Ethio Habesha

Ethio Habesha ገፁን like & share በማድረግ ይወዳጁን!

ግን እንዲህ የሚሳሳቁት የምራቸውን ነው?
27/04/2023

ግን እንዲህ የሚሳሳቁት የምራቸውን ነው?

Just heart breaking 😭 💔💔💔ስደት፥ መፈናቀል፥ ከሰብአዊነት የወረደ፥ ለሰሚውም ግራ የሆነ ጭካኔ። የሰው ልጅ በዚህ ደረጃ እንዴት የሞራል ዝቅጠት ይጠናወተዋል?
11/04/2023

Just heart breaking 😭 💔💔💔

ስደት፥ መፈናቀል፥ ከሰብአዊነት የወረደ፥ ለሰሚውም ግራ የሆነ ጭካኔ። የሰው ልጅ በዚህ ደረጃ እንዴት የሞራል ዝቅጠት ይጠናወተዋል?

ኡስስስስስስስስ እስኪ እንተኛበት!😭
28/03/2023

ኡስስስስስስስስ እስኪ እንተኛበት!😭

እስኪ ይሄንን ጥበብ ዝምብላችሁ አድንቁ!
21/03/2023

እስኪ ይሄንን ጥበብ ዝምብላችሁ አድንቁ!

አባትና ልጅ ተገናኝተዋል። ከሁለት ቀናት በፊት ተሰርቃ ጠፍታ የነበረችው ልጅ ዛሬ ሱልልታ ተገኝታለች።
21/03/2023

አባትና ልጅ ተገናኝተዋል። ከሁለት ቀናት በፊት ተሰርቃ ጠፍታ የነበረችው ልጅ ዛሬ ሱልልታ ተገኝታለች።

አይይይይ አፍሪካ 😭
21/03/2023

አይይይይ አፍሪካ 😭

በርች እህቴ!👏ዝቅ ተብሎ ተሰርቶ ነው ቀና ብሎ መሄድ የሚቻለው!
19/03/2023

በርች እህቴ!👏
ዝቅ ተብሎ ተሰርቶ ነው ቀና ብሎ መሄድ የሚቻለው!

ሙሀመድ ጋዳፊ'ም ለካ ክፉ አሟሟት ከመሞቱ በፊት የሊቢያ ፕሬዝዳንት እያለ "አረንጓዴው መፅሀፍ" የሚል ይዘት ያላቸው 3 መፅሀፍትን ፅፎ ነበር።😭አሁን ለምን ትዝ እንዳለኝ ግን አላውቅም!😀
18/03/2023

ሙሀመድ ጋዳፊ'ም ለካ ክፉ አሟሟት ከመሞቱ በፊት የሊቢያ ፕሬዝዳንት እያለ "አረንጓዴው መፅሀፍ" የሚል ይዘት ያላቸው 3 መፅሀፍትን ፅፎ ነበር።😭

አሁን ለምን ትዝ እንዳለኝ ግን አላውቅም!😀

😮
16/03/2023

😮

የአንዳንድ ሰዎች ነገረ ስራ ደግሞ በእጅጉ ያስተዛዝባል። የተቸገረን መርዳት ጥሩ ነገር ነው። ፎቶ ተነስቶ ለመምጣት እንደዚህ መጣደፍ ግን ነውር ነው። ሰዎቹ በድርቅ ምክንያት ቸገረን እንጅ እ...
15/03/2023

የአንዳንድ ሰዎች ነገረ ስራ ደግሞ በእጅጉ ያስተዛዝባል። የተቸገረን መርዳት ጥሩ ነገር ነው። ፎቶ ተነስቶ ለመምጣት እንደዚህ መጣደፍ ግን ነውር ነው። ሰዎቹ በድርቅ ምክንያት ቸገረን እንጅ እጃችንን አጥተናል አላሉም። ይዘው መጠጣት ይችላሉ። እረዳሁ ለማለት ተደፍቶ እስኪወድቁ ድረስ ለሰልፊ መጣደፍ ግን ትርፉ ትዝብት ነው።
አዛኝ መሳይ ሁላ።

