣ ላለፉት 2 ዓመታት ግልፅ ሆኗል። ስለዚህ አሁንም ደግሜ የምለው ከማንኛውም የፖለቲካ ኃይል ጋር ፣ ከማንኛውም የፖለቲካ አመራር ጋር ህዝባችንን አሁን ከገባበት መቀመቅ እና ሰቆቃ ለማውጣት መስራት ያስፈልጋል።

እዚህ ላይ ግልፅ ማድረግ የምፈልገው ከማንኛውም ኃይል ጋር እንሰራለን እንደ ድርጅትም እንደ ግለሰብም እንደ አመራርም፤ ሀገራችንን እና ህዝባችንን ወደ ሰላም መንገድ ወደ ልማት እንዲመለሱ ባለኝ እውቀት እና ባለኝ ተሰሚነት መጥቀም እፈልጋለሁ። ነገር ግን ለማንም ድርጅት ሆነ ግለሰብ መጠቀሚያ መሆን አልፈልግም ፤ ለማንም የጦር ማገዶ መሆን አልፈልግም ፣ የማንንም አንባገነናዊ አካሄድን፤ የማንም ጦረኛ አካሄድን መደገፍ አልፈልግም።

ወደ ሰላም መምጣት ከሚፈልግ አካል ጋር ለመስራት ዝግጁ ነኝ፣ ይሄ ደግሞ ኩነኔ አይደለም ይሄ ትክክለኛ ነው ብዬ የማምነው ፤ ስለዚህ ጦርነቱ መቆም አለበት ጦርነት ቆሞ ወደ ድርድር መምጣት አለብን ቴክኒካል ነገሮች መነሳት አለባቸው ስለዚህ ለመነጋገር ጋሬጣ ሆነው ያሉ ነገሮች ተሰባብረው ድልድይ ተመስርቶ ሁላችንም ወደመነጋገር መግባት አስፈላጊ ነው። "
via (ከቲክቫህ ኢትዮጵያ)


የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://www.youtube.com/channel/UCpOINfXANvOHa0oHCkq5gog

 ወ/ሮ እቴነሽ ከአቶ ታደሰ የተበደሩትን 600 መቶ ሺ ብር ሳይከፍሉ ከዚህ ዓለም በሞት ይለያሉ፡፡ ይህንን ተከትሎ የወ/ሮ እቴነሽ ወራሾች የእናታቸውን ንብረት አጣርተው የውርሱን ሀብት ሲከፋ...
25/05/2022



ወ/ሮ እቴነሽ ከአቶ ታደሰ የተበደሩትን 600 መቶ ሺ ብር ሳይከፍሉ ከዚህ ዓለም በሞት ይለያሉ፡፡ ይህንን ተከትሎ የወ/ሮ እቴነሽ ወራሾች የእናታቸውን ንብረት አጣርተው የውርሱን ሀብት ሲከፋፈሉ አቶ ታደሰ ሀገር ውስጥ ስላልነበር ወ/ሮ እቴነሽ ማረፋቸውን አላወቀም ነበር፡፡ ይሁን እንጂ አቶ ታደሰ ከውጭ ሀገር ሲመለስ ወ/ሮ እቴነሽ ማረፋቸውን ስለተረዳ ሟች የተበደሩትን 600 መቶ ሺ ብር ወራሾች ከእነወለዱ እንዲከፍሉት ይጠይቃቸዋል፡፡ ወራሾች በበኩላቸው የውርሱን ሀብት አጣርተን በፍ/ቤት አፀድቀን ንብረት የተከፋፈልን በመሆኑ ወ/ሮ እቴነሽ የተበደሩትን 600 መቶ ሺ ብር እንድንከፍል አንገደድም በማለት ይመልሱለታል፡፡
ጥያቄ
የአቶ ታደሰ እጣ ፈንታ ምንድን ነው ? ፤ ወራሾችስ እዳውን እንዲከፍሉ በሕግ ይገደዱ ይሆን?

via Legal service

የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://www.youtube.com/channel/UCpOINfXANvOHa0oHCkq5gog

 በኢትዮጵያ ውስጥ አሁን በእርግጠኝነት መናገር የሚቻለው ከዚህ በፊት አይታው የማታውቀው ግዙፍ ሀያል ዘመናዊ ጦር እየተገነባ ነው ። በስሜት ሳይሆን በስሌት ፤ በጀብደኝነት ሳይሆን በሳይንስ ...
25/05/2022



በኢትዮጵያ ውስጥ አሁን በእርግጠኝነት መናገር የሚቻለው ከዚህ በፊት አይታው የማታውቀው ግዙፍ ሀያል ዘመናዊ ጦር እየተገነባ ነው ። በስሜት ሳይሆን በስሌት ፤ በጀብደኝነት ሳይሆን በሳይንስ እየታነፀ እየተገነባ ያለ ግዙፍ ጦር አለ !

