Ethio Today

Ethio Today Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Ethio Today, Media/News Company, .

 #ትግራይበትግራይ ያለው ድርቅ . . ." ከ1977 የባሰ ጊዜ መጣብን፤ ...መሬት እህል አላበቅል አለ  "እናት  #1፦ " ችግር በዛብኝ ፤ እራሴም እየዞረብኝ ነው። እግሬንም ማንቀሳቀስ አ...
17/12/2023

#ትግራይ

በትግራይ ያለው ድርቅ . . .

" ከ1977 የባሰ ጊዜ መጣብን፤ ...መሬት እህል አላበቅል አለ "

እናት #1፦ " ችግር በዛብኝ ፤ እራሴም እየዞረብኝ ነው። እግሬንም ማንቀሳቀስ አቅቶኛል። ልቤም እየደከመብኝ ነው። በረሃብ በችግር ምክንያት ነው እንዲህ የሆንኩት። "

እናት #2 ፦ " የዘራነው እህል ዝናብ ባለመኖሩ አሯል። በዚህ ምክንያት ተርበናል። እህቴም ሁለት ልጆቿን የምታበላቸው አጥታ ቆሎ ስታገኝ የእናት ነገር ሆኖባት ለራሷ ሳትበላ ለእነሱ እያካፈለች በረሃብ በቤቷ ደርቃ ነው የተገኘችው። እኔም አሁን የምበላው የለኝም ረሃብ ሲበረታብኝ ወደ ጎረቤት ሄጄ ቡናም ካገኘው እሱን ጠጥቼ ውላለሁ። "

እናት #3 ፦ " የ2 ዓመት ከ4 ወር መንታ ልጆችን ይዤ በረሃብ ተሰቃይቼ ነው ያለሁት። ለራሴ ተሰቃይቼ ልጆቹንም አሰቃየዋቸው። የምበላው አጥቼ ፆሜን ነው ተደፍቼ የማድረው። ለምኜ እንዳልበላ ልመናው የለም። ልጆቼ ጡቴን ሲጠቡኝ ልቤን ያንሰለስለኝና ያመኛል። ለሊቱን ሙሉ ሳቃስት ነው የማድረው። "

እናት #4 ፦ " ልጄ 8 አመቱ ነው ዘንድሮ ሁለተኛ ክፍል ጨርሶ ወደ 3ኛ ክፍል ያልፍ ነበር አሁን ግን ባጋጠመን ድርቅ ተቸግረን ትምህርቱን መማር አልቻለም። በጣም ተርበናል። ልጆቻንን ካገኙ ይበላሉ ካልሆነም ውሃ ጠጥተው ይውላሉ። በረሃብ ተሰቃየን። "

ድርቅ ባመጣው ረሃብ ምክንያት ተማሪዎችም ከትምህርት ገበታቸው ቀርተዋል።

ተማሪዎች ደብተርና እስክሪብቶ የሚገዛላቸው ስላጡ ወደ ትምህርት ቤት መሄድ አቁመዋል።

ወላጆች አይደለም ለእነሱ የትምህርት ቁሳቁስ ለማሟላትና ሊያስተምሯቸው ለሆዳቸውም መሆን አቅቷቸዋል። ከባድ ችግር ላይ ናቸው።

በድርቅ የተጠቁ ወገኖች ለረሃብ ማስታገሻ ከመሬት ስር እና ከእፀዋት ፍራፍሬ በመልቀም ህይወታቸውን ለማቆየት ሲጥሩም ተስተውሏል።

እናት ፦ " ልጆችን የማበላቸው አጥቼ ጨንቆኝ ለለቀማ ኑ እንሂድ ብያቸው በረሃብ ምክንያት ከትምህርት ቀርተዋል። ትንፋሻችንን ለማቆየት ኩዕንቲ እየለቀም ነው የምንበላው። መሬት እህል አላበቅል አለ፤ እንኳን እህል ኩዕንቲ አላበቅል አለ። ከ1977 የባሰ ጊዜ መጣብን፤ በረሃብ ምክንያት ልጆቼ ቤት ውስጥ ታጥፈው እየዋሉ ነው። "

እናት ፦ " ይህ መሬት ጤፍ ያበቅል ነበር አሁን ግን ጊዜ ከዳን "

እናት ፦ " ጠኔና ረሃብ ካጋጠመን በኃላ ከፍተኛ ችግር ላይ ነው ያለነው። ኩዕንቲ እንኳን የሚለቅመው አይኑ በደንብ የሚያይ ነው። ይህን ለመብላትም ጥርስ ያስፈልጋል። "

ድርቁ ሰው ላይ እያደረሰ ካለው ጉዳት በተጨማሪ እንስሳት የሚበሉትን አጥተው እየሞቱ ነው።

በትግራይ ውስጥ የነበረው ደም አፋሳሽ አስከፊ ጦርነት ፣ በክረምቱ ዝናብ አለመኖር፣ ወቅቱን ያልጠበቀው ዝናብ፣ እንዲሁም የአንበጣ መንጋ ተዳምሮ ህዝቡን የከፋ ችግር ላይ ጥሎታል።

እንደ ክልሉ አስተዳደር መረጃ ከሆነ 2 ሚሊዮን ሰው ለረሃብ ተጋልጧል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የነዋሪዎችን ቃል ያዳመጠው ከክልሉ ቴሌቪዥን ጣቢያ ነው።

Today

ዛሬ " ገርቢ " ላይ በደረሰ የመኪና አደጋ የ7 ሰዎች ህይወት አለፈ።በምስራቅ ሸዋ ዞን ፤ በአዳሚ ቱሉ ወረዳ  ውስጥ በደረሰ የመኪና አደጋ የ7 ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡አደጋው የደረሰው ከአዳ...
20/10/2023

ዛሬ " ገርቢ " ላይ በደረሰ የመኪና አደጋ የ7 ሰዎች ህይወት አለፈ።

በምስራቅ ሸዋ ዞን ፤ በአዳሚ ቱሉ ወረዳ ውስጥ በደረሰ የመኪና አደጋ የ7 ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡

አደጋው የደረሰው ከአዳሚ ቱሉ ወረዳ ወደ #ባቱ ከተማ ሲጓዝ የነበረ ዳማስ ተሽከርካሪ እና በተቃራኒ አቅጣጫ ሲጓዝ የነበረ ቶዮታ ቪ ኤይት (v8) መኪና " ገርቢ " ተብሎ በሚጠራ አካባቢ በመጋጨታቸው ነው።

በአደጋው 4 ሰዎች ወዲያው ሕይወታቸው ሲያልፍ 3 ሰዎች የህክምና ተቋም ከደረሱ በኋላ ሕይወታቸው አልፏል። በአጠቃላይ በአደጋው 7 ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡

ሌሎች በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ኤፍ ቢ ሲ የባቱ ኮሚኒኬሽንን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።

(የአደጋውን ሁኔታ የሚያሳየውን ተንቀሳቃሽ ምስል የላከልን ሣሚ ተስፋዬ የሚባል የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ነው)

Today

በጎርፍ የተወሰዱ 2 ሴቶች አስክሬን ተገኘ   | ትላንት ምሽት 3:00  ሰዓት ጀምሮ ሲጥል የነበረዉን ዝናብ ተከትሎ በተፈጠረ ጎርፍ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ዳርፉር ወንዝ አካባቢ ይኖሩ...
15/09/2023

በጎርፍ የተወሰዱ 2 ሴቶች አስክሬን ተገኘ

| ትላንት ምሽት 3:00 ሰዓት ጀምሮ ሲጥል የነበረዉን ዝናብ ተከትሎ በተፈጠረ ጎርፍ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ዳርፉር ወንዝ አካባቢ ይኖሩ የነበሩ ሁለት ሴቶች በጎርፍ በመወሰዳቸዉ ፍለጋ ሲያካሄዱ የነበሩት የአደጋ ጊዜ ሠራተኞችና ጠላቂ ዋናተኞች ዕድሜያቸዉ 18 ዓመት የሆኑ ሁለት ሴቶችን በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ከተለያየ ቦታ ማግኘት ችለዋል።

የክረምቱ ጊዜ ሙሉ በሙሉ ያልተጠናቀቀ በመሆኑ ኑሮአቸዉን እና እንቅስቃሴያቸዉን ወንዝ አካባቢ ያደረጉ ሁሉ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግና ከአካባቢዉ እንዲርቁ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ አሳስበዋል።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ ከሀንጋሪ ቡዳፔስት ወደ አዲስ አበባ ጉዞ ጀምሯል በ19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የተሳተፈው የኢትዮጵያ ልዑክ ከሀንጋሪ ቡዳፔስት ወደ አዲስ አበባ የሚያደርገ...
28/08/2023

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ ከሀንጋሪ ቡዳፔስት ወደ አዲስ አበባ ጉዞ ጀምሯል

በ19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የተሳተፈው የኢትዮጵያ ልዑክ ከሀንጋሪ ቡዳፔስት ወደ አዲስ አበባ የሚያደርገውን ጉዞ ዛሬ ምሽት ጀምሯል ።

የልዑካን ቡድኑ አባላት ጀርመን ፍራንክፈርት ትራንዚት ካደረጉ በኋላ ማክሰኞ ንጋት 11:55 ላይ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ እንደሚደርሱ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

በ19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የተሳተፈው ልዑክ ነገ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲድረስም አቀባበል እንደሚደረግለት የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

ለአትሌቲክስ ልዑኩ ነገ ነሐሴ 23 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 12 ጀምሮ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ አቀባበል ይደረጋል ተብሏል።

በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ከጠዋቱ 12 ሰዓት እስከ 2 ሰዓት የሚደረገውን አቀባበል ቀጥሎ አትሌቶቹ በአውራ ጎዳናዎች በመዘዋወር ከህዝቡ ጋር ደስታቸውን እንደሚገልጹም ተመልክቷል።

በውድድሩ ኢትዮጵያ 2 ወርቅ ፣4ብርና 3 ነሃስ ሜዳሊያዎችን በማግኘት ከዓለም 6ኛ ከአፍሪካ ደግሞ 2ኛ ደረጃን በመያዝ ማጠናቀቋ ይታወሳል፡፡

አቶ ዓምዶም ገብረስላሴ የዓረና ሊቀመንበር ሆኑ።የዓረና ትግራይ ለዴሞክራሲ እና ሉዓላዊነት ፓርቲ (ዓረና) ባካሄደው  5ኛ መደበኛ ድርጅታዊ ጉባኤ አቶ ዓምዶም ገብረስላሴን ሊቀ መንበር አድርጎ...
28/08/2023

አቶ ዓምዶም ገብረስላሴ የዓረና ሊቀመንበር ሆኑ።

የዓረና ትግራይ ለዴሞክራሲ እና ሉዓላዊነት ፓርቲ (ዓረና) ባካሄደው 5ኛ መደበኛ ድርጅታዊ ጉባኤ አቶ ዓምዶም ገብረስላሴን ሊቀ መንበር አድርጎ መርጧል።

አቶ ካሕሳይ ዘገየ ደግሞ የፓርቲው ምክትል ሊቀ መንበር ሁነው እንዲያገለግሉ መመረጣቸው ተነግሯል።

Via Abrha Desta

Today

 ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ፤ እግዚአብሔር ለኢትዮጵያ ሰላምን ይሰጥ ዘንድ ክርስቲያ...
22/08/2023



ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ፤ እግዚአብሔር ለኢትዮጵያ ሰላምን ይሰጥ ዘንድ ክርስቲያኖች ከመጠላላት ርቀው #በፍቅር እንዲኖሩ እና #ሰላማውያን እንዲሆኑ አሳሰቡ።

ቅዱስ ፓትርያርኩ ይህንን ያሳስቡት ዛሬ በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም የጾመ ማርያም ሱባኤ ማጠናቀቂያ በዓል ላይ ነው።

ቤተክርስቲያንኗ ፤ " በኢኦተቤ በዐዋጅ ከተደነገጉት አጽዋማት መካከል አንዱ የሆነውና የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን ዕርገተ ሥጋ አስመልክተው ሐዋርያት የጾሙት ጾመ ማርያም በየዓመቱ በወርሓ ነሐሴ ከመባቻው አንስቶ ባሉት 16 ቀናት ካህናት እና ምእመናን ሌሊት በሰዓታት ጸሎት፤ ቀን በሥርዓተ ቅዳሴ በመሳተፍ በሕብረት ያሳልፉታል " ብላለች።

" በዚህ በጾመ ማርያም ወይም በተለምዶ የፍልሰታ ጾም ተብሎ በሚታወቀው ወቅት በርካታ ምእመናን እንዲሁም ሕጻናት በቤተ ክርስቲያን ተገኝተው ሥርዓተ ቅዳሴውን ይከታተላሉ፤ ቅዱስ ሥጋው ክቡር ደሙን ይቀበላሉ " ስትል ገልጻለች።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖትም በዚህ ሕጻን ዐዋቂው፤ ወንድ ሴቱ የክረምት ብርድ እና ዝናብ ሳይበግረው በሕብረት በሚጸልበት የሱባኤ ወቅት በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም በመገኘት ሥርዓተ ቅዳሴውን በመምራት እና ምእመናንን በመባረክ ማሳለፋቸውን ተገልጿል።

ቅዱስነታቸው በዛሬው ዕለት ከብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ጋር በገዳሙ ተገኝተው በዓሉን ያከበሩ ሲሆን በቅዳሴው መካከል ባስተላለፉት ትምህርትና ቃለ ቡራኬ " የሰላም ባለቤት የሆነው ልዑል እግዚአብሔርን ለኢትዮጵያ ሰላምን ይሰጥ ዘንድ ክርስቲያኖች ከመጠላላት ርቀው በፍቅር እንዲኖሩ እና ሰላማውያን እንዲሆኑ አሳስባለሁ " ብለዋል።

ቅዱስ ፓትርያርኩ በሱባኤው ወቅት የሀገሪቱን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክተው አባታዊ የሰላም ጥሪ ማስተላለፋቸው የሚታወስ ነው፡፡

መረጃ እና ፎቶ ከብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ/ጽ/ቤት የተገኘ ነው።

Today

አውሮፕላንን ከሰው ልጆች በተሻለ መንገድ የሚያበር ሮቦት መሰራቱ ተገለጸየቴክኖሎጂ ባለሙያዎች ከዚህ በፊት ሮቦቶችን በመስራት የሰው ልጆችስ ያስ ደመሙ ሲሆን አሁን ደግሞ ተራው የአርቲፊሻል ቴ...
20/08/2023

አውሮፕላንን ከሰው ልጆች በተሻለ መንገድ የሚያበር ሮቦት መሰራቱ ተገለጸ

የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች ከዚህ በፊት ሮቦቶችን በመስራት የሰው ልጆችስ ያስ ደመሙ ሲሆን አሁን ደግሞ ተራው የአርቲፊሻል ቴክኖሎጂ ሆኗል።

የደቡብ ኮሪያው አድቫንስድ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት መሀንዲሶች ከሰው አውሮ ፕላንን ከልጆች በተሻለ መልኩ ማብረር የሚያስችል ቴክኖሎጂ መፍጠራቸንዩ ሮ ኒውስ ዘግቧል።ተመራማሪዎቹ አርቲፊሻል ቴክኖሎጂን እና ሮቦት ሳይንስን በጋራ በመጠቀም ያለድካም እና ውስብስብ ቴክኖሎጂዎችን በቀላሉ መለየት የሚያስችል ᖉክጊሎ መፍጠራቸውን ተናግረዋል።
አዲሱ ፈጠራ ፓይቦት የተሰኘ ስያሜ የተሰጠው ሲሆን በተለይም የአውሮላን አብራሪዎች ከተቋም ተቋም ስራ ሲቀይሩ እንደ አውሮፕላኖቹ ባህሪ ይሰ የነበ ረውን የሙያ ስልጠና ያስቀራል ተብሏል።

በፎቶ እድሜ የሚናገረው አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ
ከዚህ በተጨማሪም በአውሮፕላኖቹ ላይ ያሉ የተለያዩ እና ውስብስብ ቴሎ ጂ ዎችን በቀላሉ ሮቦቶቹ እንዲያነቡት እና በቀላሉ እንዲተገብሩትም ያስችላል ተብሏል።አዲሱ ቴክኖሎጂ አደገኛ እና ለሰው ልጆች አደጋ የሆኑ በረራዎችን፣ የር ቀ ጠና አካባቢ እንዲሁም አድካሚ እና ረጅም ጊዜ የሚወስዱ በረራዎችን ለማድረግ እንደሚረዱ በዘገባው ላይ ተገልጿል።

መሀንዲሶቹ ሮቦቶቹን ከአውሮፕላን ማብረር ባለፈ የጦር ታንክ እና መከቦ ችን እንዲያሽከረክሩ እና በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ሲሆኑ ከአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ጋር በቀላሉ መወያየት እና እርምጃ ተደርገው መልማታ ቸውን አስታውቀዋል።ኢንስቲትዩቱ ፈጠራውን ከፈረንጆቹ 2026 ጀምሮ ለዓለም ገበያ የማቅረብ ቅድ እንዳለው ሲገለጽ ሮቦቶቹ ከፓይለቶች እና ረዳት ፓይለቶች ጋር ተግባብተእ ንዲሰሩ ለምተዋልም ተብሏል።

የጎንደር ከተማ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና ወጣቶች ውይይት ማድረግ ጀምረዋል!በጎንደር ከተማ ተፈጥሮ በነበረው የጸጥታ ችግር ዙሪያ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ወጣቶ...
17/08/2023

የጎንደር ከተማ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና ወጣቶች ውይይት ማድረግ ጀምረዋል!

