Horo Tube

Horo Tube I hate false people, false friends, false love, false promises and false relationship!!

Bulloon garmaamaa jira jechuudhumaafi
09/10/2023

Bulloon garmaamaa jira jechuudhumaafi

Uffannaa aadaa Oromoo mimmiidhagaa ayyaana Irreechaa irratti mul'atan keessaa muraasa !!
09/10/2023

Uffannaa aadaa Oromoo mimmiidhagaa ayyaana Irreechaa irratti mul'atan keessaa muraasa !!

Maalummaa Halluuwwan Alaabaa Abbaa Gadaa********************* Halluuwwan Alaabaa Abbaa Gadaa falaasama, ilaalchaa fi dhu...
09/10/2023

Maalummaa Halluuwwan Alaabaa Abbaa Gadaa
*********************

Halluuwwan Alaabaa Abbaa Gadaa falaasama, ilaalchaa fi dhugeeffannaa Oromoo mul’isu jedhan, qorataan Aadaa Oromoo Dirribii Damissee.

Hiikkaa halluuwwan Alaabichaas akka armaan gadiitti ibsu.

Halluu Gurraacha: - Ol-aantummaa Waaqaa mul’isa. Ummanni Oromoo akkuma guraacha ta’e Waaqni isa uumes gurraacha jedheeti amana. Halluu gurraachis ummaticha biratti ibsituu ol-aantummaati. Waaqni gurraachi isa uume kan jiru oli; dabbasaa gurraachi kan jiru mataa namaatirra - oli; hurriin bokkaa qabu guraachis kan jiru oli; qaroon ijaa (agartuun) gurraacha – kan argamus fuuldurarratti. Kana bu’ureeffachuun halluu gurraachi saba Oromoo biratti kan kabajaa, kan angafummaa fi waan gaarii ta’an hedduu of keessaa qaba.

Halluu Diimaa: - Ga’anii, bilchaatanii akkasumas guutanii, gameessa ta’anii argamuu dha. Ummanni Oromoo wanti tokko gahaa ta’uu yoo ibsu “diimate” jedha. Dargaggoon ykn shamarri tokko yoo ga’u/geessu, kormi yoo gooba baasu ni diimata. Kanaaf halluu diimaan wanti hedduun yeroosaa eeggatee ga’uu fi ija guutuu isaa agarsiisa.

Halluu Adii: - Raawwachuu ykn xumuramuu wantootaa mul’isa. Hurriin roobee yoo fixate ni addaata; hurrii addaatu keessa bokkaan hin roobu. Dabbasaan (rifeensi) namaa gaafa dulloomne ni harraa’a (gurraacha irraa gara adiitti jijjiirama), Qoraan gubatee dhume daaraa adii ta’a. Lafeen xuuxamee dhume adii ta’a. Kanaaf adiin raawwachuu ykn xumura waan tokkoo ibsa.

𝑴𝒂𝒋𝒐𝒓 𝑨𝒃𝒅𝒊𝒔𝒂 𝑨𝒈𝒂 𝒘𝒂𝒔 𝒕𝒉𝒆 𝒇𝒊𝒓𝒔𝒕 𝒉𝒆𝒓𝒐 𝒘𝒉𝒐 𝒆𝒏𝒕𝒆𝒓𝒆𝒅 𝒂𝒏𝒅 𝒄𝒂𝒑𝒕𝒖𝒓𝒆𝒅 𝑹𝒐𝒎𝒆, 𝒔𝒊𝒕𝒕𝒊𝒏𝒈 𝒊𝒏 𝒂 𝒋𝒆𝒆𝒑, 𝒘𝒂𝒗𝒊𝒏𝒈 𝒇𝒊𝒓𝒔𝒕 𝒂𝒏𝒅 𝒇𝒐𝒓𝒆𝒎𝒐𝒔𝒕 𝒕𝒉𝒆 𝒇𝒍𝒂𝒈...
16/06/2022

𝑴𝒂𝒋𝒐𝒓 𝑨𝒃𝒅𝒊𝒔𝒂 𝑨𝒈𝒂 𝒘𝒂𝒔 𝒕𝒉𝒆 𝒇𝒊𝒓𝒔𝒕 𝒉𝒆𝒓𝒐 𝒘𝒉𝒐 𝒆𝒏𝒕𝒆𝒓𝒆𝒅 𝒂𝒏𝒅 𝒄𝒂𝒑𝒕𝒖𝒓𝒆𝒅 𝑹𝒐𝒎𝒆, 𝒔𝒊𝒕𝒕𝒊𝒏𝒈 𝒊𝒏 𝒂 𝒋𝒆𝒆𝒑, 𝒘𝒂𝒗𝒊𝒏𝒈 𝒇𝒊𝒓𝒔𝒕 𝒂𝒏𝒅 𝒇𝒐𝒓𝒆𝒎𝒐𝒔𝒕 𝒕𝒉𝒆 𝒇𝒍𝒂𝒈 𝒐𝒇 𝒉𝒊𝒔 𝒄𝒐𝒖𝒏𝒕𝒓𝒚.

"𝑨𝒏 𝑶𝒓𝒐𝒎𝒐 𝒎𝒂𝒏 𝒘𝒉𝒐 𝒍𝒆𝒅 𝒕𝒉𝒆 𝒄𝒂𝒑𝒕𝒖𝒓𝒆 𝒐𝒇 𝑹𝒐𝒎𝒆 𝒂𝒏𝒅 𝑩𝒆𝒓𝒊𝒏 𝒊𝒏 2𝒏𝒅 𝒘𝒐𝒓𝒍𝒅 𝒘𝒂𝒓
𝑰𝒏 𝒉𝒊𝒔𝒕𝒐𝒓𝒚, 𝑨𝒃𝒅𝒊𝒔𝒂 𝑨𝒈𝒂 𝒘𝒂𝒔 𝒕𝒂𝒌𝒆𝒏 𝒂𝒔 𝒂 𝒑𝒓𝒊𝒔𝒐𝒏𝒆𝒓 𝒐𝒇 𝒘𝒂𝒓 𝒇𝒓𝒐𝒎 𝒉𝒊𝒔 𝒄𝒐𝒖𝒏𝒕𝒓𝒚 𝒊𝒏 1936 𝒕𝒐 𝒕𝒉𝒆 𝒊𝒔𝒍𝒂𝒏𝒅 𝒐𝒇 𝑺𝒊𝒄𝒊𝒍𝒚, 𝑰𝒕𝒂𝒍𝒚 𝒂𝒏𝒅 𝒂𝒍𝒍𝒆𝒈𝒆𝒅𝒍𝒚 𝒑𝒆𝒏𝒆𝒕𝒓𝒂𝒕𝒆𝒅 𝒕𝒉𝒆 𝒑𝒓𝒊𝒔𝒐𝒏 𝒄𝒂𝒎𝒑 𝒂𝒏𝒅 𝒇𝒍𝒆𝒅 𝒕𝒐 𝒕𝒉𝒆 𝒘𝒐𝒐𝒅𝒔 𝒘𝒊𝒕𝒉 𝒂𝒎𝒎𝒖𝒏𝒊𝒕𝒊𝒐𝒏 𝒂𝒏𝒅 𝒕𝒓𝒖𝒄𝒌𝒔 𝒇𝒖𝒍𝒍 𝒐𝒇 𝒔𝒖𝒑𝒑𝒍𝒊𝒆𝒔 𝒊𝒏 𝒕𝒉𝒆 𝒉𝒆𝒂𝒓𝒕 𝒐𝒇 𝑰𝒕𝒂𝒍𝒚. 𝑻𝒉𝒆 𝑰𝒕𝒂𝒍𝒊𝒂𝒏 𝒈𝒐𝒗𝒕 𝒅𝒊𝒅 𝒂𝒍𝒍 𝒊𝒕 𝒄𝒐𝒖𝒍𝒅 𝒕𝒐 𝒄𝒂𝒕𝒄𝒉 𝒉𝒊𝒎. 𝑨𝒃𝒅𝒊𝒔𝒂 𝒉𝒆𝒍𝒑𝒆𝒅 𝒇𝒓𝒆𝒆 𝒑𝒓𝒊𝒔𝒐𝒏𝒆𝒓 𝒂𝒏𝒅 𝒕𝒉𝒆𝒚 𝒃𝒂𝒕𝒕𝒍𝒆𝒅 𝒕𝒉𝒆 𝑰𝒕𝒂𝒍𝒊𝒂𝒏𝒔 𝒇𝒊𝒆𝒓𝒄𝒆𝒍𝒚. 𝑫𝒖𝒓𝒊𝒏𝒈 𝒕𝒉𝒆 2𝒏𝒅 𝒘𝒐𝒓𝒍𝒅 𝒘𝒂𝒓 𝒕𝒉𝒆 𝑨𝒍𝒍𝒊𝒆𝒅 𝒇𝒐𝒓𝒄𝒆, 𝑩𝒓𝒊𝒕𝒂𝒊𝒏, 𝑼𝑺𝑨, 𝑭𝒓𝒂𝒏𝒄𝒆 𝒂𝒏𝒅 𝑹𝒖𝒔𝒔𝒊𝒂 𝒓𝒆𝒄𝒐𝒈𝒏𝒊𝒛𝒆𝒅 𝑨𝒃𝒅𝒊𝒔𝒂 𝑨𝒈𝒂 𝒂𝒏𝒅 𝒕𝒉𝒆 𝒓𝒆𝒔𝒕 𝒐𝒇 𝒕𝒉𝒆 𝒑𝒂𝒓𝒕𝒊𝒔𝒂𝒏 𝒂𝒏𝒅 𝒔𝒖𝒑𝒑𝒍𝒊𝒆𝒅 𝒕𝒉𝒆𝒎 𝒘𝒊𝒕𝒉 𝒂𝒓𝒎𝒔 𝒂𝒏𝒅 𝒑𝒓𝒐𝒗𝒊𝒔𝒊𝒐𝒏𝒔.

