All In One Ethiopia

All In One Ethiopia Daily Business News in Ethiopia
Daily Job vacancy in Ethiopia
Daily Job vacancy in Ethiopia

Mesmerizing Addis Ababa 🌆✨ Dive into the heart of Ethiopia's capital with this stunning image!
21/03/2024

Mesmerizing Addis Ababa 🌆✨ Dive into the heart of Ethiopia's capital with this stunning image!

ባለ ሁለት መቶ ብር ሲያትም የነበረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለበቴፒ ከተማ ህብረት ቀበሌ ከረፋዱ 5:30 ሰዓት በአንድ ማተሚያ ቤት ዉስጥ ሐሰተኛ የ200 ኖቶችን ሲያሳትምና  ኮፒ ሲያደርጉ ህ...
19/03/2024

ባለ ሁለት መቶ ብር ሲያትም የነበረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ
በቴፒ ከተማ ህብረት ቀበሌ ከረፋዱ 5:30 ሰዓት በአንድ ማተሚያ ቤት ዉስጥ ሐሰተኛ የ200 ኖቶችን ሲያሳትምና ኮፒ ሲያደርጉ ህብረተሰቡ ለፖሊስ በተሰጠ ጥቆማ ኮፒ የተደረገ ዘጠኝ ሺህ ሁለት መቶ ብር እና አንድ ተጠርጣሪ፣ ፎቶ ኮፒ ፣ኮምፕተር ጋር እጅ ከፍንጅ ተይዞ ምርመራ እየተጣራ እንደሚገኝ የቴፒ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ በማህበራዊ ትስስር ገፅ ገልጿል።
VAI FAST MERJA

እራስህን ፈታኝ!
15/03/2024

እራስህን ፈታኝ!

የአፍሪካ ሕብረት መዝሙርን ፃፊው ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን ቀዌሳ የአምቦ ልጅየአፍሪካ ሕብረት ባንዲራን /ሰንደቅ/ዲዛይን ቀራጭና ሳይ ያዴሳ ቦጂሀ የአምቦ ልጅ የኢትዮጵያ ብሔራዊ መዝሙር ደራሲ ...
25/02/2024

የአፍሪካ ሕብረት መዝሙርን ፃፊው ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን ቀዌሳ የአምቦ ልጅ
የአፍሪካ ሕብረት ባንዲራን /ሰንደቅ/ዲዛይን ቀራጭና ሳይ ያዴሳ ቦጂሀ የአምቦ ልጅ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ መዝሙር ደራሲ ደረጄ መላኩ የአምቦ ልጅ
የጀግኖችና የጠቢባን ሀገር!የአፍሪካ ሕብረት መዝሙርን ፃፊው ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን ቀዌሳ የአምቦ ልጅ
የአፍሪካ ሕብረት ባንዲራን /ሰንደቅ/ዲዛይን ቀራጭና ሳይ ያዴሳ ቦጂሀ የአምቦ ልጅ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ መዝሙር ደራሲ ደረጄ መላኩ የአምቦ ልጅ
የጀግኖችና የጠቢባን ሀገር!

Derartu Tulu of Ethiopia celebrates after winning the women's 10000m final at the 8th IAAF World Athletic Championships ...
06/11/2023

Derartu Tulu of Ethiopia celebrates after winning the women's 10000m final at the 8th IAAF World Athletic Championships in Edmonton, Canada, 7 Aug 2001

Photo by Adam Pretty

«ተፀፅቻለሁ ይቅርታ እጠይቃለሁ!» FastMerejaባለፈው ሳምንት በሰይፉ ሾው ላይ የቀረበው ረጅሙ ሰው ነገዎ ጅማ መኪና ካልተገዛልን ዜግነት እቀይራለው ማለቴ ትክክል አልነበረም ለመጓጓዝ መ...
05/11/2023

«ተፀፅቻለሁ ይቅርታ እጠይቃለሁ!» FastMereja
ባለፈው ሳምንት በሰይፉ ሾው ላይ የቀረበው ረጅሙ ሰው ነገዎ ጅማ መኪና ካልተገዛልን ዜግነት እቀይራለው ማለቴ ትክክል አልነበረም ለመጓጓዝ መኪና የሚያሳፍረኝ ሰው በመጥፋቱ ተበሳጭቼ ስለነበር ስሜታዊ ሆኜ የተናገርኩት ነው ሀገሬን ዜግነቴን አልቀይርም ለተናገርኩት ይቅርታ እጠይቃለሁ ሲል ተናግሯል።

አትሌት ታምራት ቶላ የኒው ዮርክ ማራቶንን የቦታውን ሪከርድ በመስበር አሸነፈ። በ2:04:58 በመግባት ሲያሸንፍ የሚያሳየውን አጭር ቪዲዮ ይመልከቱ
05/11/2023

አትሌት ታምራት ቶላ የኒው ዮርክ ማራቶንን የቦታውን ሪከርድ በመስበር አሸነፈ።
በ2:04:58 በመግባት ሲያሸንፍ የሚያሳየውን አጭር ቪዲዮ ይመልከቱ