በጎንደር ከተማ ተፈጥሮ በነበረው የጸጥታ ችግር ዙሪያ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ወጣቶችን ጨምሮ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ውይይት ማድረግ ጀምረዋል።

የውይይት መድረኩን የመሩት የአማራ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ሀላፊና የጎንደር ቀጣና ኮማንድ ፖስት ምክትል ሰብሳቢ ደሳለኝ ጣሰው፤ የጋራ ውይይቱ ዓላማ በጋራ ችግሮች ላይ መፍትሄ ለመሻት መሆኑን ገልጸዋል።

Via Ethio Today

16/08/2023



" የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል " ም/ቤት መሥራች ጉባዔ በመጪው ዓርብ ነሐሴ 12 ቀን 2015 ዓ.ም. #በሐዋሳ እንደሚካሄድ ተነግሯል።

ክልሉ ካቀፋቸው ከአምስቱ ዞኖች ፦
- ከከምባታ ጠምባሮ፣
- ከሀዲያ፣
- ከጉራጌ፣
- ከስልጤ
- ከሀላባ ዞኖች እንዲሁም ከየም ልዩ ወረዳ የተወከሉ የክልል ም/ቤት አባላት ለስብሰባው ሐሙስ ሐዋሳ ገብተው እንዲያድሩ ጥሪ ተላልፏል።

በአርቡ ጉባኤ በረቂቅ ሕገ መንሥት ላይ ውይይት ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ከረቂቅ ሕገ መንግሥት በተጨማሪ የክልሉን ማዕከላዊ ክላስተር ከተሞችና የተለያዩ መዋቅሮች ድልድልን በሚመለከት ውሳኔ እንደሚያስተላለፍ ይጠበቃል።

ይሁን እንጂ ከመሥራች ም/ቤቱ በፊት " ጥያቄዎቻችን ይመለሱ " ያሉ አካላት ከወዲሁ ስብሰባውን እየተቃወሙ ነው።

በተለይ ከተቋማት ድልድል ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ቅሬት ሲያቀርቡ የቆዩት የከምባታና ጠምባሮ ዞን የም/ቤት አባላት የዞኑ ጥያቄ ሳይመለስ ወደ ከልል ማደራጀት መገባቱ ቅሬታ እንደፈጠረባቸው ገልጸዋል።

እንደ ዱራሜ ባሉ በከምባታ ጠምባሮ ዞን ከተሞች ተጠርቶ የነበረው ሰላማዊ ሠልፍ ሰኞ ዕለት እንዳይካሄድ መደረጉን የገለጹት የዞኑ ምክር ቤት ተወካዮች፣ ባለፉት ሁለት ቀናት ከፍተኛ ቁጥር ያለው የልዩ ኃይል ፖሊስ በዞኑ መሰማራቱንም አመልክተዋል።

ሥራና እንቅስቃሴ ማቆም እንዲሁም በቤት ውስጥ የመቀመጥ አድማው በዞኑ ረገብ ያለ መልክ ቢይዝም፣ ቅሬታውና ውጥረቱ ግን እንዳለ መሆኑን ተወካዮቹ ገልጸዋል፡፡

ባለፈው እሑድ ነሐሴ 7 ቀን 2015 ዓ.ም. የዞን ምክር ቤት ስብሰባ ለግማሽ ቀን ያደረገ ሲሆን በዚህም ወቅት የክልሉ መዋቅር ድልድልን የሠራው የጋራ ኮሚቴ በፍትሐዊነት የቢሮዎች ምደባን አላደረገም በሚል የፍትሃዊነት ጥያቄ ተነስቷል።

የምክር ቤቱ አባላት በክፍፍሉ ጉዳይ የፌዴራሉ አካል ጣልቃ እንዲገባ በመስማማት ይህንን የሚጠይቅ ደብዳቤ በፅሁፍ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት እና ለጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት አስገብተዋል።

መረጃው ከሪፖርተር እና ቪኦኤ የተጠናከረ ነው።

12/08/2023

የፀጥታ ኃይሉ በአማራ ክልል የተሰባሰበውን ዘራፊና አጥፊ ቡድን በመምታት ከተሞቹ ወደ ሰላማዊ ሁኔታ እንዲመለሱ ተደርጓል - ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር)

የፀጥታ ኃይሉ በአማራ ክልል የተሰባሰበውን ዘራፊና አጥፊ ቡድን በመምታት ከተሞቹ ወደ ሰላማዊ ሁኔታ እንዲመለሱ ተደርጓል ሲሉ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

የአስቸኳይ ጊዜ ጠቅላይ መምሪያ ዕዝ እስካሁን በተሰሩ ፀጥታ ሥራዎች ላይ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) በአጠቃላይ ሁኔታዎች ላይ በሰጡት መግለጫ በባሕር ዳር፣ ደብረ ማርቀስ፣ ደብረ ብርሃን፣ ላሊበላ፣ ጎንደር እና ሸዋ ሮቢት አካባቢ የተሰባሰበውን ዘራፊና አጥፊ ቡድን በመምታት ከተሞቹ ወደ ሰላማዊ ሁኔታ እንዲመለሱ ተደርጓል ብለዋል፡፡

በከተሞቹ ውስጥና ዙሪያ የተሰገሰጉ ቡድኖች መሳሪያን እንዲያስረክብና እጁን ለፀጥታ ኃይሎች እንዲሰጥ የተሰጠውን ዕድል ባለመጠቀሙ አርምጃ እንደተወሰደባቸውም ገልጸዋል፡፡

የሕግ በላይነት እንዲከበር ተደርጓል ያሉት ሚኒስትሩ የአካባቢው ሕብረተሰብም በዘራፊው ቡድን ከመማረሩ የተነሳ የሕግ አስከባሪ አካላት ተልዕኳቸውን በስኬት እንዲወጡ የሚጠበቅበትን ድርሻ ሁሉ አበርክቷል ብለዋል፡፡

በዚህም ከተሞቹ በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ተሟላ ሰላማዊ እንቅስቃሴ እንዲመለሱ ማድረጉን ገልጸዋል፡፡ የየአካባቢዎቹ ማኅበረሰብም መረጃ በመስጠት፣ ከመከላከያ ሰራዊቱ ጋር በመሰለፍ፣ ስንቅ በማቀበል እንዲሁም የተዘጉ መንገዶችን በራሱ አቅም በመክፈት አቅሙ በፈቀደ ሁሉ ድጋፉን እያደረገ እንደሚገኝም ተናግረዋል፡፡ ለዚህም ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

Today

12/08/2023

የሕወሓት አመራሮች ከነሐሴ አጋማሽ በኋላ ወደ ራያ በኃይል ለመግባት ማቀዳቸው ተሰማ

የሕወሓት አመራሮች ሐሙስ ነሐሴ 04/2015 በመሆኒ ከተማ ባደረጉት ሚስጥራዊ ስብሰባ፤ “የራያ አካባቢዎችን ከነሐሴ 16/2015 እስከ መስከረም 01/2016 ባለው ጊዜ በኃይል እንቆጣጠራለን” ማለታቸውን አረጋግጫለሁ ሲል የአላማጣ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ለአዲስ ማለዳ ገልጿል።

የአላማጣ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ሞገስ እያሱ፤ “በራያ አላማጣ የወሰንና የማንነት ጥያቄ በሕዝበ ውሳኔ ምላሽ እንዲያገኝ መታቀዱን ተከትሎ የሕወሓት አመራሮች በመሆኒ ከተማ ባደረጉት ስብሰባ፤ “ሕዝበ ውሳኔውን ማደናቀፍ አለብን” በሚል ከነሐሴ 16/2015 ጀምሮ ውጊያ ለመክፈት ወስነዋል፡፡” ነው ያሉት።

ኃላፊው አክለውም፤ “የመከላከያ ሠራዊት በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ከፋኖ ታጣቂዎች ጋር እየተደረገ ባለው ውጊያ በመዳከሙ፤ ራያን ከነሐሴ 16/2015 እስከ መስከረም 01/2016 ድረስ እንቆጣጠራለን የሚል ዕቅድ ማውጣታቸውን ከተሰብሳቢዎች መረጃ አግኝተናል ብለዋል፡፡በራያ አላማጣ የሚገኙ ስድስት ወረዳዎች በዋናነት በጀት እንዲለቀቅላቸው የሚጠይቅ በፊርማ የተደገፈ የሕዝብ አቤቱታ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ማስገባታቸውን ተከትሎ፤ የሕወሓት አመራሮች የሕዝበ ወሳኔው ሃሳቡን ሲቃወሙ መቆየታቸውንም ጠቁመዋል፡፡

Today

 - የአውስትራሊያ ፣ - የጃፓን ፣ - የኒውዚላንድ፣ - የእንግሊዝ እና የዩናይትድ ስቴትስ መንግስታት በቅርቡ በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች የሰላማዊ ዜጎች ሞት እና አለመረጋጋት ያስከተለው ግ...
11/08/2023



- የአውስትራሊያ ፣
- የጃፓን ፣
- የኒውዚላንድ፣
- የእንግሊዝ እና የዩናይትድ ስቴትስ መንግስታት በቅርቡ በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች የሰላማዊ ዜጎች ሞት እና አለመረጋጋት ያስከተለው ግጭት እንዳሳሰባቸው ዛሬ በጋራ ባወጡት መግለጫ አሳውቀዋል።

ሀገራቱ ፤ ሁሉም ወገኖች ሰላማዊ ሰዎችን እንዲጠብቁ፣ ሰብአዊ መብቶችን እንዲያከብሩ እና የሚያጋጩ ውስብስብ ጉዳዮችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ተባብረው እንዲሰሩ አበረታተዋል።

ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለሁሉም ኢትዮጵያውያን ለዘላቂ ሰላምና መረጋጋት እንዲኖር ድጋፉን እንደሚቀጥል አሳውቀዋል።

በሌላ በኩል ፦
- የአውሮፓ ህብረት ልዑክ በኢትዮጵያ
- የኦስትሪያ ፣
- የቤልጂየም ፣
- የቼክ ሪፖብሊክ ፣
- የዴንማርክ ፣
- የፊንላንድ ፣
- የፈረንሳይ ፣
- የጀርመን ፣
- የሃንጋሪ ፣
- የአየርላንድ ፣
- የኢጣሊያ ፣
- የሉክሰምበርግ ፣
- የማልታ ፣
- የኔዘርላንድስ ፣
- የሮማኒያ ፣
- የፖላንድ ፣
- የፖርቹጋል ፣
- የስሎቬንያ ፣
- የስፔን እና የስዊድን ኤምባሲዎች በጋር ባወጡት መግለጫ ሰሞኑን በአማራ ክልል የተቀሰቀሰው ሁከትና የዜጎች ሞትና አለመረጋጋት እንዳሳሰባቸው ገልጸዋል።

