Ethio TECHi4

Ethio TECHi4 EthioTechI4 make an implementation of Technlogy on kids and youth for14 Disruptive future technolgy.

ለወጣቶች።
07/12/2022

ለወጣቶች።

አሁን አሁን ባደጉት ሃገራት ታዳጊዎች ጥሩ የሆነ አወንታዊ አስተሳሰብ እንዲኖራቸው የአዳጊ እምሮ(Growth mind set up) ክህሎት ስልጠና እና ልምምድ አስፈላጊነቱ እየጨመረ መጥቷል ።ቴ...
05/12/2022

አሁን አሁን ባደጉት ሃገራት ታዳጊዎች ጥሩ የሆነ አወንታዊ አስተሳሰብ እንዲኖራቸው የአዳጊ እምሮ(Growth mind set up) ክህሎት ስልጠና እና ልምምድ አስፈላጊነቱ እየጨመረ መጥቷል ።ቴክኖሎጂ በራሱ ቀን በቀን እየተለዋወጠ እና እየተቀየረ ስለሚመጣ ሰዎችም እራሳቸውን በየጊዜው እያስተካከሉ መሄድ አለበት ።ታዳጊዎች ቀን በቀን ከሚለዋወጠው ቴክኖሎጂ ጋር አብረው ለመሄድ ተቀያያሪ ልምምዶችን በማድረግ ወደፊት ከሚፈጠረው ዲጂታል ቴክኖሎጂ የቢዝነስ ሥራ ፈጠራ እና ሥራን በቴክኖሎጂ ለመሥራት የሚያስችል ትልቅ ንቃተ ህሊና እና አቅምን መፍጠር ይቻላል ታዲያ ይህን ልምምድ በታዳጊዎች ላይ እንዴት መገንባት የሚቻለው በመጀመሪያ ደረጃ የፊክስድ ማይንድ(Fixed mind set) ሴት እና የግሮዝ ማይንድ(growth mind set) ሴት ክህሎትን በመረዳት ተግባራዊ ለውጥ እንዲያመጡ ማድረግ ነው።ፊክስድ ማይንድ ሴት በአብዛኛውን ጊዜ አንድ ነገር ላይ ብቻ ቆሞ ወይም ከዚህ እውቀት ውጭ ለኔ ሌላ የለም በማለት ሁል ግዜ እሱ ብቻ አዋቂ በመሆን ሌላው እንኳን ተመሳሳይ ነገር ቢሰራ ለክ ነው ብሎ አያምንም እንደዚህ አይነት ሰዎች ለአዳዲስ ለውጥን መቋቋም ለየሱ በጣም ከባድ ከመሆኑ የተነሳ እነሱን የሚበልጡ ሰዎች እንደጠላት ስለሚቆጥሩ የማበረታትም ሆነ የማገዝ ምንም አይነት መንፈስ የላቸውም።

አጀንዳ 2063የአግሪካልቸር ኢንደስትሪ ፖርክ::United nation development goal
30/11/2022

አጀንዳ 2063
የአግሪካልቸር ኢንደስትሪ ፖርክ::
United nation development goal

30/11/2022
"Striving for digitalizing Africa with own Technolgy "
30/11/2022

"Striving for digitalizing Africa with own Technolgy "

