Awash 90.7 FM

Awash 90.7 FM Awash fm 90.7 is a pioneer private radio station based in Addis Ababa.

Addis Ababa gears up for the fifth edition of the Ethiopia Real Estate and Home Expo.Addis Ababa, Ethiopia, December, 20...
07/12/2022

Addis Ababa gears up for the fifth edition of the Ethiopia Real Estate and Home Expo.

Addis Ababa, Ethiopia, December, 2022 – Ethiopia Real Estate and Home Expo, an annual gathering of the leading local and international Home developers showcasing the latest offers and solutions, is again back with the latest edition. Set to be held on the 17th and 18th of December 2022, the fifth Ethiopia Real Estate and Home expo comes at a time when the demand for residential houses in urban Ethiopia, especially in Addis Ababa, has dramatically risen over the past years.

The Ethiopian’s economy rapid growth has placed increasing pressure on urban areas, as individuals transition from rural upbringings to urban environments. According to data from the World Bank, Ethiopia’s urban land and urban population are expected to grow significantly in the coming years and bring with it an increased need for housing. The real estate market has already experienced significant growth and data suggests there will be more opportunities for real estate developers to provide new projects.

Addis Ababa gears up for the fifth edition of the Ethiopia Real Estate and Home Expo. Addis Ababa, Ethiopia, December, 2022 – Ethiopia Real Estate and Home Expo, an annual gathering of the leading local and international Home developers showcasing the latest offers and solutions, is again back wit...

የክቡር አርቲስት አሊ ቢራ የአስክሬን ሽኝት በነገዉ እለት በወዳጅነት አደባባይ እንደሚደረግ ተገለጠ።ባለፉት ከ6 አስርት አመታት በላይ በሰባት ቋንቋ  ለሀገሪቱ የሙዚቃ እድገት የበኩሉን ሲወጣ...
07/11/2022

የክቡር አርቲስት አሊ ቢራ የአስክሬን ሽኝት በነገዉ እለት በወዳጅነት አደባባይ እንደሚደረግ ተገለጠ።
ባለፉት ከ6 አስርት አመታት በላይ በሰባት ቋንቋ ለሀገሪቱ የሙዚቃ እድገት የበኩሉን ሲወጣ ለነበረው አርቲስት አሊ ቢራ የአስክሬን ሽነኝት በነገዉ እለት እንደሚካሄድ ተገልጠዋል።

የዶክተር አሊ ቢራ የቀብር አስፈጻሚ ኮሚቴ በዛሬዉ እለት በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቀው የአሊ ቢራ አስከሬን ሽኝት በነገዉ እለት ከሁለት ሰዓት ጀምሮ በወደጅንት ፓርክ እንደሚካሆድ አስተባባሪዎቹ ገልጠዋል።

በዚህ መሰረት የክቡር አርቲስት አሊ ቢራ የቀብር ስረዓት በነገዉ እለት በትዉልድ ከተማዉ ወዳጆቹ ዘመዶቹ እና አድናቂዎቹ በተገኙበት ይፈጸማል ብሏል ኮሚቴዉ።

የቀደሞ የሙያ አጋራቸው እና የቀብር አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል የሆኑት ዳዊት ይፍሩ ዶክትር አሊ ቢራ ኢትዮጵያ የወላድ መካን አለመሆኗን የሳየ ድንቅ ኢትዮጵያ በለዉለታ ነዉ ብለዋል።

አርቲስት ጸጋዬ ደንደና በበኩላቸዉ አሊ ቢራ በሀሉም የሀገሪቱ ክፍል ከመወደዱ በተጨማሪ በሱዳን እና በሌሎች የጎረቤት ሀገራት ጎልተዉ የሚደመጡ የሙዚቃ ስራዎችን ለአድማጮቹ የደረሰ ድንቅ ችሎታ ያለዉ ጀግና ነዉ ብለዋል።

አርቲስት ጸጋዬ አክለዉም አሊ ቢራ ለአፋን ኦሮሞ አቀንቃኞች ፈር ቀዳጅ እና ለኦሮሞ ብሄረሰብ ደግሞ የማይደበዝዝ አርማ ነዉ ብለዋል።

በያሬድ እንዳሻዉ

05/11/2022

ነጭ የውኃ የፕላስቲክ ጠርሙስ ለጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪ የሚሆነው ግብዓት በማምረት ከውጭ የሚመጣውን በሀገር ውስጥ መተካት ያስችላል ተባለ።

የታሸጉ ውኃ አምራቾች በተለምዶ ሲጠቀሙበት የነበረውን የውኃ ማሸጊያ ፕላስቲክ ጠርሙስ ማቅለሚያ የውጭ ምንዛሬን የሚያባክን፣ መልሶ ጥቅም ላይ የማይውል፣ የአካባቢ ብክለትን የሚያባብስና የማምረቻ ወጪን የሚጨምር ከጥቅምት 1/2015ዓ.ም ጀምሮ ጥቅም ላይ እንዳይውል መወሰኑ ይታወቃል፡፡

የውኃ ማሸጊያ ፕላስቲክ ጠርሙስ ከሰማያዊ ወደ ነጭ ቀለም በመቀየሩ ለማቅለሚያ ጥሬ እቃው በዓመት ይወጣ የነበረውን ከ50 ሚሊዮን በላይ ዶላር የውጭ ምንዛሬ ማዳን እንደሚቻል የኢትዮጵያ በቨሬጅስ አምራች ኢንዱስትሪዎች ማህበር ቦርድ ፕሬዘዳንት ጌትነት በላይ (ኢንጂነር) ገልጸዋል፡፡

የውኃ የፕላስቲክ ጠርሙስ ነጭ መሆኑ ለጨርቃጨርቅ ማምረቻ ግብዓት የሚሆን ፓሊስተር፣ፋብሪክና ያርን በሰፊው በማምረት ከውጭ የሚመጣውን ሀገር ውስጥ በመተካት በዓመት ውስጥ ከ45-50ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ማዳን ያስችላል ብለዋል፡፡ ነጭ የፕላስቲክ ጠርሙሱ ተፈጭቶና ፕሮሰስ ተደርጎ ወደ ውጭ ኤክስፖርት ሲደረግ ቀድሞ ከነበረው በዓመት ውስጥ በአማካይ በአንድ ቶን እስከ 15 የአሜሪካን ዶላር ተጨማሪ ገቢ እንደሚያስገኝ ኢንጅነር ጌትነት ገልፀዋል፡፡

የኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ም/ዳይሬክተር አቶ ስለሽ ለማ በበኩላቸው ይህ እንቅስቃሴ አንዱ የኢትዮጵያ ታምርት የንቅናቄ አካል መሆኑን በመግለፅ ሁሉም ሰው በነጭ የፕላስቲክ ጠርሙስ የተመረተ ውኃን በመጠቀም ለአካባቢ ጥበቃና ለሀገር ኢኮኖሚ እድገት የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ አሳስበዋል፡ አከፋፋዎች፣ቸርቻሪዎችና ባለሱቆች ያለ ማስተርባች የተመረተ ነጭ ፕላስቲክ ጠርሙስ የታሸገ ውኃ ለህብረተሰቡ ማቅረብ እንደሚጠበቅባቸው ተመላክቷል ።

በመቅደላዊት ይግዛው

ከንፈር እና የላንቃ መሰንጠቅ ህጻናት ከመወለዳቸው በፌት የሚከሰት ችግር ሲሆን በእርግዝና ወቅት የህጻኑ/የህጻኗ ከንፈር ወይም ላንቃ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ሳይገጥም ሲቀር የሚፈጠር ክፍተት...
04/11/2022