ሀገራቱ ፤ " ሁሉም ወገኖች ሲቪሎችን እንዲጠብቁ ፣ ጉዳት ለደረሰባቸው ህዝቦች የተሟላ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ እና ቀጣይነት ያለው ሰብአዊ ተደራሽነት እንዲረጋገጥ፣ የውጭ ዜጎች ከግጭቱ አካባቢ ለቅቀው እንዲወጡ እና ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ እንዲተላለፉ እንዲፈቀድ፤ የሰላም ስምምነቱ አፈፃፀም በሚቀጥልበት ጊዜ ውስብስብ ጉዳዮችን በሰላማዊ ውይይት ለመፍታት በጋራ መስራት፣ እና ግጭቱ ወደ ሌሎች የሀገሪቱ ክልሎች ተዛምቶ ብጥብጥ እንዳይፈጠር ተገቢው መከላከል እንዲደረግ እናበረታታለን " ብለዋን።

አለም አቀፉ ማህበረሰብ ለሁሉም ኢትዮጵያውያን የረዥም ጊዜ የመረጋጋት ግብ ድጋፉን ይቀጥላል ሲሉ ገልጸዋል።

08/08/2023

ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የተሰጠ መግለጫ።

ሰሞኑን በክልላችን በአንዳንድ አካባቢዎች ተከስቶ የነበረው በፅንፈኛና በዘራፊ የስልጣን ጥመኛ ቡድኖች በትጥቅ የታገዘ ሁከትና ብጥብጥ በሁሉም የክልሉ አከባቢዎች ወደ አንፃራዊ ሰላምና መረጋጋት እየተመለሰ ይገኛል።

ከብዙ ትዕግስትና የሰላም አማራጮች በኃላ አሻፈረኝ ብሎ ክልሉን የእልቂትና የትርምስ ማዕከል ለማድረግ በተደራጀ ሁኔታ ከውስጥና ከውጭ ጠላቶቻችን ጋር በማበር በፋይናንስና በፅንፈኛ ሚዲያዎች ታግዞ ጦርነት አውጆ በተለይም ከተሞችን ማዕከል አድርጎ መንግሥትን በመገዳደር ነፍጥ የመዘዘው ኃይል ላይ መንግሥት ህግ የማስከበር ግዴታውን ተጠቅሞ ህግ ወደ ማስከበር ሥራ መገባቱ የሚታወቅ ነው።

በዚህም መሰረት የምንግዜም የሰላም ዘብ የሆነው የሃገር መከላከያ ሰራዊት በእነዚህ ዘራፊና መረን የለቀቁ ፅንፈኛ ቡድኖች ላይ በወሰደው ተመጣጣኝ እርምጃ ሁከት ተከስቶባቸው የነበሩ የክልላችን አብዛኞቹ ከተሞችን ወደ አንፃራዊ ሰላም እየተመለሱ ይገኛል።

በክልላችን ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ወሎ፣ ዋግ ኽምራ፣ ሰሜን ሸዋ፣ ደብረ ብርሃን፣ ሰሜንና ደቡብ ጎንደር አካባቢዎች በንፅፅር ሰላማዊ የሆነ እንቅስቃሴ ያለባቸውና ሕዝባችን በተረጋጋ መንፈስ የዘወትር ህይወቱን እያከናወነ የሚገኝባቸው ናቸው።

በአንፃሩ በክልላችን ርዕሰ መዲና ባሕር ዳር እና ጎንደር ከተሞች መሽጎ ሕዝባችን እንዲታወክ ሲያደርግ የነበረው ዘራፊ ቡድን ከትላንት ምሽት ጀምሮ በተወሰደ እርምጃ ከእነዚህ ፅንፈኛ ቡድኖች ነፃ የማድረግ ሥራ የተሠራ ሲሆን በቀጣይ በሁሉም የክልላችን አካባቢዎች የማያዳግም የህግ የማስከበር ሥራውን አጠናክሮ በመቀጠል ሕዝባችን ያለስጋት የእለት ከለት ሥራውን በተሟላ ሁኔታ እንዲከውን ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን እየገለፅን መላው የክልላችን ሕዝብ ከሀገር መከላከያ ሰራዊት ጎን ተሰልፎ አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርግና ለህግ ማስከበር ተልዕኮው የበኩሉን ትብብር እንዲያደርግ ጥሪ እናስተላልፋለን።

በመጨረሻም ሕዝባችን በፅንፈኛና የጠላት ተላላኪ ሚዲያዎች አሉቧልታ ሳይደናገር ተረጋግቶ ወደ መደበኛ ህይወቱ እንዲመለስ እያሳሰብን ዝርዝር የህግ ማስከበር አፈፃፀሙንና ክልላዊ የሰላም ሁኔታችንን በተከታታይ የምናሳውቅ መሆኑን እንገልፃለን ።

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት
ነሃሴ 2/12/2015

አቶ ክርስቲያን ታደለ እና ዶ/ር ካሳ ተሻገር “አካልን ነጻ የማውጣት” አቤቱታ ለፍርድ ቤት አቀረቡ‼️በፖሊስ ቁጥጥር ስር የሚገኙት የፓርላማ አባሉ አቶ ክርስቲያን ታደለ እና የአዲስ አበባ ም...
08/08/2023

አቶ ክርስቲያን ታደለ እና ዶ/ር ካሳ ተሻገር “አካልን ነጻ የማውጣት” አቤቱታ ለፍርድ ቤት አቀረቡ‼️

በፖሊስ ቁጥጥር ስር የሚገኙት የፓርላማ አባሉ አቶ ክርስቲያን ታደለ እና የአዲስ አበባ ምክር ቤት አባሉ ዶ/ር ካሳ ተሻገር በጠበቆቻቸው አማካኝነት “አካልን ነጻ የማውጣት” (habeas corpus) አቤቱታ ለፍርድ ቤት አቀረቡ። አቤቱታው የቀረበለት ፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ተረኛ ችሎት፤ የፌደራል ፖሊስ በጽሁፍ ምላሽ እንዲሰጥ አዝዟል።

የአቶ ክርስቲያን እና ዶ/ር ካሳ ጠበቆች አቤቱታቸውን ዛሬ ማክሰኞ ነሐሴ 2፤ 2015 ያቀረቡት፤ የፌደራል ፖሊስ ያለመከሰስ መብት ያላቸው ደንበኞቻቸውን ካለፈው ሳምንት መጨረሻ ጀምሮ “ያለምንም ፍርድ በእስር ላይ ያቆያቸው” መሆኑን በመጥቀስ ነው። በጠበቃ ሄኖክ አክሊሉ እና ሰለሞን ገዛኸኝ አማካኝነት የቀረበው አቤቱታ፤ በምክር ቤት የህዝብ ተወካዮቹ የተያዙበትን መንገድ ለፍርድ ቤቱ አብራርቷል።

በአንድ ገጽ የተዘጋጀው ይህ አቤቱታ፤ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ክርስቲያን ታደለ ባለፈው ሳምንት አርብ ከመኖሪያ ቤታቸው “እየተደበደቡ ተይዘው” በፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ መታሰራቸውን አትቷል። ዶ/ር ካሳ ተሻገርም በዚሁ ቀን ከለሊቱ ስድስት ሰዓት ገደማ በፌደራል ፖሊስ ተይዘው፤ በተመሳሳይ ቦታ ታስረው እንደሚገኙ በአቤቱታው ላይ ሰፍሯል። የፌደራል ፖሊስ ሁለቱንም ግለሰቦች የያዛቸው “ለጥያቄ እፈልጋቸዋለሁ” በሚል መሆኑንም በአቤቱታው ተመላክቷል።

የ2015 አገር አቀፍ የ12 ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከማንኛውም ኩረጃና ስርቆት በፀዳ መልኩ ተሰጥቶ ተጠናቋል - ትምህርት ሚኒስቴር “የ2015 አገር አቀፍ የ12 ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከማንኛውም ...
04/08/2023

የ2015 አገር አቀፍ የ12 ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከማንኛውም ኩረጃና ስርቆት በፀዳ መልኩ ተሰጥቶ ተጠናቋል - ትምህርት ሚኒስቴር

“የ2015 አገር አቀፍ የ12 ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከማንኛውም ኩረጃና ስርቆት በፀዳ መልኩ ተሰጥቶ ተጠናቋል” ሲሉ የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ገለጹ።

ፈተናው ከሐምሌ 19 እስከ 21 በማህበራዊ ሳይንስ እንዲሁም ከሐምሌ 25 እስከ 28/ 2015 በተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፍ ተሰጥቷል።

ፈተናውን ለመፈተን በአጠቃላይ 868 ሺህ 74 ተማሪዎች መመዘግባቸውንና ከዚህ ውስጥ 840 ሺህ 859 ፈተናውን መውሰዳቸውን ፕሮፌሰር ብርሃኑ በሰጡት መግለጫ ገልጸዋል።

“በፈተናው የተወሰነ የስነ ምግባር ግድፈት ጨምሮ አንዳንድ ችግሮች ተስተውለዋል” ብለዋል።

ካጋጠሙት ችግሮች መካከል ለፈተና ያልተፈቀዱ ነገሮችን ወደ ዩኒቨርሲቲ ይዞ ለመግባት መሞከር አንዱ መሆኑን በማሳያነት ጠቅሰዋል።

ጋምቤላ ላይ የተወሰኑ ተማሪዎች ባጋጠማቸው ሕመም 38 ተማሪዎች ፈተና እንዳልወሰዱም ነው ሚኒስትሩ የተናገሩት።

በአንጻራዊነት ሲታይ ከባለፈው ዓመት አንጻር ሲታይ የፈተና አሰጣጡ ስኬታማ ነበር ብለዋል።

በአማራ ክልል ካለው ወቅታዊ ሁኔታ አንጻር በጎንደር በሚገኙ ሶስት ካምፓሶች የተፈጠረ ችግር እንደነበር ገልጸው፤ በሌሎች በክልሉ ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች ፈተናው በሰላም መጠናቀቁን ጠቅሰዋል።(ኢዜአ)