30/11/2022

የቴክኖሎጂ ማይንድ ሴት
እንደሚታወቀው የሰው ልጅ ከብዙ ውጣውረድ እና አሰልቺ የምርምር ሂደት አሁን ወዳለንበት የዲጅታል አለም አምጥቶናል ይህ ሁሉ ሲሆን የሰው ልጆች ይቻላል የማይባለውን በመሥራት እና በመሞከር አልፈዋል ለምሳሌ እንደ ቶማስ ኤደሰን፣ማርያ ኩሬ ፣አልበርት ኢንስታይን እና በርካታ ሳይንቲስቶችን መጥቀስ ይቻላል።በዚህ ሁሉ ውጣ ውረድ እነዚህን ድንቅ ሰዎች ማንም ሲደግፋቸው አልነበረም እንዲያውም ሲገፉ እና ከየተቋሙ ሲባረሩ ነበር ይህም የሚሆነው በዘመኑ የነበሩ ሰዎች ባለ እራይ መሆን ስላቃታቸው እና ምንም ነገር የሚሆን አልመሰላቸውም ይህ ምክንያቱ የፊክስድ ወይም በአንድ የአስተሳሰብ ቋት ብቻ ስለሚያስብ የሰው ልጅ አንድ ነገር ሞክሮ ከተበላሸበት እንደውድቀት ስለሚያስብ ነው ግን በተቃራኒው አዳጊ ወይም በብዙ ቋት የአእምሮ እድገተ ውስጥ ያሉ ሰዎች አንድ ነገር ሞክረው ቢበላሽባቸው እንኳን ደግመው በመሞከር ማስተካከል እና በየጊዜው ከስተታቸው በመማር የሚለወጡ ናቸው።ትችት እና ሰርቶ መሳሳትን ያለመደ የ 21 ኛው ክፍለዘመን ሰው ውጤታማ ለመሆን ብዙ ተግዳሮቶች ሊገጥሙት ይችላል ከዚህ በኃላ ደግሞ ነገሩ እየጨመረ ስለሚመጣ ብዙ የዲጅታላይዜሽን ልምምድ ሊያስፈልገው ይችላል ለዛ ነው መንግስት ዘለቄታዊ የዲጅታል ቴክኖሎጂ የእድገት እቅድ አውጥቶ ከፖሊሲዎች ጋር ለማስታረቅ ደፋ ቀና ሲል የምናየው።አሁን አሁን ባደጉት ሃገራት ታዳጊዎች ጥሩ የሆነ አወንታዊ አስተሳሰብ እንዲኖራቸው የአዳጊ እምሮ(Growth mind set up) ክህሎት ስልጠና እና ልምምድ አስፈላጊነቱ እየጨመረ መጥቷል::

መልካም ቀን

29/11/2022
በዲጂታል ዘመን የታዳጊዎች ስራ ፈጠራጥናቶች እንደሚያሳዩት በ2025 አለማችን ያሉ ድርጅቶች ከ75% በላይ የሆነውን ስራቸውን ወደ ዲጅታል ቴክኖሎጂ እና ተመሳሳይነት ወዳላቸው የአሰራር ሲስተም...
29/11/2022

በዲጂታል ዘመን የታዳጊዎች ስራ ፈጠራ

ጥናቶች እንደሚያሳዩት በ2025 አለማችን ያሉ ድርጅቶች ከ75% በላይ የሆነውን ስራቸውን ወደ ዲጅታል ቴክኖሎጂ እና ተመሳሳይነት ወዳላቸው የአሰራር ሲስተም ስለሚቀይሩ የሰራተኛቸውም ክህሎት በዚው ልክ ማደግ አለበት ።

በተጨማሪም በዚህ የቴክኖሎጂ ጊዜ የሚገኙ ታዳጊዎች ከዛሬ አስርት አመት ከነበሩት ትውልድ ስራ ለማግኘት እጅጉን ሊቸገሩ ይችላሉና ግን በተቃራኒው በዲጂታል ቴክኖሎጂ የታነፁ ታዳጊዎች ችግሮቹን መቋቋም የመቻል አቅማቸው ከፍተኛ ነው።

በበርካታ ያለማችን ሃገራት የታዳጊዎች የሥራ ፈጠራ ክህሎት አሁን አሁን በትምህርት ካርኩለም ውስጥ ከማካተት ጀምሮ በስልጠና በመታገዝ ለመጪው የዲጂታል የሥራ ፈጠራ ጊዝያት እያዘጋጁ ይገኛሉ ።

በሃገራችን ኢትዮጲያ ይህን አይነት ተግባር ለማከናወን የሚንቀሳቀሱ ባለ እራይዎችም ይሁኑ የመንግስት አካላት ብዙም አይታዩም በእርግጥ ከዚህ ጋር በተያያዘ የመንግስት ፖሊሲዎች ሰፊ ክፈት ከትምህርት ባለድርሻ አካላትና ጋር ተጣምሮ የጉዳዩ ብልጫ ማሳየት አልተቻለም።

መልካም ቀን።

Scientists, technologists, engineers, and visionaries are building the future. Amazing things are in the pipeline. It’s ...
26/11/2022

Scientists, technologists, engineers, and visionaries are building the future.

Amazing things are in the pipeline. It’s a big deal. But you already knew all that.

Such speculation is common. What’s less common? Scale.

