ቤተ-አማራ / Bete-Amhara TV

ቤተ-አማራ / Bete-Amhara TV Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ቤተ-አማራ / Bete-Amhara TV, Media/News Company, Addis Ababa.

Like እና Share ያድርጉ:- ለፈጣን እና አስተማማኝ መረጃ!
ቤተ-አማራ ቴቪ - Bete-Amhara TV covers wide-range of timely and historical issues about the Amhara people, Ethiopians, the Greater Horn of Africa and the Globe.

17/01/2024

ሳልድን የሄድኩ እንደሁ መኖሬ እንዴት ያንገበግበኝ!

08/08/2023

ሰበር ዜና‼️

ፋኖ ዛሬ ጎንደር ላይ 8 ታንክ እና 3 ጄኔራሎችን እና 2400 ወታደሮችን ማርኳል፡፡

Mesganaw Andualem

07/08/2023

ሥርዓቱ ከውስጥ መፍረክረክ ጀምሯል !
በአዲስ አበባ ከተማ የፀጥታ አካላት መካከል ከፍተኛ አለመግባባት ተከሰተ።
ሁለት የወንጀል መከላከል ኮሚሽነሮች እንለቃለን ብለዋል።
ፋኖና አማራ ስልጣናችንን ሊነጥቁን ነው በሚል በሸኔ የሚመራ የተደራጀ ኃይል በአዲስአበባ እና በሸገር ዙሪያ እንዲሸምቅ መደረጉን ነው።
ሁሉንም የፖሊስ መኮንኖች በከተማው ላይ ለሚደርሰው ቀውስ ተጠያቂ አንሆንም ለሕዝብ እናሳውቃለን።
ሕዝብ ራሱን ይጠብቃል ብለዋል። ሁለት የኦሮሞ የፖሊስ መኮንኖች ይሄ ነገር ለኦሮሞም አይጠቅምም ብለዋል።
አዲስአበባ ውስጥ ሦስት እጅ በላይ ሕዝቡ የፋኖ ደጋፊ ነው የሚል ግምገማ ቀርቧል።

07/08/2023

ላስታ፦
ግዳን ሙጃ ወሳኝ ገዥ መሬት ለመቆጣጠር ከባድ ውጊያ ቀጥሏል፡፡ ይህንን ቦታ መቆጣጠር የአካባቢውን ጦርነት 80 በመቶ ይቋጫል፡፡ እስካሁን ፋኖ ከፍተኛ ድል እየተቀዳጀ ነው፡፡
ጎንደር፦
አንድ ሻለቃ መከላከያ ጦር ከድቶ ወደ ፋኖ ተቀላቅሏል፡፡ 4 ዲሽቃ፣ 8 መትረየስ፣ 14 ስናይፐር እና ከ600 በላይ ክላሽንኮፍ ይዘው ነው ፋኖን የተቀላቀሉት፡፡

06/08/2023

ይድረሰ ለአማራ ፋኖ‼️
በአማራ ህዝብ ላይ በአምባገነኑ መንግሰት የታወጀበትን ጦርነት በሚገባ እየመከታቹህ እንደሆነ እንደ አንድ ተገፊ አማራ ሁኔታውን እየተከታተልኩኝ ነው።
ስለሆነም አንዳንድ ጠቃሚ መረጃ ስለመከላከያ ሰራዊት አድረጃጀቱና ሰለታጠቃቸው ከነፍሰ ወከፍ እሰከ ሚካናይዝድ መሳሪያዎች ጉዳት የማድረሰ አቅማቸውና አጠቃቀማቸውን ትንሸ ልንገራቹህ። እየተዋጋቹህ ያላቹህት ውጊያ የሸምቅ ወይም የደፈጣ ውጊያ ሰለሆነ ለደፈጣ ወይም ለሸምቅ ወጊያ የማይሆኑ ወይም የማይመቹህ መሳሪያዎች ዝርዝር እንደሚከተለው ተዘርዝረዋል።
1, 82mm ሞርታር
2, 120mm ሞርታር
3, መድፍ
4,መቶ ሰባት ሮኬት
5, ታንክ
6, ቢኤም ባለ አሰራሁለት አፈሙዝና ባለ አርባ አፈሙዝ እና ከእነዚህ በላይ ከባድ መሳሪያዎች ለቀጥታ ተኩሰ ወይም ለድንገተኛ ማጥቃት የማይሆኑ፣ ያለካርታ ጥቅስ እና ያለዲግሪው ወይም ያለ ሚልሰ ታርጌት መምታት አይችሉም።
ለመደበኛ ውጊያ ላይ ብቻ ነው ትልቅ አገልግሎት ያላቸው ስለዚህ እነዚህን ከላይ የጠቀሰኳቸውን መሳሪያዎች መከላከያ ሰራዊት ወደ እናንተ ሊዋጋ ቢመጣ ያለምንም ፍራቻ እና መደናገጥ በነፍሰ ወከፍ መሳሪያ ማለትም በክላሸ በመግጠም በእጅ በእጅ ወጊያ መማረክና ማሸነፍ የምትችሉ መሆኑን ለመግለፅ እወዳለሁ።
ሌላው ለደፈጣ ወይም ለሸምቅ ውጊያ በቀላሉ ሊተኮሱ እና ኪሳራ የሚያሰከትልሉ መከላከያ የታጠቃቸው ትጥቆች ዝርዝር፦
1,ዙ 23 ባለ ሁለት አፈሙዝ
2, ነጥብ አሰራ አራት
3,ብሬን
4, ዲሸቃ
5, እሰናይፐር እና ክላሸ እንኮፍ መሳሪያ ናቸው። ስለሆነም ከላይ የጠቀሰኳቸውን ትጥቆች ይዞ የሚዋጋ ሰራዊት ካጋጠማቹህ ወታደራዊ ሰልት በመጠቀም በጥንቃቄ ውጊያውን መምራት ያሰፈልጋል።
በመጨረሻ የመከላከያ ሰራዊት አሁናዊ ቁመና በተመለከተ
አሁን ባለው አደረጃጀት ውጊያን በአግባቡ መምራት የሚችል የአመራር ሰንሰለት የለውም። አብዛኛው በጓድ መሪና በመቶ መሪ ደረጃ ያሉ በ2013 አመት ምህረት ወደ ትግል የተቀላቀሉ አዎግተው የማያውቁ አዳዲሰ ስለሆኑ በቀላሉ የሚበተን ወይም መሳሪያ ጥሎ የሚሸሽ ኃይል ነው ያለው።
በአጭሩ አሁን ያለው ወታደር ከመቶ ዘጠና ፐርሰንቱ አዲስ ስለሆነ ችግርን መቋቋም የማይችል እና ነባር ታጋይ ወይም አመራር የሌለው ስለሆነ በቀላሉ ድል ማድረግ ስለሚቻል እርምጃቹህን አጠናክራቹህ ቀጥሉበት።
እንደ ተቋም በሚዲያ ከሚታዩት ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ውጭ ሌላው ከጁንታው ተማርኮ የተመለሰ እና አዲሰ ምልምል ስለሆነ ተረጋግቶ የመዋጋት አቅም የለውም።
ድል ለተገፋው ለአማራ ሕዝብ።
የጣናው ሞገድ ከቤተ አማራ!