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድና አመራራቸው የሀገሪቱን ጦር ለማዘመን የሄዱበት እርቀት አስደማሚ ነው ። አዎ ኢትዮጵያ ከዚህ በሗላ የማንም ውርጋጥ እየተነሳ የሚደፍራት ሀገር አትሆንም !!

የኢትዮጵያ ጦር ከ 50,000 አይበልጥም ብለው በህዝባዊ ማእበል ጦርነት የከፈተው ህወሃት እና አጋሩ ሸኔ አሁን አከርካሪያቸው ተመቶ አሁን ጉልበታቸውን ብርክ ይዞታል ። ህወሃት አሁን የሚፈነጭበትን ጊዜ ሳይሆን የሚጠፋበትን ወቅት የሚጠባበቅ ቀቢፀ ተስፋ ሆኗል ። ምክንያቱም አሁን ከፊት ለፊቱ ያለው ቁጥሩ ከግማሽ ሚሊዮን የሚልቀው ከታጠቀው መሳሪያ በላይ ወኔው የሚያርበደብደው ጀግናው የመከላከያ ሰራዊታችን ነው ።

የኢትዮጵያ ጦር ግንባታ በዚህ ፍጥነት ከቀጠለ በቅርብ አመት ውስጥ የአፍሪካ ሀያሉ አስፈሪው ጦር እንደሚሆን አያጠራጥርም ። ሱዳንን የመሰሉ ደካሞች ይቅርና ሱዳንን የሚልኳት ላኪዎቿን ሳይቀር የሚያስፈራ ጦር ይኖረናል !! ክብር ለጀግናው መከላከያ ሀይላችን !!!

via Seid_Mohammed_Alhabeshiy

የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://www.youtube.com/channel/UCpOINfXANvOHa0oHCkq5gog

 ”በኤርትራ በኩል የባህር በር ማስከፈት !”ሁሉም በሮቹ ተዘጋግተውበት ያደረጋቸው ሁሉ ሙከራዎች ከሽፈውበት ወደ መመሸጊያው አኮብሽሾ የተመለሰው ህወሃት አሁን የመጨረሻ አማራጭ ያለውን የጦር ...
25/05/2022



”በኤርትራ በኩል የባህር በር ማስከፈት !”

ሁሉም በሮቹ ተዘጋግተውበት ያደረጋቸው ሁሉ ሙከራዎች ከሽፈውበት ወደ መመሸጊያው አኮብሽሾ የተመለሰው ህወሃት አሁን የመጨረሻ አማራጭ ያለውን የጦር ግንባር ሊከፍት ተዘጋጅቷል - በኤርትራ ላይ !

ህወሃት ይህን የሚያደርገው የኤርትራን የተወሰኑ ግዛቶች በመቆጣጠር ከቀይ ባህር ጋር የሚያገናኝ ቀዳዳ ለማግኘት ነው ። ያንን ማሳካት ከቻለ ከ 360 ዲግሪ ከበባ በመውጣት ከአለምአቀፍ ረዳቶቹና ጌቶቹ ጋር በቀጥታ ይገናኛል ማለት ነው ። ለዚህም ሲል አብዛኛውን ጦሩን ወደ ኤርትራ ድንበር አስጠግቶ እያሟሟቀ ይገኛል ።

ህወሃት ከከበባ የመውጫ መንገድ ለማግኘት ያላደረገው ሙከራ አልነበረም ። ሁሉም ልፋቶቹ በኢትዮጵያ ጦር ከሽፎበታል ። በሱዳን ድንበር በኩል ለማስከፈት ያደረገው ጦርነት በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ወጣቶችን ከማስፈጀት ውጭ ያሳካው ነገር አልነበረም ። የምእራቡ ግንባር ከተደጋጋሚ ሙከራ በሗላ አልሳካለት ሲል ተስፋ የቆረጠው የትግራይ ወራሪ ፊቱን ወደ ምስራቅ በማዞር ሚሌን የማስከፈት የሞት ሽረት ጦርነት አወጀ ። ግና አናብስቶቹ የአፋር አርበኞች ከጀግናው መከላከያ ሰራዊት ጎን በመሆን የአፋር በረሃ ሲሳይ አድርገው አስቀሩት ።
በምስራቁም በምእራቡም ሲከሽፍበት የመጨረሻ አማራጭ ያለው ወደ አዲስ አበባ መትመም ነበር ። እርሱም የህልም ቅዠት ሆኖበት ቀረ ። በወሎና በአፋር ግንባር ብቻ ከ 300,000 በላይ ወጣቶችን አስረግፎ መቶ ሺህ ቁስለኞችን ተሸክሞ ወደ መጣበት ተመለሰ ። ግና ህወሃት ካለ ጦርነት መኖር አይችልምና ዙሪያውን ታፍኖ ከመሳሪያ አቅርቦትም ታግዶ እየመነመነ ነውና ሌላ የጦርነት ግንባር ፈጥሮ የከፈለውን መስዋእትነት ከፍሎ በቀይ ባህር ሊዘልቅ አስቧል ።
ህወሃት ቀይ ባህርን ለማግኘት መቶ ኪሎሜትሮችን ብቻ መቆጣጠር ብቻ ነው የሚጠበቅበት ። ግና የኤርትራ ጦር ለህወሃት ጦር ይንበረከካል ግዛቶቹንስ ያስወስዳል ነው ወይ ነው ጥያቄው ።

ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ይህንን የህወሃትን አላማ ከተናገሩ በሗላ " ህወሃት ጦሩን ኤርትራ ውስጥ ካስገባ መቀበሪያ አዘጋጅተን እንጠብቀዋለን " ብለዋል ። የኤርትራ ጦር ህወሃትን ጦርነት ከከፈተ ከነዘላለሙ ለማጥፈት በሙሉ ዝግጁነት ላይ መሆኑን ነው ኢሳያስ የተናገሩት ።
አዎ ቀጣይ የጦርነቱ ግንባር ወደ ኤርትራ መሆኑ የሚቀር አይመስለም ። ሻእቢያና ህወሃት መታኮስ ከጀመሩ ሳምንት አለፋቸው ። በሻእቢያና በህወሃት መካከል በሚደረገው ጦርነት የኢትዮጵያ ጦር ሚና ምን ይሆናል የሚለውም በከፍተኛው ትኩረትን የሚስብ ጉዳይ ነው ።

via Seid_Mohammed_Alhabeshiy


የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://www.youtube.com/channel/UCpOINfXANvOHa0oHCkq5gog

 በቆቦ ከተማ ከሦስት ሚሊየን ብር በላይ በቁጥጥር ስር ማዋሉን ፓሊስ አሰታወቀ ***********በቆቦ ከተማ ከሦስት ሚሊየን ብር በላይ በቆቦ ከተማ ህዝብ፣በከተማው ፓሊስና ሕዝባዊ ሚሊሻ ሰራ...
24/05/2022



በቆቦ ከተማ ከሦስት ሚሊየን ብር በላይ በቁጥጥር ስር ማዋሉን ፓሊስ አሰታወቀ
***********
በቆቦ ከተማ ከሦስት ሚሊየን ብር በላይ በቆቦ ከተማ ህዝብ፣በከተማው ፓሊስና ሕዝባዊ ሚሊሻ ሰራዊት አማካኝነት በቁጥጥር ስር ውሏል።
የከተማ አስተዳደሩ ፓሊስ ፅ /ቤት ኃላፊ ኮማንደር ታደሰ ተሰሜ እንደገለጹት ጋሪው የተሰራው ሙሉ በሙሉ ውስጡ ክፍት በሆነ ቁሳቁስ ሲሆን ስም የተፃፈበት ብር በእያንዳንዱ ብረት ውስጥ አድርገው ይዘው ለማለፍ ሞክረዋል።
የተጠቀሙበት መንገድ ያልተጠበቀ ቢሆንም የቆቦ ከተማ ህዝብና የፀጥታ አካሉ በመተባበር መያዝ ተችሏል።
የቆቦ ከተማ አስተዳደር ሠላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ሀምሳ አለቃ አበበ ደርሶ በበኩላቸው የውስጥ ባንዳዎችን በመጠቀም ወገናቸውን አሳልፎ እንዲሰጡ ቢደረግም በሁሉም የፀጥታ ኃይል አማካኝነት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የክልሉ ኮሙዩኒኬሽ መረጃ ያመለክታል።


የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://www.youtube.com/channel/UCpOINfXANvOHa0oHCkq5gog

  የአውሮፓ ህብረት አዲሱ አጀንዳ አውሮፓ ሕብረት አዲስ በጦር ወንጀል የተሳተፉ ሀይሎችን ለህግ እንዲያቀርብ መንግስትን ጠይቋል። ለመንግሥት ማንኛውን ወገን ለፍርድ አቅርብ እንዳለው ምናልባት...
23/05/2022