ከፍተኛው ቴክኖሎጂ ኢክስፖርት የሚያደርጉ ሃገራትና ከገቢያቸው ምንጫቸው ጋር።ምንጭ Worldatlas.com
25/11/2022

ከፍተኛው ቴክኖሎጂ ኢክስፖርት የሚያደርጉ ሃገራትና ከገቢያቸው ምንጫቸው ጋር።

ምንጭ Worldatlas.com

እስቲም ኤዱኬሽን(STEM) Education በትምህርት የተደገፈ ትውልድ ከምንም በላይ አስተሳሰቡም ጭምር ስለሚለወጥ እና በመልካም ስብዕና ስለሚገነባ ለሃገር እድገት የራሱ የሆነ ከፍተኛ አስተ...
25/11/2022

እስቲም ኤዱኬሽን(STEM) Education
በትምህርት የተደገፈ ትውልድ ከምንም በላይ አስተሳሰቡም ጭምር ስለሚለወጥ እና በመልካም ስብዕና ስለሚገነባ ለሃገር እድገት የራሱ የሆነ ከፍተኛ አስተዋፅዎ አለው።

አሁን አሁን ግን የትውልድ ብቃት መለኪያ እየሆነ የመጣው የሳይንስ፣ቴክኖሎጂ፣ኢንጂነሪንግ እና የሒሳብ ትምህርቶች ላይ ያላቸው አቅም እና ክህሎቶች ናቸው ይህ ጉዳይ እንኳን ባላደጉት ሃገራት በአደጉት ሃገራትም እንደ ትልቅ አጀንዳ ሆኖ በትምህርት ስራት ውስጥ ማካተትን በሰፊው እየሰሩበት የሚገኝ ሃሳብ ሆኗል።

ግን የእስቲም የትምህርት መርሃ ግብር ምንድነው? ይህ አይነት የማስተማር ዘዴ ታዳጊዎችን በሳይንስና ቴክኖሎጂ አቅማቸውን በማጎልበት በዚህም ሂደት ውስጥ ወሳኝ

የ አስተሳሰብ ሂደት ልምምድን(Critical thinking)፣ችግር አፈታትን (Problem solving skill)፣በጋራ ተደራጅቶ ሃሳብ ማጎልበትን(Team building) በአንድ በማጣመር ብሩህ ተሰፋ ያላቸውን ትውልድ በመፍጠር ወደፊት ስራ ፈላጊ ሳይሆኑ ሥራ ፈጣሪ ማድረግ ያስችላል

የወደፊት የሥራ ባህል።
25/11/2022

የወደፊት የሥራ ባህል።

የቴክኖሎጂ አክቲቪስቶች ስለ ኢትዮጲያ እያሉ ያሉት ።
25/11/2022

የቴክኖሎጂ አክቲቪስቶች ስለ ኢትዮጲያ እያሉ ያሉት ።

በ1963 ነበር የተተነበየው።ቴክኖሎጂ ከዛ ጊዜ በበለጠ በፍጥነት እያደገ ነው።ኢትዮጲያ ውስጥ  ግንባር በጣም ዘገምተኛ ነውትውልድ የቴክኖሎጂ ንቃተ ህሊናውን መጨመር ያስፈልጋል2030,2040....
24/11/2022

በ1963 ነበር የተተነበየው።

ቴክኖሎጂ ከዛ ጊዜ በበለጠ በፍጥነት እያደገ ነው።

ኢትዮጲያ ውስጥ ግንባር በጣም ዘገምተኛ ነው

ትውልድ የቴክኖሎጂ ንቃተ ህሊናውን መጨመር ያስፈልጋል

2030,2040.....?

መልካም ቀን

22/11/2022

የታዳጊዎች ኮዲንግ መግብያ እጅግ ጠቃሚ መረጃ ።

በዚህ ክፍል Scratch Jr በቃላሉ መማመድ እንደሚቻል ለማሳዬት ነው።

Link:https://www.scratchjr.org

ድጅታል ፊሪለንሰር እና ሥራ መስፋፋትበሚቀጥሉት አስርት አመታት የድጅታል ቴክኖሎጂ መስፋፋት ልክ እንደሌላው የሥራ ዘርፍ ሁሉ የፍሪላንሲንግ እንቅስቃሴዎችንም ሙሉ በሙሉ የመቀየር ዕድሉ የጨመረ...
22/11/2022