𝑴𝒂𝒋𝒐𝒓 𝑮𝒆𝒏𝒆𝒓𝒂𝒍 𝑨𝒃𝒅𝒊𝒔𝒂 𝒘𝒂𝒔 𝒄𝒉𝒐𝒔𝒆𝒏 𝒕𝒐 𝒍𝒆𝒂𝒅 𝒊𝒏𝒕𝒆𝒓𝒏𝒂𝒕𝒊𝒐𝒏𝒂𝒍 𝒑𝒂𝒓𝒕𝒊𝒔𝒂𝒏 𝒂𝒓𝒎𝒚 𝒘𝒉𝒊𝒄𝒉 𝒄𝒐𝒏𝒔𝒊𝒔𝒕𝒆𝒅 𝒐𝒇 𝑨𝒎𝒆𝒓𝒊𝒄𝒂𝒏𝒔, 𝑭𝒓𝒆𝒏𝒄𝒉, 𝑬𝒏𝒈𝒍𝒊𝒔𝒉, 𝑬𝒕𝒉𝒊𝒐𝒑𝒊𝒂𝒏𝒔 𝒂𝒏𝒅 𝒐𝒕𝒉𝒆𝒓 𝒏𝒂𝒕𝒊𝒐𝒏𝒂𝒍𝒔. 𝑻𝒉𝒊𝒔 𝒘𝒂𝒚 𝒕𝒉𝒆 𝒑𝒂𝒓𝒕𝒊𝒔𝒂𝒏 𝒘𝒆𝒆𝒌𝒆𝒏𝒅 𝒕𝒉𝒆 𝑰𝒕𝒂𝒍𝒊𝒂𝒏 𝒂𝒓𝒎𝒚 𝒂𝒏𝒅 𝒄𝒐𝒏𝒕𝒓𝒊𝒃𝒖𝒕𝒆𝒅 𝒕𝒉𝒆𝒊𝒓 𝒅𝒆𝒇𝒆𝒂𝒕.
𝑴𝒂𝒋𝒐𝒓 𝑨𝒃𝒅𝒊𝒔𝒂 𝑨𝒈𝒂 𝒘𝒂𝒔 𝒕𝒉𝒆 𝒇𝒊𝒓𝒔𝒕 𝒉𝒆𝒓𝒐 𝒘𝒉𝒐 𝒆𝒏𝒕𝒆𝒓𝒆𝒅 𝒂𝒏𝒅 𝒄𝒂𝒑𝒕𝒖𝒓𝒆𝒅 𝑹𝒐𝒎𝒆, 𝒔𝒊𝒕𝒕𝒊𝒏𝒈 𝒊𝒏 𝒂 𝒋𝒆𝒆𝒑, 𝒘𝒂𝒗𝒊𝒏𝒈 𝒇𝒊𝒓𝒔𝒕 𝒂𝒏𝒅 𝒇𝒐𝒓𝒆𝒎𝒐𝒔𝒕 𝒕𝒉𝒆 𝒇𝒍𝒂𝒈 𝒐𝒇 𝒉𝒊𝒔 𝒄𝒐𝒖𝒏𝒕𝒓𝒚.
𝑻𝒉𝒆 𝑩𝒓𝒊𝒕𝒊𝒔𝒉 𝒎𝒂𝒅𝒆 𝑨𝒃𝒅𝒊𝒔𝒂 𝒕𝒉𝒆 𝒄𝒐𝒎𝒎𝒂𝒏𝒅𝒆𝒓 𝒐𝒇 𝒕𝒉𝒆 𝑩𝒓𝒊𝒕𝒊𝒔𝒉 𝒑𝒐𝒍𝒊𝒄𝒆 𝒇𝒐𝒓𝒄𝒆 𝒂𝒏𝒅 𝒔𝒆𝒏𝒕 𝒉𝒊𝒎 𝒕𝒐 𝑮𝒆𝒓𝒎𝒂𝒏𝒚 𝒕𝒐 𝒇𝒊𝒈𝒉𝒕 𝒕𝒉𝒆 𝑵𝒂𝒛𝒊. 𝑨𝒇𝒕𝒆𝒓 𝒎𝒂𝒏𝒚 𝒃𝒂𝒕𝒕𝒍𝒆𝒔 𝒂𝒏𝒅 𝒄𝒂𝒑𝒕𝒖𝒓𝒊𝒏𝒈 𝒄𝒊𝒕𝒊𝒆𝒔 𝒇𝒓𝒐𝒎 𝒕𝒉𝒆 𝑵𝒂𝒛𝒊'𝒔, 𝒉𝒆 𝒆𝒏𝒕𝒆𝒓𝒆𝒅 𝑩𝒆𝒓𝒍𝒊𝒏, 𝒂𝒈𝒂𝒊𝒏 𝑾𝒂𝒗𝒊𝒏𝒈 𝒉𝒊𝒔 𝒄𝒐𝒖𝒏𝒕𝒓𝒚 𝒇𝒍𝒂𝒈. 𝑨𝒃𝒅𝒊𝒔𝒂 𝑨𝒈𝒂 𝒑𝒂𝒔𝒔𝒆𝒅 𝒂𝒘𝒂𝒚 𝒂𝒇𝒕𝒆𝒓 1974 𝑬𝒕𝒉𝒊𝒐𝒑𝒊𝒂𝒏 𝑹𝒆𝒗𝒐𝒍𝒖𝒕𝒊𝒐𝒏 𝒊𝒏 𝒉𝒊𝒔 𝒄𝒐𝒖𝒏𝒕𝒓𝒚."
𝑻𝒉𝒆 𝒕𝒆𝒙𝒕 𝒊𝒔 𝒕𝒂𝒌𝒆𝒏 𝒇𝒓𝒐𝒎 𝑩𝒂𝒅𝒉𝒂𝒔𝒂 𝑹𝒂𝒇𝒆𝒓𝒂'𝒔 𝒇𝒂𝒄𝒆𝒃𝒐𝒐𝒌 𝒑𝒂𝒈𝒆.
𝑻𝒉𝒆 𝒘𝒐𝒓𝒍𝒅 𝒇𝒂𝒎𝒐𝒖𝒔 𝒉𝒆𝒓𝒐, 𝑨𝒃𝒅𝒊𝒔𝒂 𝑨𝒈𝒂 & 𝒕𝒉𝒆 𝒑𝒊𝒄𝒕𝒖𝒓𝒆 𝒊𝒔 𝒇𝒓𝒐𝒎 𝒕𝒉𝒆 𝒑𝒐𝒔𝒕 𝒐𝒇 𝑵𝒆𝒒𝒂𝒎𝒆𝒕𝒆 𝑷𝒉𝒐𝒕𝒐 𝒂𝒏𝒅 𝑽𝒊𝒅𝒆𝒐 𝑮𝒂𝒍𝒍𝒆𝒓𝒚.

𝑺𝒐𝒖𝒓𝒄𝒆: African Voice

African Youth Reflect 🧠🧠🧠🙇🏿‍♂️🙇🏿‍♂️🙇🏿‍♂️

14/05/2022

የማይጠገን ስብራት…!

ሞቲ ቢያ

በየዘመኑ ቃል ኪዳን፣ በየዘመኑ ክህደት፣
በየዘመኑ ተስፋ፣ በየዘመኑ ውድቀት፣
በየዘመኑ ሽግግር ፣ በየዘመኑ ግርግር ።
ይህንን ነው ፖለቲካ የሚሉት፣
የማይስማሙ ልጆች ቋሚ ጩኸት፣
የግዲያ ሠፈር የለየለት አዙሪት!
በግና ተኩላ ባንድ በረት…
የማይጠገን ስብራት…!

13/05/2022

Al tokko tokko nama ati jaallatteetu si miidha osoo hin taane,eenyummaa nama jaallattuu wallaaluutu si miidha.

ሌብነትን የምትጠየፍ ፡ ሌቦችን ፊት ለፊት ሌባ ከማለት በላይ ታግላ የሌብነትን ሰንሰለት የምትበጣጥስ ፡ ለሀገሯና ለህዝቦቿ ታማኝ የሆነች ፡  ብሔራዊ ጀግናችን ኮ/ር ደራርቱ ቱሉ ክብር ይገባ...
13/05/2022

ሌብነትን የምትጠየፍ ፡ ሌቦችን ፊት ለፊት ሌባ ከማለት በላይ ታግላ የሌብነትን ሰንሰለት የምትበጣጥስ ፡ ለሀገሯና ለህዝቦቿ ታማኝ የሆነች ፡ ብሔራዊ ጀግናችን ኮ/ር ደራርቱ ቱሉ ክብር ይገባታል‼️

ጀዋር መሐመድ -- ስኬታማው እና የስኬቱ ሰለባጀዋርን በአጭሩ ግለጽ ብባል  ባለ ከባድ ሚዛን አክቲቪስት፣ በለ ብሩህ አእምሮ ምሁር እና አንደበተ ርቱእ ፖለቲከኛ እላለሁ።እድሜው ገና በ30ዎቹ...
13/05/2022