05/11/2023

እብደቱ እንደቀጠለ ነው
አስገባ አውጣ ንቀል😱

ላዳ መኪኖች በኢትዮጵያ ሊመረቱ ነውአዲስ አበባ፣ መስከረም 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ላዳ መኪኖች በኢትዮጵያ ተመርተው ለአፍሪካ ገበያ ሊቀርቡ መሆኑ ተነገረ፡፡የሩሲያዎቹን ላዳ መኪኖች በኢት...
28/09/2023

ላዳ መኪኖች በኢትዮጵያ ሊመረቱ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ላዳ መኪኖች በኢትዮጵያ ተመርተው ለአፍሪካ ገበያ ሊቀርቡ መሆኑ ተነገረ፡፡

የሩሲያዎቹን ላዳ መኪኖች በኢትዮጵያ ለማምረት የሚያስችል ሥምምነት መደረሱን ታስ የተሰኘው የሩሲያ የዜና ወኪል ዘግቧል፡፡

ከስምምነት ላይ የደረሰው አቭቶቫዝ የተሰኘው መንግስታዊው የቤት መኪና አምራች ኩባንያ መሆኑ ተገልጿል።

ኢትዮጵያ ውስጥ የሚመረቱት ላዳ መኪኖች÷ ሱዳንን፣ ደቡብ ሱዳንን እንዲሁም ኬንያን እና ሶማሊያን ጨምሮ ወደ ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ይላካሉም ተብሏል፡፡

መኪኖቹን በቅርብ ጊዜ ውስጥ በኢትዮጵያ ውስጥ ማምረት እንደሚጀመር የተጠቆመ ሲሆን፤ ሌሎች የሩሲያ መኪና አምራች ኩባንያዎችም በኢትዮጵያ የመኪና መገጣጠም ዘርፍ ላይ ለመሰማራት ፍላጎት እያሳዩ እንደሆነ መሆናቸው ተጠቁሟል።

በጉዳዩ ላይ ሁለት የሩሲያ መኪና አምራች ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ለመሥራት እየመከሩ መሆኑም ተገልጿል፡፡

Today's best photo     ゚
27/09/2023

Today's best photo
゚

Addis Ababa city of Ethiopia 🇪🇹Continent : Africa
26/09/2023

Addis Ababa city of Ethiopia 🇪🇹
Continent : Africa

26/09/2023

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በመግባት 35,000 ብር ይዞ የሮጠው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ
FastMereja
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሜጢ ቅርንጫፍ በመግባት 35,000 ብር ይዞ የሮጠው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ። በጋምቤላ ክልል ጎደሬ ወረዳ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሜጢ ቅርንጫፍ ግለሰቡ ወደ ባንኩ ከገባ በኋላ ብር ለማውጣት ወጭ የሚጠይቅ አስመስሎ ለሌላ ሰው የተቀመጠውን 35,ዐዐዐ ብር ከጠረንጴዛ አንስቶ ሲሮጥ በፀጥታ ሀይሎችና በባንኩ ጥበቃ ሰራተኞች በቁጥጥር ስር ውሏል።

ግለሰቡ አራት መታወቂያ እና የሌላ ሀገር የገንዘብ ኖት ከኪሱ የተገኘ ሲሆን በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተካሄደበት እንዳለ ጎደሬ ወረዳ መንግስት ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በአዲስ አበባ ጎፉ ማዞሪያ ከ30 አመት በላይ የቀድሞ ፍቅረኛቸውን የሚጠብቁት ግለሰብ ታሪክ ፊልም ሊሰራበት ነው::  "ለፍቅር የተከፈለ መስዋትነት"አስገራሚው እውነተኛ ታሪክ ከሙዚቃ ባለፈ ወ...
25/09/2023

በአዲስ አበባ ጎፉ ማዞሪያ ከ30 አመት በላይ የቀድሞ ፍቅረኛቸውን የሚጠብቁት ግለሰብ ታሪክ ፊልም ሊሰራበት ነው::
"ለፍቅር የተከፈለ መስዋትነት"
አስገራሚው እውነተኛ ታሪክ ከሙዚቃ ባለፈ ወደ ፊልም ሊቀየር መሆኑ ተሰምቷል::
ድምፃዊ ሀይለየሱስ ግርማ አዚሞት በግጥምና ዜማ ደራሲ እንዲሁም የሙዚቃ አቀናባሪ በአማኑኤል ይልማ የተዘጋጀው "የሌለሽበት" ሙዚቃ ወደ ፊልም እንደሚቀየር ተነግሯል::
ለአመታት የፍቅር አጋራቸው የነበረችውን ኃላ ላይ ግን ወደውጭ የሄደችውን ፍቅረኛቸውን
በተቀጣጠሩበት ቦታ ላይ ላለፈው 30 አመት ሁሌም የሚጠብቋት አቶ ለማ በተባሉ ባለታሪክ እውነተኛ ህይወትን መነሻ አድርጎ የተሰራው ሙዚቃው አሁን ወደ ፊልም ሊቀየር እንቅስቃሴ ተጀምሯል::
ከኤፍ ኤም አዲስ 97.1 መሰንበቻ ፕሮግራም ጋር ቆይታ ያደረገው አማኑኤል ይልማ እንዳለው የሙዚቃው ባለታሪክ አቶ ለማን በዚህ ሳምንት በአካል አግኝቶ አነጋግሯቸዋል::