የአውሮፓ ህብረት አዲሱ አጀንዳ
አውሮፓ ሕብረት አዲስ በጦር ወንጀል የተሳተፉ ሀይሎችን ለህግ እንዲያቀርብ መንግስትን ጠይቋል። ለመንግሥት ማንኛውን ወገን ለፍርድ አቅርብ እንዳለው ምናልባትም ሊያውቀው ወይም ልክ እንደኔ ቢጤዎቻችን ግራ ሊያጋባው ይችላል።
አውሮፓ ሕብረት ለፍርድ ይቅረቡ የሚለውን የመንግስት ወታደሮችን ነው። አንድም የአማራ ሀይል የሚባሉትን ሁለትም መከላከያ ስራዊት ውስጥ ያሉ ህወሓት ጠላት ናቸው ብሎ ፅፎ የሰጣቸውን ሰዎች ነው። መንግስት ነገሩን እንደወረደ ተቀብሎ በሚዲያ ዜና ሰራው እንጅ ይህ መርዛማ ድርጅት እንዴት ይሄንን አለ. ለምንስ ይችን አጀንዳ መዞ ሰጠን አላለም። ይሄንን ያልኩበት መንግስት ለጉዳዩ እስካሁን ማብራሪያ ስላልሰጠበት ነበር። ቢሰጥበት የመንግስትን አቋምና የምዕራባውያንን ፍላጎት ለማየት አንቸገርም ነበር፣ (ከፖለቲካ አንፃር )
አውሮፓ ህብረት እስካሁን ድረስ ከህወሓት ጎን እንደተሰለፈ ነው። ምንም እንኳን የሀይል ሚዛኑን እያየ ቢራመድና የዩክሬን ጉዳዩ ለህወሓት ያለውን ትኩረት ቢነፍገውም ህብረቱ እስካሁን ድረስ አቋሙ አንድ ነው።
በወልቃይት በኩል የተጨፈጨፉት አማሮች መሉ በመሉ የትግራይ ተወላጆች ብቻ ናቸው ብሎ ነው የሚያምነው። ይህ ከህወሓት ያገኘው ጥቅም ወይም የገባችለት ቃል ስላለ የሟቾችን አስክሬን ረግጦ ለህወሓት ያዳላ አቋም ይዟል። ህወሓት ኤርትራን ለመውረር ሞክራ ክፉኛ ከተደቀሶች በኋላ ነገሮች የመቀያየር ባህሪ አምጥተዋል።

የትግራይ ቴሌቪዥን በዚህ ሦስት ቀን ውስጥ የኢትዮጵያ አንድነት እንዲጠበቅ ከተፈለገ ሁሉንም ያሳተፈ ውይይት መረደግ አለበት የሚል ሀሽታግ ጀምሯል። ከእንገነጠላለን ወደ ውይይት መር የተመለሱት በኤርትራ ድብደባ ልባቸው ድንጋጤ ላይ ስላለ አማራጭ እየፈለጉ ነው። ይህ የህወሓት አቋም ለአፍሪካ ህብረትና ለአረብ ሊግ በደብዳቤ ተልኳል።
አውሮፓ ህብረት ከላይ ወደታች የወረደባቸውን እያንዳዱ ንግግሮቾ ህወሓትን እንዴት እንታደግ ከሚል የሚመነጭ ሀሳብ ነው። የጨመረው ያለውን አንድ ሴራ በቅርብ ቀን ለአለም ህዝብ ይፋ ያደርጋል። እሱም በወልቃይት በኩል የሰላም አስከባሪ ይግባ የሚል ነው። ሂዊ ይሄንን ማሳካት ከቻለች ትልቅ ነጥብ ጥላ ጦርነቱን በበላይነት አጠናቀቀች ማለት ነው። አሁን ሂዊ የሰላም ሰበካ ላይ ናት። ማረኳቸው የምትላቸው የመከላከያ ስራዊት አባሎችን መለሰች። ሁሉንም አካታች ድርድር ይከፈትልኝ አለች።

ከዚህ ቀጥላ በሰላም ፈላጊ ስም ወደ ወልቃይትን ለምዕራባውያን ሰጥታ የሱዳኑን ቦርደር ለመጠቀም ያስችላታል። ይህ ሂዊም የአውሮፓ ህብረትም የጋራ አጀንዳቸው ነው። በቀጣይ ቀናቶች የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ይመክራል። ሂዊም ይሄንን እድል ለመጠቀም ፍፁም ስሙን ጠርታ የማታውቀውን ፈጣሪዋን እየለመነች ማስቸገር ይዘዋለች። መቸም (ዋቃ) ለህወሓት የሚያዝን የምህረት ምዕራፍ ይኖረዋል ብየ አልገምትም። ያው እሱ ያቃል እንጅ !

via Abay News Network


የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ

https://www.youtube.com/channel/UCpOINfXANvOHa0oHCkq5gog

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gofer TUBE posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Gofer TUBE:

Videos

Share