ጀዋር መሐመድ --
ስኬታማው እና የስኬቱ ሰለባ
ጀዋርን በአጭሩ ግለጽ ብባል ባለ ከባድ ሚዛን አክቲቪስት፣ በለ ብሩህ አእምሮ ምሁር እና አንደበተ ርቱእ ፖለቲከኛ እላለሁ።
እድሜው ገና በ30ዎቹ አጋማሽ አካባቢ ነው። 36። ገና በለጋ እድሜው፣ በ20 ዓመቱ የኢትዮጵያ በተለይ የኦሮሞ ፖለቲካ መሰረቱ ምን እንደሆነ፣ ጥንካሬው የቱ ጋር እንዳለ፣ የቱ ጋር እንከን እንደ ገጠመው በጥልቀት የተረዳ ይመስላል።
እንደ የኦሮሞ ትግል የጀርባ አጥንት የሚታየው ኦነግ የማይካድ ጥንካሬዎች ቢኖሩትም በግዜ ሂደት በርካታ ውጫዊና ውስጣዊ ችገሮች እንዳጋጠሙት በአግባቡ የተረዳው የዛሬ 13 ዓመት ገደማ ነው።
ቢያንስ ለ3 አስርት ዓመታት በላይ የዘለቀ፣ ነገር ግን ጥቂት ውጤቶችን ብቻ አስመዝግቦ የነበረው የኦነግ የትግል ስልት መቀየር እንዳለበት፣ ይህ ካልሆነ ግን ኦነግ የኦሮሞን ጥያቄ ለመመለስ የሚያስችል ብቃትና ቁመና እንደሌለው፣ የትግሉ እጣፈንታም "ላም አለኝ በሰማይ" ብቻ ሆኖ ሊቀር እንደሚችል በድፍረት በአደባባይ ተናገረ። ፃፈ።
በወቅቱ ይህ አዲስ ነገር፣ አዲስ ጅምር፣ አዲስ አቀራረብ እና ያልተሄደበት መንገድ ነበር። ቀደም ብሎ አንጋፋው ሌንጮ ለታን ጨምሮ የኦነግን ድክመቶች እና ውስንነቶች የተረዱ በርካታ የኦሮሞ ምሁራን ቢኖሩም ከጃዋር በፊት ኦነግን በዚህ ልክ የተቸ አንድም የኦሮሞ ፖለቲከኛ ወ ሊህቅ አልነበረም።
በዚህ መጠን የኦነግ አካሄድ በመሰረቱ መሻሻል፣ ካልሆነም መለወጥ አለበት፤ ኦነግ መንገዱን መፈተሽ ይኖርበታል ሲል ሃሳቡን በአደባባይ የሰነዘረ አንድም የፖለቲካ ተንታኝ አልታየም።
ጀዋር መሐመድ ግን "Failure to Deliver" በተሰኘው ጽሑፉ የሚታወቀውን፣ ነገር ግን የማይነገረውን የኦሮሞ ፖለቲካ ችግር በድፍረት አፈረጠው። ይህ ቀላል ሪስክ አልነበረም። ኦነግን በአደባባይ መተቸት እንኳን ያኔ ዛሬም ከባድ ነው። ጀዋር ግን ይህን ሪስክ ወስዷል። ምክንያቱም መሪ ማለት "Risk Taker" ነውና።
የስነልቦና ባለሙያዎች እንደሚሉት አንድን ችግር ከመሰረቱ መለየት በግማሽ ያህል መፍትሔ እንደማግኘት ነው። ጀዋርም ገና በ30 ዓመቱ የኦሮሞን ትግል ሁነኛ ማነቆዎችን አንድ ሁለት ብሎ በጥንቃቄ ለይቶ ለመፍትሄ ዝግጁ አደረገ። ቀጣዩ እርምጃ ምን መሆን እንዳለበትም በማያሻማ ቋንቋ ለባለድርሻ አካላት አጋራ።
በአንድ በኩል ከዚህ በፊት የመጣንበትን አስቸጋሪ መንገድ እያስታወስን፣ ለዚህም ክብር ለሚገባው ሁሉ ክብር እየሰጠን፣ በሌላ በኩል ደግሞ ዘመኑ በሚፈለገው ልክ አዲስ ስልት፣ አዲስ አካሄድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ በአጠቃላይ ያልተሄደበት መንገድ መቅረጽ ለነገ የማይባል ስራ መሆኑን ቀስ በቀስ ነገረን። በመጨረሻም ለተግባራዊነቱ ግንባር ቀደም ሚና ተጫተ።
ጀዋር ረጅሙን ያልተሄደበት መንገድን ወደ መተግበር ሲገባ አንዱ የነዳጅ ማደያ ጋር ቆም ብሎ ነዳጅ መሙላት ነበረበት። የኦሮሞ ትግል ሁነኛ ነዳጅ ሰቦኑማውነው። ጀዋር "መጀመሪያ ኦሮሞ ነኝ -- I am Oromo first፣ ኢትዮጵያዊነቴ ቀጥሎ የሚመጣ ካባ ነው" አለ። በኢብራሂም መልካ አገላለጽ "ኦሮሞነቴን ያላከበረች ኢትዮጵያ በሊማሊሞ ትሂድ" እንደማለት ነው።
ጀዋር ነዳጁን ሳያባክን እንዴት በአግባቡ መጠቀም እንዳለበት ያውቃል። ተጠቀመበት። የኦሮሞ ህዝብ ድጋፍም ከየአቅጣጫው ጎረፈለት። በሂደቱ ከባባድ ጦርነቶችን አስተናግዶ በድል አጠናቀቀ።
አንድ ነገር የጀዋር ልዩ መለያ ነው። በፍጥነት ነገር ግን በጥንቃቄ መጓዝ። ያልተሄደበት መንገድን ለማሳለጥ አንድ ሁነኛ ህዘባዊ ሚዲያ እንደሚያስፈልግ ተረዳ። ለዚህም ሌት ተቀን መስራቱን ተያያዘ።
በዚህም "የኦሮሞን አየር ነፃ እናውጣ!" በሚል መፈክር ሚልዮኖችን ከጎኑ አሰልፎ OMN የተሰኘ የሚዲያ ተቋምን እውን አደረገ። ይህ እርምጃ ሌላኛው የትግሉ ወሳኝ መሳሪያ ነበር።
ለትግሉ ወጥ ስልትና መንገድ መቀየስ ሌላው ለነገ የማይባል ስራ መሆኑን ጀዋር ቀድሞ የተገነዘበ ይመስላል። በመሆኑም ከመላው ዓለም አሉ የተባሉ ጠንካራ የትግል አጋሮችን አሰባስቦ በየዘርፉ እንዲሰማሩ አስተባበረ።
ግማሹን ከመጋረጃ ጀርባ የስልት ቀያሽና መረጃ አጠናቃሪ ፣ ገሚሱን በአደባባይ የስልቱ ተንታኝ፣ ቀሪዎቹን ለትግሉ ነዳጅ መሙያ ፈንድ አሰባሳቢ በማድረግ መደባቸው።
ሌላው የጀዋር ጥንካሬ ፌስቡክን አሟጦ
መጠቀሙ ነው። በዚህ ስልት አገር ቤት ያለውን ወጣት በቀጥታ ማግኘት፣ መቀስቀስ፣ ማንቃት፣ ማደራጀትና መምራት ተቻለ።
ሁሉ የሆነው 10 ዓመት ባልሞላ ግዜ ውስጥ ነው። ያልተሄደበት መንገድ አተገባበር በእጅጉ ፈጠነ። 50 ዓመታትን የፈጀው የኦሮሞ ትግል ስልቱን ቀይሮ ፍሬ ወደማፍራት ተንደረደረ።
ከአገር ውጭ በጀዋር መሪነት የኦሮሞ ልህቃን እየተናበቡ በፍጥነት ወደፊት ገሰገሱ። በአገር ቤት ቄሮ አስፈሪና አስተማማኝ የትግል ኃይል ለመሆን ቻለ። እንቅስቃሴውን አይተው የተደመሙ የሌሎች ብሔሮች ወጣቶችም የቄሮን ፈለግ ተከትለው መደራጀት ጀመሩ። ፋኖ፣ ዘርማ፣ ኤጄቶ ትግሉን በይፋ ተቀላቅል።
አንባገነኑ ሕወሓት መራሹ የኢህአዴግ መንግስት ግራ መጋባት ጀመረ። ይህ ቡድን ቢያንስ ለ60 ዓመታት ስልጣን ላይ የመቆየት ህልም ነበረው። ነገር ግን ተስፋው ከቀን ወደ ቀን እየደበዘዘ መጣ።
ትንሽ ቆይቶ በአገር ቤት ሌላ አስተማማኝ አጋሮች በጉልህ መታየት ጀመሩ። በኦህዴድ ቤት ያደጉ ጉምቱ የፖለቲካ ሰዎች በጀዋር መራሹ ትግል የተደመሙ ይመስላል። በመሆኑም በመንግሥት መቀመጫ ላይ ተሰይመው ከጃዋር ግር አንድ ቋንቋ ማውራት ጀመሩ። ይህ ለትግሉ ትልቅ ድል ነበር። ለአንባገነኑ መንግስት ደግሞ ትልቅ ሽንፈት።
ብዙም ሳይቆይ የጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ መንግስት በ5 ዓመት ጊዜ ውስጥ 3 ግዜ ካቢኔውን አዋቅሮ ለመበተን ተገደደ። አልሆነም። በጀዋር መራሹ ትግል የተማረኩ የኦህዴድ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መጣ። በመሆኑም የኢህአዴግ መንግስት ከውጭም ከውስጥም ከባባድ ፈተና ገጠመው። እያደር መያዣ መጨበጫ ጠፋው። በመጨረሻም ጠቅላይ ሚንስሩ ተስፋ ቆርጦ ስልጣኑን በገዛ ፍቃዱ አስረክቦ ከአራት ኪሎ እንዲወጣ ሆነ።
በዚህ ወቅት ሁሉም ሊባል በሚችል ሁኔታ ጉምቱ የኦህዴድ ባለስልጣናት ከትግሉ ጎን በመሰለፍ ከጃዋር መራሹ እንቅስቃሴ ጋር እጅና ጓንት ሆነው በይፋ መስራት ጀመሩ። ብአዴን ውስጥ የነበሩ የተወሰኑ ሰዎችም የኦህዴድ ሰዎችን ፈለግ ተከተሉ።
ከመሰረቱ የጀዋር እና አጋሮቹ ፍላጎት መንግስት መመስረት አልነበረም። ከተቻለ ስርአቱን መቀየር ካልሆነ ደግሞ ስርዓቱን በማሻሻል ከመንገዱ ገለል ማለት ነበር። በወቅቱ ከነበረው ነበራዊ ሁኔታ አንፃር ስርዓት ማሻሻል የሚለው አማራጭ በእጅጉ አዋጭ መስሎ ታየ። በመሆኑም ጀዋርም ከኦህዴድና ከብአዴን ሰዎች ጋር በመሆን ስርዓቱን ወደ መሻሻል ገባ።
በጀዋር ሲመራ የነበረው ትግል የመጨረሻ ምእራፍ ላይ ደረሰ። አሁን አዲስ ጠቅላይ ሚንስትር መመረጥ አለበት። አዲሱ ጠቅላይ ሚንስትር ግን ኦሮሞ መሆን አለበት። እዚህ ላይ ብዙም ክርክር አልነበረም። ምክንያቱም የትግሉ ግንባር ቀዳም ተዋናይ የነበረው ኦሮሞ ነበር። ኢትዮጵያም አንድ ወጣትና መልከ መልካም ጠቅላይ ሚንስትር አገኘች -- የጅማው ዐቢይ አህመድ አሊ።
ለውጥ መጣ። ስርዓቱም ተሻሻለ። ህወሃት ወደ መቀሌ ሄደች። የፖለቲካ እስረኞቹ ተፈቱ። አሳሪው የፀረሽብር ህግ ተሻሻለ። ለበርካታ ዓመታት ውጭ አገር የቆዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና የፖለቲካ መሪዎች ወደ አገራቸው ተመሱ። ኢትዮጵያዊያን በደስታ ፈነደቁ። ሁሉም ነገር ደስ ይል ነበር።
ይሁንና፣ አንዳንድ ነገሮች በታሰበው መንገድ አልሄዱም። ብዙም ሳይቆይ የለውጥ ኃይሉ አቅም አናሳ መሆኑ እየታየ መጣ። በመሆኑም ነገሮች ወደፊት መራመድ አቃታቸው። የለውጥ ኃይሉ ከራሱም ወገን ጋር ተባብሮ በተሳካ ሁኔት ለመስራት አልታደለም። የፎቶ ፖለቲካ የለውጡ መለያ እየሆነ መጣ። የለውጡ ጀርባ አጥንት የነበሩ አንዳንድ አካላት በቅጽበት በለውጡ ጠላትነት ተፈረጁ። ይህ ወጀብ ጀዋር መሐመድ ጋርም ደረሰ።
ጀዋር ከጊዜ ወደ ጊዜ በኦህዴድ እና በብአዴን ሰዎች ዘንድ እንደ አጋር መታየቱ ቀርቱ እንደ ባላንጣ መታየት ጀመረ። በርካቶች ፈሩት። ጥቂቶች ጠረጠሩት። በመጨረሻም ....።
የሆነ ሆኖ የለውጡ መሃንዲስ ጀዋር መሐመድ እስር ቤት ገባ። በእርግጥ ይህ ለኢትዮጵያ ፖለቲካ አዲስ አይደለም። ኃይሌ ፊዳ እና ሌሎችም ተመሳሳይ ህይወት አሳልፈዋል።
ሲጠቃለል ግን ጀዋር መሐመድ የራሱ ውስንነቶች ቢኖሩትም እንደ አንድ ሰው ግዴታውን በሚገባ ተወጥቷል። አንፀባራቂ ውጤትም አምጥቷል። ትግሉን ከአሮጌው ኦነግ ነጥቆ ማርሹን ቀይሯል። የኦሮሞን ወጣት እስከ ጥግ ድረስ አንቅቷል። በርካታ ወጣት መሪዎችን አፍርቷል። በህዝባችን ላይ እንደጭሪ ተጣብቃ የነበረችውን ሕወሓትን በማባረሩ ረገድ የአንበሳውን ድርሻ ወስዷል።
በመሆኑም ጀዋር መሐመድ ለኦሮሞ ትግል ብሎም ለኢትዮጵያ ፖለቲካና ሁለንተናዊ ለውጥ የበኩሉን ሰርቷል፣ ደክሟል፣ ፍሬም አፍርቷል። ስለአባይ ጽፏል። ተከራክሯል።
ጃዋር የተሳካለት ነገር ግን የገዛ ስኬቱ ሰለባ ነው።
መልካም ልደት ጃ! 🥰

07/05/2022
"የነቃ፣ የተደራጀ፣ የታጠቀ ሕዝብ ያሸንፋል"‼       ዶ/ር ሀይሌ ፊዳ🙏ይሄን የሰማዕቱ (ለኛ ሰማዕት ነዉ) ሀይሌ ፊዳን ንግግር እንደ አልባሌ ቃል ዉረዉር ሲያደረጉት ይገረመኛል። እሱ ይሄ...
22/04/2022