ከንፈር እና የላንቃ መሰንጠቅ ህጻናት ከመወለዳቸው በፌት የሚከሰት ችግር ሲሆን በእርግዝና ወቅት የህጻኑ/የህጻኗ ከንፈር ወይም ላንቃ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ሳይገጥም ሲቀር የሚፈጠር ክፍተት /ስንጥቅ ማለት እንደሆነ የህክምና ባለሙያዎች ያስረዳሉ ። በአለማችን ላይ በየአመቱ ከ170.000 በላይ ህጻናት ከከንፈር እና ከላንቃ መሰንጠቅ ጋር ይወለዳሉ ። በአፍሪካ ውስጥም ከ32.000 ህጻናት በላይ በየአመቱ ከዚሁ ችግር ጋር ይወለዳሉ ። እንዲሁም ደግሞ በሃገራችን ኢትዮጵያ በየአመቱ ከ3000 በላይ ህጻናት ከከንፈር እና ላንቃ መሰንጠቅ ጋር ይወለዳሉም ተበሏል። ይህም ህጻናቱ ለአመጋገብ ፣ለአተነፋፈስ እንዲሁም ለአነጋገር እክሎች ያጋልጣቸዋል ነው የተባለው ። ስማየል ትሬን በአለማችን የከንፈር እና የላንቃ መሰንጠቅ ጋር ለተወለዱ ህጻናት የማስተካከያ ቀዶ ጥገና በነፃ የሚሰጥ በጎ አድራጎት ድርጅት ነው ። ስማይል ትሬን ከሰን ኢኮ አርት ፎር ሶሻል ደቨሎፕመንት ጋር በመተባበር “ሙቪንግ ስማይል” የተሰኘ የአስፋልት ላይ ባቡር መሰል መኪና በማዘጋጀት፤ አገር አቀፍ የከንፈር እና ላንቃ መሰንጠቅ የግንዛቤ ማስጨበጫ ጉዞ በይፉ መጀመሩን የሰን ኢኮ አርት ፎር ሶሻል ደቨሎፕመንት ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኤፍሬም በቀለ ተናግረዋል። ከ1999 ጀምሮ በአለማችን ላይ የክንፈር እና የላንቃ መሰንጠቅ ላጋጠማቸው 1.5 ሚሊየን ህጻናት ቀዶ ጥገና በነጻ አድረገዋል ተብሏል ።

የከንፈር እና የላንቃ መሰንጠቅ ህጻናት ከመወለዳቸው በፌት የሚከሰት ችግር ሲሆን በእርግዝና ወቅት የህጻኑ/የህጻኗ ከንፈር ወይም ላንቃ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ሳይገጥም ሲቀር የሚፈጠ....

ከአላማጣ እስከ ላሊበላ የተዘረጋው የ66 ኪሎ.ቮልት የትራንስሚሽን መስመር የጥገና ሥራ 90 ከመቶ መጠናቀቁ ተነግሯል ። በአሸባሪው የህወሓት ቡድን ወድሞ የነበረው ከአላማጣ እስከ ቆቦ ያለው ...
31/10/2022

ከአላማጣ እስከ ላሊበላ የተዘረጋው የ66 ኪሎ.ቮልት የትራንስሚሽን መስመር የጥገና ሥራ 90 ከመቶ መጠናቀቁ ተነግሯል ። በአሸባሪው የህወሓት ቡድን ወድሞ የነበረው ከአላማጣ እስከ ቆቦ ያለው የመካከለኛ ኤሌክትሪክ መስመር የጥገና ሥራ ሙሉ በሙሉ መጠናቀቁን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የኮርፖሬት ኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ መላኩ ታየ ለአዋሽ ራዲዮ ገልፀዋል። አያይዘውም ከአላማጣ እስከ ላሊበላ የተዘረጋው የ66 ኪሎ.ቮልት የትራንስሚሽን መስመር የጥገና ሥራ 90 ከመቶ መጠናቀቁንም ነው የተናገሩት ። አቶ መላኩ አክለውም ከአላማጣ እስከ ቆቦ ያለው የመካከለኛ መስመር የጥገና ስራ በአሁኑ ወቅት 100 ፐርሰንት መጠናቀቁንና አካባቢውን እንደገና የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ ለማድረግ ከአስተዳደሩ ጋር በመተባበር የዛፍ ቅርንጫፎችን የማፅዳት ሥራ እየተከናወነ መሆኑን አስታውቀዋል። የዛፍ ቅርንጫፎችን የማፅዳት ሥራው እንደተጠናቀቀ ቆቦን ጨምሮ በመስመሩ የሚገኙ አካባቢዎች የኤሌክትሪክ አገልግሎት እንደሚያገኙም ጠቁመዋል። የኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማት ጥገናውን በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ የተቋሙ ሠራተኞች ቀንና ማታ ስራውን ማከናወናቸው የተገለፀ ሲሆን ይህንንም መስመር ቶሎ በማጠናቀቅ ህብረተሰቡ የኤሌክትሪክ አገልግሎት እንዲያገኝ ለማድረግ ሠራተኞች አሁንም ከፍተኛ ርብርብ እያደረጉ ነው ተብሏል ።
በመቅደላዊት ይግዛው

ቆሼ አካባቢ በደረሰ የእሳት አደጋ 60 ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረት ወደመ በትላንትናው ዕለት በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 በተለምዶ ቆሼ እየተባለ በሚጠራው ቦታ ከቀኑ 10:34 አ...
30/09/2022

ቆሼ አካባቢ በደረሰ የእሳት አደጋ 60 ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረት ወደመ በትላንትናው ዕለት በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 በተለምዶ ቆሼ እየተባለ በሚጠራው ቦታ ከቀኑ 10:34 አካባቢ በደረሰ የእሳት አደጋ 60 ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረት መውደሙን የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ ። የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለአዋሽ ራዲዮ እንደተናገሩት አደጋው የደረሰው የተቃጠለ ዘይትን መልሶ ጥቅም ላይ የሚያውል ፋብሪካ ላይ ነው ብለዋል ። በዚህም 60 ሚሊየን ብር የተገመተ ንብረት ሲወድም አንድ የእሳት አደጋ ሰራተኛን ጨምሮ አምስት ሰዎች ላይ ቀላል ጉዳት ደርሷል ነው ያሉት ። አደጋዉን ለመቆጣጠር 10 የአደጋ መቆጣጠር ተሽከርካሪና 2 አምቡላንስ እንዲሁም 80 የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ተሰማርተው እንደነበር ያነሱት የህዝብ ግንኙነት ባለሙያው፥ የእሳት አደጋውን ሙሉ ለሙሉ ለመቆጣጠርም 2 ሰዓት ፈጅቷል ነው ያሉት ። የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች የአካባቢዉ ህብረተሰብና የጸጥታ ሀይሎች በጋራ ባደረጉት ርብርብ እሳቱ በአቅራቢያው ወደሚገኙ መነኮሳት መኖሪያ ቤቶች ተዛምቶ የከፋ ጉዳት እንዳያደርስ ማድረግ እንደተቻለ ነው አቶ ንጋቱ ያስረዱት ። በዚህ ሂደትም 350 ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረት ማዳን ተችሏል ብለዋል ። ፋብሪካዉ የተገነባበት ስፍራና በውስጡ የያዛቸዉ ተቀጣጣይ ዘይቶችና ከፍተኛ የሆነ የተቃጠለ ዘይት ክምችት ለእሳቱ መባባስ ከፍተኛ አስተዋጽዖ እንደነበረውም አቶ ንጋቱ ገልጸዋል፡፡ ፋብሪካዉ ከአደጋ ደህንነት አንጻር አሁንም ስጋት ውስጥ ይገኛል ነው የተባለው ።
በመቅደላዊት ይግዛው

የብሔራዊ የመታወቅ ቀንና የብሔራዊ መታወቂያ ምዝገባ ጅማሮ ተበሠረ። ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የመታወቅ ቀንን እያከበረች ነው። የዚህ ቀን መከበር ዜጎች የማንነት ዕውቅና አግኝተው በሀገራቸውና በ...
16/09/2022