በዛሬዉ  እለት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያው  ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ ሆነየአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሃና የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ከ50 ዓመታት ጥረት በኋ...
04/08/2023

በዛሬዉ እለት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያው ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ ሆነ

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሃና የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ከ50 ዓመታት ጥረት በኋላ የራስ ገዝ (ኦቶኖሚ) ጥያቄው መልሶ በማግኘቱ የተሰማቸውን ደስታ እየገለፁ ለመላው የዩኒቨርሲቲው ማህረሰብ እንዲሁም ፣የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎችና ለኢትዮጵያ ህዝብ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡

ከዩኒቨርስቲው ድረገጽ የተገኘ መረጃ ነው

የደቡብ ክልል ምክር ቤት ከ56 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት አፀደቀ  የደቡብ ክልል ምክር ቤት የ2016 ረቂቅ በጀት ከ56 ቢሊየን ብር በላይ በሙሉ ድምፅ አፅድቋል::የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች...
04/08/2023

የደቡብ ክልል ምክር ቤት ከ56 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት አፀደቀ

የደቡብ ክልል ምክር ቤት የ2016 ረቂቅ በጀት ከ56 ቢሊየን ብር በላይ በሙሉ ድምፅ አፅድቋል::

የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ምክር ቤት እያካሄደ ባለው 6ኛ ዙር 2ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤው የ2016 በጀት አመት ረቂቅ በጀት አዋጅ መርምሮ በሙሉ ድምጽ አፅድቋል::

ምክር ቤቱ 56 ቢሊዮን 135 ሚሊዮን 342 ሺ 85 ብር ነው ለ2016 የሥራ ዘመን ያፀደቀው::

20 ሺህ 411 ነጥብ 5 ሜትሪክ ቶን የአፈር ማዳበሪያ ወደ ሀገር ውስጥ ተጓጓዘ በትናንትናው ዕለት 20 ሺህ 411 ነጥብ 5 ሜትሪክ ቶን የአፈር ማዳበሪያ ወደ ሀገር ውስጥ መጓጓዙ ተገለጸ፡፡...
24/07/2023

20 ሺህ 411 ነጥብ 5 ሜትሪክ ቶን የአፈር ማዳበሪያ ወደ ሀገር ውስጥ ተጓጓዘ

በትናንትናው ዕለት 20 ሺህ 411 ነጥብ 5 ሜትሪክ ቶን የአፈር ማዳበሪያ ወደ ሀገር ውስጥ መጓጓዙ ተገለጸ፡፡

ማዳበሪያው በ439 ተሽከርካሪዎች እና በባቡር ወደ ሀገር ውስጥ መጓጓዙም ተመላክቷል፡፡

የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ÷ በቀጣይ ቀናት ጅቡቲ ወደብ የደረሰውን የአፈር ማዳበሪያ በአጭር ጊዜ ወደ ሀገር ውስጥ አጠቃሎ ለማጓጓዝ እየሠራ መሆኑን ከድርጅቱ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

የድርጅቱ ዋና ሥራ አሥፈፃሚ በሪሶ አመሎ (ዶ/ር ) ÷ በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ፣ የኢትዮ-ጅቡቲ የምድር ባቡር አ.ማ ፣ በኢባትሎ ጅቡቲ ኤም ቲ ኤስ አመራሮችና ሰራተኞች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት ሂደቱን በማሳለጥ ረገድ በትጋት እየሠሩ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ እና የኢትዮ ጅቡቲ የምድር ባቡር አ.ማ በሀገሪቱ ወሳኝ የሚባሉ ግብዓቶችን በፍጥነትና በብዛት ወደ ሀገር ውስጥ ለማጓጓዝ በሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች ላይ የጋራ ውይይት አድርገዋልም ነው የተባለው፡፡

 #ሀዋሳየሀዋሳ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ሀምሌ 19 በታላቅ ድምቀት የሚከበረው የቅዱስ ገብርኤል ክብረ ንግስ በዓል ያለምንም የፀጥታ ችግር በሰላም እንዲከበር ዝግጅት ማድረጉን አሳውቋል።ለበዓሉ ሰ...
24/07/2023

#ሀዋሳ

የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ሀምሌ 19 በታላቅ ድምቀት የሚከበረው የቅዱስ ገብርኤል ክብረ ንግስ በዓል ያለምንም የፀጥታ ችግር በሰላም እንዲከበር ዝግጅት ማድረጉን አሳውቋል።

ለበዓሉ ሰላማዊነት ከመምሪያውና 8ቱም ክ/ከተማ ፖሊስ ማናጀመት ፣ከ8ቱም ክ/ከተማ የሰላምና ፀጥታ ኃላፊዎች፣ ለፀጥታው አጋዥ ከሆኑ ሀይሎች ፣ ከሀይማኖት አባቶች ፣ ከሁቴል ባለቤቶች ፣ከየክፍለ ከተማ የተደራጅ ማህበራት ጋር ውይይት ተደርጓል።

ፖሊስ ከፀጥታ ኃይሉ እና ከአጋዥ ኃይሎች በተጨማሪ በከተማው በተገጠሙ የደህንነት ካሜራዎች የፀጥታውን ስራ አስተማማኝ ለማድረግ እንደሚሰራ ገልጾ የደህንነት ካሜራዎች ተደራሽ ባልደረገባቸው ቦታዎችን ካሜራ የመግጠም ስራ እየተሰራ መሆኑን አመልክቷል።

የሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎች እንዲሁም የበዓሉ ታዳሚያን በጠቅላላ አከባቢያቸውን በንቃት እንዲጠብቁና የወንጀል ድርጊትም ሲመለከቱ ለፖሊስ እንዲጠቁሙ መልዕክት ተላልፏል።

በተመሳሳይ የሲዳማ ክልል የፀጥታ ግብረሃይል ፤ በዓሉ በሰላም እንዲከበር በቅ የፀጥታ ዝግጅት ተጠናቆ ወደ ስራ መገባቱን እና ለፀጥታ ኃይሉ ስምሪት መሰጠቱን አሳውቋል።

ከበዓሉ ጋር በተያያዘ የትራፊክ መጨናነቅና አደጋ እንዳይከሰት
ለተሽከርካሪዎች ዝግ የሚሆኑ መንገዶችንም ይፋ አድርጓል።

በዚህ መነሻ ከሐምሌ 18/04/2015 ዓ.ም ከቀኑ 7:00 ጀምሮ ፦
1. ከሎጊታ - ሱሙዳ ገብርኤል
2. ከማር ስል ቤተክርስቲያን - ሱሙዳ ገብርኤል
3. ከዋርካ አደባባይ - ሱሙዳ ገብርኤል
4. ከዳሽን- ሱሙዳ ድረስ ያሉ መንገዶች በዓሉ ተከብረው እስከሚጠናቀቅ ድረስ ለትራፊክ እንቅስቃሴ ዝግ ይሆናሉ።

አሽከርካሪዎች ይህን አውቀው አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ ጥሪ ቀርቧል።

ህብረተሰቡ ማንኛውን ጥቆማ ካለው በ0462209164 እና 046 212 2468 ለክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን እንዲሁም በ0462201046 ለሀዋሳ ፖሊስ መምሪያ ጥቆማ መስጠት ይችላል።

ሀዋሳ የሚከበረው የሀምሌ 19 የቅዱስ ገብርኤል ክብረ በዓል ላይ ከሀገር ውስጥ እና ከውጭ ሀገር እጅግ በርካታ እንግዶች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ናኦሚ በሴቶች የዓለም ዋንጫ አሜሪካን ወክላለች ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ናኦሚ ግርማ በሴቶች የዓለም ዋንጫ በአሜሪካ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን ስብስስብ ውስጥ ድንቅ ብቃቷን እያሳየ...
24/07/2023

ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ናኦሚ በሴቶች የዓለም ዋንጫ አሜሪካን ወክላለች

ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ናኦሚ ግርማ በሴቶች የዓለም ዋንጫ በአሜሪካ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን ስብስስብ ውስጥ ድንቅ ብቃቷን እያሳየች ትገኛለች፡፡

የተካላካይ ክፍል ተጫዋቿ በፈረንጀቹ 2020 የአሜሪካ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን የመጀመሪያ ጥሪ የደረሳት ሲሆን፥ አሜሪካ ኡዝቤኪስታንን ባሸነፈችበት ጨዋታ ለመጀመሪያ ጊዜ 90 ደቂቃ ተሰልፋ መጫዎት ችላለች፡፡

በሰሜን አሜሪካ የሴቶች ሻምፒዮና ውድድር አራት ጊዜ ተሰልፋ መጫወት የቻለችው ናኦሚ የአሜሪካ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን ለ2023 የፊፋ የሴቶች የዓለም ዋንጫ እና ለ2024 የበጋ ኦሊምፒክ እንዲያልፍ አስተዋፅዖ አድርጋለች፡፡

ናኦሚ በኒውዝላንድ እና አውስትራሊያ አስተናጋጅነት እየተካሄደ ባለው 9ኛው የሴቶች የዓለም ዋንጫ በአሜሪካ ብሄራዊ ቡድን ስብስስብ ውስጥ በመካተት ድንቅ ብቃቷን እያሳየች ትገኛለች፡፡