"የነቃ፣ የተደራጀ፣ የታጠቀ ሕዝብ ያሸንፋል"‼
ዶ/ር ሀይሌ ፊዳ🙏
ይሄን የሰማዕቱ (ለኛ ሰማዕት ነዉ) ሀይሌ ፊዳን ንግግር እንደ አልባሌ ቃል ዉረዉር ሲያደረጉት ይገረመኛል። እሱ ይሄንን ቃል የተናገረበት አዉድ (መቼት) ፤ የተናገረበት ምክንያት እና የእያንዳንዱ ቃላት ትርጉም ከግንዛቤ ሳያስገቡ ስለሚናገሩ ወይም ስለሚፀፉ ትኩረት ሲሰጠዉ አይታይም። እስቲ በአቅሚቲ ተንተን ላድረገዉ😊
✅መቼቱ
ሀይሌ ፊዳ ይሄንን ቃል የተናገረበት አዉድ የአገሪቷ የፖለቲካ ምዕዳር ምን ይመስል ነበር? እንደሚታወቀው ጓድ መንግሥቱ ሀይለማርያም መስከረም 2/1967 ወደ መንበረ ሥልጣኑ ሲመጣ ሀይሌ ፈረንሳይ አገር ነበር። በጥቅምት ወር 1967 ላይ ስለ መንግሥቱ እንዲህ "ኮሎኔሉ በአገር ፍቅር ስሜት የተቃጠለ ነዉ፤ በአግባቡ ካልተያዘ ፍፁም አምባገነን ይሆናል" በማለት ትንቢት ተናገረ፤ ወደ አገር ቤትም ተመለሰ።
ከወዳጆቹ ከእነ ሰናይ ልኬና ከእነ ባሮ አቶምሳ እና ከሌሎችም ጋር ሆኖ በግልም በፓርቲ ደረጃም ጓድ መንግሥቱ ወደ አንባገነንነት እንዳይቀየር በሠላማዊ መንገድ አጋር ሆነዉ ከደርግ ጋር መሥራት ጀመሩ። ሀይሌ ፊዳ መንግሥቱ ሀይለማሪያምን እንደ ሕፃን ልጅ ቁጭ አድረጎ ሶሻሊስትን ያስተማረዉ እሱ ነዉ ይባላል። ከእነ ሀይሌ ፓርቲ መኤሶን በተቃራኒ የቆሙት የኢህአፓ ቡድን ደግሞ ከደርግ ጋር መደራደር አያስፈልግም አሁኑኑ ሕዝባዊ መንግሥት ይመሥረት የሚሉ ነበሩ።
ሕዝባዊ መንግሥት ይመስረት ማለት ክፋት አልነበረዉም። እስክ አፍንጫዉ ከታጠቀ ደርግ ጋር በከተማ ነዉጥ እና በጥይት ጭምር ካልተፋለምን በሚል ዕብሪት የመጀመሪያዋን ጥይት ደርግ ላይ ተኮሱ። መኢሶንም ከደርግ እኩል መፋለም ጀመሩ። የእነ ሀይሌ ፊዳ ዕዉቀት ላይ የተመሠረተና ደርግን አለዝቦ ወደ ሠላማዊ ድርድር የማምጣት መንገድ ተዘጋ። ደርግ እንደ ቆሰለ ነብር ሁሉንም ቀረጣጥፎ መብላት ጀመረ። ሀይሌ ፊዳም ቁርስ ነዉ ምሳ ነዉ የሚያደረጉኝ እያለ በራሱ ላይ እየቀለደ ወደ መንግሥቱ እየተመላለሰ ሳለ ከሁለት አንዱን አደረገዉ። አገሪቷም በቀይ እና በነጭ ሽብር አኪልዳማ ሆነች።
ሀይሌ ፊዳ በሠላማዊ ትግሉ፤ ዕዉቀት ላይ የተመሠረተ የሽግግር መንግሥት እንደማይሳካ ተሰፋ በቆረጠበት ሰዓት ይመስለኛል በርዕሳችን ያለዉን ሀይለ ቃል የተናገረው። እሱን ጨምሮ ሰናይ ልኬና ሌሎችም የመኢሶን አባላት ለሞት ተዳረጉ። ሌሎችም ለግዞትና ሰደት በቁ። ባሮ አቶምሳ ግን የጓዱን የሀይሌ ፊዳን "የነቃ የተደራጀ የታጠቀ ሕዝብ ያሸንፋል" ያለዉን በኦነግ አማካይነት ዕዉን ለማድረግ ጫካ ገባ።
ዛሬም በኮሎኔል አብይ አህመድ ተመሳሳይ ታሪክ ነዉ የተደገመው። እነ ጀዋር መሐመድ እና ኦቦ በቀለ ገርባ በግል(የእነ ሀይሌ ፊዳ አምሳል።)እና በፓርቲያቸው ኦፌኮ (መኢሶን አምሳል)አማካይነት ከ2018 ጀምረዉ ኢህአዴግ ከማፈርስ የለዉጥ ቡድኑን ደግፈን ጥገናዊ ወይም ሠላማዊ የሽግግር መንግሥት እናመጣለን የሚል እምነት ነበራቸዉ። ሆኖም ቀዮ ኮሎኔል ከጥቁሩም በከፋ መልኩ እና የኢህአፓ የያኔዎቹ ወጣት የዛሬ አዛወንቶ አንዳርጋቸዉ ፅጌና ብርሀኑ ነጋ ባዘጋጁለት ሮድ ማፕ ለዉጦ ተቀልብሶ እነሱም ለግዞት አገሪቷም አኪልዳማ ሆነች። የአዙሪት ፖለቲካ። "ወይ የሰዉ መመሳሰል" አለ ሰራዊት ፍቅሬ😊
✅የነቃ ሕዝብ
ዶ/ር ሀይሌ ፊዳ "የነቃ የተደራጀ የታጠቀ ሕዝብ ያሸንፋል።" ያለዉን አንድ በአንድ እንየዉ። ነቅቶ ተደራጅቶና ታጥቆ ያሸነፈዉስ ማን ነዉ? የነቃ ማለት አያሌ ትርጉም ሊሰጠን ይችላል። ነገር ግን ሁለቱን እንጥቀስ። የነቃ ሕዝብ ማለት ከጭንቅላት ባርነት ነፃ የወጣ ማለት ነዉ። ሁለተኛዉ ትርጉም የነቃ ሕዝብ የፖለቲካ ቁማሩን እንዴት መጫወት እንዳለበት ያዉቃል ማለት ነዉ።
በዚህ መሠረት አብዛኛዉ የኦሮሞ ሕዝብ ከጭንቅላት ባርነት ነፃ ወጥቷል። ጥቂቶቹ ብቻ የፖለቲካ ቁማሩን የመጫወት ጥበብ ደረሰዉበታል። ብዙሀኑ ግን ቁማሩን እንዳይጫወቱ እንቅፋት ሆኖባቸዋል(ለምሳሌ ጃል ዳዉድ ኢብሳ ቁማሩ እንዴት እንደሚጫወቱ ገብቷቸዉ ነበር። ግን እኔን ጨምሮ በብዙሃኑ ጩኸት ተሸነፉ። አቤት ጩቡ እኮ ነዉ የሰራነዉ ያ ጀማ😭 በድጋሚ ይቅር በሉን ማሎ🙏)ስለዚህ መንቃት ብቻዉን መፍትሄ አያመጣም። ቁማሩን ያዉም የአገራችንን ዉስብስብ ፖለቲካ እንዴት መጫወት እንዳለበት ጠንቅቆ ማወቅ ያስፈልጋል።
✅የተደራጀ ሕዝብ
መንቃት ብቻ ትረጉም የለዉም መደራጀት ያስፈልጋል። እርግጥ ነዉ። የኦሮሞ ሕዝብ ነቅቷል ግን አልተደራጀም። አንድ ታላቅ ሕዝብ መደራጀት ያለበት በፖለቲካ ፓርቲ ብቻ አይደለም። የኦሮሞ ሕዝብ ትልቁ ችግራችን አለመደራጀታችን ነዉ። ለዚህም ነዉ በየዘመናቱ እስክ ዛሬ ድረስ በጥቂት ብልጣ ብልጦች እረኛ እንደ ሌለዉ መንጋ ይሄንን ታላቅ ሕዝብ ወደ ማፈልጉበት የሚነዱት፣ የሚገሉት፣ የሚያሳድዱት ሲያሻቸዉ እየዘገኑ ግዞት ቤት የሚያጉራቸዉ።
ለመደራጀት ምንም የኒዉኩሌር ቀመር አያስፈልገዉም። በአከባቢ፣ በትምህርት ቤት፣ በሥራ ቦታ፣ በሐይማኖት ሥፍራ በንግድ በጓደኝነት በሙያ መደራጀት ይቻላል። ነገር ግን ይሄንን ለማድረግ ሦስቸኛዉ የመንቃት ደረጃ ላይ መድረሰ ያስፈልጋል። ከጭንቅላት ባርነት ነፃ የወጣዉ እንዴት የፖለቲካ ቁማሩን መጫወት ከቻለ እንዴት አድረጎ አደራጅቶ በአንድ ልብና ቃል መምራት እንደሚችል ማወቅ አለበት። የተደራጀን ሕዝብ ማንም ገፍቶ መጣል አይችልም።ይህ የመደራጀት ጉዳይ በኦሮሞ የነፃነት ትግል ታሪክ ዉስጥ ሺ ጊዜ ተደራጅቶ ሺ ጊዜ የፈረሰ ጉዳይ ነዉ። ምክንያቱም ሲደራጁ የነቃዉም ያልነቃዉ አሰስ ገሰሱም አደርባይና ባንዳ አንድ ላይ ይሞጀርና ተጠላልፈዉ ይወድቃሉ። አሁንም አልረፈደም ሌላዉ ቢቀር እዚህ ፌስ ቡክ ላይ ያለነዉ ተመሳሳይ አቋም ያለን ብንደራጅ ምን ያህል ዉጤት ማምጣት እንደምንችል ማሰቡ ተገቢ ይመስለኛል። ሁሉም በየፊናዉ መደራጀት ለነገ የማይባል የአባ ገዳ ልጆች ታሪካዊ ግዴታ ላይ የምንገኝበት ወቅት ነዉ።
✅የታጠቀ ሕዝብ
ሕዝብ ነፍጥ አንግቶ ጫካ የሚገባዉ ነቅቶና ተደራጅቶ በሠላማዊ መንገድ ያቀረበዉ ጥያቄ ምላሽ ሲያጣ፤ ነፃነቱን እና ሰብአዊነቱን የማያከብር ሥርዓተ መንግሥት ሲመጣበት ነዉ። ለዚህ ደግሞ ከኦሮሞ ሕዝብ የበለጠ አስረጅ የለም። በአያቶቻችን የተጀመረው ሠላማዊ ትግል ወደ ትጥቅ ትግል ተቀየረ። 1966 ከሸፈ!
በአባቶቻችን የተጀመረዉ የትጥቅ ትግል ድል በኦነግ አማካይነት በ1987 በአንፃራዊነት በሕገ መንግሥት የተደገፈ ምላሽ ያገኘ ቢሆንም መሬት ወረዶ ተግባራዊ አልሆነም። በዚህ የተነሳ የኦነግ ልጆች ባደረጉት እልህ አሰጨራሽ ሠላማዊ ትግል በቄሮ መሪነት በ2010/2018 ለዉጥ መጣ። እሱም በስግብግቦቹ ከሸፈ። ከዛ በኋላ እኔን ጨምሮ የሠላማዊ ትግል አራማጆችና ደጋፊዎች ተሰፋ አሰቆረጠን።
በአሁኑ ወቅት በOLA መሪነት የሚደረገዉን እልህ አሰጨራሽ የትጥቅ ትግል የምንደግፈዉ በምክንያት ነዉ። ከአንድም ሶስት ትዉልድ ከተሸወደ በኋላ ሌላ ቀልድ ማምጣት ጅልነት ነዉ። ሠላማዊ ድርድር የምትለዉ የብልፅግና የጅል ጫወታ ላይ መጃጃል የሚፈልግ መንገዱን ጨርቅ ያድረግለት። ነገር ግን ነገር ግን የትጥቅ ትግሉ ላይ እንቀፋት መፈጠር አይደለም በክፉ ዓይን ማየት በዋጋ የማይተመን ዉረደት ያከናንባል። የነቃ የተደራጀ የታጠቀ ሕዝብ ያሸንፋል የሚለዉን በተግባር ከትግራይ ሕዝብ ዉጤቱን ማየት ይቻላል።
"ያልታጠቀ ሕዝብ አገር የለዉም"‼
ታላቁ የነፃነት ታጋይ ጃል ዳዉድ ኢብሳ❤🙏

የመጫና ቱለማ መረዳጃ ማህበር ላይ ከፍተኛ የሴት አመራር የነበረችዋ ቆንጅየዋ ወ/ሮ አፀደማርያም ሀብተማርያም የደጃዝማች ሀብተማርያም ገብረእግዚአብሔር (ኩምሳ ሞረዳ) ልጅና የብርጋዴር ጄነራል...
18/10/2021

የመጫና ቱለማ መረዳጃ ማህበር ላይ ከፍተኛ የሴት አመራር የነበረችዋ ቆንጅየዋ ወ/ሮ አፀደማርያም ሀብተማርያም የደጃዝማች ሀብተማርያም ገብረእግዚአብሔር (ኩምሳ ሞረዳ) ልጅና የብርጋዴር ጄነራል ሙሉጌታ ቡሊ ሁንዴ ባለቤት ነበረች፡፡ ሙሉጌታ በምዕራብ ሸዋ የሜታ ሮቢ-ምሽጊ/ሺኖ ከተማ ተወላጅ ሲሆን የዘመናዊ ውትድርና አባት በሚለው ይታወቃል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ሜጀር ጀነራል ሙሉጌታ ቡሊ ለኢትዮጵያ እስካሁን ድረስ አድናቆትን ያስገኘውን በኮሪያ የዘመተው የኢትይጵያ ሰላም አስከባሪ ጦር መሪ ነበሩ::

በሆለታ ወታደራዊ ካምፕ የተግባረዕድ ትምህርት ቤት በእሳቸው ስም ተሰይሟል፡፡ ሜጀራል ጄነራል ሙሉጌታ በ1953ቱ መንፈንቅለ መንግስት ጊዜ ተገድሏል፡፡

18/10/2021

አልማዝ አመንሲሳ ውቢት ኢትዮጵያ!
ነፍስሽን በገነት ያኑረው
የኢትዮጵያ ቱሪዝም ኮሚሽን “የ13 ወር ፀጋ”
በሚል ርዕስ ከሚያሳትማቸው ፖስተሮች የዝነኛዋ “ውቢት ኢትዮጵያ” አስደናቂ ተፈጥሮአዊ ውበትና ግርማ ሞገስ የታየበት ፖስተርዋ ሁሌ ከማይረሱን መሃል አንዳቸው ነው። የ4 ልጆች እናት የነበረችው አልማዝ አመንሲሳ የወለጋ ክፍለ ሀገር ተወልዳ አድጋ ከልጆችዋና ለቱሪዝም ኮሚሽን ተቀጥረው ይሰሩ ከነበረው ባለቤቷ ጋር አዲስ አበባ ትኖር ነበር። ከልጇ ዲቦራ ቢሩ ልንረዳው እንደቻልነው አልማዝ አመንሲሳ ሞዴል ወይ የፊልም ተዋናይት አልነበረችም። 1970ዎቹ የብሄራዊ ቱሪዝም ኮሚሽን ለገቢ ማሰባሰብያ የሚሆኑ ድንቅ ድንቅ ፎቶዎችን አንስቶ ለመልቀቅ የፈለገበት ወቅት ነበር። አልማዝ በቱሪዝም ኮሚሽን ፎቶ የመነሳት እድል አጋጥሟት ነው ለ ነቷ ልታበቃ የቻለችው። ኩባዊ ኢትዮጵያዊው የታሪክ ምሁር ኤድዋርዶ ባይሮኖ እንዳስረዳን አልማዝ አመንሲሳ ለፎቶዉ 5 ሳንቲም ሳትቀበል ፎቶዉ ያስገኘና እስከ ዛሬ እያመነጨ ያለው ገቢ
ሙሉ ለሙሉ ለኮሚሽኑ እንዲረከብና የሃገራችን ቱሪዝምን እንዲያገለግል ፍላጎቷ ነበር።
በ2000 ዓም ለህክምና ወደ አሜሪካ አምርታ ህዳር ወር 2001 ዓም ውቢት ኢትዮጵያ በሞት ተለየችን። መልከ መልካሟ ውቢት ኢትዮጵያ ሀገርዋን ላገለገለችበትና ስማችን ላስጠራችበት ምስጋናችን ይገባታል። ነፍስሽን በገነት ያኑረው ታሪኳን ያልሰሙ የፌስቡክ ጏደኞቻችሁ ስለሚኖሩ ይህን ፎቶ LIKE እና SHARE
አድርጉ።

18/10/2021

አብን ግን አሁን ለስንተኛ ጊዜ ነው ክተት ያወጀው? እንዲህ አይነቱ በዘራችሁም አይድረስ ወገኖቼ!!