06/08/2023

ቶሎ ይዳረስ
ከጭፍራ በኩል ወደ ወልደያ አቅጣጫ በርካተ የኦነግ ጦር እየተጠጋ ነው። እንግዲህ
1. ከዞብል --ቆቦ--ተኩለሽ መስመር
2. ሐራ--ወልድያ-ሳንቃ መስመር
3. በውጫሌ -ግሼን ማርያም አቅጣጫ
4. ደሴ-ኩታበር- ደላንታ መስመር ጥብቅ ክትትል እንዲደረግ

06/08/2023

መጣንልሽ!
የአባቶቻችን ከተማ! የኢትዮጵያዊያን ከተማ-አዲስ አበባ!
መጣንልሽ!

06/08/2023

ሰበር ዜና!!!
የባህርዳር ከንቲባ ቤት በፋኖ ቁጥጥር ስር ውሏል፤ ጠባቂዎችም ተይዘዋል።

"ዘመቻ አዲስ አበባ" ግርማ ካሳ የአዲስ አበባ ህዝብ ለፋኖ ትልቅ አቀባበል ለማድረግ እየተዘጋጀ ነው::  አዲስ አበባ አቅራቢ ያሉ፣ ደብረ ብርሃን፣ ዓለም ከተማ፣ ምንጃር አረርቲ ከብልፅግና ...
06/08/2023

"ዘመቻ አዲስ አበባ" ግርማ ካሳ
የአዲስ አበባ ህዝብ ለፋኖ ትልቅ አቀባበል ለማድረግ እየተዘጋጀ ነው:: አዲስ አበባ አቅራቢ ያሉ፣ ደብረ ብርሃን፣ ዓለም ከተማ፣ ምንጃር አረርቲ ከብልፅግና አጋንንት ነፃ ወጥተዋል፡፡
በአዲስ አበባና በደብረ ብርሃን መከከል በምትገኘው ሸኖ፣ የቂቤ አገርማ በአለልቱ የነበሩ የብልፅግና ወታደሮች ጥለው ወደ አዲስ አበባ እየገቡ ነው፡፡
የአማራ ኃይሎች በሶስት አቅጣጫ ነው ፊታቸውን ወደ አዲስ አበባ እያደረጉ ያሉት፡፡ አንደኛው በጣም እየፈጠ ያለው፣ በደብረ ብርሃኑ ለገጣፎ ባለው መስመር ነው፡፡ ሸኖና አለለቱ በሰዓታት ውስጥበፋኖ እጅ ይሆናሉ ተብሎ ነው የሚጠበቀው፡፡ በተለይም የፋኖዎች እንቅስቃሴ ከደጋማ፣ ከፍተኛ ቦታዎች ዝቅ ወዳሉ ቦታዎች በመሆኑ፣የመከላከያ ጦር አባላትን ጥለው እየሄዱ በመሆናቸው በዚህ እስመር አዲስ አበባ ለመግባት ብዙ አስቸጋሪ አይሆንም ነው እየተባለ ያለው፡፡
ሁለተኛው ከዓለም ከተማ በመቂ ጡሪ አድርጎ ወደ ጫንጮ፣ ሱሉልታ በሚወስደው መስመር ነው፡፡ አገዛዙ ከመቂጡሩ ወደ ፍቼ በሚወስደው መንገድ፣ ወደ ደጀን ከፍተኛ ጦር ልኮ ነበር፡፡ ያ ጦር በጎጃም እየተደመሰሰ ባለበት ነው፣ በቆረጣ በዓለምከተማ በኩል የአዲስ አበባ ጎጃም መንገድ ለመቆጣጠር፣ በሱሉልታም በኩል አዲስ አበባ ለመግባት ፋኖዎች እየተንቀሳቀሱ ያሉት፡፡
ሶስተኛው በምን ጃር አረርቲ በኩል ነው፤፡ በዚህ መስመር የሚደረግ እንቅሳሴ። ሙሉ ለሙሉ ከአዲስ አበባ ወደ ጅቡቲ የሚወስደውን መንገድ የሚዘጋ ነው፡፡ በሞጆ በኩል ከደቡብ አቅጣጫ ደብረ ዘይትንና አዲስ አበባ ለመቆጣጠር የሚያስችል ነው፡፡
በነዚህ በሶስቱም አቅጣጫዎች እየገሰገሰ ያለው የፋኖ ኃይል በአካባቢ ነዋሪዎች እጅግ በጣም ከፍተኛ ድጋፍ ነው ያለው፡፡ በሸኖ፣ በአለልቱ፣ ሰንዳፋ፣ መኪጡሬ፣ ሞጆ፣ ደብረ ዘይት ወዘተ ፣ በኦሮሞማ ኃይሎች ኦሮሞ ያልሆኑ የኦሮሙማ አፓርታይዳዊ አገዛዝ የመረራቸው ማሀብረሰባት ማጆሪቲ የሆኑባቸው አካባቢዎች ናቸው፡፡ በዚያ ያሉ ኦሮሞዎችም ቢሆን የኦህዴድን ዱላ የቀመሱ በአገዛዙ የተማረሩ ናቸው፡፡
ምን አለፋችሁ በቀናት ውስጥ አዲስ አበባ የአማራ ኃይሎች ሊገቡ ይችላሉ፡፡ እነ ሺመለስ አብዲሳ ፣ አዳነች አበቤ የት እንደሚሄዱ የምናየው ይሆናል፡፡ አብይ አህመድ እንኳን ቤተሰቡን ወደ አሜሪካ እነንደላከ እየተሰማ ነው፡፡ እርሱም ወደ ወዳጁ የአቡዳቢ ገዢ ይሸሻል ተብሎ ነው የሚጠበቀው፡፡
ሐምሌ 30 ቀን 2015 ዓ.ም