ናኦሚ በ2019 የኮሌጅ ቡድኗ ስታንፎርድ ዋንጫ እንዲያነሳ አስተዋፅዖ ያደረገች ሲሆን በምርጥ 12 የተከላካይ ስፍራ ተጫዋቾች ስብስብ ውስጥም መካተት መቻሏን የአሜሪካ ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል።

በ2020 የአሜሪካ ከ20 ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድንን በአምበልነት መምራት የቻለችው ኖኦሚ በዚሁ ዓመት የአሜሪካ ምርጥ ወጣት ሴት ተጫዋች በመሆን ተመርጣለች፡፡

ናኦሚ ከኢትዮጵያ ወላጅ አባቷ አቶ ግርማ አወቀ እና ከእናቷ ወይዘሮ ሰብለ ደምሴ በፈረንጆቹ 2000 የተወለደች ሲሆን አሁን ላይ 23 አመቷ ላይ ትገኛለች፡፡

ወደ መደበኛ ኃይል አልገባም ብሎ የአመፅ መንገድን የመረጠውን የፋኖ ኃይል "በመረጠው መንገድ መስመር አስይዘነዋል"- ጄኔራል አበባው ታደሰየጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል ...
21/07/2023

ወደ መደበኛ ኃይል አልገባም ብሎ የአመፅ መንገድን የመረጠውን የፋኖ ኃይል "በመረጠው መንገድ መስመር አስይዘነዋል"- ጄኔራል አበባው ታደሰ

የጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል አበባው ታደሰ መከታ ከተባለ መጽሄት ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ ከፋኖ ጋር ያለውን ግጭት በተመለከተ ተናግረዋል።

በዚህም "ፖሊስ የሚሆን ፖሊስ፤ መከላከያ የሚሆን መከላከያ ይግባ ብለን ክፍት አድርገንለታል" በማለት ተናግረዋል።የሀገሪቱን የጸጥታ ሁኔታ በሚመለከት ማብራሪያ የሰጡት ጄኔራሉ፤ የመንግስትን ፕሮግራም አልቀበልም ያሉና የኃይል አማራጭ የተከተሉትን የፋኖ ኃይሎች በሁለት መንገድ አስተናግደናል ብለዋል።ፕሮግራሙን ለማስረዳትና ለማወያየት ከፍተኛ ጥረት አድርገናል ያሉ ሲሆን፤ "አብዛኛው ሊባል የሚችለው ወደ ተፈለገው መስመር ገብቷል" በማለት ተናግረዋል።

"አሻፈረኝ ብሎ የአመጽ መንገድን የመረጠውን ግን ህጋዊው አሰራር የግድ ተግባራዊ መደረግ ስለነበረበት በመረጠው መንገድ ሄደን መስመር አስይዘነዋል" ብለዋል።አጠቃላይ ሲታይ መንግስት እቅዱን እንዳሳካ የጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል አበባው ታደሰ ተናግረዋል።

ጄኔራል አበባው ታደሰ ከልዩ ኃይል ጋር በተያያዘም አሁን ላይ “ምንም በልዩ ሃይል የሚታዘዝ አደረጃጀትና የኮማንድ ስርዓት ያለው አሁን የለም፤ እንደ ሃይል ወይ መከላከያ ሆኗል ወደ መደበኛ ፖሊስ ሆኗል ወይም ደግሞ ፌዴራል ፖሊስ ሆኗል። ይሄ በተሳካ መንገድ ነው የተፈፀመው” ብለዋል።

የትግራይ ኃይልን በተመለከተ ከትግራይ ጋር ተያይዞ ያለውም እንደ ማንኛውም ክልል እሱም የሚኖረው መደበኛ ፖሊስ እና ሚሊሻ ብቻ ፤ በተቀመጠለት ስታንዳርድ ብቻ ነው የሚሄደው ሲሉም ምክትል እታማዦር ሹሙ ተግናረዋል።
Via Ethio Today

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ዩክሬን እንዲጎበኙ ከፕሬዝዳንቱ ግብዣ ቀረበላቸው፡፡ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ ዩክሬንን እንዲጎበኙ ግብዣ ማድረጋቸው ተሰምቷል፡፡ጠቅላይ ሚንስት...
21/07/2023

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ዩክሬን እንዲጎበኙ ከፕሬዝዳንቱ ግብዣ ቀረበላቸው፡፡

ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ ዩክሬንን እንዲጎበኙ ግብዣ ማድረጋቸው ተሰምቷል፡፡

ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ ከዩክሬን ፕሬዝዳንት ዘለንኪ ጋር በስልክ ከተወያዩ በኃላ ነው ዩክሬን እንዲጎበኙ ጥሪ የተደረገላቸው ተብሏል፡፡ ከሩሲያ ጋር ጦርነት ውስጥ ያለችው ዩክሬን፣ለኢትዮጵያ 300 ሺህ ቶን ስንዴ ማቅረቧ የተሰማ ሲሆን፣ከሰሞኑ በጥቁር ባህር በኩል ለዓለም ሃገራት ስንዴ ለማቅረብ የነበረው ስምምነት ሩስያ ከሰሞኑ ከስምምነቱ መውጣቷ ይታወሳል፡፡ ኬቭን እንዲጎበኙ የተጋበዙት ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ግብዣውን ስለመቀበላቸው እስካሁን የተባለ ነገር የለም።

ከሩሲያ ጋር ጦርነት ውስጥ ያለችው ዩክሬን በጦርነት ውስጥም ሆና ለኢትዮጵያ 300 ሺህ ቶን ስንዴ አቅርባለች ተብሏል። ከዚህ በተጨማሪም ዩክሬን ተጨማሪ 90 ሺህ ቶን ስንዴ ለኢትዮጵያ እንደምታቀርብ በዘገባው ላይ ተጠቅሷል።

የብዙ ሺህ አረጋውያን እና አቅመ ደካሞች ዋርካ - አቶ ቢኒያም በለጠ   *******************   ሰዎች ተክለሰውነቱን እና ገፅታውን በመመልከት ስለ እርሱ በልባቸው ይሆናል ያሉትን ...
21/07/2023

የብዙ ሺህ አረጋውያን እና አቅመ ደካሞች ዋርካ - አቶ ቢኒያም በለጠ
*******************

ሰዎች ተክለሰውነቱን እና ገፅታውን በመመልከት ስለ እርሱ በልባቸው ይሆናል ያሉትን ይገምታሉ። የሰውን ዓላማ እና ሊደርስበት የሚቻለው ሕልም ማወቅ የሚቻለው የዛ ሰው ሥራዎች ስለ እሱ ሲመሰክሩላቸው ነው።

የ10 ልጆች አባት አቶ በለጠ አዲስ እና እናት ወይዘሮ ፅጌ በቀለ ከልጆቻቸው የአካል ምቾት እና ድሎት ይልቅ ያስጨንቃቸው የነበረው በልባቸው ውስጥ የተዘራው ፍቅር እና መልካም ሥነ ምግባር ነበር። በስብዕናቸው ላይ የተደከመባቸው ልጆችም ለሰው ልጆች ፍቅርን፣ ርኅራሄን፣ ትህትናን እና ማካፈልን መለያቸው አደረጉ።

በሚያዝያ ወር 1968 ዓ.ም የተወለደው ቢንያም በለጠ ከእናቱ ፅጌ በቀለ እና ከአባቱ በለጠ አዲስ በአዲስ አበባ ተወለደ። በአዲስ አበባ ኮተቤ ብረታ ብረት አካባቢ ያደገው ቢንያም፣ ዕድሜው ለትምህርት ሲደርስ ወደ ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ትምህርት ቤት አመራ።

21/07/2023

7 ዓመታትን ያለ ኤሌክትሪክ . . .

ለ7 ዓመታት ኤሌክትሪክ በተቋረጠበት የቤንሻንጉል ጉሙዝ ፤ ካማሽ ዞን ነዋሪዎች " የከፋ ችግር ላይ " ስለመሆናቸው ቪኦኤ ሬድዮ ነዋሪዎችን ዋቢ በማድረግ ዘግቧል።

አቶ ለማ ሮሮ የተባሉ የካማሽ ዞን፤ ካማሽ ከተማ ነዋሪ ከ2010 ዓ/ም ጀምሮ ምንም አይነት የኤሌክትሪክ አገልግሎት እንዳላገኙ ገልጸዋል።

የኤሌክትሪክ እንዲጀምር ጥረት ቢደረግም ማታ ማታ ታጣቂዎች መስመሮች እየቆረጡ እንደሚያስቸግሩ በዚህም በመብራት የሚሰሩ ስራዎችን ለማከናወን መቸገራቸውን አስረድተዋል።

አሁን ያለውን ከፍተኛ ችግር ለመወጣት ስንል ነዳጅን በመጠቀም በጃነሬተር ለመስራት ጥረት እያደረግን ቢሆንም ነዳጅ ማግኘት በራሱ ፈተና መሆኑን ገልጸዋል።

በመብራት ምክንያት ኔትዎርክም እያስቸገረ መሆኑን አክለዋል።

አቶ ዳንኤል አየለ የተባሉ ነዋሪ ፤ ለዚህ ሁሉ ዓመታት የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተቋርጦ መቆየቱ መንግሥት ለችግሩ ትኩረት አለመስጠቱ ማሳያ ነው ብለዋል።