17/10/2021

ፋኖ ሲታጠቅ አርበኛ ፤ቄሮ ሲታጠቅ ደግሞ #ሸኔ የሚባለው ነገር ከአሁን ወዲህ መወገድ አለበት!!

17/10/2021
 #የጀግናው ኮ/ል አብዲሳ አጋ ¬አስገራሚ የህይወት ታሪክ! ኮ/ል አብዲሳ አጋ ከዚህ አለም በሞት ከተለየ ዛሬ ጥቅምት 3 አርባ አንድ አመት ሞላዉ።ይሄን ታሪክ ከአፄ ቴወድሮስና ከበላይ ዘለቀ...
17/10/2021

#የጀግናው ኮ/ል አብዲሳ አጋ ¬አስገራሚ የህይወት ታሪክ!
ኮ/ል አብዲሳ አጋ ከዚህ አለም በሞት ከተለየ ዛሬ ጥቅምት 3 አርባ አንድ አመት ሞላዉ።
ይሄን ታሪክ ከአፄ ቴወድሮስና ከበላይ ዘለቀ ታሪክ እኩል ስሰማዉ ያደኩት እዉነተኛ የጀግንነት ታሪክ ነዉ።
አብዲሳ አጋ በ1928 ዓ/ም የጣልያን ወረራ ወቅት ተማርኮ ወደ ጣልያን ከተወሰደ በኋላ ብርድ ልብሱን ቀዳዶ በመቀጣጠል በመስኮት አምልጦ በርካታ ጀግንነቶችን የፈጸመ የኢትዮጵያ ወታደር ነው። ኮሎኔል አብዲሳ አጋ የተወለደው በ1912 ዓ.ም ፣ ወለጋ ነበር።
በ12 ዓመቱ አባቱ በንዴት ወንድማቸውን በመግደላቸው ሲታሰሩ አብዲሳ አባቱን ለማስፈታት የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን ቢያደርግም ሳይሳካ በሞት ተቀጥተዋል። በኋላም በ14 ዓመቱ የኢትዮጵያን ጦር በመቀላቀል ሀገሩን ማገልገሉን ሀ ብሎ ጀመረ። አብዲሳ ጦሩን ከተቀላቀለ ከሁለት አመት በኋላ የአድዋን ሽንፈት ለመበቀል የዛተው ፋሺስት ሙሶሎኒ በድጋሚ ኢትዮጵያን ሲወር ሀገሩን ለመከላከል በ16 ዓመቱ ወራሪውን ጦር መዋጋት ጀመረ።
ውጊያ ላይ ባጋጠመው የመቁሰል አደጋ ህክምና ላይ ከቆየ በኋላ አዲስ አበባ ውስጥ ፒያሳ አካባቢ በሚገኝ ቤት በቁም እስር ላይ ነበር። በኋላ ጣልያን ኢትዮጲያን እንዲያስተዳድር በሾመችው ግራዚያኒ ላይ የመግደል ሙከራ ከተደረገ በኋላ አብዲሳ አጋ እና ሌሎች 37 የሚሆኑ የቁም እስረኞች ተጠርጣሪ ተብለው በከባድ ስቃይ እስር ቤት ከቆዩ በኋላ በወቅቱ የጣልያን ግዛት በነበረችው በሶማሊያ በኩል ወደ ጣልያን ተወስዶ በሲሲሊ ደሴት በሚገኝ እስር ቤት እስረኛ ተደረገ።
አልሸነፍ ባይነት መለያው የሆነው አብዲሳ ሁሊዮ ከተባለ ዩጎዝላቪያዊ የጦር እስረኛ ጋር በመተባበር ከባድ ጥበቃ ከሚደረግበት እስር ቤት ለማምለጥ ማሰላሰል ጀመረ። ተሳክቶለት ቢያመልጥ እንግዳ አገር እንደሚጠብቀው ቢያውቅም በነጻነቱ የማይደራደረው አብዲሳ የተሰጠውን የብርድ-ልብስ ቀዳዶ በመቀጣጠል በመስኮት በኩል አመለጠ።
ከዛ በኋላ ግን ሽሽት አልነበረም የጀመረው አብዲሳ። ከጥቂት ቀናት በኋላ በማታ ወደ እስር ቤቱ በመመለስ ጠባቂዎቹ ላይ ጥቃት በመፈጸም እስረኞቹን በመሉ ነጻ ማውጣት ችሎ ነበር። ያመለጡት እስረኞች ከእስር ቤቱ ጠባቂዎች በወሰዱት መሳሪያ በመታገዝ የአማጽያን ጦር ያደራጁ ሲሆን ጦሩን እንዲመራም የመረጡት ጀግናውን አብዲሳን ነበር። ከዛም የተለያዩ የጣልያን ወታደራዊ ሠፈራዎች ላይ ጥቃት በመፈጸም ወራሪዎቹ ጣልያኖች ኢትዮጵያ ውስጥ ከነበረው የአርበኛ እንቅስቃሴ ያልተናነሰ ጥቃት በሀገራቸው ያጋጥማቸው ጀመር።
በአብዲሳ ጦር እጅግ የተረበሹት ጣልያኖችም በርካታ ስጦታዎችን ቃል በመግባት ውጊያውን እንዲያቆም እና የነሱን ጦር እንዲቀላቀል ለምነውት ነበር። አብዲሳ ግን ከፋሺስት ሥርዓት ጎን እንደማይቆም በማስረገጥ ጥያቄውን ውድቅ አደርጎ ጣልያኖችን በሀገራቸው ማስጨነቅ ቀጠለ።
በወቅቱ እየተጋጋለ የመጣው የጀርመን ናዚ ሥርዓት ሁለተኛው የዓለም ጦርነትን ሲጀምር ፋሺስት ሙሶሎኒ ከጀርመኖች ጋር ሲያብር እንግሊዝ፣ ፈረንሳይ እና አሜሪካን ጨምሮ በርካታ የምዕራብ አገሮች የሕብረት ጦር መስርተው የሙሶሎኒን ጦር መውጋት ጀምረው ነበር።
በወቅቱ ይህ የሕብረት ጦር የአብዲሳን ዝና በመስማታቸው ጣልያንን ለማዳከም ለአብዲሳ ጦር የቁሳቁስ ድጋፎች ማድረግ ጀመሩ። በድጋፉ በመጠናከር ፋሺስቱን ሰራዊት ማርበድበድ የቀጠለው አብዲሳ የጣልያን ጦር ተሸንፎ ዋና ከተማዋሮም በአሜሪካን እና እንግሊዝ የሚመራ ጦር እጅ ስር ከወደቀች በኋላ የሚመራቸውን ከተለያዩ አገር የወጡ ወታደሮች በሙሉ ክንዳቸው ላይ የኢትዮጲያን ባንዲራ እንዲያስሩ በማድረግ የሃገሩን ባንዲራ እያውለበለበ ሮም ከተማ ሲገባ በአለም አቀፉ ህብረት ጦር ትልቅ አቀባበል ተደርጎለት ነበር።
ከዛም በኋላ ከተጨማሪ ወታደሮች ጋር በአለም አቀፉ ህብረት ስር የሚመራ ጦር መሪ በመሆን ጀርመንን ለማሸነፍ በሚደረገው የመጨረሻ ውጊያ ላይ ተሳትፎ ግዳጁን በሚገባ በመወጣት የኢትዮጲያን ባንዲራ ከእጁ ሳይለይ በርካታ የጀርመን ከተሞችን ነጻ ማውጣት ችሎ ነበር። ከጦርነቱ መገባደድ በኋላም የእንግሊዝ፣ የካናዳ እና የአሜሪካ መንግሥታት ጦራቸውን ተቀላቅሎ እንዲቀጥል በርካታ ጥቅማ ጥቅሞችን አቅርበውለት ነበር። አብዲሳ ግን ኢትዮጲያ ምንም ያህል ድሃ ብትሆንም ህዝቡን እና መንግስቱን ጥሎ እንደማይሄድ አስረግጦ በመናገር ጥያቄውን ውድቅ አደረገ። በዚህ የተናደዱ ምዕራብውያንም በፈጠራ ወንጀል ከሰው ወደ እስር ቤት አስገብተውት ነበር። በኋላም እስሩ ወደ ገንዘብ ቅጣት ተቀይሮ ከተከፈለ በኋላ በክብር ወደ ሃገሩ ሊመለስ ችሏል። ወደ ኢትዮጲያ ከተመለሰ በኋላ ሰራዊቱን በቅንነት ያገለገለው አብዲሳ በኮኔልነት ማዕረግ የአጼ ሃይለስላሴ ልዩ ጠባቂ ጦር እየመራ ቆይቶ ንጉሱ ከስልጣን ከወረዱ ከጥቂት አመታት በኋላ ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል።የጀግናው ኮ/ል አብዲሳ አጋ ¬አስገራሚ የህይወት ታሪክ
ኮ/ል አብዲሳ አጋ ከዚህ አለም በሞት ከተለየ ዛሬ ጥቅምት 3 አርባ አንድ አመት ሞላዉ።
ይሄን ታሪክ ከአፄ ቴወድሮስና ከበላይ ዘለቀ ታሪክ እኩል ስሰማዉ ያደኩት እዉነተኛ የጀግንነት ታሪክ ነዉ።
አብዲሳ አጋ በ1928 ዓ/ም የጣልያን ወረራ ወቅት ተማርኮ ወደ ጣልያን ከተወሰደ በኋላ ብርድ ልብሱን ቀዳዶ በመቀጣጠል በመስኮት አምልጦ በርካታ ጀግንነቶችን የፈጸመ የኢትዮጵያ ወታደር ነው። ኮሎኔል አብዲሳ አጋ የተወለደው በ1912 ዓ.ም ፣ ወለጋ ነበር።
በ12 ዓመቱ አባቱ በንዴት ወንድማቸውን በመግደላቸው ሲታሰሩ አብዲሳ አባቱን ለማስፈታት የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን ቢያደርግም ሳይሳካ በሞት ተቀጥተዋል። በኋላም በ14 ዓመቱ የኢትዮጵያን ጦር በመቀላቀል ሀገሩን ማገልገሉን ሀ ብሎ ጀመረ። አብዲሳ ጦሩን ከተቀላቀለ ከሁለት አመት በኋላ የአድዋን ሽንፈት ለመበቀል የዛተው ፋሺስት ሙሶሎኒ በድጋሚ ኢትዮጵያን ሲወር ሀገሩን ለመከላከል በ16 ዓመቱ ወራሪውን ጦር መዋጋት ጀመረ።
ውጊያ ላይ ባጋጠመው የመቁሰል አደጋ ህክምና ላይ ከቆየ በኋላ አዲስ አበባ ውስጥ ፒያሳ አካባቢ በሚገኝ ቤት በቁም እስር ላይ ነበር። በኋላ ጣልያን ኢትዮጲያን እንዲያስተዳድር በሾመችው ግራዚያኒ ላይ የመግደል ሙከራ ከተደረገ በኋላ አብዲሳ አጋ እና ሌሎች 37 የሚሆኑ የቁም እስረኞች ተጠርጣሪ ተብለው በከባድ ስቃይ እስር ቤት ከቆዩ በኋላ በወቅቱ የጣልያን ግዛት በነበረችው በሶማሊያ በኩል ወደ ጣልያን ተወስዶ በሲሲሊ ደሴት በሚገኝ እስር ቤት እስረኛ ተደረገ።
አልሸነፍ ባይነት መለያው የሆነው አብዲሳ ሁሊዮ ከተባለ ዩጎዝላቪያዊ የጦር እስረኛ ጋር በመተባበር ከባድ ጥበቃ ከሚደረግበት እስር ቤት ለማምለጥ ማሰላሰል ጀመረ። ተሳክቶለት ቢያመልጥ እንግዳ አገር እንደሚጠብቀው ቢያውቅም በነጻነቱ የማይደራደረው አብዲሳ የተሰጠውን የብርድ-ልብስ ቀዳዶ በመቀጣጠል በመስኮት በኩል አመለጠ።
ከዛ በኋላ ግን ሽሽት አልነበረም የጀመረው አብዲሳ። ከጥቂት ቀናት በኋላ በማታ ወደ እስር ቤቱ በመመለስ ጠባቂዎቹ ላይ ጥቃት በመፈጸም እስረኞቹን በመሉ ነጻ ማውጣት ችሎ ነበር። ያመለጡት እስረኞች ከእስር ቤቱ ጠባቂዎች በወሰዱት መሳሪያ በመታገዝ የአማጽያን ጦር ያደራጁ ሲሆን ጦሩን እንዲመራም የመረጡት ጀግናውን አብዲሳን ነበር። ከዛም የተለያዩ የጣልያን ወታደራዊ ሠፈራዎች ላይ ጥቃት በመፈጸም ወራሪዎቹ ጣልያኖች ኢትዮጵያ ውስጥ ከነበረው የአርበኛ እንቅስቃሴ ያልተናነሰ ጥቃት በሀገራቸው ያጋጥማቸው ጀመር።
በአብዲሳ ጦር እጅግ የተረበሹት ጣልያኖችም በርካታ ስጦታዎችን ቃል በመግባት ውጊያውን እንዲያቆም እና የነሱን ጦር እንዲቀላቀል ለምነውት ነበር። አብዲሳ ግን ከፋሺስት ሥርዓት ጎን እንደማይቆም በማስረገጥ ጥያቄውን ውድቅ አደርጎ ጣልያኖችን በሀገራቸው ማስጨነቅ ቀጠለ።
በወቅቱ እየተጋጋለ የመጣው የጀርመን ናዚ ሥርዓት ሁለተኛው የዓለም ጦርነትን ሲጀምር ፋሺስት ሙሶሎኒ ከጀርመኖች ጋር ሲያብር እንግሊዝ፣ ፈረንሳይ እና አሜሪካን ጨምሮ በርካታ የምዕራብ አገሮች የሕብረት ጦር መስርተው የሙሶሎኒን ጦር መውጋት ጀምረው ነበር።
በወቅቱ ይህ የሕብረት ጦር የአብዲሳን ዝና በመስማታቸው ጣልያንን ለማዳከም ለአብዲሳ ጦር የቁሳቁስ ድጋፎች ማድረግ ጀመሩ። በድጋፉ በመጠናከር ፋሺስቱን ሰራዊት ማርበድበድ የቀጠለው አብዲሳ የጣልያን ጦር ተሸንፎ ዋና ከተማዋሮም በአሜሪካን እና እንግሊዝ የሚመራ ጦር እጅ ስር ከወደቀች በኋላ የሚመራቸውን ከተለያዩ አገር የወጡ ወታደሮች በሙሉ ክንዳቸው ላይ የኢትዮጲያን ባንዲራ እንዲያስሩ በማድረግ የሃገሩን ባንዲራ እያውለበለበ ሮም ከተማ ሲገባ በአለም አቀፉ ህብረት ጦር ትልቅ አቀባበል ተደርጎለት ነበር።
ከዛም በኋላ ከተጨማሪ ወታደሮች ጋር በአለም አቀፉ ህብረት ስር የሚመራ ጦር መሪ በመሆን ጀርመንን ለማሸነፍ በሚደረገው የመጨረሻ ውጊያ ላይ ተሳትፎ ግዳጁን በሚገባ በመወጣት የኢትዮጲያን ባንዲራ ከእጁ ሳይለይ በርካታ የጀርመን ከተሞችን ነጻ ማውጣት ችሎ ነበር። ከጦርነቱ መገባደድ በኋላም የእንግሊዝ፣ የካናዳ እና የአሜሪካ መንግሥታት ጦራቸውን ተቀላቅሎ እንዲቀጥል በርካታ ጥቅማ ጥቅሞችን አቅርበውለት ነበር። አብዲሳ ግን ኢትዮጲያ ምንም ያህል ድሃ ብትሆንም ህዝቡን እና መንግስቱን ጥሎ እንደማይሄድ አስረግጦ በመናገር ጥያቄውን ውድቅ አደረገ። በዚህ የተናደዱ ምዕራብውያንም በፈጠራ ወንጀል ከሰው ወደ እስር ቤት አስገብተውት ነበር። በኋላም እስሩ ወደ ገንዘብ ቅጣት ተቀይሮ ከተከፈለ በኋላ በክብር ወደ ሃገሩ ሊመለስ ችሏል። ወደ ኢትዮጲያ ከተመለሰ በኋላ ሰራዊቱን በቅንነት ያገለገለው አብዲሳ በኮኔልነት ማዕረግ የአጼ ሃይለስላሴ ልዩ ጠባቂ ጦር እየመራ ቆይቶ ንጉሱ ከስልጣን ከወረዱ ከጥቂት አመታት በኋላ ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል።