የብሔራዊ የመታወቅ ቀንና የብሔራዊ መታወቂያ ምዝገባ ጅማሮ ተበሠረ።
ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የመታወቅ ቀንን እያከበረች ነው። የዚህ ቀን መከበር ዜጎች የማንነት ዕውቅና አግኝተው በሀገራቸውና በሌሎችም አካባቢዎች የሚፈልጉትን አገልግሎቶች እንዲያገኙ የሚረዳ በመሆኑ ይህንን ግንዛቤ ለማሰራጨት መሆኑ ተነግሯል። ሁነቱ በሸራተን አዲስ ሲከበር የጠቅላይ ሚኒስትሩ የካቢኔ ጉዳዮች አማካሪ አቶ ተፈሪ ፍቅሬ፣ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዲኤታ ወይዘሮ ሠላማዊት ካሳ፣ የብሔራዊ መታወቂያ አገልግሎት ስራ አስኪያጅ አቶ ዮዳሄ አርአያ ስላሴ እና ሌሎች የመንግስትና የግል የስራ ሃላፊዎች የተገኙ ሲሆን የብሔራዊ መታወቂያ ምዝገባ ማስጀመር መርሃ ግብር ተካሂዷል። ዓለም ላይ ከአንድ ነጥብ ሁለት ቢሊየን በላይ ሰዎች ምንም ዓይነት የማንነት መታወቂያ የላቸውም። ይህ አሃዝ ወደ ሀገራችን ሲመጣ በብዙ የሚመነዘር ሲሆን አሁን የተጀመረው ብሔራዊ መታወቂያ ምዝገባ ስርዓት ይህንን ችግር ያስቀራል ተብሏል። አቶ ዮዳሄ አርአያ ስላሴ በማስጀመሪያ ስነ ስርዓቱ ላይ እንዳሉት የብሔራዊ መታወቂያ ምዝገባ መካሄድ መንግስት ለያዘው የሁለንተናዊ ዲጂታላይዜሽን ጉዞ በጎ አስተዋፅኦ የሚያደርግ ሲሆን አሁን የተጀመረውን የሙከራ ምዝገባ መነሻ በማድረግ እስከ 2018 ድረስ ሰባ ሚሊየን ኢትዮጵያውያንን ለመመዝገብ ማቀዳቸውን ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ነጋዴዎች አሰራራቸውን ከማዘመን ባሻገር ከመንግስትና ከሌሎች አካላት ጋር በመተባበር ሀገራዊ ሃላፊነታቸውን እንዲወጡ ያደርጋል ያሉት ደግሞ የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ፕሬዝደንት ኢንጂነር መላኩ እዘዘው ናቸው። የምክር ቤቱ አባላትና መላው ኢትዮጵያውያን በዚህ መልካም አጋጣሚ ላይ በመሳተፍ የኢትዮጵያን የዲጂታል ጉዞ እንዲደግፉና ትርፋማና ታማኝ አገልግሎት እንዲያቀርቡም ጠይቀዋል። በመድረኩ ላይ የተለያዩ ሚኒስትሮችና ሚኒስትር ዲኤታዎች መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን የብሔራዊ መታወቂያ አገልግሎት ለቀጣይ ዕቅዶቻቸው መሣካት ምን ያህል ጠቃሚ እንደሆነ አብራርተዋል።

በጋምቤላ ክልል ከ187 ሺህ በላይ ዜጎች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸዉ ተገለፀ።በጋምቤላ ክልል ከቀናት በፊት በተከሰተ የጎርፍ አደጋ በአስር ወረዳዎች ላይ ከፍተኛ ዉድመት ያስከ...
15/09/2022

በጋምቤላ ክልል ከ187 ሺህ በላይ ዜጎች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸዉ ተገለፀ።

በጋምቤላ ክልል ከቀናት በፊት በተከሰተ የጎርፍ አደጋ በአስር ወረዳዎች ላይ ከፍተኛ ዉድመት ያስከተለ ሲሆን ሁለት ወረዳዎችን ደግሞ ሙሉ በሙሉ ማዉደሙን የጋምቤላ ክልል አደጋ ስጋት ስራ አመራር አገልግሎት ዋና ሃላፊ አቶ ጋትፔል ሙል ለአዋሽ ራድዮ ተናግረዋል።

አደጋዉ ከአስር ወረዳዎች ላይ 187ሺ ዜጎችን ያፈናቀለ ሲሆን በጎርፉ በሺዎች የሚቆጠሩ የቤት እንስሳቶች መወሰዳቸዉም ተነግሯል።
የተከሰተዉ ይህ የጎርፍ አደጋ ከአንድ መቶ ሰማንያ ስባት ሺህ በላይ ዜጎችን ከቤት ንብረታቸዉ ከማፈናቀሉ በተጨማሪም በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ንብረት ማዉደሙንም የጋምቤላ ክልል መንግስት አስታዉቋል፡፡

ይህ በአስር ወረዳዎች ላይ ከፍተኛ ወድመት ያስከተለዉ የጎርፍ አደጋ ዜጎችን ከአካባቢያቸዉ ከማፈናቀል በተጨማሪ በመቶ ሚሊዮኖች የሚገመት መንገድን እና ድልድዮችን ጨምሮ በርካታ የመሰረተ ልማት አዉታሮችን ጎርፉ ማዉደሙን የአግልግሎቱ ሀላፊ አቶ ጋትፔል ሙል ከጣብያችን ጋር በነበራቸዉ ቆይታ አንስተዋል።

የጎርፍ አደጋዉ በዜጎች ላይ ካደረሰዉ ጉዳት እና ማፈናቀል በተጨማሪ በርካታ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን ከጥቅም ዉጪ ማድረጉም ተመላክቷል ፡፡ከዚህ ባለፈም በ125 ትምህርት ቤቶች ላይ ከፍተኛ ጉዳት በማስከተሉ ትምህርት ቤቶቹ ለጊዜዉ አገልግሎት እንዳይሰጡ ማድረጉን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታዉቋል።

በጋምቤላ ክልል ከ187 ሺህ በላይ ዜጎች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸዉ ተገለፀ። በጋምቤላ ክልል ከቀናት በፊት በተከሰተ የጎርፍ አደጋ በአስር ወረዳዎች ላይ ከፍተኛ ዉድመ.....

ሃገራችን የግንባታ ዘርፍ እንዲዘምን የኮንስትራክሽን ግብዓቶችን በሃገር ውስጥ ማምረት እንደሚገባ ተናግሯል የሃገራችን የግንባታ ዘርፍ እንዲዘምን የኮንስትራክሽን ግብዓቶችን በሃገር ውስጥ ማምረ...
14/09/2022

ሃገራችን የግንባታ ዘርፍ እንዲዘምን የኮንስትራክሽን ግብዓቶችን በሃገር ውስጥ ማምረት እንደሚገባ ተናግሯል የሃገራችን የግንባታ ዘርፍ እንዲዘምን የኮንስትራክሽን ግብዓቶችን በሃገር ውስጥ ማምረት እንደሚገባ የተናገሩት የአዲስ አበባ የንግዱ ዘርፍ ማሕበራትና የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ናቸው፡፡

የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች ግንባታ ሥራ ትልቁን ድርሻ የሚይዘው በወቅቱ የግብዓቶች አቅርቦትን የማረጋገጥ ሥራ ነው። በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ውስጥ የሚካሄዱ የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች 60 በመቶ የግብዓት አቅርቦት የማረጋገጥ ሥራ መሆኑን በዘርፉ የተሰሩ ጥናቶች ያመለክታሉ። የግብዓት አቅርቦትን በበቂ ሁኔታ ማረጋገጥ መቻል የአንድን የኮንስትራክሽን ፕሮጀክት አብዛኛውን ሥራ እንደመሥራት ይቆጠራል። ሆኖም በኢትዮጵያ ውስጥ ዘርፉን ጠፍንገው ከያዙት ችግሮች ውስጥ የግብዓቶች እጥረት በግንባር ቀደምትነት ተጠቃሽ ነው። የሀገር ውስጥ የግንባታ ግብዓት አቅርቦት የፍላጎቱን ያህል ባለመሆኑ ከውጭ አገር ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ ግብዓቶች መጠን ከፍተኛ ነው።

የሃገራችን የግንባታ ዘርፍ እንዲዘምን የኮንስትራክሽን ግብዓቶችን በሃገር ውስጥ ማምረት እንደሚገባ ተናግሯል የሃገራችን የግንባታ ዘርፍ እንዲዘምን የኮንስትራክሽን ግብዓቶችን በሃ....