አቶ ለማ ለፍቅር የከፈሉት መሰዋትነት ሌላ ሀገር ቢሆን ትልቅ በጀት ተመድቦለት ፊልም ሊሰራበት ይችላል የሚለው አማኑኤል በተደጋጋሚ ሙዚቃውን በምስል ለመስራት ቢሞከረም አርኪ የሆነ ዝግጅት ባለመገኝቱ መዚቃው በቪዲዮ ክሊፕ ሳይሰራ ቀርቷል::

ይህም ቢሆን ከባለሞያዎች ተደጋጋሚ ጥያቄ እየቀረበ በመሆኑ እውቁ የፊልም ባለሞያ ቴውድሮስ ተሾመ የአቶ ለማ እውነተኛ ታሪክን ወደፊልም ሊቀይረው እንቅስቃሴ ተጀምሯል::

በፊልሙ ላይ አማኑኤል ይልማ ሊተውን እንደሚችልም ፍንጭ ሰቷል::

አቶ ለማን ያገኝሁበት አጋጣሚ ድንገት እና የተመቻቸ ባለመሆኑ በቀጣይ ደግሞ በማግኝት ተጨማሪ ነገሮችን ከአንደበታቸው ለመስማት ማሰቡንም አማኑኤል ለመሰንበቻ ፕሮግራም ተናግሯል::

ለመጀመሪያ ግዜ ባገኝቸው እለት ግን ፍፁም በተረጋጋ ሁኔታ ውስጥ ሆነው ከአንደበታቸው " ሁሉም ከንቱ ነው" የሚል ቃል የወጣቸው መሆኑንም ጠቅሷል::
አቶ ለማ ከፍቅር አጋራቸው ጋር መለያየታቸውን ተከትሎ ሁሌም በተቀጣጠሩበት ቦታ አዲስ አበባ ጎፉ ማዞሪያ አካባቢ ሁሌም ትመጣለች በሚል እየጠበቋት ይገኛሉ::
ኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ሬዲዮ/

ሀገረ ራሺያ በዚህ መልኩ የአማርኛን ቋንቋ እያስተማሩ ነው።ሀገረ ራሺያ በዚህ መልኩ የአማርኛን ቋንቋ እያስተማሩ ነው።
24/09/2023

ሀገረ ራሺያ በዚህ መልኩ የአማርኛን ቋንቋ እያስተማሩ ነው።ሀገረ ራሺያ በዚህ መልኩ የአማርኛን ቋንቋ እያስተማሩ ነው።

የቴሌ ብር አገልግሎት  በዋይፋይ ኢንተርኔት እንዳይሰራ ተደረገ።********በኢትዮጵያ 31 ሚሊዮን ደንበኞች እንዳሉት ያስታወቀው ቴሌብር በደንበኞቹ ላይ የሚደርሰውን መጭበርበር ይቀርፋል ያለ...
22/09/2023

የቴሌ ብር አገልግሎት በዋይፋይ ኢንተርኔት እንዳይሰራ ተደረገ።
********
በኢትዮጵያ 31 ሚሊዮን ደንበኞች እንዳሉት ያስታወቀው ቴሌብር በደንበኞቹ ላይ የሚደርሰውን መጭበርበር ይቀርፋል ያለውን ማዘመኛ ይፋ ማድረጉን አሳውቋል።

ማዘመኛው ስልክ በመደወል፣ የፒን ቁጥርን በማታለል በመቀበልና በሌላ ስልክ በመጠቀም አካውንቱ ላይ የሚገኝ ገንዘብን በማዘዋወር የሚፈጸምን ማጭበርበር ለመግታት እንደሆነ ኢትዮ ቴሌኮም አስታውቋል።

በዚህም መሰረት፦

👉ደንበኛው የራሱ ስልክ ቁጥር ባለበት የሞባይል ቀፎ ካልሆነ በስተቀር በሌላ አገልግሎት ቁጥር (ሲም ካርድ) እንዳይሰራ፣

👉የራሱን ስልክ የሞባይል ዳታን በመጠቀም ካልሆነ በስተቀር በዋይፋይ ኢንተርኔት እንዳይሰራ የተደረገ መሆኑንም ነው ተቋሙ የገለፀው።

አዲስ አበባ ረቡዕ መስከረም 9/2015  አመሻሽ ላይ  ይሄ ሆነ       ፌደራል ፖሊስ ነን የሚሉ ሰዎች ከትራፊክ ፖሊስ ጋር በመተባበር ኡስታዝ አቡበከርን አስቆሙት። «በመኪና ስርቆት ወንጀ...
22/09/2023