13 ቁልፍ ውጤታማ የአመራር ባህሪዎች/Key Characteristics of Effective Leadership    ✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅ስለ አመራር ሦስት መሠረታዊ መርሆችን አምናለሁ። በመ...
17/10/2021

13 ቁልፍ ውጤታማ የአመራር ባህሪዎች/Key Characteristics of Effective Leadership
✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅
ስለ አመራር ሦስት መሠረታዊ መርሆችን አምናለሁ። በመጀመሪያ ፣ እያንዳንዱ ሰው በንግድ ፣ በቤተሰብ ፣ በአትሌቲክስ ቡድን ፣ በሲቪክ ድርጅት ፣ በቤተክርስቲያን ፣ በምኩራብ ፣ በመስጊድ ወይም በመፅሃፍ ክበብ ቢሆን በተወሰነ አቅም መሪ ነው። እኔ በጣም ብዙ ሰዎች ልዩ የመሪነት ሚናቸውን ማየት እና በሌሎች ላይ ተጽዕኖ ለማሳደር እድሎችን ያጡ ይመስለኛል። ሁለተኛው መሠረታዊ እምነቴ ሁሉም እንደ መሪ ማደጉን መቀጠል አለበት የሚል ነው። ምንም እንኳን መደበኛ ጊዜን ለአመራር እድገትና ለመማር አስቸጋሪ ቢሆንም ፣ ለረጅም ጊዜ ስኬት እና ስኬት ወሳኝ የሆነ ተግሣጽ ነው። በመጨረሻም ፣ የአመራር ባህሪያትን መማር እና ማሳደግ እንደሚቻል አምናለሁ ፣ እያንዳንዳችን የተሻለ መሪ የመሆን እድልን ይፈቅዳል።
የቤከር ዶንሰንሰን ዋና ሥራ አስፈፃሚ ለመሆን ተተኪ ተብዬ ስጠራ ፣ የአመራር ዕድገትን ጨምሮ በአምስት ቁልፍ የእድገት ዘርፎች ላይ ለማገዝ የሽግግር ምክር ቤትን አሳለፍኩ። ከሌሎች የትኩረት መስኮች መካከል የአመራር ልማት ንዑስ ኮሚቴ የተሳካ መሪዎችን ዋና ዋና ባህሪያት እና ባህሪያት ዘርዝሯል። ንዑስ ኮሚቴው እያንዳንዳችን በቤከር ዶኔልሶ ውስጥ ለመኮረጅ እና ለማሻሻል የምንፈልጋቸውን ውጤታማ አመራር የሚመሰረቱትን ዋና ዋና ክፍሎች ለይቶ አውቋል።
እያንዳንዳችን ሊኖረን ፣ ሊያድግ እና ሊያሻሽለው ከሚገባቸው በጣም አስፈላጊ ባህሪዎች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል።
✍️ ውጤታማ ግንኙነት/Effective Communication
ጥሩ ግንኙነት እና አመራር በሁሉም ደረጃዎች ከሌሎች ጋር መገናኘት ነው። መገናኘት ከሰዎች ጋር የመለየት እና ከእነሱ ጋር የመገናኘት ችሎታ ነው። (I) የጋራ መግባባት በማግኘት የበለጠ ውጤታማ እንሆናለን ፤ (ii) ግንኙነታችንን ቀላል ማድረግ ፤ (iii) የሰዎችን ፍላጎት መያዝ; (iv) እነሱን ማነሳሳት; እና (v) ትክክለኛ መሆን። ውጤታማ አስተላላፊ ተገቢ በሚሆንበት ጊዜ ግልፅነትን እና የጋራ ውሳኔን ይሰጣል ፣ ግብረመልስ በቀጥታ ያስተላልፋል እንዲሁም የሌሎችን ስኬት በመደበኛነት ይቀበላል። የበለጠ ስኬታማ አስተላላፊ ለመሆን ፣ በመስተጋብር ውስጥ መገኘት አለብን። ይህ የሚያዘናጋ-ነፃ ዞን መፍጠርን (እነዚያን አይፎኖች ያስቀምጡ!) ፣ እውነተኛ መሆን እና የመልዕክቱ ባለቤት መሆንን ያካትታል።
✍️ እምነት የሚጣልበት/Trustworthy
ዘ Leadership Challenge, James Kouzes እና Barry Posner በተሰኘው ትምህርታዊ መጽሐፋቸው ውስጥ “እኛ ባደረግነው እያንዳንዱ የዳሰሳ ጥናት ፣ ሐቀኝነት ከማንኛውም የአመራር ባህርይ የበለጠ ተመርጧል” ብለዋል። አንድ መሪ በማንኛውም የሰዎች ቡድን ፣ በትልቁም በትልቁም ተከታይነትን እንዲያገኝ ፣ ሕዝቡ በመጀመሪያ ግለሰቡ ለእሱ መታመን የሚገባ መሆኑን ማረጋገጥ ይፈልጋል። የቡድን አባላት በመሪያቸው ላይ ሙሉ በሙሉ እንዲተማመኑ ፣ መሪው የቅንነት እና ትክክለኛ ባህሪ ያለው ሰው መሆኑን ማመን አለባቸው። ተዓማኒነት ከእሴቶች እና ከስነምግባር ጋር በጥብቅ የተቆራኘ ነው። አስፈላጊ በሆኑ መርሆዎች ላይ አቋም የሚወስዱ መሪዎች አባላት ይሳባሉ። ኩዌዝ እና ፖዝነር እንደሚሉት መሪዎች “ለመምራት በሚመኙት ሰዎች ፊት [ቃላቸው] ብቻ ጥሩ” ናቸው።
✍️ ቆራጥ/Decesive
ጠንካራ መሪ ጥሩ የማመዛዘን ችሎታ ያለው ፣ በመረጃ የተደገፈውን ግብዓት ያደንቃል ፣ የተለያዩ አስተያየቶችን ይቀበላል። ምርጥ መሪዎች ግን ቆራጥ ሆነው መቆየት አለባቸው። የቀድሞው የፖርሽ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፒተር ሹትዝ “እንደ ዴሞክራሲ ውሳኔዎችን ያድርጉ ፣ እንደ አምባገነን ሥርዓት ያስፈጽሙ” ይሉ ነበር። ሆን ተብሎ የውሳኔ አሰጣጥ (i) ሁሉንም ሊሆኑ የሚችሉ ውጤቶችን ትክክለኛ እና ሙሉ-ካርታ መገንባት ያካትታል። (ii) እነዚህ ሁሉ መንገዶች የት እንደሚመሩ መተንበይ ፣ እና (iii) የተለያዩ መፍትሄዎችን በማመዛዘን ውሳኔ ላይ መድረስ። መሪዎች እያንዳንዱ ውሳኔ ፍጹም እንዲሆን በመፈለግ ብዙውን ጊዜ እራሳቸውን በክርን ያያያዛሉ ፣ ሆኖም ግን ፣ ምርጥ መሪዎች ስህተት ሊሆኑ እንደሚችሉ የሚያውቁ ውሳኔዎችን ያደርጋሉ። እውነተኛው ተለዋጭ በፍጥነት እና በልበ ሙሉነት እየወሰነ ነው። ከሁሉም በላይ ታላላቅ መሪዎች ቀጣይ ውሳኔዎችን በተሻለ ለማሳወቅ ከእያንዳንዱ ውሳኔ ፣ ጥሩም ይሁን መጥፎ በሕሊና ይማራሉ።
✍️ ጥሩ አሳቢ/Independent Thinker
ከመሪ በጣም አስፈላጊ ከሆኑት ባሕርያት አንዱ ጥሩ አሳቢ የመሆን ችሎታ ነው። የቆየ ስትራቴጂ ወይም ወቅታዊ የአስተዳደር ጽንሰ -ሀሳቦች ከማግባት ይልቅ መሪዎች የጋራ የስሜት መፍትሄዎችን ማወቅ እና መተግበር አለባቸው። ጥሩ አሳቢዎች ችግሮችን ይፈታሉ እና ቡድናቸውን ወይም ድርጅታቸውን ለመገንባት ሀሳቦች በጭራሽ አይጎድሉም። ትኩስ እና የፈጠራ ሀሳቦችን ለማነቃቃት ፣ መጽሐፍትን በማንበብ ፣ ፖድካስቶችን በማዳመጥ እና ከፈጠራ አሳቢዎች ጋር በመነጋገር ጊዜዎን ያሳልፉ። ከእያንዳንዱ የሰዓት ጥረት አንድ ወይም ሁለት የሚመለከታቸው ሀሳቦችን ወደ ሁኔታዎ ብቻ ሊያገኙ ይችላሉ ፣ ግን ያ አዲስ ሀሳብ ፣ ለቡድንዎ የተቀየረው ፣ ለዘላቂ ስኬት ግኝት ሊሆን ይችላል። በሕግ ትምህርት ቤት ወቅት በሠራሁት የቴክሳስ ኩባንያ ውስጥ አንድ ከፍተኛ ባልደረባ “የመስኮት ጊዜን ማየትን” አስፈላጊነት አስተማረኝ። ሕግን በመለማመድ በተራቀቀ ፍጥነት ፣ ለደንበኞቻችን (ወይም ለቡድኖቻችን) በጣም ጥሩው እሴት የአስተሳሰብ ጊዜን ማካተት እንዳለበት አበረታቷል። ብዙ ስኬታማ መሪዎች ፈተናዎችን ፣ ዕድሎችን እና ሀሳቦችን ለማሰብ በቀን መቁጠሪያቸው ላይ ጊዜን ያግዳሉ። በዚህ ጊዜ የሚነሱ ሀሳቦችን ለመያዝ ብዕር እና ወረቀት በእጅዎ መያዙን ያረጋግጡ።
✍️ አዎንታዊ/Positive
በጣም ውጤታማ የሆኑት መሪዎች አዎንታዊ እና አነቃቂ ሆነው ይቆያሉ። ሰዎች መሪያቸው ጉልበት እና የወደፊቱን እንደሚወድ ይጠብቃሉ። እነሱ የቡድን አባላትን በጋለ ስሜት እና ድርጅቱ በሚሄድበት ጠንካራ እምነት ማነሳሳት አለባቸው። እንቅፋቶች እና ውድቀቶች እንደሚከሰቱ 100 በመቶ እርግጠኛነት አለ ፣ ይህም ውጥረት እና አሉታዊነት እንዲሰፍን ያደርጋል። አዎንታዊ መሪ በአስቸጋሪ እና አስጨናቂ ጊዜያት መካከል አዎንታዊ ሆኖ እንዲቆይ ምላሻቸውን እና ጭንቀታቸውን መቆጣጠር አለበት። መሪዎች የአባሎቻቸውን መንፈስ ከፍ በማድረግ ተስፋ መስጠት አለባቸው። እርስዎን “በቃላት ፣ በባህሪያት እና በድርጊቶች” እንደተረጋገጠ መሪ አድርገው ማየት አለባቸው ፣ ስለዚህ እነሱም “መሰናክሎች ይወገዳሉ እናም ህልሞች ይፈጸማሉ” ብለው ያምናሉ። (የአመራር ፈታኝ ሁኔታ) ይህ ደግሞ ሌሎች እርስዎ ስለሚመሩበት አካሄድ ብሩህ እና ተስፋ ሰጭ እንዲሆኑ እና ንግዱን ወደፊት ለማራመድ የሚያስፈልገውን ለማድረግ ፈቃደኛ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል።
✍️ ትሕትና/Humility
አርአያ የሆኑ መሪዎች ትልቅ ስኬት ብቻውን ሊከናወን እንደማይችል ይገነዘባሉ ፣ ግን የሌሎችን እርዳታ ይጠይቃል። መሪዎች የአገልጋይ የአመራር አስተሳሰብን መቀበል ወሳኝ ነው። ይህ ለግብረመልስ ለማዳመጥ እና ተገቢውን ምላሽ ለመስጠት እና እንደ አስፈላጊነቱ ስህተቶችን ለመቀበል ፈቃደኝነትን ያጠቃልላል። ትሑት መሪዎች ኩራት እና ማስመሰል የላቸውም ፣ ይልቁንም ለተለያዩ አመለካከቶች እና ሀሳቦች ፍላጎት አላቸው። እነሱ እራሳቸውን በሚያድግ ቀልድ ይሰራሉ ፣ ለሌሎች ክብር ይሰጣሉ ፣ እና ከሌሎች ጋር በሚኖራቸው መስተጋብር ምድር ላይ ይኖራሉ። አንድ መሪ ብዙውን ጊዜ ትክክል እንዳልሆኑ ወይም ስህተት እንደሠሩ ለመቀበል ዝግጁ መሆን አለበት። ትሑት መሪ ተነስቶ ተገቢ ሆኖ ሲገኝ ይቅርታ ይጠይቃል። ሁሉም ጉድለቶች ተሞልተው ኳሱን ይጥላሉ ፣ ግን በጣም ውጤታማ የሆኑት መሪዎች ትሁት እና የማይታመኑ ሆነው ይቆያሉ። ለመማር እና ለማደግ ሁል ጊዜ ፈቃደኛ በመሆን ድርጅቱን እና ግለሰቦቹን ይጠቅማል።