በጋዝ ሲሊንደር ፍንዳታ አራት የእሳት አደጋ ሰራተኞች ላይ ከባድ ጉዳት ደረሰበጋዝ ሲሊንደር መሸጫ ሱቅ ላይ በደረሰ የእሳት አደጋና  እሳቱን ተከትሎ በተፈጠረ  የጋዝ ሲሊንደር ፍንዳታ ቦታዉ ...
14/09/2022

በጋዝ ሲሊንደር ፍንዳታ አራት የእሳት አደጋ ሰራተኞች ላይ ከባድ ጉዳት ደረሰ

በጋዝ ሲሊንደር መሸጫ ሱቅ ላይ በደረሰ የእሳት አደጋና እሳቱን ተከትሎ በተፈጠረ የጋዝ ሲሊንደር ፍንዳታ ቦታዉ ላይ ቀድሞ በደረሱት አራት የእሳት አደጋ ሰራተኞቹ ላይ ከባድ ጉዳት መድረሱን የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።

አደጋው የደረሰው አለተ ማክሰኞ መስከረም 3 ቀን ከምሽቱ 5 ሰዓት ላይ በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ልዩ ቦታ ሱማሌ ተራ አካባቢ በሚገኝ የጋዝ ሲሊንደር መሸጫ ሱቅ መሆኑን የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለአዋሽ ራዲዮ ተናግረዋል።

የአደጋ ጊዜ ሰራተኞቹ አስፈላጊዉን ጥንቃቄ እንዳያደርጉ የጋዝ ሲሊንደር መሸጫ እንደነበረ መረጃ አልነበራቸዉ ሲሉ አቶ ንጋቱ ጨምረው ተናግረዋል። በንግድ ሱቁ ላይ የተለጠፈዉ የኤሌክትሮኒክስና የባኞ እቃዎች መሸጫ ማስታወቂያ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞቹን አሳስቷቸዋል ይላሉ ።

ጉዳት የደረሰባቸዉ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች በአቤት ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸዉ ይገኛል። በንግድ ቤቱ ላይ የደረሰዉ የእሳት አደጋ ተዛምቶ ጉዳት እንዳያደርስ በሌሎች የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች እሳቱ በቁጥጥር ስር ዉሏል በለዋል ።

ማናቸዉም የንግድና መሰል አገልግሎት የሚሰጡ ግለሰቦችና ተቋማት በዉስጣቸዉ ስለሚሸጡት ወይም ስለሚያከማቹት ንብረት አይነቶች በግልጽ ማስታወቂያ ማሳወቅ እንዲህ ያልታሰበ አደጋን ማስቀረት እንደሚያስችል ኮሚሽኑ አስታውቃል።
የኮሚሽኑ ኮሚሽነር እና አመራሮች ጉዳት የደረሰባቸውን ባለሙያዎችን ሆስፒታል ተገኝተው ጎብኝተዋል።

በመቅደላዊት ይግዛው

ኢትዮጵያ ከፍተኛ የታዳሽ ሀይል ኃብት ያላት ሀገር ትሁን እንጂ ጥቅም ላይ የሚውል እንደሌለ ተነግሯል ። አፍሪካ አስር ቢሊየን ኪሎ ዋት ለማመንጨት የሚያስችል የተትረፈረፈ የፅሀይ ሃይል እንዳ...
10/09/2022

ኢትዮጵያ ከፍተኛ የታዳሽ ሀይል ኃብት ያላት ሀገር ትሁን እንጂ ጥቅም ላይ የሚውል እንደሌለ ተነግሯል ። አፍሪካ አስር ቢሊየን ኪሎ ዋት ለማመንጨት የሚያስችል የተትረፈረፈ የፅሀይ ሃይል እንዳላት ይነገራል ።

ይህንንም ሃብት ጥቅም ላይ ለማዋል የፅሃይ ሃይል ቴክኖሎጂ በስፋት በማሰራጨት እና አፍሪካን ባላት ሃብት ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ እንደሆነ ተገልጿል ።

የኢትዮጵያ የዉሃ እና ኢነርጂ ሚንስትር ዴታ ዶክተር ሱልጣን ዋሊ እንደገለፁት ኢትዮጵያ ከፍተኛ የሆነ የታዳሽ ሃይል ሃብት እንዳላት ጠቁመው ከነዚህም ውስጥ ከሃይድሮ ፓወር ብቻ የሚገኘው አጠቃላይ እምቅ ሃብት 45 (አርባ አምስት) ሺህ ሜጋ ዋት በላይ ሲሆን የከርሰምድር ሙቀትንም በተመለከተ ጥናቶች እንደሚያሳዩት 10 ሺህ (አስር ሺህ) ሜጋ ዋት እንደሚሆንም ተናግረዋል ።

ኢትዮጵያ ከፍተኛ የታዳሽ ሀይል ኃብት ያላት ሀገር ትሁን እንጂ ጥቅም ላይ የሚውል እንደሌለ ተነግሯል ። አፍሪካ አስር ቢሊየን ኪሎ ዋት ለማመንጨት የሚያስችል የተትረፈረፈ የፅሀይ ሃይል...

በፈረንጆቹ የዘመን ቀመር ከ1980 ዓም ጀምሮ በበርካታ አለም ሀገራት ተግባራዊ መደረግ የተጀመረዉ የአካባቢ ምርጫ በሃገራችን ኢትዮጵያም በተያዘዉ አመት እንደሚካሄድ ተነግሯል፡፡ከ1988 እስክ...
06/09/2022

በፈረንጆቹ የዘመን ቀመር ከ1980 ዓም ጀምሮ በበርካታ አለም ሀገራት ተግባራዊ መደረግ የተጀመረዉ የአካባቢ ምርጫ በሃገራችን ኢትዮጵያም በተያዘዉ አመት እንደሚካሄድ ተነግሯል፡፡
ከ1988 እስክ 2006 ዓም ለአራት ጊዜ ያክል በሃገራችን ኢትዮጵያ የተካሄደዉ ይህ ምርጫ በተያዘዉ አዲሱ በጀት ዓመት የጽጥታ ችግር በሌለባቸዉ የሀገሪቱ ከፍሎች የአካባቢ ምርጫ እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ዋና ሰብሳቢ ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ አስታዉቀዋል፡፡፡፡
ከዚህ በፊት የተደረጉት የአካባቢ ምርጫዎች ምንም እንኳን በመላዉ የሃገሪቱ ክፍሎች እና አካባቢዎች ተደርገዋል ማለት ባይቻልም ኢትዮጵያ ለአራት ጊሄ ወይንም ለአራት ዙር የአካባቢ ምርጫ ማድረጓን የታሪክ ድርሳናት ያወሳሉ፡፡
ከዚህ በተጨማሪ ከዚህ በፊት ተደርገዉ የነበሩ የአካባቢ ምርጫዎች ግልጽኝነት የጎደላቸዉ ፡ነጻ እና ገለልተኛ በሆነ አካል ያልተመሩ እና ገዢዉ ፓርቲ በፈላጭ ቆራጭነት ያሻዉን ሲያደርግ እና ሲወስን የነበረበት ወቅት እንደነበር በሃገሪቱ የሚንቀሳቀሱ የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች በድፍረት ይናገራሉ፡፡
እንኳንስ የአካባቢ ምርጫ ብሄራዊ ምርጫንም በቅጡ መከወን በቻለች የሚሉ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎችም ቢሆኑ ጥቂቶች አይደሉም፡፡

በፈረንጆቹ የዘመን ቀመር ከ1980 ዓም ጀምሮ በበርካታ አለም ሀገራት ተግባራዊ መደረግ የተጀመረዉ የአካባቢ ምርጫ በሃገራችን ኢትዮጵያም በተያዘዉ አመት እንደሚካሄድ ተነግሯል፡፡ ከ1988 እ....