05/08/2023

"በመጨረሻም ላንጨርስ የጀመርነው ትግል የለምና እንኳን በእናንተ ተራ መግለጫ በያዛችሁት ግዙፍ ሰራዊት የሚበረግግ ትንሽ ልብ የለንምና ህዝብን ከማሸበር ስራ ብትወጡ ለማለት እንወዳለን።"
እነ ኮለኔል ፈንታው ሙሃቤና ኮለኔል ሞገስ ዘገየ
አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ
ሀምሌ 29/2015 ዓ/ም_አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
ከኮለኔል ፈንታው ሙሃቤና ከኮለኔል ሞገስ ዘገየ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የተሰጠ አስቸኳይ መግለጫ‼
እንደሚታወቀው ትዕግስታችን ሆደ ሰፊነታችንና ሃገር ወዳድነታችን እንደ ፍርሃት ተቆጥሮ እኛን መጨፍጨፉና ማፈናቀሉ የዕለት ተዕለት ቀላሉ የአበል ስራቸው መሆኑ አልበቃ ብሏቸው በተደጋጋሚ ክልላችንን ሆን ብለው የጦርነት ቀጠና በማድረግ አራሹና መጋቢውን ህዝባችን የሩዝና የዱቄት ተመፅዋችና የሰው እጅ ጠባቂ እንዲሆን ማድረጋቸው አንሷቸው ዛሬም አዲስ ስልት በመንደፍ ህዝባችንን የከፋና ህጋዊ ደሃ ለማድረግ የፌዴራል መንግስቱና የክልሉ መንግስት ተጣምረው በጋራ እየተናበቡ በመስራት ላይ ይገኛሉ።
አሁን ባለው ወቅታዊ ሁኔታና የትግል ምዕራፍ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ድንጋጌ የሚመጣ አንዳችም ሰላም የለም። ምናልባት የከፋ ደህንነትና ስራ አጥነት እንጂ።
እንደሚታወቀው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በሚጣልባቸው ስፍራዎች ላይ ቱሪስትም ሆነ ባለሃብቶች ወደዚያ ስፍራ አቅንተው ጉብኝትም ሆነ አዳዲስ ኢንቨስትመንቶችን እንዳያደርጉ ይገደዳሉ።
ይህ ሆነ ማለት በኦሮሚያ ክልል ሰፍኖ በነበረ የጸጥታ ስጋት ቆሞ የነበረውን የቱሪስትና የኢንቨስትመንት ፍሰት ዳግም እንዲያብብና የእኛ እንዲቀጭጭ በር ከፋች የሆነ ሆን ተብሎ ታስቦበት በስሌት የተሰራ የከፋ ውሳኔ ነው። ስለሆነም አጥብቀን እንታገላለን እንጂ በመግልጫ የሚቆም ተራ ትግል አልጀመርንም።
ለመከላከያ ሰራዊታችን ደጀን ለሃገር ካስማ የሆነው ህዝባችን ሳያሳዝናቸው አዝመራውን መዝራት ባለበት ወቅት እንዳይዘረና ነገ በረሃብ እንዲያለቅ ሆን ብለው በማሰብ ማዳበሪያ ጭምር ሲከለክሉት የከረሙትን አርሶ አደሩ ህዝባችንን ዛሬ ጥያቄያችን ይሰማ ባለና የህልውና አደጋችንን መንግስት እስኪያረጋግጥለንና እንዲሁም ገዳዮቻችን እሰኪሰንፉና አቅማቸው ተሟጦ ሳይዳከም ትጥቅ አንፈታም በማለታችን ብቻ ተጨማሪ ምክንያት በመፈለግ ዳግም ክልላችንን ከኢኮኖሚ ተጠቃሚነቱና ከሰላሙ ሊያርቀው የሚችል አዋጅ በማወጅ ኢ-ዴሞክራሲ የሆነ ውሳኔ መወሰንና በመግለጫ ማውጣታቸው ይታወቃል።
ስለሆነም ህዝባችን የታቀደለትን በሲስተም አደህይቶ የማስገበር ሴራ ቀድሞ በማውቅ የጀመረውን ሁሉን አቀፍ ህዝባዊ ትግል አጠንክሮ በመቀጠል የታቀደለትን ሴራ በጣጥሶ እንደሚወጣና ዳግም ሰላሙን በአጭር ጊዜ በክንዱ አረጋግጦ ወደ ነበረበት ሰላም እንደሚመለስ በፅኑ እናምናለን።
ማሳሰቢያ:-
▪1ኛ...በተቆጣጠርናቸውና ወደፊትም በምንቆጣጠራቸው ከተሞች ላይ ተሸናፊውና ተስፋ የቆረጠው የቀድሞው ስርዓት ጣር ላይ ስለሚገኝ በመንፈራገጥ ብዙ ውድመቶች ሊያስከትል ስለሚችሉ የጣሩንም የግነዛውንም የቀብሩንም ሂደት በጥንቃቄ ማድረግ ይጠበቅብናል።
▪2ኛ...ከተሞችን በመቆጣጠር ሂደት ውስጥ ተመሳስሎ መዝረፍም ሆነ ከማህበረሰቡ ሊለየን የሚችልን ማንኛውንም ጥፋት መፈፀም እስከ ወዲያኛው የሚያሸኝ አጸያፊ ተግባር መሆኑ እንዲታወቅ ማሳወቅ እንፈልጋለን።
▪3ኛ...በመንግሥት የጸጥታ ተቋም ውስጥ ማለትም በፖሊስ በሚሊሻና በመከላከያ ተቋም ውስጥ የምታገለገሉ አባሎችን ይፋዊ የትግል ጥሪያችንን ተቀብላችሁ እንድትቀላቀሉን ዛሬም ጥሪያችንን እናቀርባለን።
▪4ኛ...ህዝባችን በጀመረው መራር የህልውና ትግል ምክኒያት ለዚህ እንደተዳረገ ለማስመሰል የሚደረግን ለካድሬ ሸፍጥ ጆሮ ባለመስጠት ወደ ፊት ፀንቶ በመታገል ራሱንና ህዝቡን ነፃ እንዲያወጣና እስካሁን ከሆነው በላይ የሚሆነውም የሚደርስበትም አንዳች መከራ የለምና በተራ መግለጫ እንዳይደናገጥና የጀመረውን ትግል አጠናክሮ እንዲቀጥል አበክረን እናሳስባለን።
▪5ኛ...በሁሉም አቅጣጫ ያለ ፋኖ ከእንግዲህ ለሚኖረን መራር የህልውና ትግል ለዘመቻው ስያሜ እየሰጠን የራሳችንን ታሪክ በደማችን እየጻፍን የምንሄድበት ቁመና ላይ መድረሳችንን እናበስራለን።
▪6ኛ...ከመቼውም ጊዜ በላይ እያሳየን ያለነውን የመነጋገር የመደማመጥና የመከባበር ፍቃደኝነታችንን ከዚህ በላይ አጠናክረን እንድንቀጥል በታላቁ ህዘባችን ስም እንለምናለን አደራም ማለት እንወዳለን።
በመጨረሻም ላንጨርስ የጀመርነው ትግል የለምና እንኳን በእናንተ ተራ መግለጫ በያዛችሁት ግዙፍ ሰራዊት የሚበረግግ ትንሽ ልብ የለንምና ህዝብን ከማሸበር ስራ ብትወጡ ለማለት እንወዳለን።
ቅዳሜ 29/12/2015 ዓም
ጋሸና ሰሜን ወሎ ዞን

31/05/2023

That moment you realize leaving eternally is the merely way to serenity🙌

02/03/2023

ቤተ-መንግስት ያለው ስብስብ ጠላት ነው-
ጥቁር ጣልያን! "ጣልያን" ደግሞ ተጠርጎ መውደቅ ነው ያለበት::

05/02/2023

⛪️ 💒 ⛪️
መንግስት ቤተ-ክስቲያን ድረስ ከመጣ እኛም ቤተ-መንግስት ድረስ እንሄዳለን!
ለመስዋትነት የፀናችሁ እና የታመናችሁ ሁኑ!
✝️ ✝️ ✝️

03/12/2022

አይ አማራ!