ድጅታል ፊሪለንሰር እና ሥራ መስፋፋት

በሚቀጥሉት አስርት አመታት የድጅታል ቴክኖሎጂ መስፋፋት ልክ እንደሌላው የሥራ ዘርፍ ሁሉ የፍሪላንሲንግ እንቅስቃሴዎችንም ሙሉ በሙሉ የመቀየር ዕድሉ የጨመረ ነው።ሰዎች ከነዚህ የድጅታል ቴክኖሎጂ መስፋፋት ክና የኮሮና ቫይረስ እየጨመረ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ በአለማችን ላይ አዳዲስ የሥራ ልምምዶች እና ባህሎች መምጣት ጀምሯል ከነዚህም በዋናኝነት የድጅታል ፎሪላንሲንግ ሲሆን ይህም ማለት ሰዎች ካሉበት ቦታ ሆነው በተለያዩ የድጅታል መግባቢያ ሶፍት ዌር፣የድጅታል ፕላት ፍርም፣ማህበራዊ ሚድያ በመጠቀም ሥራቸውን ያለምንም መስተጓግል ማከናወን የሚችሉበት ሁኔታ ነው።በቅርብ ጊዜ እንደ ሊንክ ዲን ያሉ ማህበራዊ ሚድያ ባጠኑት መሰረትና ብዙ ሰዎች ሥራቸውን ቤት ውስጥ ቁጭ ብለው የመስራት ልምዳቸው እየጨመረ መጥቷመቷል።የድጅታል ፊሪላንሲንግ አገልግሎት እንደሌሎቹ የቢዝነስ ዓይነት ቀላል አይደለም ብዙ ጥረቶችን ቢጠይቅም እራስን በማለማመድ እና ተከታታይ ጥረቶችን በማድረግ ማዳበር ይቻላል።
መልካም ቀን

21/11/2022

ቴክኖሎጂ በአግባቡ ካልተጠቀምክበት ትውልድ ይበላል።

አፍሪካ ውስጥ ለምን ይመስላል ተፅኖ የሚፈጥር የአፍሪካን በህል የያዘ ግዙፍ የቴክኖሎጂው ተቋምም የሌለው?

ለማንኛውም ከዚህ በኃላ የሚመጡት የቴክኖሎጂው ውጤቶች እኛ አብረን ካልተቀረፅን ቢዝነስ በመስራት የበለጠ
ድህነትን ውስጥ ሊከቱን ይችላሉ!!!

ለምን ብትሉ እኛ ተጠቃሚዎች እንጂ አምራች ሆነን አናውቅም።

 #ቴክኖሎጂ እና የሰው ልጅ
19/11/2022

#ቴክኖሎጂ እና የሰው ልጅ

19/11/2022

ታዲያ እኛንስ የያዘን ምንድነው።

ሥራን በዲጅታል ቴክኖሎጂ በመታገዝ መፍጠር እና አዳዲስ ሃሳቦችን በተቀናጀ መልክ ማከናወን በሰለጠኑት ሃገራት ትንሽ የቆየ ልምድ ይህም እንደ ጊዜው እና ዘመን እንዳመጣው የቴክኖሎጂ እድገት እራሱን እያስፉፉ እና እያደራጀ ብዙ የፈጠራ ውጤቶችን እያስገኘ ያለ የኢኖቬሽን ቴክኖሎጂ ውጤት ነው ።የዲጅታል ኢኖቬሽን ሃብ ማለት የተለያዩ የቴክኖሎጂ እና የቢዝነስ የፈጠራ ሃሳቦችን በአንድ ሥነ ምህዳር ውስጥ በማስተሳሰር እና ሰፊ የመሞከሪያ ቦታዎችን በመፍጠር ጅምር ሃሳቦችን አጎልብቶ ለሚሊዮኖች ሥራ እና ቢዝነስን በመፍጠር እረገድ የሚጫወተው ሚና ቃላል አይደለም።በዚህ የኢኖቬሽን ሃብ ውስጥ በሰፊው ከሚታወቁተ ሃገራት አሜሪካ በሲልከን ቫሊ ይህ የልህቀት ማህከል በርካታ ትልልቅ የቴክኖሎጂ ድርጅቶች የሚፈለፈሉበት ሲሆን የሚገኘውም በደብባዊ ሳንፍራንሲስኮ በምትገኝ ከተማ ውስጥ ሲሆን አፖል፣ጎግል፣ፌስብክ፣እና ከ30 በላይ ግዙፍ የአለማችን ጅያንት የቴክኖሎጂ ድርጅቶችም መቀመጫ ነዉ በተጨማሪም ሰን ማይክሮ ሲስተም፣ሲስኮ፣ሀውላት ፖክድ።፣ኢንቴል ሰን ማይክሮ ሲስተም፣ኮነር ፕሪፌራል እና ሲፕረስ ሲሚ ኮንዳክተርም ድረጅቶች የጎለበቱት በሲልከን ቫሊ የልህቀት ማከል ውስጥ ነበር ።

