![](https://img3.medioq.com/025/658/122118693740256589.jpg)
16/04/2024
በጎፋ ዞን የተጀመረው "አንድ መጽሐፍ ለአንድ ተማሪ" ዘመቻ ሁሉም የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት ጥሪ ቀረበ
ላሃ፤ ሚያዝያ 07/2016 በጎፋ ዞን የተጀመረው "አንድ መጽሐፍ ለአንድ ተማሪ" ዘመቻ ሁሉም የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት ጥረ ቀርቧል።
ዘመቻው ለአንድ ወር አንድ በተለያዩ ርዕሶች የሚቀጥል ሲሆን መጽሐፍ የማሰባሰብ እና የመለገስ ዘመቻ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች በንቃት እንዲሳተፉ ጥሪ ቀርቧል።
በዞናችን በየደረጃው ባሉ ትምህርት ቤቶች ያጋጠመውን የመጻሕፍት ዕጥረት በማቃለል እንደ ሀገር የገጠመንን የትምህርት ስብራት ለመጠገን በሚደረገው ጥረት የሁሉም ሰው ድጋፍና ትብብር እንደሚሻ ተመላክቷል።
ዞናዊ ድጋፍ ማሰባሰቢያ የንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000621351323 መሆኑን እናሳስባለን።