81 + 47 በአንድ ጀንበር የተረሸኑ
***************************
ተጠርጥራችኋል ተብለው በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ትዕዛዝ በክልሉ ልዩ ኃይል ታፍሰው በእስር ቤት እንዲቆዩ ከተደረጉት የአማራ ተወላጆች መካከል ከስር ስማቸው የተዘረዘሩትን ሕዳር 19/2015 ለህዳር 20 ከእስር ቤት አውጥተው ረሽነዋቸዋል።

1ኛ. ኡመር አሊ
2ኛ. ወርቂት ሙሀመድ
3ኛ. መዲና ከማል
4ኛ. አህመድ ከማል
5ኛ. ጦይብ ከማል
6ኛ. ሼህ ከማል በድሩ
7ኛ. ኢብራሂም አሊ
8ኛ. ሙሀመድ አሊ
9ኛ. ታጁ መሀመድ
10ኛ. ሙሀመድ ዳውድ
11ኛ አስናቀው እባቡ
12ኛ. ተመስገን መልክ ነው
13ኛ. ሳኒ ከማል
14ኛ. መሀመድ ከማል
15ኛ አህመድ ከማል
16ኛ. ዚነት ሰይድ
17ኛ. ሰሚራ ሰይድ
18ኛ. ሽኩር ሙሀመድ
19ኛ. ፋጢማ ጅብሪላ
20ኛ. አስናቀው ካሳው
21ኛ. ዩኑስ ሙሀመድ
22ኛ. ኡመር ሙሀመድ
23ኛ. ጥላሁን ዘነበ
24ኛ. ኢስማኤል ደሳለኝ

ከዚህ በታች ያሉት ደግሞ ከነ ቤተሰቦቻቸው የተረሸኑ ሲሆኑ፦

1ኛ. ጀማል ዳምጤ እሱን ጨምሮ 5 የቤተሰብ አባላቱ
2ኛ. አበባው መኮነን እሱን ጨምሮ 6 የቤተሰብ አባላቱ
3ኛ. ሼህ ሙሳ የሱፍ እሱን ጨምሮ 5 የቤተሰብ አባላቱ
4ኛ. ቃሲም ሲራጅ እሱን ጨምሮ 3 የቤተሰብ አባላቱ
5ኛ. ከማል ፈድሉ ከነ ባለቤቱ ቤተሰቦች ጨምሮ 21
የቤተሰብ አባላቱ
6ኛ. ሙሳ አሊ እሱን ጨምሮ 7 የቤተሰብ አባላቱ
7ኛ. አሊ ሀሰን እሱን ጨምሮ 10 የቤተሰብ አባላቱ ናቸው።
እነዚህ በእስር ላይ እንዳሉ የተረሸኑት 81. ሰዎች
የክልሉ ፀጥታ ኃይሎች ሕዳር 9 እና ህዳር 20/2015
ዓ/ም ቤት ለቤት እየዞሩ ከገደሏቸው 47 የአማራ
ተወላጆች ተጨማሪ መሆናቸውን ማረጋገጫ የሰጡት ከአሰቃቂው ግድያ የተረፉ የአይን እማኝ ምስክሮች ናቸው።

********
ዛሬ ማለዳ 11:30 የጀመረው የጉትን ወረዳ … ዘግናኙ አማራን የመጨፍጨፍ የዘር ማፅዳት ወንጀል እንደቀጠለ ነው። እልቂቱን ለመሸፋፈን የእርስ በእርስ ግጭት እንዳለ ለማስመሰል እነ ጃዋር ጭምር እየጻፉ ይገኛሉ። አማራውን በሰቅጣጭ ሁኔታ ከጨፈ በኋላ መሰል ማደናገሪያ በማንሳት ለማዳፈን የመሞከር ስልት ዐብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጣ ጀምሮ እንደ ስልት የተያዘና የቀጠለ ሆኗል።

@ሀብታሙ አያሌው

23/11/2022

ቤተ-አማራ ክልል
"የወሎ" ሰው አማራ አይደለም:: ስለዚህ የኦሮሞ ሰራዊት ቢፈጨው ቢጋግረው የ"አማራ" ክልል መንግስት አይመለከተውም::

ትላንት የኦነግ ኡስታዞች ነበሩ "ወሎ" የሚባል ክልል እንድንሆን ሲጋብዙን የነበሩት:: በተደጋጋሚ የአማራ "ክልል" የወሎን አማራ ገፍቶታል:: ስለዚህ በቃ! የ"ወሎ" አማራ ሞት መቆም ስላለበት የራሱን የቤተ-አማራ አስተዳደር መመስረት አለበት::

ይሄን ደግሞ ነገ ሌላው አማራ ሲወጋ ዝም ብለን የምናይ የሚመስለው እና የራሳችንን ወገን ዙረን የምንወጋ የሚመስለው የትግሬው እባብም ኦነጉም እንደሚደግፈን እናውቃለን::

13/10/2022

12ሺ+ ተማሪዎች ህይወት እንዴት ነው?

1. ከመቅደላ አምባ ዩኒቨርስቲ: 1700 ተማሪ
2. ከደ/ማርቆስ ዩኒቨርስቲ: 1,226 ተማሪዎች
3. ከባ/ር ዩኒቨርስቲ: 2,711 ተማሪዎች
4. ከደ/ታቦር ዩኒቨርስቲ: 7,150 ተማሪዎች

በአጠቃላይ 12,787 ተማሪዎች ፈተና አልተፈተኑም። ከዚህ በተጨማሪ በደብረ ታቦር ዩንቨርስቲ የሞቱና የተደፈሩ ሴት ተማሪዎች እንዳሉም ታውቋል።

ፍ/ቤቱ  በእነ ጎበዜ ሲሳይ አሳዬ ደርቤና መዓዛ መሀመድ ጉዳይ ትዕዛዝ ሰጠ። የፊደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ወንጀል ምድብ ችሎት ዛሬ ለፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ በጻፈው ደብዳቤ ...
12/10/2022

