“ወይ አዲስ አበባ”ን ነገ!
================
በውቧ ቀን ቅዳሜ፣ “ወይ አዲስ አበባ” መጽሔት ተውባ ከእጃችሁ ትደርሳለች።
በዚህ ዕትም: -
☞ ኃይለጊዮርጊስ ማሞ (ጲላጦስ) “ድሃ በሕልሙ ዘይት ባይጠጣ… ” በተሰኘው ምፀታዊ መጣጥፉ መራሩን ኹነት እያዋዛ በተለየ መንገድ ያወጋናል።
☞ ኢኮኖሚስቱ ሙሼ ሰሙም እንዲሁ የኢኮኖሚያችንን ነባራዊ ሁኔታ አሳይቶን የመፍትሔ አቅጣጫውን ሙያዊ በሆነ መንገድ ይጠቁመናል። ሌላም በዚህ ዙሪያ የተፃፈ ጽሑፍም አለን።
☞ አውሮጳዊው "ራየን" ወንዝ እንደምን ለኛው "አባይ" አርአያ ሊሆን እንደሚችል አነፃፅሮ የሚነግረው አለው፤ ጌድዮን ተስፋዬ።
☞ ደራሲና ሃያሲውን አስፋው ዳምጤ፣ እንግዳችን ሆነው ከመጽሔታችን ሳሎን ውስጥ ያገኟቸዋል።
☞ ተጓዡ ጋዜጠኛ ሔኖክ ስዩም "የጁገል ሐሳቦች" የተሰኘ ውብ እና ጠለቅ ያለ ይዘት ያለው መጣጥፍ አለው። በተጨማሪም አስሩን አርበኛ ዋሻዎችም ያስተዋውቀናል።
☞ ስለ “የእኛ እና የእነሱ” ትርጉሞችና ፖለቲካዊ ፍጥጫዎች ዶ/ር ተሻገር ሽፈራው አስተማሪ ጽሑፍ ጽፏል።
☞ ገነነ መኩሪያ (ሊብሮ) በመስኮት ስላመለጠው ተጫዋች አዝናኝ በሆነ ጽሑፉ ይተርክልናል።
☞ "የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከወርቅ ወደ አልማዝ… ” የሚለን ብርሃኑ ሰሙ ነው።
☞ ብሩህ ዓለምነህ "ሜሪና ማርታ (የሁለት ስልጣኔዎች ወግ)" በተሰኘ መጣጥፉ ዶ/ር እጓለን አጣቅሶ የሚለን አለው።
☞ ዶ/ር ዮናስ ባህረጥበብ
ምኒሊክ ወስናቸው እና ኡስማን ከኡጀሌ
Minilik Wosenachew and Usman Khojali
የወይ አዲስ አበባ መፅሔት መገኛዎች
- በሁሉም ሸዋ, ጋራ እና ኦል ማርት ሱፐርማርኬቶች እንዲሁም በጃፋር መፅሐፍት መደበር
ወይ አዲስ አበባን ነገ !
==============
እንኳን አደረሳችሁ፤
የ“ወይ አዲስ አበባ” መጽሔት ስምንተኛ ዕትም በነገው ዕለት ከእጃችሁ ይገባል።
"እጃችሁ ከምን?" ለምትሉን …
ሠዓሊ እሸቱ ጥሩነህ የታዋቂው ሠዓሊና ገጣሚ ገብረክርስቶስ ደስታ ታላቅ ሥራ ስለሆነው “ጎለጎታ ወይም ሥነ-ስቅለት” አሪፍ ትንታኔ ጽፏል።
ሔኖክ ስዩም ደግሞ “የትንሳኤ እሴታችን፣ ለእሴት አልባ ፖለቲካችን” ይለናል።
ዶ/ር ተሻገር ሽፈራው፣ “የህዳሴው ግድብ በሱዳንና ግብፅ ‘ኩስምስ’ እይታ” በሚል መጣጥፉ የሁለቱን ሀገራት መገናኛ ብዙኃን ካርቱኖች ይዳስስልናል።
“ሁዳዴና ረመዷን፣ ትንሳኤና ዒድ ፈውስ ለምትሻ ሀገር” የሚለን አዲሱ ዘገየ ነው።
ሜይ ዴይ በኢንዱስትሪ ከተማዋ አቃቂ ምን መልክ እንደነበረው የሚያስነብበን ኃይሉ ውድነህ ነው፣ “የኢትዮጵያዋ ቺካጎ፣ አቃቂ!" በተሰኘው ጽሑፉ።
የኃይለጊዮርጊስ ማሞ (ጲላጦስ) “ዶሮ ሳይጮህ ዶሮን መብላት” የሚለው አዝናኝ ጽሑፍም በዚህ ዕትም ከተካተቱት መካከል ተጠቃሽ ነው።
ሌላም፣ ሌላም አሪፍ ጽሑፎችን ያገኙባታል።
ዶ/ር ዮናስ ባህረጥበብ፣ እስክንድር ከበደ፣ ቤልጂግ ዓሊ፣ ዮሴፍ ጥሩነህ፣ ብርሃኑ ሰሙ፣ እዝራ እጅጉና ሌሎችም የበኩላቸውን አዋጥተዋል።
እናም ለበዓል ሸመታ ላይ ታች ሲሉ እንዳይዘነጉ፣ “ወይ አዲስ አበባ” መጽሔትን ቀድመው ከእጅዎ ያስገቡ። “ወይ አዲስ አበባ”ን ያንብቡ፣ በ“ወይ
The biggest final kickoff is almost there everyone! You just relax and enjoy it at #GoldenTulip #Finals
Zefen Ena Zemen Aster Awoke Part 2
Zefen Ena Zemen Aster Awoke Part 1