"ሰአሉ ለነ ኢያቄም ወሐና ዘፈረይክሙ በቅድስና መሶበወርቅ እንተ መና"
👉🏽 በገድል በፆም በጸሎት የጸናችሁ በመና የተመሰለ ኢየሱስ ክርስቶስን የወለደች እርሷም በመሶብ ምሳሌነት በደጋግ አባቶች እና ሊቃውንት በደገኛው ምሳሌነት የተጠቀሰች ድንግል ማርያምን የወለዳችሁ ቅዱስ ኢያቄም እና ቅድስት ሐና በቃል ኪዳናችሁ ለተማጸንን ለእኛ ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ በሚሰማ ጸሎታችሁ ከክፉ ሁሉ እንድን ዘንድ ለምኑልን!!! አማልዱን!!!
👉🏽 የቅዱስ ኢያቄም እና የቅድስት ሐና ጸሎት ልመና እና በረከት በሐገራችን እና በአማላጅነታቸው በምናምን በሁላችን ይደርብን አሜን!!!
ያማረውን ጣዕመ ዜማ ባማረ ላህይ ወንድማችን ሊቀ መዘምራን ዘርይሁን ወርቅነህ እንዲህ አሰምቶናል።
ኢየሉጣ ወለደት ነቅዓ ጽጌ ረዳ
ፀሐየ ጽድቅ የዓውዳ
ሠናይ በዓለ ቂርቆስ ወኢየሉጣ ወበዓለ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል
ለወንድማችን ሊቀ መዘምራን ዘርይሁን ወርቅነህ ዕድሜን ከጤና ጋር ይስጥልን።
ዓለማትን የፈጠሩ ቅድስት ሥላሴ ለፍጥረታት ሁሉ በተለያየ አምሳል አንድነታቸውን እና ሶስትነታቸውን ይገልጣሉ። ይኸውም ይታወቅ ዘንድ በመምሬ ዛፍ ስር ለአብርሃም የሥላሴና የዋህድና ምስጢርን ከገለጹለት በኋላ "አመ ከመ ዮም እገብእ ኀቤከ" ብሎ እግዚአብሔር ወልድ ከእርሱ ባህርይ በስጋ እንደሚገለጥ አስታውቆታል።
ወደ አብርሃም ቤት በእንግድነት የገቡ ቅድስት ሥላሴ ሃይማኖታችንን እና ሀገራችንን ይጠብቁልን። አሜን!!!
እንደተለመደው ወንድማችን ሊቀ መዘምራን ዘርይሁን ወርቅነህ ለዕለቱ የሚስማማውን ቀለም እንዲህ አሰምቶናል።
👉 Like the page
👉 Share the post
👉 Telegram : https://t.me/gubaeQene
ውሉደ ብርሃን ጴጥሮስ ወጳውሎስ
የብርሃን ልጆች የተባሉ ጴጥሮስና ጳውሎስ የክርስቶስን ሃይማኖት በዓለም ዙርያ ያደረሱ የቤተ ክርስቲያን አዕማድ ናቸው። ሐምሌ አምስት ቀን በሮም አደባባይ የሰማዕትነትን ጽዋ አንዱ ቁልቁል ተዘቅዝቆ ፣ አንዱ ደግሞ በሰይፍ ተከልሎ ተቀብለዋል። የቅዱሳን አባቶቻችን የሐዋርያት በረከት እና ረድኤት ከሁላችን ጋር ይሁን።
ወንድማችን ሊቀ መዘምራን ዘርይሁን ወርቅነህ በዓሉን የተመለከተ ወረብ እንዲህ ያሰማናል።
ገነይነ ለኪ ኦ ወለተ ዳዊት
ጽርሐ ቅድሳቱ ለወልድ
ዘወርቅ ማኅፈድ
ወሡራሬሃ ዘመረግድ
አምንስቲቲ ሙኪርያ አንቲ ፋሲልያሱ
አምንስቲቲ ሙዳሱጣ አንቲ ፋሲልያሱ
አምንስቲቲ ሙአግያ አንቲ ፋሲልያሱ
ተዘከረነ እግዚኦ በውስተ መንግስትከ
አቤቱ በመንግስትህ በመጣህ ጊዜ አስበን።
Lord, remember us when you come into your kingdom.