መንግሥት ሁሌም " የፀጥታ ችግር " ን እንደምክንያት ቢያነሳም እኔ የማስበው ግን ትኩረት ያለመስጠት ነው ሲሉ ገልጸዋል። ባለው ሁኔታ ችግር ውስጥ ነን ሲሉ አስረድተዋል።

ሌላ ነዋሪ ደግሞ ኤሌክትሪክ ከተቋረጠ በላይ መሆኑና በህክምና ተቋማት ላይ ከባድ ተፅዕኖ እንዳሳደረ ገልጸዋል። በ5 ወረዳ ውስጥ ኔትዎርክ እንደማይሰራ ፣ ካማሽ ላይም በተቆራረጠ ሁኔታ እንደሚሰራ ፣ ባንክም አንዳንድ ጊዜ አስቸጋሪ ነው ሲሉ አክለዋል።

ሰዎች የባንክ አገልግሎት ፍለጋ 2 እና 3 ቀናት በእግር ተጉዘው ነው ካማሽ የሚመጡት ፤ ተማሪዎችም ለማጥናትም እንደተቸገሩ ነው ሲሉ አብራርተዋል።

በአካባቢው ፀጥታ ከደፈረሰበት 2010 በፊት ችግር መኖሩን ያነሱት እኚሁ ነዋሪ የሚዘረጉትን የኤሌክትሪክ መስመሮች የሚቆራርጡ አካላትን " ላይተው እንደማያውቁ " ገልጸዋል።

የካማሽ ዞን ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ጀርሞሳ ተገኝ ፥ በዞኑ አምስት ወረዎች እና አንድ የከተማ አስተዳደር እንዳለ ገልፀው ከ300 ሺህ በላይ ነዋሪዎች ከ2008 አጋማሽ አካባቢ አንስቶ መብራት መቆራረጥ እንዳጋጠማቸው ከግንቦት ወር በኃላ ግን ሙሉ በሙሉ መጥፋቱን አስረድተዋል።

አቶ ጀርሞሳ ተገኝ ለውጡን ተከትሎ በሀገሪቱ በተለያየ አካባቢ በተፈጠረ የፀጥታ ችግር የመብራት ኃይል ስራውን ማከናወን ስላልቻለ በአሁን ወቅት #መላው የዞኑ ማህበረሰብ የመብራት ተጠቃሚ እንዳልሆነ ገልጸዋል።

ቡድን መሪው ፤ " አሁን ካማሽ ከተማ ላይ ባንክ አለ ፣ ቴሌ አለ ጄነሬተር በ500 ሺህ ፣ በሚሊዮንም ገዝተው ያመጣሉ ጄነሬተሩ እራሱ እየተበላሸ ከፍተኛ እንግልት ነው እየደረሰባቸው ያለው። " ብለዋል።

" ነዳጅ በብላክ ማርኬት/ጥቁር ገበያ ነው የሚገዛው ዋጋው ደግሞ ከጣም ውድ ነው " የሚሉት ቡድን መሪው " ኮምፒዩተር ቤቶች አሉ፣ በትምህርት ቤቶች ተማሪዎች አሉ ፣ ሆስፒታል ላይ አልትራሳውንድ ፣ ላብራቶሪ ክፍል ያለመብራት አገልግሎት ስለማይሰጡ እነዚህ ተቋማት ላይ ከፍተኛ ችግር እየደረሰ ነው በመንግስት ስራ ላይ ማለት ነው " ሲሉ የችግሩን መጠን ገልጸዋል።

" እንደመፍትሄ አባይ አሁን ላይ አገልግሎት መስጠት እየጀመረ ስለሆነ ፤ የተወሰነ #ከአባይ በትልቅ ታወር ተቀንሶልን እዚህ ማዕከል ላይ ማከፋፈያ ተሰርቶ ከዚህ ጥገኝነት እንላቀቅ የሚል ጥያቄ ነው ህዝቡ እያነሳ ያለው " ብለዋል።

" የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል " ችግሩን #በዘላቂነት ለመፍታት አዲስ የማከፋፈያ ጣቢያ ለመስራት ቃል ተገብቶ የነበር ቢሆንም እስካሁን ድረስ ግን ተግባራዊ እንዳልተደረገ የቡድን መሪው አሳውቀዋል።

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪ

የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹ ሐምሌ 26 እና 27 በአካል ተገኝተዉ እንደሚመዘገቡ ጥሪ አቀረበ‼️የመቐለ ዩኒቨርሲቲ  በ2013 ዓ/ም ተመራቂ የነበሩ የመጀመርያ ዲግሪ መደበኛ ተማሪዎች ፣ የድህ...
21/07/2023

የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹ ሐምሌ 26 እና 27 በአካል ተገኝተዉ እንደሚመዘገቡ ጥሪ አቀረበ‼️

የመቐለ ዩኒቨርሲቲ በ2013 ዓ/ም ተመራቂ የነበሩ የመጀመርያ ዲግሪ መደበኛ ተማሪዎች ፣ የድህረ ምረቃ ተማሪዎች ፣የተከታታይ ትምህርትና የማታ ተማሪዎች እና የሕክምና ትምህርት ክፍል ተማሪዎቹ ሐምሌ 26 እና 27 በአካል ተገኝተዉ እንደሚመዘገቡ ጥሪ ማቅረቡን ብስራት ራዲዮ ሰምቷል።

በዚህም መሰረት በዋናዉ ግቢ ፣ በቃላሚኖ ግቢ እና በዓይደር ግቢ ተማሪዎቹ በተጠቀሱት ቀናት እንዲገኙ አሳስቧል።

በተመሳሳይ ተመራቂ ያልሆኑ የመጀመርያ ዲግሪ መደበኛ ተማሪዎችም ምዝገባቸዉ መስከረም 4 እና 5 /2016 ዓ/ም መሆኑን ጨምሮ ባወጣዉ ማስታወቂያ ጠቅሷል።

19/07/2023

በጋምቤላ ክልል በተቀሰቀሰ ግጭት ከ30 በላይ ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ተናገሩ

በጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በአኝዋክ እና በኑዌር ብሔር አባላት መካከል በተነሳ ግጭት ከኹለቱም ብሔሮች ከ30 በላይ ሰዎች መገደላቸውን የከተማው ነዋሪዎች ገልጸዋል።

ግጭቱ የተቀሰቀሰው ትናንት ሐምሌ 11/2015 ከቀኑ 10 ሰዓት ጀምሮ መሆኑን የተናገሩት ነዋሪዎቹ፤ እሁድ ሐምሌ 09/2015 የአኝዋክ ብሔረሰብ ተወላጅ የሆነ የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ የኹለተኛ ዓመት ተማሪ በኑዌር ብሔር አባላት መገደሉን ተከትሎ፣ በኹለቱ ብሔር አባላት መካከል ግጭት መቀስቀሱን ጠቅሰዋል።

በክልሉ የብሔር ብሔርሰቦች ቀን መከበር ከጀመረበት ከ2008 ወዲህ ለኹሉም ብሔር ብሔረሰቦች መገለጫ ይሆናል ተብሎ የታሰበ አንድ ቤት በጋምቤላ ከተማ የአኝዋክ ብሔረሰብ አባላት በብዛት በሚኖሩበት አካባቢ መሰራቱን ተክትሎ፣ የኑዌር ብሔረሰቦች በአካባቢው መስፈር ከጀመሩ ወዲህ በኹለቱ ብሔረሰቦች መካከል በየጊዜው ግጭት እንደሚፈጠር ነው የገለጹት።

ስለሆነም የአኝዋክ ብሔረሰብ ተወላጅ የሆነው የዩኒቨርሲቲ ተማሪው ባለፈው እሁድ ዕለት ከተገደለ በኋላም፤ የኑዌር ብሔረሰቦች አካባቢውን ለቀው ይውጡ በሚል ከትናንት ሐምሌ 11/2015 ከቀኑ 10 ሰዓት ጀምሮ እስከ ምሽት ኹለት ሰዓት ድረስ በኹለቱ ብሔር አባላት መካከል ከፍተኛ የተኩስ ልውውጥ ሲካሄድ እንደነበር ተናግረዋል፡፡

የአኝዋክ ብሔር አባላት የኑዌር ብሔር አባላትን ሰፈራችንን ለቃችሁ ውጡልን ሲሉ፣ የኑዌር ብሔር አባላት በበኩላቸው፣ ከባሮ ወንዝ ወዲህ ያለው የእኛ እንጂ የእናንተ አይደለም እንደሚሉም መረዳት ተችሏል።

ይህን ተከትሎም በዛሬው ዕለት በጋምቤላ ከተማ ባንኮችን ጨምሮ ኹሉም የመንግሥት መስሪያ ቤቶች መዘጋታቸው እንዲሁም የተሽከርካሪ እና የሰው እንቅስቃሴ አለመኖሩ ተጠቁሟል።
ከዛሬ ረፋድ ጀምሮ የመከላከያ ሠራዊት አባላት ወደ ከተማው መግባታቸውንም ነዋሪዎቹ ተናግረዋል።

የጋምቤላ ክልል የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊ ኡገቱ አዲንግ ሲሉ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።
ምንጭ፣ Ethio Today

የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመውጫ ፈተና ካስፈተኗቸው ተማሪዎች ምን ያህል ፐርሰት ተማሪዎቸው አለፉ ?(እስካሁን ድረስ ይፋ ያደረጉ)- ጎንደር ዩኒቨርሲቲ 👉 89.35 በመቶ- አዳማ ...
18/07/2023

የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመውጫ ፈተና ካስፈተኗቸው ተማሪዎች ምን ያህል ፐርሰት ተማሪዎቸው አለፉ ?