አዲስ አበባ ረቡዕ መስከረም 9/2015 አመሻሽ ላይ ይሄ ሆነ
ፌደራል ፖሊስ ነን የሚሉ ሰዎች ከትራፊክ ፖሊስ ጋር በመተባበር ኡስታዝ አቡበከርን አስቆሙት። «በመኪና ስርቆት ወንጀል ተጠርጥረሃል፤ የምትነዳው V8 መኪና የተሰረቀ ነው። ፖሊስ ጣቢያ ሂድ!» አሉት። ኡስታዝም የማጭበርበር ወንጀል መሆኑን ፈጥኖ በመረዳት ወደ ቤተሰብ ደውሎ አሳወቀ፤ ቤተሰብም በፍጥነት መጡለት ።
ከዚያም ቶታል 3 ቁጥር ማዞሪያ ወደ ሚገኘው ፖሊስ መምሪያ ይዘውት ሄዱ። ፌደራል ፖሊስ ነን ያሉት ግለሰቦች ሐሰተኛ መታወቂያቸውን ለፖሊሶች በማሳየት ኡስታዝ አቡበከርን እና መኪናውን ለፖሊስ መምሪያው አስረክበው ሄዱ።
ከለሊቱ 6 ሰዓት ሲሆን እነዚሁ አካላት ወደ ፖሊስ መምሪያው በመምጣት ተረኛ ፖሊሱን "ወንጀለኛው ፌደራል ፖሊስ ጋር ይፈለጋልና ስጡን!" አሏቸው። ፖሊሱም "ደብዳቤ ካላመጣችሁ አንሰጥም" የሚል ምላሽ ሰጣቸው።
አሳልፎ ቢሰጣቸው ኖሮ ኡስታዝን ገድለው መኪናውን ዘርፈው ይሰወሩ ነበር።
ትናንት ከሰዓት አከባቢ እነዚሁ አካላት ከለቡ ፖሊስ ጣቢያ ደብዳቤ በማምጣት ከሳሽ የሚገኘው ለቡ ፖሊስ ጣቢያ ነው በማለት ወደ ለቡ ፖሊስ ጣቢያ ወሰዱት።
ቤተሰብ የመኪናውን ሊብሬ ይዞ መንገድ ትራንስፖርት በመሄድ ሲያጣራ የመኪናው ሊብሬ በሌላ ሰው ስም ተቀይሯል።
ጉዳዩ አደገኛ የሆነ ሰንሰለት ያለበት ማጭበርበር ወንጀል መሆኑን በመረዳት ጉዳዩ ወደ ፌደራል ፖሊስ ወደ ከፍተኛ የፖሊስ አመራሮች እንዲደርስ ተደረገ።
መረጃው ወደ ሪፐብሊካን ጋርዶች ሲደርስ "የለቡ ፖሊስ ጉዳዩ እኔን አይመለከተኝም" በማለት ወደ ፔፕሲ ፋብሪካ ጎተራ ወደ ሚገኘው ፖሊስ ጣቢያ እንዲሄድ ተደረገ።
የፌደራል ፖሊስ አባላት ጎተራ ፖሊስ መምሪያ መጥተው ጉዳዩን ሲመረምሩ ፌደራል ፖሊስ ነን ያሉ አካላት ፌደራል ፖሊስ አባል እንዳልሆኑ እንዲሁም መኪናችንን ተሰርቀናል ብለው ሐሰተኛ ሊብሬ ያሰሩ አካላት በቁጥጥር ስር ዋሉ።
ኡስታዝ አቡበክር ሑሴን እንዲፈታ ተደረገ።
አሁን ጥያቄው የመኪና ሊብሬውን ማን ስሙን ቀየረ።
የእነዚህ ወንጀለኞች ሰንሰለት እስከምን ድረስ ነው? የሚለው ሲሆን በቀጣይ ፖሊስ የሚያጣራው ሆኖ ኡስታዝ አቡበከር ሁሴን ትናንት ሀሙስ ይህንን አስታውቋል።

Legandes Atilet Abebe Bikila: Legendary MarathonerAbebe Bikila was an Ethiopian long-distance runner who gained internat...
10/09/2023

Legandes Atilet Abebe Bikila: Legendary Marathoner
Abebe Bikila was an Ethiopian long-distance runner who gained international fame for winning the marathon at the 1960 Summer Olympics in Rome. Notably, he ran the marathon barefoot, becoming the first African to win an Olympic gold medal in the event. Bikila's victory made him a symbol of African excellence in athletics and an inspirational figure. He went on to win another Olympic marathon gold medal at the 1964 Tokyo Olympics, this time wearing shoes. Sadly, his running career was cut short due to a car accident in 1969, which left him partially paralyzed. Despite this setback, he remained an influential figure in Ethiopian sports and is remembered as a legendary athlete. Abebe Bikila passed away in 1973 at the age of 41.
゚viralシ

አርቲስት አንዱአለም ጎሳ እና አርቲስት ጫላ ቡልቱሜ መካከል የተፈጠረው ችግር በሽምግልና እርቅ መፈፀሙ ለፋስትመረጃ የደረሰው መረጃ ያመለክታል።
10/09/2023

አርቲስት አንዱአለም ጎሳ እና አርቲስት ጫላ ቡልቱሜ መካከል የተፈጠረው ችግር በሽምግልና እርቅ መፈፀሙ ለፋስትመረጃ የደረሰው መረጃ ያመለክታል።

በአገራችን ይህች ከተማ ስሟ ማን ነው.
06/09/2023

በአገራችን ይህች ከተማ ስሟ ማን ነው.