✍️ የግጭት አፈታት/Conflict Resolution
እያንዳንዱ የቢሮ አካባቢ እና እያንዳንዱ ቡድን ግጭት ይኖረዋል። ግጭትን የሚያደክም እና የሚያስጨንቅ ቢሆንም ዋናው ችግር ዋናው ግጭቱ አይደለም። እውነተኛው ጉዳይ አስፈላጊ የሆነውን ግጭት እንዴት እንደምንይዝ ነው። አንድ ውጤታማ መሪ አወንታዊ ውጤቶችን ለማምጣት ግጭቶችን ያስተዳድራል እንዲሁም ይፈታል። መሪው በሥራ ቦታ ያለውን የዲፕሎማሲ ጥበብ ተረድቶ ውጤታማ በሆነ መንገድ ይተገበራል። በብዙ ሁኔታዎች ውስጥ ግጭት በእርግጥ ጥሩ ነገር ነው። ከፈጠራ የሚመነጩ አወንታዊ ውጤቶችን ለማሽከርከር ፣ በባልደረቦች መካከል ያለውን ትስስር ለማጠናከር እና መላውን ቡድን እና ውሳኔን የሚጠቅሙ የተለያዩ አመለካከቶችን እንዲፈቅድ ሊረዳ ይችላል። ብዙውን ጊዜ አንድ መሪ በስራ ባልደረቦች መካከል አለመግባባትን እንዲፈጽሙ ወደ ግጭት ውስጥ መግባት የለበትም። ሆኖም ግጭቱ ለማሳካት እየሞከሩ ያሉትን ግብ ወይም ሥራው እንዴት እንደሚከናወን ሂደቱን መጣስ ከጀመረ ፣ በተዘዋዋሪም ሆነ በቀጥታ መፍታት አለብዎት። ባለፉት ዓመታት ውጤታማ ሆኖ ያገኘሁት አንድ መሣሪያ (እኔ) ሁሉንም እውነታዎች ሳላገኝ የደረስኩትን ማንኛውንም የሐሰት ግምቶች ወይም መደምደሚያዎች ከግምት በማስገባት ለጠንካራ ውይይት መዘጋጀት ነው ፤ እና (ii) ተጓዳኙን እስከ ውይይቱ ድረስ ከሁሉም አቅጣጫዎች ሁኔታውን ከግምት ውስጥ ማስገባት። ይህ መልእክቱን እና ስብሰባውን በተሻለ ሁኔታ ለማቀድ ይረዳል። ተጣጣፊ እና ተጣጣፊነትን በሚያካትት ዘዴ አቀራረብ ግጭቱ ያነሰ ውጥረት እና የበለጠ ሊሰማው ይችላል።
✍️ ባለራዕይ/Visionary
ሌላው ከፍተኛ የአመራር ባህሪ ለድርጅቱ የወደፊት አቅጣጫ እና አሳቢነት ወደፊት የመመልከት ችሎታ ነው። ጠንካራ መሪዎች ከአሁኑ ባሻገር አይተው በረጅም ጊዜ ስልታዊ በሆነ መንገድ ያቅዳሉ። እነሱን ለማነሳሳት እና ለማነሳሳት ራዕዩን ለመሸጥ ቡድናቸውን ወደፊት በሚመለከት መንገድ ይሳተፋሉ። መሪዎች አሁን ባለው ሁኔታ ሊረኩ አይችሉም ፤ ይልቁንም ነገሮች እንዴት ወደፊት የተሻለ እንደሚሆኑ ላይ ማተኮር አለባቸው። ውጤታማ መሪ ለቡድኑ ለምን በአሁኑ ጊዜ ባሉበት መቆየት ተቀባይነት እንደሌለው እና ለረጅም ጊዜ ስኬት ለማሳካት የሚያስፈልጋቸውን “እዚያ” ራዕይ ማሳየት የሚችል ለቡድኑ በግልጽ መግለፅ የሚችል ነው። መሪው በቦታው መቆየቱ በጣም ተቀባይነት የሌለው እና የእራሱን “እዛ” ለማሳካት የሚስብ ሆኖ ሁሉም እዚያ ለመድረስ በአንድ አቅጣጫ ይሰለፋል። እርግጠኛ ባልሆነ የወደፊት ጉዞ ላይ አንድ ቡድን እንዲቀላቀላቸው ሲጠይቁ መሪዎች በአእምሮ ውስጥ መድረሻ ያስፈልጋቸዋል።
✍️ የቡድን ገንቢ/Team Builder
ሙሉ እምቅ ችሎታን ለማግኘት አንድ መሪ በቡድን አባላት ላይ መዋዕለ ንዋያቸውን ማፍሰስ እና ማብቃት ወሳኝ ነው። ችሎታ ያለው የግለሰቦችን ቡድን አንድ ላይ ስለሰበሰቡ በራስ -ሰር ታላቅ ቡድን ይሆናሉ ማለት አይደለም። ሁላችንም በስፖርት ዝግጅቶች እና በንግድ ውስጥ የዚህ ምሳሌዎችን አይተናል። ይልቁንም ታላቅ የቡድን ግንባታ የሚጀምረው ከመሪው የሚጀምረው አንድነትን በመገንባት ነው። በአንድ የጋራ ምክንያት ወይም ራዕይ ዙሪያ አንድ ቡድን ለመሰብሰብ ፣ መሪው ራዕዩን ማየት እና ቡድኑ ዘወትር በእሱ ላይ እንዲያተኩር ማድረግ አለበት። የቡድን አባላት አንድ የጋራ ግብ ሲጋሩ በአንድ ላይ ተሰባስበው የታላላቅ ግለሰቦች ጥምር ብቻ የሆኑትን ተፎካካሪዎችን ይበልጣሉ። አንድ ቡድን ለመፈፀም በሚሞክሩት ላይ ጥልቅ ስሜት ሲሰማው ፣ ተጠያቂነትን ይገነባል እና ቡድኑን ይነዳዋል። ውጤታማ የቡድን ግንባታ ድሎችን በጋራ ማክበርን ፣ ወይም ጥረቶች ሲሳኩ ማበረታታትን ይጨምራል። እንደ መሪ ለማሸነፍ ከፈለጉ የተቀናጁ እና የተዋሃዱ ቡድኖችን የመገንባትን ዋጋ እና አስፈላጊነት ይቀበሉ።
✍️ ግላዊነት የተላበሰ/Personale
ከሚመራቸው ሰዎች ጋር እውነተኛ ግንኙነቶችን መገንባት ስኬታማ መሪ ለመሆን ቁልፍ ነው። አንድ መሪ በቀላሉ የሚቀረብ ፣ ተደራሽ ፣ የሰራተኞቻቸውን ፍላጎት መረዳት እና ጠንካራ ግንኙነትን ለመገንባት ቁርጠኛ መሆን አለበት። ይህንን ለማድረግ በጣም ጥሩ ከሆኑት መንገዶች አንዱ እርስዎ ከሚመሩዋቸው ጋር መሆን ነው። አዳራሾችን ይራመዱ ፣ ኃላፊነቶቻቸውን እና ተግዳሮቶቻቸውን ይረዱ ፣ እና ከሚያገለግሏቸው ሰዎች ጋር ጊዜ ያሳልፉ። ዊንስተን ቸርችል ዝነኛ ግንኙነቶችን በመገንባት ጊዜ ማሳለፉ ታላቅ ስኬቶችን እንዲያገኝ በሚረዳበት “በእራት ጠረጴዛ ዲፕሎማሲ” ውስጥ ተሰማርቷል። የአመራር ባለሙያው ጆን ሲ ማክስዌል መሪዎችን “በሕዝቡ መካከል ቀስ ብለው እንዲሄዱ ፣ የሰዎችን ስም ያስታውሱ ፣ በሁሉም ላይ ፈገግ ይበሉ ፣ እና እርዳታ ለመስጠት ፈጣን” እንዲሆኑ ይመክራል። በጣም ውጤታማ የሆኑት መሪዎች ተደራሽ ፣ ተደራሽ እና ተጠያቂ ናቸው።
✍️ አመስጋኝ/Appreciative
በመሪ እጅ ከሚገኙት በጣም ጠቃሚ መሣሪያዎች አንዱ ሁለት በጣም ኃይለኛ ቃላትን መጠቀም ነው - “አመሰግናለሁ”። ለቡድንዎ እና ለሠራተኞችዎ አድናቆት ማሳየት የረጅም ጊዜ ስኬት መሠረት ነው። አድናቆት የቡድን አባላት ዋጋ እንዳላቸው እንዲሰማቸው ያደርጋል። ሰማንያ አንድ በመቶ የሚሆኑ ሰዎች አመስጋኝ መሪ ካላቸው የበለጠ ለመስራት ፈቃደኛ እንደሆኑ ይናገራሉ። የቡድንዎ አባላት ለሚያደርጉት ጥረት ማስተዋል ፣ መታወቅ እና ማድነቅ አለባቸው። በቡድንዎ ውስጥ ያሉትን አካላት ለማመስገን ለአጭር ውይይት ፣ ማስታወሻ ወይም ጥሪ ሁል ጊዜ ጊዜ ዋጋ አለው። አድናቆትን በየጊዜው የሚገልጽ መሪ መሆንም የትሕትና ፣ ብሩህ አመለካከት እና ግላዊነትን የተላበሱ ተጨማሪ ቁልፍ የአመራር ባህሪያትን ለመገንባት ይረዳል። በቡድንዎ ውስጥ ያለን አንድ ሰው ለማመስገን ዛሬ ጊዜ ይውሰዱ እና መደበኛ ልማድ ያድርጉት።
✍️ ተስማሚ/Adaptable
አንድ መሪ ለለውጥ እና ለዕድገት ምቹ በመሆን ተጣጣፊነትን ያሳያል። ዛሬ ባለው የንግድ አየር ሁኔታ ነገሮች በፍጥነት እንደሚለዋወጡ ምንም ጥርጥር የለውም ፣ እና ምርጥ መሪዎች አዳዲስ ነገሮችን ለመሞከር ፈቃደኛ መሆን እና ለማደግ ፈቃደኛ መሆን አለባቸው። አዳዲስ ነገሮችን ለመሞከር ፈቃደኞቻችንን ስናሰፋ ፣ የእኛ የመላመድ ጡንቻ ይስፋፋል። አንድ ታላቅ መሪ ሕዝባቸው የሚገጥማቸውን የማያቋርጥ እና የማያቋርጥ ጥርጣሬ ወደ ዕድል እና እድገት ይለውጣል። በፍጥነት እየተለወጠ ያለውን የንግድ ዓለም ፍላጎትን ለማሟላት ተከታዮቻችን አዲስ አቀራረቦችን እና ቴክኒኮችን እንደምንሞክር ማየት አለባቸው። ይህ በራስ መተማመንን ያዳብራል እናም በዘመናዊ የሕግ አከባቢ ውስጥ የሚያስፈልገውን የተለወጠ ባህል ለመምራት ይረዳል።
✍️ ልብን ማበረታታት/Encouraging the Heart
ለማድመቅ የመጨረሻው ባህሪ ማበረታቻ ነው። በንግድ ውስጥ ያልተለመዱ ውጤቶችን መንዳት ከባድ ነው። በቡድኑ ውስጥ ያለ እያንዳንዱ ሰው በተመሳሳይ አቅጣጫ እየበረረ መሆኑን ለማረጋገጥ ፣ የቡድንዎን ልብ እና አዕምሮ በየጊዜው ማበረታታት እና ማሳተፍ ወሳኝ ነው። በስኬታቸው ኩራት ይግለጹ። ለጠንካራ ሥራቸው እና ለስኬታቸው በመደበኛነት እነሱን ለማመስገን አንድ ነጥብ ያድርጉ። አስፈላጊ ድሎችን ያክብሩ። የግለሰብ አስተዋፅኦዎችን በመለየት ታሪኮችን በመናገር የማህበረሰብ እና የወዳጅነት ስሜት ይፍጠሩ። የቡድንዎን ዋና እሴቶች እና ደረጃዎች ያጠናክሩ። ያልተለመዱ ውጤቶችን በማሽከርከር ይህ ሁሉ ከፍተኛ ትርፍ ያስገኛል።
መሪነት ስለ ማዕረጎች ፣ ቦታ ወይም ኃይል አይደለም። እያንዳንዱ ሰው ሌሎችን ወደ ታላቅ ስኬት የመምራት ችሎታ እና አቅም አለው። መሪነት ለምርጥ አሂድ ንግዶች ወሳኝ ግዴታ ነው። ውጤታማ አመራር በሰዎች ሕይወት ላይ ለውጥ ያመጣል እና በተወዳዳሪ የገቢያ ቦታ ውስጥ ልዩነት ነው። እና ፣ የሁሉም ጉዳይ ነው። መልካም ዜናው የትም ቢጀምሩ እያንዳንዳችን የተሻለ መሪ መሆን እንችላለን። ታላቅ አመራር ሊማር ይችላል ፣ ግን አስፈላጊ ፣ ስኬታማ እና አነቃቂ አመራር ጠንክሮ መሥራት እና ጥረት ይጠይቃል።