በኡጋንዳ አንበሶችን ገድለዋል የተባሉ ሁለት ሰዎች በ17 ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጡ።የኡጋንዳ ፍርድ ቤት በንግስት ኤልሳቤት ብሔራዊ ፓርክ ውስጥ ስድስት አንበሶችን ገድለዋል ያላቸውን ሁለት ወን...
02/09/2022

በኡጋንዳ አንበሶችን ገድለዋል የተባሉ ሁለት ሰዎች በ17 ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጡ።

የኡጋንዳ ፍርድ ቤት በንግስት ኤልሳቤት ብሔራዊ ፓርክ ውስጥ ስድስት አንበሶችን ገድለዋል ያላቸውን ሁለት ወንዶችን እያንዳንዳቸው በ17 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጡ ወሰነ።

አንበሶቹ የተገደሉት የዛሬ ዓመት ሲሆን ሁለቱ ሰዎች በቅድሚያ አንበሶቹን በመመረዝ እና ከአንገታቸው በላይ ያለውን የሰውነት ክፍል ቆርጦ በመውሰድ ቀሪ አካላቸው በአሞራ እንዲበላ ማድረጋቸው ተነግሯል።

ከዚህ ድርጊት በኋላ ኡጋንዳ በታሪኳ ከፍተኛ የሚባል ቅጣት የሚያስከትል ህግ ያወጣች ሲሆን በመሠል ድርጊት ውስጥ የተሳተፈን ግለሰብ የሚጠቁም ኡጋንዳዊ ሁለት ሺ አምስት መቶ የአሜሪካ ዶላር እንደሚሸለምም ተደንግጓል።

ቪንሰንት ቱሙሂርዌ እና ሮበርት አሪዮ የተባሉት የ49 እና 40 ዓመት ግለሰቦች ከአንበሶቹ ግድያ በተጨማሪ ያልተፈቀደ አደን በማድረግ በርካታ የአዕዋፍና እንስሳት ዝርያዎችን መግደላቸው በ14 ምስክሮች ተመስክሮባቸዋል።

በኡጋንዳ አንድ የአንበሳ ጭንቅላት አስር ዶላር የሚሸጥ ሲሆን ስቡ ደግሞ አስራ አምስት ዶላር ያወጣል።

ዘገባው የአናዶሉ ነው።

የዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመዲናዋን የትራንስፖርት ችግሮች የሚያቃልሉና የመንገድ መሰረተ ልማትን ይበልጥ ለማዘመን የሚረዱ የ3 የመንገድ ፕሮጀክቶችን የፊርማ ስነ ስርዓት አከናወነ፡፡የአዲ...
30/08/2022

የዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመዲናዋን የትራንስፖርት ችግሮች የሚያቃልሉና የመንገድ መሰረተ ልማትን ይበልጥ ለማዘመን የሚረዱ የ3 የመንገድ ፕሮጀክቶችን የፊርማ ስነ ስርዓት አከናወነ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 3 ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ወጪ የሚደረግባቸዉ በአጠቃላይ ከ10 ኪሎሜትር በላይ ርዝመት እንዲሁም ከ15-30 ሜትር የጎን ስፋት ያላቸዉን 3 የመንገዶችና ድልድይ ፕሮጀክት ግንባታዎችን ሊያከናዉን እንደሆነ አስታወቀ፡፡
ፕሮጀክቶቹ በከተማ አስተዳደሩ በጀትና በአለም ባንክ ብድር የሚከናወኑ መሆናቸዉ ተገልጿል::

የመጀመሪያዉ የአፍሪካ ጎዳና -ኤድናሞል አደባባይ-22ማዞሪያ -እንግሊዝ ኢንባሲ የአስፋልት መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ሰሆን 4.4 ኪሎሜትር እርዝመት እንዳለዉ ተገልጿል፡፡
ከ2.4-4 ሜትር ስፋት ያለዉ የእግረኛ መንገድ ፤2ሜትር ስፋት ያለዉ የብስክሌት ብቻ መሄጃ መንገድ 9የሳይክል ማቆሚያ 3 የሳይክል ማከራያ ቦታዎች እንደሚያካትትና ለከተማዋ የመጀመሪያ የሆነ የመንገድላይ የደህንነት ቁጥጥር ስርአት ያካተተ ዲዛይን መሆኑንም ይፋ ተደርጓል:: ይህንን ስራ የሚሰራዉ ኮንትራክተር የቻይና ሲቪል ኢንጅነሪንግ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን እንደሆነ ተገልጿል::

የዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመዲናዋን የትራንስፖርት ችግሮች የሚያቃልሉና የመንገድ መሰረተ ልማትን ይበልጥ ለማዘመን የሚረዱ የ3 የመንገድ ፕሮጀክቶችን የፊርማ ስነ ስርዓት አከናወ...

ፈረስ ትራንስፖርት ከ1 ሚሊየን ብር በላይ ለበጎ አድራጊ ተቋማት አስረከበ።የፈረስ ትራንስፖርት ቴክኖሎጂ አቅራቢ የሆነው ፈረስ ትራንስፖርት ከተሳፋሪዎችና አሽከርካሪዎች የሰበሰበውን ከአንድ ሚ...
27/08/2022

ፈረስ ትራንስፖርት ከ1 ሚሊየን ብር በላይ ለበጎ አድራጊ ተቋማት አስረከበ።

የፈረስ ትራንስፖርት ቴክኖሎጂ አቅራቢ የሆነው ፈረስ ትራንስፖርት ከተሳፋሪዎችና አሽከርካሪዎች የሰበሰበውን ከአንድ ሚሊየን ብር በላይ የሚሆን ሀብት ለበጎ አድራጊ ተቋማት አስረክቧል። ይህ ሁለተኛ ዙር ገንዘብ የማስረከብ ተግባር ከግብረ ሰናይ ድርጅቶች በተጨማሪ ለታላላቅ ሀገራዊ ፕሮጀክቶችም ተበርክቷል።

በዚሁ መሠረት ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ከአንድ መቶ ሺ ብር በላይ፤ ለቢላሉል ሐበሽ የልማትና የመረዳጃ ዕድር ከአንድ መቶ ሺ ብር በላይ፤ ለጌርጌሴኖን የአእምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል ከ142 ሺ ብር በላይ እና ለኢትዮጵያ የልብ ህሙማን ማዕከል ከ369 ሺ ብር በላይ ድርጅቱ የሰበሰበውን ማይልስ ወደ ብር ቀይሮ አበርክቶላቸዋል።

የገንዘብ መጠኑ የተለያየው ተጠቃሚዎች በመረጡት የዕርዳታ መሰብሰቢያ መተግበሪያ (application ) ላይ ባዘዙት መሠረት መሆኑም ተነግሯል።

በልገሳ መርሃ ግብሩ በቅርቡ የፈረስ ትራንስፖርት አገልግሎት እየሰጡ ሕይወታቸውን ላጡ ሶስት አሽከርካሪዎች ለቤተሰቦቻቸው ለእያንዳንዳቸው የሃምሳ ሺ ብር ስጦታ ተደርጓል።

የፈረስ ትራንስፖርት ከአገልግሎት ተጠቃሚዎቹ ከእያንዳንዱ ጉዞ የ5 በመቶ የፈረስ ማይልስ ተመላሽ በማድረግ የሚሰጥ ሲሆን ተመላሽ የተደረገላቸው ደንበኞች ያገኙትን ማይልስ ወደ ተለያዩ ጥቅሞች እንዲቀይሩ፣ ደግመው ጉዞ እንዲያደርጉና በስጦታ እንዲያበረክቱ ያመቻቸ የከተማችን የመጀመሪያ የትራንስፖርት ዘርፍ ሆኗል።