ዛሬ እንደዚህ ምስል ያሳቀኝ የለም።😂ፎቶዎቹን እስከመጨረሻው እዩትወቅታዊ ሁኔታዎችን ፍንትው አድርጎ ያሳያል
15/03/2023

ዛሬ እንደዚህ ምስል ያሳቀኝ የለም።😂
ፎቶዎቹን እስከመጨረሻው እዩት

ወቅታዊ ሁኔታዎችን ፍንትው አድርጎ ያሳያል

14/03/2023

የአንዳንዱ ሰው አስተሳሰብ ደግሞ አጃይብ ያሰኛል። ሀገር ስትፈርስ የሚጎዳ የሚመስለው ሌላው እንጅ እሳቱ እሱንም እንደሚለበልበው በፍፁም አያስብም። እውነታው ግን በአንድ ላይ መቆም ካልቻልን በጋራ እንጠፋለን።

ድሮም እኮ አልሰማ ብላችሁኝ እንጅ በዚች ሀገር ላይ ከሰይፉ ፈንታሁን የተሻለ መሀይም ደደብ የለም ብያችሁ ነበር። አሁን ሰው ቢጠፋ እንኳን ዮኒ ማኛ የቲቪ ሾው ላይ የሚቀርብ ሰው ነው? ዮኒ ...
12/03/2023

ድሮም እኮ አልሰማ ብላችሁኝ እንጅ በዚች ሀገር ላይ ከሰይፉ ፈንታሁን የተሻለ መሀይም ደደብ የለም ብያችሁ ነበር። አሁን ሰው ቢጠፋ እንኳን ዮኒ ማኛ የቲቪ ሾው ላይ የሚቀርብ ሰው ነው? ዮኒ ቲቪ ላይ ለትውልድ ምን ሊያስተምር ነው? ስድብ ወይስ አፉ እንዳመጣለት መዘርጠጥን? ከዚህ በኋላ በዚያ ሾው ላይ የሚቀርቡ ሰዎችን ከመላጠው ለይቸ አላያቸውም። ይሄ ጥርብ መላጣ!

ፓስተር ቢኒያም ከብዙ እንግልትና ውጣ ውረድ በኋላ ዛሬ ማምሻውን ተፈቷል።
07/03/2023

ፓስተር ቢኒያም ከብዙ እንግልትና ውጣ ውረድ በኋላ ዛሬ ማምሻውን ተፈቷል።

05/03/2023

"ሀረር ብትከበብ፥ ድሬንም ቢጨንቃት
ለገሰ ተፈሪ አርነት አወጣት።"
#ካራማራ
እንኳን አደረሳችሁ!

02/03/2023

ነጭ ጣሊያኖችን ድል ማድረግ ብንችልም፤ ጥቁር ጣሊያኖችን ግን አሁንም ገና ድል አላደረግናቸውም። ምናልባት የቀጣዩን አድዋ የምናከብረው ጥቁሮቹንም አሸንፈን ይሆናል።

" የተሰጠን ሕይወት ዛሬ በነጻነት፣ሰው ተከፍሎበታል ከደምና ከአጥንት።ስንት ወገን አለቀ በነጻነት ምድር ፣ትናገር  #ዓድዋ ትናገር ትመስክር።ትናገር  #ዓድዋ ትናገር ሀገሬ፣እንዴት እንደቆምኩ...
02/03/2023

" የተሰጠን ሕይወት ዛሬ በነጻነት፣
ሰው ተከፍሎበታል ከደምና ከአጥንት።
ስንት ወገን አለቀ በነጻነት ምድር ፣
ትናገር #ዓድዋ ትናገር ትመስክር።
ትናገር #ዓድዋ ትናገር ሀገሬ፣
እንዴት እንደቆምኩኝ ከፊታችሁ ዛሬ። "

የአድዋ ድልን በአደባባይ ማክበር እንዳንችል መከልከል ይችሉ ይሆናል፤ በልባችን የታተመውን አድዋ ግን መፋቅ አይችሉም።ምኒሊክ ዛሬም ንጉስ ነው።
02/03/2023

የአድዋ ድልን በአደባባይ ማክበር እንዳንችል መከልከል ይችሉ ይሆናል፤ በልባችን የታተመውን አድዋ ግን መፋቅ አይችሉም።
ምኒሊክ ዛሬም ንጉስ ነው።