ከለሊቱ 8:00 ሀረር ከተማ አባድር ወረዳ በ06 ቀበሌ ውስጥ በእንግድነት ሰዉ ቤት አሳድሩኝ ብላ ከተኛች በኋላ በተጠቀሰው ሰአት ከመኝታዋ ተነሰታ በቤት ዉስጥ የነበረውን የገንዘብ ሳጥን በቢ...
05/09/2023

ከለሊቱ 8:00 ሀረር ከተማ አባድር ወረዳ በ06 ቀበሌ ውስጥ በእንግድነት ሰዉ ቤት አሳድሩኝ ብላ ከተኛች በኋላ በተጠቀሰው ሰአት ከመኝታዋ ተነሰታ በቤት ዉስጥ የነበረውን የገንዘብ ሳጥን በቢላዋ በመክፈት 9ሺ ብር ሰርቃ ልታመልጥ ሰትል የአካባቢው ህብረተሰብ ለፖሊስ ጥሪ በማድረግ ወዲያው በቁጥጥር እንደዋለች የሀረሪ ፖሊስ ገልፇል።

15 𝙄𝙣𝙩𝙚𝙧𝙚𝙨𝙩𝙞𝙣𝙜 𝙁𝙖𝙘𝙩𝙨  𝙀𝙩𝙝𝙞𝙤𝙥𝙞𝙖🇪🇹1. The Ethiopian 🇪🇹  calendar is different from the Georgian calendar. There are thirtee...
04/09/2023

15 𝙄𝙣𝙩𝙚𝙧𝙚𝙨𝙩𝙞𝙣𝙜 𝙁𝙖𝙘𝙩𝙨 𝙀𝙩𝙝𝙞𝙤𝙥𝙞𝙖🇪🇹
1. The Ethiopian 🇪🇹 calendar is different from the Georgian calendar. There are thirteen months in the Ethiopian calendar, which means they are currently in 2015.

2. Ethiopians 🇪🇹 also measure the hours of a day to a different schedule based on the logic that the clock starts when the day does. Ethiopia, however, observes 13 calendar months per year. This makes the Ethiopian calendar 7 years behind the rest of the world.

3. Ethiopia 🇪🇹 is the only African country never to have been brought under colonial rule. The Itàlians tried but failed woefully and were defeated by the solid Ethiopian forces.

4. Ethiopia 🇪🇹 has the world's 0ldest Bible and the most unique.

5. Ethiopia 🇪🇹 is home to one of the world's best coffee. In fact, coffee production is huge in Ethiopia.

6. According to some archaeological findings, Ethiopia 🇪🇹 is the cradle of humànkind. Meaning lifè actually started in Ethiopia.

7. In 1960, an Ethiopian named Abebe Bikila became the first Black African to win gold in the Olympics. He won it by running barefoot.

8. Addis Ababa's name translates to ‘New Flower’ in Amharic. The city is one of the oldest cities in the world.

9. Ethiopia 🇪🇹 is home to some of the world's tastiest, healthiest and most diverse cuisines on the continent of Africa.

10. The biggest festival in Ethiopia, Timket, is a three-day annual festival that honours the baptism of Jesus Christ in the river Jordan. It's one of the world's largest festivals that takes place annually. The festival attracts millions of people from all over the world.

11. Ethiopia 🇪🇹 has the most UNESCO World Heritage Sites on the continent. Ethiopia takes first place as the African country with the most UNESCO World Heritage sites. There are 9 total ranging from religious sites to natural areas. Among them are the Simien National Park, Konso Cultural Landscape and the rock-hewn churches.

12. Over 80 languages are spoken in Ethiopia. There are over 80 languages spoken with English being the language of educational systems in addition to local languages which include Oromo, Amharic, Somali and Tigrinya.

13. Over half of Africa’s mountains are in Ethiopia 🇪🇹 Along with Ethiopia’s incredible cultural and historical significance, the natural beauty is in a league of its own. In addition to a gorgeous landscape of low desserts and volcanic plateaus, Ethiopia is incredibly mountainous. In fact, around 70% of Africa’s mountains are in Ethiopia.

14. Ethiopia 🇪🇹 is Africa’s oldest country. Originally founded in 980 BC, Ethiopia is the oldest independent nation on the continent. Additionally, Ethiopia has remnants of some of the most ancient human beings on earth dating back millions of years making it one of the most important archaeological areas in the world. Not only that, but it is the second most populated country with more than 106 million people.
15. Ethiopia 🇪🇹 is the only country in the world with its own unique Alphabet.
゚viralシ

የፀሐይ ሪል ስቴት ዋና ስራ አስኪያጅ ኪያ ዦንግንየውጭ ሀገራት ገንዘቦችን በማተምና ጥቁር ገበያን በማስፋፋት ወንጀል የተጠረጠሩ ግለሰቦች ፍ/ቤት ቀረቡ| በርካታ መጠን ያላቸው የውጭ ሀገራት ...
04/09/2023

የፀሐይ ሪል ስቴት ዋና ስራ አስኪያጅ ኪያ ዦንግን

የውጭ ሀገራት ገንዘቦችን በማተምና ጥቁር ገበያን በማስፋፋት ወንጀል የተጠረጠሩ ግለሰቦች ፍ/ቤት ቀረቡ
| በርካታ መጠን ያላቸው የውጭ ሀገራት ገንዘቦችን በማተምና ጥቁር ገበያን በማስፋፋት ወንጀል የተጠረጠሩ ግለሰቦች ፍርድ ቤት ቀረቡ።

ተጠርጣሪዎቹ በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ተረኛ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ቀርበው ጉዳያቸው ታይቷል።

የፀሐይ ሪል ስቴት ዋና ስራ አስኪያጅ ኪያ ዦንግን ጨምሮ ዘጠኝ የውጭ ሀገራት ዜጎች እና ሶስት ኢትዮጵውያን ተጠርጣሪዎች ናቸው ፍርድ ቤት የቀረቡት።