ፈረስ ትራንስፖርት አሁን አገልግሎት እየሰጠ ያለው በአዲስ አበባ ከተማ ሲሆን በቀጣይ በክልል ከተሞችና በጎረቤት ሀገራት የሚሰፋ መሆኑ ታውቋል።

የትራንስፖርት ቴክኖሎጂ አቅራቢው ፈረስ በ2015 አዲስ ዓመት " ፈረሰኛ " የሚል ስያሜ የሰጠውን " የዴሊቨሪ አገልግሎት " ወደ ስራ እንደሚገባ ተነግሯል።

ይህ የስጦታ መርሃ ግብር በሚቀጥለው ዓመትም በሶስተኛ ዙር የሚቀጥል ሲሆን #የሰንደቅ ዓላማ ፕሮጀክት ለሆነው ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በድጋሚ፤ ለኢትዮጵያ ካንሰር ህሙማን፤ ለኢትዮጵያ ዲያሊሲስ ማዕከል ፤ ለዘውዲቱ መሸሻ የሕፃናት እና ቤተሰብ በጎ አድራጎት ማህበር እና ለሜቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር ተሰብስቦ የሚበረከት መሆኑም ተገልጿል።

በዘመድኩን ብሩ

የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የውሀ ሙሌት ጋር ተያይዞ ዛሬም ግብፅእና ሱዳን የሀሰት ትርክት ለአለምአቀፉ ማህበረሰብ በተገኘው አጋጣሚ እያስተጋቡ ነው ተባለ፡፡ከታላቁ ህዳሴ ግድብ ጋር ተያይዞ መልካ...
26/08/2022

የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የውሀ ሙሌት ጋር ተያይዞ ዛሬም ግብፅእና ሱዳን የሀሰት ትርክት ለአለምአቀፉ ማህበረሰብ በተገኘው አጋጣሚ እያስተጋቡ ነው ተባለ፡፡
ከታላቁ ህዳሴ ግድብ ጋር ተያይዞ መልካቸዉን በመቀያየር የሚወጡ የሀሰት መረጃዎች መበራከታቸዉ የሚታወቅ ነዉ::
ይህንን እና መሰል ችግሮች በተመለከተ ከፍተኛ የመንግስት ሀላፊዎች ስለግድቡ ያላቸዉን እዉነታ ለአለም አቀፉ ማህበረሰቡ ሲናገሩ ቆይተዋል::
ከነዚህም መካከል የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተጠቃሽ ናቸዉ::

አምባሳደሩ ኢትዮጲያ በአባይ ወንዝ ላይ የያዘችዉ የጋራ ትብብር ያልተዋጠላቸዉ ግብፅና ሱዳን በኢትዮጲያ ላይ ያልተገባ ጫና ለማሳደር ያልፈነቀሉት ድንጋይ አልነበረም ማለታቸዉ እነዚህን ሀገራት አስደንግጧል::

ዛሬም ግብፅና ሱዳን በአባይ ወንዝ ዙሪያየሀሰት ወሬ ለማሰራጨት አለመታከታቸዉን መረጃዎች ያመለክታሉ::
የኢትዮጲያ ህዳሴ ግድብን አራተኛ ዙር የዉሀ ሙሌት ለማከናወን ዝግጅት እየተደረገ ነዉ በሚል መረጃዎች ላይ ግብፅና ሱዳን የተንሸዋረረ አመለካከት ይዘዉ ወሬዎችን ሲያራግቡ እንደተሰሙ የዘርፉ ባለሙያዎችተናግረዋል::

የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የውሀ ሙሌት ጋር ተያይዞ ዛሬም ግብፅእና ሱዳን የሀሰት ትርክት ለአለምአቀፉ ማህበረሰብ በተገኘው አጋጣሚ እያስተጋቡ ነው ተባለ፡፡ ከታላቁ ህዳሴ ግድብ ጋር ተያ....

ከሳውዲ አረቢያ የተመላሽ ዜጎች ቁጥር 68572 መድረሱ ተገለፀ ።በሳውዲ አረቢያ በተለያዩ ችግሮች ውስጥ የነበሩ ዜጎችን ወደሃገራቸው በመመለስ ተግባር የተለያዩ ሴክተር መስሪያ ቤቶች በጋራ በ...
24/08/2022

ከሳውዲ አረቢያ የተመላሽ ዜጎች ቁጥር 68572 መድረሱ ተገለፀ ።

በሳውዲ አረቢያ በተለያዩ ችግሮች ውስጥ የነበሩ ዜጎችን ወደሃገራቸው በመመለስ ተግባር የተለያዩ ሴክተር መስሪያ ቤቶች በጋራ በመሆን የተለያዩ ስራዎች ሲከወኑ መቆየታቸው የሚታወቅ ነወ ።

በዚህም ሂደት ተመላሽ ዜጎችን አቀባበል እና አሸኛኘት መጠለያ፣ ምግብ፣ የስነልቦና ምክርን ነጻ ትራንስፖርትን ጨምሮ እየተከናወነ ባለዉ ተግባር ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን የፌዴራል አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ሰፊ ስራዎችን እየሰራ እንደሆነ ገልጿል ።

የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ደበበ ዘውዴ ለአዋሽ ራዲዮ እንደገለፁት ፦በሳውዲ አረቢያ በተለያየ ችግር ውስጥ የነበሩ ዜጎችን ወደ ሃገራቸው በመመለስ ሂደት ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ነሃሴ 16 2014 ዓ.ም ድረስ 68572 ኢትዮጱያዊያን ዜጎችን ወደ ሃገራቸው መመለስ እንደተቻለ ተናግረዋል ።

ከተመላሾቹ መካከልም ከ60 ሺህ በላይ የሚሆኑት ዜጎች ወደየ ቅያቸወ ተመልሰዋል 3ሺህ የሚጠጉ ማለትም መዳረሻቸው ትግራይ የሆነ አስፈላጊው ድጋፍ እየተደረገላቸው በጊዜአዊ መጠለያ እንደሚገኙ ሃላፊው አሰረድተዋል ።

በመቅደላዊት ይግዛው

በዜግነት አገልግሎት "በጎነት ለጤናችን” በሚል መሪ ቃል ነጻ የህክምናና የምርመራ አገልግሎት  በዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል ተጀመረ ። በዜግነት አገልግሎት ነፃ የጤና ምርመራ እና የህክምና አ...
22/08/2022

በዜግነት አገልግሎት "በጎነት ለጤናችን” በሚል መሪ ቃል ነጻ የህክምናና የምርመራ አገልግሎት በዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል ተጀመረ ።


በዜግነት አገልግሎት ነፃ የጤና ምርመራ እና የህክምና አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ስራ ‘’በጎነት ለጤናችን’’ በሚል መሪ ቃል በዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል መሰጠት ተጀምሯል ።

የዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል ስራ አስፈፃሚ ዶክተር ብርሃኑ አበራ ለአዋሽ ራዲዮ እንደገለፁት ለአንድ ሳምንት የሚቆይ የነጻ ህክምና ማለትም መክፈል የማይችሉ እና በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ላሉ ዜጎች መሰጠት መጀመሩን ተናግረዋል ።

በከተማዋ በሚከናወነው የዜግነት አገልግሎት የተለያየ የህክምና አገልግሎት እንዲያገኙ መታቀዱንም ግልጸዉ በሆስፒታሉም የሚሰጡ ህክመናዎች እንደ አብነትም የቅድመ ካንሰር ምርመራ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች እንደ ስኳር ድም ግፊት
ተላላፊ ከሆኑት ደግሞ የቲቪ የኤችአይቪ እንዲሁም የአይን እና የጥርስ ህክምናን ጨምሮ የተለያዩ ህክምናዎች በመርሃ ግብሩ እንደሚሰጥ ነግረውናል

በሆስፒታሉ የተዘረዘሩትን የህክምና አይነቶች ለማግኘት ለሚመጡት ታካሚዎች በሙሉ የነፃ የህክምና አገልግሎት ለመስጠት ታቅዶ እየተሠራ ነው ብለዋል።