ፍ/ቤቱ በእነ ጎበዜ ሲሳይ አሳዬ ደርቤና መዓዛ መሀመድ ጉዳይ ትዕዛዝ ሰጠ።

የፊደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ወንጀል ምድብ ችሎት ዛሬ ለፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ በጻፈው ደብዳቤ ጋዜጠኛ መዓዛ መሃመድን ፣ አሳዬ ደርቤንና ጎበዜ ሲሳይን የፍርድ ቤቱን ትእዛዝ ተፈጻሚ በማድረግ ከእስር እንዲፈታ አዟል፡፡
አሊያም የማልፈታበት ምክንያት አለኝ ካለ ነገ ጥቅምት 3/2015 ዓ.ም ጠዋት 3፡30 ችሎት ቀርቦ እንዲያስረዳ ትእዛዝ አስተላልፏል፡፡
ባሳለፍነው አርብ መስከረም 27/2015 ዓ.ም የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ በ20 ሺህ ብር እንዲሁም ጋዜጠኛ መዓዛ መሃመድና አሳየ ደርቤ በ10 ሺህ ብር የገንዘብ ዋስትና ከእስር እንዲወጡ ማዘዙ ይታወሳል፡፡

ሂድ እንግዲህ! 😀😁😎
13/07/2022

ሂድ እንግዲህ! 😀😁😎

24/06/2022

ሊታወቅ የሚገባው መረጃ ከጋዜጠኛ ገነት አስማማው! 👇

"የሰው ዘር የተባለ ሁሉ ይህንን ይስማልን"

"የቀበሌው አስተዳዳሪ እኮ ከላይ በተላለፈልኝ ትዕዛዝ ጭፍጨፋውን አስፈጽሜያለሁ አለ ወላሂ" - የቶሌ ቀበሌ ነዋሪ

የቶሌ ቀበሌ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ንጋቱ ኡመታ እና የቀበሌዋ ሚሊሻ ጽ/ቤት ሃላፊ ኪዳኔ ወርዋ በሃገር መከላከያ ሰራዊት በቁጥጥር ስር ከዋሉ በአራተኛ ቀናቸው ዛሬ በቶሌ ቀበሌ ስለተፈጸመው ጭፍጨፋ እውነታውን በህዝብ ፊት ተናዘዋል

የቀበሌዋ አስተዳዳሪ አቶ ንጋቱ ኡመታ ኑዛዜያቸውን ሲናገሩ የጊምቢ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ባጫ እና የወረዳው ሰላም እና ጸጥታ ጽ/ቤት ሃላፊ በስልክ ደውለው ከላይ የተላለፈ ትዕዛዝ አለ አስፈጽም አሉኝ፡፡

ሰራዊታችን( ኦነግ ሸኔን) ቅዳሜ የሚያካሂደው ኦፕሬሽን አለ ብለው አስፈላጊውን ትብብር እንዳደርግ ነግረውኛል ብሏል አቶ ንጋቱ፡፡

አቶ ንጋቱ እንደሚሉት አቶ ባጫ እና የጸጥታ ሃይሉ ሃላፊ፤ ሰራዊቱ ቶሌ ቀበሌ ሃሙስ ማታ እንደሚገባ፤እኔ፤አቶ ኪዳነ መርዋ እና ሳጂን አሰፋ የፖሊስ አባላቱን እና የሚሊሻ አባላቱን ከቶሌ ቀበሌ ሃሙስ ዕለት እንድናስወጣቸው አዘዙን ብሏል፡፡

ሰራዊቱ ወደ ቶሌ ቀበሌ ሲገባም ሰንጋ እንዲታረድለትም ታዘናል የሚሉት አቶ ንጋቱ የተባልነውን አድርገናል ብለዋል፡፡

የጸጥታ ሃይሉን ጨምሮ የቶሌ ቀበሌ ዋና ዋና አመራሮች ሃሙስ ዕለት ቀበሌዋን ለቀው እንዳደሩ የተናገሩት አቶ ንጋቱ ከቀበሌዋ በቅርብ ርቀት ሂደው ማደራቸውን ገልጠዋል፡፡

ሰራዊቱ ሃሙስ ማታ ከገባ በኋላ በቀበሌዋ የተጣለለትን ሰንጋ እየተመገበ ሲጨፍር እንዳደረ ተናግረዋል፡፡

አርብ ዕለት ቀበሌዋ ምንም አይነት የመንግስት መዋቅር ቀበሌ ሆነች የሚሉት አቶ ንጋቱ አርብ ቀኑን ሙሉ የቶሌ ቀበሌ ሰፊ በመሆኑ እኛም ራሳችንን ቀይረን ከቀበሌው አንድም ሰው እንዳይወጣ ከሰራዊቱ ጋር ከበባ አደረግን ይላሉ፡፡

የጊምቢ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ባጫ እና ሰላም እና ጸጥታ ሃላፊው እያንዳንዱን እንቅስቃሴ ይከታተሉ ነበር የሚሉት አቶ ንጋቱ አርብ ዕለት ደውለውልኝ ቅዳሜ ከጠዋቱ ሁለት ጭፍጨፋው እንደሚጀመር እና ስምንት ሰአት ውስጥ እንደሚያልቅ ትዕዛዝ አስተላልፈውልኛል ብለዋል፡፡

የወረዳ አመራሮቹ ሲደውሉልኝ ሌሎች አመራሮችም ከጎኔ ነበሩ እንደ እኔ ራሳቸውን ቀይረው ከሰራዊቱ ጋር ተሰልፈዋል ብለዋል፡፡

አቶ ባጫ ቅዳሜ ተዋት ሁለት ሰአት ይጀመራል ባሉት መሰረት ጭፍጨፋውን እና ዝርፊያውን ጀመርን እስከ ስምንት ሰአትም ቆየን ብለዋል አቶ ንጋቱ

ጥቂት አማራዎች አልሞት ባይ ተጋዳይነታቸውን ሲያደርጉ የሰራዊታችን አባላት ሲመቱ ከወረዳ አምቡላንስ ተልኮልን፤የሰራዊታችንን ቁስለኞች ወደ ጊምቢ ሆስፒታል ስታመላልስ ዋለች አምቢላንስ ነበረች ያሉት አቶ ንጋቱ ኡመታ ከቀኑ ስምንት ሰአት ሲሆን በቃችሁ የመከላከያ ሰራዊት ወደ ጊምቢ እየመጣ ነው የሚል ትዕዛዝ ተላልፎልን ተመልሰን ከሰራዊታችን ጋር ወደ ጫካ ሄድን፤ከዚያም እኔ እና ባልደረቦቸ መሳሪያችንን እና ልብሳችንን ቀይረን ወደ ቶሌ ቀበሌ ሰላማዊ መስለን መጣን ሲሉ ለሃገር መከላከያ ሰራዊት አባላት ህዝብ በተሰበሰበበት ተናዘዋል፡፡