ውጫሌ ላይ ተሰርቶ ዛሬ የተመረቀው የንጉሱ የአጤ ሚኒልክና የንግስቷ ሀውልት።❤
01/03/2023

ውጫሌ ላይ ተሰርቶ ዛሬ የተመረቀው የንጉሱ የአጤ ሚኒልክና የንግስቷ ሀውልት።❤

27/02/2023

ብኩርናቸውን በምስር የሚሸጡ ሰዎች በጭራሽ አያስፈልጉንም፤ መነቀል አለባቸው።✌️

(ብዙዎች እንዲህ እያላቹ ስትለጥፉ እኔስ ለምን ይቅርብኝ ብዬ ነው😀!):ሆቴል ትገባና ጥብስ ታዛለህ።ደም ግፊት ምናምን ካለብህ እንደው ምናልባት 'ጨው እንዳይገባበት' ትል ይሆናል! ' ቅባት ...
26/02/2023

(ብዙዎች እንዲህ እያላቹ ስትለጥፉ እኔስ ለምን ይቅርብኝ ብዬ ነው😀!)
:
ሆቴል ትገባና ጥብስ ታዛለህ።

ደም ግፊት ምናምን ካለብህ እንደው ምናልባት 'ጨው እንዳይገባበት' ትል ይሆናል!

' ቅባት አይብዛበት' ብትልም አሳማኝ ነው!

እንደሁኔታው ሽንኩርት የማይወድም ስለሚኖር ' ሽንኩርት እንዳይገባበት!' ብትል ሰዎች ይረዱሃል!

'እስቲ አንድ ጥብስ አምጡልኝ! ስጋ እንዳይገባበት!' ካልክ ግን ብራዘር ደም ግፊትህን ብቻ ሳይሆን የአእምሮ ጤና ምርመራም እንድታደርግ ነው የምመክርህ!

አንዳንድ ሰዎች ሚኒልክ የሌለበት የአድዋ ድል በዓል ለማክበር ሲፍጨረጨሩ ሳይ የሚመጣብኝ ሃሳብ ነው!
**
ሞኝ ባያፍር የሞኝ ዘመድ ያፍር የሚባለው የሚገባኝ በአድዋ ሰሞን ነው።ድሮ አንድ የጣልያን ክልስ ወዳጅ(ክላየንት) ነበረኝ።'አድዋ በመጣ ቁጥር በቲቪና በራዲዮ የምታቀርቡት ፕሮግራም ያሳቅቀኛል!' ይለኝ ነበር። ዘመዶቹ በኢትዮጵያውያንላይ የፈጸሙት ግፍ ያሳፍረዋል ይመስለኛል!አሁን አሁን እኔም አድዋ በደረሰ ቁጥር ዘመዶቼ ምን ሼምለስ የሆነ ነገር ያደርጉ እና አንገቴን ያስደፉኝ እያልኩ እሳቀቃለሁ!!

ወደድክም ጠላህም ግን በአለም ላይ ያለ ጥቁር ሁሉ ሚኒሊክ ያደረገውን ገድል በሰማ ቁጥር ደሙ ይሞቃል! በነጮች ፊት አንገቱን ቀና ያደርጋል!!ሚኒሊክ ስሙ ራሱ የሚንቀለቀል እሳት ነው!ለእኛ የነጻነት አርማችን ነው!! የምንወደውም ስለምንወደው እንጂ አንተ ስለጠላኸው አይደለም!!

በጠላት ወረራ ዘመን አንዱ ሶላቶ ሃበሻን ያናደደ መስሎት ውሻውን 'ሚኒሊክ ' ብሎ ሰየመው አሉ። ኋላ ዘበኛው ሃበሻ ኖሮ ጣሊያኑ በሌለበት ውሻውን አናቱን ብሎ ገደለው። ጣሊያኑ ቤት ሲመጣ ውሻው አራቱን ወደ ሰማይ ዘርግቶ ፍንችር ብሏል።
'አንቴ አበሻ ..ውሻዬ ሚን ሆኖ ሞተ?!' ቢለው የሃበሻው ዘበኛ ምን አለ ...'ምን አውቄ ጌታው !ምናልባት ስሙ ከብዶት ይሆን?!' አለው ይባላል!!

አድዋን ስታከብር ሚኒሊክን ማየት ባትፈልግ የኛም ግምት ከዘበኛው ብዙ አይርቅም ..'ጌታው ምናልባት እንደውሻው ስሙ ከብዶህ ይሆን!!?'