በከተማዋ በሚከናወነው የዜግነት አገልግሎት 17 ሺህ አቅመ ደካሞች የተለያየ የህክምና አገልግሎት እንዲያገኙ መታቀዱንም ተናግረዋል፡፡

የተጀመረው መርሐ ግብርም በሃገሪቱ ባሉ በሁሉም ጤና ተቋማት እንደሚሰጥም እና መክፈል የማይችሉ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ በነፃ የህክምናና የምርመራ አገልግሎት እንዲያገኙ የሚያስችል መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ነፃ የምርመራና የህክምና አገልግሎቱ አቅመ ደካማ የሆኑ የሕብረተሰብ ክፍሎችን እና ኑሯቸውን በጎዳና ላይ ያደረጉ ዜጎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ተነግሯል ።

በመቅደላዊት ይግዛው

የአሸንድየ በአልን ለማክበር በላስታ ላሊበላ ዝግጅት መጠናቀቁን እና የሻደይ በአልን ደግሞ በዋግ ህምራ ሰቆጣ ለማክበር እንዲሁ ዝግጅት መጠናቀቁ ተገልጿል ።በሃገራችን በነሃሴ ወር በየአመቱ በ...
20/08/2022

የአሸንድየ በአልን ለማክበር በላስታ ላሊበላ ዝግጅት መጠናቀቁን እና የሻደይ በአልን ደግሞ በዋግ ህምራ ሰቆጣ ለማክበር እንዲሁ ዝግጅት መጠናቀቁ ተገልጿል ።

በሃገራችን በነሃሴ ወር በየአመቱ በትግራይ እና በአማራ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች ላይ የሚከበረው አሸንድየ በላስታ ቅዱስ ላሊበላ ፤ሻደይ በሰቆጣ፤ ሶለል በራያ ቆቦ አሸንዳ በትግራይ በድምቀት ይከበራሉ ።

በአሉ ፍቅር ይቅር ባይነት እና መልካም ተግባቦት በተግባር የሚንጸባረቅበት በአል ነው ።በአሉ በልጃገረዶች ይበልጥ ትኩረት ተሰጥቶት ይከበራል ።
ልጃገረዶች አደባባይ ወጥተው የሚያከብሩት ሃይማኖታዊ እና ባህላዊ በአል ነው ።

አሸንድየ በላስታ ላሊበላ ልጃገረዶች ዘንድ በጉጉት የሚጠበቅ የነሃሴ ወር ልዩ በአል ነው ።
በአሉ ከነሃሴ 16 ጀምሮ እሰከ ነሃሴ 18 2014 በልዩ ልዩ ሁነቶች ይከበራል ።
የበአሉ ዋና ባለቤቶች ልጃገረዶች ይሁኑ እንጂ እናቶች እና ልጆችም በባህላዊ አልባሳት እና ጌጣ ጌጦች ደምቀው የሚታዩበት የሴቶች የነሃሴ ገጸ በረከት ነው ።

የአሸንድየ በአልን ለማክበር በላስታ ላሊበላ ዝግጅት መጠናቀቁን እና የሻደይ በአልን ደግሞ በዋግ ህምራ ሰቆጣ ለማክበር እንዲሁ ዝግጅት መጠናቀቁ ተገልጿል ። በሃገራችን በነሃሴ ወር በ....

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የአካባቢ ምርጫ ሊያካሔድ እንደሆነ ተናገረ፡፡ዜጎች ከታችኛዉ የቀበሌ መዋቅር ጀምሮ የሚስተዳድራቸዉን አካል በቀጥታ ባለመምረጣቸዉ የአካባቢ ምርጫ ሊካሄድ እንደሆ...
19/08/2022

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የአካባቢ ምርጫ ሊያካሔድ እንደሆነ ተናገረ፡፡
ዜጎች ከታችኛዉ የቀበሌ መዋቅር ጀምሮ የሚስተዳድራቸዉን አካል በቀጥታ ባለመምረጣቸዉ የአካባቢ ምርጫ ሊካሄድ እንደሆነ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ፡፡
ምራጫ ቦርድ ለአምስተኛ ጊዜ ሰለሚካሄደዉ የአካባቢ ምርጫ ከተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች እና ከተወካይዎች እንዲሁም ደግሞ ከሲቪል መሃበራት ደርጅቶች ጋር ወይይት አድርጓል፡፡

በወይይቱም ለአምስተኛ ጊዜ ሰለሚካሄደዉ የአካባቢ ምርጫ እንዴት እና በምን መልኩ መካሄድ እንዳለበት ከፖለቲካ ፓርቲ ተዋካይዎች እና አመራሮች እንዲሁም ደግሞ ከሲቪል መሃበራት ጋር ወይይት ተደርጓል፡፡
በወይይቱ መድረክ ላይ ተገኝተዉ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ዋና ሰብሳቢ ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ይህ በሃገር አቀፍ ደረጃ ለአምስተኛ ጊዜ የሚካሄደዉ የአካባቢ ምርጫ ከቀደሙት አራት ምርጫዎች የተሻለ እንዲሆን የተለያዩ ስራዎች መሰራታቸዉን ሰብሳቢዋ ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የአካባቢ ምርጫ ሊያካሔድ እንደሆነ ተናገረ፡፡ ዜጎች ከታችኛዉ የቀበሌ መዋቅር ጀምሮ የሚስተዳድራቸዉን አካል በቀጥታ ባለመምረጣቸዉ የአካባቢ ምርጫ ሊ....

በበጄት ዓመቱ ለ2.7 ሚሊዮን ዜጎች ቋሚ የሥራ ዕድል ተፈጥሯል :- የሥራና ክሕሎት ሚኒስቴርበበጄት ዓመቱ ለ2.7 ሚሊዮን ዜጎች ቋሚ የሥራ ዕድል መፈጠሩን የሥራና ክሕሎት ሚኒስቴር አስታውቋል...
16/08/2022

በበጄት ዓመቱ ለ2.7 ሚሊዮን ዜጎች ቋሚ የሥራ ዕድል ተፈጥሯል :- የሥራና ክሕሎት ሚኒስቴር

በበጄት ዓመቱ ለ2.7 ሚሊዮን ዜጎች ቋሚ የሥራ ዕድል መፈጠሩን የሥራና ክሕሎት ሚኒስቴር አስታውቋል።
ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ በየ ዓመቱ ለ2 ሚሊዮን ዜጎች ቋሚ የሥራ ዕድል እንዲፈጥር ተስቦ በ2014 ዓ.ም የተቋቋመ ዐዲስ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ነው።

ሁለተኛው የሥራ ጉባዔ “ ዘላቂ ሥራ ለብሩህ ነገ ” በሚል መሪ ቃል ከነሐሴ 09 እሰከ 10 2014 ዓ.ም በሸራተን አዲስ ተካሒዷል።
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ጉባዔውን በይፋ ሲክፈቱ እንደተናገሩት ሁለተኛው የሥራ ጉባዔ በሥራ ዕድል ፈጠራ ፣ በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ እና የሥራ ደህንነት ዘርፎች ጠቃሚ የሆኑ የፖሊሲ ግብአቶች የሚገኝበት ነው፡፡

በሃገራችን ከፍተኛ የሆነ ሥራ አጥነት መኖሩ፣ የፈጠራና ክሕሎት ልማዶች አነስተኛ መሆናቸው እና በኢንዱስትሪው ዘርፍ ሠፊ ንቅናቄ መፍጠር ማስፈለጉ ደግሞ ለመሥሪያ ቤቱ በሚኒስቴር ደረጃ መቋቋም ሌላ ገፊ ምክኒያት ነው።

በበጄት ዓመቱ ለ2.7 ሚሊዮን ዜጎች ቋሚ የሥራ ዕድል ተፈጥሯል :- የሥራና ክሕሎት ሚኒስቴር በበጄት ዓመቱ ለ2.7 ሚሊዮን ዜጎች ቋሚ የሥራ ዕድል መፈጠሩን የሥራና ክሕሎት ሚኒስቴር አስታውቋል።...