የቶሌ ቀበሌ የሚሊሻ ጽ/ቡት ሃላፊ አቶ ኪዳነ መርዋም በተመሳሳይ የቶሌ ቀበሌ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ንጋቱ ኡመታ የሰጡትን መረጃ ተናግረዋል፡፡

ከጭፍጨፋው የተረፉት የአማራ ተወላጆች ይህንን ከሰሙ በኋላ በከፍተኛ ዋይታ እና ጩሀት ውስጥ እንደነበሩ የአካባቢው የአይን እማኝ ነግሮኛል
አሁን ላይ የሃገር መከላከያ ሰራዊት እና የኦሮሚያ ልዩ ሃይል በአካባቢው መኖሩን የገለጡት ነዋሪው ገዳዮቹን መከላከያ በቁጥጥር ስር ሲያውላቸው የኦሮሚያ ልዩ ሃይል አባላት እየተቃወሙ ነው ብለዋል፡፡

‘’ጨፍጫፊዎች ሲያዙ ፤ ልዩ ሃይሎቹ ያለቅሳሉ ይቆረቁራሉ የሚያዝኑት ለእነሱ ነው ለእኛ አይደለም ‘’ ሲሉ ገልጸውታል

መከላከያው ከልዩ ሃይሉም ጋር ተፋጧል የሚሉት የአይን እማኙ ጫካ የገባውም ሁነ ያልገባው አንድ ናቸው ሲሉ ይገልጻሉ፡፡

ከጭፍጨፋ የተረፈው ሜዳ ላይ ነው ያለው፤የሚልሰው የሚቀምሰው የለም የሚሉት ነዋሪው ለመሳፈሪያ ገንዘብ ያለው አማራ በመኪና እንኳን ተሳፍሮ እንዳይሄድ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡት ሹፌሮቹ ሁሉ አኩርፈዋል አድመውብናል ብለዋል።

ከቶሌ ቀበሌ ሸሽተው በአጎራባች ግንቢ አቅራቢያ የተፈናቀሉ 3ሺ የሚደርሱ አማራዎች በለቻቸው ብር እንኳን ገዝተው እንዳይመገቡ ብራቸውን ከፍለው እንኳን የሚሸጥላቸው ነጋዴ አላገኙም ስቃይ ላይ ናቸው ብለዋል፡፡

አማራ እዚህ መኖር የለበትም መልሰን ስንመጣ እንዳናገኛችሁ ተብለናል የሚሉት የአካባቢው ነዋሪ፣ የተረፍነውን አዲስ አበባ ድረስ እንኳን የሚወስደን እና እሩሃችንን የሚታደገን ወገን ይድረስልን፤ ድምጻችንን አሰሙልን ሲሉ ተማጽነዋል።

ዛሬም ድረስ አስከሬን እየተቀበረ እንደሆነ የሚናገሩት ነዋሪው፤ እኔ ራሴ እንኳን የ20 ቀን ህጻናትን ጨምሮ 19 ህጻናት ከተቃጠሉበት እና ታርደው ከተጣሉበት፤በጥይት ተመተው ከወደቁበት አንስቸ 20 ህጻናትን ጉድጓድ ቆፍሬ አንድ ላይ ቀብሬያለሁ ብለዋል፡፡ በቶሌ ጉትን ቀበሌ ብቻ ከአስር ሺ የማያንስ ጠቅላላ ብሬል እና መትረየስ የታጠቀ ሰራዊት ነው የጨፈጨፈን ብለዋል ነዋሪው።

ሼር ይደረግ፣ ብዙዎች ጋ ይድረስ!

23/06/2022



ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም  ወእጨጌ ዘመንበረ  ተክለሃይማኖት; በወለጋና በጋምቤላ የአገራችን ክፍል የደረሰውን አሰቃቂ...
23/06/2022

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት; በወለጋና በጋምቤላ የአገራችን ክፍል የደረሰውን አሰቃቂ የወገኖቻችን ግድያ አስመልክቶ ያስተላለፉት የኀዘን መልዕክት
+++++++++++++++++++++++++++++++++++++
በስመ አብ ወወልድ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
"ወተዘርወ ዕንቊ ቅዱስ ውስተ ኩሉ ፍኖት
“የመቅደሱ ድንጋዮች በጐዳና ሁሉ ራስ ተበተኑ። ሰቆቃ.ኤር. 4፡1
አባታዊ የኀዘን መልእክት
የተወደዳችሁ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት በአገር ውስጥ እና በውጭ ያላችሁ የአገርን ክብር ለመጠበቅ በዳር ድንበር ያላችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን፤ ዘመናትን ፈጥሮ በሚገዛ፣ ዓለማትን በቃሉ በሚያስተዳድር፣ ለህላዌው መታጣት፣ ለጌትነቱ ዳርቻ በሌለው በሕያው እግዚአብሔር ስም አባታዊ ሰላምታችንን እናስተላልፋለን።
ስሜትን በሚወርር፣ ልብን በሚያሳዝን፣ ጉልበትን በሚሰብር ኀዘን ውስጥ ላሉት ወገኖቻችን፤ ትናንት ባለ ብዙ ቤተሰብ ዛሬ ሌጣ ለሆኑት፣ የክብር ሞትና መቃብር ለተነፈጉት፣ ሰው ሆነው በሰው ለተገፉት፣ ኢትዮጵያዊ ሁነው በኢትዮጵያውያን ለተሠዉት፣ አገር : ሳላቸው እንደ ባዕድ ለተቆጠሩት ለደከሙበት ምድር : በወርቅ ፈንታ ሰይፍ ለተከፈሉት ልጆቻችን እግዚአብሔር ያጽናችሁ በማለት፣ የሞቱትንም ደመ አቤልን ያከበረ አምላክ ደማቸውን እንዲመራመር በመለመን መልእክታችንን እንጀምራለን!
ብዙ መልካም ቃላት በሚነገሩበት፣ የጥበብ ድምፆች በሚያስተጋቡበት፣ መሠረት ፈርሶ ለጉልላት ጌጥ በምንጨነቅበት በዚህ ዘመን፣ “እንዴት ካለው ጊዜ ደረስን ማለት መመጻደቅ ባይሆን ኖሮ የሚባልበት ወቅት ሁኖ አግኝተነዋል። ትናንት ገንዘብን የሚቀሙ “እንዴት የሰውን ልፋት ይወስዳሉም ተብለው በተወገዙበት ምድር ሕይወትን የሚቀሙ፡ የሰው ዘር ቅነሳ የሚያደርጉ ግፈኞች ሲንጎማለሉ ማየት ያሳዝናል። ንጹሐን ወገኖቻችን እግዚአብሔር በሰጣቸው ማንነት ብቻ ሲሞቱ ስናይ የዝቅታችንና የመውደቃችን ልክ ማጣት ጎልቶ ይታያል። በርግጥ የሞቱት ወገኖቻችን ሰማዕታት ናቸውና ቤተ ክርስቲያን ትዘክራቸዋለች። ሰማዕት ስለ እግዚአብሔር ብሎ የሚሞት ነው። እነዚህም ወገኖቻችን እግዚአብሔር በሰጣቸው ማንነት፣ ለምን እንዲህ ተፈጠራችሁ ተብለው የሞቱ ናቸውና ሰማዕታት እንላቸዋለን። ገዳዮችም ቀጥተኛ የእግዚአብሔር ተቃዋሚዎች ናቸው።
በወለጋና በጋምቤላ የአገራችን ክፍል የደረሰውን አሰቃቂ የወገኖቻችን ግድያ ስሰማ እንደ ወትሮው ልቤ በታላቅ ኀዘን ተመትቷል። በመላው የሀገራችን ክፍልም ክረምቱ ዓመት ከዓመት፣ ጠሉም የንጹሐን እንባ ሁኖ፣ “ሽሽታችሁ በክረምት እንዳይሆን ጸልዩ" ያለው የጌታችን ቃል ደርሶ እያየን ነው። ጆሮ ከአቅሙ በላይ በሚሰማበት በዚህ ዘመን ያላችሁ ልጆቻችን አሁንም ልባችሁን እንደ ነቢዩ ዳዊት በእግዚአብሔር አበርቱ። ጠብና ክርክሩ እግዚኣብሔር ከፈጠረው ሰውነት ጋር ነውና እግዚአብሔር ፍርድ እንደሚሰጥ እናምናለን። የሃይማኖት አባቶችም የምናስተምረው ሕዝብ አልቆ ማንን ልናስተምር መሆኑን ደግመን ማሰብ ያስፈልገናል። አገራችን ኢትዮጵያ የሚያስከብሯትን መሪዎች አሁንም እየተጣራች ነውና መንግሥትና ሕዝብ ግፍን በተግባር ማውገዝ ያስፈልጋቸዋል። ነቢዩ ኤርምያስ በኀዘን ልቅሶው - የመቅደሱ ድንጋዮች በጐዳና ሁሉ ራስ ተበተኑ። ብሏል ሰቆቃ ኤር 4፡1። የሰው ልጅ ሕያው የእግዚአብሔር መቅደስ ነውና በየስፍራው ሲገደልና ቀባሪ ሲያጣ ስናይ ከነቢዩ ጋር ለማልቀስ እንገደዳለን።
ጊዜው እየረፈደ፣ ሞትም ዜና እየሆነ፣ ዜጋም ክብሩን እያጣ ስጋትም ገዥ እየሆነ የምንቀጥልበት ጊዜ እንዲያበቃም ታላቅ ጥሪያችንን በሕያው እግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን!
እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ ! ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን! ሰኔ 16 ቀን 2014 ዓ.ም.