መርማሪ ፖሊስ ግለሰቦቹ በርካታ መጠን ያላቸው የውጭ ሀገራት ገንዘቦችን በማተምና ጥቁር ገበያን በማስፋፋት ወንጀል መጠርጠራቸውን ለችሎቱ አስረድቷል፡፡

በቁጥጥር ስር በዋሉበት ወቅትም የተለያዩ የውጭ ሀገራት ገንዘቦች የሚታተሙባቸው ማተሚያ ማሽኖችና ለግብዓት የሚያገለግሉ ኬሚካሎች እንዲሁም በርካታ ዩሮ፣ የአሜሪካ ዶላርና የሌሎች ሀገራት ገንዘቦች መያዙን ፖሊስ ጠቅሷል።

ተጠርጣሪዎቹ ላይ የተጀመሩ ሰፊ የምርመራ ስራዎችን አከናውኖ እና የተናጠል ተሳትፏቸውን ለይቶ ለመቅረብም የ14 ቀን ጊዜ እንዲሰጠው ጠይቋል።

ከአራተኛ ተጠርጣሪ ውጪ ያሉ ግለሰቦች ከወንጀል ድርጊቱ ጋር ግንኙነት እንደሌላቸው ገልጸዋል።

በተጨማሪም የተጠርጣሪዎቹ ጠበቆች የግለሰቦቹ የወንጀል ተሳትፎ ባልተገለጸበት ሁኔታ ላይ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ሊሰጥ አይገባም ሲሉ ተከራክረዋል።
ፀሐይ ሪል ስቴት ዋና ስራ አስኪያጅ ኪያ ዦንግን የተባሉት ግለሰብ በበኩላቸው÷ የተገኘው የውጭ ሀገራት ገንዘብ ማተሚያ በእርሳቸው ቤትና ቢሮ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የወንጀል ድርጊቱ የሚገናኘው ከእርሳቸው ጋር ብቻ መሆኑን ገልጸው÷ ሌሎች ተጠርጣሪዎች ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት እንደሌላቸው ለችሎቹ አብራርተዋል።

መርማሪ ፖሊስ በበኩሉ÷ ተሳትፏቸው አልተገለጸም ተብሎ የተነሳውን መከራከሪያ በሚመለከት በቀጣይ ተሳትፏቸውን ለይቶ በስፋት ምርመራውን አከናውኖ እንደሚቀርብ ገልጾ መልስ ሰጥቷል።
የግራ ቀኙን ክርክር የተከታተለው ጊዜ ቀጠሮ ችሎቱ ተጠርጣሪዎች ላይ ተጨማሪ የማጣሪያ ምርመራ መደረግ እንዳለበት በማመን የተጠርጣሪዎቹን የዋስትና ጥያቄ ለጊዜው ውድቅ አድርጎታል።
ፖሊስ በቀጣይ ቀጠሮ የተጠርጣሪዎችን የወንጀል ተሳትፎ ለይቶ እንዲያቀርብ ከነሐሴ 26 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ የሚታሰብ የ12 ቀን የምርመራ ጊዜ ፈቅዷል።
በሌላ በኩል ፍርድ ቤቱ ተጠርጣሪዎቹ ከቤተሰብ ጋር እንዲገናኙ እና ሕክምና ማግኘት የሚፈልጉም ሕክምና እንዲያገኙ ትዕዛዝ ሰጥቷል ሲል ኤፍቢሲ ዘግቧል።

«ልጅ ያሬድ በሚል የሚታወቀው ያሬድ ዘላለም ላይ የማድረገውን ምርመራ አጠናክሬ እቀጥላለሁ ›› ፌደራል ፖሊስየፌደራል ፖሊስ የሕዝብ ግንኙነት ሃላፊ ጄይላን አብዲ ‹‹ በመታወቂያ ስሙ ያሬድ ዘ...
04/09/2023

«ልጅ ያሬድ በሚል የሚታወቀው ያሬድ ዘላለም ላይ የማድረገውን ምርመራ አጠናክሬ እቀጥላለሁ ›› ፌደራል ፖሊስ

የፌደራል ፖሊስ የሕዝብ ግንኙነት ሃላፊ ጄይላን አብዲ ‹‹ በመታወቂያ ስሙ ያሬድ ዘላለም በቅፅል ስሙ ደግሞ ልጅ ያሬድ በሚል የሚታወቀው ግለሰብ ላይ የማድረገውን ምርመራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ›› ለአሻም ነግረዋታል፡፡

ከሰሞኑ ‹‹ ልጅ ያሬድ ›› በሚል ቅፅል ስም የሚጠራዉ የቀድሞ ኮሜዲያን ያሬድ ዘላለም በተረጋገጥ የፌስቡክ ገፁ ‹‹ የአንድ ትልቅ የእምነት ተቋምን ክብር በሚያጎድፍ መልኩ ባስተላለፈዉ ጸያፍና ማንንም ብሄር በማይወክል መልዕክት ምክንያት የፌደራል ፖሊስ ነሐሴ 26 ቀን 2015 ዓ.ም በቁጥጥር ስር እንዳዋለው ›› የሕዝብ ግንኙነት ሃላፊው ተናግረዋል፡፡