ምንጭ ፦የተለያዩ ድህረ ገፆችን እና ጥናቶች

19/11/2022

የቴክኖሎጂ ክህሎት በገጠሪቱ ኢትዮጲያ

እኔ ግን በጣም ያሳስበኛል።
ያንብቡት
የቴክኖሎጂ ዕድገትም ቀን በቀን እየተቀያየረ እና እያደገበመምጣቱ ምክንያት አዳዲስ የቴክኖሎጂ ውጤቶች እና አገልግሎቶች አለምን ከምናውቀው በላይ በፍጥነት በመቀየር እና ለበርካታ የአለም ህዝቦች በሚልዮን የሚቆጠሩ ሥራዎችን በመፍጠር ጭምር እገዛ እያደረገ ይገኛል።በሌላው በኩል ደግሞ በድሃ እና በታዳጊ ሃገራት ላይ ዘመኑ ከወለዳቸው የቴክኖሎጂ ውጤቶች እና አገልግሎቶች አብረው እኩል መሄድ ስለማይችሉ ቴክኖሎጂውን ገዝቶ ፣ሰልጥኖ እና ተክሎ ከመጠቀም ጀምሮ ከፍተኛ ዋጋ እያስከፈለ ያለ ጉዳይ ነው በተለየ መልኩ ደግሞ አንደኛውን የቴክኖሎጂ ትውልድ ዝርጋታ ሳይጨርሱ ሌላ የቴክኖሎጂ ትውልድ ይፈጠራል ለምሳሌ የ4ጂ የኔትወርክን በአግባቡ ሳንጠቀም የ5ጂ የኔትወርክ አገልግሎት ይመጣብናል ለዚህም ሌላ በቢልዮን የሚቆጠር መዋለ ንዋይ ማፍሰሳችን አይቀርም ይህ በቴሌኮሚኒኬሽኑ ዘርፍ ሲሆን ይህ አዳዲስ የቴክኖሎጂ ትውልድ በሌሎችም ዘርፍች ላይ ዱላው የበረታ ነው ለምሳሌ በመኪና ኢንደስትሪ፣በአውሮፕላን አምራቾች፣የእክምና፣የእርሻው ዘርፍ እና በርካታ ለሰው ልጆች ቀጥተኛ ጠቀሜታ ካላቸው ከትንሽ እስከ ትልቅ የቴክኖሎጂ ውጤቶች መጥቀስ ይቻላል።ይህ ሽግግር በኢኮኖሚ ካደጉት ሃገራት ይልቅ ያለደጉት አገራትን በመጉዳት የኢኮኖሚ ጥገኝነትና እንዲፈጠር የራሱ የሆነ የጎላ ሚና አለው።ይህ ሁሉ ተግዳሮት ሊያጋጥመን የቻለው በኘብዛኛው በኢትዮጲያ የሚኖሩ ዚጎች ይህም 80% የሚሆነው በገጠሪቱ ክፍለ ስለሆነ እነዚህ መህበረሰቦች እንኳን ዘመኑ የወለደውን የዲጅታል ቴክኖሎጂ ሊጠቀሙ ይቅር እና እራሱ የቴክኖሎጂው መሰረተ ልማትም እንኳን አልደረሳቸውም ታዲያ በዚህ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚኖሩትን ታዳጊዎች እዚህ የገዘፈ ኢኮኖሚ ይዞ በሚመጣው የትውልድን እሽቅድድሞሽ በሚያሳየው የዲጅታል አብዮት እንዴት አድርገው ማለፍ አለባቸው የሚለውም ሃሳብ በአገርም ደረጃ መታየት ያለበት አጀንዳ መሆን አለበት።

መልካም ውሎ!!!!