23/06/2022

አማራና ወሎዬ፣
ከ1983 ዓ.ም ወዲህ ያለው ጊዜ፣ ለአማራው ማህበረሰብ "ዘመነ-ፍዳ" ነው ማለት ይቻላል። በአማራው ላይ የተፈፀመውን/የደረሰበትን ግፍና በደል ከቶም ዘርዝሮ መጨረስ አይቻልም። በርግጥ በአማራ ሥም የበለጠ ዋጋ ከፋዩ ወሎዬ መሆኑ ግልፅ ነው። ለምን ቢባል፣ ወሎዬው በሥራና በሰፈራ ምክንያት በኦሮሚያና በሌሎች ክልሎች በብዛት ተበትኖ ስለሚኖር ነው። ወሎዬው የሚገደለው ግን "አማራ" ተብሎ መሆኑ ሊሰመርበት ይገባል። ወሎ "ኦሮሞ" ነው የሚሉት ግዛቱን ለመጠቅለል ብቻ ነው። እነዚህ ኃይሎች ግዛቱን የመጠቅለል ዕድሉ ቢቀናቸው አማርኛ ተናጋሪውን በግዛቱ (በወሎ ምድር) መጨፍጨፍና መፍጀታቸው አይቀሬ ነው።
እስካሁን እንዳየነው፣ በሥሙ ከመነገድ ባለፈ፣ ወሎን ከጅምላ ጭፍጨፋ የታደገው የለም። እደግመዋለሁ፤ ወሎዬው በጅምላ የሚጨፈጨፈው "አማራ" ተብሎ ነው። በፓርላማው ለወሎዬው ሲጮሁና ሽንጣቸውን ገትረው ሲከራከሩ ያየነው የአማራ ተወካዮችን ነው። የነታገሰ ጫፎን ጭካኔና ንቀትማ እንደዋዛ አይተነዋል። የህዝባችን በጅምላ መጨፍጨፍ ከመጤፍም አልቆጠሩት። ከዚህ ይበልጥ፣ ሌሎች "የአማራ ተወካይ" ተብዬ አሻንጉሊቶችን ዝምታ ማሰብ "ከሞታችን" እኩል ያማል።
በዚሁ አጋጣሚ፣ አንዳንድ ቅጥረኛ፣ ሆድ አደርና ባንዳ አክቲቪስቶች፣ በዚህ ሠዓት ወሎዬውን ከአማራው ለመነጠል ሲፍገመገሙ እያየን ነው። እነዚህ (በአብዛኛው) ለእስልምና ተቆርቋሪ መሳይ መሰሪዎች፣ በወሎዬው ደም መቆመር የሚፈልጉ ሰይጣኖች ናቸው። እነሱ በእስልምና ሥም የሚነግዱ የሰብኣዊነት ዝቃጮች ናቸው። እነሱ ለኢስላማዊና ሞራላዊ መርሆች ታማኞች አይደሉም። ይልቁንም ከሌሎች ጋር ተቻችሎ በመኖር በሚታወቀው የወሎ ሙስሊም ላይ የመረረ ጥላቻ እንዳላቸውና ታላላቆችን ሳይቀር በአደባባይ ሲዘረጥጡና ሲያዋርዱ እናውቃለን። የእነሱ ዓላማና ግብ ወሎዬነት የተገነባበትን እሴት ማፍረስ ነው። ወሎን ከአማራው ነጥለው ምን ሊያደርጉት እንደሚችሉ መገመት ቀላል ነው።

ስለዚህ በእኛዉ ውስጥ ያላችሁ እና በሃይማኖት የተጠለላችሁ ጆቦች እና የኦነግ ተላላኪወች ስነ ስርአት ያዙ! አንድ እጃችንን ታስረን በአንድ እጃችን ብቻ የምንታገለው ትግል አይኖርም:: ስለዚህ መጀመሪያ እናንተን ማጽዳት ይኖርብናል::

19/06/2022

NAIROBI, Kenya (AP) — Witnesses in Ethiopia said Sunday that more than 200 people, mostly ethnic Amhara, have been killed in an attack in the country’s Oromia region and are blaming a rebel group, which denies it.