‹‹ ግለሰቡ ተሰውሯራል፣ጠፍቷል እያሉ ያልተጣራና ትክክለኛ ያልሆነ መረጃ የሚነዙና ኅብረተሰቡ ላይ ዉዥንብር የሚነዙ ›› ያሏቸው ‹‹ አካላት ከድርጊታቸዉ እንዲቆጠቡም ›› አሳስበዋል፡፡

ጄይላን ሲቀጥሉ ‹‹ ይህን ከኢትጵያዊነት ያፈነገጠ ተግባር የፈጸመዉ ልጅ ያሬድ( ያሬድ ዘላለም) የተባለ ግለሰብ ከ3ቀናት በፊት የፌደራል ፖሊስ በቁጥጥሩ ስር አውሎት እንደሚገኝ ›› ጠቅሰው ‹‹ ህብረተሰቡ ግንዛቤ እንዲኖረው እንወዳለን ›› ሲሉ አክለዋል፡፡

‹‹ ግለሰቡ በማህበራዊ ሚዲያ ወጥቶ የአንድ ብሄር ተወካይ በሚመስል መልኩ ያስተላለፈው ግብረገብነት የጎደለው፣ የተወደደና የተከበረ የእምነት ተቋም ላይ ያስተላለፈው ጸያፍ ቃላቶች ታላቁን የኦሮሞ ህዝብም ሆነ የአማራን ህዝብ የሚወክል አይደልም ›› ሲሉም ነቅፈዋል፡፡

‹‹ ማንም ደግሞ ለዚህ ግለሰብ የሠጠዉ የእምነትም ሆነ የብሔር ውክልና የለም ›› በማለት ፌደራል ፖሊስ የጀመረውን ምርመራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቁዋል፡፡

‹‹ ሌሎችም ከእንዲህ ዓይነት ከኢትጵያዊነት ከወረደና የእምነት ተቋማትን በመሳደብ ህዝብን ለቁጣ የምታነሳሱና፣ አንድን ብሄረሰብ ከሌላዉ ለማጋጨት በተለያየ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች የምትቀሳቀሱ ከድርጊታቸዉ እንዲታቀቡ ›› አሳስበዋል፡፡
በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ‹‹ ልጅ ያሬድ የተባለውን ግለሰብ እና ተባባሪዎቹ ላይ ክስ እንዲመሠረት የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል ምርመራ ቢሮን ›› ጠይቃለች፡፡
‹‹ በግለሰቡ እና ተባባሪዎቹ ድፍረት የተሞላበት ድርጊት በርካታ ኦርቶዶክሳዊያንም ኢትዮጵያውያንም ላይ ከፍተኛ ቁጣን በመቀስቀሱን እና ከፍትህ አደባባይ ፍርድን ስለሚጠብቁ ፖሊስን ለማገዝ ይሔን አቤቱታ አቅርቤያለሁ ›› ብላለች።

ዘገባው የአሻም ቴሌቪዥን ነው!

04/09/2023

ምን ማለት ይቻላል!
አርሰናል 3 - 1 ማንችስተር ዩናይትድ

ከሞት ተነሳ ስለተባለው ልጅ ከፖሊስ የተሰጠ አጭር ማብራሪያ___________________በሁልባራግ ወረዳ ቢለዋንጃ ቀበሌ ከወትሮው በተለየ መልኩ የተሰማውን ነገር ለማጣራት እስከ ስፍራው የገ...
04/09/2023

ከሞት ተነሳ ስለተባለው ልጅ ከፖሊስ የተሰጠ አጭር ማብራሪያ
___________________
በሁልባራግ ወረዳ ቢለዋንጃ ቀበሌ ከወትሮው በተለየ መልኩ የተሰማውን ነገር ለማጣራት እስከ ስፍራው የገባን ሲሆን አሁን የሚገኝበት ቤተሰብ ከአራት አመት በፊት ባቂ ሲከማ መሀመድ የተባለ ልጃቸው እንደሞተና በትላንትናው ዕለት መንገድ ላይ ሰው አንስቶ እንዳመጣላቸው ይናገራሉ።

በሌላ በኩል በሁሉም ነገሩ ተመሳሳይ የሆነ አብዲ ሄራቶ አቦዬ የሚባል ልጅ የጠፋባቸው ቤተሰቦች ከሁልባራግ ወረዳ ወራበት ሻማ አከባቢ ልጃችን ነው ሲሉ መጥተዋል።

ልጁ የመስማትም የመናገርም ችግር ያለበት በመሆኑ ነገሩን ያንዛዛው ቢሆንም የሁለቱ ቤተሰቦች በተገኙበት አስፈላጊው ሁሉ ውይይትና ምርመራ የሚደረግ ሲሆን የማይተማመኑ ከሆነም በህጋዊ መንገድ የDNA ምርመራ እንደሚደረግ የወረዳው ፖሊስ አስታውቋል።
በመጨረሻም ፖሊስ ባስተላለፈው መልዕክት እስከዚያው ያልተጣሩ መረጃዎችን በማህበራዊ ሚዲያ መልቀቁ አስፈላጊ ስላልሆነ ከድርጊታችሁ እንድትቆጠቡ እናሳስባለን ብሏል።
ልጁን ለማየት በርካታ ሰዎች በሞተር፣ በባጃጅ ወደ ቤተሰቡ እየጎረፉ እንደነበር ለፋስት መረጃ የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

ተማሪ ጋሻው ምሳዬ ይባላል። አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ዛሬ ካስመረቃቸው ምሩቃን መካከል ነው። ይህ ምሩቅ ከወሰዳቸው 52 ኮርሶች ውስጥ 36A+  እና በ16A በማምጣት 4የዘጋ የአዲስ አበባ ዩኒ...
21/07/2023

ተማሪ ጋሻው ምሳዬ ይባላል። አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ዛሬ ካስመረቃቸው ምሩቃን መካከል ነው። ይህ ምሩቅ ከወሰዳቸው 52 ኮርሶች ውስጥ 36A+ እና በ16A በማምጣት 4የዘጋ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የዚህ ዓመት ሰቃይ ነው።

እንኳን ደስ አለህ🏆🎉

ማን ያዝናናል?
21/07/2023

ማን ያዝናናል?