19/11/2022

ይህን ያውቁ ኖሩዋል?
በ2030 በዲስትራፕቲቭ ቴክኖሎጂ ወይም እስማርት ኢንደስትሪ መስፋፋት አለማችን እስከ 12 ትሪሊዮን ዶላር የገበያ ዕድልን ትፈጥራለች ከዚ ውስጥ እስከ 10 ቲሪሊዬን የሚደርሰውን መሪ ቴክኖሎጂ ያላቸው አገራት ይወስዱታል የቀረውን 1.5ትሪሊዮኑን ዶላሩን ቴክኖሎጂውን በመቀላቀል ላይ ያሉ አገራት ሲሆኑ ሌላው ቀሪውን በሶስተኛ ደረጃ ላይ ያሉ አገራት ናቸው።

ይህ ማለት በሚቀጥሉት አስርት አመታት ቡና እና ስንዴው ልከን በአለም አቀፍ ኢኮኖሚ ላይ መወዳደር እጅጉን ከባድ ነው።

የቴክኖሎጂ ተጠቃሚ ብቻ ሳንሆን አምራችም እንሁ መልክታችን ነው።

መልካም ቀን

03/10/2022

Ginger plant development
ጂንጅብል ኢትዮጲያ ውስጥ የገባው በ13 ክፍለዘመን ከህንድ በመጡ አረቦች ሲሆን በዋናኝነት የሚበቅልበት ቦታ በደቡብ ኢትዮጲያ፤ በምስራቅ እና ምህራብ ጎጃም እና ጋምቤላ አከባቢዎች በስፋት መብቀል ይችላል፡፡በተለምዶ ኢትዮጲያ ወስጥ ለቅመማ ቅመም እና ተመሳሳይ አይነት አገልግሎት ላይ ይውላል አሁን አሁን ደግሞ በዘይት መልክ በመምጣት ለተለያየ የጤና አገልግሎት መዋል ምሯል ይህም በትንሹ በቤት ውሥጥ ስለሚመረት ዋጋው እጅጉን ከፍተኛ ነው ፡፡ ይህን አይነት ምርት በአሁን ግዜ በአለም ላይ ከፍተኛ ተፈላጊነት ስላለው ምርቱን ማሽነራችን በመጠቀም ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ማግኘት ይቻላል፡፡
በቀን 100-100 ሊትር
መነሻ ካፒታል 1-10 ሚሊዮን ብር
በዚህ ቪድዮ ውስጥ የፕሮጀክቱን ሙሉ ሃሳብ ያገኛሉ
ፕሮጀክቱን በመተግበር ለራሶ እና ለሰዎች የሥራ ዕድል ይፍጠሩ

  Board!!
02/10/2022

Board!!

ጥናቶች እንደሚያሳዩት በ2025 አለማችን ያሉ ድርጅቶች ከ75% በላይ የሆነውን ስራቸውን ወደ ዲጅታል ቴክኖሎጂ እና ተመሳሳይነት ወዳላቸው የአሰራር ሲስተም ስለሚቀይሩ የሰራተኛቸውም ክህሎት በ...
02/10/2022

ጥናቶች እንደሚያሳዩት በ2025 አለማችን ያሉ ድርጅቶች ከ75% በላይ የሆነውን ስራቸውን ወደ ዲጅታል ቴክኖሎጂ እና ተመሳሳይነት ወዳላቸው የአሰራር ሲስተም ስለሚቀይሩ የሰራተኛቸውም ክህሎት በዚው ልክ ማደግ አለበት ።በተጨማሪም በዚህ የቴክኖሎጂ ጊዜ የሚገኙ ታዳጊዎች ከዛሬ አስርት አመት ከነበሩት ትውልድ ስራ ለማግኘት እጅጉን ሊቸገሩ ይችላሉና ግን በተቃራኒው በዲጂታል ቴክኖሎጂ የታነፁ ታዳጊዎች ችግሮቹን መቋቋም የመቻል አቅማቸው ከፍተኛ ነው።በበርካታ ያለማችን ሃገራት የታዳጊዎች የሥራ ፈጠራ ክህሎት አሁን አሁን በትምህርት ካርኩለም ውስጥ ከማካተት ጀምሮ በስልጠና በመታገዝ ለመጪው የዲጂታል የሥራ ፈጠራ ጊዝያት እያዘጋጁ ይገኛሉ

10/09/2022

አዲሱ አመት የሰላም፤የጤና እንዲሁም የብልፅግና ይሁንልን፡፡
ኢትዮቴክአይ4 ሁለንተናዊ የቴክኖሎጂ እና የሥራ ፈጠራ ክህሎት ማዳበሪያ፡፡

Address

Akaki Kality
Addis Ababa
0000

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethio TECHi4 posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Ethio TECHi4:

Videos

Share