መጋቢት ፳፯
👉 የማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያምና ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም አብያተ ክርስቲያን የማኅሌት አገልግሎት የቀደሙት አባቶችን ትውፊት ይዞ እንዲቀጥል ከሚያደርጉትና ተጠያቂ ከሆኑት ሊቃውንት መካከል አንዱ የሆኑት ርዕሰ ደብር አሰሙ አውራሪስ እና ዛሬ ላይ በህይወት የሌሉት ሌላው ሊቅ መሪጌታ ታምሩ አስማምተው የሚሏት የቤት ቀለም ስትሆን ወንድማችን ሊቀመዘምራን ዘርይሁን ወርቅነህ እንዲህ አሰምቶናል።
በእንተ ማርያም ድንግል ፤ መሐርኩከ በለኒ መድኃኔዓለም
እስመ ኄር አልቦ ፤ እንበሌከ ቃል
መድኃኔዓለም ሆይ እኔን ባርያህን ስለ ድንግል ማርያም ምሬሃለሁ በለኝ።
ቀዳማዊው ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ካንተ በቀር ፤ እንዳንተ ያለ ቸር አምላክ የለምና።
የመድኃኔዓለም ቸርነት አይለየን አሜን።
በማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያምና ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም አብያተ ክርስቲያን የነበረው የጾመ ነነዌ የመጀመርያው ቀን ጸሎተ ምህላ በቅዱስ ሲኖዶስ ትዕዛዝና መመሪያ መሰረት የተፈጸመ ሲሆን ፣ በዕለቱም ለቁጥር የበዙ ምዕመናን ጥቁር ልብስ ለብሰው በዓውደ ምህረቱ ላይ ተገኝተዋል።
የዕለቱን የወንጌል ትምህርት መምህር አብነት አስራት ወቅቱን አስመልክተው በአሁን ሰዓት ስለተፈጠረው ችግር መነሻና መፍትሄ ሰፋ አድርገው ያስተማሩ ሲሆን ፤ የአድባራቱ የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች የበገና መዝሙር አሰምተዋል። በመቀጠልም በሊቃውንቱ መሪነት ጸሎተ ምህላው ደርሷል።
በዕለቱም የአድባራቱ ዋና አስተዳዳሪ መልአከ ገነት ሀብተወልድ ተገኝ ፣ ዋና ጸሀፊው ሊቀ ስዩማን መሐሪ አድማሱ የተገኙ ሲሆን ፣ የመጨረሻው ቃለ ምዕዳን በዋና አስተዳዳሪው ተሰጥቶ መርሀ ግብሩ አብቅቷል።
ለሚቀጥሉት ሁለት ቀናት ይህ መርሐ ግብር የሚቀጥል ሲሆን ፣ በነገው ዕለት የኪዳን ጸሎት ከጠዋቱ 12፡00 ጀምሮ የሚደርስ በመሆኑ ምዕመናን በሰዓቱ እንዲገኙ ጥሪ ተላልፏል። የአድባራቱ የወጣት ማኅበራት ህብረትም መርሐ ግብሩን በማስተባበር እና ምዕመናንን በመምራት ሲያገለግሉ አምሽተዋል።
#አንድ_ቤተክርስቲያን
#አንድ_ሲኖዶስ
#አንድ_ፓትርያርክ
#Mana_Kiristaanaa_Tokkittii
#Sinoodoosii_Tokkicha
#Phaatiraarikiin_Tokkicha
#ሓንቲ_ቤተክርስቲያን
#ሓደ_ሲኖዶስ
#ሓደ_ፓትርያርክ
#eotc_one_holy_
"ወአንቲኒ ቤተ ልሄም ማኅደረ ስብሐት ኢትተርፊ ከመ ሰማዕኪ ድምጸ ብካይ ወይሌ እስመ ናሁ ንጉስኪ መድኃኔ ዓለም ያሰምዓኪ ነገረ ፍስሐ ወሐሴት ወይፈትህ ለኪ"
በጾመ ነነዌ መግቢያ በዕለተ ሰኑይ ማኅደረ ስብሐት የሀዘን ጥላ አጥልቶባታል። ከዋናው በር መግቢያ ጀምሮ እናቶች ፣ አባቶች ፣ ወጣቶችና ህጻናት ህብረ ጸሊም በለበሱት አድባራት ውስጥ ከትመዋል።
በተለምዶ "ጥቁሯ ማርያም" ከምትባለው "ኦሆ በሃሊት" ምስል ስር የእንባ ጅረት ይፈሳል። የማያቋርጥ ጩኸትም ይሰማል። በነግህ የጸሎት ጊዜ የነበረው የእናቶቻችን የሀዘን ድምጽ ልብን ይበላል።
አባቶች ፣ እናቶች እንዲሁም ወጣቶች ያለቅሳሉ። ለቅሶው ለግል አላማና ፍላጎት አይደለም። ስለ አንዲቷ ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ነው እንጂ።
ከቀዳማዊው እጨጌ ተድላ ማኅደር የሚሰማው የለቅሶ ድምጽ መልስ ይዞ ይመጣል። ብርሃናትን የሚጎናጸፍ መድኃኔዓለምም ጸሊም ልብስን ለብሶ የልጆቹን ጸሎት ይሰማል።
በማታውም መርሐ ግብር የምህላው ስነ ስርዓት ይካሄዳል። ሁላችንም በመቅደሱ እንገናኝ።
"ወናሁ እዜንወክሙ ፍስሐ ዘይከውን ለክሙ ወለኩሉ ዓለም"
"እናንተንም ሰውንም ሁሉ ደስ የሚያሰኝ ነገር እነግራቸኋለው"
ሉቃስ = ፪ ÷ ፲
መልካም የልደት በዓል