" አራት ዓመት ልጄን በዊልቸር እያመላለስኩ አስተምሬ በማዕረግ አስመርቄያለሁ "  - ወይዘሮ እህተ በቀለወይዘሮ እህተ በቀለ ይባላሉ። ልጃቸው ዮርዳኖስ ወሮታው አካሏን በራሷ ማንቀሳቀስ የማያ...
21/07/2023

" አራት ዓመት ልጄን በዊልቸር እያመላለስኩ አስተምሬ በማዕረግ አስመርቄያለሁ " - ወይዘሮ እህተ በቀለ

ወይዘሮ እህተ በቀለ ይባላሉ። ልጃቸው ዮርዳኖስ ወሮታው አካሏን በራሷ ማንቀሳቀስ የማያስችል ጉዳት አለባት።

ዮርዳኖስ በእናቷ ድጋፍ ዛሬ ትምህርቷን አጠናቃ ከአዲስ አበባ ዮኒቨርሲቲ ከሳይኮሎጂ ትምህርት ክፍል በማዕረግ ተመርቃለች፡፡

እናት አህተ ፤ " አራት ዓመት ሙሉ ልጄን በዊልቸር እያመላለስኩ አስተምሬ አጠናቅቄያለሁ። አራት ዓመት ለእኔ እንደ አራት ቀን ነው። ምንም አልተሰማኝም ደስ ብሎኝ አልፏል" ብለዋል።

በአራት ዓመት የትምህርት ቆይታዋ የሚሰጣትን ትምህርት ክፍል ውስጥ አብረዋት ቁጭ ብለው እየጻፉላት እንዳስተማሯት እናት ለኢፕድ ተናግረዋል።

" ዮርዳኖስ የማንበብ ችሎታዋን እወድላታለሁ። ያነበበችውን አለመርሳቷንና አስተዋይነቷን እወድላታለሁ፤ ልጄ ትጉህ ናት " ሲሉ ገልጸዋል።

ዮርዳኖስ እስከ 12ኛ ክፍል በሞግዚት ድጋፍ የተማረች መሆኑን ጠቅሰው እንደምትችል መታየት አለበት ብዬ አራት ዓመት በዩኒቨርሲቲ አብሬያት ዘልቀናል ብለዋል፡፡

አትችልም የተባለች ልጅ ለዚህ በመብቃቷ ትልቅ ደስታ እንደተሰማቸው ጠቅሰው፤ የእርስዋ ብርታት እንደ ልጃቸው ቤት ለተዘጋባቸው ልጆች አርአያ የሚሆን መሆኑንም ገልፀዋል፡፡

መኖሪያ ቤታቸው ከዮኒቨርሲቲው ራቅ ያለ በመሆኑ ጠዋት 12 ሰዓት ተነስተው ለአራት ዓመታት ልጃቸውን ወደ ትምህር ገበታዋ በዊልቸር በማመላለስ ለምረቃ ያበቁት እናት ዛሬ ደስታቸው እጥፍ ድርብ ሆኖ ታይተዋል።

Credit : EPA

በጅማ ዩኒቨርሲቲ የተመረቁት ሦስት መንትዮችየጅማ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ ዘርፎች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ዛሬ አስመርቋል፡፡ከተመራቂዎቹ መካከል በጅማ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ትምህርታቸውን ሲከታተሉ...
20/07/2023

በጅማ ዩኒቨርሲቲ የተመረቁት ሦስት መንትዮች
የጅማ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ ዘርፎች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ዛሬ አስመርቋል፡፡
ከተመራቂዎቹ መካከል በጅማ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የነበሩ ሦስት የተለያዩ መንትዮች ይገኙበታል፡፡
ሜላት ደቻሳ በኤሌክትሪካል ኢንጂነሪንግ እና ሜሮን ደቻሳ በሥነ ህንጻ (አርክቴክቸር) የተመረቁ መንትዮች ናቸው፡፡
በተጨማሪም ኢዩኤል ብዙአየሁ እና ኢዩአኪ ብዙአየሁ በኮምፒውተር ሳይንስ የተመረቁ ሌሎቹ መንትዮች መሆናቸውን የኢንስቲትዩቱ መረጃ ያመላክታል፡፡
እንዲሁም ሌሎቹ መንትዮች ደግሞ አሊይ በዳሶና አማን በዳሶ ሲሆኑ÷ በሲቪል ምህንድስና ትምህርታቸውን አጠናቀው ተመርቀዋል፡፡

Address

Jamo
Addis Ababa
45

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when All In One Ethiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to All In One Ethiopia:

Videos

Share