23/11/2019

"Warrii nu arrabsaa jiru, Jabaataniitii miti nu sodaataniitii. Tuffii isinitti hin fakkaatin. Osoo isaan lafatti nu eegan mukarra baanee gadi laalle. Kanaafuu, muka nu jalatti muruu barbaadu. dheengadda yeroo aggammiin anarratti yaadame; hawwiin isaanii Oromoon gadi bayee Abiyyiin bu’i akka jedhuun barbaade. Abiyyi ammo military qabuun anaafi uummata kaan akka fixu barbaadan. Nuti san hin goone. Hulaa/balbala cufanneeti, dubbii teenya akka Oromootitti fixannee"
Jawaar Mohammed Denver kan dubbate keessa

18/11/2019

ማለዳ Media ከጀዋር ጋር ቆይታ አድርጎ ነበር

ማለዳ Media :- ጀዋር አንተና ቤተ ክርስቲያንን ምን አገናኛቸው ? አንተ ላይ እንደዚህ ከእምነት ጋር ዘመቻ የሚከፍቱብህ?

Jawar Mohammed :- በፖለቲካው ስናሸንፋቸው መደበቂያቸውን ቤተክርስቲያን አድርገውት እንጂ እኔና ቤተክርስትያን የምያገናኝን ነገር የለም። በዜግነት ፖለቲካ ተደበቁ አልቻሉም።በብሔር ተደበቁ አልቻሉም።አሁን የመጨረሻ መደበቂያቸው ወደ ቤተ እምነት አድርጓል። እየሆነ ያለዉ ይሄ ነዉ።

08/11/2019

፦ ከፕሮፌሰር መሃመድ ሀሰን አንደበት፧
~~"ኬንያ ነፃ ስትወጣ በቀን 5 ሰዐት የኦሮምኛ ፕሮግራም ይተላለፍ ነበር።"~~
~~ "እስከ 1959 ዓ.ም ድረስ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን 5 ደቂቃ እንኳን የኦሮምኛ ፕሮግራም አልነበረም።"~~
===================================
ኢትዮጵያ ውስጥ በደሎች ነበሩ፣ በደሎች ባይኖሩ ኖሮማ የብሄር ጥያቄ አይነሳም ነበር። "እስከ 1959 ዓ.ም ድረስ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን 5 ደቂቃ እንኳን የኦሮምኛ ፕሮግራም አልነበረም። አገሪቷ ለሁሉም እኩል ብትሆን ኖሮ የብሄር ጥያቄ አይመጣም ነበር።
ይሄ ሕዝብ እኮ በራሱ ባህልና በራሱ ልበስ እንዳይኮረ ተደርጎ ነው ሲያስተዳድሩት የነበረው። ኢትዮጵያዊ ለመሆን የመጣህበትን ሕዝብ ባህል ትተህ ሌላ መምሰል ግድ ነበር። የአንድ ጉሩፕ ታሪክ ተተሪኮ የኢትዮጵያ ታሪክ ማለት አይቻልም።
ኢትዮጵያን የተመሰረተችው በሚኒሊክ ሳይሆን እንደ ማንኛውም የአፍሪካ ሀገር በነጮች ነው። ነጮች ናቸው ሚኒሊክ ለሚባል የጦር አበጋዝ የጦር መሳሪያ በመስጠት ሌሎችን እንዲያስገብር የረዱት።
___
እኔ ልጅ እያለው የኢትዮጵያ ሚድያ ኦሮምኛ አይወራም ነበር። እስከ 1975 ዓ.ም ድረስ እስላም ኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩ እስላም ነው የሚባለው እንጂ የኢትዮጵያ እስላሞች አይባሉም። የብሄር ጭቆና ስለነበር ነው ብዙ ንቅናቄዎች የተፈጠሩት።
___
ዶር አቢይ የዚች ሀገር ካፒቴን ናቸው። ወደ ስልጣን የመጡትም በነበረው የፖለቲካ እና የሶሻል ምከንያት ነው። ኦሮሞን ወደጎን በመተው በፍጹም ኢትዮጵያን መምራት አይችሉም። ከኦሮሞ ጋር ከተስማሙ በኋላ ነው ከሌሎች ጋር እንዴት መስማማት እንዳለባቸው መንገድ መቀየስ ያለባቸው። የወጣበትን ሕዝብ በማታው የሚያደገው ጉዞ የትም አያደርሳቸውም።
___
"ባለፈው ዘመን በድንቁርና መንገድ ብዙ ተጉዘናል። አሁን ግን ነገሮች እዚ ላይ ማብቃት አለባቸው። ያለፈውን ታሪክ ለታሪክ ተመራማሪዎች ትተን እቺን ሀገር እንዴት ወደፊት ማስቀጠል እንዳለብን መስማማት መቻል አለብን።"
"ሁሉም የፖለቲካ ሊቃን እና ምሁራን በመሰብሰብ ስለ አባቶቻችን እና እናቶቻችን ታሪክ ትተን ለልጆቻችን የምትሆን አዲሷን ኢትዮጲያ እንመስርት"
___
የፕሬዝዳንት ሙስጠፌ ኡመር አማካሪ ሀቀኛ ምሁር ፕሮፌሰር መሀመድ
የሚገርም ነበር።

Address

Mexico
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Horo Tube posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Horo Tube:

Videos

Share



You may also like