(እስካሁን ድረስ ይፋ ያደረጉ)

- ጎንደር ዩኒቨርሲቲ 👉 89.35 በመቶ
- አዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ 👉 87.04 በመቶ
- ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ 👉 84.7 በመቶ
- ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ 👉 81 በመቶ
- ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ 👉 81 በመቶ
- ቀብሪድሃር ዩኒቨርሲቲ 👉 80.69 በመቶ
- ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ 👉 80.6 በመቶ
- ወልድያ ዩኒቨርሲቲ 👉 80.3 በመቶ
- አርሲ ዩኒቨርሲቲ 👉 79.66 በመቶ
- ጅማ ዩኒቨርሲቲ 👉 79.2 በመቶ
- ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ 👉 77.6 በመቶ
- ወሎ ዩኒቨርሲቲ 👉 72.2 በመቶ
- ደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ 👉 71 በመቶ
- ደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ 👉 70.62 በመቶ
- ሰመራ ዩኒቨርሲቲ 👉 65.7 በመቶ
- መቱ ዩኒቨርሲቲ 👉 53.00 በመቶ
- ወለጋ ዩኒቨርሲቲ 👉 41 በመቶ ተማሪዎቻቸው ዘንድሮ የተሰጠውን የመውጫ ፈተና #ማለፍ እንደቻሉ አሳውቀዋል።

እስካሁን በተቋማቸው ያለፉ ተማሪዎችን በፐርሰት ይፋ ካደረጉት ከላይ ከተዘረዘሩት ዩኒቨርሲቲዎች መካከል ወለጋ ዩኒቨርሲቲ ከ50 በመቶ በታች (ማለትም ያለፉት 41 በመቶ ብቻ) በማስመዝገብ ዝቅተኛው ሲሆን በተቋሙ የሶስት አካዳሚክ ፕሮግራም ተፈታኞች ሙሉ በሙሉ ፈተናውን ማለፍ እንዳልቻሉ ታውቋል።

የተመዘገበውን ውጤት ቀድሞውንም የተገመተና በሞዴል ፈተና ወቅትም ከተመዘገበው ጋር ተመሳሳይ መሆኑ ተመላክቷል።

ውጤቱ ወደ ትክክለኛ የተጠጋ ነው ያለው ተቋሙ ይህ ያረጋገጠው ከየትኛውም ስርቆት እና ኩረጃ ነፃ በሆነ መንገድ ፈተናው እንዲሰጥ የተያዘውን የማያወላዳ አቋም ነው ብሏል።

የተቋሙ ማኔጅመት የተመዘገበው ከግማሽ ብታች ውጤት እንደ ዩኒቨርሲቲ የታመነበት እውነተኛ ችግር ያለ በመሆኑ ውጤቱ ዝቅተኛ የሆነበትን ምክንያት የሚያጠና ኮሚቴ እንዲዋቀር ወስኗል።

ኮሚቴው የችግሩ መነሻዎችና ችግሩ ያደረሰውን ጉዳት በማጥናት ችግሮቹን ለመፍታት የሚያስችሉ ምክረ ሃሳቦችን ያቀርባል ተብሏል፡፡

የመውጫ ፈተና ውጤት መታየት ጀመረ።ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፤ የመውጫ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ውጤታቸውን በ " ኦንላይን " ማየት መጀመራቸውን ማረጋገጥ ችሏል።ምንም እንኳን የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስ...
16/07/2023

የመውጫ ፈተና ውጤት መታየት ጀመረ።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፤ የመውጫ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ውጤታቸውን በ " ኦንላይን " ማየት መጀመራቸውን ማረጋገጥ ችሏል።

ምንም እንኳን የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር ውጤት መታየት የሚጀምረው ከማታ ጀምሮ መሆኑን ቢገልጽም ከዚህ ሰዓት አንስቶ ተማሪዎች የፈተናውን ውጤት እየተመለከቱ መሆኑን አረጋግጠናል።

የመውጫ ፈተና ውጤት የሚታየው በ result.ethernet.edu.et ላይ Username እና Password በማስገባት ነው።

የውጤት መመልከቻ ድረገፁ ተመራቂዎች ፈተናውን ማለፍ አለማለፋቸውን ካገኙት ውጤት ጋር Pass / Fail እያለ ያሳውቃቸዋል።

አሁን ላይ ውጤት እየተመለከቱ የሚገኙት የመንግሥት ተቋማት ተፈታኞች መሆናቸውን ለማወቅ ችለናል።

በ2015 ዓ/ም የመውጫ ፈተና በመንግስት ተቋማት ለፈተናው ከተቀመጡት 77,981 ተማሪዎች ውስጥ 50 እና ከዚያ በላይ በማምጣት ያለፉት 48,632 ተማሪዎች ወይም 62.37 በመቶ ናቸው።

በግል ተቋማት ደግሞ ለፈተና ከተቀመጡት 72,203 ተማሪዎች ውስጥ 50 እና ከዚያ በላይ ውጤት አምጥተው ያለፉት 12,422 ተማሪዎች ወይም 17.2 በመቶ ብቻ ናቸው።

ለቀጣዮች 6 ወራት የቤት ኪራይ መጨመርም ሆነ ተከራይ ማስወጣት አይቻልም - የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከሐምሌ 2 ቀን 2015 እስከ ታኅሣሥ 2 ቀን 2016 ዓ.ም ...
12/07/2023

ለቀጣዮች 6 ወራት የቤት ኪራይ መጨመርም ሆነ ተከራይ ማስወጣት አይቻልም - የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር

በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከሐምሌ 2 ቀን 2015 እስከ ታኅሣሥ 2 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ የቤት ኪራይ ዋጋ መጨመር እና ተከራይን ማስወጣት እንደማይቻል አስተዳደሩ አስታወቀ፡፡

ቀደም ሲል ከሰኔ 2 ቀን 2015 እስከ ሕዳር 2015፣ ከሕዳር 2 ቀን 2015 እስከ መጋቢት 2 ቀን 2015፣ ከመጋቢት 2 ቀን 2015 እስከ ሐምሌ 2 ቀን 2015 ደንብ በማውጣት ከቤት ኪራይ ጋር በተያያዘ ያለውን ችግር ለመፍታት ጥረት መደረጉ ተገልጿል፡፡

አሁንም ደንቡ ለአራተኛ ጊዜ ለቀጣዮች ሥድስት ወራት መራዘሙን የአስተዳደሩ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡

ስለዚህ የቀበሌ አመራሮች፣ ማህበራዊ ፍርድ ቤቶች እና የፍትሕ አካላት የዚህን ደንብ ተፈፃሚነት እንዲያስከብሩም አስተዳደሩ አሳስቧል፡፡

 የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በሱዳን ተፋላሚ ኃይሎች መካከል ንግግር ለማስጀመር በግብፅ በተዘጋጀው መድረክ ላይ ተሳታፊ ለመሆን ወደ ካይሮ ማቅናታቸው ተሰምቷል።የኤርትራ የማስታወቂ...
12/07/2023



የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በሱዳን ተፋላሚ ኃይሎች መካከል ንግግር ለማስጀመር በግብፅ በተዘጋጀው መድረክ ላይ ተሳታፊ ለመሆን ወደ ካይሮ ማቅናታቸው ተሰምቷል።

የኤርትራ የማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገ/መስቀል ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ከግብፁ አቻቸው አብደል ፈታህ አል-ሲሲ በቀረበላቸው ግብዣ መሠረት የሱዳን ጎረቤት አገራት መሪዎች በሚያደርጉት ውይይት ላይ ተሳታፊ ለመሆን ዛሬ ረፋድ ወደ ካይሮ መጓዛቸው ተገልጿል።

የሱዳን ጎረቤት የሆነችው ግብፅ ሁለቱን የጦር ጄኔራሎችን ሐሙስ ሐምሌ 06/2015 ዓ.ም. ለማደራደር ማቀዷ ተነግሯል።

በሌላ በኩል፥ የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር " የውጭ ኃይሎችን " ወደ ሱዳን የመላክን ጥሪ እንደማይቀበለው አስታውቋል።

ሚኒስቴሩ ሱዳን ከምስራቅ አፍሪካ በይነ መንግስታት ድርጅት(ኢጋድ) ልትወጣ እንደምትችልም አስጠንቅቋል።

ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ይህን መግለጫ ያወጣው ኢጋድ በትናንትናው እለት በሱዳን ጉዳይ በአዲስ አበባ መምከሩን ተከትሎ ነው።

ሚኒስቴሩ እንደገጸው የሱዳን ልኡካን ቡድን በአዲስ አበባ መገኘት ፣ ሱዳን ለሰላማዊ መፍትሄ ያላትን ጽኑ ፍላጎት የሚያሳይ ነው ብሏል።

በሱዳን ጦር መሪ ጄኔራል አብደል ፈታህ አል ቡርሐን እና በፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ መሪ ጄኔራል ሞሐመድ ሐምዳን ዳጋሎ መካከል የተፈጠረው የሥልጣን ሹክቻ በሱዳን ሉዓላዊ እና እንድነት ላይ አደጋ ከመጋረጡ በላይ በቀጠናው ላሉ አገራት የደኅንነት ስጋት ሆኖ ቀጥሏል።

የተመድ ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ሱዳን ወደለየለት የዕርስ በዕርስ እየገባች ነው ፤ይህም ቀጠናውን ወደ ትርምስ ሊወስድ ይችላል ሲሉ ማስጠንቀቃቸው ይታወቃል።

Via BBC

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethio Today posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share