መልካም ቀን!!

እምየ ሚኒሊክ ለእናት ሀገራችን ካበረከቷቸው ታላላቅ ነገሮች በጥቂቱ፦................................1882 ዓ.ም. ---------------------ስልክ1885 ዓ.ም. -...
25/02/2023

እምየ ሚኒሊክ ለእናት ሀገራችን ካበረከቷቸው ታላላቅ ነገሮች በጥቂቱ፦................................
1882 ዓ.ም. ---------------------ስልክ
1885 ዓ.ም. ---------------------ወፍጮ
1886 ዓ.ም. ---------------------ፖስታ
1886 ዓ.ም. ---------------------ባህር ዛፍ
1886 ዓ.ም. ---------------------ገንዘብ
1886 ዓ.ም. ---------------------የውሃ ቧንቧ
1887 ዓ.ም. ---------------------ጫማ
1887 ዓ.ም. ---------------------ድር
1887 ዓ.ም. --------------የሙዚቃ ት/ቤት
1887 ዓ.ም. -------------የፅህፈት መኪና
1889 ዓ.ም. ---------------------ኤሌክትሪክ
1889 ዓ.ም. ------------ዘመናዊ ህክምና
1889 ዓ.ም. ---------------------ሲኒማ
1889 ዓ.ም. ------------የሙዚቃ ሸክላ
1889 ዓ.ም. ------------ቀይ መስቀል
1890 ዓ.ም. ---------------------ሆስፒታል
1893 ዓ.ም. ---------------------ባቡር
1893 ዓ.ም. ---------------------ብስክሌት
1896 ዓ.ም. ---------------------መንገድ
1897 ዓ.ም. ---------------------ፍል ውሃ
1898 ዓ.ም. ---------------------ባንክ
1898 ዓ.ም. ---------------------ሆቴል
1898 ዓ.ም. ---------------------ማተሚያ
1898 ዓ.ም. ---------------------ላስቲክ
1899 ዓ.ም. -------------አራዊት ጥበቃ
1899 ዓ.ም. ------------የጥይት ፋብሪካ
1900 ዓ.ም. ---------------------ጋዜጣ
1900 ዓ.ም. ---------------------አውቶሞቢል
1900 ዓ.ም. ----------የሚኒስትሮች ሹመት
1901 ዓ.ም. --------------ፖሊስ ሰራዊት
1904 ዓ.ም. -----------የመድሃኒት መሸጫ ሱቆች
ለመጀመሪያ ጊዜ ወደሀገራችን ያስገቡት ታላቁ አባታችን እምዬ ሚኒሊክ ናቸው!!!

ሌላ የአድዋ ስጦታ እንካችሁ ተብላችኋል !!!---------ፈረንሳዊው ሂዩግ ፎንቴን ;-"ኢትዮጵያ በአፄ ምኒልክ ዘመን"በሚል ርዕስ  በአማርኛ ፣ በፈረንሳይኛና ፡ በእንግሊዝኛ ግዙፍ መፅሃፍ ...
25/02/2023

ሌላ የአድዋ ስጦታ እንካችሁ ተብላችኋል !!!
---------
ፈረንሳዊው ሂዩግ ፎንቴን ;-

"ኢትዮጵያ በአፄ ምኒልክ ዘመን"

በሚል ርዕስ በአማርኛ ፣ በፈረንሳይኛና ፡ በእንግሊዝኛ ግዙፍ መፅሃፍ አሳትሞ ለዓለም ሁሉ የምኒልክን ታላቅነት ምስክርነቱን ገልጿል። የመፅሃፉ ዝግጅት 15 ዓመታት የፈጀ ሲሆን እስከዛሬ አብዛኛው ዓለም ያላያቸውን የፎቶ ስብስቦች የያዘ ነው።1200 ገፅ ያለው ሲሆን በከፍተኛ ጥራት ስዊዘርላንድ የታተመ እና ዋጋው 4500 ብር ገደማ ነው።ኢትዮጵያ ጥቂቱ የህትመት ፍሬ ደርሷታል።በቀጣይ በተለያዩ ቋንቋዎች ታትሞ ለዓለም ይሰራጫል።
ምኒልክ የዓለም ጭቁን ህዝቦችን የነፃነት ቀንዲል ያሳየ ታላቅ ንጉስ ነው!!