ከደሴ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከ638 ሺሕ ብር በላይ የሚገመቱ የህክምና ቁሳቁሶች ተሠርቀው ሊወጡ ሲሉ ተያዙከ 10ሚሊየን በላይ ተገልጋዮችን እንደሚያስተናግድ የተነገረው የደሴ ከተማ ...
12/08/2022

ከደሴ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከ638 ሺሕ ብር በላይ የሚገመቱ የህክምና ቁሳቁሶች ተሠርቀው ሊወጡ ሲሉ ተያዙ

ከ 10ሚሊየን በላይ ተገልጋዮችን እንደሚያስተናግድ የተነገረው የደሴ ከተማ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከ638 ሺህ ብር በላይ የሚገመቱ የህክምና ቁሳቁሶች ተሠርቀው ሊወጡ ሲሉ እጅ ከፋንጅ መያዙን የከተማው አስተዳደር ኮምዩኒኬሽን ቢሮ አስታውቋል።

ከአሁን በፊትም በሆስፒታሉ ሰራተኞች ከ6 መቶ ሺሕ ብር በላይ የሚገመቱ መድሃኒቶች መዘረፋቸው ተገልጿል

የደሴ ከተማ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ አብዱልከሪም ሙስጠፋ ለአዋሽ ራዲዮ እንደገለፁት፤ እለተ ስኞ ነሐሴ 2 ቀን 2014 በግምት ከሌሊቱ 6 ሰዓት በሆስፒታሉ ውስጥ ግምታቸው ከ638 ሺሕ ብር በላይ የሚገመት የተለያዩ የህክምና መገልገያ ቁሳቁሶች በረካታ የላብራቶሪ ማሽኖችን ጨምሮ የኤሌትሪክ ገመድ ይዞ ሊወጣ ሲል በጥበቃ ሰራተኞች እጅ ከፍንጅ መያዙን ገልጸውልናል ።

ወንጀለኞችም በህገ ቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራ እየተካሄደ መሆኑ አሰረድተዋል ።

የሥርቆት ወንጀሉ ከውጭና ከሆስፒታሉ ውስጥ የተያያዘ ቁርኝት ያላቸው የሌብነት ሰንሰለት እንዳለ ታውቋልም ነው ያሉት ሃላፊው ።

ሆስፒታሉ ከዚህ ቀደም በአሸባሪው ህውሃት ቡድን ከፍተኛ ውድመት ደርሶበት የነበረ ምሆኑን ያተሱት ሃላፊው በአሁኑ ስአት አግልግሎት እንዲሰጥ ከፍተኛ ጥረት መደረጉንም አስታውሰዋል ።

አክለውም፤ የጥበቃ ሥራውን አጠናክረን ስንቀሳቀስ የሥርቆት ወንጀሉ ከውጭና ከውስጥ የተያያዘ ቁርኝት ያላቸው የሌብነት ሰንሰለት እንዳለ ተረድተናልና ህብረተሠቡ ሊያግዘንና ሊተባበረን ይገባል ብለዋል።

ስለ አባይ ምን ተባለ/ የድል ዜና/እንኳን ደስ አለን
12/08/2022

ስለ አባይ ምን ተባለ/ የድል ዜና/እንኳን ደስ አለን

ጤናይስጥልን ይህ የአዋሽ ራዲዮ የዩቱብ ቻናል ነው፡፡ በሬዲዮናችን የሚቀርቡትን የተለያዩ ፕሮግራሞች እዚህ ታገኛላችሁ፡፡ በፕሮግራማችን ላይ ያላችሁን አስተያየት ከታች በኮሜንት አ.....

በጋምቤላ ክልል ከደቡብ ሱዳን በመጡ ታጣቂዎች በተፈጸመ ጥቃት የሁለት ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን ታጣቂዎቹ ሁለት ህጻናትን አግተዉ ወስደዋል ተብሏል ።በጋምቤላ ክልል ከደቡብ ሱዳን በመጡ ታጣቂ...
11/08/2022

በጋምቤላ ክልል ከደቡብ ሱዳን በመጡ ታጣቂዎች በተፈጸመ ጥቃት የሁለት ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን ታጣቂዎቹ ሁለት ህጻናትን አግተዉ ወስደዋል ተብሏል ።

በጋምቤላ ክልል ከደቡብ ሱዳን በመጡ ታጣቂዎች የሁለት ሰዎች ህይወት አለፈ
ታጣቂዎቹ ሁለት ህጻናትን አግተዉ መውሰዳቸው ተሰምቷል ።

በጋምቤላ ክልል ዲማ ወረዳ ከደቡብ ሱዳን ተሻግረዉ የመጡ ታጣቂዎች በትናንትናዉ እለት በፈጸሙት ጥቃት የሁለት ሰዎች ህይወት ማለፉን የጋምቤላ ክልል የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ሃላፊ አቶ ኡጌቱ አዲንግ ለአዋሽ ራዲዮ ተናግረዋል።ታጣቂዎቹ ሰኞ ምሽት አደረሱት በተባለዉ ጥቃት የሁለት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ አንድ ሰዉ ላይ የአካል ጉዳት መድረሱን እና ሁለት ህጻናትንም አግተዉ መዉሰዳቸዉን ሀላፊዉ ገልጸዋል።

በጋምቤላ ክልል ከደቡብ ሱዳን በመጡ ታጣቂዎች በተፈጸመ ጥቃት የሁለት ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን ታጣቂዎቹ ሁለት ህጻናትን አግተዉ ወስደዋል ተብሏል ። በጋምቤላ ክልል ከደቡብ ሱዳን በመ...

ኢትዮጵያ ለግብጽ እና ሱዳን የግድቡን ዉሃ ሙሌት በተመለከተ መረጃ የመስጥት ግዴታ የለባትም፡፡አምባሳደር ስለሺ በቀለየታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን መሰረት ያደረገ ማንኛዉም አይነት የልማት ...
10/08/2022

ኢትዮጵያ ለግብጽ እና ሱዳን የግድቡን ዉሃ ሙሌት በተመለከተ መረጃ የመስጥት ግዴታ የለባትም፡፡አምባሳደር ስለሺ በቀለ
የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን መሰረት ያደረገ ማንኛዉም አይነት የልማት እንቅስቃሴ የ2015ቱን የካርቱምን የመርሆ ስምምነት የጣሰ ነዉ ይላሉ የግብጽ እና የሱዳን መንግስታቶች እና የሁለቱ ሀገራት የግድቡ ተደራዳሪዎች፡፡

ሀገራቱ ኢትዮጵያ ከጉያዋ የሚወጣዉን ዉሃ በመስኖ አልምታ እህል ብታበቅል፡ገድባ የኤሌክተሪክ ሃይል ብታመነጭበት፡አሳ ብታረባበት አስዉባ የቱሪዝም መስህብ ብታደርገዉም ሆነ ሌሎች መሰል የልማት ተግባራት ብታከናዉንበት በግብጽ እና ሱዳን መመዘኛ መስፈርት እንዴትም ሆነ የልማት ፕሮጀክት ሆኖ አይታያቸዉም፡፡
ምሁሮቻቸዉም ቢሆኑ ያለየሌለዉን ከመዘላበድ በዘለለ የሶስቱን ሀገራት እና የተፋሰሱን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚ የሚደርጋቸዉን ስራዎች ሲሰሩ አይስተዋሉም፡፡

ኢትዮጵያ ለግብጽ እና ሱዳን የግድቡን ዉሃ ሙሌት በተመለከተ መረጃ የመስጥት ግዴታ የለባትም፡፡አምባሳደር ስለሺ በቀለ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን መሰረት ያደረገ ማንኛዉም አይነ...

Address

Ambassador Theatre
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Awash 90.7 FM posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Awash 90.7 FM:

Videos

Share