19/06/2022

በወለጋ የተፈጸመው ጭፍጨፋ ሲፈጸመም የአገሪቱ የጸጥታ ምክር ቤት ተኝቶ ነበር!?
የሽሜ ጦር(ሸኔ) በአብይ አህመድ ከጀርባ እንደሚደገፍ ብ/ጄ/ል ከማል ገልቹ የሰጡትን ምስክርነት እያሰባችሁ የትላንቱን የወለጋ በአማራ ብሔር ተወላጆች ላይ የተፈጸመውን የዘር ማጥፋት ያንብቡ ሼር ያድርጉ

***********************************************

የወለጋው የሰኔ11 ቀን 2014 በአማሮች ላይ የተፈጸመ ጭፍጨፋ

ሰኔ 12-2014ዓ.ም። ወለጋ
በምዕራብ ወለጋ ዞን በቶሌ ከተማ ጉትን ሰፈር በተባለው በትናንትናው እለት ከተፈጸመው የጅምላ ግድያ ተርፈው በየጫካው የተበተነው ግማሽ ያህሉ በተደረገው ጥረት በአርጆ የመጠለያ ጣቢያ ውስጥ የሚገኝ ሲሆን በየጢሻው ገብተው እስካሁን ያልተገኙ ህጻናትን ጨምሮ በርካታ ሰዎች በመኖራቸው፤ ጥቃት ፈጽሞ ጫካ የገባው ሐይል ተጨማሪ ጥፋት እንዳያደርስ ከፍተኛ የሆነ ሐይል ከመንግሥት በኩል ያስፈልጋል።

በተጨማሪም ነቀምት ጀምሮ እስከ ጊምቢ መካከል ባለው አርጆ ጉደቱ፣ አርጆ አውራጃ፣ ቶሌ፣ ጆግር፣ አባሴና ወሎሰፈር፣ሜጢ፣ እሁድ ገበያ፣ እና እስከ ጊምቢ ከተማ ድረስ የምትገኙ ከፍተኛ ጥንቃቄ አድርጉ።
ከነቀምት እስከ አጋምሳ የምትገኙም በጽጌ 24፣ ጃርሶ፣ ኡኬ፣ መንደር 10፣ አባሙሳ፣መ.11 ጉትን፣ መንደር9;8፣ አርቁምቢ፣ ያሶ፣ ሶጌ፣ ፊጢበቆ፣ መንደር7;6;5;4 እና ዋጃ፣ ለሊ ማሪያም፣ እንዶዴ፣ ዶሮበራ፣ ሻሾበር፣ ጌድዮ፣ ቆፍቆፌ፣ ሐሮ፣ ኪረሙና አጋምሳን ጨምሮ ጃቦዶበንና በአሙሩ ወረዳ ስር የምትገኙ ሁሉ ከፍተኛ ጥንቃቄ ይደረግ።

ከቱሉጋና፣ ጫንጮ፣ ለጋዲ፣አሊጎራ፣ጫልቲ፣ ጋሌሳ ጨሩ፣አሩሲ፣ ለጋጎርፌ፣ ሎሚጫ፣ ጨቆርሳ፣ ጎርቴ፣ወባጥጭ፣ዳልጆ፣መ.21፣ ቆጨራ፣ ባታ ማሪያም፣ መድሐኒያለም፣ጉደያቢላ፣ ሐሮ ሾጤ፣ደቢስ፣ ጃርቴ ጃርዴጋ፣ ሻምቡ፣ በፊንጨዋ ና ቱሉዋዩ(አቤደንጎሮ) ወረዳ ስር የምትገኙ ሁሉ በአስቸኳይ የፀጥታ ሐይሉ በተጠንቀቅ ይቁም።
ከባኮ ነቀምት የምትገኙ ባኮትቤ 02፣ አኖ፣ ጉባሰዮ፣ አርብ ገበያ፣ ልጎ፣ አለልቱ፣ሐሙሲት፣አራተኛ፣ መርካቶ፣ ወጤ እና በሳሲጋ እና በሲቡስሬ ወረዳ ስር የምትገኙ ሁሉ በተጠንቀቅ ሁሉም በያለበት ይዘጋጅ።

ከጊምቢ እስከ አሶሳ ዳቡስ ወንዝ ድረስ ያላችሁ ነጆ፣ ቤጊ፣ አንገር ዲዲሳና ደንቢደሎ አጠቃላይ የአማራ ሰፈሮች ከፍተኛ ጥንቃቄ ይደረግ።
በመጨረሻም በትናንትናው እለት በቶሌ ከተማ በጉትን ሰፈር ሸኔ ሰዎች ገበያ በሔደበት ያለምንም ከልካይ በጅምላ የጨፈጨፏቸው ሴት፣ ህፃናት፣ አዛውንቶች እና አራስ እናቶች ቁጥር እስካሁን 250 አስክሬን ደርሷል። በዚህም በዛሬው እለት አስክሬናቸው በመሰብሰብ ላይ ሲሆን የተረፉት በአርጆ መጠለያ ጣቢያ ውስጥ የሚገኙ ሲሆን አስቸኳይ የሰብዓዊ እርዳታ እንድደርሳቸው የሚመለከተው የመንግስ አካል እና የአለም አቀፉን ማህበረሰብ አጉልዞ ጥያቄ ጥያቄ ጥሪውን እያቀረብን፤ ነብሳቸውን ላጡ ወገኖቻችን ነብሳቸው በሰላም በአፀደ ገነት እንድያሳርፍልን እየተመኘን ለሟች ቤተሰቦችና ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ደግሞ መፅናናትን እንመኛለን።
"ነብስ ይማር!"
ከአከባቢው የተገኘውን ምስክርነት መሰረት አድርጎ የተዘጋጀ

የብአዴን (የኦሮሞ አገልጋይ ባሪያወች) ወንድማችንን ነጠቁን! የእጃችሁን ዋጋ ታገኛላችሁ!
12/06/2022

የብአዴን (የኦሮሞ አገልጋይ ባሪያወች) ወንድማችንን ነጠቁን! የእጃችሁን ዋጋ ታገኛላችሁ!

ገለል በሉለት! ይለይለት! ግፋ በለው!
04/06/2022

ገለል በሉለት! ይለይለት!
ግፋ በለው!

የአማራ ልዩ ሃይል ምረቃ

04/06/2022

ዳኞችን ያስለቀሰችው ያለም ወርቅ ጀምበሩ ድንቅ ብቃት

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ቤተ-አማራ / Bete-Amhara TV posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to ቤተ-አማራ / Bete-Amhara TV:

Videos

Share


Other Media/News Companies in Addis Ababa

Show All