የፕሮቴስታን እምነት ተከታይ የሆነውን ፓስተር ቢኒያምን ለምን ለኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ትቆረቆራለህ በሚል ባለ ጊዜወቹ ወደ ዘብጥያ አወረዱት። በምላሹ ግን በዛሬው እለት 27 የሚሆኑ የኦር...
24/02/2023

የፕሮቴስታን እምነት ተከታይ የሆነውን ፓስተር ቢኒያምን ለምን ለኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ትቆረቆራለህ በሚል ባለ ጊዜወቹ ወደ ዘብጥያ አወረዱት። በምላሹ ግን በዛሬው እለት 27 የሚሆኑ የኦርቶዶክስ አማኝ ጠበቆች ፍርድ ቤት ቀርበው ሲሟገቱለት ውለዋል። ይሄ ማለት ምን ማለት እንደሆነ ይገባችኋል? ሰው ሰው ስትሸት የምትሆነው እንደዚህ ነው። ብሄር ሀይማኖት ወዘተርፈ ሳይገድብህ ለፍትህ ብቻ ትቆማለህ።

በቦረና ውስጥ ከነበሩት ከ3 ሚሊየን 230+ሽ ከብቶች ውስጥ 3 ሚሊየኑ ሙተው አልቀዋል፤ አሁን የቀሩት 230ሽ ከብቶች ብቻ ናቸው።😭
23/02/2023

በቦረና ውስጥ ከነበሩት ከ3 ሚሊየን 230+ሽ ከብቶች ውስጥ 3 ሚሊየኑ ሙተው አልቀዋል፤ አሁን የቀሩት 230ሽ ከብቶች ብቻ ናቸው።😭

እባካችሁ ይልቁንስ ከንቱ ብሽሽቃችሁን አቁማችሁ፣ በማይረባ ነገር ሚሊየን ብሮችን በአንድ ጀምበር ቀርጥፎ መብላቱን ትታችሁ በርሀብ አለንጋ እየተገረፈ ላለው ደጉ የቦረና ህዝብ ድረሱለት።
22/02/2023

እባካችሁ ይልቁንስ ከንቱ ብሽሽቃችሁን አቁማችሁ፣ በማይረባ ነገር ሚሊየን ብሮችን በአንድ ጀምበር ቀርጥፎ መብላቱን ትታችሁ በርሀብ አለንጋ እየተገረፈ ላለው ደጉ የቦረና ህዝብ ድረሱለት።

".....አሸበረቀች" ሲባል የነበረው ዘፈን ለካ ለባሱ ነው እንዴ!😂
22/02/2023

".....አሸበረቀች" ሲባል የነበረው ዘፈን ለካ ለባሱ ነው እንዴ!😂

እሽ ተማሪዎች፥ የዛሬው ትምህርታችን ስለ ቁጥሮች ነው።😂እየተስተማራችሁ!
22/02/2023

እሽ ተማሪዎች፥ የዛሬው ትምህርታችን ስለ ቁጥሮች ነው።😂
እየተስተማራችሁ!

እነዚህ 3 ሰወች በታሪክ የሰው ልጅ በዚህች ምድር መኖር ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ወደ ስራ ሲገቡ ጥቁር ልብስ በመልበሳቸው ብቻ ከስራ ገበታቸው የተባረሩ የመጀመሪያወቹ ሳይሆኑ አይቀርም።ዘንድሮ...
21/02/2023

እነዚህ 3 ሰወች በታሪክ የሰው ልጅ በዚህች ምድር መኖር ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ወደ ስራ ሲገቡ ጥቁር ልብስ በመልበሳቸው ብቻ ከስራ ገበታቸው የተባረሩ የመጀመሪያወቹ ሳይሆኑ አይቀርም።
ዘንድሮ መቸም የማንሰማው ጉድ የለም!!!

ያላግባብ ታስረው የነበሩት እነ መ/ር ምህረተአብና ጋዜጠኛ ዮሴፍ ተፈተዋል።ለቤተክርስቲያኗ የጠበቆች ቡድን 🙏
21/02/2023

ያላግባብ ታስረው የነበሩት እነ መ/ር ምህረተአብና ጋዜጠኛ ዮሴፍ ተፈተዋል።

ለቤተክርስቲያኗ የጠበቆች ቡድን 🙏

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethio Habesha posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Share