09/09/2024
" ዘንድሮ 1,363 ትምህርት ቤቶች ምንም አይነት ተማሪ አላሳለፉም" 🙄
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ዙሪያ መግለጫ እየሰጡ ይገኛሉ።
ሚኒስትሩ የፈተናው ውጤት ለሊት 6 ሰዓት ላይ ይፋ ይደረጋል ብለዋል።
የወንዶች አማካይ ውጤት - 30.66
የሴቶች አማካይ ውጤት - 28
ዘንድሮ ብሔራዊ ፈተና ከተፈተኑት ተማሪዎች 36,409 ተማሪዎች ናቸው ያለፉት ።
አጠቃላይ ፈተናውን ያለፉ ተማሪዎች 5.4 በመቶ ናቸው።
አዲስ አበባ 10,690 ተማሪዎች በማሳለፍ ከፍተኛውን ስፍራ ይዟል። ይህ ማለት አዲስ አበባ ካስፈተናቸው ተማሪዎች በመቶኛ ሲሰላ 21.4 በመቶ አሳልፏል።
በሀገር ከፍተኛ ውጤት የተመዘገበው በትግራይ ነው።
በትግራይ ፈተናው ከ700 ነው የተሰጠው።
በወንድ ተማሪ ከቀላሚኖ 675 ከፍተኛ ውጤት ተመዝግቧል ይህም በ ኢትዮጵያ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው ተብሏል።
ሌላ በሀገር ደረጃ ከ600 ከተፈተኑት ውስጥ 575 ከተፈጥሮ ሳይንስ እንዲሁም ከማህበራዊ ሳይንስ ደግሞ 538 ከፍተኛ ውጤት ተመዝግቧል። በተፈጥሮም በማህበራዊ ሳይንስም ትልቅ ውጤት የመጣው በሴቶች ነው።
👉 ዘንድሮ 1,363 ትምህርት ቤቶች ምንም አይነት ተማሪ አላሳለፉም።
በሌላ በኩል ፤ በኦንላይን ከተፈተኑ ተማሪዎች 26.6 በመቶ የሚሆኑት አልፈዋል።